ኢንፋቅ የልማትና መረዳጃ ማህበር /ደሴ/
1.39K subscribers
2.16K photos
6 videos
172 links
ይህ የኢንፋቅ ልማትና መረዳጃ ማህበር Official የቴሌግራም ቻናል ነዉ።
.
የእርሶ ትንሽ እጅ ለሌሎች ምርኩዝ ናት!
.
Download Telegram
ዚያራው ላይ ለተገኛችሁ እንዲሁም ለተባበራችሁን አካላት በሙሉ ከልብ እናመስግናለን 🤍

አላህ ይቀበለን
💚
👏7❤3👍2🔥1🥰1🎉1
Audio
.............ቢላል (ረዲየላሁ አንሁ)

መገን ይሄ ቢላል ዚያራ መቶበት፣
በመናብ ከአይኑ ላይ ጥሪ ተወስቶበት፣
በእንባ እየዳከረ በናፍቆት አለንጋ፣
ሻምን ለቆ ሄደ ማልዶ ሌት ሲነጋ።

ለትዝታ ቢርቅ ሸሽቶ ወዲያ ማዶ፣
ግና ግን ተጠራ ውዴታ ስር ሰዶ፣
ታዲያ ያያት ለታ ውቢቱን መዲና፣
አዝና ነው ያገኛት ለብቻ መንና።

እንዴቱን አታዝን እንዴት ትሁን ደህና፣
ትተዋት ኮብልለው የውበቶ ፋና፣
ታዲያ ቢላል ሲታይ መቶ ሙነወራ፣
ጥያቄ መጣበት በል በአዛን ተጠራ።

እንቢ ማለት ቢከብድ ሊሞክር ተነሳ፣
ግን ሙሀመድ ብሎ እንዴት ይጨርሳ፣
አቆርጦት ወደቀ እንባ ሆኖ ፊቱ፣
መዲናም የዛን ለት አዘነች በብርቱ።

አሪህና የሚሉት ነቢይ የሉምና፣
ቢላል ሀዘን ወርሶት ሚም በእሱ ላይ ጠና፣
መርሀባ ቢል እንኳን የልጅ ልጅን አይቶ፣
ግና ተረታ አሉ የወዳጅ ፊት አቶ።

የውዴታ ነገር እንዴቱን ይቻላል፣
ለአንዳንዱ እየጠና
ለአንዳንዱ ይቀላል፣
አንዳንዱን ሲያሳዝን
አንዳንዱን ሲያባባ፣
ሺ አራት አልፎ መቶም ፍቅርሁ መድ አስነባ።

اللهم صل وسلم على سيدنا محمد

ገጣሚ-ፈትሁዲን ዑመር
2019 እ.ኢ.
አ

#ኢንፋቅ_ሚዲያ
#ለኸሚሳችን
❤6🔥3
Audio
📿 ዘይሩት 📿

አንቱን የወደደ ከጌታው ቀጥሎ፣
ኢማኑ ተሟላ መች አለው ጎደሎ፣
ስምሁ መዘከሩ በፋርቃኑ አልቀረ፣
ኡመትሁ ቸገረው ቃላት እያጠረ።

ሙሳም ተመኙ አሉ ህዝብ መሆን ያንቱ፣
ወስፍሁ ቢገባቸው ደረጃሁ ጥናቱ፣
እኔማ እድልተኛው ኡመትሁ ነኝና፣
ፈገግ ስል ልኑር ምን ናፍቆት ቢጠና።

አደራ እንዳትቀሩ ሸለብ ሲል አይኔ፣
በመናቤ ኑ እና አበሽሩኝ ዘይኔ፣
ሳያይሁ እንዳይለብስ ከፈን ይሄ ገላ፣
ዝለቁ ዘይሩት ወዳጅ አይጉላላ።

እጠብቅሆለሁ መለይካ እስኪመጣ፣
ጀሰድ በደን አርጎ እሩህ የሚያወጣ፣
እንዳትቀሩ ዘይኔ ዝለቁ እንዳትቀሩ፣
አንቱን ካዬሁ ወዲያ ይቆፈር ቀብሩ።

اللهم صل وسلم على سيدنا محمد

ግጥም ▻ ፈትሁዲን ዑመር
2019 እ.ኢ.አ
❤5