ለነፍሴ ቲዩብ(Lenfse tube)
2.04K subscribers
14 photos
10 videos
11 links
ማቴዎስ 16:26
ሰው ዓለሙን ሁሉ ቢያተርፍ ነፍሱንም ቢያጐድል ምን ይጠቅመዋል? ወይስ ሰው ስለ ነፍሱ ቤዛ ምን ይሰጣል?
Download Telegram
"እግዚአብሔር ረዳቴና መከታዬ ነዉ፤ልቤ በእሱ ታመነ፣እኔም ተረዳሁ ሥጋዬም ደስ አለዉ፥በፈቃዴም አመሰግንኃለሁ ።"_መዝሙር 27፣7)

የጌታ ሠላም ይብዛላችሁ
57🥰5
"አቤቱ ቃሌን አድምጥ ጩኸቴንም አስተዉል፣የልመናዬን ቃል አድምጥ ንጉሤና አምላኬ ሆይ አቤቱ ወዳንተ እጸልያለሁና። በማለዳ ድምፄን ትሰማለህ በማለዳ በፊትህ እቆማለሁ እጠብቃለሁም።"_መዝሙር 5፣1_3)

ሠላመ ክርስቶስ ይብዛላችሁ እንዴት አደራችሁ
36
"...ድንግል ሆይ የምስጢር ጠረጴዛ ወደተዘጋጀበት በላዩም ላይ የመለኮት ማዕድ የሚሆን የሰማይ እንጀራ በተሰራበት ስፍራ ያስቀምጠኝ ዘንድ እታመናለሁ..."

አርጋኖን ዘእሁድ
@amlake_birhan
60
"አቤቱ ፈጥነህ ስማኝ ነፍሴ አልቃለችና ፊትህን ከእኔ አትመልስ ወደ ጉድጓድም እንደሚወርዱ አልሁን።

አንተን ታምኛለሁና በማለዳ ምህረትህን አስማኝ አቤቱ ነፊሴን ወዳንተ አንሥቻለሁና የምሄድበትን
መንገድ አስታዉቀኝ ።"
__መዝሙር 142፣7_8)

ሠላማችሁ በክርስቶስ ይብዛ 🤗
🥰36🙏104👍2
"የህይወት ምንጭ ካንተ ዘንድ ነዉና በብርሃንህ ብርሃንን እናያለን።

ምሕረትህን በሚያቁህ ላይ ጽድቅህንም ልባቸዉ በቀና ላይ ዘረጋ።"__መዝሙር (35፣9_10)

የሰላም አምላክ ከሁላችሁ ጋር ይሁን🤗
24🙏7
ሺልማት ያለው ጥያቄ....😁

ወደ ሰማይ የወጣ የወረደስ ማን ነው?
ነፋስንስ በእጁ የጨበጠ ማን ነው?
ውኃንስ በልብሱ የቋጠረ ማን ነው?
የምድርን ዳርቻ ሁሉ ያጸና ማን ነው?
ይህን ታውቅ እንደ ሆንህ፥ ስሙ ማን፡ የልጁስ ስም፡ ማን ነው?
***በየትኛው የመፅሐፍ ቅዱስ ክፍል?
ምዕራፍ እና ቁጥሩን comment ቀድሞ መመለስ
.
17
ጥያቄ....(2)
ኢየሱስ ክርስቶስ እኔ ብሎ የተናገረበትን ሰባቱን እኔ መፅሐፍ ከነ ጥቅሱ.... and Reference?
19
"አቤቱ አምላኬ ሆይ ፣በልቤ ሁሉ አመሰግንሃለሁ ፣ለዘላለምም ስምህን አከብርሃለሁ፣ ምህረትህ በእኔ ላይ ታላቅ ናትና ፣ነፍሴንም ከጥልቋ ሲኦል አድነሃታልና።"_መዝሙር
(85፣12_13)

የጌታ ጸጋና ሰላም ይብዛላችሁ 🤗
🙏233❤‍🔥1👍1
"እግዚአብሔርን ሁል ጊዜ እባርከዋለሁ ፣ምስጋናዉም ዘወትር በአፌ ነዉ።

ነፍሴ በእግዚአብሔር ትመካለች ፣የዋሆች ሰምቶ ደስ ይላቸዋል ።

እግዚአብሔርን ከእኔ ጋር ታላቅ አድርጉት፣በአንድነትም ስሙን ከፍ ከፍ እናድርግ ።_መዝሙር(33፣1_3)

የጌታ ሰላም ከሁላችንም ጋር ይሁን 🤗
18🙏9🔥7
"በልዑል መጠጊያ የሚኖሩ፣ ሁሉን በሚችል አምላክ ጥላ ዉስጥ ያድራል ።እግዚአብሔርን፦ አንተ መታመኛዬ ነህ እለዋለሁ፣አምላኬና መጠጊያዬ ነዉ፣ በእርሱም እታመናለሁ።"
__መዝሙር (90፣1_2)

የጌታ ጸጋና ሰላም ይብዛላችሁ 🤗
35🙏2
ሐዋ. ሥራ 1:11:
ደግሞም፦ “የገሊላ ሰዎች ሆይ፥ ወደ ስማይ እየተመለከታችሁ ስለ ምን ቆማችኋል? ይህ ከእናንተ ወደ ሰማይ የወጣው ኢየሱስ ወደ ሰማይ ሲሄድ እንዳያችሁት፥ እንዲሁ ይመጣል፡” አሉአቸው።


እንኳን ለጌታችን ለመድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የእርገት በአል በሰላም አደረሳችሁ🙏🙏🙏
🥰207
"ዋላ ወደ ዉኃ ምንጭ እንደሚናፍቅ፣
አቤቱ እንዲሁ ነፍሴ ወዳንተ ትናፍቃለች።"__መዝሙር ( 41፣1 )

የጌታ ጸጋና ሰላም ይብዛላችሁ እንዴት አደራችሁ 🤗
30👍2
<<የጌታዬ እናት ወደ እኔ ትመጣ ዘንድ እንዴት ይሆንልኛል?>> ሉቃ 1፡43

በመጽሐፍ ቅዱስ ስለእመቤታችን ከተነገሩት ቃላት መካከል እጅግ በጣም ግርም ድንቅ የሚለኝ ቃል ይሄ ነው።

ለቅድስት ኤልሳቤጥ ድንግል ማርያም የጌታ እናት መሆኗን ማን ነገራት? በዛ ሰዓት የጌታን ከእመቤታችን መጸነስ የሚያውቁት ሁለት ፍጥረታት ብቻ ነበሩ።ቅዱስ ገብርኤልና እመቤታችን ብቻ ነበሩ።

ታዲያ ቅድስት ኤልሳቤጥ ድንግል ማርያም የጌታ እናት መሆኗን ማን ነገራት? ለዚህ ግሩም ምሥጢር ተሳታፊ ትሆን ዘንድ እንዴት ታደለች!?

መልሱን መጽሐፍ ቅዱስ ይነግረናል <<መንፈስ ቅዱስ ሞላባት>> ይለናል።ከሳቴ ምሥጢር መንፈስ ቅዱስ ሲያድርባት ድንግል ማርያም የጌታ እናት መሆኗን አወቀች።

ስለዚህ ቅድስት ኤልሳቤጥ መንፈስ ቅዱስን ስለተሞላች <<የጌታዬ እናት ወደ እኔ ትመጭ ዘንድ እንዴት ይሆንልኛል>> በማለት ድንግል ማርያምን አመሰገነቻት።

ከዚሁ ቀጥላ እመቤታችን እንደ ማር በሚጣፍጠው ንግግሯ ምስጋናዬ ባንቺና በሰማያውያን መላእክት ብቻ አይቀርም፤ይልቁንም የልጄ መንፈስ ያደረበት ያለፈውም የሚመጣውም ትውልድ ያመሰግነኛል ስትል <<ትውልድ ሁሉ ያመሰግኑኛል>> በማለት ለልጇ ለወዳጇ ምስጋናዋን አሰማች።ሉቃ1፥48

መንፈስ ቅዱስ ያደረባቸው ልጆቿ በዚች ዕለት

<<ከአድባራት(ከቅዱሳን) ሁሉ በልጣ የምትመሰገን ብርሀኗ ከማለዳ ብርሀን ይበልጣል፡እጅግ የምታምር ጥርት ንጽት ያለች ድንግል ማርያም ከፀሐይ ይልቅ ታበራለች>> በማለት በደብረ ምጥማቅ ተገልጣ ያዩአትን ሰዎች ዐይን ዐይናቸው አድርገው ሲያመሰግኗት አድረዋል።
34🥰4
"እግዚአብሔር ሆይ፣ ማለዳ ድምፄን ትሰማለህ ፣ማለዳ በፊቱ እቆማለሁ ፣እጠብቃለሁም ።እኔ ግን በምሕረትህ ብዛት ወደ ቤትህ እገባለሁ ።"__መዝሙር (5፣3_7)

ሰላመ እግዚአብሔር ይብዛላችሁ 🤗
34👏2
ሠላም ቤተሰብ እንዴት አደራቺው ሰለመ ክርስቶስ ከኔም ከናንተም ጋር ይሁን አንድ ትንሺዬ ፕሮጀችት ላይ ልናሳትፋቺው አስበናል እስቲ አንግሊዘኛ ላይ ጥሩ የሆናቺው ብቻ 10 ልጆች በዚ user name inbox ኑ @Alemn21
👍12
"በማለዳ ምሕረትህን እንጠግባለን ፣በዘመናችን ሁሉ ደስ ይለናል ሐሴትም እናደርጋለን።አምላካችን እግዚአብሔር ሆይ ፣ብርሃንህ በላያችን ይሁን ።"
__መዝሙር ( 89፣14_17)


የጌታችን የመድኃኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስ ጸጋና ሰላም ከሁላችንም ጋር ይሁን መልካም ቀን🤗
25👍4
"እጆቼን ወደ አንተ ዘረጋሁ ፤ ነፍሴም አንተን ተጠማች ።አቤቱ ፦ፈጥነህ ስማኝ ፤ማለዳ ምሕረትህን አሳየኝ ፥የሚሄድበትንም መንገድ አስታዉቀኝ።
(መዝሙር 142፣6_8)

ሰላማችሁ በክርስቶስ ይብዛ እንዴት አደራችሁ ቤተሰብ🤗
31
"አቤቱ አምላኬ፥እይና ስማኝ ዓይኖቼን አብራቸዉ።ጠላቴም፦ አሸነፍሁት እንዳይል። እኔ ግን በምሕረትህ ታመንኩ ልቤም በማዳንህ ደስ ይለዋል።ለእኔም ስላደረገልኝ ለእግዚአብሔር እዘምራለሁ ።"
__መዝሙር ( 12፣3_6)

የጌታ ጸጋና ሰላም ይብዛላችሁ 🤗
25
"እኔ ግን ለኃይልህ እቀኛለሁ ፥በማለዳም በምሕረትህ ሐሤት አደርጋለሁ ፣በመከራዬ ቀን መጠጌያዬ ሆነኸኛልና ።ረዳቴ ሆይ ላንተ እዘምራለሁ፤አምላኬ መጠጊያዬ ምሕረቴም ነዉና ።"
__መዝሙር (58፥16_17)

ሰላማችሁ በክርስቶስ ይብዛልኝ🙏 እንዴት አደራችሁ
29
እነሱ መሞት ሳይደክማቸው እኛ መጻፍ እየደከመን ዝም ብለን ነበር። ሻማዋ አልቅሳ አስለቅሳ እየጨረሰች ይመስላል።

በእውነት በሃይማኖታቸው በየቀኑ በቁማቸው ለሚሞቱ፣ የሚወዱትን በአሰቃቂ ሁኔታ ለሚነጠቁ፣ ሕዝቤና ልጄ የሚላቸው ላጡ የምሥራቅ አርሲ ኦርቶዶክሳውያን ምን ያጽናናቸዋል? ከሚደርስባቸው ግፍ በላይ ባለቤት አልባ መሆናቸው ያቆስላል።

ሐውለት አሕመድ ከዚህ በታች ያለውን ጽሑፍ ጥሩ አድርጋ ከተበችውና አጋራነው!

ይቺም ሻማ ሰልችታለች‼️
===============

"በአገራችን ለሚቀጥሉት ብዙ አሥርት ዓመታት ምናልባትም አሁን በሕይወት የምንገኝ ሰዎች በአጠቃላይ ሳናይ የምንሞተው ነገር የመንግሥት ከፍተኛ ባለሥልጣናት ''ኃላፊነቴን በአግባቡ ስላልተወጣሁ ሥራዬን በፈቃዴ ለቅቄያለሁ፤ ከ'ኔ የተሻለ ሰው ይምራው'' የሚለው ነው።

በአርሲ ዞን በኦርቶዶክስ ክርስትና አማኞች እና አብያተ-ክርስትያናት ላይ በተደጋጋሚ ጥቃቶች እየተሰነዘሩ ብዙ ሰው በአሰቃቂ ሁኔታ ሞተ፤ አብያተ-ክርስትያናት እና ቅርሶችም ወደሙ፤ በነዋሪዎቹ ዘንድ ሥጋትና ጥርጣሬ ሰፈነ።

ይሄን ተደጋጋሚ ጥቃት ለማስቀረት የተሠራ ሥራ አለ? ሰላም ማስከበር 100% የክልሉ መንግሥት ሥራ አይደለም እንዴ? ምን አድርጓል? ሰላም ማስከበር ካቃታቸው በኢትዮጵያ ሕግ መሠረት ''አልቻልንም፤ የፌዴራል መንግሥት ጣልቃ ይግባልን'' ይባላል እኮ! መቼም ''እኔ ለዚህ ኃላፊነት ብቁ ሆኜ አልተገኘሁም፤ የተሻለ ብስለትና ልምድ ያለው ሰው ይተካኝ'' የሚሉ ኃላፊዎችን በሕይወት እያለን እንደማናይ ዕሙን ነው።

ሰው ባለቀ ቁጥር ይቺን ሻማ ብልጭ ማድረግ ምን ፋይዳ አለው? ይሰለቻል።

ወደ ስራ ብንገባ ሁላቺንም ባለንበት ቦታ ሆነን መደራጀት ያስፈልጋል ኦርቶዶክስ እህት ወንድሞቼ ፍራቻ አስወግዱ
💔243👍3