አንተ ሰው እስኪ ንገረኝ!😐
አንድን የሥጋ ቁስል ለመፈወስ ለእያንዳንዱ ሰው ከባድ ነው፤ የነፍስን ቁስል መፈወስ ግን ለኹሉም ቀላል ነው፡፡ የሥጋ ቁስል ለመፈወስ መድኃኒት ብሎም ገንዘብ ያስፈልጋል፤ ነፍስን ለመፈወስ ግን ቀላል ብሎም ወጪን የማይጠይቅ ነው፡፡ ሥጋን ከዚያ ከሚያሰቃይ ቁስሉ ለመፈወስ አድካሚ ነው፡፡ ምክንያቱም በቀዶ ጥገና ምላጭ መቀደድ አለበት፤ መራራ መድኃኒቶችም ሊጨመሩበት ይገባል፡፡ ነፍስን ለመፈወስ ግን እንዲህ ዓይነት ነገር አያስፈልግም፡፡ ፈቃደኛ መኾን ብቻ በቂ ነው፤ ፍላጎቱ ካለ ኹሉንም ነገር ለማድረግ ቀላል ነው፡፡ የእግዚአብሔር መግቦቱም እስከ አሁን ድረስ ይህ ነው፡፡ ሥጋ ቢቆስል ያን ያህል ከባድ ጉዳትን አያመጣብንም፤ ምክንያቱም ምንም ባንታመምም እንኳን ሞት መጥቶ ይህን ሥጋችን ያፈርሷል፤ ያበሰብሷልምና፡፡ ነፍሳችን ብትታመም ግን ጉዳቱ ብዙ ነው፡፡ እግዚአብሔር የነፍስን ሕመም ለመፈወስ መድኃኒቱ ቀላል፣ ምንም ወጪና ስቃይ የሌለበት ያደረገውም ስለዚሁ ነው፡፡ ታዲያ ምንም እንኳን በሕመሙ ምክንያት የሚያገኘን ጉዳት ያን ያህል ብዙ ባይኾንም የገንዘብ ወጪን የሚጠይቀው፣ ሐኪም የሚያስፈልገው፣ ብዙ ስቃይ ያለበት ሥጋችን ሲታመም እርሱን ለማከም እጅግ የምንደክም ኾነን ሳለ፥ እጅግ ብዙ ጉዳት የሚያመጣውን፣ እርሱን ለመፈወስ ወጪ የማይጠይቀውን፣ ለማስታመም ሌሎች ሰዎች የማያስቸግረውን፣ እንደ ምላጩና እንደ መራራ መድኃኒቱ ስቃይ የሌለበትን ይልቁንም ከእነዚህ አንዱስ እንኳን ሳይፈልግ በእኛ ኃይል ባሉ ምርጫና ፈቃድ ብቻ መዳን የሚችለውን፣ ይህን ማድረግ ሳንችል ስንቀርም ከባድ ፍርድና ቅጣት ስቃይም እንደሚያገኘን በእርግጥ እያወቅን የነፍሳችንን ቁስል ችላ የምንል ከኾነ ሊደረግልን የሚችል ምሕረት እንደ ምን ያለ ምሕረት ነው? እኮ የምናገኘው ይቅርታ እንደ ምን ያለ ይቅርታ ነው?
ከዮሐንስ አፈወርቅ

✧ የሰውን ልጅ በቅዱሳን እጆቹ የቀረፀው ልዑል ፈጣሪ በተቀረፀበት ሰፋድል ፍጡሩ ያን የከበረ የሥጋ ክርታስ በቅቶ ሊቀረጽበት አይቻለውም!
እስኪ ልብ አድርጉ
እንኳን በአምላክ መጾር «በጳጳስ መንበር ቄስ ፣ በንጉሥ ዙፋን ራስ» ደፍሮ እንደማይቀመጥበት የእርሱንም ምዕራፈ ክብር ማንም አይጋራውም።
"ወይከውን ዘዚአሁ ምዕራፈ ክብር … ማረፊያውም የተከበረ ይሆናል።” [ኢሳ ፲፩፥፲]
የተመረጠው ፃድቅ ዮሴፍ ተከታይ ሞግዚቷ መንፈሳዊ አባቷ እየሆነ ፦ አማናዊት መቅደስ እናቱን ፣ ቅድስተ ቅዱሳን ትስብእቱን ሐዲስ ካህን ሆኖ ያገለገለ አረጋዊ ነው! እርሱ ምንም እንኳ በመጀመርያዋ መጽሐፍ (ብእሲቱ) በኩል ልጆች ማንበብ የሚያውቅ ቢሆንም የታተመችውን መጽሐፍ (እመ አምላክ ድንግልን) ግን በግብር አልደረሰባትምና ከመጠበቅ ውጪ እርሷን ማንበብ አይቻለኝም አለ!
“ ማንበብንም ለሚያውቅ፦ ይህን አንብብ ብለው በሰጡት ጊዜ እርሱ፦ ታትሞአልና አልችልም ይላቸዋል፤” [ኢሳ ፳፱፥፲፩]
ወደዓለም የመጣውን በኩር በሥጋ ያሳየች የበኩር እናት ተሰኘች እርሱም የበኩር ልጇ ተብሎ ተከታይ እንዳይኖረው ወልዳ ዘበኩር ተብሎ ተጠርቷል!
ይኽን ካልን ወደ ማሕፀኗ መውጣቱን ፣ በሥጋ እናቱ በምትሆን አርያም ዙፋን ማደሩን በተዋሕዶ አንድነት ምሥጢራዊ ዕርገት ይዘን ወደሰማይ ማረግ ካልነው ኋላ በአርባኛው ቀን በመርቀቅ ሳይሆን በመራቅ ከቅዱሳን ሐዋርያቱ ተለይቶ ወደላይ ሲወጣ ተመለከትንና ይኽንን (በረቀቀው ጽንሰት ስለተከወነ ዕርገት) በትህትና ያንን (በክብር ማረግ በተዋህዶ አካል ወደ ላይ መውጣቱን ) በልዕልና አልነው።
ሐዋርያው ያን በልዕልና የተፈፀመ ከትህትናው ሲለይ "ወአርገ በስብሐት ⇝ በክብር ያረገ ” (፩ኛ ጢሞ ፫፥፲፮) ሲለው ፤ ዳዊት ሁለቱን ሰማይ አካቶ ይኽን ሰማይ ያንን ከሰማያት በላይ ያለ ሰማይ ብሎ "ዘዓርገ ውስተ ሰማየ ሰማይ ዘመንገለ ጽባሕ " በማለት ገለጠው፤
↳ “በምሥራቅ በኩል ወደ ሰማየ ሰማያት ለወጣ ለእግዚአብሔር ዘምሩ፤ ” (መዝ. ፷፰፥፴፫)
በቅዱስ ኤጲፋንዮስ ቅዳሴ "በይእቲ ሥጋ ምስለ ኃይለ መለኮት ውስተ ሰማያት ዐርገ ኀበ ዘትካት ህላዌሁ ⇝ ከእናቱ በነሳው በዚኽ ሥጋ ከመለኮቱ ኃይል ጋር ወደ ቀደመ መኖርያው ወደ ሰማይ ዐረገ" እንዲል፤
————————————————————
ታቦተ መንፈስ ቅዱስ እመቤታችንን ስለምን ቀድሞ አስነሳት? ————————————————————
በፍለሰታው ሱባዕያት በሊቃውንቱ ቅዳሴ ማርያም ሲተረጎምልን እንደምንሰማው "ትምክሕቶሙ ለወራዙት ወደናግል ወመነኮሳት እለ ይተግሁ ውስተ አናቅጺሃ መዓልተ ወሌሊተ … በእርስዋ ደጃፍ (በራፍ) ሌሊትና ቀን ደጅ ለሚጠኑ ወጣቶች ደናግላንና መነኮሳት ትምክሕት ናት" ይላል ሊቁ አባ ሕርያቆስ።
በደጃፎችዋ በሚለው በሕዋሳቶቿ ለሚማጸኑ ትምክሕት ናት ይላል፤ ሕዋሳቶችዋን በሚያነሳ የሰውነት አባላቶቿን በሚያወሳ የመልክ ሰላምታ ለሚያወድሳት ትምክሕት ናት! ለምን? ለእርሱ ማደርያነት የተገቡ ናቸውና ለዘልዓለም ከብረው የሚኖሩ፤ ከፍጥረት ኹሉ ቀድመው ፈጣሪን በከዊን ያወቁና ፈጣሪን በግዘፍ ለፍጥረት ያሳወቁ ደጆች ፦ የተሸከመውን ማሕፀን፣ የጠባውን አጥባት፣ ያዘለውን ዘባን፣ ያቀፈውን እራኅ፣ በፈጣሪ የተሳመ መልታሕት… ከሌሎች ፍጡራን የአካል አባላት እና የሰውነት ሕዋሳት አብልጦ ይወዳቸዋል።
ልበ አምላክ ቅዱስ ዳዊት መዓዛ መለኮቱ የማይለያትን የሽቱ ሙዳይ “ያበድሮን እግዚአብሔር ለአናቅጸ ጽዮን ⇝ እግዚአብሔር የጽዮንን ደጆች አብልጦ ይወድዳቸዋል።” እንዳለ [መዝ ፹፮ (፹፯)፥፪] አብልጦ ይወዳቸዋልና እንደፍጡሩ ለመፍረስ ለመበስበስ አሳልፎ አልሰጠውም!
በእንዚናዙኑ ሊቅ ቅዱስ ጎርጎርዮስ ቅዳሴ ላይ "ለብሰ ሥጋ ዘይማስን ወረሰዮ ዘኢይማስን" እንደተባለ፤ ከሚፈርሰው ከእኛ ሰውነት የማይፈርሰውን ሕያው አምላክ ለማስገኘት የተመረጠችው የአብ መርዓት፣ የወልድ ወላዲት የመንፈስ ቅዱስ ታቦት የደጆችዋ መቆለፊያ በመቃብር መጥፋት በእሳትም መቃጠል ሳያገኛቸው ጸንተው ኖረዋል፤
“ጽዮንም ሆይ፥ ለአምላክሽ እልል በዪ፤ የደጆችሽን መወርወሪያ አጽንቶአልና " እንዲል [መዝ ፻፵፯፥፲፫]
ፀሐይን ያሠረቀች ዳግሚት ሰማይ፣ እግዚአብሔርን የወለደች እመ አዶናይ ፣ በሥጋና በኅሊና ዘልዓለም ድንግል የሆነች እግዝእትነ ማርያም፦
† በእነታውፋንያ ቁጣ የመጡ አይሁድ ሥጋዋን ለማቃጠል ያሰቡበት ምክር ስለምን ፈረሰ?
† በእሳት ያልጠፋውን ሥጋ "ወኢይገድፍ ምዕቅብናየ ⇝ አደራዬንማ አልተዋትም" ሲል ቅዱስ ዮሐንስ በንጽሕና በእጸ ሕይወት ሥር ሲያገለግላት መቆየቱ ለምነው?
ቀድሞ እሳት ያላቃጠለው ፣ ኋላም አፈር ያልበላውማ ስለሥጋዋ ክብር ነው እንጂ! ተረድተነውማ ቢሆን «ተቀብራ አልተነሳችም» ማለት "ወኢአማሰነ በልደቱ" እንዲል በልደቱ ያልለወጠውን የማደርያውን ክብር በሞት መፍረስና በመቃብር መበስበስ አግኝቶታል፤ አፈር ለውጦ አጥፍቶታል ወደማለት ያደርሳል! ላቲ ይደሉ ክብር ወስብሀት ወለወልዳ አምልኮ ወስግደት።

ለመቀላቀል👇
@Leoulu

+++ "እየጠላን የምናደርገው" +++
ብዙ ሰው ‹‹እኔ ሐሜት አልወድም፡፡ ግን ማማት የሚወዱ ጓደኞች አሉኝ›› ይላል፡፡ አሁን እርሱ ምን እያደረገ ነው? ‹‹ወዳጆቼ ሐሜተኞች ናቸው›› ሲል እያማቸው አይደለምን? ወይስ ለእርሱ ሲሆን ሐሜቱ ተለውጦ የመረጃ ቅብብል ይሆናል?! በነገራችን ላይ ይህ የዚህ ጽሑፍ መግቢያ ራሱ ሐሜት ነው።
የማንወደው ነገር ግን እየጠላንም ቢሆን የምናደርገው ኃጢአት ሐሜት ነው፡፡ በመጽሐፍ ቅዱስ ለመጀመሪያ ጊዜ ሐሜተኛ ሆኖ የተጠቀሰው በእባብ ያደረው ሰይጣን ነው፡፡ በመጀመሪያ የታማው ደግሞ እግዚአብሔር ሲሆን፣ ሐሜቱን ሰምታ ሳትመረምር የተቀበለችውና ለስሕተት የቸኮለችው ሴት ሔዋን ነበረች፡፡(ዘፍ 3፥1-5)
የሰይጣን ሐሜት እንዲህ በቀላሉ የሚታይ አይደለም፡፡ አንደኛ "አትሞቱም፤ እንደ እርሱ እንዳትሆኑ ነው የከለከላችሁ" በሚለው ንግግሩ "እግዚአብሔር ዋሽቷችኋል" እያለ ፍቅሩን እንድትጠራጠር እያደረገ ነው። ሁለተኛ ደግሞ ከዛፉ ብትበሉ እንደ እርሱ ትሆናላችሁ በማለት የእግዚአብሔር አምላክነት "የዛፍ ፍሬ" በመብላት የተገኘ መሆኑንና እርሱም እንደ እነርሱ የነበረበት ጊዜ እንዳለ እንድታስብ እየገፋፋት ነው። ታዲያ ከዚህ በላይ ስም ማጥፋት (Character assassination) ከየት ሊገኝ ይችላል? ሰይጣን በነገር ሁሉ ፍጹም የሆነን አምላክ ጆሮን ጭው የሚያደርግ ሐሰት ፈጥሮ ለማማት ወደ ኋላ ካላለ፣ አንዳች ጉድለት የማያጣብን እኛማ ከሐሜቱ ጅራፍ ልናመልጥ እንደማንችል ሊታወቅ ይገባል፡፡
በተለይ በአሁን ጊዜ ሐሜት በእያንዳንዳችን ልብ ውስጥ ሥሩን ሰድዷል። እንደውም ባልንጀራን ማማት እንደ ምግብ ቢሆን ኖሮ ብዙዎቻችን በዚህች ደሃ አገር ከመጠን በላይ ወፍረን እንቸገር ነበር። ማኅበራዊ ሚዲያዎቻችን የሐሜት አውድማዎች ሆነዋል። በየገጾቻችን ከሽነን የምናቀርባቸው ጽሑፎች ጠረናቸው የሰው ሥጋ የሰው ሥጋ ይላሉ። ፊታችን በሐሜት ወይቦ ሁለት መልክ ካወጣን ቆየን። ይኸው ሳንባችን በማማት አየር ተመርዞ ሳሉ ከበረታብን ሰነባብተናል። ወዳጃችንን የማናማበት ብቸኛው ጊዜ ከእርሱ ጋር የምንሆንበት ሰዓት ነው። ያውም ደግሞ ያንኑ ጊዜ ሌላኛውን ሰው ለማማት ካልተጠቀምንበት ማለቴ ነው።
ሊቁ ዮሐንስ ካዝያን እንደሚናገረው ሰው ከሚጠቅመው ቃለ እግዚአብሔር ይልቅ የማይጠቅመው ሐሜት ያጓጓዋል። የአምላክ ቃል ሲነገር እንቅልፍ እንቅልፍ የሚለው ሁሉ፣ የሐሜት ነገር ሲሆን ግን እንደ እርሱ ንቁ የሚሆን የለም። በጥፍሩ ቆሞ ይሰማል። ሌሊቱን ሁሉ ሳይተኛ ቢያድር ደስ ይለዋል።
ለመሆኑ ባልንጀራችንን ስለ ምን በቀስታ እናማዋለን? የወዳጃችንንስ ውድቀት በማውራት በእኛ ላይ የምንጨምረው ምን በጎ ነገር አለ? በሰው ፊት መልካም እየመሰልን ከኋላው ግን ስለ እርሱ ውድቀት በማውራት የራሳችንን ደረጃ ከፍ ማድረግ አይቻልም። ስለ ሌሎች በማውራት የምናጠፋውን ሰዓት ራሳችንን ለማሳደግ ብንጠቀምበት ኖሮ "መኖራችንን ትርጉም እንዲኖረው" ማድረግ ይቻለን ነበር።
"ንጹሕ ወዳጅነት" ሐሜትና ማሾክሾክ የሌለባት የታማኞች ጌጥ ናት። የሐሜት ስለታቸውን ያልጣሉ ሰዎች "እውነተኛ ባልንጀርነት"ን አያውቋትም። አንተ በፍቅር ወዳጅ አድርገህ ከፊትህ ስታቀርባቸው እነርሱ ከኋላህ ሆነው የሚያሙህን አትጥላቸው፤ አትጣላቸው። ነገር ግን የሐሜቱ እርሾ እንዳያገኝህ ቶሎ ተለያቸው። ከፊትህም አድርገህ አታሰቃያቸው። የእነርሱ ቦታ ከኋላህ መሆን ነው።
ሐሜት የሰይጣን ነው። ሰውን የሚያማ በገዛ ፈቃዱ አንደበቱን ለሰይጣን አሳልፎ የሰጠ ነው። ማማት በቤተ ክርስቲያን መለያየትን ያመጣል፣ ቤተሰብ ይበትናል፣ ወንድሞችን ያጣላል። ብንችል ስለ ሰው የምናውቀውን ጥሩውን እናውራ። የምናወራው ጥሩነት ከሌለው ደግሞ ቢያንስ ምንም አንበል።
ሔዋን ልክ እንደ አዳም እባብን "ሂጅልኝ" ብላ ብታባራት ኖሮ እነርሱም ከፈጣሪ ባልተጣሉ ሐሜትም ወደ ዓለም ባልገባ ነበር። ሐሜትን ማጥፋት ከፈለግን ሐሜተኛን እሺ አንበል። ማር ይስሐቅም "ወዳጁን በፊትህ የሚያንኳስሰውን ሰው አፉን መዝጋት ባትችል እንኳን ቢያንስ ሐሜቱን ከመስማት ተቆጠብ" ይላል። ሐሜትን ደስ ብሎህ ካልሰማኸው ደስ ብሎት የሚያማን ሰው ልትፈጥር አትችልም።
"ነገር ግን እርስ በርሳችሁ ብትነካከሱ ብትበላሉ እርስ በርሳችሁ እንዳትጠፋፉ ተጠንቀቁ" ገላ 5፥15
🌻🌼🌻🌼🌻🌼

እጅግ ክፉው ነገር በኃጢአት መውደቅ አይደለም፤ በዚያ ወድቆ መቅረት እንጂ፡፡ እጅግ አሳዛኙ ነገር ከወደቁ በኋላ ድጋሜ አለመነሣት፣ በሐኬት በስንፍና ተይዞ መቀለድ እንዲሁም የምግባር ጉድለትን በተስፋ መቁረጥ ካባን መሸፈን ነው፡፡ ባደረገው ኃጢአት ተስፋ የቆረጠ ክርስቲያን እንዲህ የሚለው የፈጣሪውን የረሳ ነው፦ "የወደቁ አይነሡምን? የሳተስ አይመለስምን?" /ኤር.8፥4/።
ከመቶ በጎች መካከል የጠፋ አንድ በግ ነበር፡፡ ያ በግ አስቀድሞም የተለየ በግ አልነበረም፤ እንደ ተቀሩት ዘጠና ዘጠኙ በጎች እንጂ፡፡ የኹሉም እረኛቸው አንድ ነው፡፡ ያ በግ ግን ከመንጋው ተለየ፡፡ ወደ ሩቅ ሀገር ተሰደደ፡፡ ወደ ሸለቆው ወረደ፡፡ ሣር እንደ ልብ ከሚያገኝበት፣ ውኃ እንዳሻው ከሚጎነጭበት ርቆ ሔደ፡፡ እረኛው ግን አልተወዉም፡፡ ዘጠና ዘጠኙ ይበቁኛል አላለም፡፡ ፈለገው፤ አገኘውም፡፡ ባገኘው ጊዜ ግን አልገረፈውም፤ አልተቆጣውም፤ በትከሻው ተሸክሞ ከዘጠና ዘጠኙ ጋር ደመረው እንጂ /ሉቃ.15፥4-5/፡፡ አንድ በግ የተባለው እኛው ነን፡፡ ዘጠና ዘጠኝ የተባሉት ቅዱሳን መላእክት ናቸው፡፡ እረኛ የተባለውም እግዚአብሔር ነው፡፡ በድለን ልንርቅ እንችላለን፡፡ በድለን ልንሸሽ እንችላለን፡፡ ፈጣሪያችን ግን ይፈልገናል፡፡ ዝም ቢለን ይበልጥ እንርቃለንና፥ አንድም በክፋት ላይ ክፋት እንጨምራለንና ዘጠና ዘጠኙን ትቶ እኛን ፍለጋ ይመጣል፡፡ እኛም ተስፋ ባለ መቁረጥ ንስሐ ገብተን ወደ እርሱ ብንመለስ ይቀበለናል፡፡ ወደ መንጋውም ይቀላቅለናል፡፡ አልቀላቀል ካልን ግን ዕድል ፈንታችን ፅዋ ተርታችን በአዳኝ ወይም በአውሬ መበላት ይኾናል፡፡
ቅዱስ አባት ሆይ! ይቅርታን ስለ ሠራህልን ክብር፣ ኃይልና ጌትነት ለአንተ ይኹን አሜን!!!

አንጋረ አበው!
1 ‹ራስህን በሐሰት አትውቀስ ራስን መክሰስ ትህትና
አይደለም ታላቁ ትህትና ሰዎች ሲወቅሱህ
መታገስ ነው።›› /ቅዱስ ስራፕዮን/
2 ‹‹የማታምንበትን ነገር ለሰው ስትል አትስራው
ከሰራኸው እንደምትጠፋበት እወቅ።›› /መጽሐፈ
ምክር/
3 ‹‹አንደበቱን ከቧልት ከሐሜት ያየውንም ሚስጥር
ከመናገር የሚከለከል ሰው ልቦናውን ከኀልዮ ኃጥያት
ያርቀዋል።›› /አረጋዊ መንፈሳዊ/
4 ‹‹ ጸጋ ቢሰጥህ በተሰጠህ ጸጋ አመስግን
ያልተሰጠህን እሻለሁ በማለት የተሰጠህን
እንዳታጣ።›› /ማር ይስሐቅ/
5 ‹‹ራሱን የሚንቅ የሚያቃልል ሰው ከእግዚአብሔር
ዘንድ እውቀትን ያገኛል አዋቂ ነኝ የሚል ሰው
ከፈጣሪው ‹ጥበብ ይለየዋል።›› /አረጋዊ መንፈሳዊ/
6 ‹‹እግዚአብሔር ሆይ አፈርና ትቢያ ሆኜ ሳለ ጻድቅ
አድርገው ከሚቆጥሩኝ ሰዎች አድነኝ።›› /አባ
እንጦንስ/
7 ‹‹ፍጡራንን መርምሮ ማወቅ ካልተቻልን ሁሉን
የፈጠረ እርሱን መርምሮ ማወቅ እንደምን
ይቻልናል።›› /ቅዱስ አትናቴዎስ/
8 ‹‹ወርቅ በእሳት እንደሚፈተን ሁሉ የክርስቶስንም
ፀጋና ክብር ሳይፈተኑ ማግኘት አይቻልም የዚህ ዓለም
ፈተናና እሳት ቶሎ ያልፋል ይጠፋል ኃጢያተኞች
የሚገቡበት የገሀነም እሳት ግን ለዘላለም እንደ ነደደ
ይኖራል።›› /ቅዱስ ሚናስ/
9 ‹‹በማንም ላይ ክፈትን አትስሩ አትፍርዱ ይህንን
ከጠበቃችሁ ርስቱን ትወርሳላችሁና።›› /ታላቁ አባ
መቃርስ/
10 ‹‹ብዙ ጊዜ ብዙ እናገራለሁ በመናገሬም አዝናልሁ
በዝምታዬ ግን ያዘንኩበት ጊዜ የለም።›› /ቅዱስ
አርሳንዮስ/
11 ‹‹ቤተክርስትያን መጠጊያችን ነች ቤተክርስትያን
የኖኅ መርክብ ነች በውስጧ እንጠለላልን ከውጭዋ
ግን ማዕበልና ቀላያት ተከፍተዋል።›› /ቅዱስ
እንድርያስ/
12 ‹‹ልባችንን ጠፊና በስባሽ ከኾነው ከምድራዊው
ምኞት አርቀን ከበደል በንስሐ ነጹሕ ካደረግነው በጸጋ
መንፈስቅዱስ የተሞላን እንሆናለን።›› /አባ አብርሃም
መፍቀሬ ነዳያን/
13 ‹‹ስጋዊ ፍላጎቶችን ማሸነፍ ለአክሊለ ህይወት
የሚያበቃ ሰማዕትነት ነው።›› /ብፁዕ አቡነ ጎርጎርዮስ
ካልዕ/
14 ‹‹የቤተክርስቲያን ህይወት በመስቀል ላይ ስለሆነ
ፈተና ይበዛበታል ስለዚህ ከግል ህይወታችሁ ይልቅ
የቤተክርስቲያናችሁን አቋም አጠንክሩ።›› /ብፁዕ አቡነ
ጎርጎርዮስ ካልዕ/
15 ‹‹ከመኝታህ በፊት የምታደርገውን ፀሎት ትተህ
እንድትተኛ መንፈስህ ሲገፋፋህ እሺ ብለህ
አትቀበለው፡፡ እንዲያውም መዝሙረ ዳዊትን ጨምርና
ሌሊቱን በሙሉ ስትፀልይ እደር።›› /ቅዱስ ይስሐቅ
ሶርያዊ/
16 ‹‹ኃጥያታችንን እኛ እያሰብን የምንፀፀት ከሆነ
እግዚአብሔር ይረሳልናል ኃጥያታችንን እኛ እረስትን
የምንፅናና ከሆነ እግዚአብሔር ያስብብናል።›› /ቅዱስ
እንጦስ/
በረከተ ቅዱሳን አበው አይለየን።አሜን
ወስብሐት ለእግዚአብሔር።
1 ‹ራስህን በሐሰት አትውቀስ ራስን መክሰስ ትህትና
አይደለም ታላቁ ትህትና ሰዎች ሲወቅሱህ
መታገስ ነው።›› /ቅዱስ ስራፕዮን/
2 ‹‹የማታምንበትን ነገር ለሰው ስትል አትስራው
ከሰራኸው እንደምትጠፋበት እወቅ።›› /መጽሐፈ
ምክር/
3 ‹‹አንደበቱን ከቧልት ከሐሜት ያየውንም ሚስጥር
ከመናገር የሚከለከል ሰው ልቦናውን ከኀልዮ ኃጥያት
ያርቀዋል።›› /አረጋዊ መንፈሳዊ/
4 ‹‹ ጸጋ ቢሰጥህ በተሰጠህ ጸጋ አመስግን
ያልተሰጠህን እሻለሁ በማለት የተሰጠህን
እንዳታጣ።›› /ማር ይስሐቅ/
5 ‹‹ራሱን የሚንቅ የሚያቃልል ሰው ከእግዚአብሔር
ዘንድ እውቀትን ያገኛል አዋቂ ነኝ የሚል ሰው
ከፈጣሪው ‹ጥበብ ይለየዋል።›› /አረጋዊ መንፈሳዊ/
6 ‹‹እግዚአብሔር ሆይ አፈርና ትቢያ ሆኜ ሳለ ጻድቅ
አድርገው ከሚቆጥሩኝ ሰዎች አድነኝ።›› /አባ
እንጦንስ/
7 ‹‹ፍጡራንን መርምሮ ማወቅ ካልተቻልን ሁሉን
የፈጠረ እርሱን መርምሮ ማወቅ እንደምን
ይቻልናል።›› /ቅዱስ አትናቴዎስ/
8 ‹‹ወርቅ በእሳት እንደሚፈተን ሁሉ የክርስቶስንም
ፀጋና ክብር ሳይፈተኑ ማግኘት አይቻልም የዚህ ዓለም
ፈተናና እሳት ቶሎ ያልፋል ይጠፋል ኃጢያተኞች
የሚገቡበት የገሀነም እሳት ግን ለዘላለም እንደ ነደደ
ይኖራል።›› /ቅዱስ ሚናስ/
9 ‹‹በማንም ላይ ክፈትን አትስሩ አትፍርዱ ይህንን
ከጠበቃችሁ ርስቱን ትወርሳላችሁና።›› /ታላቁ አባ
መቃርስ/
10 ‹‹ብዙ ጊዜ ብዙ እናገራለሁ በመናገሬም አዝናልሁ
በዝምታዬ ግን ያዘንኩበት ጊዜ የለም።›› /ቅዱስ
አርሳንዮስ/
11 ‹‹ቤተክርስትያን መጠጊያችን ነች ቤተክርስትያን
የኖኅ መርክብ ነች በውስጧ እንጠለላልን ከውጭዋ
ግን ማዕበልና ቀላያት ተከፍተዋል።›› /ቅዱስ
እንድርያስ/
12 ‹‹ልባችንን ጠፊና በስባሽ ከኾነው ከምድራዊው
ምኞት አርቀን ከበደል በንስሐ ነጹሕ ካደረግነው በጸጋ
መንፈስቅዱስ የተሞላን እንሆናለን።›› /አባ አብርሃም
መፍቀሬ ነዳያን/
13 ‹‹ስጋዊ ፍላጎቶችን ማሸነፍ ለአክሊለ ህይወት
የሚያበቃ ሰማዕትነት ነው።›› /ብፁዕ አቡነ ጎርጎርዮስ
ካልዕ/
14 ‹‹የቤተክርስቲያን ህይወት በመስቀል ላይ ስለሆነ
ፈተና ይበዛበታል ስለዚህ ከግል ህይወታችሁ ይልቅ
የቤተክርስቲያናችሁን አቋም አጠንክሩ።›› /ብፁዕ አቡነ
ጎርጎርዮስ ካልዕ/
15 ‹‹ከመኝታህ በፊት የምታደርገውን ፀሎት ትተህ
እንድትተኛ መንፈስህ ሲገፋፋህ እሺ ብለህ
አትቀበለው፡፡ እንዲያውም መዝሙረ ዳዊትን ጨምርና
ሌሊቱን በሙሉ ስትፀልይ እደር።›› /ቅዱስ ይስሐቅ
ሶርያዊ/
16 ‹‹ኃጥያታችንን እኛ እያሰብን የምንፀፀት ከሆነ
እግዚአብሔር ይረሳልናል ኃጥያታችንን እኛ እረስትን
የምንፅናና ከሆነ እግዚአብሔር ያስብብናል።›› /ቅዱስ
እንጦስ/
በረከተ ቅዱሳን አበው አይለየን።አሜን
ወስብሐት ለእግዚአብሔር።
ከቅዱሳን አንደበት ❤💜
✝ በሰው እጅ ያልተፈተለና ያልተሸመነ የደጋ ልብሳችን፣ የእርቃናችን መሸፈኛ፣ ጌጥ እና ክብራችን፣ ሊጡ አእምሮ የቦካበት አዲሱ እርሾ፣ አልጫውን ያጣፈጠ ጨው እርሱ ኢየሱስ ክርስቶስ ነው፡፡
/አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ/
✝ ሥጋን በንዳድ ሌላም ልዩ ልዩ ደዌ በያዘው ጊዜ ምንም ብርቱ ቢሆን እንደሚደክምና ከበሽታው በዳነ ጊዜ ግን ኃይሉ እንደሚመለስለትና እንዲሁ ነፍሱም በወጣትነት ወራት በደዌ ኃጢአት ትያዛለች፡፡ ትዕቢተኛነት፣ ሥጋዬ ይድላው ማለት በጾታ መፈላለግንና ይህን በመሳሰሉ ብዙ የምኞት ጣዕም ያድርባታል የእርጅና ወራት በደረሰ ጊዜ ግን ፈቃደ ሥጋን ፈጽሞ ከሰውነቱ ይርቃል፡፡
/ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ/
✝ ‹‹ሌሊት በህልም ከሴት ጋር የተገናኘህ /ዝሙት የፈጸምህ/ መስሎህ ዘር ቢወርድህ በመዓልት /በቀን/ አታስባት፡፡›› እንዲህ ማድረግህ ደግሞ በህልም የተመለከትከውን በእውን፣እያሰብከው ደስታ ከማድረግ ይጠብቅሃል፡፡
/ከመጽሐፈ መነኮሳት/
✝ ብፅዕት ማርያም፣ በእድሜ ትንሽ በመኖኗ ከሴቶች መካከል ተለይታ ቡርክት ለመሆን አልከለከላትም፡፡
/መጽሐፈ ፊልክስዮስ/
✝ በአፉ ከእግዚአብሔር በልቡ ከዓለም መነጋገሩ ከንጉሱ በፊት ቆሞ ሲነጋገር ዞሮ ከሌላ ቢጫወት ቅጣት እንደሚያገኘው እንዲሁም ልቡን ሳይጠቀልል የሚጸልይ ሰው አምላኩን የሚንቅ እና የሚያቃልል ስለሆነ ቅጣቱ እጅግ ያስፈራል፡፡
/ፍኖተ አእምሮ/

አንድ ደስ ሚሉ አባት እንዲህ አሉ
"ከውኃ እንዴት እንወለዳለን የሚል ሰው ካለ እንዴት ከአፈር ተወለድን ብዬ እጠይቀዋለው፡፡"

ተጎጂው ማን ነው?
ጓደኞቼ ልክ እንደኔ! ሌላ ሰው አደረሰብኝ የምትሉት ጉዳት ምንድነው? ተቆጣኝ ፣ ሰደበኝ፤ ያለ ስሜም የሆነ ስም ሰጠኝ የሚል ነው? ታዲያ ይኼ ምን ጉዳት አለው? በፍጹም ጉዳት የለውም፡፡ ምክንያቱም እነዚህ ነገሮች ጉዳቶች ሳይሆኑ ትዕግሥተኞች ከሆናችሁ ጥቅማቸው የበዛ ነው፡፡ ሲጀምር በእናንተ ላይ ጉዳት ለማድረስ የሚፈልገው ሰው የሚያደርገውን አያውቅም፡፡ የሚያደርገው ሁሉ ወዶና ፈቅዶ አይደለም፡፡ምንም እንኳን እናንተን የጐዳ ቢመስለውም ራሱን እየጐዳ ነው፡፡ የብዙዎቻችን ችግር ጐጂውና ተጐጂው ማን መሆኑን ለይተን አለማወቃችን ነው፡፡ ምክንያቱም ይኼንን ለይተን ብናውቅ ኖሮ ራሳችንን ለመጉዳት ባልተነሣሳን ነበር፤ ሌሎች ክፉ ይደርስባቸው ዘንድ ባልጸለይን ነበር፤ ማንንም መጕዳት እንደማንችል በገባን ነበር፡፡ ትልቁ በደል ደግሞ ክፉን መቀበል ሳይሆን በሌሎች ላይ ክፉትን መፈጸም ነው፡፡
ስለዚህ ከዛሬ ጀምራችሁ ሌላ ሰውን በድላችሁ ከሆነ ራሳችሁን ውቀሱ፤ ሌላው ክፉ አድርጐባችሁ እንደሆነ ግን ለእናንተ ያደረገው ነገር መልካም ነውና ጸልዩለት፡፡ ምንም እንኳን ሰውዬው እናንተን ለመጥቀም ብሎ ያደረገው ባይሆንም በመታገሣችሁ ግን ትልቅ ጥቅምን ታገኛላችሁ፡፡ ክፉ አደረገብኝ የምትሉት ሰውዬ ድርጊቱ ክፉ እንደሆነ ሰዎችም የእግዚአብሔር ቃልም ይፈርዱበታል፤ እናንተ ግን እንዲህ ስትታገሡ ለጊዜው ምንም የተጐዳችሁ ቢመስላችሁም ጌታ እንደተናገረ ዋጋችሁ በሰማያት ታላቅ ነው

ፍቅር ሲመነምን ውጤቱ የበዙ ጥፋቶችን ማስከተል ይሆናል!!
የፍቅር እጦት ቂም እና ጥላቻን ይፈጥራል። ይህ ደግሞ በኃጢአት ሐሴት ማድረግን ያመጣል። መጽሐፍ ቅዱስ እንዲህ ይላል፦ "ጠላትህ ቢወድቅ ደስ አይበልህ በመሰናከሉም ልብህ ሐሴት አያድርግ" ምሳ 24፥17
ሌላው የፍቅር እጦት ውጤት ቁጣ እና ክፋት ነው። እንዲህ ያለው ሁኔታ ስድብን፣ ጠብን፣ ግድያን፣ ነቀፋን፣ ማዋረድንና ስም ማጥፋት ማስፋፋትን ያስከትላል። ከዚህ በተጨማሪ የፍቅር እጦት ወይም ጉድለት ወደ ቅንዓት፣ ወደ አላዋቂነት፣ ወደ ኩራት፣ ወደ ጽናትን ማጣትና ወደ ጭካኔ ይመራል።
ለእግዚአብሔር የሚሆን ፍቅርን ማጣት በብዙ ጉዳዮች ውስጥ ሊገለጥ ይችላል፤ ከእርሱም መካከል ጸሎትን፣ መጽሐፍ ቅዱስንና ቤተ ክርስቲያንን መርሳት ጥቂቶቹ ናቸው። በእግዚአብሔር ፊት መቆምን ማጣት እና በእግዚአብሔር መንግሥት ፈጽሞ ሐሴት አለማድረግ ሌሎቹ ጉድለቶች ናቸው።
#ብጹዕ_አቡነ_ሺኖዳ_ሣልሳዊ

ሠላም ሠላም እንዴት ቆያችሁ ውድ የልዑል ትምህርት ቤት ተማሪዎች እኔ በፈጣሪ ቸርነት አለሁኝ።
ዛሬ የሥላሴ ፍቃድ ቢሆን ምንማማረው 👉👉👉👉 በስነ ፍጥረት ውስጥ አስደናቂ + አስፈሪ +3000 ክንድ ከስንዝር ቁመት ስላላቸው ፣ከሰው ልጅ ጋር ዝሙትን ፈፀሙ ስለሚባሉት መላእክት ይሆናል።👈👈👈👈👈
👈☝️☝️☝️☝️☝️
ኔፍሊም(ወይም በግእዙ ረዐይት) ወይንም የወደቁ መላእክት(the fallen angels )በመባል የሚታወቁ ናቸው ።ለመጀመርያ ክፍል የሚሆን ፅሁፍ አዘጋጅቼ ላቀርብላችሁ እየተዘጋጀሁ ስለሆነ በተስፋ እንድትጠብቁ እላለሁ፣
ሀሳብ አስተያየት ምክራችሁን 093069643/0969760409 ቴክስት በማድረግ እንዳስለመዳችሁት ጥያቄያችሁን ማቅረብ ትችላላችሁ
@Leoulu የቴሌግራም ቻናላችን ነው,join በማድረግ እንዲሁም ሼር በማድረግ የበኩላችሁን ተወጡ ፣ተማሩ እወቁ እንማማር! ሠናይ ጊዜ

በስመአብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሀዱ አምላክ አሜን!
😑😑 ኔፍሊም(የወደቁ መላእክት)ወይንም 😌
ከሰው ልጆች ጋር ዝሙት ፈፀሙ ሚባሉት መላእክት,) ክፍል 2
በቀደመው ክፍላችን እግዚአብሔር ረድቶን በመጀመርያው ዙር ወይም አለም በተፈጠረ ሰአት በሳጥናኤል ተንኮል ወይም እኔ ፈጠርኳችሁ፣ፈጣሪያችሁ እኔ ነኝ በማለቱ ምክኒያት ስለ ወደቁ ወደ ገሀነም ስለተወረወሩት መላእክት አይተናል ዛሬ ዛሬሬሬሬሬሬ ደግሞ ምናየው በሁለተኛው ዙር ማለትም በእነ ኖህ በእነ ሄኖክ በእነ ያሬድ ዘመን በሁለተኛ ዙር የወደቁት መላእክት እነማን ናቸው ?ምንድናቸው? የተከሰተው ምንድነው?የሆነውስ ምንድነው??በውኑ እነዛ መላእክት ናቸውን???ወይስ የሰው ልጆች ናቸው?? ስለወደቁት መላእክት ወይም ስለ ኔፍሊሞች በግእዙ ረዐይት ስለሚባሉት ይሆናል።
ኔፍሊም
ግማሾች ኔፍሊም ማለት ግዙፋን ወይም ረጃጅሞች ማለት ነው ሚሉ አሉ
ግማሾቹ ደግሞ መነሻው የእብራይስጥ ቋንቋ ነው።
"ነፈለ" ማለት መውደቅ ማለት ነው የሚሉም አሉ
ኔፍሊም እንግዲህ የወደቁ Gaint እንደሆኑ ነው ሚያሳየው።
ሚገርመው ስለ እነዚህ ረዐይት ወይንም የወደቁ መላእክት ወይም ስለ ኔፍሊሞች ለመጀመሪያ ጊዜ ፅፎ ምናገኘው የአዳም 7ተኛ ትውልድ የሆነው ሄኖክ ነው ።
እንግዲህ መፅሀፈ ሄኖክ ስለ እነዚህ በዝርዝር የፃፈ የመጀመርያው ፅሁፍ ነው ።ግንንንንንን መፅሀፈ ሄኖክ በብዙ ሀገር ተቆራርጦ ፣ተከፋፍሎ ያለ እንጂ እንደ ኢትዮጵያ በምልአት ወይም በሙሉ መዝገብነት ያተገኘ አልነበረም፣
ኢትዮጵያ ግን ለብዙ ዘመናት ይህ መፅሀፍ ሲነበብ፤ ሲተረጎም፣ሲመሠጠር፣ሲራቀቅ፣ሲተነተን ,በሊቃውንቱ እጅ ስለነበር መፅሀፈ ሄኖክ ለኢትዮጵያውያን እንግዳ አልነበረም፣
በኋላ በ 18ተኛው መቶ ክፍለ ዘመን ጀምስ ብሩስ ይህን መፅሀፍ ይዞ ከኢትዮጵያ ስለሄደ በተለይ መፅሀፈ ሄኖክን በመውሰዱ ጥናቱ ደግሞ የበለጠ እነዲስፋፋ ለባህር ማዶ አጥኝዎች ክፍት ሆኖላቸው እንደገና የኔፍሊም ጉዳይ በጣም በጣም እንደገና ብድግ ብሎ እስከዛሬ ድረስ ያልተቋረጠ ምርምር እና ጥናት እየተካሄደበት ይገኛል.....
ይቀጥላል ትንሽ ጠብቁ

....የቀጠለ... ክፍል 2.ኔፍሊም
ስለ መፅሀፈ ሄኖክ ብዙ ማውራት እንችላለን ግን ለሌላ ጊዜ እናድርገውና ስለ ኔፍሊሞች ብንቀጥል መልካም ነው ብዬ አስባለሁ።
እና ....
መፅሀፈ ሄኖክ ትኩረት ተፈልጎ እንዲመረመር ወይም እንዲመሰጠር ካደረገው ነገሮች አንዱ ስለ ዘመን ቀመር ስለ ስነ ከዋክብት(አስትሮኖሚ) እና ስለ ብዙ ነገሮች የፃፈ መፅሀፍ መሆኑ ነው ።
ሌላው ከመፅሀፈ ሄኖክ በጣም ጥኩረት ከሳበው መካከል ሄኖክ ስለ ኔፍሊሞች የተናገረው ነገር በጣም በአለምአቀፍ ደረጃ ከፍተኛ ትኩረትን ስቦ ምርምሩ ቀጠለ፣ ምርምሩ ሰፋ፤ብዙ ጥናቶች መቅረብ ጀመሩ ማለት ነው።
በመጀመርያ የአዳም 7ተኛ ትውልድ የሆነው ሄኖክ ስለኔፍሊሞች እንደዚህ ብሎ ፅፏል
መፅሀፈ ሄኖክ ምእራፍ 2
"የሰው ልጆች ከበዙ በኋላ እንዲህ ሆነ፣በእነዚያ ወራት መልከ መልካሞችና ደመ ግቡዎች ሴቶች ልጆች ተወለዱላቸው ፣የሰማይ ልጆች መላእክትም እነርሱን አይተው ወደዷቸው፣እርስበርሳቸውም "ኑ ለእኛ ከሰው ልጆች ሴቶችን እንምረጥ፣
ለእኛም ልጆችን እንውለድ"አሉ
ይቀጥልና ሄኖክ ከታች ቁጥር ስምንት ላይ የእነዚህ አለቃ ስማዝያ እንደሚባል ፤ቁጥራቸውም ደግሞ ወደ 200 እንደሚጠጋ ጭምር ነው የፃፈው እና ስማቸውን በዝርዝር ፅፏል እዛ ላይ ማየት ትችላላችሁ። በተለይ ያስተማሩትን በጣም በጣም ክፉ አግዚአብሔር የማይወደውን ስራም ታዩታላችሁ
ሚስቶች ካገቡ በኋላ ደግሞ ሚስቶቻቸው ፀንሰው የወለዱት ልጆች ደግሞ ረዐይት ወይንም ኔፍሊሞችን እንደወለዱና ቁጥራቸው ወደ 👉👉3000 👈👈ክንድ በጣም አስተውሉ የሰው ልጅ 👉3👈ክንድ ከስንዝር አለው ይባላል እነዚህ ግን በ ሺህ ነው ያጠፉት።እና እነዚህ እንደተወለዱ ይፅፋል።
እነዚህም ለሰዎች መነገር መገለጥ የሌለበትን በጣም secret የሆነ ነገር፣ ምስጢራዊ ነገሮች ሁሉ መንገር እና መግለጥ እንደጀመሩ፣
በተለይ በተለይ ካስተማሩት መካከል ተውላጣ አለም የሚለው በጣም ይገርማል የአለም ለውጥ ይላል ፣እና 👉👉የአንዱን ፅንስ በሌላው ላይ ማሳደር 👈 ይሄ ትልቅ እና ከባድ ነገር ነው፣፣መተርጉማን ሊቃውንት ሲናገሩ ሰውን በቅሎ እና ፈረስ ማድረግ፣ እና ደግሞ ፈረስ እና በቅሎን ሰው ማድረግ ፣ዠ
ዛሬ በ genetics እውቀት በጣም ብዙ ብዙ ነገሮች እየተደረጉ እንደሆነ በተለያዩ ሚድያዎችና ድረ ገፆች እንሰማለን፣በጣም እግዚአብሔር ከጠላቸው ስራ መካከል አንዱ ይሄ ነበር የነበረ፣
👉የሰውን ዘር ወስደው ፈረስ በቅሎውስጥ የማድረግ ነገር 👈 👉የእነዛን ዘር ወስዶ ደግሞ ሰው ውስጥ የመክተት ነገር።በዛም በጣም Hybride የሆኑ አስፈሪ ክርኤቸሮች( Creatures)
እንዲወጡ ይደረጋሉ።
እንደውም አንዳንድ አጥኚዎች ዛሬ ጭራቅ፣ሰበዳኣት ምናምን የሚባሉ ነገሮች ያን ጊዜ በነበረው የአንዱን ጂን (ዘረመል)ወደ አንዱ በመክተት ፍጥረታትን corrupt/ከነበሩበት ተፈጥሮአዊ መዋቅር ወደ ሌላ መዋቅር የመስራት፣
👉👉👉DNAን የማዛባት ስራ ያኔ በረዐይት(በኔፍሊሞች )ጊዜ ነበር የተጀመረው፣
👉👉ወንድሞቼ ያ ጊዜ በጣም ከባድ ጊዜ እንደሆነ እወቁ ፣ቀላል እንዳይመስላችሁ ከባድ ነገሮችን ነው መግለጥ የጀመሩት፣ ከባድ ቅይይሮሽን ነው መስራት የጀመሩት።
........ ይቀጥላል.........
👇👇👇👇
👉👉 @Leoulu 👈👈
👉👉 @Leoulu 👈👈
👉👉 @Leoulu 👈👈
👉👉 @Leoulu 👈👈
☝️☝️☝️☝️

ከዛ ይቀጥልና መጽሀፈ ሄኖክ እንዲህ ይላል ከመላእክት ሩፋኤል ከእግዚአብሔር ተልኮ ውጊያ ያስተማራቸውን የኔፍሊሞች አለቃ አዛዝኤልን እጅና እግሩን አስሮ 👉ዱዳኤል👈በምትባል ቦታ የነበረች ምድረበዳን ከፍቶ ጨለማ ውስጥ እንዳሰረው ፣በላዩም ጠማማና ሻፎ ሚባሉ ወይም ስልስል ድንጋዮችን እንደገጠመበት፣እክከ ፍርድ ቀን ድረስ ብርሀንን እንዳያይ እንደሸፈነው ሄኖክ ጨምሮ ፅፏል።በተለይ ይህን ምታነቡ እህት ወንድሞቼ ምእራፍ 2ት እና 3ትን በደንብ እንድታነቡ እነግራችኋለሁ
ሌላው ደግሞ 70 ትውልዶች የሚጠጉትን እንደገና በምድር ኮረብታ በታች ደግሞ እንደታሰሩ ጭምር ይናገራል።ከዛ በኋላ ከእሳቱ በታች ወዳለ ጭንቅ ቦታ እንደሚወሰዱና በግዞት ቤት ይዘጋባቸዋል የሚል በጣም በጣም ምስጢራዊ የሆነ ነገርን ፅፏል፣ 🙄😯🤔🤔70ው ትውልዶች ማን ናቸው?
አዛዝኤል ዱድኤል የምትባለው ቦታስ የት ናት?ሻፎ ድንጋይ የተገጠመበት ቦታ ምንድናት??????
ይህ ሁሉ ሚስጥር ነው።
እና መፅሀፈ ሄኖክን የሚያጠኑ ሁሉ እነዚህን ሁሉ ምስጢሮች ሁሌ ያብሰለስላሉ እና የኔፍሊም ጉዳይ ይህ ብቻም አይደለም 👉👉ነቢየ እግዚአብሔር ሙሴም እንደገና ጨምሮ ይፅፋል።
እንዲህ ሆነ ይላል በተለይ ኦሪቱ ላይ "ሰዎች በምድር ላይ መብዛት በጀመሩ ጊዜ ሴቶች ልጆች ተወለዱላቸው፣የእግዚአብሔር ልጆችም የሰውን ሴቶች ልጆች መልካሞች እንደሆኑ አዩ፣ከመረጧቸውም ሚስት ለራሳቸው ወሰዱ "በማለት ይፅፋል ,,,,,,,,ዘመኖቻቸውም ደ 120 ዘመን እግዚአብሔር እንደወሰነባቸው ፣ልጆችም በወለዱ ጊዜ ስማቸው ሀያላን ተብሎ እንደተጠራ ሰፋ ያለ ፅሁፍ በተለይ ዘፍጥረት 6 አከባቢ ላይ ፅፏል፣ይሄ ሁለተኛው Source ነው የመጀመርያው ሄኖክ ሁለተኛው ዘፍጥረት ማለት ነው!
ሌላ ሦስተኛው ሶርስ ኩፋሌ ነው፣ኩፋሌም ተመሳሳይ ነገር ነው ሚፅፈው፣"የአዳም ልጆች በምድር ላይ ይበዙ ዘንድ በጀመሩ ጊዜ እንዲ ሆነ፣ሴቶች ልጆች ተወለዱላቸው 👉፣የእግዚአብሔር መላእክትም👈በዚህ ኢዮቤልዮ በአንዲቱ አመት እነዚህን አዩአቸው ።እነዚህም ላዩአቸው መልከ መልካሞች ነበሩ፣ከመረጧቸውም ሁሉ ሚስቶች እንዲሆኗቸው ወሰዷቸው ፣ወንዶች ልጆችንም ወለዱላቸው፣እነዚህም ረዐይት ናቸው "በማለት ኩፋሌ ቁጭ አድርጎ ፅፎታል ።
ስለዚህ የእግዚአብሔር መላእክት ፣የእግዚአብሔር ልጆች ወዘተርፈ ተብለው ተጠርተዋል በእነዚህ 3ት ታላላቅ መፃህፍት ፣ማለትም በ ሄኖክ ፣ዘፍጥረት ፣እና ኩፋሌ
.......ይቀጥላል
👇👇👇👇
👉👉 @Leoulu 👈👈
👉👉 @Leoulu 👈👈
👉👉 @Leoulu 👈👈
👉👉 @Leoulu 👈👈
☝️☝️☝️☝️
https://telegram.me/Leoulu

Telegram
የሥላሴ ባርያ የልዑል ት/ት ቤት
ሥላሴ ትትረመም ወትትነከር
እንግዲህ ጠቅለል አድርገን ስናየው እይታው ለ 3 ተከፍሏል
👉1 የመጀመርያው ወይም አንደኛው እይታ ፣የወደቁ መላእክት ናቸው እንጂ በፍፁም ሰዎች አይደሉም የሚል 1 ምልከታ አለ፣the fallen angels ናቸው፣መላእክት ናቸው እንጂ ከሰው ልጆች ጋራ የተዋለዱት ሰዎች አይደሉም የሚል 1 ምልከታ አለ
👉2 ሁለተኛው ምልከታ ፣የሴት ልጆችና የ ቃየል ልጆች ናቸው እንጂ መላእክት እዚህ ውስጥ አልገቡም የሚሉ ደግሞ ሁለተኛ አመለካከት አለ
👉 3 ሦስተኛው አመለካከት ምንድነው፣ስጋ እንዲለብሱ የተደረጉ መላእክት ናቸው ነው ሚለው፣
አሁን ለ 3 ከፍለን ሰፋ አድርገን ነው የምናየው፣እንደ አጥኚ ሁሉን ነገር ማየት፣ማወቅ፣መመርመር፣መፈተሽ በተፈጥሮ የተሰጠን ስጦታ መሆኑን ማወቅ ይገባል እንጂ እንደማንም ጭፍን ጭፍንፍን ያለ ሰው ልንሆን አይገባም፣
እንዳልኳችሁ 3ት እይታ አለ፣እናነጥራለን፣እንፈትሻለን፣መልካም የሆነውን እንይዛለን ማለት ነው።
እነዚህን እይታዎች ነገ በሰፊው እንደምናይ ሙሉ እምነቱ አለኝ ፣መልካም ቆይታ ።
ሰላመ እግዚአብሔር አይለያችሁ በያላችሁበት በርቱ።

ክፍል 3 # ኔፍሊም ...የቀጠለ
👉👉1 የመጀመርያው ምልከታ እንግዲህ የወደቁ መላእክት ናቸው ፣ሰዎች አይደሉም እነዚህ፣ሁለት መቶ ከሰማይ የመጡት እነዚህ መላእክት ናቸው ካሉት ከጥንቶቹ ሊቃውን መካከል Tertulian (ጠርጠሉስ) የሚባል አንድተጠቃሽ ነው ። በተለይ ከ 240ዎቹ ጀምሮ የነበረ ከ 𝖆𝖓𝖈𝖎𝖊𝖓𝖙 𝖈𝖍𝖚𝖗𝖈𝖍 𝖋𝖆𝖙𝖍𝖊𝖗𝖘 መካከል የነበረ አንዱ እሱ ይጠቀሳል።
ሌላው ግን ከ 250-325 የነበረው 𝖑𝖆𝖈𝖙𝖆𝖓𝖙𝖆𝖓𝖎𝖚𝖘(ላክታንታኒዩስ) የተባለው ተጠቃሽ ነው። እንግዲህ እነዚህ ተመራማሪዎች በፅሁፎቻቸው 𝖋𝖆𝖑𝖑𝖊𝖓 𝖆𝖓𝖌𝖊𝖑𝖘 ወይም የወደቁ መላእክት ናቸው፣ከሰው ልጆች ጋር ተዋልደው እነዚህን ያስገኙት ሚሉት፣
እንግዲህ የእነዚህ የሁለቱ ተመራማሪዎች 𝖆𝖗𝖌𝖚𝖒𝖊𝖓𝖙 ወይም ክርክራቸው ምንድነው (𝖆𝖗𝖌𝖚𝖒𝖊𝖒𝖙1)👉1👈 3000 ክንድ ቁመትን በምንም አይነት ተአምር ከሰው ሊገኝ አይችልም ነው የእነዚህ እይታ፣ሰው 3ክንድ ከስንዝር ነው፣ 3ክንድ ከ ስንዝር ምንም ያህል ሀጥያት ቢሰራ ፣ቢዋለድም እስከ 3000 ሊረዝሙ የሚችሉ ደመና ሊነኩ የሚችሉ ፍጡራንን ሊያስገኙ አይችሉም ብለው ይሟገቱና ይከራከሩ ነበር፣እንግዲህ ይህ አንዱ እይታ ነው።።።በፍፁም ሰውች ከ3ክንድ ከስንዝር ያለፈ 3000 ክንድ ማድረስ አይችሉም ስለዚህ እነዚህ 𝖋𝖆𝖑𝖑𝖊𝖓 𝖆𝖓𝖌𝖊𝖑𝖘 የወደቁ መላእክት ናቸው እንጂ ሰዎች አይደሉም ነው ሚሉት.........
🙏💜ሁሉም እንግዲህ ለእነዚህ ቅዱሳት መጻህፍትን ይጠቅሳሉ ለዚህ ምርምራቸው ።እኛ የሁሉንም ሀሳቦች ቀንጨብ አድርገን ለማየት እንሞክራለን ፣እናያለን፣እንፈትሻለንም፣
👉👉
👉እዚችጋ በማስተዋል አንብቡ 👈👈 👉👉እንግዲህ እነሱ ሚሉት ምንድነው በ 2ኛ ጴጥ 2÷4-5 ላይ ስለ ኖህ ፅፎ ,አከታትሎ ስለ እነዚህ መላእክት ፅፏል ነውሚሉት ጴጥሮስን፣
ምነድነው ሚለው "እግዚአብሔር ሀጥያትን ላደረጉ መላእክት ሳይራራላቸው ወደ ገሀነም ጥሎ በጨለማ ጉድጓድ ለፍርድ እንዲጠበቁ አሳልፎ ሰጣቸው፣ለቀደመው አለም ሳይራራ 👉?እዚጋ ከኖህ በፊት አንድ አለም ነበረ አለ ማለት ነው 👈
"ለቀደመው አለም ሳይራራ ከሌሎች ሰባት ጋር ፅድቅን የሚሰብከውን ኖህን አድኖ በሀጥያተኞች አለም ላይ የጥፋትን ውሀ ካወረደ "ብሎ ጠቅሷል ነው ሚሉት ስለዚህ በኖህ ዘመን የመጡት ፣👉ኖህን አከታትሎ ጠቅሶ ፣መላእክት አስቀድሞ መናገሩ 👈 እነዚህ ከወረዱ በኋላ ነው የጥፋት ውሀ የመጣው የሚል እሳቤ ኢሄን ይዘው አስተምረዋል ፣ሌላው እንደገና ይሁዳ 1÷6 ላይ
"መኖርያቸውን የተውትን እንጂ የራሳቸውን አለቅነት ያልጠበቁት መላእክትን በዘለአለም እስራት ከጨለማ በታች እስከ ታላቋ ፍርድ ቀን ድረስ ጠብቋቸዋል " የሚለውን ይይዙና ፣በሄኖክ ዘመን ሻፎ ድንጋዮች ተገጠመባቸው ፣ግዞት ቤት ታሰሩ የሚለውን መኖርያቸውን ትተው የመጡ መላእክት ናቸው ፣በይሁዳ የተፃፉት ብለው ይጠቅሳሉ እነ 𝖙𝖊𝖗𝖙𝖚𝖑𝖆𝖓 እነ ,,𝖑𝖆𝖈𝖙𝖆𝖓𝖙𝖆𝖓𝖎𝖚𝖘
ሌላው የሚጠቅሱት አንድ ዶክመንት አለ በተለይ የቁምራን 11 ዋሻዎች በሚከፈቱበት ጊዜና እነዛ ዶክመንቶች ሲወጡ ""D𝖆𝖒𝖆𝖘𝖈𝖚𝖘 𝖉𝖔𝖈𝖚𝖒𝖊𝖓𝖙" (የደማስቆ ሰነድ) የሚባሉት እነዚህ ሁሉ የሚያስረዱት እነዚህ ሰዎች ሳይሆኑ ቦታቸውን ለቅቀው የወረዱ 200 መላእክት ነበሩ ብለው ነው ሀሳባቸውን ያስቀመጡት,,,,,,,,,,
👉💜👉💜ይህ 1ኛው ምልከታ መሆኑን ብቻ እወቁ እንዳትረሱ 3ት ምልከታ ነው ያለው,👈💜👈💜
........ይቀጥላል....
ስብሀት ለእግዚአብሔር ኪያነ ዘፈጠረ ከመ ናምልኮ💜
ስብሀት ለማርያም እመ አምላክ እግዚእትነ ወመድሀኒትነ💜
ስብሀት ለመስቀለ ክርስቶስ እፀ መድሀኒት ሀይልነ ወፀወንነ💜
ሰላመ እግዚአብሔር አይለያችሁ
አንብቡ ተመራመሩ ጥቅስ እየጠቀሳችሁ ብቻ እንደ አዋቂ ነን ባዮች አትሁኑ ። የመፅሀፍ ቅዱስን ጥቅስ ማወቅ መጥፎ ነው ማለቴ ግን አይደለም፣፣ፍሬ ነገሩን ነው እንጂ ፣መፅሀፍ ቅዱስ ቀለል ተደርጎ ሚነበብ ስድ ንባብ ወይም ድርሰት አይደለም ፣በማስተዋል በማራቀቅ እና በመሠጠት በውስን ሰዎች ብቻ ሚፈታ በወርቆች የተሳሰረ ቅኔ ነው። ፣ህብረቃሉን ብቻ እያነበባችሁ ሆ አትበሉ ፣መጀመርያ ጠይቁ፣ለምሰሌ ስጋ ምትለዋን ቃል መፅሀፍ ቅዱስ ላይ ስታገኙ ወይም ስናገኝ ሆዳም ስለሆንን እና(ወይም) ምግብ ስለመሰለን(ስለወደድን)ሚበላ ስጋ ብለን እንተረጉማለን! እንደዛ አይደለም መፅሀፍ ቅዱስ ሚነበበው ፣በርግጥ ስጋ ማለት ሚበላ የምግብ አይነት ነው፣ሚስጥራዊ ፍቹ ግን ለነፍስህ ስጋ ፣ፍራ ማለትም ነው ፣ማስጠንቀቅያ ነው እና ወዘተርፈ፣ ፣ሊቃውንቱ በአንድምታ በምኑ ያስቀምጣሉ ፣ስለዚህ ጠይቁ ፣"መጠየቅ ያደርጋል ሊቅ"

መስጠት ወይም ልግስና ትእዛዙን ሟሟላት ብቻ አይደለም መጽሐፍ ቅዱስ "እግዚአብሔር በደስታ የሚሰጠውን ይወዳልና።" /2ቆሮ 9፥7/ እንዲል። እግዚአብሔር የምትሰጠውን ገንዘብ ሳይሆን የመጀመሪያውን ፍሬ እና ቃል ኪዳን የሆነውን ከማዕረጎች ሁሉ የሚልቀውንና ያለ ነቀፋ በነፃነት የሚሰጠውን ፍቅር ከአንተ ይጠብቃል።
ፍቅር የመንፈስ ቅዱስ የመጀመርያ ፍሬ ነው። ስለዚህ ጌታ የኤፌሶንን ቤተ ክርስቲያን በነቀፋ ንሥሓም እንዲገባ በጠራው ጊዜ ነቀፋውን የተወሰነ ኃጢአትን በመግለጽ ሳይሆን በአንድ ሐረግ አጠቃልሎ "ዳሩ ግን የምነቅፍብህ ነገር አለኝ የቀደመውን ፍቅርህን ትተሃልና።" /ራዕ 2፥4/ በማለት ነው።
እግዚአብሔር ይህንን ፍቅር ይፈልጋል ስለዚህ "ልጄ ሆይ ልብህን ስጠኝ ዓይኖችህም መንገዴን ይውደዱ።" /ምሳ 23፥26/ አለ። ትእዛዙን መፈጸም የፍቅር ተፈጥሮአዊ ፍሬ ነው።
ውጪያዊ የንሥሓ ሕይወት ብቻ የሚኖሩ ነገር ግን ውስጣዊ ፍቅር የሌላቸው ይወድቃሉ። ምክንያቱም ሥራዎቻቸውና ከእግዚአብሔር ጋር ያላቸው ግንኙነት ፍቅር የጎደለው ነውና።
መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ከሕግ ማንኛይቱ ትእዛዝ ታላቅ ናት? ተብሎ ለተጠየቀው ጥያቄ የሰጠው መልስ "ጌታ አምላክህን በፍጹም ልብህ በፍጹም ነፍስህም በፍጹም አሳብህም ውደድ፣ ታላቂቱና ፊተኛይቱ ትእዛዝ ይህች ናት። ሁለተኛይቱም ይህችን ትመስላለች እርሷም ባልጀራህን እንደ ነፍስህ ውደድ የምትል ናት። ኦሪትና ነቢያት በነዚህ በሁለቱም ትእዛዛት ጸኑ።" /ማቴ 22፥36-40/ የሚል ነበር።
በዚያን ቀን ብዙዎቹ "ጌታ ሆይ በስምህ ትንቢት አልተናገርንም በስምህ አጋንንት አላወጣንም?" /ማቴ 7፥22/ ይሉታል። ነገር ግን እርሱ ይህን ሁሉ ትቶ በውስጣቸው ስላለው ፍቅር ይጠይቃቸዋል።
ይህ የተአምራት እና የስጦታዎች ችግር አይደለም፣ ባሏቸው በተሰጡአቸው ስጦታዎች የተነሳ የሚጠፉ ብዙዎች ናቸውና። ለዚያ ነው ሐዋርያት ስለመንፈሳዊ ስጦታዎች ባወሩ ጊዜ ሁሉ ይህንን ከሁሉ ይልቅ በተሻለ መንገድ አብራርተውታል።
#አብነ_ሺኖዳ_ሣልሳዊ

ከምን ዓይነት ነገር መላቀቅ እንዳለብህ ታዉቃለህ ??
ብጹዕ ወቅዱስ አቡነ ሺኖዳ ሳልሳዊ ምድራዊ ምኞት ምን ያህል አስከፊ እንደሆነና እንዴት ከዚህ ነገር ነፃ መውጣት እንዳለብን እንዲህ በማለት ይመክሩናል፦
"ወዳጄ ከምድራዊ ምኞትህ ተላቀቅ ከምን አይነት ነገር መራቅ እንዳለብህ ታውቃለህ? ከምድራዊ ፍላጎት ከመሳሰሉት ራቅ ፍፁም የመንፈስ ነፃነት እንዲኖርህ ከፈለክ ከምድራዊ ምኞቶችህ ተላቀቅ።
በእርጋታና በግልጽነት ላውጋህ እጅግ አብዝተህ የምትጨነቅባቸው ልብህን የተቆጣጠሩት ታላላቅ ምድራዊ ተስፋዎች አሉህ።
እነኚህም ሃሳብህን ሁሉ ይቆጣጠሩታል ብቻህን በምቶንበት ጊዜ በምናብ ይመጡብሃል በምትተኛ ጊዜ ህልምህ ሁሉ ይህ ይሆናል ልትክዳቸው የማትችለው ነገር ግን የምታውቃቸው ምድራዊ አላማዎች አሉህ። ተፈላጊነት እንዲኖርህ ትመኛለህ፣ ስልጣን እንዲኖርህና፣ ኃያል እንድትሆን፣ ዕውቅና እንዲኖርህና ስምህ ከጽንፍ እስከ አጽናፍ እንዲናኝ ትፈልጋለህ።
በሀብት፣ በምድራዊ ስልጣን፣ በዕውቀት በማዕረግና በመልክ ዝነኛ የመሆን ተስፋ አለህ ፣ በመኖሪያ ቤት፣ በምግብ፣ በልብስና በሰውነት ደስታን በሚሰጡ ነገሮችም ተስፋ አለህ።
ዓለም በአንተ እንጂ አንተ በዓለም እየኖርክ አይደለም። ስለዚህ አንተነትህ በዚህ ምድራዊ ተስፋ የታጠረ ነው። መንፈስህም ከስጋ ፍላጎቶች መራቅን ትመኛለች ሥጋ በመንፈስ ላይ መንፈስ በሥጋ ላይ ይመኛልና። (ገላ.5፥17) እነዚህ ሥጋዊ ተስፋዎችና ፍላጎቶች ስኬታማ ስለማይሆኑ ግራ ትጋባለህ።
ይህን በእርግጥ ቅሬታን ያመጣብሃል።
እነዚህን ነገሮች ሁሉ ትናፍቃለህ ነገር ግን ናፍቆትህ አያስደስትህም። ስለዚህ ለምኞትህ ሁሉ ማስተካከያ ታበጅለት ይሆናል ምናልባትም ይጠቅሙኛል የምትላቸውን ሰዎች ማግኘት፣ በምኞትህ ዙሪያ የተጻፈ መዛግብት ማገላበጥ ትፈልግ ይሆናል በዚህም ላይ ታች ስትል ምኞትህን ለማሳካት ትታገላለህ እንዲሆን ሌላ ዘዴ ልትፈጥር ትችላለህ ይሁን እንጂ ሳይሳካልህ ቀርቶ በሃሳብና በጥረት ትታክታለህ ከዚያም ትበሳጫለህ። ከዚህ የከፋው ነገር በእነዚህ ምኞቶችና ተስፋዎች ስኬታማ አለመሆን ምክንያት ለከፋ ሕይወት መዳረግህ ነው።
እንደምትሰለች አውቃለሁ አዘንኩልህ እስከመቼ ድርስ በምኞት ማዕበል ውስጥ ትኖራለህ? የምትመኘውን ባገኘህ ጊዜ ደስተኛ ትሆናለህ ይህ ደስታ ስለማያረካህ ሌላ አዲስ ደስታን እንድትመኝ ያደርግሃል። ልክ ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ "ከዚህ ውሃ የሚጠጣ ሁሉ እንደገና ይጠማል" (ዮሐ.4፥13 ) እንዳለው እርካታ አይኖርህም።
ስለዚህ ውድ ወንድሜ ነገሩን በእርጋታ ከአንተ ጋር ለመነጋገር እፈልጋለሁ። "አለሙም ምኞቱም ያልፋል" (1ኛ ዮሐ.2፥17) ታዲያ ይህን ቃል ካወክ ለምን አለማዊ ፍላጎቶችን ለማግኘት ትታክታለህ? አንተ ልክ እንደ እኔ ለመሬት እንግዳ ነህ። ዓለም የሚያልፍበት አንተም የምትጠፋበት ጊዜ ይመጣል ልክ ከእናትህ ማህጸን ራቁትህን እንደመጣህ እንደዚሁ ራቁትህን ትመለሳለህ።(ኢዮ. 1፥21)
ዓለምን ከነክብሯ ከነሀብቷና ከነስሟ ለቀሃት እንድትሄድ በመገደድ እንደ ማንኛውም ሰው ወደ መሬት ትወርዳለህ። ከዚያም ከዓለም ያገኘኽውን ደስታ ታወቂነት ወይም ምንም ይሁን ምን ሥጋህን ከሞት ሊከላከልልህ አልያም ሥጋን ከሚበሉት ትል ሊከላከልልህ አይችልም። በፍርድ ቀን ከዓለም ሀብትና ንብረት ውጭ በእግዚአብሔር ፊት ትቆማለህ። መልካም ይሁን ክፉ የሰራኸው ሥራ እንጂ የዓለም ቁሳዊ ነገር አይከተልህም።
ስለዚህ ውድ ወንድሜ ምኞትህንና ተስፋህን በዓለም ላይ በማድረግ መታወክህ ለአንተ ጥሩ አይደለም ይህችን ምድር እሾህንና አሜኬላን እንዳበቀለችልህ ትዘነጋለህን!!! ከእኛ በፊት የነበሩና ምድርን ሊረግጧት የማይገባት የቅዳሳን አባቶችና እናቶች አሠራርና ፈለግ ተከተል ቅድስናቸውን ያገኙት ይህችን ዓለም በመውደድ ሳይሆን በመናቅ ነበር ሁኔታዎች ሁሉ ተመቻችተውላቸው ሳለ በዓለም ስላሉ ነገሮች ለማንኛውም ጉጉት አልነበራቸውም ።
ውድ ወንድሜ አሁንም ምኞት አሉህ መዝገብህ ባለበት ልብህ ደግሞ በዚያ ይሆናልና (ማቴ.6፥21) የሥጋን ምኞቶችን ስለተቆራኘ መንፈሳዊ ነገሮች በአንተ አመለካከት ዋጋቸውን ያጣሉ ይህ የክብር ጌታ እንደተፈተነው ዓይነት ፈተና ነው። (ማቴ.4፥8-9)
አሁን አስተውል እነዚህን ነገሮችን ብትይዝ በጥሩ ምኞት ያላሰርካት ነፍስህን ብታጣ ጥቅሙ ምንድን ነው? ነፍስህ ነጻነትን ትሻለች።
ከስጋ ምኞት ተላቀን የመንፈስ ፍሬ የሆኑትን " የመንፈስ ፍሬ ግን ፍቅር፣ ደስታ፣ ሰላም፣ ትዕግሥት፣ ቸርነት፣ በጎነት፣ እምነት፣ የውሃት፣ ራስን መግዛት ነው።"(ገላ.5፥22) እንዳለው ብርሃነ ዓለም ቅዱስ ጳውሎስ እነዚህን ገንዘብ አድርገን እንድንኖር እግዚአብሔር አምላክ ይርዳን!!
(የብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ሺኖዳ ሳልሳዊ "የመንፈስ ነጻነት "ከሚለውና በዲ/ን ደስታ ፍፁም ከተተረጎመው መጽሐፍ ላይ የተወሰደ)