ቅንድል ኢትዮጵያ
2.7K subscribers
507 photos
28 videos
26 files
239 links
ቅንድል ዲጂታል መፅሔት በቅንድል ኢትዮጵያ የባለራዕይ ወጣቶች ተዘጋጅቶ በቅንድል ዲጂታል ሚዲያ የሚቀርብ በማህበራዊ፣ ሀገራዊ፣ ስነ-ልቦናዊ፣ ቴክኖሎጂ፣ ባህል፣ ጥበብና ጤና ነክ ጉዳዮች ዙሪያ የሚያተኩር ዲጂታል መፅሔት ነው፡፡
#ቅንነት_ድል_ያደርጋል!
https://m.facebook.com/kdigitalmagazine
Www.kdigitalmagazine@gmail.com

ለ አስተያየት @KenDelBot
Download Telegram
ማሳሰቢያ‼️

የፀሀይ ግርዶሹን ጨረር ለአንድ ደቂቃ እንኳን ያዩ ሰዎች ጉዳት ደርሶባቸዋል፡፡ በዚህ ምክኒያት የሚከሰተው ጉዳት ለመዳን ከ3-6 ወር ሊፈጅ ይችላል። እንደዛም ሆኖ ግን ወደቀድሞው የዕይታ አቅም ሳይመለስ ዘለቄታዊ የዕይታ መቀነስ ሊያስከትል ይችላል። ጨረሩን (በተለይ ልዕለሐምራዊ-ለUltraviolet -B) በቀጥታ የብርሃን መቀበያና መጋቢ ህዋሳት ላይ ኬማካዊ ለውጥ በመፍጠር ጉዳት ያስከትላል።

ህጻናትና ወጣቶች የተፈጥሮ ሌንሳቸው ሞራ ያልጀመረው ስለሚሆን በቀጥታ ፀሐይን ሲያዩ ሊጐዱ ይችላሉ። ባንጻራዊነት እድሜያቸው የገፋ ሰዎች ላይ ሞራ ስለሚጀምር ወደ ዓይን የሚገባው ጨረር ይቀንሳል፡፡ ሆኖም የሞራ ቀዶ ጥገና አድርገው አርቲፊሻል ሌንስ የገባላቸው ሰዎች ወደ ፀሐይ ቀጥታ ማየት የለባቸውም፡፡የአዕምሮ ህመም ወይም ውስንነት ያላቸው ሰዎች በብዛት ወደፀሐይ ቀጥታ ሊያዩ ስለሚችሉ ጥንቃቄና እርዳታ ያሻቸዋል፡፡

ለጨረሩ በተጋለጡ በጥቂት ሰዓታት ውስጥ ብዙ ጊዜ በ2ቱም ዓይን ላይ:- የዕይታ መቀነስ፣ በዕይታ አድማስ ውስጥ የሚታይ ጥላ፣ የዕይታ ቅርጽ መዛባት (የሚያዩት ነገር የተጣመመ ፣ በመጠን ያነሰ ወይም የተለቀ መምሰል) ፣ በተጨማሪም በግንባርና በጭንቅላት ጐን አካባቢ ራስ ምታት ሊከሰት ይችላል፡፡ ይህን ችግር መከሰቱን ለማወቅ የዓይን ምርመራ ማድረግ ያስፈልጋል፡፡ መረጃውን ለሌሎች ሼር በማድረግ የበኩልዎን ይወጡ።
Kendel on Telegram
http://t.me/KendelM
Kendel On FaceBook
http://m.facebook.com/kdigitalmagazine

🔺🀄️🀄️ሉን🔺
የዛሬው ግርዶሽ የትና ስንት ሰዓት ?

ዛሬ በአብዛኛው የኢትዮጵያ ክፍል ፀሐይ ከ60-80 ፐርሰንት ተሸፍና ከፊል ግርዶሽ ይታያል፡፡ ከ80 ፐርሰንት በላይ ያለው ዋናው ግርዶሽ ግን ከምዕራብ ኢትዮጵያ አንሥቶ እስከ ሰሜን ምሥራቅ ኢትዮጵያ በሚገኝ ስፍራ ጎልቶ ይታያል፡፡

ግርዶሹ መታየት ከሚጀምርበት ምእራብ ኢትዮጵያ (ከጠዋቱ 12:50 ሰዓት) ጀምሮ ግርዶሹ እስከሚጠናቀቅበት ሰሜን ምስራቅ ኢትዮጵያ (ከጥዋቱ 3:25 ሰዓት) በአጠቃላይ 2 ሰዓት ከ35 ደቂቃ ይፈጅበታል።

ቀለበታዊ ግርዶሽ ማየት ከሚችሉ አነስተኛ ከተሞች/ቦታዎች ቤጊ ፣ ሜቲ፣ መንዲ ፣ ጫልቱ ፣ ቡሬ ፣ አገው ግምጃቤት ፣ እንጅባራ ፣ ግሽ አባይ፣ ሞጣ ፣ ዳሞት ፣ ጋይንት ፣ ንፋስ መውጫ ፣ ጋሸና ፣ ሙጃ ፣ ዋጃ ፣ ቆቦ ፣ ኮረም፣ አላማጣ ፣ ጊራራ እና ላልይበላ ይገኙበታል፡፡

በአዲስ አበባ ፤ ሐዋሳ ፤ ድሬደዋ ፤ መቐለ ፤ ደሴ ፤ አዳማ ፤ ባህር ዳር በመሳሰሉት ከተሞች ቀለበታዊ ግረዶሽ ባይኖርም ከፊል የፀሐይ ግርዶሽ ግን ይኖራቸዋል።

ከላይ ባለው ምስል ግርዶሹ የሚጀምርበትን ሰዓት ፣ ቀለበት ካለ ቀለበት የሚታይበትን ሰዓት ፣ ግርዶሹ የሚያልቅበት ሰዓት እንዲሁም ጸሃይ የምትሸፈንበትን መጠን መመልከት ትችላላችሁ -

Via ESSS/Tikvah

Kendel On FaceBook
http://m.facebook.com/kdigitalmagazine

🔺🀄️🀄️ሉን🔺
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ከፊል ግርዶሹን የሚያሳይ ቪድዮ!

Via- elias meseret

Kendel On FaceBook
http://m.facebook.com/kdigitalmagazine

🔺🀄️🀄️ሉን🔺
አላማጣ!

Via Tigray Tv

Kendel On FaceBook
http://m.facebook.com/kdigitalmagazine

🔺🀄️🀄️ሉን🔺
አላማጣ

Via Tigray Tv

Kendel On FaceBook
http://m.facebook.com/kdigitalmagazine

🔺🀄️🀄️ሉን🔺
# የአባቶች # አባት
በስውር በቅኔ ~ ሊያስተምር አልሞ
ወንድን እንደሰራው ~ ከሴት አስቀድሞ
የፆታ እኩልነት ~ አለም እንዲገባት
ይሰጣል ፈጣሪ ~ እናት የሆነ አባት
===||===
ከሙሉቀን ሰ•
መልካም የአባቶች ቀን
Kendel on Telegram
http://t.me/KendelM
የዛሬ አመት በዛሬው ቀን ለተገደሉት የቀድሞው የኢትዮጵያ ጦር ሀይሎች ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ጀነራል ሰአረ መኮንን አዲስ አበባ ውስጥ መንገድ ተሰይሟል!

በዚህም መሰረት ከአትላስ እስከ ሩዋንዳ አደባባይ ያለው መንገድ በጀነራሉ ስም ተሰይሟል።
ፎቶ: ኤልያስ ገ/ስላሴ
@kendelM
@KendelM
የኤርትራ ፕሬስ ሚዲያ አሁን ይፋ ባደረገው መረጃ!

#ኢትዮጵያ እና #ኤርትራ የጥምር ጦር ወታደራዊ ልምምድ ማድረግ አለባቸው የሚል ሀሳብ እንደሚደግፋ ገልፃል።

ይህም ከሆነ ይህ ወታደራዊ የጥምር ጦር ልምምድ ከዚህ በፊት ኖሮ የማያውቅ እና የመጀመሪያው የኢትዮ-ኤርትራ የጥምር ጦር ልምምድ ነው የሚሆነው። ይህም የጦር ልምምድ ብዙ ጥቅም ሊኖረው ይችላል ብሎል የኤርትራው ፕሬስ ሚዲያ።

የሁለቱን ሀገራት ወዳጅነት ከማጠናከር አልፎ የሁለቱ ሀገራት ጥምር ጦር ለድንበር ፀጥታ እና ከሀገር ውስጥም ሆነ ከሀገር ውጭ የሚመጣን ጠላት ለመመከት ከፍተኛ ሚና ይኖረዋል ሲል ዘግቦል።

© Eritrea Press
https://t.me/KenDelM/411

Kendel on Telegram
http://t.me/KendelM

🔺🀄️🀄️ሉን🔺
ዜና እረፍት

በኢትዮጵያ የሙዚቃ ታሪክ በድምፃዊነት በዜማና ግጥም ስራው ትልቅ አሻራ ያኖረውና እርሱም በማቀንቀን የሚታወቀው ሱራፌል አበበ ዛሬ ከዚህ አለም ተለይቷል።

የተወዳጁ ድምፃዊ ብስራት ሱራፌል አባት የሆነው ሱራፌል አበበ ቀብርና ዝርዝር መረጃ እንደደረሰን እንገልጻለን።

ኢትዮ ኤፍ ኤም ለሟች ቤተሰብ እና አድናቂዎች መጽናናትን ይመኛል።

ኢትዮ ኤፍ ኤም የኢትዮጵያዊያን
ሰኔ 15 ቀን 2012 ዓ.ም

Kendel On FaceBook
http://m.facebook.com/kdigitalmagazine

🔺🀄️🀄️ሉን🔺
#ቅንድል_ዲጂታል_መፅሔት
ከቁጥር በላይ ቅንነትን እያበዛን ፣ ምክንያታዊነትን እያጎለበትን ፣ ሀገር ፍቅርን ከፍ ባለ ድምፅ እየሰበክን ፣ ዘገዩ ሲሉ እየፈጠንን ፣ ከእኔነት ሹመት እኛነት ዙፍን ከፍ እያልን በልዩና ማራኪ ፅሑፍ ወራችንን ጠብቀን ከተፍ ብለናል፡፡ በኢትዮጽያ ህዝብ ቅንነትና ፀሎት ዛሬ የደረሰው ሙላለም ታከለ የሀገሩን ህዝብ ደግነት ሊመሰክር በብሩሀን ገፅ ከቅንድል ጋር ቆይታ አድርጓል ይህንና ሌሎች አዝናኝ ፣ አስተማሪ ፣ ሀገራኛ ፅሑፎች በቅንድል ዲጂታል መፅሔት ይጠብቁን፡፡


★ቅፅ-፪ ቁጥር-፫

★በቅርብ ቀን | Coming Soon!

የበፊት እትሞች ለመከታተል
ይሄንን ይጫኑ

👇👇👇👇
@kendelM
@kendelM
ጥበብ
ቅንነት ድል ያደርጋል!!!
Kendel on Telegram
http://t.me/KendelM
Kendel On FaceBook
http://m.facebook.com/kdigitalmagazine

🔺🀄️🀄️ሉን🔺
🖍ኢትዮጵያ ፣ ግብጽና ሱዳን ከግድቡ ጋር በተያያዘ ባደረጓቸው ድርድሮች የግብጽ ወገን የተለያዩ አጀንዳዎችን እያቀረበ ውይይቱን ውጤት አልባ ለማድረግ ተዘጋጅቶ ይመጣ እንደነበር የ ኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ገለጡ።

የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ገዱ አንዳርጋቸው በህዳሴው ግድብ ዙሪያ ከአልጀዚራ አረብኛ ስርጭት ጋር ባደረጉት ቆይታ ግብጽ የራሷን ፍላጎት ብቻ ለመጫን ትሰራ እንደነበርም አስረድተዋል።

ግብጽ በጎረቤት ሀገሮች ላይ የጦር ካምፕ ለመመስረትና የኢትዮጵያን ደህንነት ለመፈታተን የምታደርገውን ጥረት በተመለከተ ለቀረበላቸው ጥያቄ ሚኒስትሩ በሰጡት ምላሽ ግብጽ የተለያዩ ሙከራዎችን በማድረግ ላይ መሆኗን ገልጸው ነገር ግን ኢትዮጵያ ከሱዳን፣ ጅቡቲ፣ ኬንያ፣ ሶማሊያ፣ ደቡብ ሱዳን እና ኤርትራ ጋር ጠንካራ ግንኙነት ያላት በመሆኑ ሙከራው የማይሳካ ህልም ነው ብለዋል።

ምንጭ : ኢቢስ ቲቪ

Kendel On FaceBook
http://m.facebook.com/kdigitalmagazine

🔺🀄️🀄️ሉን🔺
ግድብና ናይና እዩ!!
እሽካዕ ልውዳእ ድጋፍና ቀፃሊ እዩ!! #FillTheDam
Kendel on Telegram
http://t.me/KendelM
Kendel On FaceBook
http://m.facebook.com/kdigitalmagazine

🔺🀄️🀄️ሉን🔺
Kendel on Telegram
http://t.me/KendelM
Kendel On FaceBook
http://m.facebook.com/kdigitalmagazine

🔺🀄️🀄️ሉን🔺
"ምርጫ ማካሄድ የሚያስችል ሁኔታ እስኪረጋገጥ በየትኛውም የአገሪቱ ክልል ምርጫ አይካሄድም"- ምርጫ ቦርድ

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ 6ኛው አገራዊ ጠቅላላ ምርጫ የሚካሄድበት ጊዜ እንዲራዘም ምክንያት የሆነው የኮቪድ 19 ወረርሽኝ ሁኔታ እንደገና ተገምግሞ ምርጫ ማካሄድ የሚያስችል ሁኔታ መፈጠሩ እስኪረጋገጥ ድረስ በየትኛውም የአገሪቱ ክልል ምርጫ እንደማያካሂድ ገለጸ።

ቦርዱ ዛሬ ባወጣው መግለጫ እንደገለጸው የትግራይ ክልል ምክር ቤት "የኢፌዴሪ ህገ መንግስት በሚያዘው መሰረት ቦርዱ የክልል ምክር ቤት ምርጫ እንዲፈጸምለትና ምርጫውን ለማካሄድ  የሚያስፈልግ የሰው ሃይልና ሎጂስቲክስ ዝግጅት እንዲያደርግ" ሲል ቦርዱን መጠየቁን አስታውቋል።

ለቀረበለት ጥያቄ ምላሽ የሰጠው ቦርዱ የትግራይ ክልል ምክር ቤት የኢፌዴሪ ህገ መንግስት በሚያዘው መሰረት በክልሉ ውስጥ 6ተኛውን ዙር የክልል ምክር ቤት ምርጫ እንዲካሄድ ውሳኔ ለመስጠት እንዲሁም ቦርዱ ይህንን ውሳኔውን ተቀብሎ ሊያስፈጽም ይገባል የሚልበት ህጋዊ መሠረት የለውም ሲል ገልጿል።

ቦርዱ የትግራይ ክልል ምክር ቤት የክልል ምክር ቤት ምርጫን አስመልክቶ የሰጠውን ውሳኔ እንዲያውቅለትም ሆነ ምርጫ እንዲያስፈፅምለት ያቀረበውን ጥያቄም ያልተቀበለው መሆኑን ገልጾ የተጠየቀውን የሰው ሀይል፣ የሎጄስቲክስ እና የቁሳቁስ አቅርቦት የሚሰጥበት የህግ አግባብ አለመኖሩን አስታውቋል፡፡ 

[የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ]

Kendel on Telegram
http://t.me/KendelM
Kendel On FaceBook
http://m.facebook.com/kdigitalmagazine

🔺🀄️🀄️ሉን🔺
"በኢትዮጵያ ተጨማሪ 141 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው ተረጋግጧል፤ የ3 ሰዎች ህይወት አልፏል።" - ዶክተር ሊያ ታደሰ

Kendel On FaceBook
http://m.facebook.com/kdigitalmagazine

🔺🀄️🀄️ሉን🔺
#DrLiaTadesse

ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ በተደረገው 4,675 የላብራቶሪ ምርመራ አንድ መቶ አርባ አንድ (141) ሰዎች የኮሮና ቫይረስ ተገኝቶባቸዋል፡፡ በአጠቃላይ በሀገራችን ቫይረሱ በምርመራ የተገኘባቸው ሰዎች ቁጥር 5175 ደርሷል።

ከጠቅላላው የላብራቶሪ ምርምራ ውስጥ 18 (4 ከጤና ተቋም እና 14 ከማህበረሰብ በተወሰደ ናሙና) ናሙናዎች በአስክሬን ላይ የተደረገ የላብራቶሪ ምርምራ ሲሆን የኮሮና ቫይረስ የተገኝበት ናሙና የለም። ከዚህ ባለፈ ሶስት በህክምና ማዕከል ውስጥ በህክምና ላይ የነበሩ ሰዎች ህይወት አልፏል። በአጠቃላይ በሀገራችን ቫይረሱ የተገኘባቸው እና ህይወታቸው ያለፈ ሰዎች ቁጥር ሰማንያ አንድ (81) ደርሷል፡፡

በሌላ መልኩ በትላንትናው ዕለት ሃምሳ ስምንት (58) ሰዎች (44 ከአዲስ አበባ፣ 8 ከኦሮሚያ ክልል፣ 3 ከሶማሊ ክልል፣ 2 ከደ/ብ/ብ/ሕ ክልል፣ እና 1 ከትግራይ ክልል) ያገገሙ ሲሆን በአጠቃላይ በሀገራችን ከበሽታው ያገገሙ ሰዎች ቁጥር 1,544 ደርሷል።

Kendel On FaceBook
http://m.facebook.com/kdigitalmagazine

🔺🀄️🀄️ሉን🔺
ግድቡን የምንገነባው ይህንን ህይወት ለመቀየር ነው፡፡ ይህን ህይወት ለመቀየር የሁላችንም ድምፅ አንድ ሊሆን ይገባል!!
በሀሳብ ጎልብተን ፣ በምክንያት ተመርተን ፣ በሀገር ፍቅር ፀንተን በአንድነት የጀመርነውን እንጨርሰው፡፡
የኑሮ ድህነታችንን በግድባችን ስንፈታ የህፃናትና ሴቶች እህቶቻችንን ጥቃት በጋራ ቆመን ለአንዴና ለመጨረሻ ግዜ እናስቀረው፡፡

#ግድቡ_የኛ_ነው !
#ዝም_አልልም !


https://t.me/KenDelM/424
Kendel On FaceBook
http://m.facebook.com/kdigitalmagazine

🔺🀄️🀄️ሉን🔺
# ሰበር ዜና
ኢትዮጲያ የታላቁ የህዳሴ ግድብ ከግብፅና ሱዳን ጋር ስምምነት ላይ እስኪደርሱ ድረስ ግድቡን ውሀ ላለመሙላት ተስማማች፡፡ ይህ የስምምነት ሀሳብ የቀረበው በኢትዮጵያ በኩል ሲሆን ስምምነቱን በሁለት ሳምንት ለማድረግም ተወስኗል፡፡
©Addis standard

@KendelM
የኢትዮጵያ የውኃ፣ መስኖ እና ኢነርጂ ምኒስትር ስለሺ በቀለ (ዶ/ር) የታላቁ የኅዳሴ ግድብን ስምምነት ኢትዮጵያ፣ ግብጽ እና ሱዳን ከሁለት እስከ ሶስት ባሉ ሳምንታት ለማጠናቀቅ መግባባት ላይ መድረሳቸውን አስታወቁ።

ትናንት ማምሻውን ለኢትዮጵያውያን ግርታ የሚፈጥር ዜና ከወደ ኻርቱም እና ካይሮ ከተሰማ በኋላ ዛሬ ማለዳ ምኒስትሩ "አፍሪካዊ መፍትሔ ለአፍሪካ ችግሮች መፈለግ" በሚል መርኅ ሶስቱ አገሮች ድርድራቸውን ለመቀጠል መስማማታቸውን በትዊተር ባሰፈሩት መልዕክት ገልጸዋል።

የሱዳኑ ጠቅላይ ምኒስትር ዐብደላ ሐምዶክ "የግድቡ የውኃ ሙሌት ስምምነት እስኪፈጸም እንዲዘገይ ከስምምነት ተደርሷል" የሚል መግለጫ አውጥተዋል። የሱዳኑ ጠቅላይ ምኒስትር ቢሮ የቴክኒክ ኮሚቴዎች በመጪዎቹ ሁለት ሳምንታት ከስምምነት ለመድረስ ድርድራቸውን እንደሚቀጥሉ ገልጿል።

የደቡብ አፍሪካው ፕሬዝዳንት ሲሪል ራማፎሳ ከመሩት የቪዲዮ ኮንፍረንስ በኋላ የግብጹ ፕሬዝዳንት አብዱል ፋታኅ አል ሲሲ ሁሉም ወገኖች ስምምነት ሳይደረስ ግድቡን ውኃ መሙላትን ጨምሮ ምንም አይነት የተናጠል እርምጃ ላለመውሰድ መወሰናቸውን ገልጸዋል።
©DW amharic



Kendel On FaceBook
http://m.facebook.com/kdigitalmagazine

🔺🀄️🀄️ሉን🔺
በጠቅላይ ሚኒስቴር ፅ/ቤት የተሰጠ መግለጫ


Kendel On FaceBook
http://m.facebook.com/kdigitalmagazine

🔺🀄️🀄️ሉን🔺