የሥላሴ ባርያ የልዑል ት/ት ቤት
52 subscribers
11 photos
91 links
ሥላሴ ትትረመም ወትትነከር
Download Telegram
ከምን ዓይነት ነገር መላቀቅ እንዳለብህ ታዉቃለህ ??

ብጹዕ ወቅዱስ አቡነ ሺኖዳ ሳልሳዊ ምድራዊ ምኞት ምን ያህል አስከፊ እንደሆነና እንዴት ከዚህ ነገር ነፃ መውጣት እንዳለብን እንዲህ በማለት ይመክሩናል፦

"ወዳጄ ከምድራዊ ምኞትህ ተላቀቅ ከምን አይነት ነገር መራቅ እንዳለብህ ታውቃለህ? ከምድራዊ ፍላጎት ከመሳሰሉት ራቅ ፍፁም የመንፈስ ነፃነት እንዲኖርህ ከፈለክ ከምድራዊ ምኞቶችህ ተላቀቅ።

በእርጋታና በግልጽነት ላውጋህ እጅግ አብዝተህ የምትጨነቅባቸው ልብህን የተቆጣጠሩት ታላላቅ ምድራዊ ተስፋዎች አሉህ።

እነኚህም ሃሳብህን ሁሉ ይቆጣጠሩታል ብቻህን በምቶንበት ጊዜ በምናብ ይመጡብሃል በምትተኛ ጊዜ ህልምህ ሁሉ ይህ ይሆናል ልትክዳቸው የማትችለው ነገር ግን የምታውቃቸው ምድራዊ አላማዎች አሉህ። ተፈላጊነት እንዲኖርህ ትመኛለህ፣ ስልጣን እንዲኖርህና፣ ኃያል እንድትሆን፣ ዕውቅና እንዲኖርህና ስምህ ከጽንፍ እስከ አጽናፍ እንዲናኝ ትፈልጋለህ።

በሀብት፣ በምድራዊ ስልጣን፣ በዕውቀት በማዕረግና በመልክ ዝነኛ የመሆን ተስፋ አለህ ፣ በመኖሪያ ቤት፣ በምግብ፣ በልብስና በሰውነት ደስታን በሚሰጡ ነገሮችም ተስፋ አለህ።

ዓለም በአንተ እንጂ አንተ በዓለም እየኖርክ አይደለም። ስለዚህ አንተነትህ በዚህ ምድራዊ ተስፋ የታጠረ ነው። መንፈስህም ከስጋ ፍላጎቶች መራቅን ትመኛለች ሥጋ በመንፈስ ላይ መንፈስ በሥጋ ላይ ይመኛልና። (ገላ.5፥17) እነዚህ ሥጋዊ ተስፋዎችና ፍላጎቶች ስኬታማ ስለማይሆኑ ግራ ትጋባለህ።

ይህን በእርግጥ ቅሬታን ያመጣብሃል።
እነዚህን ነገሮች ሁሉ ትናፍቃለህ ነገር ግን ናፍቆትህ አያስደስትህም። ስለዚህ ለምኞትህ ሁሉ ማስተካከያ ታበጅለት ይሆናል ምናልባትም ይጠቅሙኛል የምትላቸውን ሰዎች ማግኘት፣ በምኞትህ ዙሪያ የተጻፈ መዛግብት ማገላበጥ ትፈልግ ይሆናል በዚህም ላይ ታች ስትል ምኞትህን ለማሳካት ትታገላለህ እንዲሆን ሌላ ዘዴ ልትፈጥር ትችላለህ ይሁን እንጂ ሳይሳካልህ ቀርቶ በሃሳብና በጥረት ትታክታለህ ከዚያም ትበሳጫለህ። ከዚህ የከፋው ነገር በእነዚህ ምኞቶችና ተስፋዎች ስኬታማ አለመሆን ምክንያት ለከፋ ሕይወት መዳረግህ ነው።

እንደምትሰለች አውቃለሁ አዘንኩልህ እስከመቼ ድርስ በምኞት ማዕበል ውስጥ ትኖራለህ? የምትመኘውን ባገኘህ ጊዜ ደስተኛ ትሆናለህ ይህ ደስታ ስለማያረካህ ሌላ አዲስ ደስታን እንድትመኝ ያደርግሃል። ልክ ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ "ከዚህ ውሃ የሚጠጣ ሁሉ እንደገና ይጠማል" (ዮሐ.4፥13 ) እንዳለው እርካታ አይኖርህም።

ስለዚህ ውድ ወንድሜ ነገሩን በእርጋታ ከአንተ ጋር ለመነጋገር እፈልጋለሁ። "አለሙም ምኞቱም ያልፋል" (1ኛ ዮሐ.2፥17) ታዲያ ይህን ቃል ካወክ ለምን አለማዊ ፍላጎቶችን ለማግኘት ትታክታለህ? አንተ ልክ እንደ እኔ ለመሬት እንግዳ ነህ። ዓለም የሚያልፍበት አንተም የምትጠፋበት ጊዜ ይመጣል ልክ ከእናትህ ማህጸን ራቁትህን እንደመጣህ እንደዚሁ ራቁትህን ትመለሳለህ።(ኢዮ. 1፥21)

ዓለምን ከነክብሯ ከነሀብቷና ከነስሟ ለቀሃት እንድትሄድ በመገደድ እንደ ማንኛውም ሰው ወደ መሬት ትወርዳለህ። ከዚያም ከዓለም ያገኘኽውን ደስታ ታወቂነት ወይም ምንም ይሁን ምን ሥጋህን ከሞት ሊከላከልልህ አልያም ሥጋን ከሚበሉት ትል ሊከላከልልህ አይችልም። በፍርድ ቀን ከዓለም ሀብትና ንብረት ውጭ በእግዚአብሔር ፊት ትቆማለህ። መልካም ይሁን ክፉ የሰራኸው ሥራ እንጂ የዓለም ቁሳዊ ነገር አይከተልህም።

ስለዚህ ውድ ወንድሜ ምኞትህንና ተስፋህን በዓለም ላይ በማድረግ መታወክህ ለአንተ ጥሩ አይደለም ይህችን ምድር እሾህንና አሜኬላን እንዳበቀለችልህ ትዘነጋለህን!!! ከእኛ በፊት የነበሩና ምድርን ሊረግጧት የማይገባት የቅዳሳን አባቶችና እናቶች አሠራርና ፈለግ ተከተል ቅድስናቸውን ያገኙት ይህችን ዓለም በመውደድ ሳይሆን በመናቅ ነበር ሁኔታዎች ሁሉ ተመቻችተውላቸው ሳለ በዓለም ስላሉ ነገሮች ለማንኛውም ጉጉት አልነበራቸውም ።

ውድ ወንድሜ አሁንም ምኞት አሉህ መዝገብህ ባለበት ልብህ ደግሞ በዚያ ይሆናልና (ማቴ.6፥21) የሥጋን ምኞቶችን ስለተቆራኘ መንፈሳዊ ነገሮች በአንተ አመለካከት ዋጋቸውን ያጣሉ ይህ የክብር ጌታ እንደተፈተነው ዓይነት ፈተና ነው። (ማቴ.4፥8-9)

አሁን አስተውል እነዚህን ነገሮችን ብትይዝ በጥሩ ምኞት ያላሰርካት ነፍስህን ብታጣ ጥቅሙ ምንድን ነው? ነፍስህ ነጻነትን ትሻለች።

ከስጋ ምኞት ተላቀን የመንፈስ ፍሬ የሆኑትን " የመንፈስ ፍሬ ግን ፍቅር፣ ደስታ፣ ሰላም፣ ትዕግሥት፣ ቸርነት፣ በጎነት፣ እምነት፣ የውሃት፣ ራስን መግዛት ነው።"(ገላ.5፥22) እንዳለው ብርሃነ ዓለም ቅዱስ ጳውሎስ እነዚህን ገንዘብ አድርገን እንድንኖር እግዚአብሔር አምላክ ይርዳን!!

(የብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ሺኖዳ ሳልሳዊ "የመንፈስ ነጻነት "ከሚለውና በዲ/ን ደስታ ፍፁም ከተተረጎመው መጽሐፍ ላይ የተወሰደ)
ወርኃ ጽጌ - 🌼🌼
(ከመስከረም 26 እስከ ኅዳር 6)

በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ስርአት መሰረት ከመስከረም 26 ቀን እስከ ሕዳር 6 ቀን ያለው 40 ቀን የእመቤታችን ና የልጇን ስደት በማሰብ ወርኃ ጽጌን (ዘመነ ጽጌን) ታከብራለች፡፡ ይህ 40 ቀን የእመቤታችንና የጌታ ስደት የሚታሰብበት ዘመን ነው፡፡ ወቅቱ የአበባና የፍሬ ወቅት በመሆኑ እመቤታችን በአበባ ጌታን በፍሬ እየተመሰሉ ጌታችን በአምልኮት እመቤታችን በፈጣሪ እናትነቷ በተለየ ምስጋና ይመሰገናሉ ፡፡

በዚህ በወርኃ ጽጌ (በዘመነ ጽጌ) የሚጾሙ ክርስቲያኖች ሲኖሩ ጾሙን መንፈሳውያን ሰዎች ሳይታዘዙ በራሳቸው ፈቃድ የሚጾሙት ጾም በመሆኑ (የፈቃድ) የትሩፋት ጾም ይባላል፡፡ በቀኖና ቤተክርስቲያን ከታዘዙት ከ7ቱ አጽዋማት ውጪ የሆነ ትርፍ ጾም ማለት ነው፡፡ ከታዘዘው አትርፎ የጾመ ሰው የመጾሙን ዋጋ ያገኛል፡፡ ብዙ መንፈሳዊ ሥራ የሰራ ሰው ብዙ ክብር እንደሚያገኝ መጽሐፍ ይናገራልና፡፡ ‘’እጅግ ወዳለችና ብዙ ያለው ሐጢአትዋ ተሰርዮላታል፡፡ ጥቂት ግን የሚሰረይለት ጥቂት ይወዳል’’ (ሉቃ. 7፡47) እንዲል፡፡

የጽጌን ጾም የሚጾሙ ሰዎች በክብርም ከእመቤታችን ጋር ይተባበራሉ፡፡ ነገር ግን የጽጌን ጾም የሚጾሙ ሰዎች ለመመጻደቅ መጾም የለባቸውም፡፡ የማይጾሙ ሰዎችንም መንቀፍና መክሰስ የለባቸውም፡፡ የጽጌ ጾም እንዲጾም በቀኖና ቤተክርስቲያን ከሰባቱ አጽዋማት አንዱ ተደርጎ ስላልተወሰነ የማይጾሙ ሰዎች ሕገ ጾምን እንዳፈረሱ አድርጎ መውሰድ ስሕተት ነው፡፡ ይልቁንም የሚጾሙ ሰዎች ቢችሉ መጾማቸው እንዳይታወቅባቸው ቢያደርጉ የተሻለ ነው፡፡ "ስትጾሙ እንደግብዞች አትጠውልጉ" (ማቴ. 6፥16) የተባለው ለዚህ ዓይነቱ ጾም ነው፡፡

@Leoulu @Leoulu @Leoulu
@Leoulu @Leoulu @Leoulu
💜"ይቅርታ"💜💚
💚 በቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ

ከሠራተኞችህ አንዱ ከአንተ መቶ ቅንጣት ወርቆችን ተበደረ እንበል፡፡ ሌላ ሰው ደግሞ ከዚህ ሠራተኛህ የተበደረው ጥቂት ብር ነበረው፡፡ ከዚህ ሠራተኛህ የተበደረው ያ ሰውም ወደ አንተ መጥቶ ቸርነትን እንድታደርግለት ለመነህ፡፡ አንተም ሠራተኛህን ጠርተህ፡- “የዚህን ሰው ዕዳ ተውለት፤ ከእኔ ከተበደርከው ዕዳህም እቀንስልሃለሁ” ብትለውና ይህ ሠራተኛህ ከዚያ በኋላ በዚያ ሰው ላይ ቢጨክንና ቢከፋ ይህን ሠራተኛ ከእጅህ ሊያድነው የሚችል ሰው አለን? እጅግ እንደ ነቀፈህ አድርገህ ቆጥረህ ብዙ ግርፋትን አትገርፈውምን? [እንዲህ ብታደርግ] እጅግ ፍትሐዊ ነው፡፡ እግዚአብሔርም የሚያደርገው እንደዚህ ነው፤ በዚያች ዕለተ ምጽአት ላይ እንዲህ ይልሃልና፡- “አንተ ክፉና ተንኰለኛ ባሪያ ያንን ሰው ይቅር ብትለው ይቅርታው የአንተ ነበርን? ለእርሱ እንድታደርግለት የታዘዝከው ከእኔ የተበደርከውን ነበር፡፡ ያልኩህ ‘ዕዳዉን ብትተውለት እኔም እተውልሃለሁ’ ነው፡፡ በእውነት እንዲህ ይህን ኹኔታ ጨምሬ ባልነግርህም እንኳን ስለ እግዚአብሔር ብለህ ዕዳዉን ትተውለት ዘንድ በተገባህ ነበር፡፡ ነገር ግን እንደ ወዳጅ ኾኜ ውለታን ጠየቅሁህ እንጂ እንደ ጌታ አላዘዝኩህም፡፡ የጠየቅሁህ የእኔ ከኾነው ነው፤ ይህን ካደረግህም እጅግ በረከተ ሥጋን በረከተ ነፍስን እንደምሰጥህ ቃል ገብቼልህ ነበር፡፡ ነገር ግን ምንም ልትሻሻል አልቻልክም፡፡”

ከዚህም በላይ ሰዎች እንደዚህ ሲያደርጉ የሚቀንሱት የዕዳ መጠን ሠራተኞቻቸው ላበደሩአቸው ሌሎች ሰዎች የቀነሱትን ያህል ነው፡፡ ለምሳሌ እንበልና አንድ ሠራተኛ ከአሠሪው መቶ ቅንጣት ወርቅን ይበደራል፡፡ ሌላው ሰው ደግሞ ከዚህ ሠራተኛ ዐሥር ቅንጣት ይበደራል፡፡ ሠራተኛው ዐሥር ቅንጣት ላበደረው ብድሩን ቢተዉለት አሠሪው ግን መቶ ቅንጣቱን አይተውለትም፤ የሚተውለት ዐሥር ቅንጣቱን ብቻ ነው፤ ሌላዉን እንዲመልስለት ይፈልጋል፡፡ በእግዚአብሔር ዘንድ ግን እንደዚህ አይደለም፡፡ አንተ ለባልንጀራህ ጥቂቱን ስትተውለት እግዚአብሔር ደግሞ ዕዳህን ኹሉ ይተውልሃል፡፡ ይህስ [መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ] የት ይገኛል? [ጌታችን] ስለ ጸሎት ባስተማረው ትምህርት ውስጥ አለ፡፡ “ለሰዎች ኃጢአታቸውን ይቅር ብትሉ የሰማዩ አባታችሁ እናንተን ደግሞ ይቅር ይላችኋልና” እንዲል (ማቴ.6፡14)፡፡ በ“መቶ ዲናር” እና በ“እልፍ መክሊት” መካከል ያለው ልዩነት ያህል ለሰው ይቅር የምንለው ዕዳና ከእግዚአብሔር ይቅር የሚባልልን ዕዳም አይነጻጸርም (ማቴ.18፡24፣28)!

እንግዲህ መቶ ዲናርን ዕዳ ይቅር ብሎ እልፍ መክሊትን የሚቀበል ኾኖ ሳለ ይህቺን ጥቂት ዕዳስ እንኳን ይቅር ሳይል ጸሎቱን በራሱ ላይ የሚያደርስ ይህ ሰው የማይገባው ቅጣት እንደ ምን ያለ ቅጣት ነው? ምክንያቱም “እኛ የበደሉንን ይቅር እንደምንል በደላችንን ይቅር በለን” ብለህ እየጸለይክ ሳለ አንተ ግን ከዚያ በኋላ ይቅር የማትል ከኾነ እግዚአብሔር ምሕረቱን ወይም ቸርነቱን ኹሉ እንዲያርቅብህ ካልኾነ በቀር ሌላ ምንም እየለመንከው አይደለም፡፡ “እኔ ይቅር በለኝ ብቻ ነው እንጂ የበደሉኝን ይቅር እንደምል በደሌን ይቅር በለኝ ብዬ አልጸልይም” የሚል ሰው ደግሞ አለ፡፡ ታዲያ ይኼ ምንድን ነው? አንተ እንዲህ ብለህ ባትጸልይም እግዚአብሔር ግን እንዲህ አያደርግም፤ ይቅር የሚልህ አንተ ይቅር ስትል ነው፡፡ ይህም ከዚያ በኋላ እንዲህ ብሎ ግልጽ አድርጎታል፡- “ለሰዎች ኃጢአታቸውን ይቅር ባትሉ የሰማዩ አባታችሁም ኃጢአታችሁን ይቅር አይላችሁም” (ማቴ.6፡15)፡፡ ስለዚህ ጸሎቱን ሙሉ ባትደግመው ወይም ዕለት ዕለት እንደዚያ ብለህ ስትጸልይ ፈርተህ ከባልንጀራህ ጋር እንድትታረቅ ብሎ እንድትጸልው ባዘዘህ መንገድ ሳይኾን ቈርጠህ ብትደግመው እንኳን ደገኛ መንገድ ነው ብለህ አታስብ፡፡

“ብዙ ጊዜ ለምኜዋለሁ፤ ተማጽኜዋለሁ፤ ማልጄዋለሁ፤ ሊታረቀኝ ግን አልቻለም” ብለህ አትንገረኝ፡፡ እስክትታረቀው ድረስ በፍጹም አታቁም፡፡ ጌታችን ሲናገር፡- “መባህን ትተህ ኺድ፤ ወንድምህንም ለምነው” አይደለምና፡፡ ያለው፡- “ኺድ፤ ታረቅ” ነው (ማቴ.5፡24)፡፡ ስለዚህ ምንም እንኳን ብዙ ጊዜ ለምነኸው ቢኾንም እስክታሳምነው ድረስ ግን ይህን ማድረግህን አታቋርጥ፡፡ እግዚአብሔር ዕለት ዕለት ይለምነናል፤ እኛ ግን አንሰማውም፡፡ ኾኖም [አልሰሙኝም ብሎ] መለመኑን አላቋረጠም፡፡ ታዲያ አንተ ባልንጀራህን ለመለመን ትታጀራለህን? እንዲህ የምታደርግ ከኾነስ ልትድን የምትችለው እንዴት ነው?

የይቅርታ ልብ ይስጠን
https://telegram.me/Leoulu
https://telegram.me/Leoulu
https://telegram.me/Leoulu
"ሰማዕትነት ስር ነው፡፡ ክርስቲያኖች ደግሞ ከዚኽ ስር የሚያቆጠቁጡ ምርጥ ዘሮች ናቸው፡፡ ብዙ ዛፍ የሚያቆጠቁጥበት ስር በለም አፈር ስለሚሸፈን አይታይም፡፡ ከዚያ በሚያቆጠቁጡ ዛፎች ግን ስሩ እንዴት እንደተመቸው ይታወቃል፡፡ ሰማዕታትም በግዙፉ ዓይናችን እንደምን ያለ አክሊል ሽልማት እንደተቀበሉ አይታየንም፡፡ ፍሬያቸው ግን እነርሱን መስለው እነርሱን አኽለው በሚጋደሉ ምርጥ ዘሮች ይታወቃል፡፡

ሰማዕታት አክብሩን ብለው አይናገሩም፡፡ ነገር ግን በክርስቲያኖች ልብ የሚዘሩት ፍሬ ምእመናንን በፍቅር ያስገድዳል፡፡ እነርሱን እንዲመስሉ ያሳስባል፡፡

ሰማዕታት እንደ ፍቅረኛ ናቸው፡፡ አንድ ሰው የፍቅረኛውን ስም በየአጋጣሚው ያነሣል፡፡ በዓይነ ሕሊናው ያስባል፡፡ በተለያየ መልኩ ያያል፡፡ ሰማዕታትም ለክርስቲያኖች እንደዚያ ናቸው፡፡ እጅግ የተወደዱና በፍጹም ከሕሊና የማይጠፉ ተወዳጆች ናቸው፡፡ የልጆቻችንን ስም በነርሱ ስም የምንሰይመው፣ ሥዕላቸውን ሥለን የምንተሻሸው የምንስመው ለሰማዕታቱ ያለንን ጥልቅ ፍቅር የምንገልጽበት መንገድ ስለኾነ ነው፡፡"

(ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ)

የሰማዕቷ ቅድስት አርሴማ በረከት አይለየን!
❤️😘🥰😍🥰😍🙏🙏
የጋስጫው ሊቅ አባ ጊዮርጊስ እንዲህ አለ

የዓለም ሁሉ መድኃኒት የምትሆን ብላቴና እግሯ የተመላለሰበቱን ምድር እስም ዘንድ ማን በከፈለኝ፡፡ ይቅርታን የምታሰጥ ብላቴና ጥላዋ ይነካኝ ዘንድ ማን በከፈለኝ፡፡ የብርሃን ልጅ ወደ ሄደችበት እከተላት ዘንድ ማን በከፈለኝ የእግሯንም ጫማ እሸከም ዘንድ ማን በከፈለኝ፡፡

አሁንም ያን ጊዜ በዕብራይስጥ ማሪሃም ከተባለች ከተመረጠች ድንግል ማርያም ጋራ ያን ጊዜ ካሉት አላንስም ሀሳቤን ከዚያ እንዳለሁ አድርጌ አለሁና፡፡ በስጋ አልነበርሁም በመንፈስ ግን አለሁ፡፡ ባነዋወር አልነበርሁም በሃይማኖት ግን አለሁ በገጽ አልነበርሁም በማመን ግን አለሁ፡፡ ሳልኖር እራሴን እንዳለሁ ያረደረግሁ እኔ የተመሰገንሁ ነኝ ጌታችን በወንጌል እንደተናገረ እንዲህ ሲል ሳያዩኝ የሚያምኑብኝ ግን የተመሰገኑ ናቸው፡፡

እኔ ባሪያህ ስለሃይማኖቴ የተመሰገንሁ ነኝ፡፡ ስለ ዕውነቴ አይደለም ስለ መረዳቴም የተመሰገንሁ ነኝ፡፡ ስለ ንጽህናዬም አይደለም በእግዚአብሔር ስም ስለ አመንኩ የተመሰገንሁ ነኝ፡፡ በናቱም ጸሎት ስለ አመንሁ ንዑድ ክቡር ነኝ፡፡
ኢይፃእ ዐብይ ነገር እምአፉክሙ

#አንደበትም እሳት ነው።ይላል የጌታ ወንድም ያዕቆብ በመልዕክቱ  በሰዎች መካከል ጠብን ክርክርን ያነሳል ከዛም አልፎ ሥጋን ያሳድፋል የፍጥረትንም ሩጫ ያቃጥላል በሕይወት ዘመን ውስጥ ጥቁር የሆነ አስተሳሰብን እንዲኖርህ ያደርጋ። ቅዱስ ጳውሎስ በመልክታቶቹ አብዛኛው ጊዜ ጸያፍ ንግሮች ያወግዛል በኤፌሶን መልዕክቱ ላይ “ክፉ ቃል ከአፋችሁ ከቶ አይውጣ።” በቆላስይስ መልዕክቱ ላይም እንዲህ ይላል “ከአፋችሁም ስድብን የሚያሳፍርንም ንግግር እነዚህን ሁሉ አስወግዱ” አንደበት የመልካም ንግግሮች መፍሰሻ ነው ከዚህ በቀር ውጭ  የኃጢአት መፈንጫ ነው ጠቢብ ሰሎሞን በምሳሌ መጽሐፉ ላይ ሲናገር “በቃል ብዛት ውስጥ ኃጢአት ሳይኖር አይቀርም ከንፈሩን የሚገታ ግን አስተዋይ ነው።”
 

#የአንደበት ጸያፍ ንግግሮች በዓለም እስከኖርንበት ድረስ ዋጋ ታስከፍላለች። ጌታችን በማቴዎስ ወንጌል ላይ መስማት ና ማየት የተሳነው ሰው ጌታችን  ጋኔኑን ፈውሷል ይህን በማድረጉ  ፈሪሳውያን ጸያፍ ቃላት አውጥተው ከሰሁት ነበር ጌታችን በጸያፍ አነጋገራቸው በማውገዝ ለዐብይ አነጋገራቸው በሚገርም ሐረጎች መልስ ሰቶቿዋል "ኄር ብእሲ እምሠናይ መዝገበ ልቡ ያወፅእ ሠናየ "መልካም ሰው ከልቡ መልካም መዝገብ መልካም ነገርን ያወጣል እናትተ ግን ስራችሁ ከዳቢሎስ መዝገባች ልባችሁ ከሲኦል ስለሆነ  ለምን መልካም ነገር ትናገራለች "ወመዐምፅ ብእሲ እመዝገበ ዐመፃ ያወፅእ ዐመፃ" ክፉ ሰውም ከክፉ መዝገብ ክፉ ነገርን ያወጣል። ከፈሪሳዊያን እስከ ሌዋዋውያን ነን እስከሚሉ ሊቃነ ካህናት ድረስ የአንደበታቸው ውሸት የሐሰት ፍርድ ያወግዝ ይገጽጻቸዋል።


#የሰው ልጆች በቀን ውስጥ ከ፴፭፻/3,500 በላይ ቃላትን ይናገር ከእነዚህ ውስጥ መልካምም የአንደበት የስህተት ንግግርም  ዋጋ የሚከፈለንም የምንጠየቅበት ነው። አብዛኞቻችን በንግግር ኃጢያት ፍርድ ያለ አይመስለንም ጌታችን ለፈሪሳዊያን በመለሰላቸው ገጽ ላይ እንዲህ ይላል
"ሰዎች ስለሚናገሩት ስለ ከንቱ ነገር ሁሉ በፍርድ ቀን መልስ ይሰጡበታል" የአንደበታችን ተርታ ንግግሮች በፍርድ ፍዳ የምናገኝበት መከራ ሲኦል የምንቀላቀልበት ነው። እዛው በማቴዎስ ወንጌል ላይ  '' ከቃልህ የተነሣ ትጸድቃለህና ከቃልህም የተነሣ ትኰነናለህ።''  ቃላችን ዋጋ አላት በቃላች መጽደቅ በቃላችን በኃጢያት መኖ ይገኛል።


#አንደበት ከሽንገላ ካልገራን የብዙን ሰው መቃብር ትሆናች  መዝሙረኛው እንዲህ “በአፋቸው እውነት የለምና ልባቸውም ከንቱ ነው ጕሮሮአቸው የተከፈተ መቃብር ነው በምላሳቸው ይሸነግላሉ።” ከእንደዚህ ያለ ንግር እርቀን መልካም በሆነው ወይም ቅዱስ ጳውሎስ በቆላስይስ መልዕክቱ ላይ “ለእያንዳንዱ እንዴት እንድትመልሱ እንደሚገባችሁ ታውቁ ዘንድ ንግግራችሁ ሁልጊዜ፥ በጨው እንደ ተቀመመ፥ በጸጋ ይሁን።”አባ መቃርስ ስለ ልብ ንጽሕና ሲናገር አንተ ባህታዊ ሆይ ለወራት በርህን መዝጋትህ ምን ጥቅም የለውጥ ግን ከዚህ ቀድመህ የአንደበትህ እና የልብህን በር ካልዘጋ የአንተ በር ዘግቶ በተባትኦ መቀመጥ ምን አይጠቅም ይላል።
ቅዱስ ኤፍሬም  እንዲህ ይላል "ለአፍህ ተጠንቀቅ  ግን በዋነኝነት በአእምሮህ ክፉ ሐሳቦች ከአንተ ጋር ማውራት አትፍቀድ። አፍህ ምናልባት ወንድምህን ሊጎዳ የሚችል ቃላትን ይናገራልና።  ድፍረት እና ተስፋ ውስጣዊውን ሰው የሚገልጠው የአንድ ሰው አፍ ነውና።"

#ይቆየን
@Leoulu
@Leoulu
@Leoulu

''ወእግዚእነ ኢየሱስ ክርስቶስ የሀሉ ምስለ መንፈሰክሙ ወጸጋሁ ምስሌክሙ አሜን!''
“ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ ከመንፈሶቻችን ጋር ይሁን። ጸጋ ከእናንተ ጋር ይሁን፤ አሜን።”
በአንድ ወቅት አንድ መንፈሳዊ አባት ከነበሩበት ቦታ ወደ በረሃ መሰደድ ግድ ሆነባቸው። ከቅዱስ መጽሐፋቸው ሌላ ሦስት ነገሮች ነበሯቸው።

እነሱም፦
1ኛ ቅዱስ መጽሐፉን በጨለማ ወቅት ለማንበብ የሚጠቅማቸው ኩራዝ ።

2ኛ ጎህ ከመቅደዱ በፊት ከእንቅልፍ የሚቀሰቅሳቸው አንድ አውራ ዶሮ።

3ኛ ለመጓጓዣነት የሚገለገሉበት አንድ አህያ ነበሩ።
አንድ ቀን ምሽት ከጉዞ የተነሣ በጣም ስለ ደከሙ እኚህ መንፈሳዊ አባት ወደ አንድ መንደር ቀርበው ማደሪያ ቢጠይቁም መንደርተኛው በሙሉ ልክ እንደተመካከረ ሰው ፈቃደኛ ባለመሆኑ ማንም አላሳደራቸውም።
ስለዚህም አማራጭ ስላልነበራቸው ከመንደሩ አቅራቢያ አንድ ጉድጓድ ያገኙና በዚያ ውስጥ ገብቶ ለማደር በመወሰን ወደ ጉድጓዱ ገብተው አደሩ። እንደ ወትሮው ቅዱስ መጽሐፋቸውን ለማንበብ ኩራዛቸውን ቢለኩሱትም የነበረው ብርቱ ነፋስ አጠፋባቸው። ደጋግመው ቢሞክሩም ሊሳካላቸው አልቻለም
ስለዚህም ለመተኛት ጋደም እንዳሉ ተኩላ መጥቶ አውራ ዶሮዋቸውን፣ አንበሳም አህያቸውን በሉባቸው።
የተደራረበ ጉዳት ስለደረሰባቸው ሽማግሌው እርዳታን በመሻት ወደዚያ መንደር ቢመለሱ ዘራፊ ሽፍታዎች የመንደሩን ነዋሪዎች በሙሉ ገድለው ንብረት ዘርፈው ዖና መንደር ሆኖ አገኙት።
ሽማግሌው ይህን ሁሉ ባጤኑ ጊዜ እግዚአብሔር ምን ያህል መልካም ነገርን እንዳደረገላቸው አስተዋሉ። በዚያች ምሽት በመንደርተኞቹ በአንዱ ቤት ቢያድሩ ኖሮ የዘራፊዎች ሰለባ ሆነው ሊገደሉ በቻሉ ነበር።
ቀንዲላቸውንም (ኩራዝ) ነፋስ ባያጠፋው የብርሃኑ ወጋገን እዚህ ጋር ሰው አለ በማለት ለሽፍታዎቹ ያሳብቅ ነበር። አውራ ዶሮአቸውና አህያቸውም ባይበሉ ኖሮ ከሽፍታዎቹ ተደብቀው ማደር ባልቻሉ ነበር።” እግዚአብሔር ከክፉ ነገሮች ውስጥ መልካም ነገር ማውጣት የሚችል አምላክ ነው
@Leoulu
"የወንድምህን ኃጢአት መሸፈንና የእርሱን ኃጢአት እንደራስህ አድርግህ በእርሱ ፋንታ መሞት ካልቻልክ ቢያንስ ስለ ኃጢአቱ አትፍረድበት።››

ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ
††† እንኩዋን ለቅዱሳን ነገሥታት "አብርሃ ወአጽብሃ" እና ለቅዱስ "ሐናንያ ሐዋርያ" ዓመታዊ የዕረፍት በዓል በሰላም አደረሳችሁ †††

+"+ ቅዱሳን አብርሃ ወአጽብሃ +"+

=>እነዚህ ነገሥታት ሞገሶቻችን: ብርሃኖቻችን ናቸውና ደስ እያለን እንወዳቸዋለን: እናከብራቸዋለን:: ሥላሴ ቢመርጧቸው ዛሬ ላለንበት ሕይወት መሠረቱን ጥለው አልፈዋልና::

+2ቱ ቅዱሳን ነግሥታት መንትያዎች ሲሆኑ ወላጆቻቸው ንጉሥ ታዜር / አይዛና / ሠይፈ አርዕድ እና ንግሥት አሕየዋ / ሶፍያ ይባላል:: ንጉሡና ባለቤቱ ልጅ ቢያጡ ወደ እግዚአብሔር ለመኑ:: ፈጣሪም በቅዱስ ሚካኤል አብሳሪነት 2 ዕንቁዎችን አስረከባቸው::

+ንግስት አሕየዋ (ሶፍያም) መጋቢት 29 ቀን በ311 ዓ/ም ጸንሳ: ታሕሳስ 29 ቀን በ312 ዓ/ም 2ቱን ቅዱሳን ወልዳቸዋለች:: "አምላክ ሽሙጥን አራቀልኝ" ስትልም "አዝጉዋጉ" ብላቸዋለች:: እነዚህ 2 ፍሬዎች በልጅነታቸው ከወቅቱ ሊቀ ካህናት እንበረም ኦሪቱን ጠንቅቀው ተምረዋል::

+ከእግዚአብሔር የተሰጡ ናቸውና በ12 ዓመታቸው ወደ ቤተ መቅደስ ገብተዋል:: ትንሽ ቆይቶ ግን አባታቸው ታዜር በማረፉ ሕዝቡ 2ቱን ቅዱሳን "ንገሡልን" አሏቸው:: እነርሱም "እኛ የፈጣሪ አገልጋዮች ነንና አንችልም" በማለታቸው ለተወሰነ ጊዜ እናታቸው አስተዳደረች::

+ቆይቶ ግን ቅዱስ ሚካኤል ለሊቀ ካህናቱ እንበረም "የፈጣሪ ፈቃዱ ስለ ሆነ አትዘኑ:: 2ታችሁም በአንድ ዙፋን ላይ ንገሡ: ታላቅ ጸጋ ለሃገሪቱ ይሆናል በላቸው" አለው::

+ሊቀ ካህናቱም የታዘዘውን ተናግሮ: በ19 ዓመታቸው: 2ቱንም በአንድ ዙፋን ላይ "ነገሥተ ኢትዮዽያ" ሲል አስቀምጦ ቀባቸው:: ስማቸውን "ኢዛና" እና "ሳይዛና" አላቸው:: ቅዱሳኑ እንደ ነገሡ ቀዳሚ ሥራቸው የቀናችውን ሃይማኖት መፈለግ ሆነ::

+በወቅቱ ፍሬምናጦስ (የሁዋላው አቡነ ሰላማ) በቤተ መንግስቱ ውስጥ የቅርብ አማካሪ ነበርና ጠርተው ተጨዋወቱት:: "አንተ ወንድማችን! ክርስቶስ ይወርዳል: ይወለዳል ተብሎ የተቆጠረው ሱባኤ እኮ አልፏል:: ምነው ቀረሳ?
ምሥጢሩን ንገረን" አሉት::

+እርሱም አትቶ: አመሥጥሮ: ከ300 ዓመታት በፊት አምላክ ሰው መሆኑንና ዓለምን ማዳኑን አስተማራቸው:: "አጥምቀን?" ቢሉት "አልችልም" አላቸው:: እነርሱም ከብዙ ስጦታ ጋር ወደ ግብጽ ላኩት::

+ቅዱስ አትናቴዎስም ፍሬምናጦስን "አቡነ ሰላማ" ብሎ ከብዙ መጻሕፍት ጋር ላከው:: በመጀመሪያ ኢዛናና ሳይዛና ተጠመቁ:: ስማቸውም "አብርሃ ወአጽብሃ" ተባለ:: ቀጥሎም ሠራዊቱና ሕዝቡ ተጠመቀ::

+ሃገራችንም በእነዚህ ቅዱሳን አማካኝነት ከጨለማ ወደ ብርሃን መጣች:: የክርስትና ደሴት ሆነች:: ሃገረ እግዚአብሔርነቷንም አጸናች:: ቅዱሳኑ ከዚህ በሁዋላ በሞገስ ክርስትናን ያስፋፉ ዘንድ ደከሙ:: ከ154 በላይ አብያተ ክርስቲያናትን ሲያንጹ አብዛኞቹ ፍልፍል ነበሩ::

+በተለይ ግን በአክሱም ከተማ ላይ ያነጿትና 12 ቤተ መቅደሶች የነበሯት የጽዮን ቤተ ክርስቲያን ልናያት ትናፍቀናለች:: ጌጧ: ብርሃኗ ውል ውል ይልብናል:: ይህቺው ቤተ ክርስቲያን በ10 ኛው ክ/ዘመን ዮዲት ጉዲት በእሳት አውድማታለችና:: መሠረቱ ግን ዛሬም አለ::

+ቅዱሳን አብርሃ ወአጽብሃ ግን ክርስትናን ለማስፋፋትና መንግስትን ለማጽናት ሲሉ ከአክሱም በተጨማሪ በሽዋም ዙፋንን ዘረጉ:: ለብዙ ዓመታትም አምላክ በፈቀደው መንገድ እስከ የመን ድረስ ገዙ:: ክርስትናንም አስፋፉ::

+ቅዱስ አብርሃ በተወለደ በ52 ዓመቱ: በ364 ዓ/ም ጥቅምት 4 ቀን ሲያርፍ ወንድሙ ለ15 ዓመታት ብቻውን አስተዳድሯል:: በ379 ዓ/ም ደግሞ በዚሁ በጥቅምት 4 ቀን ቅዱስ አጽብሃም በተወለደ በ67 ዓመቱ በክብር ዐርፏል::

+ከሁለቱም መቃብር ላይ ለ30 ቀናት የብርሃን ምሰሶ ተተክሎ ታይቷል:: ጌታችንም በማይታበል ቃሉ "ስማችሁን የጠራውን: መታሰቢያችሁን ያደረገውንም እምርላቹሃለሁ" ሲል ቃል ኪዳን ገብቶላቸዋል::

+"+ ቅዱስ ሐናንያ ሐዋርያ +"+

=>ሐናንያ ቁጥሩ ከ72ቱ አርድእት ሲሆን መጽሐፍ ቅዱስ ላይ ስማቸው ተመዝግቦ ከተቀመጠልን ከጥቂቶቹ ዋነኛው ነው:: ከነገደ እሥራኤል ተወልዶ: በሕገ ኦሪት አድጐ: ከወጣትነት ዕድሜው ትንሽ እልፍ ሲል ጌታችን ወንጌልን ማስተማር ጀምሯልና ጠራው:: እርሱም በበጐ ፈቃድ ተከትሎታልና ከ72ቱ አርድእት ደመረው::

+ለ3 ዓመታት ከጌታ እግር ተምሮ: ከዕለተ ስቅለት በፊት ሀብተ ፈውስም ተሰጥቶት ነበር:: ምክንያቱም ቅዱስ ሉቃስ እንደ ጻፈልን ሰብዐው አርድእት "ጌታ ሆይ! አጋንንት በስምህ ተገዙልን" ማለታቸውን አስቀምጦልናል:: (ሉቃ. 10:17) ቅዱስ ሐናንያ በበዓለ ዕርገት ተባርኮ በ50ኛው ቀንም መንፈስ ቅዱስን ተቀብሎ ለስብከተ ወንጌል ወጥቷል::

+በሚያስተምር ጊዜ የሶርያዋን ደማስቆን ማዕከል አድርጐ ነበር:: በሁዋላም አበው ሐዋርያት የዚህች ከተማ የመጀመሪያው ዻዻስ አድርገው ሹመውታል:: ጌታ ባረገ በ8ኛው ዓመት ክርስቲያኖችን ያሰቃይ የነበረው ሳውል (የሁዋላው ቅዱስ ዻውሎስ) ወደ ደማስቆ የተጉዋዘው ክርስቲያኖችን በተለይም ቅዱስ ሐናንያን ለማሠር ነበር::

+ለእግዚአብሔር ምርጥ ዕቃ ይሆን ዘንድ መብረቅ ዐይኑን አጠፋው:: ወዲያውም ጌታችን ሳውልን ወደ ሐናንያ እንዲሔድ ነው የነገረው:: ከ3 ቀናት በሁዋላ ጌታችን ለሐናንያ ተገልጦ አነጋግሮታል:: ሳውል (ዻውሎስ) ወደ ሐናንያ የደረሰው በመሪ ነበር::

+2ቱ እንደተገናኙ ቅዱስ ሐናንያ ሳውልን አስተማረው: ፈወሰው: አጠመቀው: በጐ መንገድንም መራው:: በዚህ ምክንያት ቅዱሱ ሐዋርያ የቅዱስ ዻውሎስ የንስሃ አባቱ ይሰኛል:: (ሐዋ. 9:1-19)

+ከዚህ በሁዋላ ቅዱስ ሐናንያ ለብዙ ዓመታት በተለያዩ የዓለም ክፍሎች ወንጌልን አስተማረ መከራንም ተቀበለ:: በመጨረሻም በዚህ ቀን ክፉዎች ከብዙ ስቃይ በሁዋላ በድንጋይ ወግረው ገድለውታል::

=>አምላከ አብርሃ ወአጽብሃ "ድሃ ተበደለ: ፍርድ ተጉዋደለ" የሚል ዳኛ: ሃይማኖቱ የቀና መሪንም ያምጣልን:: የቅዱሳኑን ክብር በእኛ ላይ ያድርግልን::

=>ጥቅምት 4 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት=
1.ቅዱሳን ነገሥት አብርሃ ወአጽብሃ
2.ቅዱስ ሐናንያ ሐዋርያ (ከ72ቱ አርድእት)
3.ቅዱስ በርተሎሜዎስ ሐዋርያ
4.ቅዱስ ባኮስ ሰማዕት
5.ቅዱሳን ባባ እና ማማ
6.ቅዱስ ዮሐንስ ሕጽው

=>ወርኀዊ በዓላት
1.ቅዱስ ዮሐንስ ወንጌላዊ
2.ቅዱስ እንድርያስ ሐዋርያ
3.ቅድስት ሶፍያ ሰማዕት
4.ቅዱስ ዮሐንስ ዘሐራቅሊ (ሰማዕት)

=>+"+ እንግዲህ እግዚአብሔርን በመምሰልና በጭምትነት ሁሉ: ጸጥና ዝግ ብለን እንድንኖር: ልመናና ጸሎት: ምልጃም: ምስጋናም ስለ ሰዎች ሁሉ: ስለ ነገሥታትና መኩዋንንትም ሁሉ እንዲደረጉ ከሁሉ በፊት እመክራለሁ:: ሰዎች ሁሉ ሊድኑና እውነቱን ወደ ማወቅ ሊደርሱ በሚወድ በእግዚአብሔር በመድኃኒታችን ፊት መልካምና ደስ የሚያሰኝ ይህ ነው:: +"+ (1ጢሞ. 2:1-4)

††† ወስብሐት ለእግዚአብሔር †††
✞✞✞ በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ ፡፡ አሜን ፡፡ ✞✞✞

❖ ጥቅምት ፭ (5) ❖

✞✞✞ እንኩዋን ለጻድቁ "አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ" እና "ቅዱስ ኪራኮስ አረጋዊ" ዓመታዊ በዓል በሰላም አደረሳችሁ ✞✞✞

+"+ አቡነ ገብረ ሕይወት +"+

=>ጻድቁ የተወለዱት ግብፅ (ንሒሳ አካባቢ) ሲሆን
አባታቸው ስምዖን እናታቸው አቅሌስያ ይባላሉ:: አባታችን
ገብረ ሕይወት የጻድቃን አለቃ: የቅዱሳን የበላይ:
ተጋድሎአቸውና ድንቅ ተአምራቸው እንደ ሰማይ
ከዋክብት የበዛ ቅዱስ ሰው ናቸው::

+የጻድቁን ክብር መናገር የሚችል ምን አነደበት
ይኖራል?
እንደ ምንስ ባለ ብራና ይጻፋል?
ዜናቸውንስ ለመስማት የታደለ እንደ ምን ዓይነት ሰው
ይሆን?

+አባታችን ገብረ መንፈስ ቅዱስ ለ562 ዓመታት በዚህች
ዓለም ሲኖሩ እህል ያልቀመሱ (ምግባቸው ምስጋና
ነውና): ልብስ ያልለበሱ (ጠጉር አካላቸውን ይሸፍን
ነበርና): ሐዋርያዊ ሆነው ከግብፅ እስከ ኢትዮዽያ ብዙ
ነፍሳትን ያዳኑ አባት: ሃገራችንን አስምረው: አስራት
እንድትሆናቸውም ተቀብለው ምድረ ከብድ አካባቢ
አርፈዋል::

+ጻድቁ ገብረ መንፈስ ቅዱስም: ገብረ ሕይወትም
ይባላሉ:: በ562 ዓመታት ሕይወታቸው እንደ ሐዋርያት
ከምድረ ግብጸ እስከ ኢትዮዽያ ወንጌልን ሰብከዋል::
በዚህም በሚሊየን (አእላፍ) ለሚቆጠሩ ነፍሳት የድኅነት
ምክንያት ሆነዋል::

+ጻድቁ እንደ ሰማዕታትም ከከሃዲ ሰዎች ብዙ መከራን
ተቀብለዋል:: እንደ ባሕታውያን ለብዙ መቶ ዓመታት ሰው
ሳያዩ ቆይተዋል:: ለየት የሚለው ግን የጽድቅ
ሕይወታቸው ነው:: ከእልፍ አዕላፍ አጋንንት ጋር
ተዋግተው ድል ማድረግ ችለዋልና::

+የንሒሳው ኮከብ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ለኢትዮዽያ ልዩ
ፍቀር አላቸው:: ስለ ሃገሪቱና ሕዝቧ ፍቅር ሲሉ ለ100
ዓመታት በደብረ ዝቁዋላ መከራን ተቀብለዋል:: ምሕረትን ሲለምኑ ሥጋቸው አልቆ በአጥንታቸው ቁመው
ነበርና ሃገራችን አሥራት ሆና ተሰጠቻቸው::

+ስለዚህም ነው በሃገሪቱ ውስጥ ከ2,000 በላይ የጻድቁ
አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ገዳማትና አድባራት ዛሬም
ድረስ ያሉት:: በ8ኛው ክ/ዘመን አካባቢ የተወለዱት
አባታችን ያረፉት በ14ኛው መቶ ክ/ዘመን አካባቢ ነው::
ፍጥረታትን ሁሉ አዘው መጋቢት 5 ቀን ሲያርፉ ግሩማን
መላእክት ገንዘው አካላቸውን ሠውረዋል::

+ሥላሴን የተሸከመ አካላቸው በጐልጐታ ተቀብሯል
የሚሉም አሉ::
"ሰላም ለመቃብሪከ ዘኢተከሥተ ለባዕድ:
ከመ መቃብሩ ለሙሴ ወልደ ዮካብድ:
ዜና መቃብሪከሰ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ጸማድ:
ቦ ዘይቤ በኢየሩሳሌም አጸድ:
ወቦ ዘይቤ ኀለወ በከብድ::" እንዲል::

+የጻድቁ በዓል ጥቅምት 5 ቀን የሚከበረው ብዙ ጊዜ
መጋቢት 5 ዐቢይ ጾም ውስጥ ስለሚውል ተውላጥ
(ቅያሪ) ሆኖ ነው::

+"+ ቅዱስ ኪራኮስ አረጋዊ +"+

=>ይህ ቅዱስ አባት ስም አጠራሩ የከበረ:
ሽምግልናውም ያማረ ነው:: ብዙዎቻችን የምናውቀው
በበዓለ መስቀል ስሙ ተደጋግሞ ሲጠራ ነው:: ግን ይህ
ታላቅ ሰው ለቅድስት እሌኒ መካነ መስቀሉን አሳያት
ከሚል አረፍተ ነገር የዘለለ ታሪኩ ሲነገርለት ብዙ ጊዜ
አንሰማምና እስኪ በዕለተ ዕረፍቱ ስለ ቅዱሱ ጥቂት
እንበል::

+ቅዱስ ኪራኮስ የተወለደው በ3ኛው መቶ ክ/ዘመን
ሲሆን እናቱ ቅድስት ሐና ትባላለች:: በእጅጉ የተባረከች
ሴት ናት:: ምንም በነገዳቸው አይሁድ ቢሆኑም የዘመኑ
የአይሁድ ክፋት አልገዛቸውም:: የተባረከች እናቱ ታሪክ
እያስጠናች ከማሳደጉዋ ባለፈ አስቀድማ ኦሪቱን:
ነቢያቱን እንዲያውቅ አደረገች::

+አስከትላም ሕገ ክርስትናን እንዲረዳ አደረገችው::
የታሪክና የመጻሕፍት ምሑሩ ቅዱስ ኪራኮስ ከእናቱ ጋር
ሆኖ እግዚአብሔርን እያገለገለ: ክርስቶስን እያመለከ
ቆየ:: በዚህ ጊዜ ግን እድሜው እየገፋ ነበር::

+ሠለስቱ ምዕት (318ቱ ሊቃውንት) ጉባኤያቸውን
ከፈጸሙ በሁዋላ ቅድስት እሌኒም መስቀሉን ፍለጋ
ስትወጣ ትልቁ ፈተናዋ የተቀበረበትን ቦታ ማወቅ
አለመቻሏ ነበር:: እንዲያውም አማራጭ ስታጣ
በአካባቢው የነበሩ አይሁድን ምሥጢር እንዲያወጡ
ቀጥታቸው ነበር:: በሁዋላ ግን ኪራኮስ ስለሚባል ደግ
ታሪክ አዋቂ ሰው ሰምታ ተገናኙ::

+ቅዱስ ኪራኮስም አባቶቹ አይሁድ ናቸውና አካባቢውን
ያውቀው ነበር:: ችግሩ ቆሻሻው ተራራ በመሆኑ ከ3ቱ
የትኛው እንደ ሆነ አለመታወቁ ነበር:: ቅዱሱ ግን
ለዚህም መፍትሔ ነበረውና "ደመራ ደምረሽ: በእሳት
አቃጥለሽ: እጣን ጨምሪበትና ይገለጥልሻል" አላት::

+ቅድስት እሌኒም የተባለችውን በትክክል ፈጽማ
የመድኅን ክርስቶስን ቅዱስ ዕጸ መስቀል አገኘች::
ቅድስት እሌኒ ወደ ሃገሯ ከተመለሰች በሁዋላም ቅዱስ
ኪራኮስ በኢየሩሳሌም አካባቢ ዻዻስ ሆኖ ተሾመ::

+አረጋዊው ቅዱስ የሚገርም እረኛ ነውና የባዘኑትን
ሲፈልግ: በቤቱ ያሉትንም ሲያጸና ብዙ ደከመ:: በቅርቡ
ያሉትን በአፉ: የራቁትን ደግሞ በጦማር (በመልእክት)
አስተማረ:: በወቅቱ በአካባቢው ኤልያኖስ የሚሉት ከሃዲ
ንጉሥ ነበርና በቅዱስ ኪራኮስ ላይ ተቆጣ::

+ወደ እርሱ አስጠርቶ በአደባባይ: ቅዱስ ቃሉን ይጽፍበት
የነበረው ቀኝ እጁን አስቆረጠው:: ቅዱስ ኪራኮስ ግን
እጁ መሬት ላይ ወድቃ: ደሙ እየተንጠፈጠፈ ተናገረ:-
"አንተ ልብ የሌለህ ንጉሥ! እጄን ቆርጠህ ከክርስቶስ
ፍቅር ልትለየኝ አትችልም" አለው::

+በዚህ የተበሳጨ ንጉሡ እሳት አስነድዶ: አልጋውን
አግሎ ቅዱሱን ጠበሰው:: ኪራኮስ ግን በእሳቱ ላይ ሳለ
ወደ እሥራኤል ፈጣሪ በእብራይስጥኛ ጸለየ:: በማግስቱ
እናቱን ቅድስት ሐናን አምጥተው የነደደ እሳት ውስጥ
ጣሏት::

+ለ3 ሰዓት ያህል በእሳት ውስጥ ስትጸልይ ቆይታ በጦር
ወግተው ገደሏት:: ቅዱስ ኪራኮስንም ለአራዊት ሰጡት::
አራዊቱ ሰገዱለት:: በሌሎች ዓይነት ስቃዮችም ፈተኑት:
ግን እንቢ አላቸው:: በመጨረሻው በዚህ ቀን ገድለውት
የክብርን አክሊል ተቀዳጅቷል::

=>አምላከ ቅዱሳን በእነርሱ ላይ የበዛች ፍቅሩን ለእኛም
ያድለን:: ፍሬ ትሩፋት: ፍሬ ክብር እንድናፈራም ይርዳን::
ክብራቸውንም አያጉድልብን::

=>ጥቅምት 5 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት=
1.አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ጻድቅ
2.ቅዱስ ኪራኮስ አረጋዊ (ዻዻስ ወሰማዕት)
3.ቅድስት ሐና ሰማዕት (እናቱ)
4.ቅዱስ ያዕቆብ ወልደ እልፍዮስ (ከ12ቱ ሐዋርያት)
5.አባ ዻውሎስ ሰማዕት (አርዮሳውያን አንቀው የገደሉት አባት)

=>ወርሐዊ በዓላት
1.ቅዱስ ዼጥሮስ ሊቀ ሐዋርያት
2.ቅዱስ ዻውሎስ ብርሃነ ዓለም
3.ቅዱስ ዮሐኒ ኢትዮዽያዊ
4.ቅዱስ አሞኒ ዘናሒሶ
5.ቅድስት አውጋንያ (ሰማዕትና ጻድቅ)

=>+"+ ነገር ግን ዓለም ለእኔ የተሰቀለበት: እኔም
ለዓለም የተሰቀልሁበት ከጌታችን ከኢየሱስ ክርስቶስ
መስቀል በቀር ሌላ ትምክህት ከእኔ ይራቅ:: በክርስቶስ
ኢየሱስ አዲስ ፍጥረት መሆን ይጠቅማል እንጂ መገረዝ
ቢሆን ወይም አለመገረዝ አይጠቅምምና:: +"+ (ገላ. 6:14)

<<< ወስብሐት ለእግዚአብሔር >>>
እንኳን ለአጋእዝተ ዓለም ሥላሴ እና ለቅዱሳን አበው አብርሃም ወርሀዊ መታሰቢያ በአል አደረሳችሁ

ሥሉስ ቅዱስ

በአንድነቱ ምንታዌ (ሁለትነት): በሦስትነቱ ርባዔ (አራትነት) የሌለበት የዘለዓለም አምላክ: የፍጥረታት ሁሉ ፈጣሪ እግዚአብሔር ነው:: አብ :ወልድ : መንፈስ ቅዱስ በስም: በአካል: በግብር ሦስትነት: በባሕርይ: በሕልውናና በፈቃድ አንድነት የጸኑ ናቸው:: በዚህ ጊዜ ተገኙ: በዚህ ጊዜ ያልፋሉ አይባሉም:: መጀመሪያም መጨረሻም እነርሱ ናቸውና::

ርሕሩሐን ናቸውና በእናት ሥርዓት "ቅድስት ሥላሴ" እንላቸዋለን:: የሚጠላቸው (የማያምንባቸውን) አይጠሉም:: የሚወዳቸውን ግን እጽፍ ድርብ ይወዱታል:: በቤቱም መጥተው
ያድራሉ::

ከፍጥረታት ወገን ከእመቤታችን ቀጥሎ የአብርሃምን ያህል በሥላሴ ዘንድ የተወደደ ፍጡር የለም:: አባታችን ቅዱስ አብርሃም የደግነት ሁሉ አባት ነውና በኬብሮን በመምሬ ዛፍ ሥር ሥላሴን ተቀብሎ አስተናግዷል:: ሥላሴ አኀዜ ዓለም (ዓለምን በእጁ የያዘ) ነው:: ነገር ግን በፍቅር ለሚሻው በፍቅር ይመጣል::

አባታችን አብርሃም በ99 ዓመቱ: እናታችን ሣራ በ89 ዓመቷ ሥላሴን በድንኩዋናቸው አስተናገዱ:: አብርሃም እግራቸውን አጠበ:: (ወይ መታደል!) በጀርባውም አዘላቸው:: (ድንቅ አባት!) ምሳቸውንም አቀረበላቸው:: እንደሚበሉ ሆኑለት:: በዚያው ዕለትም የይስሐቅን መወለድ አበሠሩት:: ቅድስት ሣራ ሳቀች::

እንደ ዘንድሮ ወገኖቻችን የማሾፍ አይደለም:: ደስታና ጉጉት የፈጠረው እንጂ:: ሥላሴ "ምንት አስሐቃ ለሣራ በባሕቲታ" ብለው ነበርና በዚህም ምክንያት ነው "ይስሐቅ" የተባለው::
@Leoulu
ሥላሴን ያስተናገደች ድንኩዋን (ሐይመት) የድንግል እመቤታችን ማርያም ምሳሌ ናት:: በድንግል ላይ አብ ለአጽንኦ: መንፈስ ቅዱስ ለአንጽሖ: ወልድ በተለየ አካሉ ለሥጋዌ በእርሷ ላይ አርፈዋል / አድረዋልና::

ሐምሌ 7 ሥሉስ ቅዱስ ለአብርሃም የተገለጠለት በቤቱም የተስተናገዱበት ዕለት ነው ፣ይህም ስለሆነ እኛ ኦርቶዶክሳውያን ይህን የተባረከ እለት በአለ ሥላሴ ብለን በየወሩ ወር በገባ 7 ቀን አክብረን :በስማቸው ዘክረን በረከት ተቀብለን ፣እናሳልፋለን !
@Leoulu
@Leoulu
መልካም አድርግና እርሳው...

ስላደርግኸው ስለዚህ ነገር ማንኛውንም ዓይነት ውዳሴም ሆነ ሙገሳ አትሻ። መልካም ያደረግህለት ሰው አንተ እንዳደረግህለት ለአንተ መልካም የሆነውን አጸፋ እንዲመልስልህ ወይም አንተ አንደተንከባከብከው እርሱም እንዲንከባከብህ አትጠብቅ።

መልካም ስታደርግ በምላሹ መልካም ዋጋ አገኛለሁ ብለህ በመጠበቅ ላለመሆኑ እርግጠኛ ሁን! መልካም የምታደርገው መልካም ማድርግን ስለምትወድ ወይም መልካም ከማድረግ መከልከል ስለማትችል ለመሆኑ እርግጠኛ ሁን። መልካም መሆን በውስጥህ ያለ ጠባይ ይሁን። መልካም ጠባይ እንደ መተንፈስ ምንም ዓይነት ጥረት የማይጠይቅ ግብታዊ ነገር ይሁን።

እንዲህ ያለውን ነገር የምትረሳው ከሆነ እግዚአብሔር በዚህ ምድርም ሆነ በሚመጣው ዓለም ያስታውስሃል። መልካም ማድረግህን የምታስታውሰውና በውስጥህ ይዘኸው የምትቆይ ከሆነ ግን ታጣዋለህ
🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹
👉 ሰላምኪ ማርያም አብቆለት ዕፀ ትእምርት
ወአውጽአት ጽጌ እም አፈ ምውት
ማርያም ሰላምታሽ የታምር እንጨትን አበቀለች ከሞተ ሰው አፍ አበባን አወጣች
🌹ስቅለት ከሞተ ሰው መቃብር ላይ የበቀለች የእንጨቷ ስምና ታሪክአንድ ድሀ የዕለት ምግቡን እየሰረቀ የሚበላ ነበር ነገር ግን እመቤታችን ድንግል ማርያምን ይወዳትና ብዙ ግዜ ሰላምታዋን ያቀርብላት ነበር።
ከዕለታት አንድ ቀን የዚያች አገር ሰዎች በግፍ ሰቀሉት ተሰቅሎ እያለ ነፍሱ እስከወጣች(ከስጋው እስከተለየች) ድረስ የእመቤታችንን ሰላምታ አላቋረጠም።
በዚያች አገር ላለው ኤጲስቆጶስ አስቀድማ እመቤታችን እንደ ነገረችው በክርስቲያኖች መቃብር መካከል አስቀበረው ከ4 ቀን በኋላም ስሟ ፈርከሊሳ የምትባል ትንሽ እንጨት ከመቃብሩ ላይ በቀለች ቁመቷ አንድ ክንድ ያህል ነበር።
መልኳም ያማረ ቅጠሏም ለምለም ሲሆን አበቦቿም እንደ ብር ነጭ ነበሩ።
በቅጠሎቿም ውስጥ ወርቅ በመሰለ ቀለም የእመቤታችን የድንግል ማርያም ሰላምታ ተጽፎ ይታይ ነበር ሁሎችም አደነቁ ለኤጲስቆጶሱም ያዩትን ታምር ሁሉ ነገሩት መቃብሩንም ይቆፍሩ ዘንድ ያች እንጨትም ከየት እንደመጣችና ሥሯን ያዩ ዘንድ አዘዛቸው እንደአዘዛቸውም መቃብሩን በቆፈሩ ግዜ ከመቃብሩ ወደላይ ወጥታ ያች ዕንጨት አበባን አብባ ተገኘች ስለዚህ እግዚአብሔርንና እመቤታችንን ፈጽመው አመስግነዋልና።
።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።
ሰላምኪ ማርያም አብቆለት ዕፀትእምርት
መሐርኪያ ፍቅረዚአኪ ለአሐቲ ብእሲት
እንዘትብሊ ኢታጐጒኢ አንብቦተዛቲ ጸሎት
እስመ ትኤድመኒ ሊተ እምኩሉ ስብሐት
.........................................
ሰላምታሽ ማርያም የታምር ዕንጨት አበቀለች
የዚች ጸሎት መድገምን(መጸለይን) አታስቸኩዪ አታጣድፊ ብለሽ ለአንዲት ሴት ያንቺን ሰላምታ(የቅዱስ ገብርኤል ምሥጋናን) አስተማርሻት
ለኔ ከምሥጋናው ሁሉ ይልቅ ይች ምሥጋና ደስ ታሠኘኛለችና።
🌹የጽጌረዳ አበባን ያበቀለች የእመቤታችን ምሥጋና ለአንዲት ሴት ቃልኪዳን ስለመሰጠቷ 🌹
በአንድ ገዳም ውሥጥ የመነኮሰች አንዲት ደሀ ሴት ነበረች እመቤታችንን እጅግ ትወዳት ነበር ሰላምዋንም ታዘወትር ነበር ብዙ ቤተክርስቲያንንም ትጎበኝና የተቻላትን ያህል ለቤተክርስቲያን ትሰጣለች
በአንዲት ቀንም በአንዲት ቤተክርስቲያን ውስጥ ሰላምታዋን ስትጸልይ እመቤታችን በራእይ ታየቻትና ለኔ እና ለልጄ የምታቀርቢው ክብርና ምሥጋና ፈጽሞ ደስ ስላሰኘኝ ባንቺ ደስ አለን በመልካም ሥራሽም ሁሉ አመሰገንሽ አለቻት ነገር ግን ዋጋሽ በመንግስተ ሰማያት ፍጹም ይሆን ዘንድ በገብርኤል ሰላምታ ሰላም እልሻለሁ ብለሽ እጅ በምትነሽኝ ግዜ ተጠንቀቂ አትቸኩዪ ይቺ ጸሎት ደስ ትለኛለች እወዳታለሁና የሚለውን በጎ ምክር ከነገረቻት በኋላ ከእሷ ተሰወረች ያችም ጸሎተኛ ሴት እመቤታችን ስለተገለጸችላት ደስ ተሰኘች ከዚህ በኋላ ያለችኮላ ያለመጣደፍ በዘመኗ ሁሉ የገብርኤልን ሰላምታ እየጸለየች ኖራለችና እንዲህ አለ።
+++ የተሰጠ እንባ +++

የሰው ልጅ ደካማ ነው። በውስጡ የሚፈራረቁበትን ስሜቶች ተሸክሞ ለማቆየት ይቸገራል። በጣም ሲደሰት ወይም በጣም ሲያዝን እነዚህን ስሜቶች የሚያስተነፍስበት ሳቅ ወይም ልቅሶ ይፈልጋል። ይህ ካልሆነ ግን ሰውነት ይጨነቃል። አዲስ የወይን ጠጅ እንደ ገባበት አሮጌ አቁማዳ እቀደድ እቀደድ ይላል። ከባዱን የስሜት ሰደድ እሳት የሚያበርድበት ትኩስ እንባ ከዓይን ካላዘነመ ዕረፍት የሚባል ነገር አያገኝም። ዓይን አላነባ ሲል የውስጥ ሕዋሳት የሕመም እንባ ማንባት ይጀምራሉ።

የሕክምና ሰዎች እንደሚናገሩት ሦስት ዓይነት እንባዎች አሉ። የመጀመሪያው ዓይን ውስጥ ባዕድ (ቆሻሻ) ነገር ሲገባ የምናነባው ቅጽበታዊ እንባ (Reflex tear) ሲሆን፣ ሁለተኛው ዓይናችን እንዳይደርቅና ራሱን ከinfection ለመከላከል ሲል የሚያመነጨው የማይቋረጥ እንባ (Continuous tear) ነው። ይህም እንባ 98% ውኃ ነው። ሦስተኛውና በጣም ጠቃሚው እንባ ደግሞ የውስጥ ስሜት ፈንቅሎ የሚያወጣው እንባ (Emotional tear) ነው። ተጨማሪ ጥናቶች ቢፈልግም የዘርፉ ሊቃውንት እንደሚሉት በተለይ በኃዘን ጊዜ የሚፈስሰው እንባ ከሌሎቹ እንባዎች በተለየ በሰውነት ውስጥ የተለቀቀውን stress hormone ይዞ በማስወጣት ውጥረትን ለመቀነስ ትልቅ ፋይዳ አለው። ከዚህ እንባ ጋር ተያይዘው በሰውነት ውስጥ የሚለቀቁት እንደ oxytocin እና endorphins ያሉት ሆርሞኖች ደግሞ መረጋጋትና ዕረፍትን እንድናገኝ ያግዙናል።

ይህን የእንባ ጸጋ ለእኛ የሰጠ የሰውን ድካም የሚያውቅ እግዚአብሔር ነው። ልቅሶውንም ለውስጥ ውጥረት ማስተንፈሻ ብቻ ሳይሆን፣ የነፍሳችንን ጉድፍ የምናጠራበትና ወደ እርሱ ይዘን የምንቀርበው የተወደደ መባ አደረገልን። የፈጣሪን የምሕረት ልቡን የምናውክበትና ፈጥኖ እንዲታረቀን ደጅ የምንጠናበትን የእንባ ምንጭ እርሱ ባለቤቱ ከዓይናችን ሥር አኖረ።(መኃል 6፥5) ሊቁ ዮሐንስ ዘሰዋስው እንደ ተናገረው ይህንንም እንባ ወደ ሰማይ ለምንወጣበት የብርሃን መሰላል አንደኛው እርከን አድርጎ ሰጠን። ልቅሷችንን ለመጽናናት አደረገው። "ከፊት ኀዘን የተነሣ ልብ ደስ ይሰኛል"ና (መክ 7፥3)

የምትወደውን ሰው አጥተህ የምታነባ አንተ ሰው "እንዲህ ሳዝን ወዴት አለህ?" ብለህ ፈጣሪህን አትክሰስ። እግዚአብሔርን እንባህ ውስጥ ፈልገው ታገኘዋለህ። የውስጥህን ኃዘን ከሚያበርድበትና ስብራትህን ከሚጠግንበት መንገዶቹ አንዱ "በሰጠህ እንባ" ነው።

ዲያቆን አቤል ካሳሁን
#ጥቅምት_13

#ቅዱስ_ዮሐንስ_አፈወርቅ

ጥቅምት አስራ ሦስት በዚችም ዕለት የዓለሙ ሁሉ መምህር የሆነ የከበረ አባት ዮሐንስ አፈወርቅ መታሰቢያው እንደሆነ ስንክሳሩ በስም ይጠቅሰዋል።

ይህም አባት ከእስክንድርያ አገር ሰዎች ወገን ነው የአባቱም ስም አስፋኒዶስ የእናቱም ስም አትናሲያ ነው እሊህም እጅግ ባለጸጎች ነበሩ ይህንንም ልጃቸውን በመልካም አስተዳደግ አሳደጉት ትምህርትንና ጥበብንም ሁሉ አስተማሩት እርሱ ወደ አቴና ሔዶ በመምህራን ቤት ተቀምጦ ትምህርትን ሁሉ ተምሮ በዕውቀቱ ከብዙዎች በላይ ከፍ ከፍ ብሏልና።

ከዚህም በኋላ ገና በታናሽነቱ መነኰሰ የዚህንም የኃላፊውን ዓለም ጣዕም ንቆ ተወ ከእርሱም ቀድሞ በዚሁ ገዳም ቅዱስ ባስልዮስ መንኵሶ ነበር በአንድነትም ተስማምተው ብዙ ትሩፋትን ሠሩ ወላጆቹም በሞቱ ጊዜ ከተውለት
ገንዘብ ምንም ምን አልወሰደም ለድኆችና ለምስኪኖች ሰጠ እንጂ ከዚያም በምንኵስና ሥራ በመጠመድ ፍጹም ገድልን እየተጋደለ ኖረ።

በዚያም ገዳም ሶርያዊ ጻድቅ ሰው ስሙ ሲሲኮስ የሚባል መነኰስ ነበረ እርሱም ወደፊት የሚሆነውን በመንፈስ ቅዱስ ያይ ነበር በአንዲት ሌሊትም ለጸሎት እየተጋ ሳለ ሐዋርያትን ጴጥሮስንና ዮሐንስን አያቸው ወደ ዮሐንስ አፈወርቅ ገብተው ጴጥሮስ መክፈቻ ሰጠው ወንጌላዊ ዮሐንስም ወንጌልን ሰጠው እንዲህም አሉት በምድር ያሠርከው በሰማይ የታሠረ ይሆናል በምድርም የፈታኸው ደግሞ በሰማያት የተፈታ ይሆናልና በውስጥህ መንፈስ ቅዱስ ያደረብህ አዲስ ዳንኤል ሆይ የክብር ባለቤት ከሆነ ከታለቅ መምህር ኢየሱስ ክርስቶስ ዘንድ ወደ አንተ ተልከናልና ዕወቅ እኔም የመንግሥተ ሰማያት መክፈቻ የተሰጠኝ ጴጥሮስ ነኝ።

ሁለተኛውም እኔም በመጀመሪያው ስብከቴ በከበረ ወንጌል ቃል አስቀድሞ ነበረ ያልኩ ይህም ቃል በጠላት ላይ የእሳት ሰይፍ የሆነ ዮሐንስ ነኝ። ለአንተም ከክብር ባለቤት ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ ዘንድ ወገኖችህ ምእመናንን በቀናች ሃይማኖት ታሳድጋቸው ዘንድ ዕውነተኛ አእምሮ ደግሞ ተሰጥቶሃል።

ጻድቅ ሲሲኮስም ይህን ራእይ በአየ ጊዜ ቅዱስ ዮሐንስ ቸር ታማኝ እረኛ ሁኖ እንደሚሾም ዐወቀ። ከዚህም በኋላ በቅዱስ ዮሐንስ ላይ የመንፈስ ቅዱስ ጸጋ በላዩ ወርዶ አደረበትና ብዙ ድርሳናትንና ተግሣጻትን ደረሰ ዲያቆን ሁኖ ሳለም የቤተ ክርስቲያንን መጻሕፍት ብሉያትንና ሐዲሳትን ተረጐመ። በአንዲት ሌሊትም ቅዱስ ዮሐንስ ሲጸልይ የእግዚአብሔር መልአክ በድንገት እንደ በረድ ነጭ በሆነ ልብስ ተገለጠለት ቅዱስ ዮሐንስም ሲያየው ደንግጦ በምድር ላይ ወደቀ መልአኩም አርአያውን ለውጦ እንደ ሰው ሁኖ ታየው ወዳጄ አዲስ ዳንኤል ሆይ አትፍራ ተነሣ አለው የቅዱስ ዮሐንስም ልቡ ተጽናንቶ ጌታዬ አንተ ማነህ ግርማህ አስፈርቶኛልና አለው የእግዚአብሔር መልአክም ትሠራው ዘንድ የሚገባህን ልነግርህ ወዳንተ የተላክሁ ነኝ።

አሁንም እግዚአብሔር አምላክ ያዘዘህን ለመሥራት ልብህን አበርታ ቃልህ ከጽንፍ እስከ ጽንፍ በአራቱ ማእዘን ይደርሳልና እልፍ አእላፋትም ትምህርትህን ተቀብለው ትእዛዝህን ሰምተው ወደ ፈጣሪያቸው እግዚአብሔር ተመልሰው ይድናሉና በእግዚአብሔር መንግሥትም ውስጥ የጸና የብርሃን ዐምድ ትሆናለህና። እነሆ የአንጾኪያ ሊቀ ጳጳሳት ወደ አንተ ይመጣል ከእርሱም ጋራ ሁሉም ካህናትና ዲያቆናት በየማዕረጋቸው የሚያዝህንም አድርግ የእግዚአብሐር ትእዛዝ ነውና ልትተላለፍ አይገባህም አለው። ከዚህም በኋላ ያ መልአክ ለአባ ፊላትያኖስ ተገልጦ ቅዱስ ዮሐንስን ቅስና እንዲሾመው አዘዘው በማግሥቱም ሊቀ
ጳጳሳቱ መጣ ከርሱ ጋራም ካህናት አሉ ይህን ቅዱስ ዮሐንስንም ይዞ ቅስና ሾመው።

የቍስጥንጥንያ ሊቀ ጳጳሳትም በአረፈ ጊዜ ንጉሥ አርቃድዮስ ልኮ አስመጥቶ ቅዱስ ዮሐንስን በቍስጥንጥንያ ላይ ሊቀ ጵጵስና ሾመው አባቶቻችን ሐዋርያት እንደሚያደርጉት በሊቀ ጵጵስናው ሥራ ላይ ጸና ሕይወትነት በአላቸው ትምህርቶችና ተግሣጾች ሕዝቡን ሁልጊዜ የሚአስተምር ሆነ። ከኤጲስቆጶሳትም ሆነ ከመንግሥት ወገን ሕግን የሚተላለፉትን ሁሉ ይገሥጻቸዋል ማንንም አይፈራም ፊት አይቶም አያደላም።

የንጉሥ አርቃድዮስ ሚስት አውዶክስያም ገንዘብ ወዳጅ ስለሆነች የአንዲት ድኃ መበለት ቦታዋን በግፍ ወሰደች ያቺ መበለትም ወደ ቅዱስ ዮሐንስ መጥታ ንግሥት አውዶክስያ ቦታዋን እንደነጠቀቻት ነገረችው እርሱም የደኃዋን ቦታዋን መልሺላት ብሎ ከብዙ ምክር ጋር እንድትመልስላት ንግሥት አውዶክስያን ለመናት እርሷ ግን እምቢ በማለት አልታዘዘችለትም። ወደ ቤተ ክርስቲያን ገብታ ሥጋውን ደሙን እንዳትቀበል አውግዞ ለያት።

ቍጣንና ብስጭትንም ተመልታ ስለ ክፉ ሥራቸው ከሹመታቸው እርሱ የሻራቸውን ኤጲስቆጶሳት ሰበሰበች እነርሱም ንግሥቲቱን ስለ ተቃወመ ስደት እንደሚገባው በእርሱ ላይ ተስማምተው ጻፉ እርሷም አጥራክያ ወደ ሚባል ደሴት ሰደደችው።

ከዚያም በደረሰ ጊዜ የዚያች ደሴት ሰዎች በክፉ ሥራ ጸንተው የሚኖሩ ከሃድያን ሁነው አገኛቸው ቅዱስ ዮሐንስም አስተማራቸው ገሠጻቸውም በፊታቸው ስለ አደረጋቸው ድንቆች ተአምራት ወደ ቀናች ሃይማኖት አስገባቸው።

የሮሜ ንጉሥ አኖሬዎስና ሊቀ ጳጳሳቱ ዮናክኒዶስ ስለ ቅዱስ ዮሐንስ ስደት በሰሙ ጊዜ እጅግ አዘኑ በንጉሥ አርቃድዮስ ላይም በመቆጣት እንዲህ የሚል ደብዳቤ ጽፈው ላኩ ከዚህ ከክፉ ሥራ ተጠበቅ ትእዛዛችንንም ተቀብለህ የከበረ
ዮሐንስን ከስደቱ ከአልመለስከው በአንተና በእኛ መካከል ሰላም አይኖርም። መልእክታቸውንም በአነበበ ጊዜ እጅግ አዘነ ሚስቱንም አግዶ ልኮ ቅዱስ ዮሐንስን ከስደቱ መለሰው በተመለሰ ጊዜም የቍስጥንጥንያ ሰዎች በመመለሱ ታላቅ ደስታ አደረጉ። ከጥቂት ቀኖች በኋላም ንግሥቲቱ ወደ ክፋቷ ተመልሳ ሁለተኛ ወደ አጥራክያ ደሴት ሰደደችውና በዚያው አረፈ።

ንጉሥ አኖሬዎስና ሊቀ ጳጳሳት ዮናክኒዶስም በሰሙ ጊዜ መልእክትን ላኩ ሊቀ ጳጳሳቱም የከበረ ዮሐንስን ከስደቱ እስከምትመልሰው ድረስ ሥጋውንና ደሙን እንዳትቀበል አውዶክስያን አወገዛት። ከዚህም በኋላ የከበረ ዮሐንስን ይመልሱት ዘንድ ንጉሥ ላከ ግን ሙቶ አገኙት ሥጋውንም ተሸክመው ወደ ቊስጥንጥንያ ከተማ አደረሱት። የከበረ ዮሐንስም በተሰደደበት አገር እንደአረፈና ሥጋውንም ወደ ቍስጥንጥንያ ከተማ እንዳመጡ ወደ አባ ዮናክኒዶስ መልእክት ጽፈው አስረዱት። ሁለተኛም የሮሜ ሊቀ ጳጳሳት ወደ ቤተ ክርስቲያን ገብታ ሥጋውንና ደሙን እንዳትቀበል ልኮ አውድክስያን አወገዛት እየለመነችውም ስምንት ወር ያህል ኖረች በብዙ ልመናም ፈታት።

ነገር ግን ጭንቅ በሆነ ደዌ እግዚአብሔር አሠቃያት ያድኗት ዘንድ ገንዘቧን ለባለ መድኃኒቶች ጥበበኞች እስከ ሰጠች ድረስ ግን አልዳነችም ወደ ቅዱስ ዮሐንስ መቃብርም ሔዳ በእርሱ ላይ ያደረገችውን በደል ይቅር ይላት ዘንድ እየሰገደችና እያለቀሰች ለመነችው እርሱም ይቅር አላት ከደዌዋም ፈወሳት። ጌታችንም ከሥጋው ታላላቅ ድንቆች ታአምራትን ገለጠ።

ስለርሱም እንዲህ ተባለ በአንዲት ዕለትም ከንጉሥ አርቃዴዎስ ጋር ተቀምጦ ሳለ ንጉሡ እንዲህ አለው አባቴ ሆይ ስለ አንድ ቃል እንድታስረዳኝ እለምንሃለሁ። ይህም ቃል ከብዙ ጊዜ ጀምሮ በልቤ ውስጥ ይመላለሳል ወንጌላዊ ማቴዎስ ቅድስት ድንግል እመቤታችን ማርያምን የበኵር ልጅዋን እስከ ወለደች ድረስ ዮሴፍ አላወቃትም ስለምን አለ ወንዶች ሴቶችን እንደሚአውቋቸው ዮሴፍ አወቃትን አለው።
የከበረ ዮሐንስም ንጉሥ ሆይ እንዲህ አትበል እንዲህ አንተ እንደምትለው አይደለም የከበረች ድንግል እመቤታችንስ የክብር ባለቤት ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በሆድዋ ውስጥ በነበረ ጊዜ የእርሱ ኅብረ መልክ በሚለዋወጥ ጊዜ ከእርሱ ጋር መልኳ ይለወዋወጥ ነበር። በንጹሕ ብርሌ ውስጥ ውኃ በጨመሩ ጊዜ ውኃ መስሎ እንደሚታይ ወይን ጠጅም ቢጨምሩ ያንኑ መስሎ እንደሚታይ ወይም ከውስጡ በተጨመረው ቀይም ቢሆን ቀልቶ እንደሚታይ ቅጠልያም ቢገባበት ቅጠልያ መስሎ እንደሚታይ። ድንግልም በሆድዋ ውስጥ የልጅዋ መልክ በሚለዋወጥ ጊዜ ከእርሱ ጋራ መልኳ ይለዋወጥ ነበር። እንደ ሮማን አበባ የምትቀላበት ጊዜ አለ እንደ ናርዶስም የምታብለጨልጭበት ጊዜ አለ የለመለመ ቅጠል የምትመስልበትም ጊዜ አለ ከወለደች በኋላ ግን አልተለወጠችምና ዮሴፍ በአንድ በቀድሞው ኅብረ መልኳ ተወስናለት መልኳን ተረዳ ማለት ነው አለው። በዚያን ጊዜ በንጉሥ አዳራሽ ውስጥ ከወርቅ የተሠራ የእመቤታችን አምላክን የወለደች የድንግል ማርያም ሥዕል ነበረችና አፈ ወርቅ ዮሐንስ ልሳነ ወርቅ ዮሐንስ አፈ በረከት ዮሐንስ መልካም ተናገርክ የሚል ቃል ከእርሷ ወጣ።

ንጉሡና ከእርሱ ጋር ያሉት በሰሙ ጊዜ እጅግ አደነቁ እግዚአብሔርንም አመሰገኑት በዚያን ጊዜ ንጉሥ አዝዞ ወርቅ ሠሪ አስመጥቶ ለከበረ ዮሐንስ የወርቅ ልሳን አሠርቶ ለሚያየው ሁሉ መታሰቢያ ምልክት ሊሆን አምላክን ከወለደች ከእመቤታችን ከድንግል ማርያም ሥዕል ዘንድ ሰቀለው። ቅዱስ ዮሐንስንም ከዚያች ቀን ወዲህ ልሳነ ወርቅ ብሎ ጠራው አፈ ወርቅም ተብሎ እስከዛሬ ተጠራ።

ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን እኛንም በቅዱሱ ጸሎት ይማረን በረከቱም ከእኛ ጋር ትኑር ለዘላለሙ አሜን።

(#ስንክሳር_ዘወርኀ_ኅዳርና_ግንቦት)