Khemise Network
327 subscribers
1.05K photos
34 videos
2 files
578 links
ታማኝ የመረጃ ምንጭ
Download Telegram
መንግስት በሃይማኖታችን ጣልቃ እንዲገባ አንሻም፣ ሃይማኖቶችም በመንግስት ስራ ጣልቃ መግባት እንደሌለባቸው እናምናለን። ይህ ሃገራችን ኢትዮጵያ የምትተዳደርበት የሴኩላሪዝም መርህ ዋና ህግጋት ነው።

ነገር ግን "ያለፈው መንግስት" ከዚህ በፊት ህግ ጥሶ በተቋማችን ጣልቃ በመግባት ያስቀመጠብንን የመጅሊስ ካድሬዎች እንዲያነሳልን እንሻለን። የእምነት ነፃነታችንን ለማስከበር እና ተቋማችንን ከሌቦች ለመታደግ ከበቂ በላይ ታግለናል፣ ታግሰናልም።

በሙስሊሙም ትግል ጭምር የተገኘው ሃገራዊ ለውጥ እና ጭላንጭል ተስፋ ሙስሊሙ የታገለለት ተቋማዊ ለውጥን ለማሳካትም ማገዝ ይገባዋል።

የመጅሊሱ ከሙሰኛ አስተዳደሮች ይንፃ ጥያቄ እና ትግል ፍሬ ሊያፈራ ጫፍ በደረሰበት በዚህ ጊዜ የመጅሊሱ አመራሮች ነገ በሚያካሂዱት ጉባኤ ስልጣናቸውን ለሚቋቋመው ባለአደራ መጅሊስ ላለማስረከብ እያሴሩ እንደሆነ መረጃዎች እየወጡ ነው።

የመጅሊሱ አስተዳደሮች በነገው እለት ይህንን ውሳኔ የሚያፀድቁ ከሆነ የስልጣናቸውም ሆነ ማናለብኝነታቸው ምንጭ ህዝበ ሙስሊሙ አይደለምና አይዟቹ ባያቸው ማን እንደሆነ በቦታው ያስቀመጣቸው መንግስትን ለመጠየቅ እንገደዳለን!

"አዲሱ መንግስት" ሙሰኞችን አይዞህ ማለቱ ላይ እጁ ከሌለበት የቀድሞ የፓርቲው ሰዎች ያስቀመጡብንን ጠምጣሚ ካድሬዎች አይዟችሁ ባለማለት እና በማስወገድ ከማን ወገን መሆኑን እንዲያሳየን ስንል እንጠይቃለን።

#አይዞህባዩማነው #የህዝብወይስየሌባወገን #EnoughIsEnough #መጅቴክ

Office of the Prime Minister-Ethiopia

https://t.me/ALJUEDNEWS
—————————
መጅሊሱ ለውጡን ለመቀልበስ ለሚያደርገው እንቅስቃሴ መንግሥትም ተጠያቂ ነው!
—————————
. © Isaac Eshetu
.
መጅሊሱ ነገ ሰኞ በጠራው ስብሰባ ለባለአደራ አሥተዳደሩ ሽግግሩን ለማመቻቸት የሚያስችለውን ሥራ መሥራት እና አሥተዳደራዊ መዋቅሩን መበተን ይጠበቅበት ነበር። እየደረሱን ያሉት መረጃዎች ግን በነገው ስብሰባ ዕድሜውን ለማስቀጠል መወሰኑን ነው! ይህ ደግሞ እስከእስትንፋሳችን መጨረሻ የምንታገለው ጉዳይ መሆኑ አይጠረጠርም!
.
ሕገ-ወጡ የመጅሊስ አሥተዳደር ምንጩ ይታወቃል። እሱም መንግሥት ነው። ዋነኛ ሥራቸውም ለሁለት ዐሥርት ዓመታት የመንግሥትን ፍላጎት ማስፈጸም ሆኖ ቆይቷል። እናም ለሚፈጽሙት ሁሉ ተጠያቂ መንግሥት ከመሆን አይዘልም። ከሚወስኗት እያንዳንዷ ውሳኔ ጀርባ ማን ሊኖር እንደሚችል ይታወቃል። የሾማቸው መንግሥት ነው። «አንሻርም» እያሉ መበጥበጥ ሲጀምሩም ከጀርባ ሆኖ የሚያደፋፍራቸው አካል እንደሚኖር ግልጽ ነው። መጅሊሱ ለሚያደናቅፈው ለውጥ መንግሥት ተጠያቂ ከመሆን አያመልጥም።
.
ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ ለውጡን ለመቀልበስ የሚጥሩ አካላትን መንግሥት ሥርዓት እንደሚያስይዝ ቃል ገብተው ነበር። እየሆነ ያለው ለምን ተቃራኒ ሆነ? ካሜራ ፊት ሌላ፣ ከውስጥ ሌላ እየተሠራ ነውን? መንግሥት የመጅሊስ ተቋም እንደዱሮው በካድሬ ቁጥጥር ሥር ሆኖ እንዲቀጥል ነው የሚፈልገው? ያ ከሆነ በግልጽ ይነገረንና እኛም ለረጅም ትግል እንዘጋጃለን! መንግሥት የአገሪቱ ግማሽ የሆነውን ሙስሊም ሕዝብ ፈቃድ ለማክበር ካልፈለገ እኛም እስከእስትንፋሳችን መጨረሻ ለመታገል አንሰንፍም!
.
ከታች ባለው ሐሽታግ ሐሳብዎን በመግለጽ ከሕዝብ ጋር ይቁሙ!
.
#አይዞህባዩማነው?

https://t.me/ALJUEDNEWS
ብዙሃኑ ሙስሊም መማር፣ መመረቅ እና ትልቅ ቦታ መድረስ ከሚሉት የህይወት እርከኖች ባልተናነሰ ሃጅ ማድረግ የሚለውንም ከልጅነቱ ጀምሮ ያልማል።

እኔም እንደ ብዙሃኑ ሙስሊም ሃጅ ማድረግ የሚለው ህልሜ ጠቅላይ ሚኒስትር፣ ጋዜጠኛ እና አስተማሪ መሆን ከሚሉት እቅዶቼ እኩል እድሜን አስቆጥሯል።

እኔና መሰሎቼ መማር፣ መመረቅ፣ ራስን መቻል እና መሰል ነገሮች በራስ ጥረት እና ምርጫ የሚደረስባቸው ነገሮች ስለሆኑ በቀላሉ ብናሳካቸውም የሃጁ ጉዳይ ግን የኢትዮጵያውያን ሙስሊሞችን የሃጅ ጉዞ ወኪልነት በብቸኝነት በያዘው መጅሊስ ሙሰኛ አመራሮች ምክንያት እስካሁን እያማረን ቀርቷል።

በአንዲት ድሃ ሃገር ኑሮ፣ ከመሰረታዊ ፍላጎቶች ተርፎ በሚጠራቀም ገንዘብ ሃጅ ለመሄድ ዘንድሮስ ሞላልኝ ሄድኩ ሲባል በየአመቱ የመጅሊሱ የሃጅ ጉዞ ዋጋ አላግባብ ይንራል።

ዋጋው የሚንረው ደግሞ ለሃጃጁ አስፈላጊ ወጪዎች ሳይሆን ሚልዮን ብሮች አላግባብ የሙሰኛ ጠምጣሚ ካድሬዎችን ኪስ እንዲያደልቡ መሆኑ ያበግናል።

አንድ ሰው በአለም ካሉ ሃገራት ውዱ የሚባል የሃጅ ክፍያን ከፍሎ ሃጅ እየሄደ የሚጠብቀው ከፍተኛ መንገላታት እና አሳፋሪ መስተንግዶ ደግሞ ይበልጥ ያበግናል።

ሃጅ መሄድ እፈልጋለው/ እንፈልጋለን ነገር ግን መዘረፍም ሆነ አላግባብ መንገላታት አንፈልግም።

የመጁሊሱ ሙሰኞች ለፍርድ ይቅረቡ፣ ቦታው ህዝቡን በአግባቡ ለማገልገል ፈቃደኛ ለሆኑ ሰዎች ይረከብ።

የመጅሊስን ብልሹ አሰራር ለማስተካከል፣ በሃይማኖታዊ ተቋሞቻችን ውስጥ የመንግስትን ጣልቃ ገብነት ለማስቆም፣ ሁሉን አቀፍ እና ኢትዮጵያውያን ሙስሊሞች በፍትህ የሚያገለግል ተቋም ለመመስረት እና መሰል እሴቶች ኢትዮጵያውያን ሙስሊሞች ያደረጉት/እያደረጉ ያሉት ትግል በሃገራችን ሰላማዊ ትግል ታሪክ ረጅሙ ነው።

ኢንሽአላህ ይህ ረጅም ትግል ፍሬ አፍርቶ የምንፈልገውን ለውጥ የምናይበት ቀን ሩቅ አይደለም። ዘንድሮ በፍፁም መዘረፍም ሆነ መንገላታት አንሻም፣ የአሰራር ለውጥ ሊመጣ እንዲሁም ሙሰኞች በቃችሁ ሊባሉ እና ለፍርድ ሊቀርቡ ይገባል።

#ዘንድሮምልንዘረፍ?
#የመጅሊስሙሰኞችለፍርድይቅረቡ

© Moonirah Abdelmenan
Cc Office of the Prime Minister-Ethiopia
https://t.me/ALJUEDNEWS
አንዳንድ መረጃዎች በመጅሊስ ጉባዔ ዙሪያ...
—————————
. © Isaac Eshetu
.
ከነገው ዕለት ጀምሮ ራሱን ለሽግግር ለማዘጋጀት ጠቅላይ ጉባዔውን መጥራት እና ለርክክብ መዘጋጀት የሚጠበቅበት ሕገ-ወጡ የመጅሊስ አሥተዳደር የሚያዝያ 23ቱ የዑለሞች እና ምሁራን ጉባዔ በባለአደራ አሥተዳደር ተረካቢነት እንዳይጠናቀቅ እና የሕዝቡ ጥያቄ ምላሽ እንዳያገኝ ጥረት እያደረገ ይገኛል። መጅሊሱ በተቋማዊ ለውጥ ኮሚቴው አማካኝነት ከመግለጫው ቀድሞ ለቀረበለት ጥያቄ ምላሽ ለመስጠት በቀን 16/08/2011 በቁጥር ጠ/ም/0/65/12/20/11 በመጅሊሱ ዋና ጸሐፊ በሐጂ አልፋድል አሊ ሙስጠፋ ፊርማ እና ማኅተም አማካኝነት በጻፈው ደብዳቤ የሚያዝያ 23ቱ ጉባዔ መዛወር እንዳለበት ገልጿል።
.
የሕዝበ-ሙስሊሙን የዓመታት ትግል እና የአስቸኳይ ለውጥን አስፈላጊነት ከምንም ባለመቁጠር «... ለዚህ ሁሉ አለመግባባት የሚዳርግ አጣዳፊ ነገር በሌለበት...» ስብሰባውን ለመጥራት እንደሚቸገር መወሰኑን በደብዳቤው የገለጸው መጅሊሱ በአመራሮቹ መካከል የሐሳብ ልዩነት መፈጠሩንም ማወቅ ተችሏል። ገሚሶቹ «የከፋ ነገር ሳይመጣ ጥለን እንሂድ፤ እምቢታችን አገራዊ ቀውስ ሊፈጥር ይችላል» የሚል አቋም ያንጸባረቁ ሲሆን አንዳንዶቹ ደግሞ መቀጠል እንዳለባቸው እና በፍርድ ቤት ሂደቱን ማዘግየት እንደሚችሉ አቋም ይዘዋል። «በድምጽ ብልጫ በጉባዔያችን ወስነናል» በሚል የመጅሊሱ እና የሚያዝያ 23ቱ ጉባዔዎች እርስ በእርስ እንዲቃረኑ በማድረግ ንትርክ እንዲነግሥ ለማድረግ ያቀዱ ሲሆን ጉባዔውን ረግጦ እስከመውጣት የደረሱ ሤራዎችንም በመጎንጎን ላይ ይገኛሉ።
.
የማዘግየቱ ሐሳብ ዋነኛ መግፍዔ ሕዝበ-ሙስሊሙ በስፋት በጉዳዩ ላይ በንቃት እንደሚሳተፍበት የሚጠበቀውን የረመዳን ወር በሥልጣናቸው ላይ እንዳሉ የማሳለፍ ፍላጎት ሲሆን ከሁለት ወራት በኋላ የሚካሄደውን የመጅሊሱ ዋነኛ የሙስና ምንጭ የሆነውን የሐጅ ጉዞ በማሥተናበር ለመጨረሻ ጊዜም ቢሆን የሙስና ገቢያቸውን ለማግኘት ያሰቡ መሆኑም ታውቋል። አንዳንድ የአመራር አባላት «ይህኛውን የሐጅ ጉዞ ሳናስተናብር በምንም መልኩ መውረድ የለብንም» የሚል አቋም እንደያዙም ማወቅ ተችሏል።
.
ለመጅሊሱ ሙያዊ እገዛ ለማድረግ የሕግ ባለሙያ የሆኑት ሐጂ ቃሲም ታጁዲን ዋና አጋዥ ሆነው እየተንቀሳቀሱ መሆናቸውን በተጨማሪ ማወቅ የተቻለ ሲሆን ለጉዳዩ ግላዊ ሃይማኖታዊ ተቆርቋሪነት እንደማያሳይ የገመቱትን አንድ ሙስሊም ያልሆነ ጠበቃ ማናገራቸውንም ማጣራት ተችሏል።
.
የመጅሊሱን ደብዳቤ የጻፉት ሐጂ አልፋዲል ዓሊ የመጅሊሱ ዋና ጸሐፊ ሲሆኑ በሕወሓቱ የሊባኖስ አሕባሽ-ጠበቃ ፕሮጀክት ወቅት ከፍተኛ ሚና ሲጫወት ከነበረውና ሰሞኑን ሚስቱ እና ሕፃን ልጁን በአሥተናባሪነት ስም በማስመዝገብ የሐጅ አበል ሲመዘብር እንደነበር የተጋለጠው ሸኽ ዑመር ይማም (ዑመር ኮምቦልቻ) ጋር እጅና ጓንት ሆነው የሚሠሩ መሆናቸው ይታወቃል።
.
—————————
መንግሥት በሕዝበ-ሙስሊሙ ፋንታ የመጅሊሱን ማፊያዎች የሚመርጥ ከሆነ ለምን በግልጽ አይናገርም?
—————————
.
የዶ/ር ዐቢይ መንግሥት ኮሚቴውን ሲያቋቁም ለውጡን ለመቀልበስ የሚሞክሩ አካላትን በዝምታ እንደማያይ ቃል ገብቶ ነበር። አሁን ግን የመጅሊሱ የለውጥ ቅልበሳ ድፍረት ሲታይ መንግሥት ራሱ ካሜራ ፊት ሌላ እያወራ ከጀርባ ግን ሕዝብ የሰጠውን የመጨረሻ ዕድል እያበላሸ ያለውን መጅሊስ «አይዞህ» እያለ ያለ ነው የሚመስለው። የፈለገ ቢሆን መንግሥት ራሱ አምጥቶ የጫነብንን ካድሬዎች የማስወገድ ኃላፊነት አለበት። የሕዝቡን ድምጽ አክብሮ እርምጃ የማይወስድ ከሆነ ግን የሁለቱ ጉባዔዎች ስኬታማ መሆን የሕልውና ጥያቄ በመሆኑ ሕዝበ-ሙስሊሙ መጅሊሱ ላይ በራሱ እርምጃ ለመውሰድ ይገደዳል። መንግሥትም በመጅሊሱ ለውጥ ቅልበሳ «ገለልተኝነት» መርጦ በሕዝቡ እርምጃ ጣልቃ ሊገባ እንደማይችል ሊያውቀው ይገባል። መጅሊሱ ለውጡን ለመቀልበስ ሲታትር በዝምታ እየተመለከቱ ሕዝበ-ሙስሊሙ ተቋሙን ለማስከበር ሲንቀሳቀስ እንቅፋት መፍጠር በምንም መልኩ ተቀባይነት የለውም።
.
ከዚያም ውጭ መንግሥት በሕዝበ-ሙስሊሙ ፋንታ የመጅሊሱን ማፊያዎች የሚመርጥ ከሆነ በግልጽ ሳይሸፋፍን ይናገር። ያኔ እኛም ማንን መታገል እንዳለብን ጥርት ያለ ምስል ይኖረናል!
.
#አይዞህባዩማነው? #የህዝብወይስየሌባወገን? #መጅቴክ
.

Office of the Prime Minister-Ethiopia
Ministry of Peace የሰላም ሚኒስቴር

https://t.me/ALJUEDNEWS
#አዲስ ዜና አለኝ!

የፌዴራልና የክልል መጅሊስ ሹማምንት በስምምነቱ መሠረት በነገው እለት በሚያካኼዱት ጠቅላላ ጉባዔ ሁሉም በገዛ ፈቃዳቸው ሥልጣቸውን ለመልቀቅ ስምምነት መደረሱ ይታወቃል፡፡ ኾኖም ዛሬ እሁድ የፌዴራል መጅሊሱና የአዲስ አበባ መጅሊስ ሹመኞች ባደረጉት ቅድመ-ጉባዔ (ሕጋዊነቱን እጠራጠራለሁ) ብዙዎቹ ከሥልጣናቸው ለመልቀቅ ፈቃድኝነታቸውን አሳይተዋል ቢባልም፣ በመጅሊሱ ውስጥ የአሕባሽን ፕሮጀክት የሚያስፈጽሙት ሹመኞች በተለይም ኡመር ይማም (በበረሃ ስሙ ኡመር ኮምቦልቻ 😆 ) ‹‹ሥልጣኑን ለ‹ወሃቢያ› አንለቅም፣ እስከመጨረሻውም እንታገላለን›› የሚል አቋም አራምደዋል፡፡ የቅደም-ጉባዔው ተሳታፊዎችም በዚህ አቋም የኋላ-ኋላ ተስማምተው ጉባኤው እንደተጠናቀቀ ሰምቻለሁ፡፡ በመኾኑም የጉባዔው አባላት ነገ በሚደረገው የጠቅላላ ጉባዔ፣ ተሳታፊዎች በሙሉ ይኼንኑ አቋም እንዲያንጸባርቁና ሕገ-ወጡን መጅሊስ አዲስ ባጀት ጭምር በማጸደቅ ለማስቀጠል ስምምነት ላይ እንዲደርሱ የማሳመንና የማስወሰን ውሳኔ ላይ ደርሰው ተለያይተዋል፡፡

በዚህም መሠረት የፌታችን ረቡእ ሚያዚያ 23 በሚደረገው የ9ኙ ተቋማዊ ለውጥ ኮሚቴ የሽግግር መጅሊስና አዲስ የኡለማ ካውንስል ምሥረታ ላይ የሚገኙት ሕገ-ወጥ የመጅሊስ ሹመኞች፣ የጠቅላላ ጉባዔ አባላቶቻቸው በሕገ-ወጥነት ከመመረጡ በላይ የሥራ ዘመኑንም ጭምር የጨረሰውን መጅሊስ ባለበት ለማስቀጠል መስማማታቸውን በመግለጽ የአዲሱን የሽግግር መጅሊስ ምሥረታ እንደማይቀበሉ ለመግለጽ እቅድ አውጥተዋል፡፡ በተጨማሪም የተቋማዊ ለውጥ ኮሚቴው በሚያዋቅረው አዲስ የኡለማ ካውንስል ውስጥ ከየመን በዶክትሬት ተመርቋል የተባለ አንድ የሊባኖሱ የአሕባሽ ድርጅት AICP የኢትዮጵያ ተጠሪ ግለሰብን ዋና ጸሐፊ ለማስደረግ እቅድ ተይዟል፡፡

የመጅሊሱ ሹመኞች ዛሬ በደረሱበት ጉባዔ ላይ አዲሱ መንግሥት ሥልጣን ከየዘ ወዲህ ሸሽቶ መቐሌ ገብቶ የነበረው አቶ ጀማል ወይም በስፋት የሚታወቅበት ስሙ አቶ ገብሬ በመጅሊሱ ጊቢ ውስጥ መታየቱን የአይን ምንጮቼ ገልጸውልኛል፡፡ አቶ ጀማል ‹‹ገብሬ›› የሚለውን ስሙን ወደ ሙሐመድ ሳላሕ በመለወጥ ‹‹ሰልሚያለሁ›› በሚል በመጅሊሱ በጽ/ቤት ኋላፊትና በሌሎችም ዘርፎች ላይ ሹመኛ ኾኖ የቆየ ሲኾን፤ ከእነ ሐሰን ታጁ ጋር በመኾን የለውጥ እንቅስቃሴውን በማደናቀፍ ላይ ያለው የኑር መስጂድ አሥተዳደር መንሡር ጋርም የጠበቀ ግንኙነት እንዳለው ከዚህ ቀደም ተዘግቧል፡፡ አሁን የተገኙ መረጃዎች አቶ ገብሬ አሁንም ከለውጥ አደናቃፊው ቡድን ጋር በጋራ እየሠራ እንደኾነ አመላክተዋል፡፡ ገብሬ በተደጋጋሚ የማጭበርበር ወንጀል ከመጅሊሱ ተባሯል ሲባል ቢቆይም በተቋሙ ቁልፍ ሥልጣን ያለው ግለሰቡ ኾኖ ቆይቷል፡፡

አቶ ገብሬ ማን እንደኾነ ለማስታወስ እንዲረዳ በስርቆት የተባረረበትን ደብዳቤ ጨምሮ ሙሉ መረጃ በቀጣይ እለቃለሁ፡፡
© Akemel Negash
https://t.me/ALJUEDNEWS
የለውጥ አደናቃፊው ቡድን ውስጥ ከፍተኛ ሚና ያለው አቶ ገብሬ ማን ነው?
© Akemel Negash

በ 24/06/01 በቃለ ጉባዔ ቁጥር ስ/አ/ኮ/307 መሠረት በተጻፈና በመጅሊሱ ፕሬዚዳንት በሸኽ አሕመዲን ዓብዱላሂ በተፈረመ ደብዳቤ የጠቅላይ ምክር ቤቱ ጽ/ቤት ኃላፊ ተደርጎ የተሾሙት አቶ ጀማል (ገብሬ) ከዚህ በፊት ሙስናና ማጭበርበርን ጨምሮ በበርካታ ወንጀሎች የተከሰሰ ነው። አቶ ጀማል የመጅሊሱ ፖስተኛ በነበረበት ወቅት አቶ ከሊፋ ሙስጠፋ የተባሉ ግለሰብና የሁለት ልጆቻቸውን 14,802 ብር አጭበርብሮ ከተቀበለ በኋላ እንደተሰወረ በመግለጽ በወቅቱ የጠቅላይ ምክር ቤቱ ምክትል ፕሬዚዳንት የነበሩት ሼሕ አሕመድ ሙሐመድ ኪቦ ለወረዳ 16 ፖሊስ ደብዳቤ ጽፈው ነበር። በቁጥር ጠ/ም/0646/45/94 በተፃፈው በዚሁ ደብዳቤ ‹‹የግለሰቡ የማጭበርበር ድርጊት ተገቢ የሆነ ሕጋዊ እርምጃ ይወሰድበት ዘንድ የወረዳ 16 ፖሊስ በአስቸኳይ ግለሰቡን በቁጥጥር ሥር አውሎ ገንዘባቸውን የተቀሙት ግለሰቦች ውሳኔ እንዲያገኙ›› ሲሉ አመልክተዋል።

የአቶ ጀማል የግል ማኅደር እንደሚያመለክተው ከ 1991 ጀምሮ ለበርካታ ጊዜያት የማስጠንቀቂያ ደብዳቤ ደርሶታል። ግለሰቡ ከስህተቱ ሊታረም ባለመቻሉም ሰኔ 23 ቀን 1991 በቁጥር ጠ/ጉ/6369/54/91 በተጻፈ ደብዳቤ የመጨረሻ ማስጠንቀቂያ እንደተሰጠው በመግለጽ በአሥተዳደርና ፋይናንስ መምሪያ ኃላፊው በአቶ ኑረዲን ሙሐመድ በተፈረመው ደብዳቤ ሰኔ 24 ቀን ከሥራው ተሰናብቷል። ግለሰቡ ተመልሶ ወደ መጅሊስ ከገባ በኋላም ማጭበርበሩን እንዳላቆመ መስከረም 30፣ 1993 ከበላይ አለቃው ከአቶ መዚድ ሰይድ ቡደላ ለጠቅላይ ምክር ቤቱ ጽ/ቤት የተጻፈ ደብዳቤ ያስረዳል።

አቶ ጀማልን አስመልክተው የተጻፉት የስርቆት ክስ እና የሹመት ደብዳቤዎችን አያይዣለሁ::

https://t.me/ALJUEDNEWS
—————————
መጅሊስ እና የዝምድና ቅጥሮቹ - ናሙና 1
—————————
via Isaac Eshetu
.
በሕገ-ወጥ ሕወሓት አመጣሽ ሹማምንት መዳፍ ሥር ወደሙስና መናኸሪያነት የተቀየረው መጅሊስ (The Ethiopian Islamic Affairs Supreme Council) የኃላፊነት ቦታዎቹ በሙያ ሳይሆን የጥቅም ትስስር ባጠበቀው የሥጋ ዝምድና የተጠረነፉ መሆናቸው አሳዛኝ እውነታችን ነው። ዘመዳሞች ተጠራርተው ሠፍረውባቸዋል። ይህም በውስጡ ለሚፈጸሙ የሙስና ወንጀሎች ዋነኛ ማነሣሻ እና መደበቂያ ምሽግ እንዲፈጠር አድርጓል። ለጊዜው አንድ ናሙና ወስደን እንመልከት፦
.
በምስሉ ላይ የምትመለከቱት ግለሰብ የፌዴራል መጅሊሱ የቤኒሻንጉል ተወካይ እና የመጅሊሱ ዋና ጸሐፊ ሐጂ አልፋድል አሊ ሙስጠፋ ሲሆን የሕወሓት አሕባሽ ፕሮጀክት አስፈጻሚ ከሆነው ሸኽ ዑመር ይማም (ዑመር ኮምቦልቻ) ጋር እጅና ጓንት ሆኖ ይሠራል። ይህ ግለሰብ ብቻውን 7 የቅርብ ዘመዶቹን አምጥቶ በመጅሊሱ እና በሚያሥተዳድራቸው ተቋማት ውስጥ አስቀጥሯል። የልማት ኤጀንሲው የፋይናንስ ክፍል ኃላፊ አቶ አሕመድ እሸቱ የባለቤቱ ወንድም ሲሆን የፒያሳ አወሊያ ቅርንጫፍ ምክትል ዳይሬክተሯ ወ/ሮ ኢማን በቀለ፣ የዐረብኛ እና የዲን ዘርፍ ኃላፊው አቶ ዐብዱልዓሊም፣ ሴክሬተሪው ወ/ሮ ሳሚያ፣ ሹፌሩ አቶ ኑረዳኢም፣ የአልፋ ሕንፃ ጸሐፊ ወ/ሮ ከልቱም ሙሣ እና የጠቅላይ ምክር ቤቱ ጥበቃ አቶ ሙስጠፋ በሙሉ የሥጋ ዘመዶቹ ናቸው።
.
.
#ዘንድሮምልንዘረፍ?
#የመጅሊስሙሰኞችለፍርድይቅረቡ

https://t.me/ALJUEDNEWS
በመልቀቂያ ድራማ አንሸወድም!

ለሚሆነው ሁሉ መንግስትም ተጠያቂ ከመሆን አይዘልም!

ሕዝበ‐ሙስሊሙን ከሚበዘብዝበት ሥልጣን አልወርድ ያለው ሕገ‐ወጡ የመጅሊስ አመራር አሁንም በ«አይዞህ ባዮች» አደፋፋሪነት በሚመስል ሁኔታ ድራማ መሥራቱን ቀጥሏል። የሕወሓቱ የአሕባሽ ፕሮጀክት ቁልፍ ሰው በሆነው ዑመር ኮምቦልቻ ሲዘወር የነበረው አመራር እምብዛም ተጽእኖ ያልነበረውን ፕሬዚደንቱን በማንሣት ለውጥ የመጣ ለማስመሰል እየሞከረ ነው።
.
———
«አማናውን ተቀብያለሁ» ዑመር ኮምቦልቻ
———
ተወዳጁ አባታችን ተቀዳሚ ሙፍቲ ሐጂ ዑመር ኢድሪስ ሲሰደቡ እና ሲወገዙ ባረፈዱበት በዛሬው የመጅሊስ ጉባዔ «መልቀቂያውን» ያስገባው ፕሬዚደንቱ ሐጂ ሙሐመድ አሚን በመተዳደሪያ ደንቡ መሠረት ቦታውን ለሙሰኛው ዑመር ኮምቦልቻ ማስረከቡ ተረጋግጧል። ከቀናት በፊት በሕፃን ልጁ እና በሚስቱ ስም የሐጅ መሥተንግዶ አበል ሲመዘብር እንደነበር የተረጋገጠበት ይኸው ዑመር ኮምቦልቻም «አማናውን ተቀብያለሁ» ብሎ ሥልጣኑን ተረክቧል። በቀሪው የስብሰባው ጊዜም አመራሩ ሥልጣኑን እንዴት እንደሚያስቀጥል እና ስለበጀት ጉዳይ የሚወያዩ ይሆናል።
.
ይህ ውሳኔ ምን ያክል የሚያዝያ 23ቱን ጉባዔ በማደናቀፍ ሕዝበ‐ሙስሊሙን ሊያስቆጣ እንደሚችል ግልጽ ነው። ሕዝበ‐ሙስሊሙ ሁሉም የመጅሊሱ አመራሮች ሥልጣናቸውን ከሁሉም መዝሃብ ለሚውጣጡ ዑለሞችና ምሁራን ከማስረከብ በታች ያለን መፍትሔ አይቀበልም! እናም አንሸወድም!!!
.
———
የ«እንልቀቅ» — «አትለቁም» ድራማ
———
.
ሕገ‐ወጡ የመጅሊስ አሥተዳደር ትናንት ያቀደው እና ዛሬ እየተወነው ያለው ተውኔት ርዕስ «እንልቀቅ — አትለቁም» ነው። የሥራ አስፈጻሚ አባላት ትናንት በተስማሙት መሠረት «እንለቃለን» ይላሉ። የዛሬው ጉባዔ ላይ ያቀርባሉ። በሕወሓት ምርጫ የተቀመጡት የጠቅላላ ጉባዔ አባላት ደግሞ «በጭራሽ አትለቁም» ይላሉ። ከዚያ «መቼስ ጠቅላይ ጉባዔው አትለቁም ካለ ምን ይደረጋል» ይሉና የሚያዝያ 23 ጉባዔ ላይ «አትልቀቁ ስለተባልን አንለቅም» ይላሉ። ክርክር፣ ንትርክ፣ ፍርድ ቤት ጉተታ ሌላም ሌላም…! በመካከል «ረመዳን ያልፋል! የአንድ ተጨማሪ ሐጅ ሙስና እናገኛለን» የሚል ተስፋ ሠንቀዋል! እናም አንሸወድም!!!
.
———
ለሚሆነው ሁሉ መንግሥትም ተጠያቂ ከመሆን አይዘልም!
———
.
ሕገ‐ወጡን የመጅሊስ አሥተዳደር አምጥቶ የሾመብን መንግሥት ነው። አሁን እየፈጸሙት ያለው ድፍረት ምንጭ እና አይዞህ ባይም መንግሥት ከመሆን እንደማይዘል ብዙኃኑ ሙስሊም ያምናል። የጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐብይ አሕመድ አሥተዳደር ምን እየሠራ እንደሆነ ራሱን ሊፈትሽ ይገባል። ከተለያዩ የማኅበረሰብ ክፍሎች ጋር መጋጨት ሕወሓት መራሹን ኢሕአዴግን አልጠቀመውም። አዲሱን አመራርም አይጠቅመውም።
.
ዛሬ ካሜራ ፊት መልካም ንግግሮችን በመናገር የሚሸወድ ትውልድ የለም። ትውልዱ ተግባር ይፈልጋል። Office of the Prime Minister-Ethiopia ዋና ተግባሩ የሕዝብን ድምጽ ማዳመጥ አይደለምን? Ministry of Peace የሰላም ሚኒስቴር ሥራው የአገርን ሠላም ማስጠበቅ አይደለምን? ለምን ከኢትዮጵያዊው ሙስሊም ጋር የመጋጨትን መንገድ ትመርጣላችሁ? ይህ ነው መደመር? ይህ ነው አንድነትን ማበረታታት? ለዚህ ነው ኮሚቴ ተቋቁሞ 10 ወር የተለፋው? እንዲህማ አትቀልዱብንም! በፍጹም አንሸወድም!!!
.
#አይዞህባዩማነው? #የህዝብወይስየሌባወገን? #መጅቴክ

ሼር በማድረግ እና ሐሽታጎቹን በመጠቀም ከሕዝብ ጎን ይቁሙ!
https://t.me/ALJUEDNEWS
ቅጽ 1፣ ቁጥር 07 - ጁምዐ።
Tuariq Magazine - ጧሪቅ መጽሔት
በ2010 የሐጅ ወቅት ብቻ 333.5 ሚሊዮን ብር በመጅሊስ ሹመኞችና ከእነሱ ጋር የጥቅም ትስስር ባላቸው ግለሰቦች ተመዝብሯል፡፡

ይኼ ወንጀል የተሠራው አዲሱ የጠ/ሚኒስትር አብይ መንግሥት ወደ ሥልጣን ከመጣ ወዲህ ነው፡፡

በመጅሊሱ ውስጥ ለዓመታት ሙስና ሲፈጽሙ የኖሩና በሕወሓት/ኢሕአዴግ ቀጥተኛ ድጋፍ ወደ ሥልጣን የመጡ ከኤሊያስ ሬድማን ጀምሮ ያሉ ግለሰቦች ለፍርድ እንዲቀርቡ ድጋፍ ለመጠየቅ ይፋዊ ፒቲሽን ማሰባሰብ እንጀምራለን፡፡

ሁላችንም ንቁ ተሳትፎ እንድናሳይ በአክብሮት እጠይቃለሁ፡፡

© Akemel Negash

#ለውጥማአለ
#አይዞህባዩማነው?
#ዘንድሮምልንዘረፍ?
#የመጅሊስሙሰኞችለፍርድይቅረቡ
በፌድራል መጅሊስ የሀጅና ኡመር ዘርፍ ሃላፊ ሁኖ የሚሰራው አሕመድ የሱፍ ከመጅሊሱ ምክትል ፕሬዝዳንቱ ኡመር ኮምቦልቻ ጋር የአንድ መንደር ሰው መሆናቸውና ልዩ የጥቅም ትስስር እንዳላቸው ታውቋል።
በዚህ ምክኒያት ኡመር ይማም በርካታ ዘመዶቹን ወደ ሀጅ መላኩ ታውቋል።

ኡመር ይማም በልኡካን ቡድን ስም ገንዘብ ከመዘበረባቸው አዲስ ያገኘነው መረጃ የሚከተለው ነው
- ኑሩ ይማም የኡመር ኮምቦልቻ ወንድም
-የሱፍ ይማም የኡመር ኮምቦልቻ ወንድም
የየሱፍ ይማም ልጅ --የኡመር ኮምቦልቻ የወንድም ልጅ
ሼህ ኡመር ጀሜ - የኡመር ኮምቦልቻ የእህቱ ባል
ሌሎችም ዘመዶቹ ይገኙበታል።

ከዚህ ቀደም ምንም በጨቅላ ልጁና ሚስቱ የፈጸመውን ምዝበራ ማየታቸው ይታወቃል።
ኡመር ኮምቦልቻ በሱ መንገድ ለተከተሉ ወንድሞቹና ዘመዶቹ እንጅ ውህብያ ለሚላቸው ዘመዶቹ ወንድሙ አሊ ይማምን ጨምሮ ካፊር ነው በማለት ጸበኛ መሆኑ ታውቋል።

ግለሰቡ ይህን ሁሉ ምዝበራ በህዝበ ሙስሊሙ ላይ ከፈጸመ በሁላ አሁን ስልጣን ላለመልቀቅ ከፍተኛ ተጋድሎ እያደረገ ሲሆን ሙስሊሙ ማህበረሰብ ላይ በፈጸመው ምዝበራ እንዲጠየቅለት ህዝቡ ይፈልጋል ።

https://t.me/ALJUEDNEWS
#update የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ፕሬዚዳንት ሼህ መሀመድ አሚን ጀማል ያቀረቡት የስራ መልቀቂያ በጉባኤው ተቀባይነት ሳያገኝ ቀርቷል። ፕሬዚዳንቱ ዛሬ እየተካሄደ ባለው ጉባኤ በጤና ችግር ምክንያት ከዚህ ቀደም ያቀረቡት የስራ መልቀቂያ ተቀባይነት ያገኝ ዘንድ ጥያቄ ቢያቀርቡም ተቀባይነት ሳያገኝ ቀርቷል።

የመደበኛ ጠቅላላ ጉባኤ አባላቱ እስካሁን በጥሩ መንገድ ሲመሩት የነበረውን ተቋም ምርጫ እስከሚካሄድ አልያም በቀጣይ ረቡዕ በሚካሄደው ሀገራዊ ጉባኤ መጅሊሱን የተመለከቱ ውሳኔዎች እስከሚታወቁ በሃላፊነታቸው እንዲቀጥሉ ጠይቀዋል። የጤናቸው ጉዳይ አሳሳቢ ቢሆንም በሙስሊሙ ማህበረሰብ ዘንድ የተጣለባቸውን ሃይማኖታዊ ሃላፊነት እየተወጡ እንዲቀጥሉም አባላቱ ጥያቄ አቅርበዋል።

በመጨረሻም ጉባኤው #ፕሬዚዳንቱ በሃላፊነታቸው እንዲቀጥሉ ወስኗል። ጉባኤው በመድረኩ በተቋሙ ውስጥ የሚካሄደውን ለውጥ የሚመሩ 10 አባላት ያሉትን ኮሚቴም አዋቅሯል።

Via FBC
https://t.me/ALJUEDNEWS
በ"ጉዳያችን" ፕሮግራም ከኢትዮጲያ ፌዴራል መጅሊስ ፕሬዝዳንት እና የስራ አስፈፃሚዎች ጋር ወንድም ዲኑ ዓሊ ያደረገው ቆይታ ክፍል 1 ዛሬ ምሽት 2፡30 በዛውያ ቲቪ ይቀርብላችኋል፡፡
ዛውያ ቲቪ
ተግባራዊ ዳዕዋ!
#EthioMuslims #EthioMuslimCommittee
****
«የሚያዚያ 23ቱ ጉባኤ መሳካት የኢትዮጵያ ሙስሊሞች ጥያቄ መሳካት ጅምር ነው!»
«ይህን ጅምር ህዝቡ በንቃትና በጥንቃቄ እንዲከታተለው ጥሪያችንን እናስተላልፋለን!»
«ኮሚቴያችን የህዝበ ሙስሊሙ ተቋም ህዝቡ በምርጫ በመረጣቸው መሪዎች በቋሚነት እስኪቋቋም ድረስ የህዝብ ውክልናውን ከግብ ለማድረስ ጥረቱን ይቀጥላል!»
«በነገው ጉባኤ የሽግግር መጅሊስ ቦርድ በማቋቋም የመጅሊስ አመራሮችን መተካት ለድርድር የማይቀርብ የጉባኤው የውሳኔ አጀንዳ ነው!»
የሚያዝያ 23ቱን ጉባኤ አስመልክቶ ከ17ቱ የሙስሊም መፍትሄ አፈላላጊ ኮሚቴ የተሰጠ መግለጫ
ማክሰኞ ሚያዝያ 22/2011
አዲስ አበባ/ኢትዮጵያ
****
©ድምፃችን ይሰማ

የኢትዮጵያ ሙስሊሞች ተቋማዊ ለውጥ የጋራ ኮሚቴ መጋቢት 17/2011 በሰጠው መግለጫ መሰረት ነገ ሚያዚያ 23/2011 የሚደረገው ጉባኤ የኢትዮጵያውያን ሙስሊሞችን መሪ ድርጅት የወደፊት ዕጣፈንታ የሚወስነው ጅምር ሂደት የሚጠነሰስበት እንደሆነ ይታወቃል። በዕለቱ በዋናነት በህዝበ ሙስሊሙ ላይ በህገ-ወጥ መንገድ የተጫኑበትን የመጅሊስ አመራሮች ከላይ እስከታች በማውረድ ዋናውን ምርጫ የሚያመቻች የሽግግር ቦርድ የማቋቋም ስራ የሚሰራ መሆኑን 9ኙ ኮሚቴ በመግለጫው ጠቀሷል።

ይህ ውሳኔ በተጠቀሰው መሰረት የግድ መከናወን የሚኖርበት ሲሆን በዚሁ ጉባኤ ከሁሉም ወገን የተውጣጡ የዑለማ ምክር ቤት አባላት ተመርጠው ነባሩን የዑለማ ምክር ቤት እንዲተኩ መደረጉም የግድ መፈጸም ካለባቸው ተግባራት ይመደባል።

እነዚህ ሁለት መሰረታዊ ተግባራት ለአገራችን ሙስሊም ማህበረሰብ ጥያቄ ምላሽ ለማግኘት መሰረታዊ እርምጃ እንደሆኑ ቢታመንም በትናንትናው ዕለት ሚያዚያ 21/2011 15ኛ ጠቅላላ ጉባኤውን ያደረገው ህገ ወጡ መጅሊስ ግን በገዛ ፈቃዱ ወርዶ ቦታውን ለማስረከብ ከመዘጋጀት ይልቅ የህገ ወጡን ፕሬዚደንት መልቀቅና መመለስ ዋና አጀንዳ አድርጎ ድራማ ሲሰራ መዋሉ ለነገው ጉባኤ የታሰበ ሴራ ለመኖሩ ጠቋሚ መሆኑ አያጠራጥርም። ስለሆነም ህዝበ ሙስሊሙ ከነገው የሚያዚያ 23/2011 ጉባኤ እየጠበቀ ያለውን መሰረታዊ ተግባራት በግልጽ ልናስቀምጥ እንወዳለን፡-

• የሽግግር መጅሊስ ቦርድ ምስረታ፤
• አሁን ያለው የመጅሊስ አመራር ከስልጣን መውረድ፤
• አዲስና ሁሉን አቀፍ የዑለማ ምክር ቤት መቋቋም፤

መፍትሄ አፈላላጊ ኮሚቴያችን እኒህ መሰረታዊ አጀንዳዎች ለድርድር የማይቀርቡ መሆናቸውን የሚያምን ሲሆን በዚህ ረገድ የተለየ ሃሳብና አቋም ለማንጸባረቅ የሚሞከር ከሆነም በቸልታ የማይመለከተው መሆኑን ይገልጻል። ህዝቡም ይህ ወሳኝ ጉባኤ የሚጠበቅበትን ይወስን ዘንድ ጉዳዩን በአንክሮ እንዲከታተል ይጠይቃል።

መንግስትም ቢሆን አሁን እየተካሄደ ያለውን ሂደት ለመደገፍ ያሳየውን ተነሳሽነት በማሳደግ የህዝብ ጥያቄ በአግባቡ እንዲመለስ የሚደረገውን ማንኛውም ጥረት እንዲያግዝ ኮሚቴያችን ጥሪውን እያቀረበ በተጻራሪ ወገን በመቆም ይህን ጉባኤ እንዳይሳካ ያላሰለሰ ጥረት ለማድረግ እየተዘጋጁ ያሉ አካላት ህዝብን አስቆጥተው ወደ አላስፈላጊ አቅጣጫ እንዲጓዝ ከማድረግ እንዲቆጠቡ ያሳስባል። መንግስትም የማደናቀፍ ሙከራዎችን በዝምታ እንዳይመለከት ኮሚቴያችን ያሳስባል።

አላሁ አክበር!

https://t.me/ALJUEDNEWS