ቅንድል ኢትዮጵያ
2.7K subscribers
507 photos
28 videos
26 files
239 links
ቅንድል ዲጂታል መፅሔት በቅንድል ኢትዮጵያ የባለራዕይ ወጣቶች ተዘጋጅቶ በቅንድል ዲጂታል ሚዲያ የሚቀርብ በማህበራዊ፣ ሀገራዊ፣ ስነ-ልቦናዊ፣ ቴክኖሎጂ፣ ባህል፣ ጥበብና ጤና ነክ ጉዳዮች ዙሪያ የሚያተኩር ዲጂታል መፅሔት ነው፡፡
#ቅንነት_ድል_ያደርጋል!
https://m.facebook.com/kdigitalmagazine
Www.kdigitalmagazine@gmail.com

ለ አስተያየት @KenDelBot
Download Telegram
የፀሐይ ግርዶሽ እና የዓይናችን ጤናን በተመለከት ፣ የዓይን ሐኪም እና የቪትሮ-ሬቲና ድህረ-ስፔሻሊስት ዶ/ር ጸደቀ አሳምነው ተከታዩን ጠቃሚ መረጃ በፌስ ቡክ ገፁ አጋርቶናል።ምስጋናዬን አስቀድሜ እንሆ ታነቡ ዘንድ...
:
#ፀሐይግርዶሽ እና #ዓይናችን
በሰኔ 14, 2012 ዓ.ም #የፀሐይ ግርዶሽ በ #ኢትዮጵያ እንደሚታይ ከመዘገቡ ጋር ተያይዞ የፀሐይ ግርዶሹን ለማየት ሲባል ቀጥታ ወደ ፀሐይ ማየት ስለሚያስከትለው ጕዳትና እንዴት መከላከል እንደሚቻል ማብራሪያ ለመስጠት እሞክራለሁ።

በፀሐይ ጨረር የሚመጣ የ #ሬቲና (የብርሃን መቀበያ) ጉዳት በእንግሊዝኛ , #solarretinopathy , photic retinopathy, foveomacular retinitis, solar retinitis, and eclipse retinopathy ይባላል። ይኽ ጉዳት የሚከሰተው በቀጥታ ፀሐይን ወይም የፀሐይ ግርዶሽን ለማየት ሲሞከር የሚከሰት ችግር ሲሆን የብርሃን መቀበያችን(ሬቲና) ላይ ጉዳት በማድረስ ዕይታችንን ይቀንሳል፡፡ ጨረሩን ለአንድ ደቂቃ እንኳን ያዩ ሰዎች ጉዳት ደርሶባቸዋል፡፡ በዚህ ምክኒያት የሚከሰተው ጉዳት ለመዳን ከ3-6 ወር ሊፈጅ ይችላል። እንደዛም ሆኖ ግን ወደቀድሞው የዕይታ አቅም ሳይመለስ ዘለቄታዊ የዕይታ መቀነስ ሊያስከትል ይችላል። የዚህ ችግር ዋና መንስዔ ከፀሐይ የሚወጣው ጨረር ቢሆንም በብረት ብየዳ ጊዜ ከሚወጣ ጨረር፣ ከትክክለኛው ኃይል በላይ የሚለቀቁ ሌሎች የብርሃንና የሌዘር ምንጮችም ሊከሰት ይችላል። ጨረሩን (በተለይ ልዕለሐምራዊ-ለ #Ultraviolet -B )በቀጥታ የብርሃን መቀበያና መጋቢ ህዋሳት ላይ ኬማካዊ ለውጥ በመፍጠር ጉዳት ያስከትላል።

#አጋላጭ_ሁኔታዎች፡-
- ህጻናትና ወጣቶች የተፈጥሮ ሌንሳቸው ሞራ ያልጀመረው ስለሚሆን በቀጥታ ፀሐይን ሲያዩ ሊጐዱ ይችላሉ፡፡
- ባንጻራዊነት እድሜያቸው የገፋ ሰዎች ላይ ሞራ ስለሚጀምር ወደ ዓይን የሚገባው ጨረር ይቀንሳል፡፡
- ሆኖም የሞራ ቀዶ ጥገና አድርገው አርቲፊሻል ሌንስ የገባላቸው ሰዎች ወደ ፀሐይ ቀጥታ ማየት የለባቸውም፡፡
- የአዕምሮ ህመም ወይም ውስንነት ያላቸው ሰዎች በብዛት ወደፀሐይ ቀጥታ ሊያዩ ስለሚችሉ ጥንቃቄና እርዳታ ያሻቸዋል፡፡
- ወንዶች ከሴቶች የበለጠ ተጋላጭ ናቸው
- ነጮች ከጥቁሮች የበለጠ ተጋላጭ ናቸው
- በብየዳ ጊዜ ተገቢውን መነጽርና የፊት ጋሻ አለመጠቀም ለተመሳሳይ ጉዳት ይደርጋል።

#ምልክቶቹ
በዚህ ችግር የተጠቁ ሰዎች ለጨረሩ በተጋለጡ በጥቂት ሰዓታት ውስጥ ብዙ ጊዜ በሁለቱም ዓይን ላይ፦
- የዕይታ መቀነስ
- በዕይታ አድማስ ውስጥ የሚታይ ጥላ
- የዕይታ ቅርጽ መዛባት (የሚያዩት ነገር የተጣመመ ፣ በመጠን ያነሰ ወይም የተለቀ መምሰል)
- በተጨማሪም በግንባርና በጭንቅላት ጐን አካባቢ ራስ ምታት ሊከሰት ይችላል፡፡
ይህን ችግር መከሰቱን ለማወቅ የዓይን ምርመራ ማድረግ ያስፈልጋል፡፡ በማይክሮስኮፕ በማየት ወይም ሬቲናውን ፎቶ በማንሳት ወይም OCT በሚባል መሳሪያ በማየት ችግሩ መከሰቱን ማረጋገጥ ይቻላል።

#ህክምናው
ምንም እንኳን ይህን ችግር ለማከም የተለያዩ መድኃኒቶች (ስቴሮይድን ጨምሮ) ቢሞክሩም አጥጋቢ ውጤት አላመጡም፡፡ ስለዚህ ዋነኛው ነገር ችግሩ እንዳይከሰት አስቀድሞ #መከላከል ነው ።

#መከላከያ_መንገዶች
ፀሐይን ፣ ፀሐይ ግርዶሽን ፣ የብየዳ ጨረርና ሌሎች ኃይለኛ ብርሃን የሚረጩ ነገሮችን በቀጥታ አለማየት፣
በፀሐይ ግርዶሽ በዓመታት አንዴ የሚታይ በመሆኑና ብርሃኑም የቀነሰ ስለሚመስለን ለማየት ሊያጓጓን ይችላል... ሆኖም በፍጹም በቀጥታ ማየት የለብንም
ህጻናት፣ የአዕምሮ ህመምና ውስንነት ያለባቸውን ሰዎች ወደ ፀሐይ እንዳያዩ መከላከል፣ ጥንቃቄ ማድረግ፣ መርዳት
የፀሐይ ግርዶሽን ለማየት ዓላማ የተሰሩ ISO እና CE ሰርቲፊኬት ያላቸው ልዕለሐምራዊ (UV) ንዑሰ - ቀይ (Infrared) ጨረሮችን 99 - 1ዐዐ% የሚከላከሉ ጥቁረታቸው (shade no 12) የሆኑ መነጽሮችን ብቻ መጠቀም ይቻላል። ሆኖም እንደነዚህ ዓይነት መነጽሮች በሀገራችን ስለመግባታቸው እርግጠኛ አይደለሁም፡፡ ቱሪስቶች ወደእኛ ሀገር ሲመጡ ይዘው ይመጡ ይሆናል፡፡

#የተለመዱትን_የፀሐይ_መነጽሮች_ማድረግ_ይቻላል ?
በፍጹም! ምንም እንኳን የፀሐይ መነጽሮች ጐጂ ጨረሮችን መቀነስ ቢችሉም በቀጥታ ወደ ፀሐይ ለማየት ተብሎ ስላልተሰሩ ተጨማሪ ጨረሮችን ወደ ዓይን ያስተላልፋሉና በፍጹም እነዚህን መነጽሮች ተማምነው ወደ ፀሐይ/ ፀሐይ ግርዶሽ ማየት የለብዎትም፡፡ ጥቁር መነጽር መሆኑ ብቻ ጨረሮቹን ይከላከላል ማለት አይደለም።
መንግስት ይኽን አጋጣሚ ተጠቅመው ጥራታቸው ያልተረጋገጠ መነጽሮች እንዳይሸጡ ቁጥጥር ማድረግ ይገባዋል።

ምንጭ:- ዶ/ር ጸደቀ አሳምነው
(የዓይን ሐኪም፣ የቪትሮ-ሬቲና ድህረ-ስፔሻሊስት)

ሼር እያደረጉ የሌሎች ወዳጆችዎን የዓይን ጤና ይጠብቁ!

Kendel On FaceBook
http://m.facebook.com/kdigitalmagazine

🔺🀄️🀄️ሉን🔺
ተጨማሪ 116 ሰዎች የኮሮና ቫይረስ ሲገኝባቸው የ7 ሰው ህይወት አልፏል

አዲስ አበባ ፣ ሰኔ 12 ፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) ባለፉት 24 ሰአታት ለ4 ሺህ 809 ሰዎች የላቦራቶሪ ምርመራ ተደርጎ 116 ሰዎች የኮሮና ቫይረስ እንደተገኘባቸው የጤና ሚኒስትር ዶክተር ሊያ ታደሰ አስታወቁ።
@KendelM
Audio
#staysave
#stayhome
Kendel on Telegram
http://t.me/KendelM
Kendel On FaceBook
http://m.facebook.com/kdigitalmagazine

🔺🀄️🀄️ሉን🔺
ግብፅ በህዳሴግድብ ጉዳይ ለተመድ የፀጥታ ምክር ቤት አቤቱታ አስገባች
---
ግብፅ በህዳሴ ግድብ ከውሀ አሞላል ጋር በተያያዘ ከኢትዮጵያ ጋር የተፈጠረባትን አለመግባባት የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የፀጥታው ምክርቤት እንዲታይላት አቤት አለች።
ካይሮ በጥያቄው ላይ የፀጥታው ምክር ቤት “ለታላቁ የህዳሴ ግድብ ፍትሃዊና ሚዛናዊ መፍትሄ ለመድረስ የሶስት አገራት በስምምነት የሚቀጥሉበትን አስፈላጊነት እንዲያረጋግጥ” ትላንት የግብፅ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ያወጣው መግለጫ ይጠቅሳል ፡፡
ግብፅ የፀጥታው ም / ቤት ጣልቃ ገብቶ ማንኛውንም ዓይነት ውጥረትን የማስቀረት እና ዓለም አቀፍ ሰላምና ደህንነትን ጠብቆ ለማቆየት ኃላፊነቱን እንዲወስድ ጥሪ አቅርበዋል ፡፡
በኢትዮጵያ በኩል የግድቡ ውሀ ሙሌት በግብፅም ሆነ በሱዳን ላይ የሚያመጣቸው አሉታዊ ችግር አለመኖሩን በተደጋጋሚ በመግለፅ በግብፅ በኩል የቅኝ ግዛት ውል ስራ ላይ እንዲውል የሚደረገው ጫና ተቀባይነት እንደሌለው መገለፁ የሚታወስ ነው።
ኢትዮጵያ በቀጣይ ወር የህዳሴ የውሀ ሙሌት ለመጀመር ዝግጅት አጠናቃለች።
ሶስቱ ሀገራት ከውሀ ሙሌቱ አካሄድ ጋር በተያያዘ ሰሞኑን እየተወያዩ የሰነበቱ ሲሆን የአሁኑ የግብፅ እርምጃ የምክክር ሂደቱን ሊጎዳ እንደሚችል ተገምቷል።
Kendel on Telegram
http://t.me/KendelM
Kendel On FaceBook
http://m.facebook.com/kdigitalmagazine

🔺🀄️🀄️ሉን🔺
የፀሐይ ግርዶሽ በኢትዮጵያ ታሪክ ውስጥ ___________
____________________________
የሰው ልጅ እጥቁሩ የሰማይ ሰሌዳ ላይ የተለያየ ቅርጽ ሰርተው የተደረደሩትን ክዋክብት በመመልከት ዘመኑን ሲዋጅና እጣፋንታውን ለመተንበይ ሲሞክር ዘመናት አልፈዋል፡፡ ከአውደ ነገስቱ፤ፉካሬ ክዋክብት እስከ ስነፈለክ ጥናት ያሉ ሁሉ የሰው ልጅ እራሱን ለማኖርና ህልውናውን ለማረጋገጥ የፈጠራቸው የባህል ዘርፎች ናቸው፡፡
ቀደምት የኢትዮጵያ የሥነ ፈለክ ሊቃውንት ስለ ፀሐይና ጨረቃ ግርዶሽ ትርጓሜ ሚጠተ ብርሃናት በተባለ መጽሐፋቸው የራሳቸውን ምልከታና ምርምር ጽፈው አልፈዋል፡፡
ከሳይንስ ለየት ባለ መልኩም ቀደምት ኢትዮጵያውያን ሦስት ዓይነት ግርዶሽ እንዳሉ የጻፉ ሲሆን እነዚህም የፀሓይ ግርዶሽ፣ የጨረቃ ግርዶሽ እና የ600 ዓመት የዐቀድ ግርዶሽ የሚባሉት ናቸው፡፡ የአቀድ ግርዶሽ ዕሪና መዓልት ዕሪና ሌሊትም በመባል ይታወቃል፤ በሳይንሱ ደግሞ ቴትራድ ይባላል፡፡
ለምሳሌ ያህል በጥንት ኢትዮጵያውያን ከተመዘገቡ የግርዶሽ አይነቶች ውስጥ የሚከተሉት ጥቂቶቹ ናቸው፡፡
• በዐጼ ገላውዴዎስ (አጽናፍ ሰገድ )ዘመነ መንግሥት በ1545 ዓ.ም. ፀሐይ ጨለመች፡፡
• በጻድቁ ዮሐንስ (አእላፍ ሰገድ) ዘመነ መንግሥት በ1661 ዓ.ም. ኅዳር 5 (ጥቅምት 28 የሚልም አለ) በ9 ሰዓት ላይ ፀሐይ ጨለመች፤ በዚህ ምክንያት ንጉሡ በዕለቱ ሞት ተፈርዶባቸው የነበሩት ወንጀሎቹ እንዳይነኩ አዘዙ፡፡
• በጻድቁ ዮሐንስ (አእላፍ ሰገድ) ዘመነ መንግሥት በድጋሚ በ1672 መጋቢት 24 ፀሐይ ጨለመች፡፡
• በዐጼ በካፋ (ዳግማዊ እስክንድር) ዘመነ መንግሥት ጊዜ በ1720 ዓ.ም. ፀሐይ ጨለመች፡፡ ከዚህ በተጨማሪ የጨረቃ ግርዶሽና የጅራታም ኮከቦች የታዩበትን ጊዜም መዝግበው አሰቀምጠዋል፡፡
ኮኮብ ቆጣሪዎች(Astrologers) የሰው ልጅ እጣ ፋንታ ሁሉ በከዋክብት እንቅሰቃሴ ይወሰናል ብለው ያምናሉ፡፡ ጥንታዊው ፍልስፍና በላይ በሰማይ የሚሆነው ሁሉ በምድርም ህልው ይሆናል (As above, so below) እንደሚለው ሁሉ፣ ዕጣ ፋንታችን-እድል ተርታችንን የክዋክብቱን አቀማመጥ ተመልክተን ማወቅ እንችላለን የሚሉ ጥቂት አይደሉም፡፡
ለእንደዚህ ላለው አስተሳሰብ መጽሐፍ ቅዱሳዊ ማስረጃም የሚያቀርቡ ፀሐፊዎች ብዙ ናቸው፡፡ ክርስቶስ ሲወለድ ስበአ ሰገል(The three magi) በኮኮብ መመራትን ምሳሌ አድረገው ይጠቅሳሉ፡፡ ምን ይሄ ብቻ፣ ከመጽሐፈ መሳፍንት፤ የነብይት ዲቦራ ምስጋና፤
ክዋክብት ከሰማይ ተዋጉ
በአካሄዳቸውም ከሲሦራ ጋር ተዋጉ፡፡
የሚለውን ጠቅሰው፣ ለጦርነት ለመውጣት ፉካሬ ክዋክብቱን ማንበብ ግድ ይለናል ይላሉ፡፡ ከሐይማኖቱ ጎራ የሆኑት ሌሎቹ ደግሞ፣ እንዲህ አይደለም፣ ለትልልቅ ኩነቶች ክዋክብቱ ምልክት ይሰጣሉ፣ ነገር ግን አውደ ነገስቱ የሰው ፍልስፍና እንጂ ከመጽሐፍ ቅዱስ ጋር አብሮ አይሄድም ይሉናል፡፡ ክርሰቶስ የፀሐዮች ፀሐይ በመሆኑ ሰማይና ምድሩ ሁሉ ለእሱ የተገዛ ነውና ከእሱ በቀር ምንም አያሻንም የሚለው ክፍልም ብዙ ነው፡፡ በአብርሐምውያን እምነቶች ማለትም፣ አይሁድ፣ ክርስትናና እስልምና ሐይማኖቶች ውስጥ እንደየእምነታቸው ኮኮብ ቆጠራን የሚያወግዙ አሉ፡፡ ተሞልሏዊ( Mystic) የሆኑ ግን ሰማያዊ ምልክቶችን አጽንኦት ሰጥተው የሚከታተሉ ናቸው፡፡
ከመካከለኛው ዘመን በኋላ ካባላውና አልኬሚው ውስጥ የነበረው ክዋክብትን ማንበብ ወደ ጂኦደሲ- ስነፈለክ(Geodetic Astronomi) ጥናት ሲቀየር፣ ኮኮብ ቆጠራን እንደ አጉል እምነት የሚቆጥሩ በምክንያተዊነትና በተጠየቅ የሚያምኑ ሰዎች እየተበራከቱ መጥተዋል፡፡ በነገራችን ላይ ካባላ የህብሪው ቃል ሲሆን ትረጓሜው ሲወርድ ሲዋረድ የመጣ የተቀበልነው ማለት ነው፡፡ ልክ እንደ አማርኛው መቀበል ማለት ነው፡፡ ካባለው የሚከተለውና ነገሮችን የሚያመሰጥርበት የህይወት ዛፍ ምስል( Sefirot) አለው፡፡
ሳይንስ ሰማያዊ አካላት(Celestial bodies) በሰው ልጅ ፊሶሎጂ የውስጥ አካል አሰራር ላይ በአካሄዳቸው ለውጥ ሊያሰከትሉ እንደሚችሉ ያምናል፡፡ የሰው ልጅ ትክክለኛ ተክለ ሰውነት እንዲኖረው ከፀሐይ የሚያገኘው ቫይታሚን ዲ ያሰፈልገዋል፡፡ ከፀሐይ የሚመጡ የጨረር አይነቶችም በሰው አካል ላይ ሊያደርሱ የሚችሉት ጉዳት አለ፡፡ ይህንን የሳይንስ ቀዳዳ ተጠቅመው የባህር መዕበል የሚነሳው በጨረቃ ስበት ምክነያት ስለሆነ የሰው ልጅ በአማካኝ ሰልሳ በመቶ አካሉ ውሃ በመሆኑ፣ በተለይም የውስጥ ብልቶቻችን ማለትም ልብ፣ሳንባ፣ኩላሊት፣አዕምሯችን… ከ70- 85 % ውሃ በመሆናቸው ፣ የክዋክብት አካሄድና አቀማመጥ ባህሪያችንና ዕጣ ፋንታችን ላይ ተጽእኖ ያደርጋል ሲሉ የሚሞግቱ አሉ፡፡
ወደ ዋናው ነገሬ ስመለስ ይህን ያክል የተንደረድረኩት ሰኔ 14፣2012 ዓ.ም. ሰለሚከሰተው የፀሐይ ግርዶሽ ጥቂት ለማለት ነው፡፡ በኢትዮጵያ ታሪክ ነገስታቱና ካህናቱ በዘመናቸው በሰማይ ላይ ይከሰቱ የነበሩ ምልክቶችን ሁሉ ዘግበው አስቀምጠዋል፡፡ ራቅ ያለውን ትቼ በሪቻርድ ፓንክረስት ተሰብስቦ በኢትጵዮጵያ ጥናት ኢንስቲቱዩት ከቀረበ ጽሑፍ ያገኘሁትን ላካፍላችሁ፡፡
ከ መቶ ሀምሳ አመት በፊት ኢትዮጵያን ለማዘመን የቻሉትን ያህል የሞከሩት አፄ ቴውድሮስ ነበሩ፡፡ በግዜያቸው አሰገድደው መድፍ ለማስራት ካሰሯቸው ፈረንጆች ማስታውሻ የምናነበው አፄው ስለ ሰነፈለካት ለማውቅ ከፍተኛ ጉጉት እንደ ነበራቸውና አዘውትረው ፈረንጆቹን ይጠይቁ እንደነበር ነው፡፡በእሳቸው ዘመን አውሮፓውያን የደረሱበት የስነፈለክ ጥናትን(Astronomy) የማወቅ ጉጉት ነበራቸው፡፡
በሸዋው ንጉስ ሣህለስላሴ ዘመን 1834ዓ.ም. ከጥምቀት በዓል በኋላ ኢትዬጵያ ውጥ የጨረቃ ግርዶሽ ተከስቶ ነበር፡፡ በወቅቱ አንኮበር ከተማ ላይ የነበረውን ስሜት ካፒቴን ሃሪስ የተባለ እንግሊዛዊ በጥሩ ሁኔታ ዘግቦታል፡፡ ህዝቡ፤ ወንዱ፣ ሴቱና ቀሳውስቱ በየጎዳናውና ቤተክርሰቲያኑ ተሰብስቦ ይህንን ምልክት ተከትሎ ከሚመጣው በሽታ፣ርሃብና ጦርነት ፈጣሪያቸው እንዲጠብቃቸው በአማርኛና ኦሮሚኛ በከፍተኛ ጩኸት ፀሎት አድርገዋል፡፡
ንጉሱ ግርዶሹን እንደ መጥፎ ምልክት ነበር የተመለከቱት፡፡ ለመኳንቶቻቸውም የትግሬው ስባጋድስ የተገደሉትና የ ወሎው ራስ አሊ የተሸነፉት እንዲህ አይነት ምልክት በሰማይ ከታየ በኋላ መሆኑን ገልጸው፣ የቤተመንግሰታቸውን የአንጥረኞች አለቃ እራሱን ለሎጋሊዚም ሰንጠረዥና ሰማያትን መንበብ ሚያስችለው እውቀት ለማወቅ እንንዲተጋ ትእዛዝ ሰጡት፡፡ በግዜው ንጉሱ በህክምና ላይ የደርጉ የነበረውን ጥናት ወደ ስነፈለክ አዙረውት ነበር፡፡
በአፄ ዮሃንስ 4ኛው ዘመነ መንግስት 1874 ዓ.ም. የሚያበራ ኮኮብ(ኮሜት) በመታየቱ ደስ ብሎአቸው ስለነበር የወሎን ክፍለሀገር ዋና ከተማ ደሴ ብለው ጠሩት፡፡ በዚያን ግዜ የእሳቸው ልጅ አራያ ስላሴ ከነጉስ ምንሊክ ልጅ ዘውዲቱ ጋር ተጋብቶ ስለ ነበር እንደ ጥሩ ምልክት ነበር የተወሰደው፡፡በትግራይ የሚነገር አንድ ታሪክ አለ፡፡ በእሳቸው ዘመን የጨረቃ ግርዶሸ ተከስቶ ጨረቃ ደም መሰለች፡፡ ይኼኔ ነጉሱ ተረበብሸው ሕዝቡ ሁሉ እንዲጸልይ ለአጋፋሪ ኪዳኑ መልእክት እንዲያስተላልፍ ይነግሩታል፡፡ አጋፋሪ ኪዳኑም መልእክቱን ሳያስተላለፉ ይቀራሉ፡፡በኋላ አፄ ዮሃንስ ተቆጥተው ወደ አጋፋሪው ቢሄዱ፤ የእኔ ፀሐይ ንጉስ ዮሃንስ ደህና ከሆኑ ስለ ታመመች ጨረቃ ምን አገባኝ ብለው አሳቋቸው ይባላል፡፡
አፄ ምንሊክ የአያታቸውንና የአፄ ቴውድሮስ 2ኛን ፈለግ በመከተል እሳቸውን ያገለግል ከነበረውን ከአርመናዊው የሳይንስ ሊቅ ከሪኮር ሆውያን ጋር በመ
ሆን በ108 ሚሊሜትር ባርዶ ቴሌስኮፕ በ1900 ዓ.ም. ህዳር ወር መጀመሪ ላይ ፕላኔት ሜርኩሪን ማየት ችለው ነበር፡፡ በወቅቱ የፈረንሳይ የስነፈለክ ፕሬዚዳንት የነበረው ቻሚሌ ፍላማሪዎን መሐበሩ በረጅም ግዜ የሚከሰተውን የዚህን ክስተት ዘገባ ለሳይንስና ሥነጥበብ ፍላጎት ከነበራቸው ንጉስ በማገኘቱ ንጉሱን በማድነቅ በአለም ላይ ክስተቱን ያዩ ብቸኛው ንጉስ በማለት አድንቆ ንግግር አድርጓል፡፡
ከስድስት ወራት በኋላ አፄ ምኒልክ ለፈረንሳይ ስነፈለክ ምርምር ማህበር ባቀረቡት ማመልከቻ መሰረት 4730ኛ አባል ሆነዋል፡፡ ለመሐበሩም የአንድ ሺህ ፍራንክ ስጦታ አበርክተዋል፡፡
ሰኔ 14፣ 2012ዓ.ም. በኢትዮጵያ ሰማይ ላይ የሚሆነው አኑላር የፀሐይ ግርዶሽ ተከትሎ የሚመጣ ነገር ስለሚኖር ግዜያችንን ልንዋጅበት ይገባል? ለኢትዮጵያውያንስ ትርጉሙ ምን ሊሆን ይችላል? እንዲህ ያሉ ጥያቄዎችን ስናነሳ የታሪክ መዛግብትን ማገላበጥ የግድ የሚል ነው፡፡
በጥንት ግዜ ቻይና ሀገር ውስጥ ቀን ሆኖ ሳለ ፀሐይ ትጨልማለች፡፡ በሁኔታው የተደናገጠው ንጉሰ ፀሐይን ድራጎን የተባለ አውሬ እየዋጣት ስለሆነ ህዝቡ የሚነኮሻኮሽ ነገር ሁሉ ይዞ ወጥቶ ድራጎኑን እንዲዋጋ አዋጅ ያስነግራል፡፡ ከዚያም ፀሐይ ወደ መንበሯ ተመለሰች፡፡ ንጉሱ የቤተ መንግሰቱ ኮኮብ ቆጣሪዎች የነበሩትን ሆ እና ሂስን ጠርቶ ይህ ነገር እንደሚከሰት አስቀድመው ባለማስጠንቀቃቸው አንገታቸውን ተቀልቶ እንዲሞቱ አደረጋቸው፡፡
ከመካከለኛው አፍሪካ ከኮነጎ ተነስቶ እስከ ቻይና ድረሰ ሄዶ ሰላማዊ ውቅያኖስ ውስጥ የሚያበቃው የፀሐይ ግረዶሹ አካሄዱ ከምዕራብ ወደ ምስራቅ ወደ ላይ ከርቭ ሰርቶ ነው፡፡ ኢትዮጵያንም በሚያቋርጥበት ግዜ ጉዞው ከደቡብ -ምዕራብ ተነሰቶ ወደ ሰሜን-ምስራቅ በመጓዝ ነው፡፡
በዚህ ጉዞ ላይ የፀሐይ ግርዶሹ እሳታማ ቀለበት ሰርቶ ከሚታይባቸው ጥቂት የኢትዮጵያ ቦታዎች አንዱ ላሊበላ ነው፡፡ ይህን ክስተት ከኮረና በሽታ ጋር አያይዘው የሚተርኩ የውጭና የሃገራችን ተመራማሪዎች አሉ፡፡ አኔ ደግሞ ሃሳቤን ለማካፈል ከውቅር አብያተ ክርስቲያናቱ አሰራረ ጀምሬ መመርመርን አሻሁ፡፡
ስለ ላሊበላ ውቅር አብያተ ክርስቲያናት አሰራርና የተሰሩበት ዘመን የተለያየ አመለካከት አለ፡፡ ውቅር አብያተ ክርሰቲያናቱ ከክርስቶስ ልደት በፊት በሚያስደንቁ የሰማይ ኃያላት የተሰሩ ናቸው፡፡በኋላ ላሊበላ በዘመኑ የለበሱትን አፈር አራግፎ ቁጥቋጦውን መንጥሮ ገለጣቸው ብለው የጻፉ አሉ፡፡ ኢምጋርድ ቢድር ላሊበላ በሚለው መጽሐፏ ከቄሶቹ ሰማሁት የለቸውን መረጃ ይዛ ተመሳሳይ አመለካከት አንፀባርቃለች፡፡
ሌላው የውጭ ጸሐፊ ፐሮፌሰር ዴቪድ ፊሊፐሰን ሲሆን፣ የውቅሮቹን ሰተራከቸር ምህንድስና ተከትሎ ከ7ኛው ክ/ዘመን ጀምሮ እስከ 13ኛው ክ/ዘመን ድረስ የተሰሩ ናቸው የሚል ጥናት አቅረቧል፡፡ ሌለኞቹ ወገኖች ደግሞ፣ በላሊበላ ዘመን ኢትዮጵያውያን ወደ ርስት ምድራቸው እየሩሳሌም( ዴርሱልጣን) የደርጉ የነበሩት ሐይማኖታዊ ጉዞ በመስቀል ጦርነት(Crusade) ምክንያት ተስተጓጉሎ ስለነበር፤ ንጉስ ላሊበላ ዳግማዊት እየሩሳሌምን ለመፍጠር አብያተ ክርሰቲያናቱን ላሊበላ ላይ እዚሁ ኢትዮጵያ ውስጥ አነጻቸው የሚሉ ናቸው፡፡
በውቅር አብያተ ክርሰቲያናቱ ላይ ያሉ ክርስቲያናዊ ምልክቶችን ዋቢ በማድረግ፣ አብያተ ክርስቲያናቱን አቋርጦ የሚሄደውን የዮርዳኖስ ወንዝ ጨምሮ፣በተጨማሪም ድርሳናቱንና ገድላቱን በማጣቀስ ውቅር አብያተ ክርስቲያናቱ ከላሊበላ ዘመን በኋላ የተወቀሩ ናቸው የሚለው ሃሳብ ሚዛን ደፍቶ ገዢ ሆኗል ይተረካል፡፡
የተለያዩ ተመራማሪዎችን ጽሑፍ አንብቤ በሶስት መጽሓፎቼ ላይ ስለ ላሊበላ ውቅር አብያተ ክርስቲያናት፣ የራሴን አመለካከት ላለፉት ሃያ አንድ አመታት ለህዝብ ሳቀርብ ቆይቻለሁ፡፡ በተደጋጋሚ ላሊበላን በጎበኘሁበት ግዜ ካገኘኋቸው አባቶች ያገኘሁት መረጃም ያረጋገጠልኝም ነገር ቢኖር ያሾለቅኩበት መነጽሬ ትክክለኛነት መሬት የያዘ መሆኑን ነው፡፡
ልክ ሰኔ 14፣2012 ዓ.ም. የሚሆነው የፀሐይ ግርዶሽ መንገድ፣ ኢትዮጵያን በተመለከተ፣ በደቡብ- ምዕራብ ኢትዮጵያ ጀምሮ ሰሜን- ምስራቅ ኢትዮጵያ ላይ ያበቃል፡፡ ይህ ፍኖት ሙሉ በሙሉ አስራ አንዱን ውቅር አብያተ ክርስቲያናት ለሁለት ከደቡብ-ምዕራብ ወደ ሰሜን-ምስራቅ አቋርጦ የሚሄደውን ዬዮርዳኖስ ወንዝ ከሰማይ አመላክቶ በላዩ ላይ ተደርቦ የሚያልፍ ባይሆንም፣ በቤተ ግዮርጊስና ዮርዳኖስ ወንዝ መጀመሪያ አካባቢ አቋርጦት ያልፋል፡፡ ስካይ ማፑን መሬት ካለው ሁኔታ ጋር አነፃጽሮ ማየትም ግን ያስፈልጋል፡፡
በላሊበላ ጉብኝቴ ግዜ ቤተጊዮርጊስ ያገኘኋቸው ቄስ ይዘው የወጡትን ክብ መስቀል አሰታውሳለሁ፡፡ ይህ የቤተ ጊዮርጊስ ምድራዊ ፕላን( Floor plan) ነው ብለው ነግረውኛል፡፡ ቤተ ጊዮርጊስ በመስቀል ቅርጽ የተሰራና በአራቱም የመስቀል ጎን ክፍሎች ላይ ሶስተት መስኮቶች አሉት፡፡ ቄሱ አሰራሁለት ጉጥ ያለውን ክብ መስቀል የቤተ ክርስቲያኑ ወለል ፕላን ነው ሲሉ ገለጻ ሰጥተውኛል፡፡ ላሊብላ የሰራቸውን ውቅር አብያተ ክርስቲያናት ዲዛይን፣ ተመርዞ ለሞት በተቃረበበት ግዜ ወደ ሰማይ ነፍሱ ተነጥቃ ስለነበር ንድፉን ከፈጣሪ ተቀብሎ መምጣቱን ገድሉ ያትታል፡፡
የአስራ ሁለት ቁጥር ጥያቄን ከእየሩሳሌም ምስጢር ጋር አገናኝቼ 1991 እና 1995 ዓ.ም. ላይ መጽሐፍት ጽፌ ስለነበር የቄሱ ገለፃ ግምቴን ያረጋገጠልኝ ነበር፡፡ ላሊበላን በተመለከተ ሁል ግዜ አዕምሮዬን ያዝ አድርጎ ጥያቄ የሚያጭርብኝ ነገር ቢኖር አስራ ሁለት ቁጥር ነው፡፡
የዮሴፍ ህልም( ዘፍ ም.37 ቁ. 9-10፤ እራሱን ሲቀር አስራ አንድ ኮኮቦች( ወንድሞቹ)፣ ፀሐይ( አባቱ)ና ጨረቃ(እናቱ) የሰገዱለት ምስጢር፡፡ ይህም በግብጽ ስደት ግዜ የተፈፀመ ነው፡፡ እንዲሁም ሚካ. ም 4 ቁ 9-10 ታላቅ አንደምታ ያለው፤ የባቢሎንን ስደት የሚያስታውሰን ሲሆን አስራሁለት ቁጥር በአስራሁለት ነገድ፣ በአስራሁለት ክዋክብት፤ በአስራ ሁለት ዕንቁዎች የሚመሳጠር በብሉይ ኪዳንም ሆነ በአዲስ ኪዳን ምስጢራዊና መንፈሳዊ የሆነ ቁጥር ነው፡፡
ዋናው ግን በራዕየ ዮሐንስ ምዕራፍ 12 የተነገረው ነው፡፡ የአይሁድ እምነት ተከታይ የነበሩት በቁምራን ገዳም ገድመው የነበሩት እሴይዋውያንም ተመሳሳይ መገለጥ እንደነበራቸው እነሱ ጽፈውት የነበረ ጽሑፍ ነው ተብሎ ወደ እንግሊዘኛ የተተረጎመ ጽሑፍ አንብቤለሁ፡፡ ዮሃንስ ራዕይ ም. 12፤
ታላቅ ምልክት በሰማይ ታየ፡፡ ፀሐይን ተጎናጽፋ፣ ጨረቃን የተረገጠች በራሷም ላይ አስራ ሁለት ክዋክብት አክሊል የሆነላት አንዲት ሴት ነበረች…
ሴቲቱ አህዛብን በብረት በትር ይገዛቸው ዘንድ ያለውን ወንድ ልጅ ወለደች፡፡ ልጁም ወደ እግዚአብሔር ወደ ዙፋኑ ተነጠቀ፡፡ ሌላም ምልክት ታላቅ ቀይ ዘንዶም የተወለደውን ልጅ ሊበላ በሴቲቱ ፊት ቆመ፡፡ እግዚአብሔርም ሺህ ሁለት መቶ ስልሳ ቀን በበርሃ እንድትቀመጥ የታላቁ የንስር ክንፍ ለሴቲቱ ሰጥቶ አበረራት፡፡ በዚያም የሚመግባት ከእግዚአብሔር ዘንድ ተዘጋጅተ ነበር፡፡…እባቡም ሴቲቱን በወንዝ እንድትወሰድ ሊያደርግ ወንዝ የሚያክልን ውኃ ከአፉ በስተ ኋለዋ አፈሰሰ፡፡ ምድሪቱም ሴቲቱን ረዳቻት፡፡ ምድሪቱም አፉዋን ከፍታ ዘንዶው ከአፉ ያፈሰሰውን ወንዝ ዋጠችው፡፡
ይህንን ጥቅስ ከላይ ከተጠቀሱት ሁለት ጥቅሶች ጋር አያይዘው የሚተረጉሙ ሊቃውንት በቀጥታ ለቅድስት ድንግል ማርያም ነው የሚመለከተው ብለው፣ ልጇን ክርስቶስን ይዛ ካደረገችው ሽሽት ጉዞ ጋር በማመሳጠር ይተረጉሙታል፡፡ የዚህ አንደምታ በመስቀሉ ዙሪያ ሁሌ የሚታወሱትን አስራ ሁለቱን ሐዋርያትንና ክርስቶስንም ያመሳጥራል
ይላሉ፡፡
በላሊበላ ጎሎጎታ የሚገኘው የላሊበላ መጾር መስቀል በሁለት በተያያዙ ክበበ ፀዳል ውስጥ ሁለት መስቀሎችን ይዞ፣ ከላይ ያዘረዘሩ አስራ ሁለት ክዋክብትን በመመሰል ተቀርጾ፣ ከጎኑና ከጎኑ ሶስት-ሶስት ክንፎችን በድምሩ ስድስት ክነፎችን በመያዝ የተሰራ መስቀለወ ነው፡፡
ይህ መስቀል ዮሃንስ ራዕይ ም. 12 የተገለጠውን ሰማያዊ ትእይንት በቀጥታ ገላጭ ነው፡፡ ሁለቱ ክበበ ፀዳሎች ፀሐይና ጨረቃን ሲወክሉ፣ ያዘረዘሩት አስራሁለት ቅርንጫፎች ደግሞ አስራሁለቱ ክዋክብት ናቸው፡፡ ስድስቱ ክንፎች የታለቁ ንስር(ሱራፌል) ክንፎች ሆነው ይተረጎማሉ፡፡ በላሊበላ የሚገኙ መስቀሎች ብዙ ሚስጥራትነ በውስጣቸው የያዙ ናቸው፡፡
እኔ እራሴን እጠይቅ የነበረው፣ ላሊበላ አሰራሁለት ቁጥር በመጽሐፍ ቅዱስ ትርክት ውስጥ ታላቅ ሚና እንደሚጫወት እያወቀ ለምን በውስጥ ለውስጥ ዋሻ መንግድ የሚገናኙትን አስራ አንድ ውቅር ቤተ ክርስቲያናት ብቻ ወቀረ የሚል ነበር፡፡
አሰራ አንዱን ውቅር አብያተ ክርሰቲያናት ለሁለት ከፍሎ የሚያለፍ ላሊብላ የስራው የዮርዳኖሰ ወንዝ አለ፡፡ ከወንዙ ሰሜን -ምዕራብ አምስቱን ውቅሮች ስናገኝ፣ በደቡብ ምዕራብ በኩል ሌሎቹ አምስቱን እናገኛልን፡፡ ቤተጊዮርጊስ ወደ ደቡብ ፈንጠር ብሎ ነው የሚገኘው፡፡ ከቤተ ጊዮርጊስ በስተምስራቅ በዮርዳኖ ወንዝ ውስጥ አንድ ውቅር መስቀል ቆሞ ይገኛል፡፡
ክርስቶስ በተጠመቀበት ዮርዳኖስ ወንዝ ውስጥም መስቀል አድርጎ መሳል ከበባዛነታይን ዘመን ጀምሮ የነበረ የምስራቃውያኑ መንፈሳዊ የአሳሳል ጥበብ ባህል ነበር፡፡ ከመረመርነው ግን ይህን ውቅር መስቀል አንደ አንድ ውቅር ስራ በመቁጠር አስራሁለተኛ ልናደርገው እንችላለን፡፡
ናሳ የለቀቀውን የፀሐይ ግርዶሹ ጎግል ማፕ ትክክለኛነት መቶ በመቶ እርግጠኛ እንዳለሆነ መግለጫ ቢሰጥበትም፤ እሳታማ ቀለበት የጠቆረች ጨረቃን ይዛ ሰኔ 14 የምታልፈው በመስቀል ቅርጽ በተሰራው ቤተ ጊዮርጊስና በውቅር መስቀሉ አናት ላይ አቋርጦ ነው፡፡ ግንቦት 28፣ 2012 ዓ.ም. የነበረውን የጨረቃ ግርዶሽም አንርሳ፡፡ ሌላ የጨረቃ ግርዶሽ ሰኔ 28፣ 2012 ዓ.ም. ይሆናል፡፡
በስነፈለክና ፉካሬ ክዋክብት ላይ ጥናት የሚያደርጉ ተመራማሪዎች በዮሃንስ ራዕይ ም. 12 ላይ የተገለጠው ሰማያዊ ምልክት መስከረም11፣ 2010 ተከስቷል ይላሉ፡፡ በፉካሬ ክዋክብቱ ሴቷ ቪርጎ በእግሯ ስር ጨረቃን አናቷ ላይ ፀሐይን ይዛ አስራሁለት ክዋክብትን ከአንበሳው አውደ ነገስት በመያዝ በሰማይ ሰሌዳ ላይ ወጥታለች፡፡ ጁፒተር ሆዷ ውስጥ ቆይቶ በእግሯ ስር ሾልኮ ወጥቷል ስለዚህም የራዕዩ ገለጻ ተፈጽሟል ይላሉ፡፡
የዚህ አይነቱ የክዋክብት ድርድር በየሁለት መቶ አረባ አመት የሚከሰት ነው፡፡ የመጨረሻው ዘመን መገለጫ አድርገው የወሰዱትም ነበሩ፡፡ ነገር ግን የነበረው የክዋክብት አቀማመጥ ዮሃንስ ያየው ነው ብለን ብንወስደው እንኳን፣ስለ ዘንዶውና ወንዙ እንዲሁም የንስር ክንፎቹ ክዋክብቱ የሆነ የሚመስል ነገር ማለት አለባቸው፡፡
እሺ ነገራቸውን ከኢትዮጵያ ሰማይ አንጻር አይተን፣ እሳታማው ቀለበት እንደጥንቱ ባህል ፀሐይ በበራሪው እባብ ስትዋጥ ተከሰተ እንበል፣ወንዙስ? ወንዙንም ከኮንጎ እስከ መጨረሻው ሰላማዊ ውቂያኖስ ድረስ ያለው የግርዶሹ መሰመር ነው ብለን እንውሰድ፣ የተወለደውስ ንጉስ የት አለ?
እኒህን ጥያቄዎች እራሴን ከጠየቅኩ በኋላ ወደ ላሊበላ ልመለስ፡፡ በላሊበላ ያለው ዬርዳኖስ ወንዝ ለኔ ሚልክ ዌይ በመባል የሚታወቀውን የሰማይ ዥረት ተምሳሌት አድርጌ ነው የማየው፡፡ ውቅር መስቀሉም የደቡቡ መሰቀል(The southern cross) ፉካሬ ክዋክብት ነው፡፡
ከላይ የጠየቅኳቸውን ጥያቄዎች ይዤ ከላሊበላው የሰማይ ጅረት ምሳሌ ጋር ያላቻም ይሁን ባልተቀደሰ ጋብቻ ሃሳቦቹን አጋብቼ የዮሃንስ ራዕይ ም. 12 እስከ ሴቲቱ በወንዝ እንድትወሰድ ውኃ ከአፉ አፈሰሰ እስከሚለው ምልክት ድረስ ተፈጽሟል ብዬ ባምንም እንኳን የንስሩን ክንፎች ለማየት እናፍቃለሁ፡፡ ያ ከሆነ እንሆ አዲስ ዘመን ለሁላችን! ምን አልባት ከሰው ልጅ ጋር እስከ ዛሬ ድብብቆሽ የመሰለ ጨዋታ ሲጫወቱ የነበሩት የሰማይ ኀያላት በቅርቡ ይገለጹ ይሆንን?
ነገሩን ካነሳሁት ዘንደ፣ አንድ ለመንገድ ብዬ ላብቃ፡፡ ሁለት የበቁ በፍቅር የሚኖሩ ባህታውያን ነበሩ አሉ፡፡ ታዲያ አንደኛቸው አንድ አይና ሲሆኑ ሌላኛው ደግሞ አንድ እግራቸው የተቆረጠ ነበር፡፡ ሴይጣን በፍቅራቸው ቀንቶ ሚዳቆ መሰሎ ታያቸው፡፡ የሰጣቸው እይታ ግን የተለያየ ነበር፡፡ ለአንድ አይናው እግረ ቆራጣ ፣ ለቆራጣው ደግሞ አንደ አይና ሚዳቆ ሆኖ ታያቸው፡፡
ታዲያ በለአንድ አግሩ ባህታዊ ለጓደኛቸው አየሃት ያቺን አንድ አይና ሚዳቆ ሲሉ ጠየቁ፡፡ ሌላኛውም መልሰው እግረ ቆራጣዋን ማለትህ ነው ሲሉ መለሱ፡፡ አንዲ ነች እንዲያ ነች ብለው ሲከራከሩ ወደ ጠብ አመሩና አረፉት፡፡ ባህታውያኑ ጠባቸውን መርምረው ሴጣናዊ አይታቸውን ኋላ ላይ ደረሱበት፡፡ እኛ ግን ማለቴም እትዮጵያውያን ይህን የሴይጣን መነጥር ከአይናችን ላይ አውልቀን መጣል ተሳነንሳ፡፡እኸኸ እኸኸይ… ብቻ ዘፋኟ እንዳለችው፤
እንደ እየሩሳሌም እንደ አክሱም ጽዮን
ተሳልሜው መጣሁ አይንና ጥርሱን፡፡
አይንና ጥርሱንስ በግዜ ሸኘንው
ሽንጡ ማደሪያ አጥቶ ሲጓዝ አገኘንው፡፡
እኸኸ እኸኸይ፣ እኸኸ እኸኸይ…
ምንጭ:- ከአበው ሊቃውን ማህደር የተሰባሰበ
*
*
*
(ጌቱ አዲስ - ዶ/ር )
ማሳሰቢያ‼️

የፀሀይ ግርዶሹን ጨረር ለአንድ ደቂቃ እንኳን ያዩ ሰዎች ጉዳት ደርሶባቸዋል፡፡ በዚህ ምክኒያት የሚከሰተው ጉዳት ለመዳን ከ3-6 ወር ሊፈጅ ይችላል። እንደዛም ሆኖ ግን ወደቀድሞው የዕይታ አቅም ሳይመለስ ዘለቄታዊ የዕይታ መቀነስ ሊያስከትል ይችላል። ጨረሩን (በተለይ ልዕለሐምራዊ-ለUltraviolet -B) በቀጥታ የብርሃን መቀበያና መጋቢ ህዋሳት ላይ ኬማካዊ ለውጥ በመፍጠር ጉዳት ያስከትላል።

ህጻናትና ወጣቶች የተፈጥሮ ሌንሳቸው ሞራ ያልጀመረው ስለሚሆን በቀጥታ ፀሐይን ሲያዩ ሊጐዱ ይችላሉ። ባንጻራዊነት እድሜያቸው የገፋ ሰዎች ላይ ሞራ ስለሚጀምር ወደ ዓይን የሚገባው ጨረር ይቀንሳል፡፡ ሆኖም የሞራ ቀዶ ጥገና አድርገው አርቲፊሻል ሌንስ የገባላቸው ሰዎች ወደ ፀሐይ ቀጥታ ማየት የለባቸውም፡፡የአዕምሮ ህመም ወይም ውስንነት ያላቸው ሰዎች በብዛት ወደፀሐይ ቀጥታ ሊያዩ ስለሚችሉ ጥንቃቄና እርዳታ ያሻቸዋል፡፡

ለጨረሩ በተጋለጡ በጥቂት ሰዓታት ውስጥ ብዙ ጊዜ በ2ቱም ዓይን ላይ:- የዕይታ መቀነስ፣ በዕይታ አድማስ ውስጥ የሚታይ ጥላ፣ የዕይታ ቅርጽ መዛባት (የሚያዩት ነገር የተጣመመ ፣ በመጠን ያነሰ ወይም የተለቀ መምሰል) ፣ በተጨማሪም በግንባርና በጭንቅላት ጐን አካባቢ ራስ ምታት ሊከሰት ይችላል፡፡ ይህን ችግር መከሰቱን ለማወቅ የዓይን ምርመራ ማድረግ ያስፈልጋል፡፡ መረጃውን ለሌሎች ሼር በማድረግ የበኩልዎን ይወጡ።
Kendel on Telegram
http://t.me/KendelM
Kendel On FaceBook
http://m.facebook.com/kdigitalmagazine

🔺🀄️🀄️ሉን🔺
የዛሬው ግርዶሽ የትና ስንት ሰዓት ?

ዛሬ በአብዛኛው የኢትዮጵያ ክፍል ፀሐይ ከ60-80 ፐርሰንት ተሸፍና ከፊል ግርዶሽ ይታያል፡፡ ከ80 ፐርሰንት በላይ ያለው ዋናው ግርዶሽ ግን ከምዕራብ ኢትዮጵያ አንሥቶ እስከ ሰሜን ምሥራቅ ኢትዮጵያ በሚገኝ ስፍራ ጎልቶ ይታያል፡፡

ግርዶሹ መታየት ከሚጀምርበት ምእራብ ኢትዮጵያ (ከጠዋቱ 12:50 ሰዓት) ጀምሮ ግርዶሹ እስከሚጠናቀቅበት ሰሜን ምስራቅ ኢትዮጵያ (ከጥዋቱ 3:25 ሰዓት) በአጠቃላይ 2 ሰዓት ከ35 ደቂቃ ይፈጅበታል።

ቀለበታዊ ግርዶሽ ማየት ከሚችሉ አነስተኛ ከተሞች/ቦታዎች ቤጊ ፣ ሜቲ፣ መንዲ ፣ ጫልቱ ፣ ቡሬ ፣ አገው ግምጃቤት ፣ እንጅባራ ፣ ግሽ አባይ፣ ሞጣ ፣ ዳሞት ፣ ጋይንት ፣ ንፋስ መውጫ ፣ ጋሸና ፣ ሙጃ ፣ ዋጃ ፣ ቆቦ ፣ ኮረም፣ አላማጣ ፣ ጊራራ እና ላልይበላ ይገኙበታል፡፡

በአዲስ አበባ ፤ ሐዋሳ ፤ ድሬደዋ ፤ መቐለ ፤ ደሴ ፤ አዳማ ፤ ባህር ዳር በመሳሰሉት ከተሞች ቀለበታዊ ግረዶሽ ባይኖርም ከፊል የፀሐይ ግርዶሽ ግን ይኖራቸዋል።

ከላይ ባለው ምስል ግርዶሹ የሚጀምርበትን ሰዓት ፣ ቀለበት ካለ ቀለበት የሚታይበትን ሰዓት ፣ ግርዶሹ የሚያልቅበት ሰዓት እንዲሁም ጸሃይ የምትሸፈንበትን መጠን መመልከት ትችላላችሁ -

Via ESSS/Tikvah

Kendel On FaceBook
http://m.facebook.com/kdigitalmagazine

🔺🀄️🀄️ሉን🔺
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ከፊል ግርዶሹን የሚያሳይ ቪድዮ!

Via- elias meseret

Kendel On FaceBook
http://m.facebook.com/kdigitalmagazine

🔺🀄️🀄️ሉን🔺
አላማጣ!

Via Tigray Tv

Kendel On FaceBook
http://m.facebook.com/kdigitalmagazine

🔺🀄️🀄️ሉን🔺
አላማጣ

Via Tigray Tv

Kendel On FaceBook
http://m.facebook.com/kdigitalmagazine

🔺🀄️🀄️ሉን🔺
# የአባቶች # አባት
በስውር በቅኔ ~ ሊያስተምር አልሞ
ወንድን እንደሰራው ~ ከሴት አስቀድሞ
የፆታ እኩልነት ~ አለም እንዲገባት
ይሰጣል ፈጣሪ ~ እናት የሆነ አባት
===||===
ከሙሉቀን ሰ•
መልካም የአባቶች ቀን
Kendel on Telegram
http://t.me/KendelM
የዛሬ አመት በዛሬው ቀን ለተገደሉት የቀድሞው የኢትዮጵያ ጦር ሀይሎች ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ጀነራል ሰአረ መኮንን አዲስ አበባ ውስጥ መንገድ ተሰይሟል!

በዚህም መሰረት ከአትላስ እስከ ሩዋንዳ አደባባይ ያለው መንገድ በጀነራሉ ስም ተሰይሟል።
ፎቶ: ኤልያስ ገ/ስላሴ
@kendelM
@KendelM
የኤርትራ ፕሬስ ሚዲያ አሁን ይፋ ባደረገው መረጃ!

#ኢትዮጵያ እና #ኤርትራ የጥምር ጦር ወታደራዊ ልምምድ ማድረግ አለባቸው የሚል ሀሳብ እንደሚደግፋ ገልፃል።

ይህም ከሆነ ይህ ወታደራዊ የጥምር ጦር ልምምድ ከዚህ በፊት ኖሮ የማያውቅ እና የመጀመሪያው የኢትዮ-ኤርትራ የጥምር ጦር ልምምድ ነው የሚሆነው። ይህም የጦር ልምምድ ብዙ ጥቅም ሊኖረው ይችላል ብሎል የኤርትራው ፕሬስ ሚዲያ።

የሁለቱን ሀገራት ወዳጅነት ከማጠናከር አልፎ የሁለቱ ሀገራት ጥምር ጦር ለድንበር ፀጥታ እና ከሀገር ውስጥም ሆነ ከሀገር ውጭ የሚመጣን ጠላት ለመመከት ከፍተኛ ሚና ይኖረዋል ሲል ዘግቦል።

© Eritrea Press
https://t.me/KenDelM/411

Kendel on Telegram
http://t.me/KendelM

🔺🀄️🀄️ሉን🔺
ዜና እረፍት

በኢትዮጵያ የሙዚቃ ታሪክ በድምፃዊነት በዜማና ግጥም ስራው ትልቅ አሻራ ያኖረውና እርሱም በማቀንቀን የሚታወቀው ሱራፌል አበበ ዛሬ ከዚህ አለም ተለይቷል።

የተወዳጁ ድምፃዊ ብስራት ሱራፌል አባት የሆነው ሱራፌል አበበ ቀብርና ዝርዝር መረጃ እንደደረሰን እንገልጻለን።

ኢትዮ ኤፍ ኤም ለሟች ቤተሰብ እና አድናቂዎች መጽናናትን ይመኛል።

ኢትዮ ኤፍ ኤም የኢትዮጵያዊያን
ሰኔ 15 ቀን 2012 ዓ.ም

Kendel On FaceBook
http://m.facebook.com/kdigitalmagazine

🔺🀄️🀄️ሉን🔺
#ቅንድል_ዲጂታል_መፅሔት
ከቁጥር በላይ ቅንነትን እያበዛን ፣ ምክንያታዊነትን እያጎለበትን ፣ ሀገር ፍቅርን ከፍ ባለ ድምፅ እየሰበክን ፣ ዘገዩ ሲሉ እየፈጠንን ፣ ከእኔነት ሹመት እኛነት ዙፍን ከፍ እያልን በልዩና ማራኪ ፅሑፍ ወራችንን ጠብቀን ከተፍ ብለናል፡፡ በኢትዮጽያ ህዝብ ቅንነትና ፀሎት ዛሬ የደረሰው ሙላለም ታከለ የሀገሩን ህዝብ ደግነት ሊመሰክር በብሩሀን ገፅ ከቅንድል ጋር ቆይታ አድርጓል ይህንና ሌሎች አዝናኝ ፣ አስተማሪ ፣ ሀገራኛ ፅሑፎች በቅንድል ዲጂታል መፅሔት ይጠብቁን፡፡


★ቅፅ-፪ ቁጥር-፫

★በቅርብ ቀን | Coming Soon!

የበፊት እትሞች ለመከታተል
ይሄንን ይጫኑ

👇👇👇👇
@kendelM
@kendelM
ጥበብ
ቅንነት ድል ያደርጋል!!!
Kendel on Telegram
http://t.me/KendelM
Kendel On FaceBook
http://m.facebook.com/kdigitalmagazine

🔺🀄️🀄️ሉን🔺
🖍ኢትዮጵያ ፣ ግብጽና ሱዳን ከግድቡ ጋር በተያያዘ ባደረጓቸው ድርድሮች የግብጽ ወገን የተለያዩ አጀንዳዎችን እያቀረበ ውይይቱን ውጤት አልባ ለማድረግ ተዘጋጅቶ ይመጣ እንደነበር የ ኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ገለጡ።

የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ገዱ አንዳርጋቸው በህዳሴው ግድብ ዙሪያ ከአልጀዚራ አረብኛ ስርጭት ጋር ባደረጉት ቆይታ ግብጽ የራሷን ፍላጎት ብቻ ለመጫን ትሰራ እንደነበርም አስረድተዋል።

ግብጽ በጎረቤት ሀገሮች ላይ የጦር ካምፕ ለመመስረትና የኢትዮጵያን ደህንነት ለመፈታተን የምታደርገውን ጥረት በተመለከተ ለቀረበላቸው ጥያቄ ሚኒስትሩ በሰጡት ምላሽ ግብጽ የተለያዩ ሙከራዎችን በማድረግ ላይ መሆኗን ገልጸው ነገር ግን ኢትዮጵያ ከሱዳን፣ ጅቡቲ፣ ኬንያ፣ ሶማሊያ፣ ደቡብ ሱዳን እና ኤርትራ ጋር ጠንካራ ግንኙነት ያላት በመሆኑ ሙከራው የማይሳካ ህልም ነው ብለዋል።

ምንጭ : ኢቢስ ቲቪ

Kendel On FaceBook
http://m.facebook.com/kdigitalmagazine

🔺🀄️🀄️ሉን🔺
ግድብና ናይና እዩ!!
እሽካዕ ልውዳእ ድጋፍና ቀፃሊ እዩ!! #FillTheDam
Kendel on Telegram
http://t.me/KendelM
Kendel On FaceBook
http://m.facebook.com/kdigitalmagazine

🔺🀄️🀄️ሉን🔺