እልመስጦአግያ+++
568 subscribers
244 photos
51 videos
5 files
96 links
"እልመስጦአግያ ብሂል ትምህርተ ኃቡአተ"
እልመስጦአግያ ማለት የተሠወረ ትምህርት
—— ማለት ነው
ጌታችን መድኃኒታችን ከትንሳኤው በኁዋላ በመጽሐፈ
…… ኪዳን ያስተማረው ትምህርት ነው ……

ያንብብዋ ምዕመናን እምቅድመ ቅዳሴ ንጹሕ ለዛቲ
ሃይማኖት እልመስጦአግያ
—— 《ሃይማኖተ አበው ምዕ ፪ ፥ ፩》——
#አማርኛ #ትግርኛ #ኦሮምኛ_ቋንቋ
Download Telegram
በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ

አሐዱ አምላክ አሜን
+++++++++++⊙+++++++++++++
+እልመስጦአግያ ዘተዋህዶ ————⊙+ሃይማኖት
+++++++++++⊙+++++++++++++
ይቤሉ ፲ ወ ፪ቱ ሐዋርያት ወጳውሎስ ነዋይ ኅሩይ ወያዕቆብ ዘተሰምየ እኁሁ ለእግዚእነ ኤጲስ ቆጶስ ዘኢየሩሳሌም ወ፯ቱ ዲያቆናት ፸ ወ፪ቱ አርድእት እመጽሐፈ ኪዳን ። ሐይማኖት ዘመሀረነ እግዚእነ ወመድኃኒነ ኢየሱስ ክርስቶስ ለሐዋርያቲሁ ቅዱሳን ያንብብዋ ምዕመናን እምቅድመ ቅዳሴ ንጹሕ ለዛቲ ሃይማኖት እልመስጦአግያ ።
+++++++++++⊙+++++++++++++
ከአስራ ሁለቱ ሐዋርያት ምርጥ ዕቃ ጳውሎስ፣ የጌታ ወንድም የተባለ የኢየሩሳሌም ኤጲስ ቆጶስ ያዕቆብ፣ ሰባቱ ዲያቆናት፣ ሰባ ሁለቱ አርድእት፣ ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ያስተማረን ለኛ ለሐዋርያት ያስተማረን ሃይማኖት ከመጽሐፈ ኪዳን የተገኘች ናት፤ይህችንም እልመስጦአግያ የተባለችውን ሃይማኖት ምዕመናን ከቅዳሴ በፊት ያንብቧት አሉ።
+++++++++++⊙+++++++++++++
ይህችውም ምዕመናን ከቅዳሴ አስቀድመው የሚያነብቧት ጌታችን ፈጣሪያችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ለደቀ መዛሙርቱ ያስተማራቸው ሃይማኖት ናት ።

——『ሃይማኖተ ዓበው ምዕ ፪ ፥ ፩』——
☀️☀️☀️☀️☀️ ☀️☀️☀️☀️
☀️
@JohnDPT27 ☀️
☀️@Learn_With_John☀️
☀️☀️☀️☀️☀️ ☀️☀️ ☀️☀️
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
#ElmestoAgya #እልመስጦአግያ

#ሊቀ_መዘምራን_ቴዎድሮስ_ዮሴፍ🎙
እኔ አንተ ቤት እኔ አንተ ቤት
የምቆም ሰው አይደለሁም
ግን ፍቅር ነህ ለዘለዓለም
የሚመስልህ ማንም የለም

🌹ዕፁብ ድንቅ መክሊት 🌹

@Learn_with_John @JohnDPT27
#ElmestoAgya #እልመስጦአግያ

የመላእክት መምህር ዮሐንስ"!

ቅዱሳን መላእክት ዓይን በተገለጠ ጊዜ ከማየት በፍጡርነት ከታዩ ጊዜ ጀምሮ ሕሊናቸው ዕመቀ መለኮቱን በመመኘት አንደበታቸው ሙሐዘ ስብሐቱን በመቅዳት የኖሩ ናቸው ። ዘወትር ያመሰግኑታል፡፡ግን አይጠግቡትም።ዓለም ከተፈጠረ ጀምሮ እስከአሁን አመስግነውት አንዷን ሰዓት ከአራት ከፍለው የዚያችን ደግሞ ሩብ ያመሰገኑት አይመስላቸውም። "ወኢይመስሎሙ ከመ ዘወደስዎ መጠነ መንፈቀ መንፈቃ ለሰዓት እም አመ ተፈጥረ ዓለም እስከ ይእዜ" እንዲል።

ከባሕሩ ይጠጣሉ ፡፡ግን ማዕበለ እሳቱን መሻገር አይቻላቸውም። ይመገቡታል ግን በእጃቸው አይነኩትም። ነገር ግን ከእነርሱ የተሰወረ ነው። ተሸክመውታል፤ ግን አነርሱን ተሸክሞ ያለ መሠረት ነው። በሕሊናቸው ነግሶ አለ ነገር ግን የዓለማት ዓለም ነው። መንበሩን ተሸክመዋል ነገር ግን እስከ መንበሩ ይበራሉ እንጅ ከዚያ ወዲያ ነደ እሳቱ ያዩታልአያሳልፋቸውም። ስለዚህም ዘለዓለም ይመኙታል። "ዘያፈትዎሙ ለመላእክት እለ የሐውጽዎ=አብረውት የሚኖሩ መላእክትስ እንኳ ሊመለከቱ ይመኛሉ"እንዲል።፩ ጴጥ፩፥፲፪

ነገር ግን እንደ እኛ አፈር ሲሆን ከመላእክት በላይ ከንፎ ዕመቀ መለኮቱን የቀዳውን ዮሐንስን እንመልከት። ይህ የሃይማኖት ንሥር እንደ ንሥር እስከ ሕዋ አልበረረም። ወይም እንደ ከዋክብት እስከ ጠፈር ተወርውሮ አልበቃውም። ወይም እንደ ባቢል ነፋስ ሐኖስ ላይ አልቆመም። ወይም እንደ ሊቃናት በኤረር አልተወሰነም። ወይም እንደ አርባብ በራማ ላይ አልበቃውም። ወይም እንደ ኃይላት ኢዮር ላይ አላበቃም። ወይም እንደ ኪሩቤል መንበሩ ሥር አይኖቹን በክንፎቹ ሸፍኖ አልቀረም። ወይም እንደ ሱራፌል አክሊሉን አውርዶ መንበሩን አጥኖ አልተመለሰም፡፡ ሰረገላ እሳቱን አልፎ መጠቀ እንጅ! የመንበሩ ጫፍ ላይስ መች በቃውና ማንም ሊቀርበው የማይችለውን ነደ እሳት ቀረበው። ወደ ውስጥ ገባ። በምስጢረ መለኮቱ ሰጠመ። ያንንም የቀዳውን የሃይማኖት ውኂዝ ለቤተክርስቲያን አፈሰሰው። ጽሙአን ልጆቿም ቀዳሚሁ ቃልን ጠጥተው ልቡ ምስኩራነ መንፈስ ሆነው ትርጓሜን አፈለቁ።

በእውነት መላእክት እስከ መንበረ ሥላሴ በረሩ። ዮሐንስ ግን እስከ ልበ ሥላሴ በረረ! ለምን ብትሉኝ "ቃል" ሲል የቃል መኖሪያው ልብ ነውና፥ልብ ማለቱ ነውና! ቃል ሲል የልብና የእስትንፋስ መዲናቸው ነውና ልብንም እስትንፋስም ማለቱ ነውና። ልብ የሌለው ቃል የለም። ቃልም የሌለው ልብ የለም። ቃል የሌለው እስንፋስ የለም። ልብ የሌለው እስንፋስም የለም። እስትንፋስ የሌለው ልብ ወይም ቃል የለም። ስለዚህ ዮሐንስ "ቀዳሚሁ ቃል" ሲል አብን ልብ ወልድን ቃል መንፈስ ቅዱስን እስትንፋስ ማሉቱ ነው። ውሳጣዊ ሕሉና ሥላሴ ድረስ የበረረ እንደ ዮሐንስ ያለ ማን አለ?

ቅዱሳን መላእክት ይህንን የሰሙት ከዮሐንስ ነው። ወዳጆቼ ዮሐንስ ለመላእክት ሳይቀር እንደ ሰበከ እናስተውል። ቤተ ክርስቲያንም የመላእክት ትምህርት ቤት መሆኗን እንረዳ። ይህ ምሥጢር የተርጓሚው የቅዱስ ዮሐንስ አፈ ወርቅ ነው። ዮሐንስን በዮሐንስ መማር እንዴት ደስ ይላል!
"Since they too have learned by the voice of John with us, and by us, the things which we know. and this has another Apostle declared ,sayng," To the intent that now unto the principalities and powers in heavenly(places) might be known by the churh the manifold wisdom of God" = መላእክትም የሃይማኖትን ምሥጢር ከእኛ ጋር እንደ እኛ ከዮሐንስ ቃል ይማራሉ። ስለዚህ ነገር ሌላው ሐዋርያ ንዑድ ክቡር ጳውሎስም እንዲህ አለ" ብዙ ልዩ ልዩ የእግዚአብሔር ጥበብ አሁን በቤተክርስቲያን በኩል በሰማያዊ ስፍራ ድንግል ውስጥ ላሉት አለቆችና ሥልጣናት ትታወቅ ዘንድ" ኤፈ ፫፥፲" ቅዱስ ዮሐንስ አፈ ወርቅ ዮሐንስ ወንጌል ትርጓሜ ድርሣን አንድ።
ለመሆኑ ዮሐንስን ለዚህ ያበቃው ምንድን ነው? የጌታ ፈቃድ ፈጻሚ መሆኑ፤ በንጽሕና መኖሩ፤ ምናኔውና ትሕርምቱ፣ መንፈሳዊነቱና ተጋድሎው፥ በፍቅረ ክርስቶስ የነደደ ሆኖ መኖሩ ነው እንጅ ሌላ ምንድን ነው ? ከዚህ ሁሉ ጋር ለዚህ ሁሉ መሠረቱ ምንድን ነው? የሞሥጢር መዝገብ የሆነችውን ማርያምን ከመስቀሉ ሥር ተቀብሎ ቤቱን ይዞ መሄዱ ነዋ!ቤትን ይዞ መሄድስ ምንድን ነው?ፍቅሯን በልብ ውስጥ እንደ ተክሎ የኃይለ ድንግልናዋን ሥር ወደ ጥልቁ ሕሊና ሰዶ የውዳሴዋን ቅርንጫፍ በአንደበት ማውጣት ነው እንጅ ለሐዋርያ ደግሞ ምን ቤት አለው? የሕይወትን ዛፍእናት በልቡ ይዟልና ድሮስ ሕይወት ባለበት ከመቼ ወዲህ ሞት ይቀርባል! ከሞት መሰወሩስ ለዚህ አይደል!
በስብከቱ ከዓይነ መናፍቅ፤ በሕይወቱ ከአይነ ሞት ይሰውረን!

ሊቁ አባ ገብረ ኪዳን

@JohnDPT27
@Learn_with_John
አጥንትን የሚያለመልም ዝማሬ!

🎙በዲ/ን ፍሬዘር

ፍጥረትን በሚያስምር📌
በእናቱ ልመና📌
ክርስቶስ ይማረን 📌
መሀሪ ነውና!📌


በጉባኤ ደቂቀ አበው ላይ የቀረበ!

@JohnDPT27
@Learn_with_John
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
#ElmestoAgya #እልመስጦአግያ

የግብፅ ኮፕቲክ ኦርቶዶክስ አባቶቻችን ስለ ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሲዘምሩ !

ዝማሬ መላዕክትን ለአባቶቻችን ያሰማልን።

አቤቱ ህብረታችንን አፅናልን 🙏

@JohnDPT27
@Learn_With_John
ስለ ራዕየ ማርያምና ኦሮሞ.pdf
610.6 KB
#ElmestoAgya #እልመስጦአግያ

OMN በተባለው ጣብያ ላይ ቀርበው ኦርቶዶክስ እንዲህ ብላለች የሚሉት የሰሞኑን ዜና ከየት የመጣ ትርክት ነው?

1⃣ ቅድስት ቤተክርስቲያናችን መጽሐፈ "ራዕየ ማርያምን" ከየት ተቀበለችው

2⃣ "ራዕየ ማርያም" ኦሮሞ መንግስተ ሰማያትን አይገባም ብሏል የሚለው መጽሐፉ ውስጥ አለ ወይ

3⃣ ፈላሻ እና ሻንቅላስ መንግስተ ሰማያት መግባት አይችሉም ይላል

በአምሳሉ ተፈራ

☀️☀️☀️☀️☀️☀️☀️☀️☀️☀️
☀️@JohnDPT27 ☀️
☀️
@Learn_with_John ☀️
☀️☀️☀️☀️☀️☀️☀️☀️☀️☀️
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
#ElmestoAgya #እልመስጦአግያ

#ሊቀ_መዘምራን_ቴዎድሮስ_ዮሴፍ🎙
አይናችን ነሽ ማርያም አንቺን አይንኩብን
የተዋህዶ ልጆች እንወድሻለን
ግቢ ከቤታችን በረከታችን ነሽ
በሐሴት ቆመናን ደስታን ስለወለድሽ



🌹ዕፁብ ድንቅ መክሊት 🌹

@Learn_with_John @JohnDPT27
ስለ "Corona Virus" ሚስጥራዊ ምንነት ማወቅ እንፈልጋለን የምትሉ እጃችሁን አውጡ !
እግዚአብሔር አምላካችን ከ "Corona virus" ይታደገን አሜን( 🙏 )