Jafer Books 📚
28.4K subscribers
7.43K photos
123 videos
72 files
1K links
የንባብ ባህል እንዲዳብር እንተጋለን !!
አድራሻችን
ለገሃር ተወልደ ህንጻ
አራት ኪሎ ብርሃና ሰላም ፊት ለፊት
አብርሆት ቤተመጻሕፍት ግቢ ውስጥ
ጥቁር አንበሳ ትምህርት ቤት ፊት ለፊት
ሳሪስ አዲሱ ሰፈር
ጀሞ

ለቴሌግራም https://t.me/Jafbok

ለፌስቡክ https://www.facebook.com/jaferbookshop?mibextid=ZbWKwL

ለዌብሳይት www.jaferbooks.com
Download Telegram
Forwarded from Troubled Thoughts Dept.
እነሆም የመጀመሪያ እርምጃ

እኔ ሕይወትን ብዙ አልችልበትም። እንዳመጣልኝ ነው። እግዚአብሔር ግን እንደ እሱባለው አበራ ያለ ጓደኛ ሰጥቶ ከራሱ ጋር አብሮ የእኔንም አለመቻል ይሸፍንልኛል። ያጎደልኩትን ይኖርልኛል።
ዝርዝሩ ብዙ ነው። ብቻ ግን የመጀመሪያ የልብወለድ መጽሐፌን እኔም እንደ እንግዳ ሆኜ "በየት ገባ?" "በየት ወጣ" ሳልል እጄ ላይ አምጥቶ አስደንግጦኛል። እነሆም የመጀመሪያ መጽሐፌ ዛሬ በገበያ ላይ ውሏል። እንደምትወዱት አስባለሁ። ለደስታዬ ደስ ለሚላችሁ ሁሉ አብዝቼ አመሰግናለሁ።

የመሸበት እንግዳ የምታስተናግዱ ከአሁኑ ሰዓት ጀምሮ መጽሐፉን በጃዕፋር መጻሕፍት መደብር ታገኙታላችሁ ! መልካም ንባብ !
" ሀገር ያጣ ሞት " መጽሐፍ ለንባብ በቃ ::

በሄኖክ በቀለ ለማ የተጻፈው " ሀገር ያጣ ሞት " መጽሐፍ ትናንት ለንባብ በቅቷል :: መጽሐፉ በይዘት በአርትኦት በገጸ - ውበት በዕትመት የተዋጣለት ሆኖ ለንባብ በቅቷል ::

" ይህ ድርሰት የቋንቋ ጥራቱና ቁጥብነቱ (አንድም የባከነ ቃል የለም) ፤ የተረኮቹ እምቅነት፤ ሥነ ጽሑፋዊ ቅርጹና ቴክኒካዊ ልሕቀቱ እጅግ የላቀ የጥበብ ሥራ መሆኑን ያለጥርጥር ይመሰክራሉ ። ደራሲው ከአጠቃላይ የሥራው ውቅር እስከ ጥቃቅን ቴክኒካዊ ጉዳዮች ድረስ ሳይሰስት ያሳየው ትጋትና መሰጠት ለሥነ ጽሑፍ ያለውን ከፍ ያለ ክብር ያሳያል ብዬ አምናለሁ:: በስተመጨረሻም አንድ ገለጻ ተውሼ እደመድማለሁ።

"ይህ የአንድ ወጣት ጀብደኛ የሥነ-ጽሑፍ ዘራፍ ነው! " ።


የመጽሐፉ የሽፋን ሠዓሊ መርሐጽዮን ጌታቸው ::

ሽያጭ ላይ ነን ::

የመጀመርያው ዕትም ጥቂት ነው የታተመው ::

ጃዕፈር መጻሕፍት ::

አድራሻ :- ለገሃር ኖክ ተወልደ ሕንጻ ስር ::
" የልብ ጠጋኙ ማስታወሻ " መጽሐፍ ለንባብ በቃ ::

ኢትዮጵያ ካሏት የልብ ቀዶ ጥገና ሀኪሞች አንዱ የሆነው ዶ/ር ፈቀደ አግዋር ባለፉት 4 ዓመታት ብቻ ከ300 በላይ ልቦችን ቀዶ ጠግኗል ። ከእነዚያ መሀል አብዛኞቹ በሀገራችን የልብ ቀዶ ጥገና ታሪክ የመጀመሪያ የሆኑ የ17 አስገራሚ ቀዶ ጥገናዎችን ልብ መሳጭ በሆነ ቋንቋ ከሽኖ አቅርቦላችኋል ። ከ90 ዓመቱ የሮይተርስ ጋዜጠኛ የወራት እድሜ እስካላቸው ጨቅላ ህጻናት ልባቸውን ከፍቶ አክሟል ። ይህን አነጋጋሪ መጽሐፍ ወደ መደብራችን ጎራ ብለው ያግኙ ።

ጃዕፋር መጻሕፍት ::
" ኢትዮጵያ ካሏት የልብ ቀዶ ጥገና ሀኪሞች አንዱ የሆነው ዶ/ር ፈቀደ አግዋር ባለፉት 4 ዓመታት ብቻ ከ300 በላይ ልቦችን ቀዶ ጠግኗል ። ከእነዚያ መሀል አብዛኞቹ በሀገራችን የልብ ቀዶ ጥገና ታሪክ የመጀመሪያ የሆኑ የ17 አስገራሚ ቀዶ ጥገናዎችን ልብ መሳጭ በሆነ ቋንቋ ከሽኖ አቅርቦላችኋል ። ከ90 ዓመቱ የሮይተርስ ጋዜጠኛ የወራት እድሜ እስካላቸው ጨቅላ ህጻናት ልባቸውን ከፍቶ አክሟል ።
ይህ መጽሐፍ የተዋቀረው በአስራሰባት ታሪኮች ቢሆንም፤ የመጨረሻዎቹ ሶስት ታሪኮች ግን የአንድ አላማ መዳረሻ ቅርንጫፎች ናቸው። ታዲያ እነዚህ ታሪኮች ምንም እንኳን በልብወለድ መልክ ቢቀርቡም እውነት ከመሆንም ባሻገር በሀገራችን ልጆች እውቀት የልብ ቀዶ ጥገና እንዴት እንደተደፈረ፤ በመቀጠልም ትልልቅ የሚባሉ የልብ ቀዶ ጥገናዎች እንዴት እንደተጀመሩ በትረካ መልክ ያቀርባል። በመጽሐፉ ፍጻሜ ላይ እነዚህ ታካሚዎች ያንን አስቸጋሪ ጊዜ አልፈው፤ ዛሬ ላይ ይህንን መጽሐፍ ባነበቡ ወቅት የተሰማቸውን ስሜት አስፍረነዋል። አሁን ያለውም ሆነ መጪው ትውልድ የልብ ቀዶ ጥገና ከውጪ ዜጎች ግዛትነት እንዴት ወደ ሀገር በቀል እውቀት እንደተሸጋገረ ቁልጭ አድርጎ ያመላክታል ብየ አምናለሁ። ከሁሉም ባሻገር በዚህ መጽሐፍ ውስጥ የሚንጸባረቁ ብዙ ስብዕናዎች ትውልድን ያነቃቃሉ፤ ያነጋግራሉ ብየ አምናለሁ። "
ፈቃደ አግዋር (የልብ ቀዶ ጠጋኝ)
ሶስቱም ከባድ + ወሳኝ + ብርቱ ቲም ናቸው !!
ሲተባበሩ ደግሞ ዘመን የሚሻገር ታሪክ እየሰሩ ነው !!

ሔኖክ በቀለ ( ' ሀገር ያጣ ሞት ' መጽሐፍ ደራሲ )

እሱባለው አበራ ንጉሴ ( የ' ትዝታሽን ለኔ ትዝታዬን ላንቺ ' መጽሐፍ ደራሲ )

መርሐጽዮን ጌታቸው ( ' ሀገር ያጣ ሞት ' ን መጽሐፍ ጨምሮ የብዙ ምርጥ መጽሐፍ የሽፋን ምስል ከያኒ )

እንኳን ደስ ያላችሁ !!
Forwarded from Troubled Thoughts Dept.
❝የሀገር እናቶች ትላንትን የሙጥኝ እንዳሉ ያዘግማሉ። ክሳዱን ጨምድደው ሊጥ በሚጠልቁበት ቅል አናት አናቱን ይቀውሩታል — “ጊዜ የሰጠው ቅል እንኳን ትላንትን ድንጋይ ይሰብራል”። ሮጠው ያልጠገቡ ልጆቻቸው መልኩን አይተውት ለማያውቁት ንጉሥ፤ ጎባጣ ይሁን ለግላጋ... ግራጫ ይሁን ቢጫ ለማይለዩት ርዕዮተ—ዓለም ሲሞቱ አይተዋል። ማኀፀናቸው ውስጥ ሲገላበጥ የረገጣቸው እግር ተቆርጦ ሲመለስ፤ በውስጣቸው የተላወሰ ገላ በሦስት ክንድ መሬት ውስጥ ሲረጋ አልቅሰው ሸኝተዋል። በሆዳቸው ውስጥ ተቀምጦ የተዋደደ አጥንት ሲከሰከስ፤ በሰውነታቸው ውስጥ የተቋለፈ ጅማትና ደምሥር በአንዲት አረር ዓይናቸው ሥር ታሪክ ሲሆን፤ ከዚያችም አረር ጀርባ ታጣፊ ክላሺንኮቭ፤ ከእርሱ ጀርባ ቃታውን የሳበች ጣት፤ ከእርሷ ጀርባ ሌላኛው ልጃቸው መኖሩን ተመልክተዋል። ለሞተው ልጃቸው ባማረሩበት አፍ፤ ገዳይ ሆኖ ለተረፈ ልጃቸው “ተመስገን” ይሉበታል።
-
|ከመጽሐፉ የተወሰደ - ሀገር ያጣ ሞት
ሄኖክ በቀለ|
.
.
አከፋፋይ — ጃዕፈር መጻሕፍት።
አድራሻ :- ለገሃር ኖክ ተወልደ ሕንጻ ሥር።
.
የእርስዎን ቅጂ ፎቶ በማንሣት፣ እንዲሁም መጽሐፉን አንብበው የተሰማዎትን ያጋሩን!!
Forwarded from Esubalew Abera N. (: |)
Book Title : ሀገር ያጣ ሞት
Author : HEnock Bekele Lemma
Genre : Fiction
Page : 208
Page Layout : Reminiscent
Book Cover Design : Merhatsion Getachew
Price : 200 Birr
Publisher : Jafer Shifa Book
Printing : Gola Publishing Service
Published : 27/12/2013

Photography : Gebrela Shewakena
በ 80 ብር ብቻ ::

ጥቂት ቅጂዎች ብቻ ነው ያሉን !!

337 ገጽ ጥቂት ጥራት ያለው ዕትመት በጥልቅ ምርምርና ጥናት የተዘጋጀ ታዕማኒነቱን በአጭር ጊዜ ያተረፈ መጽሐፍ ::

በሸገር FM የእሁድ " የሸገር ካፌ " ላይ በ17 ተከታታይ ሳምንታት ከመዓዛ ጋር ቆይታ እያደረጉ ያሉት ዶክተር በለጠ በላቸው ሁለት መጽሐፍ አላቸው ::

አንደኛው ከስድስት ዓመታት በፊት ለዕትመት የበቃው ግን በበቂ ሁኔታ ያልተነበበው ሰሞኑን እጅግ ተፈላጊ የሆነው " ጅቡቲ የጥገኝነታችን መስፈሪያ " የተሰኘው መጽሐፍ ነው ::

ሁለተኛው ደግሞ ለንባብ ከበቃ ሳምንታት የተቆጠሩት " የኢትዮጵያ ዳር ድንበር ያልተቋጨ የቤት ስራ " የተሰኘው እጅግ ወቅታዊና ባጭር ጊዜ ታማኒነትን ያተረፈ መጽሐፍ ነው ::

ሁለቱንም መጽሐፍ በ 130 ብር መሸመት ይችላሉ :: ( መቼም ቀጣይ ዕትሞቹ በዚህ ዋጋ እንደማይገኙ ይረዱናል :: )

ጃዕፈር መጻሕፍት ::

አድራሻ :- ለገሃር ኖክ ተወልደ ሕንጻ ስር ::
Forwarded from Esubalew Abera N. (: |)
“ ° ° ° ለእዚህች ሕይወቴ አምርሬ ለምጠላት፤ ቂም ለምታበቅል ፍቅር ፊት ብተክላት፤ ለዚህች ሕይወቴ ለማትረባው፤ ለእዚህ ወጣትነት ልጅነት ላልገባው፤ እናቴን ስላሳመምኳት፣ ስለበደልኳት በምጧ፤ ስላስቆምኳት በ‘ወይኔ’ታ፤ ስላስኬድኳት በቅምጧ ‘ይቅር’ በለኝ።”

፠ ፠ ፠

ለእዚህች ሕይወቴ ለምታፈቅረው ጨለማ፤ “ሀ…… ሁ” “ለ……ሉ”ውን ለማትሰማ፤ ኑሮውን፣ ቄንጡን፣ ጉልምስናውን ስለወሰድኩበት፤ ለደኅና ያሰበው ልክፍቱን ስላባከንኩበት፤ ‘ልጄ ከእኔ ይሻላል’ ያለው አባቴን ስላሳፈርኩት፤ ‘ማንም ከዘሬ እንዳይነካው’ ያለውን ድህነት ስለደፈርኩት ‘ይቅር’ በለኝ። በል መጣሁ እጅህን ዘርግተህ ተቀበለኝ! • • • ”

ከሞት በፊት በተስፋ የተጸለየ ጸሎት | (ከ) ሀገር ያጣ ሞት | HEnock Bekele | ገጽ 167 | Photography Gebrela Shewakena
' ሀገር ያጣ ሞት '

በ ሄኖክ በቀለ ለማ

የገጽ ብዛት - 208

". . . ሮጠው ያልጠገቡ ልጆቻቸው መልኩን አይተውት ለማያውቁት ንጉሥ ጎባጣ ይሁን ለግላጋ . . . ግራጫ ይሁን ቢጫ ለማይለዩት ርዕዮተ-ዓለም ሲሞቱ አይተዋል፡፡ ማህጸናቸው ውስጥ ሲገላበጥ የረገጣቸው እግር ተቆርጦ ሲመለስ በውስጣቸው የተላወሰ ገላ በሶስት ክንድ መሬት ውስጥ ሲረጋ አልቅሰው ሸኝተዋል። በሆዳቸው ውስጥ ተቀምጦ የተዋደደ አጥንት ሲከሰከስ በሰውነታቸው ውስጥ የተቋለፈ ጅማትና ደምስር በአንዲት አረር አይናቸው ስር ታሪክ ሲሆን ከዚያችም አረር ጀርባ ታጣፊ ክላሽንኮቭ ፥ ከእርሱ ጀርባ ቃታውን የሳበችው ጣት ከእርሷ ጀርባ ሌላኛው ልጃቸው መኖሩን ተመልክተዋል ። ለሞተው ልጃቸው ባማረሩበት አፍ ጋዳይ ሆኖ ለተረፈ ልጃቸው 'ተመስገን ' ይሉበታል "

ከመጽሐፉ የተወሰደ
ጋዜጠኛ እና ደራሲ ጳውሎስ ኞኞ በስተግራ - ጋዜጠኛ እና ደራሲ መዝገቡ አባተ በስተቀኝ
" ሀገር ያጣ ሞት "