ኢንፋቅ የልማትና መረዳጃ ማህበር /ደሴ/
1.39K subscribers
2.16K photos
6 videos
172 links
ይህ የኢንፋቅ ልማትና መረዳጃ ማህበር Official የቴሌግራም ቻናል ነዉ።
.
የእርሶ ትንሽ እጅ ለሌሎች ምርኩዝ ናት!
.
Download Telegram
Audio
አፍሬ ነው

አፍሬ ነው ሆዴ
አንቱ የኔ መውደድ፣
ስራዬ ከስራሁ
እርቆ ቢንጋደድ፤

አስቀረኝ መሰለኝ
የራሴው ስንክሳር፣
ላፍታ መጣ ብዬ
ወዳአንቱ እንዳልሀድር።

አፍሬ ነው
አፍሬ ነው ቀና ማልል፣
አቀርቅሬ የቀረሁት ብጎዳድል፣
ብሞላማ የአንቱን ሱና ብራመደው፣
ባልተከዘ ሰውነቴም ባላፈረው።

አንተ ሀጁ ተሳፋሪው ተመዲና፣
የሰራሁት ያረከሰኝ
ያመፅኩበት ያሳነሰኝ
ያደፍኩበት ዝቅ ያረገኝ
እስኪሸሸኝ፤
ይህ አንገቴ እስኪቃና እስኪያነሳኝ፣
ለወዳጄ ሰላምታዬን አድርስልኝ።

اَللّٰهُــمَّ صَــلِّ عَلَـــى سَيِّــدِنَا مُحَــمَّــدْ

ተፃፈ-በፈትሁዲን ዑመር
1447 ዐ.ሂ

.
#ኢንፋቅ_ሚዲያ
#ኢንፋቅ
❤5🔥1
♦️የአዲስ አባላት ትውውቅ ፕሮግራም♦️

💭 ለኢንፋቅ ለመስራት በቅርቡ የተመዘጋችሁ አዳዲስ አባላት በሙሉ የፊታችን #እሁድ ነሀሴ 24 የትውውቅ ፕሮግራም ስለሚኖረን ሁላችሁም እንድትገኙ ለማለት እንወዳለን❗

🗓 እሁድ ነሀሴ 24
🕑 ከጠዋቱ 2:30 ጀምሮ
📍 ፒያሳ ሰይድ ያሲን ህንፃ 5ተኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 516


#መልካም_ጁምዓ
#ኢንፈቅ_ሚዲያ
#ኢንፋቅ
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
❤4🎉3👍1🔥1🥰1👏1🤔1🤩1
ወዳጄዋ ምኞቴ ነው የጧት ማታ፣
መጎራበት ከአንቱ ቅጥር በዚያ ቦታ፣
የሞትኩ እለት ሲዘጋጋ ሙላው ሁላ፣
ወዳጅ ሁኑኝ አማላጄ ለእኔው መላ።

ገጣሚ▻ ፈትሁዲን_ዑመር

#የኸሚስ_ብዕሮች
#ኢንፋቅ_ሚዲያ
#ኢንፋቅ
❤7🔥2🥰1
Audio
......የሄዱ እለት

መዲናይቱ በቀን ፀሀይ ስትጨልም፣
ሀዘን ወርሷት ዞላም ከቧት ስትል እልም፣
ሶሀበቶች ክው ሲሉ ውስጥ ነዶ፣
ሰይፍ ሳቡ ያ ኡመር ማመን ገዶ።

የሄዱ እለት የመዲናው የኑር አምባ፣
ሞላት ሀዘን ሂጃዚቱን እያደባ፣
ቀምቶ አዛን ቅላፄውን ውቡን ቃና፣
አባረረው ያንን ቢላል ከመዲና።

በአንቱ መምጣት
የተዋበው ያ ጎዳና፣
የሄዱ እለት
ሀዘን ቃኘው እንደገና፣

የአንቱ መምጣት
ከፍ ያረጋት መዲናይቱ፣
የሄዱ እለት
ከብዷት ታዬ መፅናናቱ።

ወዳጄዋ ምኞቴ ነው የጧት ማታ፣
መጎራበት ከአንቱ ቅጥር በዚያ ቦታ፣
የሞትኩ እለት ሲዘጋጋ ሙላው ሁላ፣
ወዳጅ ሁኑኝ አማላጄ ለእኔው መላ።

اَللّٰهُــمَّ صَــلِّ عَلَـــى سَيِّــدِنَا مُحَــمَّــدْ

ገጣሚ ▻ ፈትሁዲን_ዑመር
1448 ዐ.ሂ
❤3
Audio
--------ውበትሁ

ከጨረቃ ጋራ
ያውም ደምቃ ሞልታ
ብቻዋንም ሆና
ከኮኮብም ሀታ
በሚያምር መካበብ
ብትታይም ጎልታ
ግን ማነሷ ታይቶል
ከጅሁ ላይ ተረታ።

ታዲያ ምን ተገኘ ሁሉ አንሶ ማነሱ፣
ዝም ይሻላል እንጂ ከልኬት ሳይደርሱ፣
እንደ አሚናቱ ልጅ ከቶ ማን ያምርና፣
ስንቱን ብዕረኛ ዘመን ደጅ አስጠና።

አምሳያሁ ታጣ
ወዳጄ የአንቱ፣
ውበት በሞላ
ተሰቶ ለአንቱ፣
ቀለም ቢቀዘፍ
ባህሩን መስሎ፣
መሬት ቢነጠፍ
ሉህን አክሎ፣
እንጃ መግለፁን ውበትሁን ኩሎ።

እንዴት ነሁ ያለሁት መዲና ቀበሌ፣
ናፍቆት አወጋለሁ ብቻ ተነጥሌ፣
ብዕር መጨበጤን አልተውም ለአፍታ፣
ሰርክ እኳትናለሁ እስከለህዴ ቦታ።

اللهم صل وسلم على سيدنا محمد

ገጣሚ- ፈትሁዲን_ዑመር
1448ዐ.ሂ
.
#ኢንፋቅ_ሚዲያ
#ኢንፋቅ
❤5
🍒 ኢንፋቅ ዚያራ 🍒

አሰላሙ አለይኩም ውድ የኢንፋቅ ቤተሰቦች ኢንፋቅ የልማትና መረዳጃ ማህበር የ2019 አ.ል የመጀመሪያ ስራውን በገራዶ መጠለያ ካምፕ የሚገኙ ተፈናቃይ ወገኖችን ከ አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ሙስሊም ተማሪዎች ጀመዓ ጋር በመተባበር የልብስ እና የማቴሪያል ድጋፍ ለማድረግ አስቧል ስለሆነም ነገ ከቀኑ 7:30 ጀምሮ ኢንፋቅ ቢሮ እንድትገኙና ዚያራውን አብረን እንድናደርግ ስንል ጥሪያችንን እናቀርባለን❗️

ኢንፋቅ ዚያራ
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
👍5
🍒 ኢንፋቅ ዚያራ 🍒

አሰላሙ አለይኩም ውድ የኢንፋቅ ቤተሰቦች ኢንፋቅ የልማትና መረዳጃ ማህበር የ2019 አ.ል የመጀመሪያ ስራውን በገራዶ መጠለያ ካምፕ የሚገኙ ተፈናቃይ ወገኖችን ከ አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ሙስሊም ተማሪዎች ጀመዓ ጋር በመተባበር የልብስ እና የማቴሪያል ድጋፍ አደረገ ለተሳተፋችሁ በሙሉ ከልብ እናመሰግናለን❗️

ኢንፋቅ ዚያራ
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
❤10