"ቃለ እግዚአብሔር "
7.8K subscribers
675 photos
22 videos
7 files
241 links
"ጥበብን ማግኘት ምንኛ ከወርቅ ይሻላል! ማስተዋልንም ማግኘት ከብር ይልቅ የሚመረጥ ነው።" ምሳ 16

"ሥጋችን ምግብ ሲያጣ እንደሚደክም ሁሉ ነፍስም ምግቧን የእግዚአብሔርን ቃል ስታጣ ትደክማለች።" - ብጹዕ አቡነ ሽኖዳ

በመንፈሳዊ ህይወት ዙሪያ ጥያቄ ካላችሁ ለመምህራችን በ @henokasrat3 መላክ ትችላላቹ።
Download Telegram
💦💦💦 በጭንቀት ጊዜ ለራሳችን የምንሰጣቸው የተሳሳተ የውድቀት ምላሾች
💦💦💦💦💦💦💦💦💦💦💦💦💦
በአንድ ወቅት በቅርበት የማቃቸው አንዲት ሴት በመንገድ ላይ አገኘኋቸው፡፡ ግንባራቸውን በህክምና ታሽጎ ነበር ፡፡ እኔም በቅርበት አውቃቸው ነበርና ምን ሆነው ነው? አልኳቸው፡፡ በመፀፀት ተበሳጭቼ ነበር አሉኝ፡፡ በወቅቱ ስላልገባኝ ቢበሳጩስ? አልኳቸው፡፡ ለነገሩ አሁን ቆጭቶኛል በወቅቱ ግን ከፍተኛ ብስጭት ላይ ስለነበርኩ አልታወቀኝም አሉኝ፡፡
ነገሩ ግራ አጋባኝና እንዲያብራሩልኝ ጠየኳቸው፡፡ ባለፈው ሳምንት በገንዘብ ጉዳይ ከባለቤታች ጋር ተጋጭተው እንደነበር ነገሩኝ፡፡ እና ደበደብዎት? ስል ጠየኳቸው፡፡ በጭራሽ ብስጭት ሲያደርገኝ የምሆነውን ባጣ በገዛ እጄ ድንጋይ አንስቼ ደስ ይበለው ብዬ ግንባሬን አልኩት አሉኝ፡፡
ከዚህ አስገራሚ ገጠመኝ ብዙ ነገር እንደምትረዱ ተስፋ አለኝ፡፡ ተመልከቱ ሰው በጭንቀት /በብስጭት/ ጊዜ ለራሱ የሚሰጠው የተሳሳተ የውድቀት ምላሽ ምን እንደሚመስል፡፡
ሁል ጊዜ ሰው ለራሱ በየትኛውም ጊዜና ቦታ ተገቢውን ዋጋ መስጠት ሲሳነውና ህይወቱ በተሳሳተ የውድቀት ምላሾች እንደሚወጠር ልብ ልትሉት ይገባል ይህ ደግሞ የሚሆነው እጆቹን ለጭንቀትና ብስጭት መንፈስ ሰቶ ራሱን ማዘዝ የማይችል ሲሆን ነው፡፡
በጭንቀት ጊዜ ምሬት ተስፋቢስነት፣ ራስን መቃወም ብዙ ሰውች በጭንቀት መንፈስ ሲረቱ ለራሳቸው ሕይወት ዋጋ የሚያሳጣ የውድቀት ምላሾችን ይሰጣሉ፡፡
በሰው ሕይወት ውስጥ ከሚንፀባረቁ ልዩ ልዩ ተፈጥሮአዊ መሰል ጠባዮች ረብየለሽ የምንላቸው ብስጭትና ጭንቀት ነው፡፡ ምክንያቱም ብስጭት ባሕሪዬ ነው ተብሎ ሊወሰድ የማይገባውና ለደስተኛ ሕይወትና ለሰላማዊው የዕለት ተዕለት እንቅስቃሴ የዕውቀት ምንጭና ውጤቱም ጭንቀት የሆነ ለማንም የማይጠቅም ነው፡፡
ብስጭት የተሸለ ትርጉም ለመስጠት ሞክረነው ባልተሳካ ወይም የፍላጎታችን ተቃራኒ የሆነ ነገር ሲገጥመን ራሳችንን ወደየትኛውም አቅጣጫ እንዳንቀሳቀስ አስረን አምሮችንን የምናቃውስበት የውስጥ ስሜታችንን የሚያደፈርስና በዕቅዳችን የሌለ በኋላ ለከፍተኛ ፀፀት የሚዳርገንን አንድ ነገር ድንገት እንድንፈፅም የሚያሰክረንና የቁጣን መንፈስ በደማችን የሚያሰርጽ መርዛማ ስሜት ነው፡፡
ይህ ደግሞ መጀመሪያ ካልተከላከሉት ከተከሰተም በኋላ በአግባቡና በአፋጣኝ ካላስወገዱት የቁጣው መርዛማነት በሚበክለው ራስን ወይም ሌሎችን ሊሆን ይችላል፡፡ በይበልጥም በዚህ ክፍል እያነየነው የምንገኘው ለራስ የምንሰጠው የተሳሳተ የውድቀት ምላሾች የሚከሰቱት በአብዛኛውን ጊዜ በዚህ ጊዜ ነው፡፡ ምክንያቱም በአሉታዊ ተጽዕኖ ብቻ የሚገለጥ ምክንያት ንዴት በህይወታችን የሚከሰተው በዚህ ሁኔታ ስለሆነ ነው፡፡
ሰይጣን ደግሞ በተጣለበት በዚህች ምድር የጥፋት ዓላማውን ለማስፈፀምና የሰው ልጆችን በፅኑ ጠላትነት ለማጠቃት ትልቁ መሳሪያው ይህ ስለሆነ በዚህ ጊዜ የክርስቲያኖችን ሕይወት በፈተና ለማበጠር የተሸለ ጊዜና ሁኔታ ሊያገኝ ስለሚችል በዚህ ጊዜ በመንፈሱ ስለማደሩ ልትጠራጠሩ አይገባችሁም፡፡ ሕይወታችን የታነቀችበት ይህ ብስጭትና ንዴት የሥጋ ሥራ እንጂ የመንፈስ ፍሬ እንዳልሆነ የተረጋገጠ ሐቅ ነው፡፡ /ማር. 7÷21፣ ገላ. 5÷6፣ ሮሜ. 12÷19/
ብስጭት ከሚያስከትለው የተሳሳተ የውድቀት ምላሾች የተነሳ ከሰዎች ጋር የሚኖረንን ሰላማዊ ግንኙነት ያበላሻል፡፡ እንደምሳሌ በጥቂቱ ለማየት ከሥነ ልቦና አንፃር የፍቅር ግንኙነት ያበላሻል፡፡ ከማንኛውም ሰው ጋር የሚኖረንን የመግባባት ክህሎት ይቀንሳል፡፡ በአጠቃላይ ለመንፈሳዊ ሕይወት መመሪያ ተቃራኒዎች እንድንሆን ያደርገናል፡፡ ከሰዎች ጋር በሰላም መኖርን ያጣ ሰው መንፈሳዊነቱ ጥያቄ ምልክት ውስጥ የገባ ሰው ነው፡፡ በእግዚአብሔር ቃል ‹‹ቢቻላችሁስ በእናንተ በኩል ከሰው ሁሉ ጋር በሰላም ኑሩ›› /ሮሜ. 12÷8/ ይላል፡፡
ከዚህ ቀጥሎ በዚህ ርዕስ ሥር የተሳሳቱ የውድቀት ምላሾች የምንላቸውን ጥቂቶችን ከዚህ በታች እንመለከታለን፡፡
ይቀጥላል
🙏🙏🙏ጸሎት ህይውት ነው ለጸሎት ተነሱ🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏
ጠዋት ከእንቅልፍህ ተነስተህ ሥራህን ከመጀመርህ በፊት #የእግዚአብሔር ቃል አጥና። አንተ #የእግዚአብሔር ቃል የዘውትር ወዳጅህ አድርገህ የምትይዘው ከሆንህ በዓለማዊ ነገሮች ባተሌ አትሆንም፥አትታወክም፥ኋጢአት አትሰራም።

#አባ_ኢሳይያስ
👏👏እናንተ ብትሆኑ እንዴት መፍቴ ትሰጣላችሁ👏👏👏👏👏👏👏👏👏👏👏👏👏👏
፩.ከንስሐ አባት ርቆ የሚኖር ሰው ምን ማረግ አለበት ?
አንድ ሰው የንስሐ አባት ኖሮት በሥራ ምክንያት ቢለያዩና እስከ ሁለትና ሦስት ዓመት የማይገናኙ ቢሆን ይህ ሰው በዚህ ጊዜ ውስጥ ለሰራው ኃጢያት የግድ ንስሐ መግባት እንዳለበት ይታወቃል ።ስለዚህ ባለበት አካባቢ ሌላ ካህን ፈልጎ ቢናዘዝና በኃላ ሲመለስ ደግሞ ከመጀመሪያው አባቱ ዘንድ ሄዶ ንስሐ መግባት ይችላል ወይ? ወይስ የግድ አንድ ጊዜ ከያዛቸው አባት ዘንድ ብቻነው ንስሐ መግባት ያለበት?
፪ መጠጥ ኃጢአት ነው ?
መጠጥ ካልጠጣን እያሉ ብዙ ጓደኞቼ ያስቸግሩኛል እኔ ግን መጠጥ መጠጣት ኃጢአት መሆኑን ደጋግሜ እነግራቸዋለሁ ።እንሱም መጠጥ ኃጢአት አይደለም ብለው ይከራከሩኛል። ለመሆኑ ማንኛችን ልክ ነን?
መልስ
....:
ጥያቄ ፩ ፦ መጠጥ ኃጢአት ነው?

መጠጥ ካልጠጣን እያሉ ብዙ ጓደኞቼ ያስቸግሩኛል። እኔ ግን መጠጥ መጠጣት ኃጢአት መሆኑን ደጋግሜ እነግራቸዋለሁ። እነርሱም መጠጥ ኃጢአት አይደለም ብለው ይከራከሩኛል። ለመሆኑ ማናችን ልክ ነን?

መልስ ፦ እዚህ ላይ ሁላችንም ልናስተውለው የሚገባን ነገር አለ። ይኸውም ጥቅስ እየጠቀሱ ኃጢአት ነው አይደለም የሚለው ክርክር ወይም እንካ ሰላንቲያ ምንም አይጠቅመንም ይህንንም ከተገነዘብን በኅላ አንድ ነገር እንመልከት። ከመጠጥ በስተጀርባ የሚመጣውን ችግር ። <<ጉድና ጅራት ከወደኋላ ነው።>> እንዲል።
እንኳን እኛ ደካሞች ከቁጥር የማንገባው ቀርቶ በመንፈሳዊ ሕይወት ታላላቅ የሚባሉ ሰዎች በመጠጥ ምክንያት ሲወድቁ ታይተዋል። ከዚህ ላይ እግዚአብሔር ያልከሰሳቸውን መክሰስ ባይገባም ለአብነት ግን እንጠቅሳቸዋለን።
አባታችን ኖኀ ከጥፋት ውኃ በኋላ የወይን ጠጅ ጠጥቶ በመስከሩ ራሱን ስቶ እርቃኑን ተዘርሮ የወደቀበት ጊዜ ነበር። ዘፍ.19_33_35። ይህንንም ይዘን እንኳን እነእገሌ ሰክረዋል ብንሰክር ምን አለበት እያልን እንድንጠቅሳቸው ሳይሆን ከእነርሱ ተምረን አቅማችንን ዐውቀን ራሳችንን እንድንጠብቅ ነው። ምን አልባት ከመጠኔ አላልፍም በመጠን እጠጣለሁ እንል ይሆናል። ነገር ግን በመጠን እንጠጣ ዘንድ እራሳችንን የገዛን ሰዎች ነን ወይ? ብለን ልንጠይቅ ያስፈልጋል። ምክንያቱም ራሳችንን ካልገዛን መስከራችን ስለማይቀር ነው። ራስን አለመግዛት ደግሞ የሚያጋልጠው ለሥካር ብቻ ሳይሆን ለዝሙትና ለተቀሩትም የኃጢአት ዓይነቶች ነው። <<ስለዚህ የልቡናችሁን ወገብ ታጥቃችሁና በመጠን ኑራችሁ ኢየሱስ ክርስቶስ ሲገለጥ የምታገኙትን ጸጋ ተስፋ አድርጉ።>> 1ኛ ጴጥ.1_13። እንደተባለ በመጠን ለመኖር የግድ ራስን መግዛት ያስፈልጋል። ራስን መግዛትም የመንፈስ ፍሬ ነው። ገላ.5_23 ስለዚህ አንተም ሆንክ ጓደኞችህ የመጠጥን ጉዳይ ስታነሱ ከሁለት አንጻር ተመልከቱት።
1. መጠንን ከማወቅና ራስን ከመግዛት
2. የምንሠራው ሥራ ለፈቃደ ሥጋ አሣልፎ እንዳይሰጥ፤እና የድኅነት ጉዟችንንም እንዳያሰናክል ከምናደርገው ጥንቃቄ አንጻር ሊታይ ይገባል። ከነዚህ ጋር የሚጋጭ ከሆነ ግን ኃጢአት ነው።

ጥያቄ ፪፦ ከንስሐ አባቱ ርቆ የሚኖር ሰው ምን ማድረግ አለበት?

አንድ ሰው የንስሐ አባት ኖሮት በሥራ ምክንያት ቢለያዩና እስከ ሁለትና ሦስት ዓመት የማይገናኙደግሞ ቢሆን ይህ ሰው በዚህ ጊዜ ውስጥ ለሠራው ኃጢአት የግድ ንሰሐ መግባት እንዳለበት ይታወቃል። ስለዚህ ባለበት አካባቢ ሌላ ካህን ፈልጎ ቢናዘዝና በኅላ ሲመለስ ከመጀመሪያው አባቱ ዘንድ ሄዶ ንሰሐ መግባት ይችላል ወይ? ወይስ የግድ አንድ ጊዜ ከያዛቸው አባት ዘንድ ብቻ ነው ንስሐ መግባት ያለበት?

መልስ ፦ ንሰሐ በነቢያትም በሐዋርያትም የተሰበከ የክርስቲያኖች የሕይወት ዋስትና የሆነ ድንቅ ምሥጢር ነው። ምንም እንኳን የሰው ልጅ ከበደል ባይርቅም እግዚአብሔር በቸርነቱ ብዛት በሰጠው በዚህ ታላቅ ምሥጢር የበደለው ሁሉ ይሠረይለታል። ሕይወቱም ይታደሳል። በመሆኑም አንድ ኦርቶዶክሳዊ ክርስቲያን የንስሐ አባት ሊኖረው የግድ የግድ ነው። ይህንንም የሚያደርገው እንዲያው የንስሐ አባት አለው እንዲባል ሳይሆን ዕለት በዕለት የሚበድለውን በደል ለመምህረ ንስሐው እየተናገረ ይቅርታን እንዲያገኝ ነው።
ስለዚህ ከንስሐ አባቱ ሳይርቅ በየጊዜው እየተገናኙ ኃጢአቱን ሊናዘዝ ያስፈልጋል። ከዚህ አንፃር ጠያቂያችን ያሉት ሁለትና ሦስት ዓመት ማለት በጣም ረጅም ጊዜ ነው። እንዲያውም ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ <<ተቆጡ ኃጢአትንም አታድርጉ፣ በቁጣችሁ ላይ ፀሐይ አይግባ፣ለዲያብሎስም እድል ፈንታ አትስጡት>> ኤፌ.4፥26_27።በማለት ኃጢአትን ለነገ ማሳደርና ፀሐይ ዕድሜያችን እስክትጠልቅ ለንስሐም ጊዜ መስጠት እንደሌለብን ይናገራል። ጌታችንም በወንጌል ለነገ አትበሉ ማለቱ ማለቱ ኃጢአታችንን ነገ እንናዘዘዋለን አትበሉ ማለቱ ነው። ማቴ.6፥34። ስለዚህ አንድ ክርስቲያን ራቅ ወዳለ ሥፍራ ሄዶ ለተወሰኑ ጊዜያት የሚቆይ ከሆነ በሄደበት የንስሐ አባት መያዝ ይኖርበታል። ይህ ሲባል ለሁለትና ሦስት ቀናት በየቦታው በዞረ ቁጥር የንስሐ አባት መቀያየር አለበት ማለት እንዳልሆነ መታወቅ አለበት።
ፆመ ፍልሰታ የእመቤታችን እረፍት ትንሳኤና እርገት ሚታሰብበት ወቅት ነው፡፡ እመቤታችን በተለያዩ ጊዜያት ሞትና ትንሣኤዋን ለሐዋርያት የገለጸችበትን ምስጢር ከነሐሴ 1-16 ድረስ ምእመናን በጾም በጸሎት ተወስነው የልጇን ቸርነት የእርሷን አማላጅነት በሱባኤ ይማጸናሉ፡፡ የሱባኤው ወቅት ሲፈጸም “እመቤታችን በእውነት ተነሥታለች” ብለው በደስታ የጾሙን ወቅት ይፈጽማሉ፡፡ ሞቷ የሚያስደንቅ መሆኑን ቅዱስ ያሬድ “ሞትሰ ለመዋቲ ይደሉ ሞታ ለማርያም የሐጽብ ለኲሉ፤ ሞት ለማናቸውም ሰው ሁሉ የተገባ ነው፡፡ የማርያም ሞት ግን ሁሉን ያስደንቃል” በማለት ገልጾታል፡፡
በኢትዮጰያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ትውፊት መሠረት እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም በዚህ ዓለም በሕይወተ ሥጋ 64 ዓመታት ያህል ቆይታ አርፋ ተነሥታ በክብር አርጋለች፡፡ ይህንን የትንሣኤና ዕርገት ዐቢይ ምሥጢር ነቢየ እግዚአብሔር ቅዱስ ዳዊት “ተንሥአ እግዚኦ” ውስተ ዕረፍትከ፡፡ አንተ ወታቦተ መቅደስከ፤ አቤቱ ወደ ዕረፍትህ ተነሥ፡፡ አንተና የመቅደስህ ታቦት” /መዝ.131፡8/፤ እንዲሁም “ወትቀውም ንግሥት በየማንከ በአልባሰ ወርቅ ዑጽፍት ወኁብርት፤ በወርቅ ልብስ ተጎናጽፋና ተሸፋፍና ንግሥቲቱ በቀኝህ ትቆማለች” /መዝ.44፡9/ ሲል የተናገረው ቃለ ትንቢት በንጽሐ ሥጋ፣ በንጽሐ ነፍስ፣ በንጽሐ ልቡና የጸናች የቅድስት ድንግል እመቤታችንን ዕረፍት፣ ትንሣኤ፣ ፍለሰት /ዕርገት/ ያስገነዝባል፡፡ /ራእ.11፡19/
እመቤታችን ታቦተ እግዚአብሔር መሆኗን አባ ጽጌ ድንግል በማኅሌተ ጽጌ ሲገልጽ “ከመ ታቦት ሥርጉት በወርቀ ዓረብ ወተርሴስ በድንግልና ማርያም ሥርጉተ ሥጋ ወነፍስ” ሲል አመስግኗታል፡፡ ሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያን በትርጓሜያቸው ይህንን ቃለ ትንቢት ቅዱስ ዮሐንስ በራእዩ ከገለጣት “ንግሥተ ሰማይ፤ የሰማይ ንግሥት” /ራእ.12፡1/ ጋር በማገናዘብ የእመቤታችንን ሁለንተናዊ ክብርና ልዕልና አምልተውና አስፍተው ገልጸውታል፡፡
ቅዱስ ዮሐንስ በራእዩ “… በጌታ የሚሞቱ ሙታን ብፁዓን ናቸው፡፡….. ከድካማቸው ያርፉ ዘንድ ሥራቸውም ይከተላቸዋል” /ራእ.14፡13/ ብሎ እንደመሰከረው እመቤታችን ከዕረፍቷና ዕርገቷ በኋላ የመጨረሻ ወደ ሆነው ክብር መሸጋገሯ ያስረዳል፡፡
ይህንን ክብርዋን በመረዳት ሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያን ዘወትር “ወበእንተዝ ናዐብየኪ ኩልነ ኦ እግዝእትነ ወላዲተ አምላክ ንጽሕት ኩሎ ጊዜ፡፡ ንስአል ወናንቀዐዱ ኀቤኪ ከመ ንርከብ ሣህለ በኀበ መፍቀሬ ሰብእ፤ ሁልጊዜ ንጽሕት የምትሆኚ አምላክን የወለድሽ እመቤታችን ሆይ ስለዚህ ነገር እናከብርሻለን፣ እናገንሻለን፡፡ ሰውን ከሚወድ ልጅሽ ዘንድ የቅርታንና ምሕረትን እናገኝ ዘንድ ሁል ጊዜ ዓይነ ልቡናችንን ወደ አንቺ እናነሣለን፡፡ በማለት ቤዛዊተ ዓለም ድንግል ማርያም ሁል ጊዜ ዓይነ ልቡናችንን ወደ አንቺ እናነሣለን፡፡ በማለት ቤዛዊተ ዓለም ድንግል ማርያም ከልዑል እግዚአብሔር ዘንድ የተሰጣትን ልዩ የቃል ኪዳን ጸጋና አምላካዊ ክብር እያመሰጠሩ ያመሰግኗታል፡፡ ሊቁ “ቀስተ ደመና ማርያም ትእምርተ ኪዳኑ ለኖኅ፣ ዘእግዚአብሔር ሤመኪ ለተዝካረ ምሕረት ወፍትሕ፣ ህየንተ ቀስፋ ለምድር ወአማሰና በአይኅ፡፡ ብሎ እንዳመሰገናት፡፡
እመቤታችን በአጸደ ሥጋ ሳለች ከሦስቱ አካላት አንዱ አካል እግዚአብሔር ወልድ በተለየ አካሉ በተዋሕዶ ሰው ሆኖ በመዋዕለ ሥጋዌ ላደረገው የድኅነት ዓለም ጉዞ ምክንያት ነበረች፡፡ ኢየሱስ ክርስቶስ የሰው ልጆችን ባርነትና ስደት ለማጥፋት ወደዚህ ዓለም በመጣ ጊዜ የሰው ልጆችን ያሳደደ ሠይጣን በሄሮድስ አድሮ ሲያሳድደው ልጇን ይዛ በመሰደድ ለድኅነታችን ምክንያት ነበረች፡፡ ኢየሱስ ክርስቶስ የሰው ልጆችን ባርነትና ስደት ለማጥፋት ወደዚህ ዓለም በመጣ ጊዜ የሰው ልጆችን ያሳደደ ሠይጣን በሄሮድስ አድሮ ሲያሳድደው ልጇን ይዛ በመሰደድ ለድኅነታችን ምክንያት ነበረች፡፡ ቅዱስ ዮሐንስ ወንጌላዊ በራእዩ እንዳየው፤ “ታላቅ ምልክትም በሰማይ ታየ ፀሐይን ተጐናጽፋ ጨረቃ ከእግሮችዋ በታች ያላት በራስዋም ላይ የአሥራ ሁለት ከዋክብት አክሊል የሆነላት አንዲት ሴት ነበረች፡፡ እርስዋም ፀንሳ ነበር፡፡ ምጥም ተይዛ ልትወልድ ተጨንቃ ጮኸች፡፡ ዘንዶውም ሴቲቱ በወለደች ጊዜ ሕፃንዋን እንዲበላ ልትወልድ ባላት ሴት ፊት ቆመ፡፡ አሕዛብንም ሁሉ በብረት በትር ይገዛቸው ዘንድ ያለውን ወንድ ልጅ ወለደች፤ ልጅዋም ወደ እግዚአብሔር ወደ ዙፋኑ ተነጠቀ፡፡ ሴቲቱም ሺህ ከሁለት መቶ ስልሳ ቀን በዚያ እንዲመግቡአት በእግዚአብሔር ተዘጋጅቶላት ወደ ነበረው ስፍራ ወደ በረሀ ሸሸች ”/ራእ.12፡1-6/
🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏እንኳን አደረሳችሁ አምላክ ይጠብቃችሁ ይቀድሳችሁ ጽሎታችንን ልመናችንን የተቀበለ አምላክ ክብር ምስጋ ይግባው የአመት ሰው ይበለን በሽታውን ያስወግድልን በቸርነቱ ይታደገን ለሚቀጥለው አመት በሰላም ያድርሰን ከቁጥር አያጉለን🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏
💦💦💦💦በጭንቀት ጊዜ ለራሳችን የምንሰጣቸው የተሳሳተ የውድቀት ምላሾች💦💦💦💦💦 ካለፈ የቀጠለ💦💦💦💦💦💦 ክፍል ሁለት

2 ሕይወትን ማቋረጥ
ማንም ሰው በፈቃዱ እንዳልተወለደና በኃይሉ ዓለም እንዳልመጣ ሁሉ በራሱ ፈቃድና በኃይሉ ሕይወቱን እንዲያቋርጥ /እንዲያጠፋ/ አልተፈቀደለትም፡፡ ይህ የፀና የአምላክ ሕግ ነው፡፡
በዚህች ጊዜያዊ ዓለም ስንኖር የፈጠረንን አምላክ በፈቃዱና በጊዜው እስኪጠራን ድረስ ሕይወትን የመጠበቅ ግዴታ አለብን፡፡ ይሁን እንጂ በተቃራኒው ብዙ ሰዎች ሕይወትን ለማቋረጥ /ለማጠፋት/ ሲገፋፉ ይታያሉ፡፡ ጥቂት የማይባሉም ራሳቸውን ሊያጠፉ ሲሞክሩ ይደረስባቸዋል፡፡ በሀራችን ራሳቸውን ሰቅለው ገዳይ መርዝ ጠጥተው ሰዎች ራሳቸውን ያጠፋፈሉ፡፡ በውጭው ዓለም ከረጅም ፎቅ ራሳቸው ጥለው መሣሪያ ተጠቅመው ራሳቸውን ሲገድሉ ይታያሉ፡፡ ይህ ውድ የሆነችውን እና ልንንከባከባት ኃላፊነት ያለብንን ሕይወት እንድናጠፋ ከሚያደርጉን ዋነኛው ምክንያቱ ብዙ ሆኖ ጭንቀት ብስጭት ነው፡፡
መጽሐፍ ቅዱስ ስለ ሕይወት እንዲህ ይላል፡-
የሕይወት ምንጭ እግዚአብሔር ነው፡፡ ሕይወት የተገኘው ከእርሱ ነው፡፡
‹‹እግዚአብሔር ሰውን ከምድር አፈር አበጀው የሕይወትንም እስትንፋስ በአፍንጫው እፍ አለበት፡፡ ሰውም ሕያው ነፍስ ያለው ፍጡር ሆነ፡፡›› ኢዮ. 33÷4፣ ዘፍ. 2÷7
በኋላም ብዙ ተባዙ ምድርን ሙሏት ባለው አምላካዊ ቃሉ መሠረት ሰው ከወንድና ሴት ይወለዳል፡፡ በዚህም የተፈጥሮ ህግ መሠረት ሰውን በእናቱ ማኅጸን የሚሰራው ሕይወትንም የሚሰጠው እግዚአብሔር ነው፡፡ እንዲህ እንደተፃፈ፡-
‹‹ በውኑ እንደ ወተት አላፈሰሰኸኝም? እንደ እርጎስ አላረጋኸኝም? ቁርበትና ሥጋ አላለበስኸኝም በአጥንተና በጅማት አጠናከርኸኝ ሕይወትና ቸርነት አደረግህልኝ›› /ኢዮብ 10÷10/
በዚህም መሠረት ከፈጣሪ የተገኘውና ለሰው ልጅ የተሰጠው ሕይወት ማንም በፈቀደ ጊዜ እንዲያቋርጠው /ሕይወቱን እንዲያጠፋ/ አይፈቀድለትም፡፡ ሕይወት በምድር ላይ ፅኑ ሰልፍ ናትና፡፡ የሕይወትን ፈተና መቋቋም ያልቻሉ ሰዎች እራሳቸውን ከዚህ የሕይወት ውጣ ውረድ ለማግለል በሚመርጡት ምርጫ ለራሳቸው ከሚሰጧቸው የተሳሳተ ምላሽ አንዱ እራስን ማጥፋት ሲሆን ከሞት በኋላ ባለውም ዘላለማዊና ሰማያዊ ሕይወት የሚያስኮንን እና ከእግዚአብሔር የሚለይ ነው፡፡ በቅዱሱ መጽሐፍ የተገለፀውም በእውነት ይህ ነው፡፡
ፍጥረታትን ያስገኘው እግዚአብሔር አምላክ በእስራኤል በኩል ለዓለም በሰጠው ትዕዛዝ አስርቱ ህግጋት ከምንላቸው አንዱ ‹‹አትግደል›› /ዘፀ. 20÷13/ ይላል፡፡ ይህ የራስንም ሕይወት ስለ ማጠፋት ይመለከታል፡፡ ቀጥሎም በሐዲስ ኪዳን የሐዋርያት ትምህርት ይሕንኑ ሚያፀናነው፡፡
የእግዚአብሔር መቅደስ እንደሆናች የእግዚአብሔርም መንፈስ እንዲኖርባችሁ አታቁምን? ማንም የእግዚአብሔርን ቤተ መቅደስ ቢያፈርስ እግዚአብሔር እርሱን ያፈርሰዋል፡፡›› /1ኛ ቆሮ. 3÷16-17/
በእርግጥ ሰዎች ሕይወትን ለማቋረጥ የሚነሳሱት የሕይወትን ዋጋ ባለመገንዘባቸው ብቻ ነው የሚል ድምዳሜ መስጠት ፍጹም ስህተት ነው፡፡ ከሞቱ በኋላ ስለመኮነን አለመኮነን ብዙ ሊያሳስብ አይችል ይሆናል፡፡ የሚገርማችሁ ግን ትልቅ የሕይወት ስህተት ያለው እዚህ ላይ ነው፡፡ በራሱም ይህ የሚያመለክተው ያሰው ከእግዚአብሔር ጋር ያለው የሕይወት ቁርኝቱ ልኩ የሚታወቅበት ጊዜ ነው፡፡ ምክንያቱም በሕይወቱ ለእግዚአብሔር የመጨረሻን ቦታ የሰጠ ሰው ከዚህ ዓለም በኋላ ስለሚጠበቀው ሕይወትና ክብር ያለው ቁርጠኝነት ለድርድር የሚበቃ ስላልሆነ፡፡
እራስ ማጠፋት በተአምራዊ ኃይል የተገደድንበት ሳይሆን የአስተሳሰባችን ውጤት ነው፡፡ ይህ ደግሞ ተቀጣትሎ ውጤቱ አመጽ /ሞት / እንዲሆን የሚያደርገው የሚያራግበው ጭንቀትና በጭንቀት ማዕቀፍ ውስጥ የሚገኙት ብስጭት፣ ቁጣ፣ ንዴት ናቸው፡፡ ራስን ማጥፋት ደግሞ ሌሎችን ወይም ከዚህ ውሳኔ ያደረሰንን ችግር የምንበቀልበት ሳይሆን ራሳችንን የምንበቀልበት የተሳሳተ ውሳኔ ነው፡፡ ‹‹ተወዳጆች ሆይ ራሳቹን አትበቀሉ›› /ሮሜ. 12÷19/
🙏🙏ይቀጥላል🙏🙏🙏
💦💦💦💦የጭንቀት ጊዜ ለራሳችን የምንሰጣቸው የተሳሳተ የውድቀት ምላሾች 💦💦💦💦💦💦💦💦💦💦💦💦💦💦💦
የቀጠለ ክፍል ፫
፫.ራስን ማግለል እና መደበቅ
ሌላው ብዙ ቁጥር ያላቸው ሰዎች በጭንቀት ምክንያት ለራሳቸው ከሚሰጧቸው የተሳሳቱ የውድቀት ምላሾች አንዱ ራስን ማግለልና መደበቅ ነው፡፡
እንደነዚህ አይነት ሰዎች መጸለይ አልቻልኩም፣ ማጥናት አልቻልኩም፣ መማር አልቻልኩም፣ እያሉ ራሳቸውን ሲያገሉና ሲደብቁ ታገኟቸዋላችሁ፡፡ ይህ ደግሞ ቅዱሳን ራሳቸውን ዝቅ ከሚያደርጉበትና ከሚደብቁበት የትህትና ሕይወት ጋር ምንም ዓይነት ተዛምዶ የለውም፡፡
የሚገርመው ያን ጉዳይ ማድረግ ያልቻሉት ማድረግ ስላልቻሉ ሳይሆን አልችልም ከሚለው አስተሳሰብ ራሳቸውን ስላላወጡና ወኔያቸውንና መንፈሳቸውን ከገደለባቸው አጨናናቂ ሁኔታ ለመውጣት ስላልጣሩ በይበልጥ ለራሳቸው እራስን የማግለል እና የመደበቅ የውድቀት ምላሽ ነፃ ለማድረግ በድፍረት እንዳይወጡ ወኔ ስላጡ ነው፡፡
ብቸኝነትን የመረጡበት ምክንያት በፈቃደኝነት አይደለም፡፡ በፈቃደኝነት ብቸኝነትን የሚመርጡ መንፈሳዊያን ሰዎች ከእግዚአብሔር ጋር ለመነጋገር ሰላማቸውን ከሚነሳ ሁኔታ ለመሸሽ ሲሆን በብቸኝነት ጊዜያቸው ፍፁም የሆነ የውስጥ ሰላምና ፀጥታ አላቸው፡፡
በዚህ በብቸኝነትን በመረጡበት ጊዜም ሥራ አይፈቱም ጸሎት፣ ተመስጦ፣ ቅዱሳት መጻሕፍትን ማንበብ የመሳሰሉ ተግባራትን ያከናውናሉ፡፡
ራስን ማግለልና መደበቅ ለተጨነቁበት ጉደይ ወይም ለደረሰባቸው ችግር መፍትሔ አድርገው የተቀበሉ ሰዎች ግን በመረጡት ከሌሎች የመራቅ አካሄድ ብቻቸውን ሆነው የሚያመላልሱት በሕይወታቸው ተፅዕኖ የሚያሳድሩ ነገሮችን ነው፡፡ ለሌሎች ሰዎች ቀላል የሆኑ ነገሮች ሁሉ በእነዚህ ሰዎች ላይ ጉልበተኞች ናቸው፡፡
ከብዙ የአዕምሮና የተግባር ሥራዎች ተገልለው በብቻቸው ስለተገኙ በሕይወታቸው የማይፈነጭባቸው አስጨናቂ እና አስፈሪ ሀሳበ የለም፡፡ በገዛ ሀሳባቸው እየተሞገቱ ይሰቃያሉ፡፡
ከዚህ የውድቀት ምላሽ ራሳቸውን ለማላቀቅ መጀመሪ ‹‹እችላለሁ›› ብለው ሊነሱ ይገባል፡፡ ከዚም እግዚአብሔር እንዲረዳቸው ‹‹መታመን›› ይኖርባቸዋል፡፡ የሚያስቡት ነገር አሉታዊ ምላሽ ያለው ሳይሆን አውንታዊ ምላሽ ያለው ሀሳብ ሊሆን ይገባል፡፡ ይሁን እንጂ ብቻውን ሀሳብ ምንም ሊሰራ አይችልም፡፡ በተግባር ራሳቸውን ለመለወጥ መነሳት አለባቸው፡፡ ለዚህ ደግሞ ራሳቸውን ከማግለልና ከመደበቅ በአዕምሮም ሆነ በመንፈስ የተሸለ ሰው ሆኖ ለመገኘት በጽኑ ፍላጎት መነሳት አለባቸው፡፡
ይቀጥላል
💦💦💦💦💦የጭንቀት ጊዜ ለራሳችን የምንሰጣቸው የተሳሳተ የውድቀት ምላሾች💦💦💦💦💦💦💦💦💦💦💦💦💦💦💦
ካለፈ የቀጠለ
ክፍል ፬

፨፨፨፨፨፨ ፬ በዝምታ መታፈን፨፨፨፨፨፨፨፨፨ ፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨
በዝምታ መኖርና በዝምታ መታፈን ሰፊ ልዩነት አላቸው፡፡ ዝምታ ብዙ ጊዜ የመንፈስ ቅዱስ ፍሬ መሆኑ የሚተረጎም ሲሆን በዝምታ መታፈን ግን ሰዎች ከጭንቀት የተነሳ ለራሳቻ የሚሰጡት የተሳሳተ የውድቀት ምላሽ ነው፡፡
ልብ በሉ በዝምታና በዝምታ በመታፈን መካከል ልዩነት አለ ማለት ነው፡፡ ይኸ የውስጥ ሰላም ደግሞ በዙሪያችን የሚሆኑ ሁኔታዎች የሚደፈርስና በቀላሉ አስጨናቂ አበሳጭ እና አናዳጅ ነገሮች የሚሰጡት የሸንበቆ አጥር ሳይሆን የብረት ምሰሶ ነው፡፡ ያ ሰው በሁከትም በፀጥታም ስፍራ ያለው ዝምታ አንድ ዓይነት ነው፡፡ በፀጥታ ጊዜ ዝም አይልም፤ በሁከትም ጊዜ አይናወጥም፡፡ ይህ ደግሞ ጽኑ የውስጥ ሰላም ነው፡፡ የዚህ ሰላም ዋስትና ደግሞ እግዚአብሔር ስለሆነ ሰው የመጨረሻዋን ዋስትና ከያዘ የመጨረሻውን የውስጥ እረፍት ያገኛል፡፡ ሰላም ማለት ደግሞ ውስጣዊ እረፍት ማለት ነው፡፡ /ዮሐ. 14÷27/
በዝምታ መታፈን ግን ከዚህ የተለየ ትርጉም አለው፡፡ ያ በዝምታ የታፈነ ሰው ውስጡ ይብላላል፤ አንዳች ማእበልም እንደመታው ባህር ይናወጣል፡፡ ይህ ሰው ምንም ዓይነት ውስጣዊ ዕረፍት እና ፀጥታ የለውም፡፡
ራሱን በዝምታ ማፈኑ ደግሞ ብዙ ሊያማክራቸውና ሊረዱት የሚችሉና በውስጡ የታፈነውን ሊተነፍስ የሚችልባቸውን መንገዶች የሚመለከቱትን ሰዎች ያሳጣዋል፡፡ እነዚህ ሰዎች ነገሮችን ለብቻቸው ስለያዙ ወደ ሰውም በጸሎት ወደ እግዚአብሔር ስለማይተነፍሷቸው ከቁጥጥር ውጪ ሲሆኑ የእብደትንና የቅውስናን አቅጣጫ ይመሩአቸዋል፡፡ እንዲህ ዓይነት ሰው በጊዜ ተመለስ ካልተባለ ወይ እራሱ በውሳኔ ካልመለሰ የሚደርስበት ውጤት ራሱን መምራት የማይችልበትና በሌሎች የሚመራበት ሁኔታ ነው፡፡
ወደ ጭንቀት የጨመሩንን ነገሮች ይዞ በዝምታ የመታፈን አቅጣጫ ከመከተል ምንም ይሁን ምንም የቱንም ያህል ያሳፍር የእኔ ለምንለው ሰው መተንፈስ በይበልጥም ለቤተ ክርስቲያን መግለፁ ጤናማነት ነው፡፡
አንድ ሰው ሲበሳጭ ቁጣ መነጫነጭ ይታይበታል፡፡ በዚሁም ከቀጠለ ውስጡ መቃጠል ይጀምራል፡፡ የልብ ምቱም የጨምራል፡፡ ራሱንም መቆጣጠር ያቅተዋል፡፡ ሁልጊዜ ይህን የሚያደርግና ይህንንም እንደተፈጥሮ ባሕርይው የሚወስደው ከሆነ የሁልጊዜ ሁኔታው ያደርገዋል፡፡ ይህ ደግሞ እጅግ አድካሚ ስለሆነ ምንም ዓይነት መፍትሔ ከመፈለግ ይገታና በዝምታ ታፍኖ መብሰልሰልን ይመርጣል፡፡ ከዚህ በኋላ በዚህ ሳቢያ ለሚመጡ በሽታዎች ይደረጋል፡፡ በጭንቀትና ብስጭት አማካኝነት ሰው የሚዳረግባቸው በሽታዎች በቁጥር አንድ መጽሐፌ የገለጥኳቸው ቢሆንም ለዚህ ርዕስ ግንዛቤ እደግማቸዋለሁ፡፡
ደም ግፊት፣ ካንሰር፣ የልብ ችግር፣ የአንጎል፣ የራስ ምታት፣ ነርቭ ሽባ መሆን የመሳሰሉት በብስጭት የሚመጡ ጭንቀትም የሚያጧጡፋቸው በሽታዎች ናቸው፡፡
በየትኛውም ሁኔታ ይሁን ከእናንተ አቅም በላይ ሆኖ እንቅስቃሴዎችሁን የገታ ወይም ውስጣችሁን የሚያብሰለስል ግራ አጋቢ ሀሳብ ሲከሰትባችሁ ያን የእኔ ለምትሉት ሰው መተንፈሱ ለቤተ ክርስቲያን መናገሩ በዝምታ ከመታፈን የተሸለ አማራጭ ነው፡፡ በዝምታ መታፈን ግን በራሳችን ላይ የምናውጀው የውድቀት አዋጅ ነው፡፡ ይቀጥላል💦💦💦💦💦💦💦
ሚስትህን አትናቃት
ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ

“በቤት ውስጥ በሚስትህ ምክንያት አንድ ደስ የማያሰኝ ስሕተት ቢፈጠር ‘አይዞሽ’ ልትላት ይገባል እንጂ ኀዘኗን ልታባብሰው አይገባህም፡፡ ኹሉንም ነገር ብታጣም እንኳን ከጎኗ ኹን፡፡

እርግጥ ነው ለባልዋ ደንታ ከሌላት ሚስት በላይ ምንም አሳዛኝ ነገር የለም፡፡ በእናንተ መካከል ጸብ ክርክር ከሚፈጥር የሚስትህ ጥፋት በላይ አሳዛኝ ነገር የለም፡፡ ስለዚሁ ዋና ምክንያት ግን ለእርስዋ ያለህ ፍቅር እጅግ ጽኑዕ ሊኾን ይገባዋል፡፡ እኛ ክርስቲያኖች አንዳችን የሌላችንን ሸክም እንድንሸከም የታዘዝን ከኾነ፥ ከዚህ በላይ ደግሞ አንተ የሚስትህን ሸክም ልትሸከም ይገባሃል፡፡

በመኾኑም ድኻ ብትኾን ስለዚሁ ምክንያት በፍጹም አትናቃት፡፡ ሰነፍ ብትኾን ስለዚሁ ምክንያት አስተካክላት እንጂ አታዋርዳት፡፡ እርስዋ አካልህ ነችና፤ አንተም አካልዋ ነህና፤ አንድ አካል ናችሁና፡፡

‘ክፉ ነች፤ ቁጡ ነች፤ ራስዋን መቈጣጠር የማትችል ግልፍተኛ ነች’ ልትለኝ ትችላለህ፡፡ ስለዚሁ ጠባይዋ እጅግ ልታዝን ይገባሃል፡፡ ነገር ግን እግዚአብሔር ይህን ጠባይ ያርቅላት ዘንድ ጸልይላት እንጂ አንተም መልሰህ አትቈጣት፡፡ ልታሳምናት ሞክር እንጂ ወደ ሙግት አትግባ፡፡ እነዚህን ክፍተቶችዋን ከእርስዋ ለማራቅ ኹሉንም ዓይነት በጎ ዘዴዎችን ተጠቀም፡፡”

“ይህን እንደማድረግ ሚስትህን የምትመታትና የምታሠቃያት ከኾነ ግን እነዚህ ሕመሞችዋ እንዲድኑ አታደርጋቸውም፡፡

ኃይለኝነት የሚወገደው በጭካኔ ሥራ ሳይኾን በየውሃት ነውና፡፡ ከዚሁ በተጨማሪም ሚስትህ በየውሃት ስትይዛት ከእግዚአብሔር ዘንድ ሹመት ሽልማት እንደምታገኝ አስታውስ፡፡

ከአሕዛብ ፈላስፎች አንዱ ክፉ፣ መራራና ሥርዓት የለሽ ሚስት ነበረችው ይባላል፡፡ ከዕለታት በአንዱ ቀን ለምን ከእርስዋ ጋር እንደሚኖር (ለምን እንደማይፈታት) በተጠየቀ ጊዜ ጠቢቡ ሰው በገዛ ቤቱ ውስጥ የፍልስፍና ትምህርት ቤት እንዳለው ነበር የመለሰው፡፡ ‘ዕለት ዕለት በዚህ ትምህርት ቤት የምማር ከኾነ ከሌሎች ሰዎች ይልቅ ታጋሽ እኾናለሁ’ ነበር ያለው፡፡ በዚህ ተደነቅህን? እኔ ግን መላእክት እንዲያውም ከእነርሱም በላይ የዋሃን ኾነን እግዚአብሔርን እንድንመስለው ከታዘዝነው ከእኛ ይልቅ አረማውያን ሰዎች ጠቢባን ኾነው ስመለከታቸው ፈጽሜ አለቅሳለሁ፡፡ ያ ፈላስፋ ሚስቱን እንዳይፈታት ምክንያት የኾነው የእርስዋ ክፉ ጠባይ ነው፡፡ እንዲያውም አንዳንድ ሰዎች ‘ይህ ፈላስፋ ይህቺን ሴት ሚስት ትኾነው ዘንድ ያገባት ይህን ለማግኘት ብሎ ነው’ ይላሉ፡፡

አንተም ዕጮኛ ስትመርጥ በምርጫህ ተሳስተህ ክፉ ሚስት አግብተህ ከኾነ (ብታገባ) ቢያንስ ቢያንስ ይህን አረማዊ ፈላስፋ አብነት አድርገው፡፡ ሚስትህን ለማስተካከል የተቻለህን አድርግ፡፡ ክፋትዋን በሌላ ክፋት አትመልስላት፡፡

ከእርስዋ ጋር ኾነህ የትዳርን ቀንበር የምትሸከም ከኾነ ሌሎች ብዙ ረብ ጥቅሞችንም ታገኛለህና፤ መንፈሳዊ ተግባራትን ለመተግበር ቀላል ይኾንልሃልና።
መንፈስ ቅዱስ በልባችን ውስጥ ካላደረ በዚህ ጸሎት ውስጥ ያለውን የፍጹምነት ደረጃ ልናገኝ አንችልም። #መንፈስ_ቅዱስ በልባችን ውስጥ ካደረ ግን ጸሎታችን ሊቋረጥ አይችልም፥እንቅልፍ ቢወስደንም እንኳ።

#አባ_ይስሐቅ
🙏🙏🙏🙏 ለጸሎት ተነሱ🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏
ውድ የቻናል አባላቶች አብራችውኝ በመንፈስ የምንረዳዳ መንፈሳዊ እህት ውንድሞቼ ሰላም ለናንተ ይሁን ለምትጠይቁት ጥያቄ ቶሎ መልስ ባለመጠቴ ይቅርታ እጠይቃለው ለምትሰጡኝ ሀሳብ አስተያየት እጅግ ደስተኛ ነኝ በናንተ ላይ አድሮ ፈጣሪ ስለሚመክረኝ ተባረኩልኝ በጸሎትም አስቡኝ እዚህ ያልተቀላቀሉትን በመቀላቀል የናንተ ስራ ሲሆን ሌላው ማስተማሩ የፈጣሪ እና የባርያው ስራ ይሆናል የጠፍትን የምንፈልግበት በቤቱ ያሉትን የምናበረታበት ይህ መንፈሳዊ ጉባኤ ነው በመንፈሳዊ ጉባኤ ልዩ የሚያደርገው ወንድሞች እህቶች የውስጥ ችግሮቻቸውን የሚፈቱበት የማይፈታ የሚመስለውን ሁሉ እዚህ መፍቴ ያገኛሉ በተጨማሪ ካህናቶች አብረውኝ ስለሚሰሩ ጭንቀት የውስጥ ችግሮች አብረን እፈታለን ንስሀ አባት ከሌሎት ከእርሶ የሚጠበቀው መንገር ብቻ ነው በተቀመጠው ሰዓት በመግባት ባሉበት በጋራ እንጸልያለን ባባቶች እንባረካለን ። ከእርሶ የሚጠበቀው ውንድምና እህቶቻችንን እዚህ በማስገባት መንፈሳዊ ግዴታዋን ይወጡ
ትልቅ ምክር

ትልቅ አምላክ እንጅ ትልቅ እሚባል ችግር የለም /ረበና/
የምታመልከው አምላክ በነገሮች ሁሉ ላይ የበላይ እንደሆነ አትዘንጋ /ጀሊሉ
ፈተና ከገጠመህ ፀልይ እንጅ አታጉርምርም ፈጣሪ ሁሌም ታላቅ ነውና
ወዳጅ ሆይ ለህሊናህ እርፍት ለልብህ ደስታን ከፈለክ ሁልጊዜ መልካም
ሰው ሁን መልካምነት ለራስ ነው።
በልባችን መልካምነት ካለ እንኳን የተርፈን ያለችንን እንካፈላታለን
ሁሌም ጥሩ ነገር እናድርግ ምክኒያቱም ከክፋት ደግነት ትልቅ ዋጋ
አለውና።
ደግነት አንድ ቀን መልሶ ይከፍላል መልካምነት ለራስ ነውና
መልካም ሰው መልካም ሂወትን ያገኛል
መልካም ወንድ መልካም ሚስትን ያገኛል
መልካም ሴት መልካም ባልን ታገኛለች
መልካም ሰው መልካም ልጆችን ያገኛል
መልካም ሰው ደስታን ያገኛል
መልካም ሰው ሰላምን ያገኛል
መልካም ሰው ፍቅርን ያውቃል
መልካም ሰው መልካም ነገርን ያገኛል
ታዲያ መልካም ሰው መሆንን የማይፈልግ ማነው።
ፈጣሪ መልካም ሰው እንድንሆን ይርዳን አሜን።
____ ___
💦💦💦💦💦የጭንቀት ጊዜ ለራሳችን የምንሰጣቸው የተሳሳተ የውድቀት ምላሾች💦💦💦💦💦💦💦💦💦💦💦💦💦💦💦
የመጨረሻ ክፍል
ክፍል 5
5 ራስን ማፈር
ወደ ጤናማ የንስሐ ሕይወት ከምንመራባቸው መንገዶች አንዱ የጥፋተኝነት ስሜት መሰማቱ ነው፡፡ ይህ ደግሞ ጤናማ የሆነ በሰራነው ስህተት የጥፋተኝነት ስሜትና የእረፍት ስሜት እንዲኖረን ደደርጋል፡፡ ይሁን እንጂ ራስን ማፈን ግን ለራሳችን ከምንሰጣቸው የተሳሳቱ የውድቀት ምላሾች አንዱ ነው፡፡
ራሱን የማፈር ስሜት ያደረበት ሰው ራሱን ይደብቃል፣ ያገላል፣ ራሱን የሚደብቅና የሚያገል ከሆነ ደግሞ ራሱን ወደ ንስሐ ይዞ አይወጣም፡፡ ራስን በማፈር ሳቢያ በብዙ ሰዎች ሕይወት የሚያድረው የጨካኝነት መንፈስ በራሳቸው ላይ የጭካኔ እርምጃ እንዲወስዱ ይገፋፋቸዋል፣ ሲናገሩ የሚደመጡትም በራሳቸው ላይ አሉታዊ የሆኑ ነገር ነው፡፡ ለምሳሌ፡-
ሞት ይገባኛል
እኔ ሰው አይደለሁም
ራሴን ማትፋት ብችል
ሰው ለምን ተፈጠረ
ይህን ባደርግ ምን ይጠቅመኛል
መኖሬ ትርጉም የለውም
የሚሉ ራሳቸውን ከማፈራቸው የተነሳ በሕይወት ቁም ነገር ላይ ተስፋ መቁጠራቸውን የሚመላክቱና ቀጣዩ ሁኔታቸው ምን ሊሆን እንደሚችል የሚያሰጋ ቃል ከአንደበታቸው ሲወጣ ይደመጣል፡፡
እነዚህ ሰዎች በዚህ ዓይነት ሁኔታ የሚመላለሱት ሽንፈትን አሜን ብለው ተቀብለውና በፍርሀት እንደ ጥጥ እየባዘቱ ራሳቸውን ከማፈራቸው የተነሳ ራሳቸውን ደብቀው የሚኖሩና ውስጣቸው ጭንቀት በተባለው ጽኑ ባለጋራ ሲተራመስ የሚኖሩ ናቸው፡፡
በእርግጥ የሰው ልጅ ለተፈጥሮው የማይስማማና የሞራል ጥያቄ ለሚያስከትልበት ተግባር ራሱን ባይደርግ መልካም ነው፡፡ ስህተቶች ከተከሰቱ በኋላ ወይም ችግር ውስጥ ከገቡ ለራሳችን የውድቀት ምላሽ ከመስጠት መጠበቅ የቀደመውን ስህተት ሁሉ የሚያስተካክል መንገድ ነው፡፡
ሁልጊዜ ለሽንፈት እጃችንን ላለመስጠት የምንጋደል ልንሆን ይገባል፡፡ ራስን ማፈር አሜን ብሎ መቀበል ሽንፈትን በጸጋ መቀበል የሚመለክት ነው፡፡ ቅዱስ መጽሐፍ ‹‹ጻድቅ ሰባት ጊዜ ይወድቃል ሰባት ጊዜ ይነሳል›› በማለት ቅዱስ ዳዊት የእግዚአብሔር ሰዎች ወድቀው መቅረትን /ሽንፈትን/ እንደ ማያስተናግዱ ይነግረናል፡፡
ራስን አፍሮ በመኖር ሕይወት ውስጥ የሚመላለሱ ነገሮችን መሰላቸት፣ እርካታ ማጣት፣ ተስፋ ቢስነት በማናቸውም ነገሮች ደስታ ማጣት ስለሆነ በራሳችን ላይ ጉዳት ለማስከተል እንገፋፋለን፡፡ በዚህ ሁኔታ ህይወትን ትርጉም ባላቸው እውነታዎች ለመሙላት ወደሚስችል የሕይወት አማራጭ ለመምራት አዳጋች ነው የሚሆነው፡፡
ስለዚህ እንደዚህ ዓይነት ችግር ውስጥ ላለ ሰው ከውድቀት ማገገም ቀስ በቀስ የየዕለቱን እንቅስቃሴ ትርጉም ያላቸው በማድረግ ምንም ይሁን ምንም ማናቸውንም ነገር ለመጋፈጥ ወስኖ ባልሸነፍም ባይነት የእግዚአብሄርን ክንድ ተንተርሰን ችግሮችን ሁሉ ከማሸነፍ በኋላ ያለውን ደስታ ለማግነት በመጓጓት በቀደመው ስህተቶቹ ላይ ጠባሳ የማያስቀር ንስሐ በመግባት ካለፈው ስህተት በመማር ራሱን ማግኘት ይኖርበታል፡፡
ተፈጸመ 👏👏👏👏👏👏👏👏👏👏👏👏👏👏👏
ለጸሎት ተነሱ

ውሎሕ
🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿
አንተ የምትመስለው ውሎሕን እንደመሆኑ ሁሌ ማታ ላይ የት ነበር የዎልኩት? በልና ራስሕን ጠይቅ ከዛም ከውሎሕ ያገኘኸውን መልካም ነገርና ያገኘኽን መልካም ያልሆኑ ነገሮች ተመልከታቸው ምን የሕል ተጠቅመሀል? ምን ያሕልስ ተጎዳሕበት አንተ መዎያሕን ስታስተካክል የሚያሳየው የልብሕ ፍላጎት በምን አይነት የሕይወት መንገድ መሔ እንደሚፈልግ ነው አንተ ቀድመሕ መዎያሕን ስታስተካክል ውሎሕ ደግሞ መልሶ አንተን እያስተካከለ ይመጣል በውሎሕ ከተዘናጋሕ በሕይወትሕ ትልቁን መዘናጋት አምጥተኃል ማለት ነው ። ምንም እንኳን ለጊዜው ደስታ የማይሰጥ አሰልቺና ደስ የማይል መዎያ ቢሆንብሕም በመልካም ቦታዎች ለመዎል ራስሕን አስገድድ ለጊዜው ራስሕን በማስገደድም ቢሆን የምትውልባቸው ጥቅሙን ስታይና ተጠቃሚነትሕን ስታረጋግጥ እየወደድከው ደስ እያለሕ መዎል ትጀምራለሕና ይሕን በኑሮሕ ተለማመድ
መልካም ምሽት ይሁንልን
🙏🙏🙏🙏🙏ለጸሎት ተነሱ 🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🏿🙏🙏🙏🙏🙏
#አንጨነቅ

በርግጥም ተፈጥሮአችንን ካለ መኖር ወደ መኖር ያመጣው እርሱ ነውና፥ የሚያስፈልገን ምን እንደ ኾነም ጠንቅቆ ያውቃል፡፡ ስለዚህ፡- “ርግጥ ነው፥ እርሱ አባታችን ነው፡፡ የምንሻቸው ነገሮችም እጅግ አስፈላጊ ናቸው፡፡ ነገር ግን አሁን እንደሚያስፈልጉን አያውቅም” ማለት እንደ ምን ይቻልሃል? የገዛ ተፈጥሮአችንን እንኳን የሚያውቅ እርሱ፣ ማወቅ ብቻም ያይደለ ይህን ተፈጥሮአችንን የፈጠረ እርሱ፣ የፈጠረ ብቻ ያይደለ እንዲህ [ያስፈልጋል የምንለው ነገር እንደሚያስፈልገው] አድርጎ የፈጠረው እርሱ፥ አንተ ራስህ ለራስህ ያስፈልገኛል ከምትለው በላይ ምን እንደሚያስፈልግህ ያውቃል፡፡ ተፈጥሮአችን እንደዚህ ያለ ነገር እንዲያስፈልገው አድርጎ የፈጠረው እርሱ ራሱ ነውና፡፡ ስለዚህ እርሱ አስቀድሞ ያስፈልገዋል ብሎ ፈቅዶ ለፈጠረው፣ እንደሚያስፈልገው አድርጎ ፍላጎት ለሰጠው ተፈጥሮህ አያስፈልገውም ብሎ እንደ ገና ራሱን መቃወም አይቻለውምና፥ ተፈጥሮህ የሚሻውንና አጽንቶ የሚያስፈልግህን ነገር አይነሳህም፡፡

ስለዚህ አንጨነቅ፡፡ በመጨነቃችን ራሳችንን ከመጉዳት የዘለለ ሌላ የምናተርፈው ወይም የምናገኘው ነገር የለምና፡፡ እግዚአብሔር ብንጨነቅም ባንጨነቅም የሚያስፈልገንን ነገር ይሰጠናልና፡፡ በተለይ ደግሞ የማንጨነቅ ስንኾን የሚያስፈልገንን ነገር እንደሚያስፈልገን ዐውቆ ይሰጠናል፡፡ እንደዚህ ከኾነ ታዲያ እንዲያውም “አትጨነቅ” የሚለውን ትእዛዝ በመተላለፍህ ተጨማሪ ቅጣት በራስህ ላይ ከማምጣት በቀር፥ ተጨንቀህ የምታተርፈው ነገር ምንድን ነው? አንድ ሰው ወደ ባለጠጋ ሰው ቤት ለግብዣ እየኼደ “ምን እበላለሁ?” ብሎ አይጨነቅም፤ ወደ ምንጭ ውኃ እየኼደም “ምን እጠጣለሁ?” ብሎ አይብከነከንም፡፡ እንግዲያውስ እኛም ከየትኛውም ዓይነት ምድራዊ ምንጭ በላይ የተትረፈረፈ ውኃ ወይም ቊጥር የሌለው የተሰናዳ ማዕድ አለንና እርሱን እያየን ነዳያን ወይም በአእምሮ ሕፃናት አንኹን፡፡ ይኸውም መግቦተ እግዚአብሔርን ማለቴ ነው፡፡

(#ቅዱስ_ዮሐንስ_አፈወርቅ፣ የማቴዎስ ወንጌል፣ ድርሳን ፳፪፥፫)

@KaleEgziabeher
ክፋትን_ከአንተ_አርቃት።

"ሰይጣን ክርስቶስ በልብህ ውስጥ ያለ መሆን አለመሆኑን ያውቃል፡፡ ይኸውም ስትቆጣ ወይም ስትጮህ ወይም የማይረቡ ከንቱ ነገሮችን ስትናገር ሲያይህ ጠላት በአንተ ዘንድ እግዚአብሔር እንደሌለ ያውቃል ያን ጊዜ በውስጥህም በውጭህም ያለውን ሳይቀር ይገዛል ፤ መዝጊያ እንደሌለው ቤት እንደ ክፉ ሌባ ይገባና ውስጥህን ይበረብረዋል፡፡"

#ቅዱስ_ባስልዮስ
🙏🙏🙏🙏 ለጸሎት ተነሱ🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏
"ከውሻ እና ከ አቦሸማኔ የቱ ሊፈጥን ይችላል?" ተብሎ በዓለም ላይ ካሉ ፈጣን የውሻ ዝርያወች ተመርጠው ከአንድ አቦሸማኔ ጋር የውድድር ፕሮግራም ይደረጋል።

ውድድሩ ሲጀመር ውሾቹ ተፈትልከው ሲሮጡ አቦሸማኔው ስንዝር ያህል እንኳአ ለመሮጥ ፍላጎት አላሳየም።
በዚህ የተገረሙት ታዳሚዎች የውድድሩን አላፊ "አቦሸማኔው ለምን ሊሮጥ አልሞከረም?" አሉት።

አላፊውም "አንዳንዴ ምርጥነትህን_የማይገባ (የማይመጥንህ) ቦታ ላይ ለማሳየት መሞከር የስድብ ያህል ነው" አላቸው።
Don't prove your self every where' ማንነትህን በማንኛውም ቦታ ላይ ለማሳየት አትሞክር።
ምክንያቱም እንደ አቦሸማኔ የሆነ አቅምህን ከውሾች ጋር አውርደህ አትፎካከር።

ወዳጄ ሁሉም ነገር ቦታ እና ጊዜ አለው
በልክ እና የእውነት እንኑር
መልካም ቀን