✨KB Orthodox✝️
1.76K subscribers
267 photos
5 videos
1 file
11 links
ኦርቶዶክሳዊ ጥቅሶችና መዝሙሮችን ያገኛሉ✝️

ሌላኛውን ቻናላችንን ይቀላቀሉ 👉 @KB_Creatives
Download Telegram
መናገር ባለብህ ሰአት ብቻ ተናገር ... "አስተውል ከአይሁድ ጫጫታ ይልቅ የክርስቶስ ዝምታ ነው ጲላጦስን ያስጨነቀው"

አስተዋይ ግን ዝም ይላል(ምሳሌ 11:12)


✝@KB_ORTHODOX✨
🥰8❤3😍2👍1
ለማትኖሩበት ጊዜያዊ ዓለም ደክማችሁ ፤ ወደምትኖሩበት ዘላለማዊ ዓለም ባዶ እጃችሁን እንዳትሄዱ ተጠንቀቁ።

✝@KB_ORTHODOX✨
😍6😘4👍1
መልካም አድርግና እርሳው!

ስላደርግኸው ስለዚህ ነገር ማንኛውንም ዓይነት ውዳሴም ሆነ ሙገሳ አትሻ። መልካም ያደረግህለት ሰው አንተ እንዳደረግህለት ለአንተ መልካም የሆነውን አጸፋ እንዲመልስልህ ወይም አንተ አንደተንከባከብከው እርሱም እንዲንከባከብህ አትጠብቅ።

መልካም ስታደርግ በምላሹ መልካም ዋጋ አገኛለሁ ብለህ በመጠበቅ ላለመሆኑ እርግጠኛ ሁን! መልካም የምታደርገው መልካም ማድርግን ስለምትወድ ወይም መልካም ከማድረግ መከልከል ስለማትችል ለመሆኑ እርግጠኛ ሁን። መልካም መሆን በውስጥህ ያለ ጠባይ ይሁን። መልካም ጠባይ እንደ መተንፈስ ምንም ዓይነት ጥረት የማይጠይቅ ግብታዊ ነገር ይሁን።

እንዲህ ያለውን ነገር የምትረሳው ከሆነ እግዚአብሔር በዚህ ምድርም ሆነ በሚመጣው ዓለም ያስታውስሃል። መልካም ማድረግህን የምታስታውሰውና በውስጥህ ይዘኸው የምትቆይ ከሆነ ግን ታጣዋለህ።

✍🏻ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ሺኖዳ ሣልሳዊ
❤7👍2🥰2😍1
ጠቃሚ ምክር!

ገንዘብ ወዳጅ አትሁን ከባለፀጋም ሽሽ ትሑት ሰው ፈልግ እንጂ በእግዚአብሔር ዘንድ ክቡር ትሆን ዘንድ የባሕርይ ፍላጎትህንና ምኞትህን ሁሉ ተው የዚህን ዓለም ትርፍ ሁሉ ንቀህ አቃልለህ ተወው እጅህን ለመቀበል ያላይደለ ለመስጠት ዘርጋ!

(መፅሐፈ ወግሪስ በአባ ገብረኪዳን)
😍3❤2👍1🥰1😘1
🥰5❤1👍1😍1
"ያልጠፋነው ከእግዚአብሔር ምሕረት የተነሣ ነው፤ ርኅራኄው አያልቅምና።
ማለዳ ማለዳ አዲስ ነው፤ ታማኝነትህ ብዙ ነው። "
ሰቆቃወ ኤርምያስ 3÷22-23

ለአዲስ ዘመን የቀረችውን ይህቺን ቀን እንዴት አየን?
ምሕረት፣ ርኅራኄና ትዕግስት ገንዘቡ በሆነ በእግዚአብሔር አይደለምን።

ታዲያ ያለህ ዛሬ ከዛሬም አሁን ሆኖ ሳለ ወደርሱ ላለመመለስ ታመነታ ይሆን? 
"ወደ እኔ ተመለሱ፥ እኔም ወደ እናንተ እመለሳለሁ፥ ይላል የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር። "
ሚልክያስ 3÷7

ምሕረት ለማድረግ የታመነ አምላክ አለህና ተነስ ቀኗ ሳታልፍ ወደ ርሱ ሩጥ ወደ ርሱ ተመለስ።
"በኃጢአታችን ብንናዘዝ ኃጢአታችንን ይቅር ሊለን ከዓመፃም ሁሉ ሊያነጻን የታመነና ጻድቅ ነው። "
1 ዮሐንስ 1÷9

✨✨✨ሠናይ ቀን ✨✨✨

✝@KB_ORTHODOX✨
😍5❤1👍1😘1
“እጅግ ምርጡ ጸሎት 'ጌታ ሆይ
አንተ ሁሉን ታውቃለህ
የፈቀድከውን አድርግልኝ።'
ማለት ነው።’’

✍️ባሕታዊው ቴዎፋን

✝@KB_ORTHODOX✨
👍6😘2❤1🥰1😍1
“ፊተኛ ኑሮአችሁን እያሰባችሁ እንደሚያታልል ምኞት የሚጠፋውን አሮጌውን ሰው አስወግዱ፥ በአእምሮአችሁም መንፈስ ታደሱ፥ ለእውነትም በሚሆኑ ጽድቅና ቅድስና እንደ እግዚአብሔር ምሳሌ የተፈጠረውን አዲሱን ሰው ልበሱ።”

ኤፌሶን 4፥22
👍5❤3😍3😘1
“በራስህ ጽድቅ አትታመን፤
ስላለፈው አትጨነቅ፤
ይልቅኑ አንደበትህንና ሆድህን ግዛ።’’

✍️ቅዱስ አባ እንጦንስ

✝@KB_ORTHODOX✨
😍4❤1👍1🥰1😘1
ተሰፋ በፍፁም አትቁረጥ !

ወዳጄ! ተስፋ መቁረጥህ ለሰይጣን ድግስ ነው፤ ስብራትህ ግን ለእግዚአብሔር የሥራ ቦታ ነው። ልበ አምላክ መዝሙረኛው ዳዊት እንዲህ ብሏልና ... 'እግዚአብሔር ልባቸው ለተሰበረ ቅርብ ነው'

'ከዐሥሩ ድሪም' ውስጥ ዘጠኙም ቢጠፉ፣ ባለቤቱ አልጠፋም! እርሱ 'ዐሥር' አድርጎ ሊመልስልህ የታመነ ነው።

ዛሬም በምሬትህ ውስጥ ሆነህ 'ጌታ ሆይ! ቤቴን ጥረገው፣ መብራትህንም አብራው፣ እኔንም አግኘኝ' በል።
አንተ ስትገኝ የጠፋው ሰላምህና ደስታህ እንደ አዲስ ይበራል። እግዚአብሔርም ፀሎትህን ይሰማል።
❤8👍2😍1😘1
“ሥራ ስትሠሩ እግዚአብሔርን ፈርታችሁ ሥሩ፤
ስትናገሩ እግዚአብሔርን ፈርታችሁ ተናገሩ፤
ስታገቡ እግዚአብሔርን ፈርታችሁ አግቡ፤
ስትነግዱ እግዚአብሔርን ፈርታችሁ ነግዱ፤
መንገድ ስትሄዱ እግዚአብሔርን ፈርታችሁ ሂዱ፤
ስታስተዳድሩ እግዚአብሔርን ፈርታችሁ አስተዳድሩ።’’

✍️አባ ገብረ ኪዳን

✝@KB_ORTHODOX✨
❤6😘5👍1😍1