አልወድህም አፈቅርሃለሁ
ባሏን ሁልጊዜም እንደምትወደው ትነገረው ነበር፤ ሆኖም እንደቀልድ ይወስደው ስለነበር በጣም አዝና አንድ ቀን፡- እንደምወድህ ስነግርህ ለምንድነው የምትስቀው ብላ ጠየቀችው፡፡
ባሏም እንድህ አለ፡- እንደምትወጂኝ ሳይሆን እንደምታፈቅሪኝ ስለማውቅ አፈቅርሃለሁ ከማለት ይልቅ እወድሃለሁ ማለቱን ማዘውተርሽ ስለሚገርመኝ ነው ብሎ መለሰላት፡፡
ልጅቷም ጭንቀት እና ሃዘን የተሞላበት ፊቷን ወደ ፈገግታ ቀይራው ኦ… የኔ ፍቅር በጣም አፈቅርሃለሁ አለችው፡፡
ባሏም፡- የኔ ውድ አንድ ለየት ያለ ነገር እንድታደርጊልኝ እፈልጋለሁ
ልጅቷም፡- ምን?
ባሏም፡- ማታ ቤት ስትገቢ እናትሽን አመስግኚልኝ
ልጅቷም፡- እሺ… ግን በምን ምክንያት?
ልጁም፡- በሕይወቴ መጥታ ደስታን የሰጠችኝኝ ነገ ደግም የትዳር አጋሬና የልቤ መርጊያ አንቺን ስለወለደች ነው፡፡ ብሎ መለሰላት ደስ አይሉም?? በአሏህ!!!
#ጥሩን ለጥሩ ነው አላህ የኸለቀው

«ውሸት ወደ ጥመት የሚመራ ታላቅ ወንጀል
_*መሐላና ውሸት*_
መሐላ ሶስት አይነት ነው።
① ሳይታመንበት እንዲሁ በልምድ የሚፈፀም መሐላ።
ለምሳሌ፦ ለአንድ ወንድምህ "ወላሂ መብላት አለብህ… ወላሂ መቀመጥ
አለብህ… ወላሂ አልችልም ወዘተ…" ብትል እንደ ማለት ነው።
*ወላሂ* የምትለው መሐላ ከጅለህ ሳይሆን እንዲሁ በልምድ፣ በንግግሩ
ጣልቃ የሚመጣ ከሆነ ይህ አይነቱ መሐላ " ﻟﻐﻮ" (ለግው) ይባላል። አላህ
ይህን በማስመልከት እንዲህ ብሏል፦
*«ሳታስቡት በምትፈጽሙት መሐላዎች አላህ አይዛችሁም፤ ግና ልቦናቻችሁ
እያሰቡ በፈፀማችሁት (መሐላ) ይይዛችኋል። አላህ መሐሪም ታጋሽም
ነው።»* (አል_በቀራህ: 225)
እንዲህ አይነቱ መሐላ ወንጀል ባይሆንም ሙእሚን ግን ሊጠነቀቀው
ይገባል። በትንሹም በትልቁም በአላህ መማል ልምድ እንዳይሆንብት ብሎም
በሀሰት ወደመማል እንዳያመራ ለመጠንቀቅ ሲባል።
*②* ሌላው የመሐላ አይነት ወደፊት አንድ ነገር ለመፈጸም ወስኖና ምሎ
ሳለ ከርሱ የተሻለ ነገር ማግኘቱ የተገለጸለት ነው። ለምሳሌ "ወላሂ ነገ
እመጣለሁ።" ቢልና ከማለ በኋላ የተሻለ ነገር ቢታየው ከፈለገ ለመሐላው
ካሳ (ከፋራ) በመክፈል አለመፈፀም ይችላል። ይህ ነገር ነብዩ (ሰለላሁ
አለይሂ ወሰለም) ላይም ተከስቷል። የተወሰኑ የምግብ ዓይነቶችን
ላለመመገብ መሐላ ፈፀሙ። በራሳቸውም ላይ እርም አደረጓቸው።
ከዚያም በኋላ ቀጣዩ የቁርአን አንቀጽ ወረደ፦
*«አንተ ነብዩ ሆይ! አላህ የፈቀደልህን ነገር ሚስቶችህን ለማስደሰት
በመሻት፥ በራስህ ላይ ለምን እርም ታደርጋለህ? አላህም እጅግ መሐሪ አዛኝ
ነው። አላህ መሐሎቻችሁን መፍቻ ደነገገላችሁ፤ አላህም ረዳታችሁ ነው፤
እርሱም ዐዋቂ ጥበበኛው ነው።»* (አት_ተሕሪም 1_2)
የአላህ መልዕክተኛ(ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም)
_«እኔ በአንዳች ነገር እምላለሁ። ከርሱ የተሻለ ነገር ሳገኝ ያን የተሻለውን
ፈፅሜ ለመሐላዬ ካሳ (ከፋራ) እከፍላለሁ።»_ ብለዋል
ማካካሻችሁን በሚመለከት ቁርአን እንዲህ ይላል፦
*«አላህ ከመሐላ ድንገተኛ በሆነው አይዛችሁም። ግና አስባችሁና ፈቅዳችሁ
በፈፀማችሁት መሐላ ይይዛችኋል። (ባፈረሳችሁም ጊዜ) ማስተስሪያው
ቤተሰቦቻችሁን ከምትመግቡት ከመካከለኛው ምግብ አስር ድሆችን ማብላት
ወይም እነርሱን ማልበስ ወይም ባሪያ ነፃ መልቀቅ ነው። (ከተባሉት
አንዱንም) ያላገኘ ሦስት ቀናትን መጾም (በቂው) ነው።»* (አለ_ማኢዳህ:
89)
ለመሐላቸው ካሳ ለመክፈል ሲሹ ሦስት ቀን የሚጾሙ ሰዎች አሉ። ስህተት
ነው። ምክንያቱም የመሐላ ካሳ አስር ድሆችን መመገብ ወይም ማልበስ
ወይም ባሪያ ነፃ መልቀቅ ሲሆን እነዚህን ማድረግ የማይችሉት ብቻ ናጨው
ሦስት ቀን በመጾም መሐላዎቻቸውን እንዲያካክሱ የተፈቀደላቸው።
*③* የሐሰት መሐላ ። ይህም መሐላ ( ﻳﻤﻴﻦ ﺍﻟﻐﻤﻮﺱ ) በመባል ይታወቃል።
_*«ባለቤቶቹ ጀሀነም ውስጥ እንዲዘፈቁ ሰበብ የሚሆን መሐላ»*_ ማለት
ነው። ይህ ዓይነቱ መሐላ የተለያዩ ደረጃዎች አሉት።
ከሁሉም አደጋው ያነሰው ለአንድ ሰው ያለፈን ነገር መዋሸትና ምለህ መንገር
ነው። ለምሳሌ "ትናንት እገሌ ዘንድ ሄደሀልን?" ተብለህ ስትጠየቅ። "ወላሂ
አልሄድኩም" በማለት የውሸት መልስ ብትሰጥ እንደማለት። ነገሩ ኃጢአት
መሆኑ ምንም አያጠራጥርም። ምንም ማካካሻ ወይም ከፋራ የለውም።
ተውባ ብቻ እንጂ።
ከሁሉም የከፋው ደግሞ ፍርድ ቤት ውስጥ የሐሰት ምስክርነት መስጠት
ነው። ለከፋ የጀሀነም ቅጣት ይዳርጋል። ማካካሻው ሁለት ነገሮችን መፈፀም
ብቻ ነው።
አንደኛ፦ በተውባ ወደ አላህ መመለስ።
ሁለተኛ፦ በሐሰት ምስክርነትህ ያበላሸኸውን ነገር ማስተካከል። ምስክርነት
ከሰጠህበት ቦታ በመመለስ "የሰጠሁት ምስክርነት ሐሰት ነው። እውነቱ
ይህ፣ ይህ ነው።" በማለት በአንተ የሐሰት ምስክርነት ሰበብ የተዛቡ ፍርዶችን
ፈር ማስያዝ ይጠበቅብሃል።
ውሸቶች አይነታቸውና ደረጃቸው ይለያይ እንጂ ሁሉም አደጋቸዎች ናቸው!
አላህ ይጠብቀን

በአንድ ዚክር ጀነት መግባት ይፈልጋሉ? እግዲያው ይሄ ከታች ያለው ዚክር ሀፍዘው ጥዋትና ማታ ማዘውተርዎን አይርሱ።
ነብዩ ሙሀመድ ሰለላሁ አለይሂ ወሰልም አንድን ሰው ይሄን ዚክር ጥዋት ላይ ብሎት በዛን ቀን የሞተ ጀነት ይገባል። ማታ ላይ ብሎት በዛን ለሊት የሞተ ጀነት ይገባል ብለዋል። {ኢማሙል ቡሓሪ}
ﺍﻟﻠﻬﻢ ﺍﻧﺖ ﺭﺑﻲ ﻻ ﺇﻟﻪ ﺇﻻ ﺍﻧﺖ، ﺧﻠﻘﺘﻨﻲ ﻭﺍﻧﺎ ﻋﺒﺪﻭﻙ، ﻭﺍﻧﺎ ﻋﻠﻰ ﻋﻬﺪﻳﻚ ﻭﻭﻋﺪﻳﻚ ﻣﺎ ﺍﺳﺘﻄﺎﺕ، ﺍﻋﻮﺫﻭ ﺑﻴﻚ ﻣﻴﻨﺸﺮ ﻣﺎ ﺻﻨﻌﺖ، ﺍﺑﻮﺀ ﻟﻚ ﺑﻴﻨﻌﻤﺘﻴﻚ ﻋﻠﻲ ﻭﺍﺑﻮﺀ ﺑﻴﺬﻧﺒﻲ ﻓﻐﻔﻴﺮ ﻟﻴﻰ ﻓﺈﻧﻪ ﻻ ﻳﻐﻔﻴﺮ ﺫﻭﻧﻮﺏ ﺇﻻ ﺍﻧﺖ .
አላህ ሆይ! አንተ አምላኬ ነህ። ከአንተ ውጭ ሌላ አምላክ የለም። ፈጥረህኛል። እኔ ባሪያህ ነኝ። እኔ የቻልኩትን ያክል ያንተን ቃል ኪዳን ለመሙላት እሞክራለሁ። ከሰራሁት ነገር ከክፉው በአንተ እጠበቃለሁ። በኔ ላይ ለዋልከው ጸጋህ እውቅና እሰጣለሁ። ሐጢአቴም እናዘዛለሁ። ማረኝ። ከአንተ ውጭ ሐጢአትን የሚምር የለም።

This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
Prophet Muhammad - The best example of good moral character