የዒልም ቁንጮው አላህን መፍራት ነው!
~
"መዕሩፍ አልከርኺይ እውቀት ነበረው ግን?" ብዬ አባቴን ጠየቅኳቸው አሉ፣ 0ብዱላህ ብኑ አሕመድ ብኒ ሐንበል። በዚህን ጊዜ የኢማሙ አሕመድ ምላሽ እንዲህ የሚል ነበር፦
"يا بني كان معه رأس العلم: خشية اللَّه تعالى!"
"ልጄ ሆይ! ከሱ ጋር የዒልም ቁንጮው ነበር፣ የላቀውን አላህን መፍራት!" [ጦበቃቱል ሐናቢላህ፡ 1/382]
ዓሊም ማለት አላህን የሚፈራ ነው። የላቀው አላህ እንዲህ ይላል:-
{ إِنَّمَا یَخۡشَى ٱللَّهَ مِنۡ عِبَادِهِ ٱلۡعُلَمَـٰۤؤُا۟ۗ }
"አላህን ከባሮቹ ውስጥ የሚፈሩት ዐዋቂዎቹ ብቻ ናቸው።" [ፋጢር፡ 28]
ስለዚህ ተነስቶ ህዝብ መስበክ ባይችል፣ የመረጃ ክምችቱ የቀለለ ቢሆን እንኳ አላህን የሚፈራ ሁሉ ዓሊም ነው። በሌላ በኩል ደግሞ ማወቁ አላህን መፍራትን ያላወረሰው ሰው ጃሂል ነው። የተማረው ዒልም የሰው ሐቅ ከመብላት፣ ከመዋሸት፣ ከማታለል፣ ሰዎችን ከመበደል ያልገታው ሰው በኢማን መነፅር ጃሂል ነው። ረቢዕ ብኑ አነስ ረሒመሁላህ "አላህን የማይፈራ ሁሉ ዓሊም አይደለም" ይላሉ። ሙጃሂድም እንዲሁ "አዋቂ ማለት አላህን የፈራ ነው" ይላሉ። ሰዕድ ብኑ ኢብራሂም "ከመዲና ነዋሪዎች ሁሉ ይበልጥ አዋቂው ማነው?" ተብለው ተጠየቁ። "ይበልጥ ጌታውን የሚፈራው ነው" ብለው መለሱ። [ተፍሲሩል ቁርጡቢ]
=
የቴሌግራም ቻናል:-
https://t.me/IbnuMunewor

Telegram
Ibnu Munewor (ኢብኑ ሙነወር)
كناشة ابن منور
Forwarded from Abu_Oubeida~channel
መልከም ዜና ለእውቀት ፈላጊዎች፦
በሸይኻችን ሸይኽ አወል ቢን አሕመድ ሲሰጥ የነበረው የ"ሱነኑ አት'ቲርሚዚይ"ኪታብ በመጠናቀቁ በቦታ የ"ሱነኑ ነሳኢ"ኪታብ ነገ ከፈጅር በኋላ ስለሚጀመር መከታተል የምትፈልጉ ካላችሁ በጊዜ እንድትገኙ አስታወስናችሁ።
የስርጭት ሊንክ፦
t.me/SheihkAbuAmarAwolIbnuAhmed

ማስታወሻ የምይዝበት የቴሌግራም ቻናሌ ላይ አገኘሁት። ከተወሰኑ ዓመታት በፊት ውስጤ የነበረን ስሜት የገለፅኩበት ነው። ህመሜን ስሜቴን ለመግለፅ ብሞክረም አውጥቶ መለጠፉ ለአንዳንዶች እኔ ያላሰብኩት አንድምታ ቢኖረውስ ብዬ ተውኩት። በርግጥ የጭንቀቴ ምክንያት የግል ጉዳይ አልነበረም። ግን እንቅልፍ የሚነሳ ትልቅ ሃሳብ ነበር። ዛሬ ላይ ጉዳዩ ያኔ በነበረው መጠን ባለመሆኑ አልሐምዱ ሊላህ እላለሁ። አላህ የተሻለውን ያምጣልን።
=
የቴሌግራም ቻናል፦
t.me/IbnuMunewor
=
የቴሌግራም ቻናል፦
t.me/IbnuMunewor
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
رحم الله الشيخ عبد العزيز آل الشيخ
ሳይታወቀን የሸር መክፈቻ እንዳንሆን
~
የሆነ ጊዜ አንድ ጎረቤት ከሌላ ጎረቤቱ ቤት እየተጫወተ ይቆያል። ምግብ ቀረበ። ጎረቤት ከምግቡ ጋር የተያያዘ የቀልድ አስተያየት ጣል አደረገ፣ እንዲሁ እየሳቀ ነበር። አንዳንድ እየተባለ በባልና ሚስት መሃል ያልታሰበ ከባድ ጥል ተከሰተ። ሲመስለኝ የቀደመ ክፍተት ኖሮ ጎረቤት ሳያስበው ሰበብ ሆኗል። የልጅነት ትዝታ ስለሆነ ዝርዝሩ ትዝ አይለኝም። ትዝ ቢለኝም የሚጠቅም አይደለም። ቀጥዬ ለማነሳው ነጥብ ማሳያ ምሳሌ እንዲሆነኝ ነው ያነሳሁት።
ሚስትን ከባል፣ ልጅን ከወላጅ፣ ሰራተኛን ከአሰሪ፣ ጓደኛን ከጓደኛ፣ ሸይኽን ከሸይኽ፣ ማጋጨትና ማለያየት የከፋ ሸር እንደሆነ ለማንም ግልፅ ነው። ነገር ግን አንዳንዴ እንዲህ አይነት ጥፋቶችን ክፋትን ሳናስብ ልንፈፅመማቸው እንደምንችል እንዘነጋለን።
* ታመህ ሊጠይቅህ የመጣ ሰው ምንም ክፋትን ሳያስብበት እንደዋዛ "እንትና ይጠይቅሃል?" ብሎ የጣለው ቃል ውስጥህን ሊያደፈርሰው ይችላል።
* "ባልሽ ለጥሎሽ ያደረገው ይሄው ነው? የወለድሽ ጊዜስ? የኔኮ እንዲህ እንዲህ አድርጎልኛል?" የሚል ቃል ምናልባት ሚስትን በባሏ ላይ ቅሬታ ውስጥ ሊከት፣ እሱንም "አቅሜን እያወቀች ለምን ታጨናንቀኛለች? እንዴት አትረዳኝም?" እያለ ነገር ተጓጉኖ ያልተጠበቀ ውጤት ሊያስከትል ይችላል።
* "ጓደኛህ እገሌ ግን ምን ሆኖ ነው ሰርግህ ላይ ያልተገኘው?"፣ "ሰራተኛሽ ምግብ ከናንተው ጋር ነው የምትቀርበው? ይሄማ ማቅበጥ ነው!"፣ "ልጅህ ምን ሆኖ ነው ለዒድ መጥቶ ያልዘየረህ?"፣ ... የመሳሰሉ ጥያቄዎች እና ሀሳቦች እንደዋዛ ጥለናቸው አልፈን ውጤታቸው የከፋ ሊሆን ይችላል።
እና ባላሰብነው አቅጣጫ ሰዎችን ማቀያየም፣ ትዳርን ማደፍረስ፣ አሰሪና ሰራተኛን ማለያየት፣ ጓደኛና ጓደኛን ማራራቅ ውስጥ እንዳንገባ እላፊ ቃላትን ከመሰንዘር መጠንቀቅ አይከፋም። የአላህ መልእክተኛ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም እንዲህ ይላሉ፦
"إِنَّ مِنَ النَّاسِ مَفَاتِيحَ لِلْخَيْرِ مَغَالِيقَ لِلشَّرِّ، وَإِنَّ مِنَ النَّاسِ مَفَاتِيحَ لِلشَّرِّ مَغَالِيقَ لِلْخَيْرِ، فَطُوبَى لِمَنْ جَعَلَ اللَّهُ مَفَاتِيحَ الْخَيْرِ عَلَى يَدَيْهِ، وَوَيْلٌ لِمَنْ جَعَلَ اللَّهُ مَفَاتِيحَ الشَّرِّ عَلَى يَدَيْهِ"
"ከሰዎች ውስጥ የኸይር መክፈቻዎች እና የሸር መዝጊያዎች የሆኑ አሉ። ሌሎች ደግሞ የሸር መክፈቻዎች እና የኸይር መዝጊያዎች የሆኑ አሉ። አላህ የኸይር መክፈቻዎችን እጁ ላይ ያደረገለት ሰው ምንኛ የታደለ ነው!! አላህ የሸር መክፈቻዎችን እጁ ላይ ያደረገበት ሰው ወዮለት!!" [አስሶሒሐህ፣ አልባኒይ፡ 1332]

የማለዳ መልእክት
~
የነብዩ ﷺ ባለቤት ጁወይሪያ የፈጅርን ሶላት ከሰገደች በኋላ ዚክር ማድረግ ያዘች። ነብያችን ﷺ ውጭ ቆይተው ረፋድ ላይ ሲመለሱ አሁንም በዚያው ሁኔታዋ ላይ ናት። "ስልለይሽ በነበርሽበት ሁኔታ ላይ ነው እስካሁን የቆየሽው?" ሲሉ ጠየቋት። "አዎ" አለቻቸው። "እኔ ካንቺ በኋላ አራት ንግግሮችን ሶስት ጊዜ ደጋግሜ ብያለሁ። ቢመዘኑ አንቺ እስካሁን ከቆየሽበት ይከብዳሉ" አሉ። ከዚያም አራቱ ንግግሮችን አያይዘው ተናገሩ።
سُبْحَانَ اللَّهِ وَبِحَمْدِهِ ، عَدَدَ خَلْقِهِ ، وَرِضَا نَفْسِهِ ، وَزِنَةَ عَرْشِهِ ، وَمِدَادَ كَلِمَاتِهِ
"ሱብሐነ'ላሂ ወቢሐምዲሂ ዐደደ ኸልቂሂ፣ ወሪዷ ነፍሲሂ፣ ወዚነተ ዐርሺሂ፣ ወሚዳደ ከሊማቲሂ።"
[ሶሒሕ ሙስሊም፡ 2726]

ይሄ የሰሞኑ ቻሌንጅ ቢቀር ነው የሚሻለው። ከዚህ በላይ መነጋገሪያ ሳይሆን ብታቀዘቅዙት ጥሩ ነው ወንድሞች። ዝርዝር መግባት ሳያስፈልገን ምን ሊያስከትል ይችላል የሚለውን በማሰብ ብንግባባ ጥሩ ይመስለኛል። الحر تكفيه الإشارة
=
የቴሌግራም ቻናል፦
t.me/IbnuMunewor
t.me/IbnuMunewor
=
የቴሌግራም ቻናል፦
t.me/IbnuMunewor
t.me/IbnuMunewor
Telegram
Ibnu Munewor (ኢብኑ ሙነወር)
كناشة ابن منور
"ጨው ውሃ ሊቀዳ ወርዶ ቀልጦ ቀረ"
~
የሰው ልጅ ባህሪ እንደ መልኩ ብዙ ነው። አንድ ሰው ራሱ ከተለያዩ ጉዳዮች አንፃር ቢታይ የተለያየ አመል ሊኖረው ይችላል። ለሆነ ነገር ያመንነው አካል በሌላ ጉዳይ ያልጠበቅነው ቦታ ልናገኘው እንችላለን። በገንዘብ የሚታመን ሆኖ በፆታዊ ጉዳይ ግን ፍፁም አስደንጋጭ አመል ሊኖረው ይችላል። በዚህ በኩል የማይታማ ገንዘብ ላይ ግን ለህመምተኛ መታከሚያ የተሰበሰበን የማይምር፣ ከደካማ ጉሮሮ የሚነጥቅ ጨካኝ ሊሆን ይችላል።
ምን ማለት ነው የፈለግኩት? በዚህ ዘመን በእከሌ ኡስታዝ ገንዘብ ተበላን የሚሉ ወገኖች እየበዙ ነው፣ በተለይ ዐረብ አገር ያሉ እህቶች። አንድን ሰው በደዕዋ ስም፣ በኡስታዝነት ዘርፍ ስላወቃችሁት ብቻ የዋህ አትሁኑ። ተቸግሮ መተባበር ሌላ ነው። አማና ለማስቀመጥ፣ ጉዳይ ለመዋዋል ግን ታማኝነቱ በተጨባጭ ለማይታወቅ ሰው የለፋችሁበትን ገንዘብ እንደዋዛ አትጣሉ። ታዋቂ ሰው መሆን እና ታማኝ መሆን ይለያያሉ። ታዋቂ ሆነው ግን ታማኝነት የሌላቸው በተጨባጭ ብዙ አሉ። ስለዚህ አመንን ብላችሁ ልባችሁን ሰጥታችሁ፣ አዘንን ብላችሁ በስራ ተባብራችሁ እጃችሁን ሊነክሷችሁ ይችላሉና ጥንቃቄ አድርጉ።
በሆነ ምክንያት ለማድረግ ከወሰናችሁም በራሳችሁ ይብቃ። ሌላ ሰው አትጎትቱ። ያለበለዚያ ጉዳቱ ይበልጥ የከፋ ሊሆን ይችላል። በተረፈ እነዚህን ክስተቶች መነሻ በማድረግ ጅምላ ፍረጃ ውስጥ አትግቡ። ይህም ሌላ ከባድ ጥፋት ነው። በቃ ከማንኛውም ሰው ጋር የሚኖራችሁን ጥንቃቄ አድርጉ።
በዚህ አይነት አማናን ማጉደል ላይ በተደጋጋሚ እየወደቃችሁ ያላችሁ ኡስታዞች ግን ወላሂ ከገንዘቡ በላይ ደዕዋው ላይ ጭምር ከባድ ጠባሳ እየጣላችሁ ነው። አውቆ አጥፊን መምከር እምብዛም ዋጋ ባይኖረውም ለማይረባ ዱንያ ብላችሁ ኣኺራችሁን ባታጨልሙ ይሻላችኋል እላለሁ። የኣኺራው ጉዳይ ብዙም ካላሳሰባችሁ እወቁት ያለ ጥርጥር በዱንያም ውርደት ይከተላል። ሁሉ ተደብቆ አይቀርም። እንዲህ አይነት ነውር በተራ ሰዎች ከሚፈፀመው በላይ ስለሚሰቀጥጥ ውጤቱም ይበልጥ አዋራጅ ነው የሚሆነው። አላህ ለሁላችንም ልብ ይስጠን።

Forwarded from ابو ألوا ن علي الأواشي.١
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
የማለዳ መልእክት
~
የበድር ጦርነት ላይ የተማረኩ የመካ ሙሽሪኮችን አስመልክቶ የአላህ መልእክተኛ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም እንዲህ ብለው ነበር።
لو كانَ المُطْعِمُ بنُ عَدِيٍّ حَيًّا، ثُمَّ كَلَّمَنِي في هَؤُلَاءِ النَّتْنَى؛ لَتَرَكْتُهُمْ له.
"ሙጥዒም ብኑ ዐዲይ በህይወት ቢኖርና በነዚህ ጥ ^ን - ቦች ጉዳይ ቢያናግረኝ ኖሮ ለሱ ስል እተዋቸው ነበር።" [ሶሒሕ አልቡኻሪይ፡ 3139]
ሙጥዒም ብኑ ዐዲይ ማነው?
በነብያችን ደዕዋ ያቄሙ የቁረይሽ ንኡስ ጎሳዎች ተሰባስበው በኑ ሃሺም እና በኑል ሙጦሊብ ላይ በደለኛ ማእቀብ ጥለው በወረቀት ፅፈው ከዕባ ላይ ሰቅለው ነበር። ሙጥዒም ብኑ ዐዲይ ይህንን የግፍ ሰነድ ቀዶ የጣለ ነው። በተጨማሪም ጧኢፍ ላይ ተንገላተው ሲመለሱ ልጆቹን ይዞ ማንንም እንዳይነካቸው ከለላ የሰጣቸው ሰው ነው።
ከዚህ ምን እንማራለን?
* ፈተና ላይ እያለን በትንሽ ነገር እንኳ ቢሆን ከጎናችን የቆመን ሰው ውለታውን ልንረሳ አይገባም። ያ አካል በሌላ ነገሩ ጥሩ የሚባል ባይሆን እንኳ ውለታን መዘንጋት የለብንም። ልብ በሉ! ሙጥዒም ብኑ ዐዲይ ሙሽሪክ (አጋሪ) ነበር። ሳይሰልም ነው የሞተው። ስለዚህ በዱንያም ይሁን በዲን ጉዳይ በወሳኝ ጊዜ ከጎናችን የቆመን ሰው ውለታውን ማወቅ፣ ብንችል ለበጎ አድራጎቱ ዋጋ መስጠታችንን የሚያሳይ መልካም ምላሽ ማድረግ ታላቅነት ነው።
* ታመን ከጎናችን የሆነን፣ ተቸግረን ሰዎች ፊት ሲነሱን የደገፈንን፣ በስልጣኑ፣ በገንዘቡ፣ በእውቅናው፣ በእውቀቱ፣ በጉልበቱ፣ በአንደበቱ፣ ... የደገፈንን ሰው ውለታውን ዋጋ መስጠት ይገባል።
* ተውሒድን በማስተማር፣ ከተሳሳተ መስመር በማውጣት፣ ወደ መስጂድ በመመለስ፣ በደዕዋ ወይም በደርስ በማንቃት፣ እንዳጠቃላይ ዲን በማስተማር ውለታው ያለብንን አካል ውለታውን አፈር ድሜ ልናበላ አይገባም።
{ وَلَا تَنسَوُا۟ ٱلۡفَضۡلَ بَیۡنَكُمۡۚ }

አባት!
~
4 አመት ሳለሁ ፡ አባቴ ከሁሉም ሰው የሚበልጥ ነው።
6 አመት ሳለሁ ፡ አባቴ ሁሉን ነገር ያውቃል።
10 አመት ሳለሁ : አባቴ ጎበዝ ነው፤ ግን ፀባዩ ከባድ ነው።
12 አመት ሳለሁ : ልጅ እያለሁኮ አባቴ ያዝንልኝ ነበር።
14 አመት ሳለሁ ፡ አባቴ በጣም ስሜታዊ እየሆነ ነው።
16 አመት ሳለሁ : አባቴ ከዘመኑ ጋር መሄድ አይችልም።
18 አመት ሳለሁ : አባቴ ጊዜ ባለፈ ቁጥር ሃይለኝነቱ እየባሰበት ነው።
2ዐ አመት ሳለሁ : አባቴን ይቅር ልለው ይከብደኛል። ግን እናቴ እንዴት ቻለችው?
25 አመት ሳለሁ : አባቴ ሁሉን ነገር ነው የሚቃወመው።
30 አመት ሳለሁ : አባቴ ጋር መግባባት ከባድ ነው።
35 አመት ሳለሁ : አባቴ በህይወቴ ሲያሳድገኝ ብዙ ህጎች ነበሩት። እኔም በልጆቼ ላይ እተገብራቸዋለሁ።
40 አመት ሳለሁ : አባቴ ግን እንዴት ይህን ሁሉ ልጅ ማሳደግ እንደቻለ ሳስበው ግራ ይገባኛል።
45 አመት ሳለሁ : ልጆቼን መቆጣጠር በጣም ከባድ ሆኖብኛል። አባቴ ግን እኛን ለማሳደግና ለመቆጣጠር ስንት መከራ ነው ያሳለፈው?!
50 አመት ሳለሁ : አባቴ ግን በብዙ ነገሮች ላይ እይታው ጥልቅ ነበር። የኔ አባትኮ እንደ ሌሎች አባቶች አይደለም! ከሰው የተለየ፣ አዛኝ ነበር። ከሁሉም የሚበልጥ ነው።
የኔ አባት ከሁሉም የሚበልጥ ነው ወደሚለው የ4 አመቱ መነሻ ለመመለስ ይህን ያህል ዓመት ፈጅቷል።
አባቱ በህይወት ያለ ሰው ጊዜው ሳያልፍ በፊት መልካም ይዋል። አባቱ የሞተበት ደግሞ አላህ እንዲምረውና እንዲያዝንለት ዱዓእ ያድርግለት።
(ከአንድ የዐረብኛ ፅሁፍ የተመለሰ)

* የአላህ መልእክተኛ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም በአንድ ወቅት : "የከሰረ ሰው ማለት ማን እንደሆነ ታውቃላችሁ?" ብለው ጠየቁ።
- ሶሐቦችም ፡ "ከእኛ መካከል የከሰረ ማለት ገንዘብ እና ንብረት የሌለው ሰው ነው" ብለው መለሱ።
* ነብያችን በዚህን ጊዜ እንዲህ አሉ፦
«إن المفلس من أمتي من يأتي يوم القيامة بصلاة وصيام وزكاة، ويأتي وقد شَتَمَ هذا، وقذف هذا، وأكل مال هذا، وسَفَكَ دم هذا، وضرب هذا، فيعطى هذا من حسناته، وهذا من حسناته، فإن فنيت حسناته قبل أن يُقْضَى ما عليه، أخذ من خطاياهم فَطُرِحتْ عليه، ثم طُرِحَ في النار».
"ከሕዝቦቼ መካከል በእውነት የከሰረ ማለት፤ በቂያማ ቀን የሶላት፣ የጾም፣ የዘካ፣ ... (ምንዳ) ይዞ የሚመጣ ነው። ነገር ግን ይህንን ሰድቦ፣ ይህንን በዝሙት ወንጀሎ፣ የዚህን ገንዘብ (በግፍ) በልቶ፣ የዚህን ደም አፍስሶ፣ ይህንን መትቶ፣ ... ይመጣል።
ከዚያም ለዚህኛው ከመልካም ስራው ይሰጠዋል፤ ለዚያኛውም ከመልካም ስራው ይሰጠዋል። በእርሱ ላይ ያለበት (የበደል) እዳ ተከፍሎ ሳያልቅ መልካም ስራዎቹ ካለቁበት፣ ከእነርሱ (ከበደላቸው ሰዎች) ወንጀል ተወስዶ በእርሱ ላይ ይጫንና ከዚያም ወደ እሳት ይወረወራል።"
[ሶሒሕ ሙስሊም፡ 2581]
ይህ ሐዲሥ በኢስላም ውስጥ እጅግ አስፈሪ እና ትልቅ ማስጠንቀቂያ ከያዙ ሐዲሦች ውስጥ አንዱ ነው።
ከሐዲሡ ከሚወሰዱ ቁም ነገሮች ውስጥ ጥቂት ለማንሳት ያህል፦
=
1- የኪሳራ ትርጉም፡
ሰዎች በተለምዶ ኪሳራ ሲባል የሚያውቁትና የሚያስደነግጣቸው የገንዘብና የንብረት ማጣት ነው። ይህ ዓይነቱ ኪሳራ ግን በዱንያ የሚያልቅ ቀላል ኪሳራ ነው። ከባዱ ኪሳራ የቂያማ ቀን ኪሳራ መሆኑን ከሐዲሡ እንማራለን።
2- ዒባዳ ብቻውን ዋስትና አይደለም፡
አንድ ሰው ሶላት ቢሰግድ፣ ፆም በያይነቱ ቢጾም፣ ዘካ ቢያወጣም፣ ሌሎች ዒባዳዎችንም ቢፈጽም፤ ከሰዎች ጋር ያለው ግንኙነት (ስነ-ምግባሩ) የተበላሸ ከሆነ ለአደጋ የተጋለጠ ነው። ኢስላም ከአላህ ጋር ያለን ግንኙነት (ዒባዳ) እና ከሰዎች ጋር ያለን ግንኙነት (ሙዓመላ) ያጣመረ ሃይማኖት ነው።
3- የቂያማ ቀን መገበያያ፡
በዚያ ቀን ብር ወይም ወርቅ አይሰራም። መገበያያው "ሐሰናት" (መልካም ስራ) እና "ሰይኣት" (ወንጀል) ብቻ ነው። የሰው መብት የነካ ሰው መልካም ስራውን ለበደላቸው ሰዎች ይከፍላል። መልካም ስራው ካለቀበት ደግሞ የእነሱን ወንጀል ተሸክሞ ወደ እሳት ይወርዳል።
4- የሰዎች ሐቅ፡
ይህ ሐዲሥ የሰዎችን ደም ማፍሰስ፣ ገንዘብ መብላት፣ ስም ማጥፋት እና መሳደብ ምን ያህል ከባድ ዋጋ እንደሚያስከፍል ያሳያል።
አላህ የሰዎችን መብት ከመንካት፣ የዚያን ቀን ከሳሪዎች ከመሆንም ይጠብቀን።
* ይሄ ሁሉ ሰልፈኛ ሐቃቸውን ከኛ ለመውሰድ የተሰለፉ ቢሆኑ ብለን እናስብ እስቲ። አላህ ልብ ይስጠን።

የሒስኑል ሙስሊም ኪታብ ደርስ ይኖራል።
~
• ደርሱ የሚሰጥበት ቦታ:- አሸዋ ሜዳ፣ ጉቱ ሪል እስቴት መስጂደል ዋሊደይን
• ጊዜ፦ ከመግሪብ እስከ ዒሻእ
• የኪታቡን pdf ፋይል በዚህ ማግኘት ይቻላል:-
https://t.me/IbnuMunewor/8340
• የእለቱ ደርስ መነሻ፦ ገፅ 41፣ ሐዲሥ ቁጥር 102
• ደርሱ በዚህ የቴሌግራም ቻናል ይተላለፋል፣ ኢንሻአላህ፦