Jafer Books 📚
28.2K subscribers
7.42K photos
123 videos
72 files
1.01K links
የንባብ ባህል እንዲዳብር እንተጋለን !!
አድራሻችን
ለገሃር ተወልደ ህንጻ
አራት ኪሎ ብርሃና ሰላም ፊት ለፊት
አብርሆት ቤተመጻሕፍት ግቢ ውስጥ
ጥቁር አንበሳ ትምህርት ቤት ፊት ለፊት
ሳሪስ አዲሱ ሰፈር
ጀሞ

ለቴሌግራም https://t.me/Jafbok

ለፌስቡክ https://www.facebook.com/jaferbookshop?mibextid=ZbWKwL

ለዌብሳይት www.jaferbooks.com
Download Telegram
ለ_ር ግ ብ : ሴ ት፥ ዝ ማ ሬ፡፡

ባለ አክናፍ አካልዋን፥ ስትበርበት ቢያያት
ከ እ ጁ  እ ን ድ ት ገ ባ፥  በ ዓ ይ ኑ  ተ ማ ጸ ና ት፡፡

ከሰማይ ወረደች፥ ርግብም ዝቅ ብላ
ገ ባ ች  ከ ጠ ራ ት  ቤ ት፥  ነ ጻ ነ ቷ ን  ጥ ላ፡፡

ርግብን ሲጨብጥ፥ ሰው ፍርሃት ወረሰው
እ ግ ረ ኛ  ነ ው ና፥ ክ ን ፋ ም  ሴ ት ጨ ነ ቀ ው፡፡

ጎጆ መሳይ ወኅኒ፥ ለምሽቱ አዘጋጀ
ቀ ለ በ ት  አ ው ል ቆ፥  እ ግ ረ-ሙ ቅ  አ በ ጀ፡፡

ወ ዳ ጄ  :  ሆ ይ፥ 
እ ን ግ ዲ ህ  :  ም ን : ት ሆ ኚ?

ባለ አክናፍ አካልሽ
በ ሰ ው  እ ጅ  ወ ድ ቆ፥ ከ ሰ ማ ይ ባ ይ ወ ጣ ም
ብረሪ ወ'ዳሻሽ
በ ዕ ን ቅ ል ፍ ሽ  ው ስ ጥ  ያ ለ ው፥  ሕ ል ም ሽ  አ ል ታ ሰ ረ ም፡፡

@Nomadicpoems
Forwarded from Esubalew Abera N.
ለ_ር ግ ብ : ሴ ት፥ ዝ ማ ሬ፡፡



ባለ አክናፍ አካልዋን፥ ስትበርበት ቢያያት
ከ እ ጁ  እ ን ድ ት ገ ባ፥  በ ዓ ይ ኑ  ተ ማ ጸ ና ት፡፡

ከሰማይ ወረደች፥ ርግብም ዝቅ ብላ
ገ ባ ች  ከ ጠ ራ ት  ቤ ት፥  ነ ጻ ነ ቷ ን  ጥ ላ፡፡

ርግብን ሲጨብጥ፥ ሰው ፍርሃት ወረሰው
እ ግ ረ ኛ  ነ ው ና፥ ክ ን ፋ ም  ሴ ት ጨ ነ ቀ ው፡፡

ጎጆ መሳይ ወኅኒ፥ ለምሽቱ አዘጋጀ
ቀ ለ በ ት  አ ው ል ቆ፥  እ ግ ረ-ሙ ቅ  አ በ ጀ፡፡

ወ ዳ ጄ  :  ሆ ይ፥ 
እ ን ግ ዲ ህ  :  ም ን : ት ሆ ኚ?

ባለ አክናፍ አካልሽ
በ ሰ ው  እ ጅ  ወ ድ ቆ፥ ከ ሰ ማ ይ ባ ይ ወ ጣ ም
ብረሪ ወ'ዳሻሽ
በ ዕ ን ቅ ል ፍ ሽ  ው ስ ጥ  ያ ለ ው፥  ሕ ል ም ሽ  አ ል ታ ሰ ረ ም፡፡


#Nomadic_Poems
ወደ ውበት መንገድ ::

በእሱባለው አበራ ::
Forwarded from Esubalew Abera N.
ወደ ውበት መንገድ፡፡


በደረቅ ምሽት፥ ዕንቅልፍ ንቆኝ ሲሔድ
ደጃፌን ከፍቼ፥ ኮረብታ ላይ ወጣሁ
ፍለጋ ብገጥምም፥ ወደ ውበት መንገድ
ከራሴ በስተቀር፥ የሚወስደኝ አጣሁ፡፡


በዚያን ምሽት
እንኳን ኮከብ፥ ሰማይ አልነበረም
በዚያን ምሽት
ተረት ናት ጨረቃም፡፡


የ ት : ገ ቡ : ይ ባ ላ ል?

“አቤት” ን ባያውቅም፥
ሰማይን ተጣራሁ፥ ጉሮሮዬን ስዬ
ብርሃን ባይለግሱም፥
ከዋክብት ኀሰስኩኝ፥ ዛፍ ላይ ተንጠልጥዬ
ፊቷን ባታሳይም፥
ዘመርኩ ለጨረቃ፥ “ድምቡል ቦቃ” ብዬ፡፡


መልስ : የለም
መልስ : የለም፥
እንዲያው : ዝም
እንዲያው : ዝም፡፡

መንፈስና አካሌ፥ እርስ በእርስ ሲጣሉ
ከኮረብታው ወረድኩ፥ ወደ ቤቴ አቀናሁ
ዝንተ ዓለም ስራገም፥ የጠፉኝን ሁሉ
በእኔው ዕንቅልፍና አልጋ፥ ተኝተው አገኘሁ፡፡


የ ተ ረ ገ ሙ !





#Nomadic_Poems
Forwarded from Esubalew Abera N.
ዘመን እንደ ክረምት ፍሳሽ ነው፡፡ ልጅነታችን እንደ ምንጭ ጠበል ያስፈስሰናል፡፡ ወጣትነታችን እንደ ደራሽ ጎርፍ ያምታታናል፡፡ ሽምግልናችን እንደ ውቅያኖስ ውኃ ያረጋጋናል፡፡


ዛሬም የሚፈስሱ ሕጻናትን አያለሁ፡፡ የሚስቁ፥ የሚያለቅሱ፥ የሚቦርቁ፥ የሚፈነድቁ ምንጮችን፡፡

የሚጎርፉ ወጣቶችንም አያለሁ፡፡ ደፋር፥ ጉልበታም፥ ሯጭ፥ ሐሳቢያውያን፥ ሕልመኛ፥ መልከኛ፥ ድርጊታም ወንዞችን፡፡

የተረጋጉ ሽማግሌዎችንም አያለሁ፡፡  ጡረታ የወጡ፥ እንቅልፍ 'ሚለጥጡ፥ ካፌ 'ሚቀመጡ፥ ወግ 'ሚጠረቁ፥ ዝምብ 'ሚያባርሩ፥ ትውልድ 'ሚታዘቡ፥ አይ ጊዜ የሚሉ፥ ወደ ሞት 'ሚነጥፉ እልፍ ውቅያኖሶችን፡፡

ስለሕይወት መልክ ስንጠይቅ. . .


ስንት ሻሂ፥ ስንት ቡና ጠጣን? ስንት ሲጋራ አጢሰን፥ ስንት ቢራ ጨለጥን? ስንቴ በሰዓት ደርሰን፥ ስንቴስ አረፈድን? ስንት ሳቆች ስቀን፥ ስንት ፈገግታ ፈገግን? ስንቴስ ተደብረን፥ ስንቴ ሐዘን ገባን? ስንት ጨለማ አይተን፥ ስንት ዕንባ አነባን? ስንት ሰው አወቅን፥ ስንት ሰው ጠበስን? ስንት ሰው ተኳርፈን፥ ስንት ሰው ታረቅን? ስንት ሰው ጨብጠን፥ ስንት ሰው አቀፍን? ስንት ሰው ሸኝተን፥ ስንት ሰውስ ገፋን? ስንት ሰው አፍቅረን፥ ስንት ሰውስ ተኛን? ስንቱን ገላ ዳብሰን፥ ስንቱን ቀዳዳ አየን? ስንት ሰው ፈውሰን፥ ስንት ሰው ገደልን? ስንት ሰዎች ሰብረን፥ ስንት ሰው ጠገንን? ስንት ሰው አስቀን፥ ስንቱን አስለቀስን? . . .ብለን ነው፡፡ ከዚህ ሌላ የምናወራርደው ሒሳብ የለብንም፡፡ የሕይወት መልክ ያለው ዲቴይሉ ውስጥ ነው፡፡

ስታስታውስ. . .

አጥብቀህ አስረኸው የተፈታብህ የጫማ ክር የለም? ፈቅደህ ሳትፈታው፥ እንዴት በራሱ ጊዜ ተፈታ? ቆም ብለህ የአፈታቱን ሒደት ማወቅ አትፈልግም? . . .ሕይወት እኮ ጫማ ክርህ በተፈታበት መንገድ ነው ላንተም የምትሠራው፡፡ ወይስ ዩ ዳዝንት ኬር?


ስንነቃ. . .


ምንጩ ይደርቃል፡፡ ጎርፉም ያልፋል፡፡ ውቅያኖስነቱም አንድ ቀን ይነጥፋል፡፡ አየር ላይ የሚቀረው የተሰበሰበው ትዝታ ብቻ ነው፡፡ ሰው ሲሞት ትዝታው ወዴት ይሄዳል? ቀሪን የሚገርመው እኮ  የተደራረግናቸው ነገሮች እጅግ ስለሚያስደነግጡ ነው፡፡ የሕይወታችንን ጣዕም ለመቀየር የተመኘነው ምኞት አለ፡፡ ከሰውነት ወጥተን አማልክት ለመሆን ተጉዘናል፡፡ ከቤታችን ርቀን የምንሞተው ነገር አለ – ያማል፡፡ በዘመናችን፥ በጊዜያችን የምንረዳው ሰው መሆን እንዳልቻልን ነው፡፡


ማለት ሕይወት እንዴት የሚደብር ነገር ነው?




[Image  : sariphotography]




#Nomadic_Poems
Forwarded from Esubalew Abera N.
Forwarded from Esubalew Abera N.
Forwarded from Esubalew Abera N.
ሁሉ ነገር የሚዳምንበት ጊዜ አለ፡፡ ምናልባትም ያ ጊዜ በፍቅር ያዘን'በት፥ የልብ መሰበራችን ቀን ነው፡፡

ሰማያዊ ነጠላ አዘቅዝቆ የለበሰ ሰማይ፥ እንደ ብራና ይዘረጋል፡፡  መብረቅም እንደ ሰማያዊ መቀስ፥ ሰማዩን እየቀደደ ያልፋል፡፡ የነጎድጓድ ድምጽ፥ ሰማያዊ ቁጣውን  ያሰማል፡፡ ደመናት ሰማያዊ ዝናብ ያረግዛሉ፡፡ ወደ ምድርም ሰማያዊ ማይ እንደ ኢንጆሬ ፍሬ ያንጠባጥባሉ፡፡

ከዝናቡ ለመጠለል የምንዘረጋቸው ዣንጥላዎቻችን፥ ባለ ሰማያዊ ቅጠልማዎች ናቸው፡፡ ዝናቡ ሲያልፍ የምትወጣው ጸሐይ ይዛ የምትገለጠው ሰማያዊ መልኳን ነው፡፡ ዛፎችን ሊያዘምር የሚመጣው ነፋስም  ሰማያዊ ፉጨቱ ይለቀዋል፡፡


መንፈሳችን ለሰማያዊነት ሲጠይም፤ አካላችን እንደሰማያዊ የነዶ ክምር ይሰበሰባል፡፡ ጥላችን ወደ ሰማያዊነት ሲወድቅ፤ የሚወደቅ ጥላችንን እጁን ዘርግቶ የሚቀበለው የመሬት አፈርም ባለ መረሬ ሰማያዊ ነው፡፡

ቀን ያልፋል፡፡ ምሽትም ይመጣል፡፡  ሲመጣ ግን የከዋክብት ዝናብን ይዞ ነው፡፡ ከዋክብት የደጉ ዘመን  ትውስታዎቻችን ናቸው – Memory፡፡ ነገር ግን ሕመም የሚቀሰቅስ ያለፈን ትዝታ ማን ይፈልጋል? የትውስታችን ሰማይ የኮከብ ዝናብ ይጥላል፡፡ ትዝታዎቻችን ተገፍተው  ይረግፋሉ፥ ከሰማይ ይወድቃሉ፡፡ እያንዳንዱ ሰው ማስታወስ ከማይፈልገው ትዝታ በገዛ ዝንጋኤው የተጠለለ ነው፡፡ ባንተያይም፥ ባንነቃቃም – ሁላችንም የዘረጋነው ዣንጥላ አለ፡፡


እነሆ በፍቅር ባዘንን ጊዜ፥ መልካችን ሰማያዊ ነው፡፡ ከሰማያዊነት ርቀን ወደ የት እንሄዳለን?  ከሰማያዊነት ወደ የትስ እንጠለላለን? ከራስ ሐዘንስ ወደ የት ይሸሻል?


[ Image : yehonech lij ]





#Nomadic_Poems
በእሱባለው አበራ ::
Forwarded from Esubalew Abera N.
የ ነ በ ር : ነ በ ር – ታ ሪ ክ፡፡


የእግር መንገድ እያደረግሁ የሚያምር የጸሐይ ግባት ያየሁት በጅማ ሰማይ ላይ ነው፡፡ ለአረጀ አቁማዳ ልቤ. . . በዓይኖቼ የተመለከትኩት ውብ ጀምበር እንደ አዲስ የወይን ጠጅ ያለ ነበር፡፡

ልቤ ተተርክኮ የፈሰሰኝ የወይን ጠጅ እስከ ቅርብ ጊዜ ድረስ በውስጤ ሲንጠባጠብ ቆይቶ ቀስ በቀስ ከልቤ ጋር ጠፍቷል፡፡

" And no man putteth new wine into old bottles; else the new wine will burst the bottles, and be spilled, and the bottles shall perish. " ( Luke 5: 37) Yaa Rabbi !




የ አ ሁ ን : አ ሁ ን – ታ ሪ ክ፡፡


አሁን የምትጠልቅ ጀምበር አልወድም፡፡ እንዲህ የምሽት ብሥራት ሊሆን ሲያፍገመግም ቀና ማለት እፈራለሁ፡፡ ጉንጮቹን በሐምራዊነት ያቀላ ሰማይ ይረብሸኛል፡፡

ከዕለታት አንድ ቀን. . . እኔም ባለ ጀምበር ሰማይ ነበርኩ፡፡ እና ጀምበር ስትሸሸኝ፥ ስትለየኝ የተሰማኝ ጠንካራ የባዶነት ስሜት አለ፡፡ የ'ኔ ጀምበር የምትመለስ አልነበረችም፡፡ እንደሔደች፥ እንደ ጠለቀች የቀረች ናት፡፡



ምዕራቧን የሚያውቅ ማን ነው?




[ Image : Ad Mino ]




#Nomadic_Poems
Forwarded from Esubalew Abera N.
በእሱባለው አበራ የሐሳብ መንገድ ፍሰሱ :: ሐሳቡ ሐሳባችሁ ሊሆን ይችላልና ::
Forwarded from Esubalew Abera N.
በእሱባለው አበራ የሐሳብ መንገድ ፍሰሱ :: ሐሳቡ ሐሳባችሁ ሊሆን ይችላልና ::
Forwarded from Esubalew Abera N.
“ እንዲያ እንዳልተገናኘን፥ እንዲህ እንለያያለን !”



የምድርን ክስተት ማሰብ አለባችሁ – የዓለምንም። አዎ፥ በዓለም ኅልዉ መሆንና በእኔና “እሷ” መጠፋፋት መሐል ማስተማስያ ቀጭን ክር አለች። የምንተርከው ስለዚህች ቀጭንና ደቃቅ ክር ነው። ክሯ?. . .ብትሰልም ክር ናት። የመታናትንና የገረፍናትን ያህል ሲቃ ታወጣለች። እንደ ቅኝታችን የመቃኛ ዙረት ድምጿ ዜማ ያወጣል። ይሕቺ ክር ቀጭን ናት ስትበጠስ አትቀጠልም፥ አትለወጥም። ሲቃ፥ ድምጽ፥ ዜማ አይኖርም – ፍጹም ዝምታ እንጂ።


የምንኖርበት፥ ይሄ ግዙፉና ሰፊው ዓለም በአንዴ ወደ “መሆን” አልመጣም። ዓለም ኅልውናን ለመላበስ፥ ካለመኖር ወደ መኖር ለመከሰት ሲያምጥ፤ በሰው ልጅ ኅሊና ያልተቆጠረለት ሽበታማ ጊዜ አለ። እኔና እሷ ከመገናኘታችንና ከመጠፋፋታችን እውንነት በፊት በቀደሙ የትውልዶች ባላነት ስንሳሳብ ነበር። ለእውንነት ጥረናል፥ በአልቦነት ምኅዳር ውስጥ ለኢምንትነት ተፈላልገናል። ይህ ምድር፥ አፈር - ከተራራው፥ ውቅያኖስ ከእሳቱ፥ ከረቂቁ አየር እስከ ሩቁ ጠፈር፥ ከተሻጋሪው ኅዋ - እስከ ምስለ ከዋክብት፥ ጸሐይ - ከጨረቃው. . . ከይህነት ጀርባ ተተርኮ የማያልቅ ክሽፈት ነበራቸው።


1*“ ከታላቁ ፍንዳታ በፊት ደቃቃ ፍንዳታዎች ነበሩ፤ ምናልባትም የትሪሊዮን፥ ትሪሊዮን የሚደርሱ። ስንቴ ተሳክቶ ደቃቁ ተለቀ? ተልቆ ሊገኝ የነበረው ደቂቁ ውጥንስ ስንቴ ከሸፈ? ዐኹንም ሽል ፍንዳታዎች በቅጽበት፥ በቅጽበት እንደዓለም ለመግዘፍ፥ ልቆ ለመገኘት ሲድኹ ይኖራሉ። ” እኔና እሷ እንግዲህ ይሔ የኅላዌ ናፍቆት እንደ ሱፍ አበባ ፊቱን ወደ ጸሐይ ባዞረበት ዓለም ውስጥ ነው የተገናኘነው። ታዲያ ይሕ ዓለም እንዴት ሊሳካ ቻለ? በዚህኛው ኅላዌ ሕይወት እንዴት ብር - ትር እያለ እስትንፋስን ዘራ? እኔና እሷስ እንዴት ተገናኘን? የከሸፉትን የመገናኘት ጽንሰትና ትልምስ ማን ተግቶ ቆጠረ?


የዓለም፥ የእኔና የእሷም ክስተት እንዲህ ነበር የሆነው:


ብዙ የልብስ መሸጫ መደርደሪያዎች ባሉት መሸጫ ውስጥ እየባዘናችሁ ነው። ርቃንነታችሁን ለመሸፈን ልክነት ያለው አልባስ በመፈለግ ተጠምዳችኋል። ለመልበስ ያላችሁ ናፍቆት፥ እርሱ የትሪሊዮን፥ ትሪሊዮን ፍለጋ ማድረጊያ ጉልበታችሁ ነው። ልብሱን በልካችሁ የሚሰፋው ለኅላዌ ያላችሁ ናፍቆት ነው። የዓለምን መገለጥ፥ የሕይወትንም መንሰራፋት፥ የእኔና የእሷንም መገናኘት የሸመነው ቀጭኑ የናፍቆት ክር ነው። 2* “ ሕይወት በዚያ ልክነት ውስጥ ጠልቃ ነው የተገኘችው። ” እናማ? እንደ ዓለም ኹሉ፥ እኛም የመፈላለግ ርቃናችንን በመሆን ልብስ ሸፍነነው ነበር። ስንገናኝ፥ ባላወቅነው መንገድ ነፍሶቻችን ውስጥ የተጠራቀመ ናፍቆት እንዳለ አይተን ተገረምን። እሷም ያልተዋወቅንባቸውን ጊዜያቶች በመርገም፥ ስላለፈው “ያለመሆን” ጉዞ አምርራ ትራገም ነበር። ድምጿን ስሰማ፥ ቀጭን ክር በኅሊናዬ ይሳላል። ስታወራ በናፍቆትና በመፈላለግ ብቻ የቀረ ያልኖርኩት ትዝታ ይታወሰኛል። መገናኘታችን በማንም እንዳይናቅ ደጋግሜ ማስረዳት ነበረብኝ። ምክንያቱም የተገናኘነው መገናኘት? ከትሪሊዮን፥ ትሪሊዮን እንደ አንድ ነው።


በዚህ ኹሉ መሐል ዓለም ድንገት ሊንሸራተት ይችላል። በአረም እንደሚበላ የውቅያኖስ ውኃ፥ በእሳተ ገሞራ ፍንዳታ እንደሚበታተን ተራራ፥ እንደ ቅሪላ ተወርውራ ከመሬት እንደምትረግፍ ኮከብ ዓለም በሽርፍራፊ ሰከንድ ድንገት በአለመኖር የመዋጥ ዕጣ አላት። ከትሪሊዮን፥ ትሪሊዮን እንደ አንዱ በድንገት በና ትጠፋለች። የእኔና እሷ መለያያት፥ መተጣጣት፥ መጠፋፋት እንደ ለመዳችሁት ተረክ አይደለም። ተለያየን ስል? . . .ዓለም ጠፋ፥ ሰማይ ተናደ፥ ውቅያኖስ ነጠፈ እያልኩ ነው። ለዓለም ምጥና ውልደት የተሰጠው ቀመር፥ ለእኔና እሷም ይመሰላል። ዐኹን ያለችበትን አላውቅም። እርስ በእርስ መኖርን ለምደን በየቅል የመለያየት ጎዳና ወደ አለመኖር ስንራመድ ያቺ ቀጭን ክር እየተበጠሰች ነበር። በሌሊት እየተቀባበልን የተወጣነው ስንኝና ዜማ እየነጠፈ የጸጥታ ባሕር ውስጥ ሰጠመ።


ዓለም እንዴት ይናዳል እኛስ እንዴት ተጠፋፋን?የኅላዌ ልብስ እንደምን ይሳሳል? እንዴት ይቀደዳል?የተዋደደ ሰውስ እንዴት ይለያያል? የተፈላለገ ሰውስ እንዴት ይጠፋፋል? በምሽት ያዜመ ሰውስ እንዴት ሌሊትን ይረግማል?. . . በተጠላለፈ ምኅዋር ውስጥ ጀርባ ተሰጣጥተን፥ ለርቃንነታችን የፍቅር ቅጠል ሰፍተን እንዳላገለደምን፤ በሕይወት እንዳልሆነ፥ በአካል እንዳልተገናኘ ሰው ደብዛችን ሲጠፋ፤ ለአታካቹ ትሪሊዮን፥ ትሪሊዮን የናፍቆት አዙሪት ድጋሜ ስንታጭ፤ እሪሪሪሪ ማለት አያንስም ወይ? በዚህኛው ባይሆን፥ በዚያኛው ፍንዳታ ለመከሰት “ያለንቃት ” እናደባለን። ዓለም እንዲህ ናት። ምንኛ ብትገዝፍም የምትቆመው እና ኅልውናዋን የምታስቀጥለው ግን በአንዲት ቋፍ ነው። ያቺ ቋፍ ከተዛነፈች፥ ዓለም ቋሚው እንደተሰናከለ ድንኳን ትወድቃለች። 3* “ የመሬት ስበት ዐኹን ካለበት በሽርፍራፊ መጠን ቢጠነክር ወይ ቢሳሳ ዓለም ራሷን ለማስቀጠል የሚያስችሏትን ንጥረ አካሎች ታጣለች። ”


እንዲያ እንዳልተገናኘን፥ እንዲህ እንለያያለን። እንዲያ እንዳልተለያየን ደግሞ እንዲህ እንፈላለጋለን። ለብ ባይልም ሥጋ፥ ኅሊና ባያውቅም፤ ያለ ዓለም፥ ያለ አካል፥ ያለ ድምጽ፥ ያለ ስም፤ በዝምታ ብቻ – እንጠራራለን።

°°°°°°°°°°°°°°°°||°°°°°°°°°°°°°°°°°

*1 Edward P. Tryon and Guth.
*2 Martin Rees, Britain’s astronomer royal.
*3 Billy Bryson.






“ እንዲያ እንዳልተገናኘን፥ እንዲህ እንለያያለን !”




[ Image : Tareonthestreet ]




#Nomadic_Poems
የሰንበት አሚናዎች ::

በእሱባለው አበራ ::


አንብቡት ግጥሞቹ ከተመቻችሁ .. የዝርው አጻጻፉ ከተመቻችሁ .. ስልቱ ከወደዳችሁት በዚህ በሐሳቡ ከፈሰሳችሁ የሱ ሁኑ እርሱም የናንተ ነው :: እስከጻፈና እስካነበባችሁ ድረስ ::

የቴሌግራም ቻናሉ ተከተሉት :: አንብቡለት ::
Forwarded from Esubalew Abera N.
“ የሰንበት አሚናዎች ”


ሕይወቴን ብትመለከችው የሚነግርሽ አንዳች እውነት እያለ “ ጨለማ ትፈራለህ ወይ? ” ስትይ ጠይቀሺኛል፡፡


. . .አልፈራም፡፡ የምፈራው እኔን፥ ራሴኑ ነው፡፡ የምተክዘው ጨለማ ቀን መጥቶብኝ አይደለም፡፡ የምሰጋው? በባሕርነቴ ውስጥ የባሕሩን አጽናፈ - ዓለም ላልተረዳች አሳዊ ማንነቴ ነው፡፡


ከዬት እንደተነሳ ባላወቅኩት ነፋስ እናጣለሁ፡፡ በመልኬ ላይም ቁጣዬ ይገለጣል፡፡ የተረጋጋሁ ይመስለኝ ነበር፡፡ ጸጥ ያልኩ፥ የበረድኩ፥ የቀዘቀዝኩ፡፡ ነገር ግን ባሕርነቴ ይጨነቃል፡፡ ባሕሩም እኔ፥ አሳዪቱም እኔ፡፡ ይሄ ኹሉ ቁጣ ለምንና ለማን ነው??


“ ሕልሞችህን ንገረኝ? ” አላልሺኝም፡፡
እውነተኛ ማንነቶቻችን ግን በሕልሞቻችን ውስጥ ተደብቀዋል፡፡


አስቢው እስኪ? . . .በመልክ አና ፍራንክን የምትመስል ሴት፤ ሕልሞቿ ሒትለራዊ መልኮች ቢኖራቸው? የምትዳኘው በመልኳ ነው ወይስ በሕልሟ??


ለምሳሌ. . .


እኔ ተኝቼ የማልመው ስለሰማይ ነው፡፡ ስለሰማያዊ ሰማይ፡፡ ስለዚህ “ እኔ ሰማይ ነኝ ” ማለት እችላለሁ? ወይስ ከሰማያዊነት የተሻገረ ትርጉም ልትሠጪኝ ትችያለሽ??


ይኸውልሽ. . .


ንጋት በጣሪያዬ ቀዳዳ ብርሃን እያዜመ ይገባል፡፡ እኔም ዓይኖቼን፥ ጸጉሬን እያሸኹ ከዕንቅልፌ እነሳለሁ፡፡ የአፌን ዳር ዳርታም በእጄ እሞዥቃለሁ፡፡ ልብሴን ለመቀየር ሳወላልቅ ከገላዬ፥ [ካሻሻሁት ቅንድብ፥ ካፏሸኩት አፌ፥ ካከ'ኩት ጸጉሬ] . . . እየተላቀቀ፥ ወለል ሰፌዴ ላይ የሚወድቅ የኮከብ እንጎቻ አለ፡፡ ታዲያ “ ስለ ሰማይ የሚያልም በሥጋ የተገለጠ ሰማይ ነኝ ” ለማለት የሚያንሰኝ ምንድነው?


አንዳንዴ ደመና ያዘለ ሰማይ በሕልሜ አያለሁ፡፡ በንጋታውም ቀኑን ዝዬ አሳልፋለሁ፡፡ ድሮስ ደመናውን ያዘለው ማን ነው? ሰማይ አይደለምን?? . . .እንደ እኔ በሰማያዊነት ያልተሸከሙት፥ ገና ጠቁሮ ያዩት ሰዎች እንኳን? “ ደመናው ከብዶታል” ብለው ይሮጡ አይደለምን? . . .የደመና ምሕዋር ነኝ፡፡ ያኮፎኮፈው፥ ለመትከፈ ሰብእ የከበደው ደመናም የራሴው መልክ ነው፡፡ አዎን፡፡ ከበደኝ የምለው ደመና የራሴው ቀንበር ነው፡፡ ጭፍጉግነቴን አምናለሁ፡፡ አዎን ያኮረፈ ደመናም ነኝ፡፡


ለዚያም ነው፡፡ “ ከበስተ - ውጪ ያለው ጨለማ፤ እዚህ እ'ልቤ ውስጥ ካንጃበበው ጨለማ እንዴት ሊበልጥ፥ እንዴትስ ሊያሥፈራኝ ይችላል?? ” ስል የምጠይቀው፡፡ እያንዳንዱ ሰው በውስጡ ጠቅጥቆ ስለያዘው የጨለማ መጠን ቢያውቅ ኖሮ፤ በበስተ - ውጪ ባለው የደከመ ጨለማ አይደነግጥም ነበር፡፡


ትላንት ከደመናነቴ ላይ ዝናብ እየተንጠባጠበ ሲወርድ፤ ዘነበ ብለው በአጠገቤ ብዙ ሰዎች ተሯሯጡ፡፡የአንዳንዱን ' የነፍስ አውጪኝ ' አሯሯጥ አይቼ፥ “ እኚህ ሰዎች ከሰማይ እኔነቴ ላይ ድንጋይ ቢዘንብባቸው ኖሮ እንዴት ይሮጡ ይኾን? ” ስል ኩሸት ቢጤ አሰብኩ፡፡ በኩሸቴ በኩል ክፋቴን ማየት ከቻልሽ? እስቲ ንገሪኝ . . .የጨለማ መጠኔ ስንት ነው??


የኩሸቴ ሰለባዎች በዝናቡ ይራወጣሉ፡፡ ዳስ ይፈልጋሉ፡፡ እኔ ግን እንደ አፈሣሰሴ እያዘገምኩ ነበር፡፡ ሰዎች ተጠልለው ያዩኛል፡፡ ወጨፎዉ እየመታቸው በሞጨሞጨ ዓይኖቻቸው ይታዘቡኛል፡፡ ተገላምጬ አልፈረድኩም፡፡ እነዚህ ሰዎች 'ይህ ማይ' ከደመናነቴ ውስጥ ተረግዞ የተወለደ በኩር ውኃዬ መኾኑን አያውቁም፡፡ ቢያውቁማ “ ወትሮስ ከራስ ዝናብ ወዴት ይሸሻል?? ” ብለው ይመልሱ ነበር፡፡


በሬን ከፍቼ ቤቴ ስገባ የሚጠብቀኝ ሰማያዊ ጸሐይ አለ፡፡ በራሴ እጆች ሸራ ላይ የተሳለ የጸሐይ ወገግታ ነው፡፡ ከሰማያዊ ጸሐይ የተወለደ ምጥን ሰማያዊ ብርሐንን ጸንሷል፡፡ ከስዕሉ ላይ እምቦቀቅላ ሰማያዊ የቀለም ብርሃን ገጼ ላይ እግሩን እየዘረጋ መንፈሴን ያርሳል፡፡ የራሴው ጸሐይ ሁለመናዬ ላይ ይወለዳል፡፡ ነገርዬው እንደ ቅዝቃዜ ውልደትም ነው፡፡ ስሜቱ ግን ብርዳዊ አይደለም፡፡ ሰማያዊነት በውስጤ እስከ ተንሠራፋ ድረስ? . . .ቢበርደኝ የምነድ፥ ተቃጥዬ የማቃጥል የእሳት ውስጥ መልክ አይደለሁም ወይ??


ኾኖም የቱንም ልሁን የቱን፤ የቱንም እንሁን የቱን - ሁላችንም እንደ ሞቀ የሚያበቃ ሕይወት አይኖረንም፡፡ ሥጋችንም እንደጋለ አፈር አይለብስም፡፡ ለባዊነቱ በጊዜ ሒደት ይቀዘቅዛል፡፡ በአማልክት እፍታ ተሎኩሶ የጋለው የሕላዌ እስትንፋስም፤ በሞት ርግብግብታ ይጠፋል፡፡ ይከስማል፡፡ ይቀዘቅዛል፡፡ ይወሰዳል፡፡

ከዚህ ሁሉ በኋላም “ አንተ 'ይሄ' አይደለህም ” እንዴት ትይኛለሽ?
ታዲያ ወደ ራስ የሚወስደው መንገድ የቱ ነው ትያለሽ?




[ Image : Internet ]




#Nomadic_Poems
የዛሬዋን እሁድ የወጣት እሱባለው አበራ የስነ-ጽሑፍ ስራዎችን ስናስነብባችሁ ውለናል :: ስላነበባችሁልን ከልብ እናመሰግናለን ::

እሱባለው የግጥምና የአጫጭር ልቦለድ ጽሑፍ ተሰጥኦን ክሂሎት ያለው ነው :: ምናልባትም በዚህ ዓመት መጨረሻ ላይ የግጥም መድብል እና የአጫጭር ልቦለድ ድርሰት ሊያስነብበን እንዲሁም ግጥሞቹን በድምጽ ቀርፆ ሊያስደምጠን ይችላል ::

የእኛ ዋና ዓላማ ወጣት የስነ - ጽሑፍ ሰዎቻችንን ለአንባቢው ማስተዋወቅና የወደፊቶቹን ደራሲ ሀዲስ ዓለማየውን ገጣሚ ገብረክርስቶስ ደስታን ደራሲ አዳም ረታን ካህሊል ጂብራንን ሊሆኑ የሚችሉ የስነ-ጽሑፍ ሰዎችን በቻልነው ያህል በጨረፍታም ቢሆን ለመግለጽ መሞከር ነው ::


የእሱባለው አበራን ጅማሬን ከወደዳችሁለት ሐሳቡ ሐሳባችሁ ከሆነ አጻጻፉ ከማረካችሁ በዚህ የቴሌግራም መስመር ተከተሉት @Nomadicpoems

ለራሱ አስተያየት ለመስጠት ደግሞ በዚህኛው ሊንክ አግኙት :: @Yatseb

በፌስቡክ ደግሞ በዚህ በኩል ተወዳጁት https://www.facebook.com/100011399174147/posts/1102159856840643/?substory_index=0&app=fbl

Esubalew Abera Niegussie


ውብ ምሽት
ውብ አዳር ይሁንልን !!
Forwarded from Jafer Books 📚
የሳምንቱ ተወዳጅ መጻሕፍቶች በምስል ::
የ3ኛው ሆሄ የሥነ ጽሑፍ ሽልማት ::


በረጅም ልብወለድ ዘርፍ የዓመቱ ምርጥ አምስት ዕጩ መጽሐፍት፤

• መልህቅ (ዘነበ ወላ)
• መርበብት (ዓለማየሁ ዋሴ)
• አፍ (አዳም ረታ)
• ኤቶዮጵ (ዶ/ር ኤሊያስ ገብሩ)
• ጃን ተከል (ፍሬ ዘር)