[[ተምሳሌቶችሺን ሰለፎችሺን አስታዉሺ]]
6.64K subscribers
1.21K photos
661 videos
99 files
3.87K links
وَأَعْظَمُ مَا أَمَرَ اللَّهُ بِهِ التَّوْحِيدُ، وَهُوَ : إِفْرَادُ اللَّهِ بِالْعِبَادَةِ. وَأَعْظَمُ مَا نَهَى عَنْهُ الشِّركُ، وَهُوَ: دَعْوَةُ غَيْرِهِ مَعَهُ،
https://t.me/LetusfearAllah ጆይን በሉ
Download Telegram
«የፈለጉት ለማዘዝ ከታች ያለዉን  አድራሻ ይጠቀሙ!»


   «telegram»፦@Hayat_bint_Seid_Aselefly

«whatsapp» ለማናገር፦+966554605973

አድራሻ፦ ሳዑድ አረቢያ  ፣ጅዳ፣ መካ ፣ሪያድ፣ መዲና ፣ጣኢፍ፣ ፣ደማም......! እንልካለን !



« ጠቃሚ ነገሮችን ለማገኘት ይቀላቀሉ፦»
   t.me/Online_Eslamawiy_Market
~አንዳንዴ... ከዚህ ከማህበራዊ ሚዲያ ሁካታ ጥቅልል ብለህ መጥፋት፣ አካውንትህን አጥፍተህ ለነፍስህ ሰላም መስጠት እጅግ ያሰኝሃል። ዘመኑ መልካምነት የከበደበት፣ ጥሩነት እንደ ሞኝነት የሚቆጠርበት ወቅት ሆኗልና መሸሽ ይቀላል።

ግን ደግሞ ቆም ብዬ አስባለሁ። ምናልባት በዚህ አስቸጋሪ መድረክ ላይ የምናጋራው መልካም ነገር፣ ለአንድ ሰው የሂዳያ መንገድ ቢሆነውስ? ምናልባት የምንፅፋት ፊደል አላህ ዘንድ በግዙፍ ሚዛን ተመዝና ለጀነት መግቢያችን ሰበብ ብትሆነውስ? እሾሁን ታግሰን የምንቆየው ለዚህ ነው። አላህ በትንሹ ሰበብ ትልቁን ደረጃ ይስጠን።ፅናቱንም ኢኽላሱንም ይወፍቀን!
✈️ t.me/AbuSufiyan_Albenan
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
🎁አልሐምዱሊላህ! የተጠየቀው የህክምና ወጪ ሞልቷል!

ውድ ወንድሞች እና እህቶች፣ ለወንድማችን ህክምና ጠይቀን የነበረው መሰረታዊ የገንዘብ መጠን በአላህ ፈቃድ ከዚያም በእናንተ ርብርብ 1,000,000 ብር ተሟልቷል። ቃል በገባነው መሰረት  ይህንን የምስራች ስናበስራችሁ ደስታችን ላቅ ያለ ነው።

💰ነገር ግን አንድ መረሳት የሌለበት ጉዳይ አለ፤ የተሰበሰበው ሂሳብ ቀጥታ ለህክምናው ክፍያ የሚውል ሲሆን፣ ወንድማችን ከህክምናው በኋላ የአልጋ ላይ ክትትል ሲያደርግ ለሚያስፈልጉት ተያያዥ ወጪዎች እንዲሁም ከትንሽ ወራቶች በፊት ህክምናውን ለመጀመር ሲባል ከሰዎች የተበደረው እዳ ስላለበት፤ እዳውን ከፍሎና አገግሞ ወደ ስራው በሰላም እስኪመለስ ቃል ገብታችሁ ገና ያላስገባችሁ ወንድምና እህቶች፣ የወንድማችንን ጭንቀት ሙሉ በሙሉ በማቃለል አጅራችሁን እንድትሞሉ የጀመራችሁትን ኒያ እንድታስገቡ በትህትና እንጠይቃለን።
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
7,000 እናስገባት የኡስታዛችን ቻናል

        ሼር 👇👇👇
https://t.me/durusuabihizam
https://t.me/durusuabihizam
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ከላይ ለሚያየን በኢስላማዊ ነፀብራቆች ያሸበረቀ፣ በሱና የደመቀ፣ ለዲን ለሱና ዘብ የሆነ፣ ... የምንመስል ውስጣችን ግን በክፋት፣ በምቀኝነት፣ በማስመሰል የተበከለ ስንትና ስንት ሰዎች አለን! ውስጥ አዋቂው ጌታ ሁለ ነገራችንን ያውቃል። ስለሆነም ልባችንን በማከም ላይ በቂ ትኩረት እንስጥ። ውጫዊ ቆሻሻዎችን ለማስወገድ ከምንጠነቀቀው በላይ ልባችን ውስጥ የሚገኙ የስነ ምግባር ቆሻሻዎችን ለማፅዳት እንጣር። በዐቂዳ፣ በመንሀጅ ሰለፎችን ለመከተል እንደምንጥረው ሁሉ በስነ ምግባር እነሱን ለመከተል እንጣር።

=
የቴሌግራም ቻናል፦
https://t.me/IbnuMunewor
https://t.me/IbnuMunewor
~ ነፍስህን ተረጋጊ በላት! እረፍት ስጪኝ እስኪ ሰከን በይ በላት! ተቅበዘበዘች ተልከፈከፈች ለሀጯን አዝረከረከች!  እውነት ነው! ያዙኝ ልቀቁኝ ብላ ተኮፈሰች። የያሁትን ሁሉ ካልነከስኩ ብላ እንደ እብድ ውሻ አለከለከች። እናም ረጋ በይ በላት!

منقول
=
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ቁርኣንን ከዐረብኛ ቋንቋ ውጭ መፃፉ…

~በአሁኑ ሰዓት በማህበራዊ ሚዲያዎች ላይ እየተስፋፋ የመጣ እጅግ አደገኛ አካሄድ አለ። ይኸውም የአላህን ንግግር ቁርኣን የዐረብኛውን ድምፅ በአማርኛ ፊደላት ቀይሮ መፃፍ ነው (ምሳሌ፡ «ቁል ሁወላሁ...፣ «ኢዛ ጃኣ...»እያሉ መፃፍ)። ይህ ተግባር ሐራም የሆነ ተግባር ነው። ብዙ ዑለማዎችም አጥብቀው ይከለክላሉ።

📖ይህንን ድርጊት የሚፈጽሙ ሰዎች ኒያችን ጥሩ ነው፣ ሰውን ለማስተማር ነው ቢሉም፤ መልካም ኒያ መጥፎን ስራ ወደ ጥሩ አይቀይርም። ቁርኣን የተለየ ክብርና ጠባቂ ያለው መለኮታዊ ቃል እንጂ እንደ ግጥም በፈለግነው ፊደል የምንከትበው አይደለም።

ጌታችን አላህ ቁርኣንን በዐረብኛ ቋንቋ ብቻ እና በዛው የቃላት አወቃቀር እንደመረጠው በግልፅ ተናግሯል። ቋንቋውንም ሆነ ፊደሉን መቀየር የአላህን ምርጫ መቃወም ነው።

📚  إِنَّا أَنزَلْنَاهُ قُرْآنًا عَرَبِيًّا لَّعَلَّكُمْ تَعْقِلُونَ
እኛ (ፍቹን) ታውቁ ዘንድ ዐረብኛ ቁርኣን ሲሆን በእርግጥ አወረድነው፡፡»

አላህ «ዐረብኛ አድርገን አወረድነው»እያለ፤ አንተ በአማርኛ ፊደል ቀይረህ ስትፅፈው፣ አላህ ያጸደቀውን ማንነት እየቀየርክ ነው።

📚በሌላ ቁርኣን አንቀፅም፦
{وَلَوْ جَعَلْنَاهُ قُرْآنًا أَعْجَمِيًّا لَّقَالُوا لَوْلَا فُصِّلَتْ آيَاتُهُ ۖ أَعَأْجَمِيٌّ وَعَرَبِيٌّ}
«(ቁርኣኑን) በውጭ ቋንቋ (የተነበበ) ባደረግነው ኖሮ አንቀጾቹ (በዐረብኛ) ለምን አልተብራሩም ነበር? (መልክተኛው) ዐረብ (መጽሐፉ) ዐጀም (የውጭ ቋንቋ) ይሆን ነበርን? ይሉ ነበር።»

ቁርኣን በሌላ ቋንቋ ንባብ (ፊደል) ቢወርድ ኖሮ ሰዎች በተቃወሙ ነበር። ዛሬ ላይ የአላህን ቃል በአማርኛ ፊደል መፃፍ ማለት የቁርኣኑን "ሙዕጂዛ" ማጥፋት ነው።

🔹ሌላው እና አደገኛው ነጥብ ትርጉምን ማበላሸት ይከሰታል።ይህ ነጥብ በጣም አሳሳቢው ነው። የዐረብኛ ፊደላት ባህሪያት (መኻሪጅ) በአማርኛ ፊደላት ፈጽሞ ሊወከሉ አይችሉም። በአማርኛ ስትፅፉት የቁርኣኑ መልእክት ከምስጋና ወደ ስድብ፣ ከኢማን ወደ ኩፍር ሊቀየር ይችላል።

💡ታላቁ ኢማም ማሊክ ስለ ቁርኣን አጻጻፍ ተጠይቀው እንዲህ አሉ፦
"لا، إلا على الكتبة الأولى"
«አይቻልም! (በሰሀቦች ዘመን) በነበረው የመጀመሪያው አጻጻፍ ቢሆን እንጂ።» ብለው መልስ ሰጥተዋል። በራሱ በዐረብኛ ቋንቋ ውስጥ እንኳን ዘመናዊ የአጻጻፍ ስልት መጠቀም ከተከለከለ ማለትም ከ "ዑስማኒ" አጻጻፍ ውጭ ሐራም ነው ከተባለ በአማርኛ ሲሆንስ እንደት ይሁን!?

አላህ እውቀትንና ትክክለኛውን መረዳት ይስጠን!
t.me/AbuSufiyan_Albenan
t.me/AbuSufiyan_Albenan
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
ከልማድ የወጣ ነገር
አጫጭር ምክሮች
ከልምድ የወጣ አለባበስን መራቅ

🎙 ኡስታዝ ኢብኑ ሙነወር
Forwarded from Abu_Oubeida~channel
ማነህ ወንድሜ ይሄን ኪታብ ባለፈው 10 ፍሬ እፈልጋለሁ ያልከኝ ስልክህ ጠፍቶኝ ነው ደውልልኝ።
እናንተ ደግሞ ሽር በማድረግ እንዲደርሰው እንተባበር ባረከሏሁ ፊኩም

የቴሌግራም አድራሻ፦
@Oubeida22