[[ተምሳሌቶችሺን ሰለፎችሺን አስታዉሺ]]
6.64K subscribers
1.21K photos
661 videos
99 files
3.87K links
وَأَعْظَمُ مَا أَمَرَ اللَّهُ بِهِ التَّوْحِيدُ، وَهُوَ : إِفْرَادُ اللَّهِ بِالْعِبَادَةِ. وَأَعْظَمُ مَا نَهَى عَنْهُ الشِّركُ، وَهُوَ: دَعْوَةُ غَيْرِهِ مَعَهُ،
https://t.me/LetusfearAllah ጆይን በሉ
Download Telegram
📝 ማህበረሰብህን አንቃ አትዘናጋ


◾️ሸይኽ ኢብኑ ኡሰይሚን "አላህ ይዘንላቸውና" እንዲህ ብለዋል።

ሰዎች ከዙልሒጃ አስር ቀናቶች በመዘናጋት ላይ ናቸው። እውቀት ፈላጊ ተማሪዎች ስለነዚህ ቀናት ትሩፋት ለማህበረሰቡ ግልፅ ሊያደርጉ ይገባል። ሰፊው ማህበረሰብ መልካም ነገርን ይወዳል። ነገር ግን ጣሊበል ኢልሞች እነርሱን በዚህ ላይ ከማንቃት ሲዘናጉ ይስተዋላል።http://t.me/Sadik_Ibnu_Heyru

📚{مجموع فتاوى ورسائل الشيخ ابن عثيمين (٢٥/١٨٩)}
👍1
" ምን ያክል ለቁርአን ትኩረት ሰተናል ወንድም እህቶች እጅግ በርካቶች ማሻ አላህ እኪታብ ላይ በመማርም ይሁን በማስተማር ተሳትፈናል ነገር ግን ሃቂቃው አላህ ካዘነላቸው ሰወች በስተቀር ቁርአን አንስተው አይቀሩም ለምን !
" ቁርአንኮ ከንግግሮች ሁሉ እውነተኛ የአላህ ንግግር ነው የላቀው ጌታችን እንድህ ይላል፣↙️


اللَّهُ نَزَّلَ أَحْسَنَ الْحَدِيثِ كِتَابًا مُّتَشَابِهًا مَّثَانِيَ تَقْشَعِرُّ مِنْهُ جُلُودُ الَّذِينَ يَخْشَوْنَ رَبَّهُمْ ثُمَّ تَلِينُ جُلُودُهُمْ وَقُلُوبُهُمْ إِلَىٰ ذِكْرِ اللَّهِ ۚ ذَٰلِكَ هُدَى اللَّهِ يَهْدِي بِهِ مَن يَشَاءُ ۚ وَمَن يُضْلِلِ اللَّهُ فَمَا لَهُ مِنْ هَادٍ

አላህ ከዜና ሁሉ መልካምን፣ ተመሳሳይ፣ ተደጋጋሚ የኾነን መጽሐፍ አወረደ፡፡ ከእርሱ (ግሣጼ) የእነዚያ ጌታቸውን የሚፈሩት ሰዎች ቆዳዎች ይኮማተራሉ፡፡ ከዚያም ቆዳዎቻቸውና ልቦቻቸው ወደ አላህ (ተስፋ) ማስታወስ ይለዝባሉ፡፡ ይህ የአላህ መምሪያ ነው፡፡ በእርሱ የሚሻውን ሰው ይመራበታል፡፡ አላህም የሚያጠመው ሰው ለእርሱ ምንም አቅኚ የለውም፡፡
"""""""""""""""""""""""""""""""""""""""""""""""""
ስለዝህ ቁርአንን እናብበው እንማረው በአግባቡ ተጅዊዱን ጠብቀን።
አደራ አደራ ቁርአንን አንራቅ ወላሂ ሳትቀራ ውለህ ልብህ እማይረበሽ ከሆንክ እራስህን ፈትሽ ።

( አቡ ዓኢሻ አወል ካሳው)

⤵️⤵️⤵️⤵️
https://t.me/Abuebrahim22322
https://t.me/Abuebrahim22322
👍2
ሸርሑ ሱና፡ ክፍል -1
Ibnu Munewor (ኢብኑ ሙነወር)
♦️አድስ ተከታታይ የኪታብ ቁረአት
➱➱➱➱➱➱➱➱➱➱➱➱➱➱

ሸርሑ ሱና ሊልበርበሃሪ

▪️ክፍል አንድ

♦️ሶፍት ኮፒውን በዚህ ማግኘት ይቻላል። (መትኑ የሚጀምረው ከገፅ 35 ነው።)
➘➘➘➘➘➘➘➘➘➘➘➘➘➘
https://t.me/IbnuMunewor

🎙በኡስታዝ ኢብኑ ሙነወር حفظه الله
https://t.me/LetusfearAllah
👍2
Forwarded from Abdusomed MuhammedNur (Abdusomed MNur Al-Jeberty)
ሳዑዲ ጨረቃ ታይታለች።
ነገ ዙል ሒጃ 1 ነው።
👍6
⭕️👉እነዚህን ውድ አስር ቀናቶች በሰላም ላደረሰን አላህ የላቀ ምስጋና ይገባው።


♦️الحمد لله ثم الحمد لله!!

📝 እድለቢስ ማለት ይህንን ትልቅ አጋጣሚ በከንቱ የሚያሳልፍ ሰው ነው።

እነዚህ የዙልሂዳ አስርቱ ውድ ቀናቶች ምናልባትም የእድሜያችን የመጨረሻ ሊሆኑ ይችላልና በኢባዳ ልንጠቀምባቸው ይገባል። እነዚህ ቀናቶች እስከ የውመል ቂያማ ድረስ በየአመቱ ይመላለሳሉ። አንተ ግን በህይወት ላታገኛቸው ትችላለህ። ምክንያቱም አጀልህ መች እንደሆነ አታውቅምና። ይህንን ትልቅ እድል ተጠቅመን ትንሽ ሰርተን ብዙ ልናተርፍ ይገባል።

በነዚህ አስር ቀናቶች ሸይጧንና ነፍሳችን መርታት ይጠበቅብናል። ትርፍ ሀጃዎቻችን በመቀነስ በመልካም ስራ ልንወጠር ይገባል። እነዚህ ቀናቶች ከዚህ በፊት ከነበሩ ቀናቶች በበለጠ መልኩ በኢባዳ ለየት ልናደርግባቸው ይገባል።


💦ተውበት በማድረግ
💦ፃም በመፃም
💦ተክቢራ በማለት
💦ከወንጀል በመራቅ
💦ቁርአንን በመቅራት
💦ሰደቃ በመስጠት
💦ሌሊት በመቆም
💦ዚክር በማብዛት
💦ዱአ በማብዛት
💦ኢልም በመፈለግ
💦ዳእዋ በማድረግ
💦ሱና ሶላቶች በማብዛት
💦ፈርድ ሶላት በጊዜው በመስገድ
💦ለእናት አባታችን መልካም በመዋልና

♦️ሌሎችም መልካም ስራዎች ላይ እንበርታ።

◾️አላህ ሆይ፦ እኔንም አጠቃላይ ሙስሊም ወንድም እህቶቼን በነዚህ ቀናት ከሚጠቀሙት አድርገን። በዚህም ላይ አግዘን። በውስጣቸው ያለውን መልካም ነገር ወፍቀን።
http://t.me/Sadik_Ibnu_Heyru
👍1
ከሰለፎች የተገኙ የተክቢራ አይነቶች


⭕️👉 በነዚህ ውድ ቀናቶች ውስጥ ከሚፈፀሙ ታላላቅ ኢባዳዎች ውስጥ አንዱ ተክቢራ ነው። አላህ በቁርአኑ መልእክተኛው በሀዲሳቸው ተክቢራ በማለት ላይ ከመጠቆምና ከማመላከት ውጪ ይህን ተክቢራ ይበል በሚል የመጣ የተክቢራ አይነት የለም። ስለዚህ አንድ ሰው በየትኛውም አላህ ማላቂያ ተክቢራ ማድረግ ይችላል። ነገር ግን ከቀደምት የዲን ሊቃውንቶች ከሰለፎቻችን የተገኙ የተክቢራ አይነቶች አሉ። እነሱን መጠቀም ግን የተሻለ ይሆናል። ከነዚህ ተክቢራዎች መካከል፦

①) አንደኛ
«الله أكبر، الله أكبر، لاإله إلا الله، والله أكبر، الله أكبر ، ولله الحمد»
♦️ኡመር፣ አልይ፣ ኢብኑ መስኡድ፣ አቡሀኒፋ፣ ሰውርይ፣ ኢስሀቅ፣ ኢብኑ ተይምያ፣ ኢብኑ ረጀብ ሸኽ አልባንይና ኢብኑ ኡሰይሚን ይህንን መርጠዋል።
*ـ•┈┈┈┈•✿❁✿•┈┈┈┈•ـ​*

②) ሁለተኛ
«الله أكبر كبيرًا، الله أكبر كبيرًا، الله أكبر وأجل، الله أكبر ولله الحمد»

♦️ከኢብኑ አባስ ተወርቷል። ኢብኑ አቢሸይባ መርጦታል። አልባንይ ሶሂህ ነው ብለውታል
*ـ•┈┈┈┈•✿❁✿•┈┈┈┈•ـ​*

③) ሶሰተኛ
«الله أكبر كبيرًا، والحمد لله كثيرًا، وسبحان الله بكرة وأصيلا»

♦️ኢማሙ ሻፍእይና ኢማሙ ነወውይ መርጠውታል።
*ـ•┈┈┈┈•✿❁✿•┈┈┈┈•ـ​*

④) አራተኛ
«الله أكبر، الله أكبر، الله أكبر، لا إله إلا الله، والله أكبر، ولله الحمد»

♦️ከኢብኑ አባስ ተወርቷል።
*ـ•┈┈┈┈•✿❁✿•┈┈┈┈•ـ​*

⑤) አምስተኛ
«لا إله إلا الله، والله أكبر، الله أكبر، ولله الحمد".»

♦️ኡመርና ኢብኑ መስኡድ ብለውታል።
*ـ•┈┈┈┈•✿❁✿•┈┈┈┈•ـ​*

⑥) ስድስተኛ
«الله أكبر، الله أكبر، الله أكبر»

♦️ከኢብኑ አባስ፣ ከኢማሙ ማሊክና ሻፍእይ ተወስቷል።
*ـ•┈┈┈┈•✿❁✿•┈┈┈┈•ـ​*

⑦) ሰባተኛ
«الله أكبر، الله أكبر، الله أكبر كبيرًا ".*»

♦️ከሱፍያን ተወርቷል። ኢብኑ ሀጀር መርጦታል።
*ـ•┈┈┈┈•✿❁✿•┈┈┈┈•ـ​*

⑧) ስምንተኛ
«الله أكبر، الله أكبر، الله أكبر، ولله الحمد، الله أكبر وأجل، الله أكبر على ما هدانا»

♦️ከኢብኑ አባስ ተወርቷል። አልባንይ ሶሂህ ነው ብለውታል።
*ـ•┈┈┈┈•✿❁✿•┈┈┈┈•ـ​*

➡️ በተገኘ አጋጣሚ እየቀያየርን በሆነ ጊዜ አንዱ በሌላ ጊዜ ሌላውን መጠቀም እንችላለን።http://t.me/Sadik_Ibnu_Heyru
👍1
በነዚህ በዙልሒጃ 10 ወርቃማ ቀናቶች ውስጥ ቁርኣንን ለማኽተም የተዘጋጀ ፕሮግራም


①) የመጀመርያው ቀን
◾️ከሱረቱል ፋቲሀ እስከ ሱረት ኣሉ ኢምራን መጨረሻ

②) በሁለተኛው ቀን
◾️ከሱረቱ አንኒሳእ እስከ ሱረቱል አንአም መጨረሻ

③) በሶስተኛው ቀን
◾️ከሱረቱል አእራፍ እስከ ሱረቱ አትተውባ መጨረሻ

④) በአራተኛው ቀን
◾️ከሱረት ዩኑስ እስከ ሱረት አረእድ መጨረሻ

⑤) በአምስተኛው ቀን
◾️ከሱረቱል ኢብራሂም እስከ ሱረቱል ካህፍ መጨረሻ

⑥) በስድስተኛው ቀን
◾️ከሱረቱል መርየም እስከ ሱረቱል ሙእሚን መጨረሻ

⑦) በሰባተኛው ቀን
◾️ከሱረት አሹአራዕ እስከ ሱረቱል አህዛብ መጨረሻ

⑧) በስምንተኛው ቀን
◾️ከሱረት አስሰበእ እስከ ሱረት ፋሲለት መጨረሻ

⑨) በዘጠነኛው ቀን
◾️ከሱረት አሽሹራ እስከ ሱረቱል ሀዲድ መጨረሻ

①∅ በአስረኛው ቀን
◾️ከሱረቱል ሙጃደላህ እስከ ሱረት አንናስ

➡️ እንደሚታወቀው ሰለፎቻችን ለቁርአን የነበራቸው ትኩረት በጣም የተለየ ነበር። ከነሱ መካከል በአንድ ሌሊት ቁርአንን ሙሉ ለሙሉ የሚያኸትም ነበር። በየሶስት ቀን፣ በየአምስት በየሰባትና በየአስር ቀን ሁሌም የሚያኸትሙ እጅግ ብዙዎች ነበሩ።

➡️ አላህ ለወፈቀው ሰው በነዚህ አስር ውድ ቀናቶች ውስጥ ሶስቴ ማኽተም ይችላል። ሌላው ቢያቅተን አንዴ ለማኽተም ጥረት ልናደርግ ይገባል።


➡️ ለእያንዳንዱ ቀን አንድ አንድ ሰአት ለቁርአን ብቻ ብንሰጥ በቀላሉ ሙሉውን ማኽተም እንችላለን። አላህ ያግራልን።http://t.me/Sadik_Ibnu_Heyru
ሸርሕ_አቂደቱል_ዋሲጥያ_በኡስታዝ_አቡ_አብደላህ_ኢብን_ኸይሩ_ያለኔት.apk
211.7 MB
◾️ሸርሕ አቂደቱል ዋሲጥያ ሙሉ ቂርአት ያለኔት


🎙በአቡ አብዲላህ ኢብኑ ኸይሩ

➡️ አንዴ ካወረዱት በኋላ ያለኔት በፈለጉት ጊዜና ቦታ እንደፈለጉ መጠቀም ይችላሉ‼️
📚📚📚📚📚📚📚📚📚📚📚📚

◼️በአፕልኬሽን መልክ የቀረበ


♦️ሼር በማድረግ የኸይር ሰበብ ሁኑ!
http://t.me/Sadik_Ibnu_Heyru
http://t.me/Sadik_Ibnu_Heyru
👍2