ለነፍሴ ቲዩብ(Lenfse tube)
2.04K subscribers
14 photos
10 videos
11 links
ማቴዎስ 16:26
ሰው ዓለሙን ሁሉ ቢያተርፍ ነፍሱንም ቢያጐድል ምን ይጠቅመዋል? ወይስ ሰው ስለ ነፍሱ ቤዛ ምን ይሰጣል?
Download Telegram
ፊቱ እንደ ፀሐይ በራ፥ ልብሱም እንደ ብርሃን ነጭ ሆነ።(ማቴዎስ 17:2)
​ጌታችን በታቦር ተራራ መለኮታዊ ክብሩን የገለጠበትና ሐዋርያትም "የክብሩ ምስክሮች ነበርን" ብለው የመሰከሩለት ታላቅ ዕለት ነው (2ኛ ጴጥሮስ 1:18)። ሙሴና ኤልያስ መገለጣቸውም የሕጉና የነቢያት ፍጻሜኢ እርሱ መሆኑን ያሳያል።
​የደብረ ታቦር ብርሃን የሕይወታችን ጨለማ አስወግዶ ሰላም እና ፍቅር ያድልልን እንኳን አደረሳችሁ መልካም በዓል 🙏🥰
136🥰27👍2
የውይይት ጥሪ እንደተቀበልኩ የማሳይ ቢዶ😂😂😂
😁5618🤣10👍8🔥1
ይህም ጸጋ በኀጢአት መኖርንና ዓለማዊ ምኞትን ክደን፣ በአሁኑ ዘመን ራሳችንን በመግዛት በጽድቅ፣ በእውነተኛ መንፈሳዊ ሕይወት እንድንኖር ያስተምረናል፤ ይህም የተባረከ ተስፋችን የሆነውን የታላቁን የአምላካችንንና የአዳኛችንን የኢየሱስ ክርስቶስን ክብር መገለጥ በመጠባበቅ ነው፤ እርሱም ከክፋት ሊቤዠን መልካም የሆነውን ለማድረግ የሚተጋውን የእርሱ የሆነውን ሕዝብ ለራሱ ያነጻ ዘንድ ራሱን ስለ እኛ ሰጥቶአል። ቲቶ 2:12-14

አሜን ኢየሱስ ሆይ በመንግሥትህ አስበን ::
124🙏17❤‍🔥2👍2
እንኳን ለአምላክ እናት በዓለ ትንሳኤ በሰላም አደረሳችሁ።
190🙏8👍4👎1
ኦርቶዶክሳውያን ምንድነው እየተከሃደ ያለው ነገር?
👀59🤷‍♀27🤬19💔17🤔5😭3
ተጀምሯል ኑ
35👍6
በሕግህ ያለውን ተአምራት አይ ዘንድ ዓይኖቼን ክፈት።" (መዝሙር 119፡18)
በዮሐንስ ራእይ ውስጥ በሰባት ማኅተም የታተመ መጽሐፍ ይታያል፤ ይህንንም መጽሐፍ ለተማረ ሰው ሰጥተህ "እባክህ ይህንን አንብብ" ብትለው፣ እርሱም "ታትሟልና (ተዘግቷልና) አልችልም" ብሎ ይመልስልሃል።
ዛሬም ቢሆን ራሳቸውን እንደ ተማሩ የሚቆጥሩ፣ ነገር ግን ቅዱሳት መጻሕፍት ለእነርሱ የታተሙ (የተዘጉ)ባቸው ስንቶች ናቸው! የዳዊት መክፈቻ ካለው፣ "እርሱ ሲከፍት የሚዘጋ የሌለ፥ ሲዘጋም የሚከፍት የሌለ" (ራእይ 3፡7) ከተባለው ከእርሱ በስተቀር ሊከፍቱት አይችሉም።
በሐዋርያት ሥራ መጽሐፍ ውስጥ፣ ያ ቅዱስ ጃንደረባ የኢሳይያስን መጽሐፍ ሲያነብ ፊልጶስ "የምታነበውን ታስተውላለህን?" ብሎ በጠየቀው ጊዜ፣ "የሚመራኝ ሰው ሳይኖር እንዴት እረዳለሁ?" ብሎ መለሰለት። ... ከዚያም ፊልጶስ መጥቶ በቃላቱ (በፊደሉ) ሥር ተሰውሮ የነበረውን ኢየሱስን አሳየው። የአስተማሪው ድንቅ ብቃት እንዴት ይገርማል! በዚያችም ሰዓት ጃንደረባው አመነ፣ ተጠመቀም፤ ከምእመናንና ከቅዱሳን አንዱ ሆነ። ከዚያ በኋላ እርሱ ተማሪ ሳይሆን መምህር ሆነ፤ በወርቅ ከተለበጠው የምኩራብ ቤተ መቅደስ ይልቅ፣ በዚያ በምድረ በዳ ባለችው የቤተክርስቲያን መጠመቂያ የላቀ ነገር አገኘ።
የማታውቀውን ነገር ለማስተማር መሞከር ከንቱነት ነው፤ በጥቂት ቁጣ (በኃይለ ቃል) ለመናገር ካስፈለገ ደግሞ፣ አለማወቅህን አለማወቅህ (አለመረዳትህን አለመረዳትህ) ከሁሉ የከፋ ነው።

....... St. Jerome ለጳውሊኖስ ከጻፈው ደብዳቤ (Letter 53) የተወሰደ ::
75🔥1👏1
ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ ተስፋን ሲያብራራ.....

በሕይወት ማዕበል መካከል ነፍስ እንዳትሰምጥ የሚያጸና "መንፈሳዊ መልሕቅ" እንደሆነ ይገልጻል። ዕብራውያን 6፡19 ላይ የሚገኘውን "ይህም ተስፋ እንደ ነፍስ መልሕቅ አለን" የሚለውን ቃል ሲያብራራ፣ ምድራዊ መልሕቅ ወደ ባሕሩ ጥልቀት እንደሚጣል ሁሉ፣ የክርስቲያን ተስፋ ግን ወደ ላይ ወደ ሰማያዊው መቅደስ (ወደ ክርስቶስ) የሚጣል እንደሆነ ያስተምራል። ይህ ተስፋ ከምድራዊ ሁኔታዎች ላይ ሳይሆን ከማይለወጠው የእግዚአብሔር ቃል የሚመነጭ በመሆኑ፣ አማኙ በታላቅ ፈተናና በጭንቀት ጊዜ እንኳ ተስፋ በመቁረጥ እንዳይሰበር ይረዳዋል። ይህም ተስፋ በሮሜ 5፡5 ላይ እንደተጠቀሰው "አያሳፍርም"፤ ምክንያቱም መሠረቱ በሰው ጥንካሬ ላይ ሳይሆን በክርስቶስ የትንሣኤ ኃይልና በማይለወጠው ቸርነቱ ላይ የተገነባ ነውና።

የአባቶቻቺን በረከት አይለየን::
70👍5👏1
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ምንግሥት ሰማያት ለመውረስ መታገል አለብን ተስፋቺን ክርስቶስ ከሆነ መታገል ነው እስከመቸርሻ......****
81🥰5👍2🍓2
ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ ስለ አዲስ ዓመት ተስፋ ሲያስተምር፣ እውነተኛው መታደስ የሚገኘው የቀኑ መለወጥ ሳይሆን የልባችን መለወጥ ሲሆን ነው ይላል። እርሱ እንደሚለው፣ አዲስ ዓመት ተስፋን የሚሰጠን እግዚአብሔር ለንስሐና ለበጎ ሥራ ሌላ ጊዜ ስለሰጠን እንጂ ዝም ብሎ ዓመቱ ስለተፈራረቀ አይደለም።
ቅዱስ ጳውሎስ በ2ኛ ቆሮንቶስ 5፡17 ላይ "ማንም በክርስቶስ ቢሆን አዲስ ፍጥረት ነው፤ አሮጌው ነገር አልፎአል፤ እነሆ፥ ሁሉም አዲስ ሆኖአል" እንዳለው፣ አፈወርቅም ተስፋችንን በክርስቶስ ላይ በማድረግ አሮጌውን የኃጢአት ልማድ ትተን በቅድስና ሕይወት እንድንመላለስ ያሳስባል። ይህም አዲስ ዓመት ላለፈው ድካማችን ይቅርታን የምናገኝበትና ለወደፊቱ ሕይወታችን ደግሞ በእግዚአብሔር ቸርነት የምንታደስበት የጸጋ ዘመን መሆኑን በመረዳት፣ በዓለም ተለዋዋጭ ሁኔታዎች ውስጥ ሳንታወክ በክርስቶስ ዘላለማዊ ተስፋ እንድንጸና ይመክረናል።
86🙏7👀1
አንድ ትንሺዬ ፕሮጀክት ለመጀመር አስበናል
ለዚህ አገልግሎት የሚፈለጉት ጥቂት ሰው ብቻ ነው ።

       ጠቅላላ መስፈርት

1. ኦርቶዶክሳውያን መሆን አለባቸው።
2. ለቤተክርስቲያን አገልግሎት ተነሣሽነት ያላቸው።
3. ለአገልግሎቱ የሚያስፈልጉትን ትምህርቶች ለመማር ፈቃደኛ የሆኑ እና ጊዜያቸውን ለመስጠት ፈቃደኛ የሆኑ።
4. የአባቶች ትምህርት እና የእንግሊዝኛ ነገረ መለኮታዊ ጽሑፎችን አንብቦ መረዳት ላይ ጎበዝ የሆነ/ች።
5. የቃል እና ጽሑፍ ፈታና ለመፈተን ፍቃደኛ የሆነ/ች

በትምህርት ጊዜ መቅረት፣ በሥራ ጊዜ አለመገኘት እና መዘግየት፣ ከወንድሞች እና ከእህቶች ጋር ክርስቲያናዊ ባልሆነ መንገድ ማንኛውንም ሁኔታ ከ ፕሮጀችት ቃጥታ ያስባርራል ።

@Lisanenzira2429 ወይም
@Alemn21

በዚህ ይጻፉልን 👆👆👆
63🔥6
ቅዱስ አትናቴዎስ "ስለ ሥጋዌ" ባስተማረበት መፅሐፍ :.........የክርስቶስ ዳግም ምጽዓት አማኞች ሞትን ድል አድርገው
የማይበሰብሰውን የትንሣኤ ሕይወት የሚቀበሉበት ታላቅ የተስፋ ቀን ነው። መጀመሪያ የእግዚአብሔር ቃል ሰው ሆኖ በመምጣት ሞትን በሥጋው እንደገደለው ሁሉ፣ በዳግም ምጽዓቱ ደግሞ የሁላችንንም ሥጋ ለክብር እንደሚያስነሣውና ወደማይጠፋው መለኮታዊ ጸጋ እንደሚያሸጋግረን ያስተምራል። ይህ ተስፋ ክርስቲያኖች በምድር ላይ በሚደርስባቸው መከራና ስደት ውስጥ ጸንተው እንዲቆሙና ሕይወታቸውን ለሚመጣው የክብርና መንግሥት በቅድስናና በዝግጅት እንዲመሩ ታላቅ ብርታት እንደሚሰጣቸው አትናቴዎስ በጥልቀት ያብራራል።
ሁሌም ተስፋቺን ክርስቶስ ነው ❤️
74👍5🙏5👏1
ዘይገርም

በስትራቴጂክ መንገድ ከእነሱ እምነት ውጪ እንዴት ማጥፋት እንዳለባቸው የሚያሰለጥኑት(አሕመዲን ጀበል) በነጻነት እየሄዱ
የቤተክርስቲያን የ3ሺ አመት ታሪክ በመረጃ ለምን ጻፋችሁ ተብለው ከነ አሳታሚው እስር ቤት ናቸው።

ለታሪክ ይቀመጥ!!
😢8619😁1
Forwarded from Effoy Official
እንኳን አደረሳችሁ!!!
የአዲስ አመት ስጦታዬ😍😍😍
124👏101🤣1🍓1
🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼
"ወትባርክ፡አክሊለ፡ዓመተ፡ምሕረትከ፡ወይጸግቡ፡ጠላተ፡ገዳም"                  
መዝ ፷፬÷፲፩       
"በቸርነትህ ዓመታትን ታቀዳጃለህ ምድረ በዳዎችም ጠልን ይጠግባሉ።"
መዝ 64÷11         
🌼🌼🌼 እንኳን ወደ ዘመነ ሉቃስ በሰላም አሸጋገረን ዘመኑ የፍቅር የሰላም የበረከት የይቅርታ የንስሐ እና መልካም ፍሬ የምናፈራበት የስኬት ዓመት ያድርግልን።
     መልካም አዲስ ዓመት
🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼
88🙏5🍓1
እግዚአብሔር ለእናንተ ያስበው አሳብ የሰላም እንጂ የክፉ አይደለም፤ መጨረሻችሁና ተስፋችሁም ሕያው እንዲሆን ይሰጣችኋል።» — ትንቢተ ኤርምያስ 29፥11
​እንኳን አደረሳችሁ🌼🌼 ይህች አዲስ ዓመት በንስሐ ታጥበን ንጹሕ ሕሊና ይዘን የጌታችንን ቅዱስ ሥጋና ክቡር ደሙን የምንቀበልባት የበረከትና የቅድስና ዘመን እንድትሆንልን እመኛለሁ። አምላካችን አዲሱን ዓመት የሰላም፣ የፈውስና የዕረፍት ዓመት አድርጎ ለሀገራችን ሰላሙን እንዲያወርድልን አጥብቀን እንጸልያለን ባላችሁበት ሁሉ የክርስቶስ ሠላም አይለያችሁ
​መልካም አዲስ ዓመት።🌼🌼🌼
91👍12🙏7🥰4🍓1
ሠላም እንዴት ቆያቺው ቤተሰብ እስቲ ከ አሜሪካ አትላንታ ስቴት እና አከባቢ በቅርቡ የምትመጡ ካላቺው ዋይም የሚመጣ ሰው የምታቁ ከታች user name ፃፉልኝ
@Alemn21
21🍓1
https://vt.tiktok.com/ZS9Sn2n4KMuCf-gr13z/ አላችሁ 🤔ኬሌላችሁ ኑ
20🍓1