ቅንድል ኢትዮጵያ
2.7K subscribers
507 photos
28 videos
26 files
239 links
ቅንድል ዲጂታል መፅሔት በቅንድል ኢትዮጵያ የባለራዕይ ወጣቶች ተዘጋጅቶ በቅንድል ዲጂታል ሚዲያ የሚቀርብ በማህበራዊ፣ ሀገራዊ፣ ስነ-ልቦናዊ፣ ቴክኖሎጂ፣ ባህል፣ ጥበብና ጤና ነክ ጉዳዮች ዙሪያ የሚያተኩር ዲጂታል መፅሔት ነው፡፡
#ቅንነት_ድል_ያደርጋል!
https://m.facebook.com/kdigitalmagazine
Www.kdigitalmagazine@gmail.com

ለ አስተያየት @KenDelBot
Download Telegram
የዛሬ አመት በዛሬው ቀን ለተገደሉት የቀድሞው የኢትዮጵያ ጦር ሀይሎች ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ጀነራል ሰአረ መኮንን አዲስ አበባ ውስጥ መንገድ ተሰይሟል!

በዚህም መሰረት ከአትላስ እስከ ሩዋንዳ አደባባይ ያለው መንገድ በጀነራሉ ስም ተሰይሟል።
ፎቶ: ኤልያስ ገ/ስላሴ
@kendelM
@KendelM
የኤርትራ ፕሬስ ሚዲያ አሁን ይፋ ባደረገው መረጃ!

#ኢትዮጵያ እና #ኤርትራ የጥምር ጦር ወታደራዊ ልምምድ ማድረግ አለባቸው የሚል ሀሳብ እንደሚደግፋ ገልፃል።

ይህም ከሆነ ይህ ወታደራዊ የጥምር ጦር ልምምድ ከዚህ በፊት ኖሮ የማያውቅ እና የመጀመሪያው የኢትዮ-ኤርትራ የጥምር ጦር ልምምድ ነው የሚሆነው። ይህም የጦር ልምምድ ብዙ ጥቅም ሊኖረው ይችላል ብሎል የኤርትራው ፕሬስ ሚዲያ።

የሁለቱን ሀገራት ወዳጅነት ከማጠናከር አልፎ የሁለቱ ሀገራት ጥምር ጦር ለድንበር ፀጥታ እና ከሀገር ውስጥም ሆነ ከሀገር ውጭ የሚመጣን ጠላት ለመመከት ከፍተኛ ሚና ይኖረዋል ሲል ዘግቦል።

© Eritrea Press
https://t.me/KenDelM/411

Kendel on Telegram
http://t.me/KendelM

🔺🀄️🀄️ሉን🔺
ዜና እረፍት

በኢትዮጵያ የሙዚቃ ታሪክ በድምፃዊነት በዜማና ግጥም ስራው ትልቅ አሻራ ያኖረውና እርሱም በማቀንቀን የሚታወቀው ሱራፌል አበበ ዛሬ ከዚህ አለም ተለይቷል።

የተወዳጁ ድምፃዊ ብስራት ሱራፌል አባት የሆነው ሱራፌል አበበ ቀብርና ዝርዝር መረጃ እንደደረሰን እንገልጻለን።

ኢትዮ ኤፍ ኤም ለሟች ቤተሰብ እና አድናቂዎች መጽናናትን ይመኛል።

ኢትዮ ኤፍ ኤም የኢትዮጵያዊያን
ሰኔ 15 ቀን 2012 ዓ.ም

Kendel On FaceBook
http://m.facebook.com/kdigitalmagazine

🔺🀄️🀄️ሉን🔺
#ቅንድል_ዲጂታል_መፅሔት
ከቁጥር በላይ ቅንነትን እያበዛን ፣ ምክንያታዊነትን እያጎለበትን ፣ ሀገር ፍቅርን ከፍ ባለ ድምፅ እየሰበክን ፣ ዘገዩ ሲሉ እየፈጠንን ፣ ከእኔነት ሹመት እኛነት ዙፍን ከፍ እያልን በልዩና ማራኪ ፅሑፍ ወራችንን ጠብቀን ከተፍ ብለናል፡፡ በኢትዮጽያ ህዝብ ቅንነትና ፀሎት ዛሬ የደረሰው ሙላለም ታከለ የሀገሩን ህዝብ ደግነት ሊመሰክር በብሩሀን ገፅ ከቅንድል ጋር ቆይታ አድርጓል ይህንና ሌሎች አዝናኝ ፣ አስተማሪ ፣ ሀገራኛ ፅሑፎች በቅንድል ዲጂታል መፅሔት ይጠብቁን፡፡


★ቅፅ-፪ ቁጥር-፫

★በቅርብ ቀን | Coming Soon!

የበፊት እትሞች ለመከታተል
ይሄንን ይጫኑ

👇👇👇👇
@kendelM
@kendelM
ጥበብ
ቅንነት ድል ያደርጋል!!!
Kendel on Telegram
http://t.me/KendelM
Kendel On FaceBook
http://m.facebook.com/kdigitalmagazine

🔺🀄️🀄️ሉን🔺
🖍ኢትዮጵያ ፣ ግብጽና ሱዳን ከግድቡ ጋር በተያያዘ ባደረጓቸው ድርድሮች የግብጽ ወገን የተለያዩ አጀንዳዎችን እያቀረበ ውይይቱን ውጤት አልባ ለማድረግ ተዘጋጅቶ ይመጣ እንደነበር የ ኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ገለጡ።

የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ገዱ አንዳርጋቸው በህዳሴው ግድብ ዙሪያ ከአልጀዚራ አረብኛ ስርጭት ጋር ባደረጉት ቆይታ ግብጽ የራሷን ፍላጎት ብቻ ለመጫን ትሰራ እንደነበርም አስረድተዋል።

ግብጽ በጎረቤት ሀገሮች ላይ የጦር ካምፕ ለመመስረትና የኢትዮጵያን ደህንነት ለመፈታተን የምታደርገውን ጥረት በተመለከተ ለቀረበላቸው ጥያቄ ሚኒስትሩ በሰጡት ምላሽ ግብጽ የተለያዩ ሙከራዎችን በማድረግ ላይ መሆኗን ገልጸው ነገር ግን ኢትዮጵያ ከሱዳን፣ ጅቡቲ፣ ኬንያ፣ ሶማሊያ፣ ደቡብ ሱዳን እና ኤርትራ ጋር ጠንካራ ግንኙነት ያላት በመሆኑ ሙከራው የማይሳካ ህልም ነው ብለዋል።

ምንጭ : ኢቢስ ቲቪ

Kendel On FaceBook
http://m.facebook.com/kdigitalmagazine

🔺🀄️🀄️ሉን🔺
ግድብና ናይና እዩ!!
እሽካዕ ልውዳእ ድጋፍና ቀፃሊ እዩ!! #FillTheDam
Kendel on Telegram
http://t.me/KendelM
Kendel On FaceBook
http://m.facebook.com/kdigitalmagazine

🔺🀄️🀄️ሉን🔺
Kendel on Telegram
http://t.me/KendelM
Kendel On FaceBook
http://m.facebook.com/kdigitalmagazine

🔺🀄️🀄️ሉን🔺
"ምርጫ ማካሄድ የሚያስችል ሁኔታ እስኪረጋገጥ በየትኛውም የአገሪቱ ክልል ምርጫ አይካሄድም"- ምርጫ ቦርድ

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ 6ኛው አገራዊ ጠቅላላ ምርጫ የሚካሄድበት ጊዜ እንዲራዘም ምክንያት የሆነው የኮቪድ 19 ወረርሽኝ ሁኔታ እንደገና ተገምግሞ ምርጫ ማካሄድ የሚያስችል ሁኔታ መፈጠሩ እስኪረጋገጥ ድረስ በየትኛውም የአገሪቱ ክልል ምርጫ እንደማያካሂድ ገለጸ።

ቦርዱ ዛሬ ባወጣው መግለጫ እንደገለጸው የትግራይ ክልል ምክር ቤት "የኢፌዴሪ ህገ መንግስት በሚያዘው መሰረት ቦርዱ የክልል ምክር ቤት ምርጫ እንዲፈጸምለትና ምርጫውን ለማካሄድ  የሚያስፈልግ የሰው ሃይልና ሎጂስቲክስ ዝግጅት እንዲያደርግ" ሲል ቦርዱን መጠየቁን አስታውቋል።

ለቀረበለት ጥያቄ ምላሽ የሰጠው ቦርዱ የትግራይ ክልል ምክር ቤት የኢፌዴሪ ህገ መንግስት በሚያዘው መሰረት በክልሉ ውስጥ 6ተኛውን ዙር የክልል ምክር ቤት ምርጫ እንዲካሄድ ውሳኔ ለመስጠት እንዲሁም ቦርዱ ይህንን ውሳኔውን ተቀብሎ ሊያስፈጽም ይገባል የሚልበት ህጋዊ መሠረት የለውም ሲል ገልጿል።

ቦርዱ የትግራይ ክልል ምክር ቤት የክልል ምክር ቤት ምርጫን አስመልክቶ የሰጠውን ውሳኔ እንዲያውቅለትም ሆነ ምርጫ እንዲያስፈፅምለት ያቀረበውን ጥያቄም ያልተቀበለው መሆኑን ገልጾ የተጠየቀውን የሰው ሀይል፣ የሎጄስቲክስ እና የቁሳቁስ አቅርቦት የሚሰጥበት የህግ አግባብ አለመኖሩን አስታውቋል፡፡ 

[የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ]

Kendel on Telegram
http://t.me/KendelM
Kendel On FaceBook
http://m.facebook.com/kdigitalmagazine

🔺🀄️🀄️ሉን🔺
"በኢትዮጵያ ተጨማሪ 141 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው ተረጋግጧል፤ የ3 ሰዎች ህይወት አልፏል።" - ዶክተር ሊያ ታደሰ

Kendel On FaceBook
http://m.facebook.com/kdigitalmagazine

🔺🀄️🀄️ሉን🔺
#DrLiaTadesse

ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ በተደረገው 4,675 የላብራቶሪ ምርመራ አንድ መቶ አርባ አንድ (141) ሰዎች የኮሮና ቫይረስ ተገኝቶባቸዋል፡፡ በአጠቃላይ በሀገራችን ቫይረሱ በምርመራ የተገኘባቸው ሰዎች ቁጥር 5175 ደርሷል።

ከጠቅላላው የላብራቶሪ ምርምራ ውስጥ 18 (4 ከጤና ተቋም እና 14 ከማህበረሰብ በተወሰደ ናሙና) ናሙናዎች በአስክሬን ላይ የተደረገ የላብራቶሪ ምርምራ ሲሆን የኮሮና ቫይረስ የተገኝበት ናሙና የለም። ከዚህ ባለፈ ሶስት በህክምና ማዕከል ውስጥ በህክምና ላይ የነበሩ ሰዎች ህይወት አልፏል። በአጠቃላይ በሀገራችን ቫይረሱ የተገኘባቸው እና ህይወታቸው ያለፈ ሰዎች ቁጥር ሰማንያ አንድ (81) ደርሷል፡፡

በሌላ መልኩ በትላንትናው ዕለት ሃምሳ ስምንት (58) ሰዎች (44 ከአዲስ አበባ፣ 8 ከኦሮሚያ ክልል፣ 3 ከሶማሊ ክልል፣ 2 ከደ/ብ/ብ/ሕ ክልል፣ እና 1 ከትግራይ ክልል) ያገገሙ ሲሆን በአጠቃላይ በሀገራችን ከበሽታው ያገገሙ ሰዎች ቁጥር 1,544 ደርሷል።

Kendel On FaceBook
http://m.facebook.com/kdigitalmagazine

🔺🀄️🀄️ሉን🔺
ግድቡን የምንገነባው ይህንን ህይወት ለመቀየር ነው፡፡ ይህን ህይወት ለመቀየር የሁላችንም ድምፅ አንድ ሊሆን ይገባል!!
በሀሳብ ጎልብተን ፣ በምክንያት ተመርተን ፣ በሀገር ፍቅር ፀንተን በአንድነት የጀመርነውን እንጨርሰው፡፡
የኑሮ ድህነታችንን በግድባችን ስንፈታ የህፃናትና ሴቶች እህቶቻችንን ጥቃት በጋራ ቆመን ለአንዴና ለመጨረሻ ግዜ እናስቀረው፡፡

#ግድቡ_የኛ_ነው !
#ዝም_አልልም !


https://t.me/KenDelM/424
Kendel On FaceBook
http://m.facebook.com/kdigitalmagazine

🔺🀄️🀄️ሉን🔺
# ሰበር ዜና
ኢትዮጲያ የታላቁ የህዳሴ ግድብ ከግብፅና ሱዳን ጋር ስምምነት ላይ እስኪደርሱ ድረስ ግድቡን ውሀ ላለመሙላት ተስማማች፡፡ ይህ የስምምነት ሀሳብ የቀረበው በኢትዮጵያ በኩል ሲሆን ስምምነቱን በሁለት ሳምንት ለማድረግም ተወስኗል፡፡
©Addis standard

@KendelM
የኢትዮጵያ የውኃ፣ መስኖ እና ኢነርጂ ምኒስትር ስለሺ በቀለ (ዶ/ር) የታላቁ የኅዳሴ ግድብን ስምምነት ኢትዮጵያ፣ ግብጽ እና ሱዳን ከሁለት እስከ ሶስት ባሉ ሳምንታት ለማጠናቀቅ መግባባት ላይ መድረሳቸውን አስታወቁ።

ትናንት ማምሻውን ለኢትዮጵያውያን ግርታ የሚፈጥር ዜና ከወደ ኻርቱም እና ካይሮ ከተሰማ በኋላ ዛሬ ማለዳ ምኒስትሩ "አፍሪካዊ መፍትሔ ለአፍሪካ ችግሮች መፈለግ" በሚል መርኅ ሶስቱ አገሮች ድርድራቸውን ለመቀጠል መስማማታቸውን በትዊተር ባሰፈሩት መልዕክት ገልጸዋል።

የሱዳኑ ጠቅላይ ምኒስትር ዐብደላ ሐምዶክ "የግድቡ የውኃ ሙሌት ስምምነት እስኪፈጸም እንዲዘገይ ከስምምነት ተደርሷል" የሚል መግለጫ አውጥተዋል። የሱዳኑ ጠቅላይ ምኒስትር ቢሮ የቴክኒክ ኮሚቴዎች በመጪዎቹ ሁለት ሳምንታት ከስምምነት ለመድረስ ድርድራቸውን እንደሚቀጥሉ ገልጿል።

የደቡብ አፍሪካው ፕሬዝዳንት ሲሪል ራማፎሳ ከመሩት የቪዲዮ ኮንፍረንስ በኋላ የግብጹ ፕሬዝዳንት አብዱል ፋታኅ አል ሲሲ ሁሉም ወገኖች ስምምነት ሳይደረስ ግድቡን ውኃ መሙላትን ጨምሮ ምንም አይነት የተናጠል እርምጃ ላለመውሰድ መወሰናቸውን ገልጸዋል።
©DW amharic



Kendel On FaceBook
http://m.facebook.com/kdigitalmagazine

🔺🀄️🀄️ሉን🔺
በጠቅላይ ሚኒስቴር ፅ/ቤት የተሰጠ መግለጫ


Kendel On FaceBook
http://m.facebook.com/kdigitalmagazine

🔺🀄️🀄️ሉን🔺
#FactCheck

የህዳሴ ግድብ ውሀ ሙሌት ተራዝሟል ተብሎ የሚፃፈው እና የሚነገረው ስህተት እንደሆነ የውሀ፣ መስኖ እና ኢነርጂ ሚኒስትር ኢ/ር ስለሺ በቀለ ዛሬ አሳውቀውኛል!

"ትክክል አይደለም! በሁለት ሳምንት ግዜ ውስጥ ስምምነት ላይ እንድንደርስ፣ እስከዛውም ለውሀ ሙሌት ዝግጅት እንድናደርግ ነው ያለን አካሄድ" ብለውኛል።

Via Elias Meseret

Kendel On FaceBook
http://m.facebook.com/kdigitalmagazine

🔺🀄️🀄️ሉን🔺
"ዛሬ አል አህራም፣ ሮይተርስ እና አልጀዚራ የተሰኙ የመገናኛ ብዙኃን የውኃ ሙሌቱ ሦስቱ ሀገራት ስምምነት እስኪደርሱ እንደተራዘመ አስመስለው የዘገቡት ዘገባ የተሳሳተና የጋራ አቋም ያልተያዘበት ነው። ግድቡን ለመገንባት የማንም ፈቃድ እንዳልተጠየቀው ሁሉ ለውኃ ሙሌቱም ፈቃድ አያስፈልገውም ስለዚህ ግንባታው የውኃ ሙሌት በተያዘለት ጊዜ ይከናወናል"--- የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አምባሳደር ዲና ሙፍቲ

Via አብመድ/ Elias meseret

Kendel On FaceBook
http://m.facebook.com/kdigitalmagazine

🔺🀄️🀄️ሉን🔺
Audio
የዘመን ቁጭት የጊዜው ተስፋ አባይ......


🎤አዘጋጅ እና አቅራቢ በሀይሉ ወንድይፍራው

#ከቅንድል_ዲጂታል_መፅሔት_የተወሰደ

Kendel On FaceBook
http://m.facebook.com/kdigitalmagazine

🔺🀄️🀄️ሉን🔺
#BREAKING

አርቲስት ሃጫሉ ሁንዴሳ ዛሬ ሰኔ 22/2012 ዓ/ም ለጊዜው ማንነታቸው ባልታወቁ ሰዎች በጥይት ተመትቶ ህይወቱ አልፏል።

አርቲስት ሃጫሉ ሁንዴሳ አመሻሹ ላይ ገላን አካባቢ በጥይት መመታቱን በኦሮሚያ ክልል ያሉ አንድ ከፍተኛ የመንግስት ባለስልጣን 'ለኢትዮጵያ ኢንሳይደር' #አረጋግጠዋል

Kendel On FaceBook
http://m.facebook.com/kdigitalmagazine

🔺🀄️🀄️ሉን🔺
አርቲስት ሃጫሉ ዛሬ ማምሻውን “ገላን ኮንደሚኒየም” ተብሎ በሚጠራው ቦታ ላይ በግምት ከምሽቱ 3፡30 ባልታወቁ ሰዎች መገደሉን ተገልፀዋል።

ቅንድል ዲጂታል መፅሔት በአርቲስት ሀጫሉ ሁንዴሳ ድንገተኛ ህልፈተ ህይወት የተሰማውን ሀዘን እየገለጸ ለቤተሰብና ለወዳጅ ዘምዶቹ እንዲሁም ለአድናቂዎቹ መጽናናትን ይመኛል።
@kendelM
አርቲስት ሃጫሉ መገደሉን ፖሊስ አስታወቀ!

አርቲስት ሃጫሉ ሁንዴሳ በጥይት ተመትቶ ሆስፒታል ከገባ በኃላ እርዳት ሲደረግለት ቆይቶ ህይወቱ ማለፉን ማረጋገጡን የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን አስታውቋል።

ከግድያው ጋር በተያያዘ የተወሰኑ ተጠርጣሪዎች መያዛቸውን ፖሊስ ያስታወቀ ሲሆን በአርቲስት ሀጫሉ ሁንዴሳ ግድያ የተሳተፉ አካላትን ፖሊስ የማጣራት ስራ በመስራት ህጋዊ እርምጃ እንደሚወስድ ገልጿል።

Kendel On FaceBook
http://m.facebook.com/kdigitalmagazine

🔺🀄️🀄️ሉን🔺