ቅዱሳት መጻሕፍት
6.54K subscribers
929 photos
33 videos
265 files
666 links
በዚህ ቻናል

👉ቅዱሳት መጻሕፍት ይጠናሉ::
👉መጽሐፍ ቅዱሳዊ ትምህርቶች ይቀርባሉ::
👉 ለቅዱሳት መጽሐፍት ጥናት የሚያግዙ መጻሕፍት ይለቀቃሉ።

⭐️⭐️⭐️⭐️⭐️

@Holy_scriptures
Download Telegram
👤ፍጥረታዊ፣ ሥጋዊ እና መንፈሳዊ ሰው



ክፍል-3

ቀደም ሲል በአገባቡ እንደተገለጠው (1ኛ ቆሮ. 1:18፥ 23)፣ ከመለኮታዊው መገለጥ ከፊሉ “ለፍጥረታዊ ሰው. . .ሞኝነት” ነው። “የመስቀሉ ቃል ለሚጠፉት ሞኝነት፥ ለእኛ ለምንድን ግን የእግዚአብሔር ኃይል ነውና።” “እኛ ግን የተሰቀለውን ክርስቶስን እንሰብካለን፤ ይህም ለአይሁድ ማሰናከያ ለአሕዛብም ሞኝነት ነው፥” እዚህ የተገለጠው በታሪክ ስለታወቀው የክርስቶስ ሞት ብቻ ሳይሆን፣ ከዚያም የበለጠ ነገር ነው። ያም በእርሱ በኩል የተደረገውን ዘላለማዊ ግንኙነት የሚያጠቃልልና በጸጋው በኩል መዋጀታችንን የሚያሳይ መለኮታዊ መግለጥ ነው። በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የተነገሩት ግብረገባዊ መርሆዎችና ብዙዎቹ ሃይማኖታዊ ትምህርቶች ፍጥረታዊው ሰው ሊገባው በሚችል ደረጃ ይገኛሉ። “የእግዚአብሔር ጥልቅ ነገሮች” መኖራቸውን እንኳን ሳያውቅ ከእነዚህም ምንጮች በመቅዳት አንደበተ-ርቱዕ እና ከልቡ የሚያገለግል ሰባኪ ሊሆን ይችላል።

ሰይጣን በአስመሳይ ዘዴው የሚገልጣቸው “ጥልቅ ነገሮች” (ራእይ 2፡24) እና “የዲያብሎስ ትምህርቶች” (1ኛ ጢሞ. 4፡1፥2) እንዳሉት እና እነዚህንም ነገሮች “ከሌላው ግን ይሸሻሉ እንጂ አይከተሉትም፤ የሌሎችን ድምፅ አያውቁምና” (ዮሐ. 10፡5) እንደተባለ እውነተኛው የእግዚአብሔር ልጅ በእርግጥ እንደማይቀበላቸው ተጽፏል። ሆኖም እነዚህ የሰይጣን “ጥልቅ ነገሮች” ለታወረው “ተፈጥሯዊ ሰው” በጣም ምቹ ናቸው፤ ስለዚህም ይቀበላቸዋል። የዘመናችን የስሕተት ሃይማኖቶች ሁሉ የዚህን መግለጫ እውነትነት ያረጋግጣሉ።

ያልዳነ ሰው ምንም እንኳ “በሰብአዊ ጥበብ” ሁሉ የሠለጠነና ንቁ ሃይማኖተኛ ቢሆን፣ ለወንጌል የታወረ ነው (2ኛ ቆሮ. 4፡3፥4)። የተማረ አእምሮ በጣም ይረዳል ይባል ይሆናል፤ ነገር ግን በውስጥ ያለው መምህር (መንፈስ ቅዱስ) ካልኖረ የተገለጡትን የእግዚአብሔር ነገሮች መንፈሳዊ ትርጉም ለመረዳት የሠለጠነ አእምሮ ምንም ለማድረግ አይችልም። ያለ መንፈስ ቅዱስ፣ ዳግም ልደት አይኖርም። “የእግዚአብሔርም ጥልቅ ነገሮች” አይታወቁም። ለዚህም ነው ከእግዚአብሔር እንዲያው የተሰጧቸውን ነገሮች ያውቁ ዘንድ ለዳኑት መንፈስ ቅዱስ የተሰጣቸው።

ያም ቢሆን ከክርስቲያኖችም መካከል አንዳንዶቹ ከሥጋዊነታቸው የተነሣ ውሱኖች ሆነው ይኖራሉ። ካለማወቅ ሳይሆን በሥጋዊነት ምክንያት እነዚህ ሰዎች ጠንካራ ምግን ሊመገቡ አይችሉም።
ያልዳኑትን በተመለከተ በመለኮት ዘንድ ምንም ልዩነት አልተደረገም። ሁሉም “ፍጥረታውያን” ተብለዋል።

ስለፍጥረታዊ ሰው ስንደመድም፦

ተፈጥሮአዊ ወይም መንፈሳዊ ያልሆነ ነው (ግሪክ፡ “ሱኪኮስ”፣ 1ቆሮ. 2፡14) ዳግም ልደት ያላገኘን ሰው ያመለክታል። መለያ ባህሪያቶቹም፦

👉በተፈጥሮ ስሜት ብቻ የሚመራ ለሥጋውና ለስሜቱ ባሪያ ነው (2ጴጥ 2:12፤ ኤፌ. 2፡3)።

👉ከዓለም ስለሆነ የዓለም ወዳጅ ነው (ያዕ. 4፡4)

👉የመንፈስ ቅዱስን የጽድቅ መንገድ ይቃወማል፤ መንፈሳዊ ነገርንም መረዳት አይችልም። ለእርሱ ሞኝነት (1ቆሮ. 2፡14)

ይቀጥላል...



ምንጭ፦

👉“ምሉእ ሕይወት መጽሐፍ ቅዱስ”፣ አዲሱ መደበኛ ትርጉም፣ ዋና አርታኢ፦ ዶናልድ ሲ. ስታምፕስ፣ ተባባሪ አርታኢ፦ ጄ. ዌስሊ አዳምስ

👉"መንፈሳዊ ሰው"፣ የመንፈሳዊነት ትምህርተ-ሃይማኖት ጥናት፣ በዶክተር ሉዊስ ስፔሪ ቼፈር፣ የዳላስ ቲዮሎጂካል ሰሚነሪ መሥራችና ፕሬዚደንት፣ ተርጓሚ ዘላለም መንግሥቱ



Join us
📚@Holy_scriptures📚
📚@Holy_scriptures📚
🀄️🀄️ሉን
' ==❀❀❀===❀❀❀==
የዕለቱ ጥቅስ
==❀❀❀===❀❀❀==
“እግዚአብሔር ወዴት ነው?’ ብለው፣ ካህናቱ አልጠየቁም፤ ከሕጉ ጋር የሚውሉት አላወቁኝም፤ መሪዎቹ ዐመፁብኝ፤ ነቢያቱም በበኣል ስም ተነበዩ፤ ከንቱ ነገሮችን ተከተሉ።”
ኤርምያስ 2፥8 (አዲሱ መ.ት)


Join us
📚@Holy_scriptures📚
📚@Holy_scriptures📚
🀄️🀄️ሉን
👤ፍጥረታዊ፣ ሥጋዊ እና መንፈሳዊ ሰው



ክፍል-4


🌱ሥጋዊ ሰው

ሐዋርያው ጳውሎስ ለቆሮንቶስ ሰዎች ሲጽፍላቸው (ጳውሎስ መልእክቱን የጻፈው ለአማኞች እንደሆነ ልብ በሉ።) አንዳንዶች እንደ ዓለማዊ ወይም መንፈሳዊ እንዳልሆነ ሰው (ግሪክ፡ “ሳርኪኮስ”) በመጥፎ ባሕርይ እየተመላለሱ መሆናቸውን አመልክቶአቸዋል፤ የራሳቸውን የኀጢአተኛ ተፈጥሮ ዝንባሌ ባለማቋረጥ ሙሉ በሙሉ ከመቃወም ይልቅ አብዛኛውን ጊዜ ለአንዳንዶቹ ስሜቶቻቸው ተገዥ ሲሆኑ ይታያሉ። በዐመፃቸው ጸንተው ባይኖሩም፣ የእግዚአብሔር ሕዝብ ወገን ሆነው መቆየትን እየፈለጉ በአንዳንድ የሕይወታቸው ክፍል ከዓለም፣ ከኀጢአተኛ ተፈጥሮና ከዲያብሎስ ጋር በመተባበር ሂደት ውስጥ ይገኛሉ። እንደዚህ ዓይነት ሰዎች ሥጋዊ ይባላሉ።

በ1ኛ ቆሮንቶስ 3፡1-4 ሐዋርያው ስለ “ሥጋዊ” ሰው ገለጣውን በመቀጠል እንዲህ ይላል፦

“እኔም፥ ወንድሞች ሆይ፥ የሥጋ እንደ መሆናችሁ፥ በክርስቶስም ሕፃናት እንደ መሆናችሁ እንጂ መንፈሳውያን እንደ መሆናችሁ ልናገራችሁ አልቻልሁም። ገና ጽኑ መብል ለመብላት አትችሉም ነበርና ወተት ጋትኋችሁ፤ ገና ሥጋውያን ናችሁና እስከ አሁን ድረስ ገና አትችሉም። ቅናትና ክርክር ስለሚገኝባችሁ ሥጋውያን መሆናችሁ አይደላችሁምን? እንደ ሰው ልማድስ አትመላለሱምን? አንዱ፦ እኔ የጳውሎስ ነኝ፥ ሁለተኛውም፦ እኔ የአጵሎስ ነኝ ቢል ሰዎች ብቻ መሆናችሁ አይደለምን?”

አንዳንድ ክርስቲያኖች “ሥጋውያን” የተባሉበት ምክንያት የቃሉን ወተት ብቻ እንጂ፣ ጠንካራውን ምግብ መቀበል ስለማይችሉ ነው። ለቅንዓት፣ ለክርክርና ለመከፋፈል ይሸነፋሉ፣ እንደ ሰው ልማድም ይመላለሳሉ፤ ከእውነተኛ የእግዚአብሔር ልጅ የሚጠበቀው ግን “በመንፈስ መመላለስ” (ገላ. 5፡16)፣ “በፍቅር መመላለስ” (ኤፌ. 5፡2) እና “የመንፈስን አንድነት መጠበቅ” ነው (ኤፌ. 4፡3)። ሥጋውያን ክርስቲያኖች ምንም እንኳ የዳኑ ቢሆኑ፣ የሚመላለሱት “እንደዚህች ዓለም አሳብ” ነው። ሥጋቸው ስለሚገዛቸውም “ሥጋውያን” ናቸው (ሮሜ 7፡14) ።

በነገራችን ላይ “ሥጋዊ ሰው” የሚለውን ከቆሮንቶስ ምዕራፍ 2-3 አንጻር እንጂ ከሙሉ መጽሐፍ ቅዱስ አንጻር አይደለም። ምክንያቱም አንዳንድ ቦታዎች ላይ “ሥጋዊውን ሰው” ፍጥረታዊ አድርጎ ይመለከታል። ለምሳሌ፦ ሮሜ 8፡5-9።

“ሥጋዊው” ሰው ወይም “በክርስቶስ ሕፃን የሆነው” የእግዚአብሔርን ጥልቅ ነገር ለመሸከም “የሚችል” አይደለም። ገና ሕፃን ብቻ ነው፤ ይሁን እንጂ ሊጤን የሚገባው ነገር ይህ ከፍ ያለ ስፍራና እውነታ ምንም ሊያደርግ ከማይችለው ከ”ፍጥረታዊው ሰው” ጋር ሊወዳደር ያለመቻሉ ነው። “ሥጋዊው” ሰው በእውነተኛው መንፈሳዊ ምግብ ላይ ብዙ ጊዜ ስለማያሳልፍ በአማኞች መካከል መለያየትን ለሚፈጥሩት ለቅንዓትና ለክርክር ተሸናፊ ይሆናል። ይህ ክፍል የሚናገረው እጅግ ውድ የሆነውን የቅዱሳንን ኅብረትና ፍቅር ስለሚያፈርሰው ቅንዓትና ክርክር ነው። የተለያዩ ድርጅቶች በአማኞች መካከል የተለያዩ ደረጃዎችን በመፍጠር ሊከፋፈሉ ይችሉ ይሆናል፤ ግን ይህ የግድ ይሆናል ማለት አይደለም። በዚህ ክፍል የተመለከተው ኃጢአት ሰብአዊ መሪዎችን የመከተል የአማኝ ኃጢአት ነው። ይህ ኃጢአት የሃይማኖት ድርጅቶች በሙሉ በቅፅበት ከምድረ-ገጽ ተጠራርገው ቢጠፉ ወይም አንድ ሆነው ቢዋሐዱ እንኳ የሚፈወስ አይደለም። በዚያን ዘመን “ጳውሎሳውያን”፣ “ኬፋውያን”፣ “አጵሎሳውያን” እና “ክርስቶሳውያን” ነበሩ (1ኛ ቆሮ. 1፡12ን ይመልከቱ)። እነዚህ እርስ በርስ የሚሻኮቱ ድርጅቶች ሳይሆኑ ከቅንዓትና ከክርክር የተነሣ በቆሮንቶስ ቤተክርስቲያን ውስጥ የተቀፈቀፉ ቡድኖች ናቸው። እንዲህ ያሉት ቡድኖች መጨረሻቸው ተሻኳች ድርጅቶችን መፍጠር መሆኑን ታሪክ ያመለክተናል። መለያየት ሌላ ነገር ሳይሆን፣ የፍቅር የለሽና ሥጋዊ ሕይወት ጠሊቅ ኃጢአት ውጪአዊ መግለጫ ነው።


ይቀጥላል...


ምንጭ፦

👉“ምሉእ ሕይወት መጽሐፍ ቅዱስ”፣ አዲሱ መደበኛ ትርጉም፣ ዋና አርታኢ፦ ዶናልድ ሲ. ስታምፕስ፣ ተባባሪ አርታኢ፦ ጄ. ዌስሊ አዳምስ

👉"መንፈሳዊ ሰው" ፣ የመንፈሳዊነት ትምህርተ-ሃይማኖት ጥናት፣ በዶክተር ሉዊስ ስፔሪ ቼፈር፣ የዳላስ ቲዮሎጂካል ሰሚነሪ መሥራችና ፕሬዚደንት፣ ተርጓሚ ዘላለም መንግሥቱ


Join us
📚@Holy_scriptures📚
📚@Holy_scriptures📚
🀄️🀄️ሉን
' ==❀❀❀===❀❀❀==
የዕለቱ ጥቅስ
==❀❀❀===❀❀❀==
“ከእንግዲህ በማዕበል ወደ ፊትና ወደ ኋላ እየተነዳን፣ በልዩ ልዩ ዐይነት የትምህርት ነፋስ፣ በሰዎችም ረቂቅ ተንኰልና ማታለል ወዲያና ወዲህ እየተንገዋለልን ሕፃናት አንሆንም።”
ኤፌሶን 4፥14 (አዲሱ መ.ት)


Join us
📚@Holy_scriptures📚
📚@Holy_scriptures📚
🀄️🀄️ሉን
የስሙ ትርጉም "የመጽናናት ልጅ" የሚባለው ማን ነው?
Anonymous Quiz
15%
ሀ. ሲላስ
18%
ለ. ባስልኤል
7%
ሐ. ቲቶ
61%
መ. በርናባስ
👤ፍጥረታዊ፣ ሥጋዊ እና መንፈሳዊ ሰው



ክፍል-5


የሥጋዊ ሰው መለያ ባህሪያት፦

1⃣በክርስቶስ ሕፃናት ናቸው

ማንኛውም አማኝ የሚጀምረው እንደ ሕፃን ክርስቲያን ነው። በዚህ አሳፋሪነት የለውም። ነገር ግን ሕፃናት ሆነን መቅረት አይኖርብንም! ሥጋዊያን ግን ከማደግ ይልቅ በሕፃንነት ረጅም ጊዜ ይቆያሉ።

2⃣መንፈሳዊ ኃይል የላቸውም

“ገና ጽኑ መብል ለመብላት አትችሉም” (ቁ. 2)

“መቻል” የሚለው ቃል፣ የግሪክ ቃል “dunamai” ሲሆን፣ ፍቺውም የማድረግ ኃይል፣ ለመቀዳጀት፣ ወደ መዳረሻው ውጤት መሥራት ነው። እነዚህ አማኞች ምንም የንግሥና ኃይል የላቸውም፣ ሥጋዊ ኃይል ብቻ፣ እሱም፣ አቅመ-ቢስነት ነው!

3⃣መቀናናትና መለያየት

እነዚህ በገላ. 5:19-21 ላይ የተዘረዘሩት ሁለት የሥጋ ሥራዎች ናቸው። እነዚህም ማስረጃዎች ናቸው፣ አንዳንድ የቆሮንቶስ ክርስቲያኖች እስካሁን ሥጋዊ ለመሆናቸው።

4⃣እንደ ሰው ልማድ መመላለስ

ዳግም የተወለደን አማኝ መጽሐፍ እንደሚከተለው ያዘዋል፦

“የእግዚአብሔር ፈቃድ እርሱም በጎና ደስ የሚያሰኝ ፍጹምም የሆነው ነገር ምን እንደ ሆነ ፈትናችሁ ታውቁ ዘንድ በልባችሁ መታደስ ተለወጡ እንጂ ይህን ዓለም አትምሰሉ።” (ሮሜ 12፡2)

ሥጋዊያን ግን እንደሰው ልማድ እንደ ዓለም ይመላለሳሉ፤ ያስባሉም። የሕይወታቸውም መርህ ከዓለማዊያን አይለይም።

ሥጋዊ ሰው ከፍጥረታዊ ሰው በምን ይለያል፦

ሥጋዊውን ሰው ከፍጥረታዊ ለመለየት በጣም አስቸጋሪ ነው። ምክንያቱም በብዙ ነገራቸው ስለሚመሳሉ። ልዩነታቸው ሥጋዊ ሰው ዳግም መወለዱ ነው። ሌላው የሚያደናግረው ሥጋዊ ሰው የተለያዩ የጸጋ ስጦታዎች ተገልጠውበት “መንፈሳዊ” ሊመስል ይችላል። ነገር ግን ከላይ የተመለከትናቸው የሥጋዊነት መለያ ከታየበት ያለጥርጥር ሥጋዊ ነው። አንድ አማኝ የተለያየ የጸጋ ስጦታ ከተገለጠበት መንፈሳዊ ሰው ነው ብለን መደምደም አንችልም።

⚠️ለሥጋዊ ክርስቲያኖች የተሰጡ ማስጠንቀቂያዎች፦

1⃣ሥጋዊ ክርስቲያኖች እግዚአብሔርን ከማያስደስቱ ነገሮች ራሳቸውን ለማንጻት ፈቃደኛ ካልሆኑ በእምነት ከሚገኘው የሕይወት መንገድ የመውጣት አደጋ ውስጥ እንዳሉ ማወቅ አለባቸው (ሮሜ 6:14-16፤ 1ቆሮ 6፥9-10፤ 2ቆሮ 11፥3፤ ገላ. 6፥7-9፣ ያዕ. 1፥12-16) ፣

2⃣በኀጢአታቸው ምክንያት እግዚአብሔር ካጠፋቸው ከእስራኤላውያን አሳዛኝ ምሳሌነት ትምህርት መውሰድ ይገባቸዋል (1ቆሮ. 10፥5-12) ፤

3⃣በአንድ ጊዜ የእግዚአብሔርን ነገርና የሰይጣንን ነገር ማድረግ እንደማይቻል መረዳት አለባቸው (ማቴ. 6፥24፤ 1ቆሮ. 10፥21) ፤

4⃣ከዓለም ሙሉ በሙሉ ራሳቸውን መለየት (2ቆሮ 6፥14-18) እንዲሁም እግዚአብሔርን በመፍራት ቅድስናቸውን ፍጹም ለማድረግ ሥጋንና መንፈስን ከሚያረክስ ነገር ሁሉ ራሳቸውን ማንጻት አለባቸው (2ቆሮ. 7፥1) ።



ይቀጥላል...


ምንጭ፦

👉“ምሉእ ሕይወት መጽሐፍ ቅዱስ”፣ አዲሱ መደበኛ ትርጉም፣ ዋና አርታኢ፦ ዶናልድ ሲ. ስታምፕስ፣ ተባባሪ አርታኢ፦ ጄ. ዌስሊ አዳምስ

👉“የጳውሎስ መልዕክቶች ለታወከችው ቤተ ክርስቲያን 1ኛ እና 2ኛ ቆሮንቶስ”፣ ቦብ አትሊ የትርጓሜ ፕሮፌሰር (የመጽሐፍ ቅዱስ ትርጓሜ)፣ የጥናት መመሪያ ተከታታይ ሐተታ አዲስ ኪዳን፣ ቅጽ 6 ዓለም አቀፍ የመጽሐፍ ቅዱስ ትምህርት፣ ማርሻል፣ ቴክሳስ 2002 (በ2011 የተከለሰ)


Join us
📚@Holy_scriptures📚
📚@Holy_scriptures📚
🀄️🀄️ሉን
ቅዱሳት መጻሕፍት pinned «"ፍጥረታዊ ሰው፣ ሥጋዊ ሰው እና መንፈሳዊ ሰው" በሚለው ጥያቄ ካላችሁ መጠየቅ ይቻላል»
' ==❀❀❀===❀❀❀==
የዕለቱ ጥቅስ
==❀❀❀===❀❀❀==
“ስለ እስራኤልም ልጆች ክርክር፦ እግዚአብሔር በመካከላችን ነውን ወይስ አይደለም? ሲሉ እግዚአብሔርን ስለተፈታተኑት የዚያን ስፍራ ስም ማሳህ፥ ደግሞም መሪባ ብሎ ጠራው።”
(ዘጸአት 17፥7)


Join us
📚@Holy_scriptures📚
📚@Holy_scriptures📚
🀄️🀄️ሉን
“የአምልኮት መልክ አላቸው ኃይሉን ግን ክደዋል፤ ከእነዚህ ደግሞ ራቅ።”
(2ኛ ጢሞቴዎስ 3፥5)

“ሃይማኖታዊ መልክ አላቸው፤ ኀይሉን ግን ክደዋል። ከእነዚህ ራቅ።”
2ኛ ጢሞቴዎስ 3፥5 (አዲሱ መ.ት)


“They will act as if they are religious, but they will reject the power that could make them godly. You must stay away from people like that.”
2Tim 3:5 (NLT)


“For they hold a form of piety (true religion), they deny and reject and are strangers to the power of it . Avoid such people .”
2Tim 3:5 (AMP)



Join us
📚@Holy_scriptures📚
📚@Holy_scriptures📚
🀄️🀄️ሉን
' ==❀❀❀===❀❀❀==
የዕለቱ ጥቅስ
==❀❀❀===❀❀❀==
“መለያየትን የሚያነሣ ሰው ጠማማ እንዲሆን በራሱም ላይ ፈርዶ ኃጢአትን እንዲያደርግ አውቀህ፥ አንድ ጊዜ ሁለት ጊዜም ከገሠጽኸው በኋላ እንዲህ ከሚመስል ሰው ራቅ።”
(ቲቶ 3፥10-11)


Join us
📚@Holy_scriptures📚
📚@Holy_scriptures📚
🀄️🀄️ሉን
👤ፍጥረታዊ፣ ሥጋዊ እና መንፈሳዊ ሰው



ክፍል-6


🍇መንፈሳዊ ሰው


መንፈሳዊ ሰው (ግሪክ፡ “ኑማቲኮስ”፤ 1ቆሮ. 2፡15፤ 3፥1) ዳግም ልደት ያገኘን ሰው ያመለክታል፤ ይኸውም መንፈስ ቅዱስ ያደረበት ሰው ማለት ነው። ይህ ሰው አስተሳሰቡ መንፈሳዊ ስለሆነ፣ እግዚአብሔር የሚያስበውን ነገር ያስባል (1ቆሮ. 2፡11-13)፣ በእግዚአብሔርም መንፈስ ይኖራል (ሮሜ 8፡4-17፤ ገላ. 5፡16-26)። እንዲህ ዓይነቱ ግለሰብ በኢየሱስ ክርስቶስ ያምናል፤ በውስጡ ያደረውን የመንፈስ ቅዱስን ምሪት ለመከተል ይጥራል፤ ለሥጋ ስሜትና ለኀጢአት ተገዥ መሆንን ይቃወማል (ሮሜ 8፡13-14)።

የመንፈሳዊ ሰው መለያ ባህሪያት፦

1⃣ከእግዚአብሔር የተሰጣቸውን ነገር ይረዳሉ

“እኛ ግን ከእግዚአብሔር እንዲያው የተሰጠንን እናውቅ ዘንድ ከእግዚአብሔር የሆነውን መንፈስ እንጂ የዓለምን መንፈስ አልተቀበልንም።” ቁ.12

በርግጥ በእውነቱ አማኞች እንኳ እግዚአብሔርን በሙላት፣ በተጠናቀቀ መልኩ ሊረዱት አይችሉም፣ በዚህ በወደቀና ጊዜያዊ በሆነ አቋም፤ ግን ለደኅንነትና ለመልካም ኑሮ የሚያስፈልጋቸውን ነገሮች ሁሉ ያውቁና ይገነዘቡ ዘንድ ይችላሉ፣ በአብ መገለጥ በኩል፣ በወልድ አካልና ሥራ በኩል፣ እንዲሁም በመንፈስ ብርሃን በኩል። ሌላው ወሳኝ የሚሆነው፣ አማኞች መረዳት ያለባቸው፣ የእግዚአብሔር ጥበብ “በነጻ መሰጠቱን” ነው (ሮሜ. 8፡32)። እሱም የእግዚአብሔር ስጦታ ነው፣ ይሄውም በአምሳሉ ለፈጠራቸው ሰዎች ሁሉ ለመስጠት የሚሻው (ዘፍ. 1፡26-27)፣ አሁን ግን በዐመጸኝነታቸው ምክንያት ከእሱ ለራቁት (ማለትም፣ ዘፍጥረት 3)።

መንፈስ ቅዱስ ክርክር የሌለበት የመገናኛ መስመር ነው (ዮሐንስ 16፡8-14)። እሱም መንፈሳዊ እውነቶችን ይገልጣል፣ በክርስቶስ ባመኑት የሚያድረውን መንፈስ ለተቀበሉት።

2⃣የእግዚአብሔርን ፈቃድ ያውቃሉ ወይም በነገሮች መካከል ይፈርዳሉ።

“መንፈሳዊ ሰው ግን ሁሉን ይመረምራል” (ቁ. 15)

ይህ ሕግ-ነክ ቃል ሲሆን ከፍርድ በፊት ያለውን ጥብቅ ምርመራ ያሳያል (ሉቃስ 23:14፤ ሐዋ. 12:19፤ 24:8፤ 25:26፤ 28:18) ወይም አንድን ነገር በጥንቃቄ መመርመር (ማለትም፣ ቅዱስ ቃሉን፣ ሐዋ. 17:11፤ ምግብ፣ 1ቆሮ. 10:25፣27)። ይሄው ተመሳሳይ ቃል ቁ. 15 ላይ 2 ጊዜ ይከሰታል። በመንፈስ የተሞሉ አማኞች በሥጋዊም ሆነ በመንፈሳዊው ዓለም በሚገኙት ነገሮች ላይ በትክክል ሊፈርዱ ይችላሉ (ዘካ. 1:22-25 እና 2:2፣ እንዲሁም ደግሞ 14:29 እና 1ተሰ. 5:20-21።

3⃣የክርስቶስ ልብ አላቸው

“እኛ ግን የክርስቶስ ልብ አለን።” ቁ. 16

“እኛ” የሚለው ተውላጠ ስም አጽንዖታዊ ነው! ይሄም ሊያመለክት የሚችለው (1) ጳውሎስንና ጓደኞቹን፤ (2)ክርስቲያን ሰባኪዎችን፤ ወይም (3) የበሰሉ ክርስቲያኖችን ነው። ይህ ማለት ግን አማኞች ክርስቶስ የሚያውቀውን ሁሉ ያውቃሉ ማለት አይደለም፣ ነገር ግን መንፈስ ቅዱስ አዕምሯችንን ይከፍትልናል፣ ለእሱ አስተሳሰብ፣ እሱ ቅድሚያ ለሚሰጣቸው ነገሮች፣ ለእሱ ልብ (ሐሳብ) (ሮሜ 12፡2፤ ፊሊጵ. 2፡5)።


ይቀጥላል...



ምንጭ፦

👉 “ምሉእ ሕይወት መጽሐፍ ቅዱስ”፣ አዲሱ መደበኛ ትርጉም፣ ዋና አርታኢ፦ ዶናልድ ሲ. ስታምፕስ፣ ተባባሪ አርታኢ፦ ጄ. ዌስሊ አዳምስ

👉 “የጳውሎስ መልዕክቶች ለታወከችው ቤተ ክርስቲያን 1ኛ እና 2ኛ ቆሮንቶስ”፣ ቦብ አትሊ የትርጓሜ ፕሮፌሰር (የመጽሐፍ ቅዱስ ትርጓሜ)፣ የጥናት መመሪያ ተከታታይ ሐተታ አዲስ ኪዳን፣ ቅጽ 6 ዓለም አቀፍ የመጽሐፍ ቅዱስ ትምህርት፣ ማርሻል፣ ቴክሳስ 2002 (በ2011 የተከለሰ)



Join us
📚@Holy_scriptures📚
📚@Holy_scriptures📚
🀄️🀄️ሉን
' ==❀❀❀===❀❀❀==
የዕለቱ ጥቅስ
==❀❀❀===❀❀❀==
“የእግዚአብሔርን ምክር ሁሉ ነግሬአችኋለሁና፥ ምንም አላስቀረሁባችሁም።”
(ሐዋርያት 20፥27)


Join us
📚@Holy_scriptures📚
📚@Holy_scriptures📚
🀄️🀄️ሉን
👤ፍጥረታዊ፣ ሥጋዊ እና መንፈሳዊ ሰው



ክፍል-7


መንፈሳዊ ሰው መሆን ዝም ብሎ የሚመጣ ጉዳይ አይደለም።

“እግዚአብሔርን ለመምሰል ግን ራስህን አስለምድ።” (1ኛ ጢሞቴዎስ 4፥7)

ስለዚህ በአጭሩ መንፈሳዊ ሰው ለመሆን መንፈሳዊ እድገት ያስፈልጋል።

🌾መንፈሳዊ እድገት፦

➡️መንፈሳዊ ዕድገት በማይታየው ቅዱስ መንፈስ የተደገፈ የሚታይ ኑሮ ነው፡፡

➡️መንፈሳዊ ዕድገት ያመነ ሰው እምነቱን በሥራ የሚገልጥበት ሂደታዊ(ዘላቂነት ያለው) አኗኗር ነው፡፡

➡️መንፈሳዊ ዕድገት የመንፈሳዊ ሰው የከፍታ ምስጢር ነው፡፡

➡️መንፈሳዊ እድገት መንፈሳዊ ሰው በመንፈስ ቅዱስ በመታገዝ በመንፈስ ፍሬዎች የሚያጌጥበት የሕይወት ውበት ነው፡፡ ይህ ኑሮ ሰው እንዲጠቀምበት፥ እግዚአብሔር እንዲከብርበት በመለኮት ዕቅድ ቀድሞ የታሰበ ኑሮ ነው፡፡

➡️መንፈሳዊ ዕድገት የቅድስና መንገድ ነው፡፡

➡️መንፈሳዊ ዕድገት በግንዱ በክርስቶስ በመሆን ፍሬ የምናፈራበት አኗኗር ነው፡፡ ከግንዱ ተለይቶ ማፍራት አይቻልም፡፡

"እኔ የወይን ግንድ ነኝ እናንተም ቅርንጫፎች ናችሁ። ያለ እኔ ምንም ልታደርጉ አትችሉምና በእኔ የሚኖር እኔም በእርሱ፥ እርሱ ብዙ ፍሬ ያፈራል።" (ዮሐንስ 15:5)

በግንዱ ካልሆነ ድርቀት እንጂ እድገት አይኖረንም፡፡

➡️የመንፈሳዊ እድገት መሠረቱ በግንዱ ሆኖ ማፍራት ነው፡፡

➡️መንፈሳዊ እድገት ሰሞነኛነት አይደለም፡፡

➡️ መንፈሳዊ ሕይወት የማይቋረጥ ኑሮ ነው፡፡በየጥቂቱ የሚያድግ አኗኗር ነው፡፡ ቅዱስ ጴጥሮስ ይህን ኑሮ በሚገባ ተርኮታል፦

"ስለዚህም ምክንያት ትጋትን ሁሉ እያሳያችሁ በእምነታችሁ በጎነትን ጨምሩ፥ በበጎነትም እውቀትን፥ በእውቀትም ራስን መግዛት፥ ራስንም በመግዛት መጽናትን፥ በመጽናትም እግዚአብሔርን መምሰል፥ እግዚአብሔርንም በመምሰል የወንድማማችን መዋደድ፥ በወንድማማችም መዋደድ ፍቅርን ጨምሩ።" 2ጴጥ 1:5-10፡፡

 እስኪ ራሳችንን እንጠይቅ መንፈሳዊ ሕይወታችን እየጨመረ ነው ወይስ እየቀነሰ ነው? በቦታ እና በሁኔታዎች አይወስንም ??? በጊዜ ሂደት አልቀነሰም ??? መንፈሳዊ ሰው በመጨመር በማብዛት እና በመብዛት ፍሬው ይገለጣል፡፡መንፈሳዊ ዕድገት ክርስቶስን ወደ መምሰል የምናደርገው ጉዞ ነው፡፡

የመንፈሳዊ ዕድገት መሠረት፦

ሕንፃ ያለ መሠረት እንደማይመሠረት መንፈሳዊ ዕድገትም ያለ መሠረት አይወጠንም፡፡ የመንፈሳዊ ሕይወት ጽኑ መሠረት ኢየሱስ ክርስቶስ ነው፡፡ ጥሩ መሠረት ያለው ቤት ሞገድ እና ነፋስ እንደማይነቅለው በክርስቶስ ላይ ሥር ሰዶ በመታነጽ የመንፈሳዊ ዕድገት ጉዞ የወጠነ አማኝም በምንም ሁኔታ በፍጹም አይናወጽም፡፡ መሠረቱ ላይ ያልተተከለ፥ ራስ በሆነው ያልተጋጠመ ይህን ክፉ ዘመን አያልፍም፥ ነፋስ አቅጣጫ ያስቀይረዋል፡፡ተወዳጆች ሆይ፦ እምነት እና አላማችንን መሠረቱ ላይ እናድርግ፡፡የሁሉም መነሻ እና መድረሻ እርሱ ነውና፡፡

"የእምነታችንንም ራስና ፈጻሚውን ኢየሱስን ተመልክተን፥ በፊታችን ያለውን ሩጫ በትዕግሥት እንሩጥ።" (ዕብ 12:1-2)

በእድገት ላይ እንዳሉ እንደማንኛውም ነገሮች፣ አዲስ መንፈሳዊ ማንነትህ በእድገት ጎዳና ላይ ጉዞውን እንዲቀጥል አስተዋፅኦ የሚያደርጉ በርካታ ምክንያቶች ይኖራሉ፡፡ እነርሱም፦


1. የክርስቶስ ጌትነት
2. መጽሐፍ ቅዱስ
3. ጸሎት
4. ሕብረት
5. ምስክርነት
6. መታዘዝና ድርጊት

ቀልጣፋና ውጤታማ የእድገት ልምምድ የምትሻ ከሆነ እላይ ከተገለፁት ሁለቱ ወይም ሶስቱ ላይ ብቻ መደገፍ ሳይሆን ያለብህ ስድስቱንም በተመጣጣኝ ደረጃ መለማመድ ይኖርብሃል፡፡ እነዚህ ነገሮች በቅንጅት በመጠቀም እንዴት ‹‹የመብሰል ጉዞህን›› ስኬታማ ልታደርግ እንደምትችል ለማስረዳት፣ በዚህ ጥናት ውስጥ ‹‹የጎማ ምሳሌን›› እንጠቀማለን፡፡ እንዴት ከእግዚአብሔር እቅድ ጋር በመተባበር ማደግ እንደሚቻል በቀላሉ በማስረዳት ይህ መርጃ መሳሪያ ጠቃሚ ነው፡፡

1. የክርስቶስ ጌትነት

ኃይል፣ ከጎማው እምብርት (ማዕከል) ይነሳና በሽቦዎቹ መሃከል ከተሰራጨ በኃላ ለጎማው ጠርዝ ይደርሳል፡፡ በማናቸውም ጎማዎች ውስጥ የሚሆነው ነገር እንዲሁ ነው፡፡ የአንድ ክርስቲያን ማዕከላዊ የኃይል ምንጭ፣ በአማኙ ሕይወት ውስጥ በቅዱስ መንፈሱ አገልግሎት የሚገለጠው ኢየሱስ ክርስቶስ ነው፡፡

በመጀመሪያ ከዚህ በታች የቀረቡትን ጥቅሶች አንብብ፡፡
✔️ማቴዎስ 6፡33
✔️ዮሐንስ 12፡26
✔️ዮሐንስ 15፡4-7

⚠️ኢየሱስ ክርስቶስ የሕይወትህ አዳኝ እንዲሆን መጋበዝ አንድ ነገር ነው፡፡ ጌታህ እንዲሆንስ ጋብዘኸዋል? ካላደረግህ ለምን አሁን ጥቂት ጊዜ ወስደህ ይህንን አታደርግም?


ይቀጥላል...


ምንጭ፦

👉“የማይገታ እድገት”፣ በክሪስ አድሲት፣ ትርጉም አዳነው ዲሮ፣ በደራሲው ፈቃድ፣ ለግሬት ኮሚሽን አገልግሎት የተተረጎመ፣ 2003 ዓ.ም.

👉 michaelyemane.blogspot.com



Join us
📚@Holy_scriptures📚
📚@Holy_scriptures📚
🀄️🀄️ሉን
በብሉይ ኪዳን በአንበሶች ጉድጓድ የተጣለው ማን ነው?
Anonymous Quiz
74%
ሀ. ዳንኤል
2%
ለ. ሲድራቅ
1%
ሐ. ብልጣሶር
18%
መ. ሀ እና ሐ
5%
ሠ. ሁሉም
' ==❀❀❀===❀❀❀==
የዕለቱ ጥቅስ
==❀❀❀===❀❀❀==
“ስለዚህ ሕዝቡን በብዙ ሌላ ምክር እየመከራቸው ወንጌልን ይሰብክላቸው ነበር፤”
(ሉቃስ 3፥18)


Join us
📚@Holy_scriptures📚
📚@Holy_scriptures📚
🀄️🀄️ሉን
👤ፍጥረታዊ፣ ሥጋዊ እና መንፈሳዊ ሰው



ክፍል-8


2. መጽሐፍ ቅዱስ

በተፈጥሮ ህግ የማይመገብ ሰው ይራባል ፣ይደክማል፣ ይታመማል ፣ባለመመገቡ ከጸና ይሞታል። ቃሉን የማይመገብ ክርስትያን መንፈሳዊ ረሃብ (የፍቅር፣የትህትና ፣የበጎነት ፣የቅንነት ወዘተ…  ረሃብተኛ)፣ ድካም (ለፀሎት ፣ለአገልግሎት ፣ለፆም ወዘተ…  ደካማ)፣ ህመም ( ቃሉ ምንድነው ? መንፈሳዊነት ምንድነው ? ቤተክርስትያን ምንድናት ወዘተ…  የሚል ህመምተኛ )፣ ሞት (ያለእግዚአብሔርና ያለቃሉ የሚኖር ስም ያለው ነገር የሞተ ማንነት ያለው ይሆናል)።

"ጌታ ቸር መሆኑን ቀምሳችሁ እንደ ሆነ፥ ለመዳን በእርሱ እንድታድጉ አሁን እንደ ተወለዱ ሕፃናት ተንኰል የሌለበትን የቃልን ወተት ተመኙ።"
(1ኛ ጴጥሮስ 2:2-3)።

ቃሉ ለእድገታችን ጠቃሚ የሆነ ዋና ምግብ ነው፡፡በቃሉ በኩል እግዚአብሔር ለእኛ ያለውን የፈቃዱን ምስጢራት እናውቃለን፡፡ ስለዚህ እንደ ፈቃዱ የሆነ እድገት ይኖረናል፡፡ የቃሉ ወተት የሚያስፈልገን አሁን እንደ ተወለዱ ሕፃናት ነው፡፡ ወተት አሁን ለተወለዱ ሕፃናት የግድ አስፈላጊ ነው፡፡ ካደጉ በኋላ ግን ብዙ አማራጭ ይኖራቸዋል፡፡ መንፈሳዊ ሰው በዋናነት ሁልጊዜ የቃል ወተት ያስፈልገዋል፡፡ቃሉ የልጅነት ትዝታችን፥ የጉልምስና ትጥቃችን፥ የሽምግልና ወራት ኃይላችን ነው፡፡ ቃሉ የማያስፈልግበት ጊዜ የለም፡፡ ስለዚህ ሁልጊዜ የቃሉ ወይን ጠጅ የማይጎድልባቸው ማድጋዎች እንሁን፡፡ ያለ ቃሉ ድጋፍ መንፈሳዊ እድገት አይከናወንም፡፡ ሕፃናት ከእናታቸው የሚያገኙት ወተት ጤናማ እንደሚያደርጋቸው ሁሉ የጌታ ምክርም ጤናማ ዕድገት እንዲኖረን ያደርጋል፡፡

የእግዚአብሔር ቃል ለአዲሱ ተፈጥሮህ መንፈሳዊ ምግቡ ነው፡፡

‹‹…አሁን እንደ ተወለዱ ሕፃናት ተንኰል የሌለበትን የቃልን ወተት ተመኙ›› (1ጴጥሮስ 2፡2)

አንድ ህፃን የሚፈልገው ወተት ካልተሰጠው (ከማልቀስ በተጨማሪ) ምን የሚሆን ይመስልሃል? የእግዚአብሔር ቃል በሕይወትህ ላይ ያለው ተፅዕኖ ከዚህ በታች የቀረቡትን እያንዳንዱን ጥቅሶች መርምር፡፡ መጽሐፍ ቅዱስን ለማንበብ ጊዜ ስትሰጥ፣ ስትወያየውና በሕይወትህ ላይ ተግባራዊ ስታደርገው ምን አይነት ጥቅሞች እንደምታገኝ እነዚህ ጥቅሶች ይነግሩሃል፡፡

‹‹የዚህ ሕግ መጽሐፍ ከአፍህ አይለይ፣ ነገር ግን የተጻፈበትን ሁሉ ትጠብቅና ታደርግ ዘንድ በቀንም በሌሊትም አስበው፤ የዚያን ጊዜም መንገድህ ይቀናልሃል ይከናወንልሃልም።›› (ኢያሱ 1፡8)

‹‹የአምላኩ ሕግ በልቡ ውስጥ ነው፣ በእርምጃውም አይሰናከልም።›› (መዝሙር 37፡31)

‹‹ጕልማሳ መንገዱን በምን ያነጻል? ቃልህን በመጠበቅ ነው። በፍጹም ልቤ ፈለግሁህ፣ ከትእዛዝህ አታርቀኝ። አንተ እንዳልበድል፣ ቃልህን በልቤ ሰወርሁ።›› (መዝሙር 119፡9-11)

‹‹ሕግህ ለእግሬ መብራት፣ ለመንገዴ ብርሃን ነው።›› (መዝሙር 119፡105)

‹‹በእኔ ብትኖሩ ቃሎቼም በእናንተ ቢኖሩ የምትወዱትን ሁሉ ለምኑ ይሆንላችሁማል።›› (ዮሐንስ 15፡7)

‹‹የእግዚአብሔር ሰው ፍጹምና ለበጎ ሥራ ሁሉ የተዘጋጀ ይሆን ዘንድ፣ የእግዚአብሔር መንፈስ ያለበት መጽሐፍ ሁሉ ለትምህርትና ለተግሣጽ ልብንም ለማቅናት በጽድቅም ላለው ምክር ደግሞ ይጠቅማል።›› (2ጢሞቴዎስ 3፡16-17)

“ኢየሱስም ያመኑትን አይሁድ፦ እናንተ በቃሌ ብትኖሩ በእውነት ደቀ መዛሙርቴ ናችሁ፤”
(ዮሐንስ 8፥31)



ይቀጥላል...


ምንጭ፦

👉“የማይገታ እድገት”፣ በክሪስ አድሲት፣ ትርጉም አዳነው ዲሮ፣ በደራሲው ፈቃድ፣ ለግሬት ኮሚሽን አገልግሎት የተተረጎመ፣ 2003 ዓ.ም.

👉 michaelyemane.blogspot.com



Join us
📚@Holy_scriptures📚
📚@Holy_scriptures📚
🀄️🀄️ሉን
' ==❀❀❀===❀❀❀==
የዕለቱ ጥቅስ
==❀❀❀===❀❀❀==
"በጥፋትና በመፈራረስ፣ በችግርና በሽብር ተሠቃየን። የእንባ ጐርፍ ከዐይኔ ፈሰሰ፤ ሕዝቤ አልቋልና።"
ሰቆ. ኤር. 3፥47-48 (አዲሱ መ.ት)


Join us
📚@Holy_scriptures📚
📚@Holy_scriptures📚
🀄️🀄️ሉን
በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ "በመጀመሪያ" በማለት የሚጀምረው መጽሐፍ የቱ ነው?
Anonymous Quiz
48%
ሀ. ዘፍጥረት
1%
ለ. ራእይ
11%
ሐ. ዮሐንስ
39%
መ.ሀ እና ሐ
' ==❀❀❀===❀❀❀==
የዕለቱ ጥቅስ
==❀❀❀===❀❀❀==
“እኔ የምወዳቸውን እገሥጻለሁ፤ እቀጣለሁም። ስለዚህ ትጋ፤ ንስሓም ግባ።”
ራእይ 3፥19 (አዲሱ መ.ት)


Join us
📚@Holy_scriptures📚
📚@Holy_scriptures📚
🀄️🀄️ሉን
👤ፍጥረታዊ፣ ሥጋዊ እና መንፈሳዊ ሰው



ክፍል-9


3. ጸሎት

ለምን እንጸልያለን?

-ፈቃዱን ለማወቅ ዘፍ 24:11-14

-ለማመስገን መዝ 12:6

-ወደፈተና እንዳንገባ ማቴ 26:41

-ከክፉ ለመጠበቅ ማቴ 6:13

-ዲያብሎስን ለመርታት ማቴ 17:21

እኛ መሥራት ያልቻልነውን እግዚአብሔር እንዲሠራልን የምንጠይቅበት መሳሪያ ጸሎት ይባላል፡፡ ነገር ግን መጸለይ ባለመቻላችን የጸሎትን ኃይል መጠቀም አልቻልንም፡፡ ባለመጸለያችን ከነችግራችን እንኖራለን። ጸሎት የሕይወታችን እንቅስቃሴ በጌታ ፈቃድ እንዲመራ ፈቃደኝነታችንን የምናሳውቅበት መንገድ ነው፡፡ ለመንፈሳዊ ዕድገት እጅግ ቁልፍ መሳሪያ ነው፡፡ ጸሎት የማይቋረጥ ድርጊት ነው፡፡ ጸሎት በእኛ እና በእግዚአብሔር መካከል ያለ የግንኙነት መስመር ነው፡፡ መጸለይ ካቆምን ከአገልግሎት መስጫ ክልል ውጭ እንሆናለን፡፡ በብዙ ጉዳዮች ስለተያዝን የጸሎት ጊዜና አቅም አጥተናል፡፡ ስለዚህ ለመጸለይ እንኳ ጸሎት ያስፈልጋል፡፡ ጸሎት የመንፈስ ብልጽግና ያመጣል፤ ኃይል ያጎናጽፋል፤ በጸጋ ያሳድጋል፡፡

ጸሎታችን፦ በእምነት፥ በመንፈስ፥ በስሙ፤ እንደ ፈቃዱ መሆን አለበት፡፡ ያለ ጸሎት የመንፈሳዊ ዓለም ተጋድሎ አይቻልም፡፡ ድል የኛ እንዲሆን፥ እንድናድግ ጸሎት ያስፈልገናል፡፡ ጸሎታችን ምስጋናን፥ የኃጢአት ይቅርታን፣ምልጃን እና ልምናን ማካተት አለበት፡፡ (1ጢሞ 2:13) ፡፡

እግዚአብሔር የልጆቹን ጸሎት በደስታ ይሰማልና ጸሎት ብዙ ኃይል አለው፤ 1ጴጥ. 3፥12፤ ያዕ. 5፥17። አለመጸለይ ኃጢአት ነው፤ 1ሳሙ. 12፥23። ጸሎታችን እንደሚከተለው መሆን አለበት፦

🔑በእምነት፤ ዕብ. 11፥6።

🔑በኢየሱስ ስም፤ ዮሐ. 14፥6፡13፤ 16፥23።

🔑እንደ እግዚአብሔር ፈቃድ፤ 1ዮሐ. 5፥14-15።

🔑በመንፈስ ቅዱስ፤ ይሁዳ 20።

🔑ንስሐ በመግባት፤ መዝ. 66፥18፤ ኢሳ. 59፥1-2፤ ማቴ. 5፥23-24።

🔑ይቅር ባይ መሆን፤ ማቴ. 6፥14-15።

🔑ባለመሰልቸት፤ ሉቃ. 11፥5-13።

🔑በነገር ሁሉ፤ ፊል. 4፥6።

🔑ስለ ሰው ሁሉ፤ 1ጢሞ. 2፥1-4።

🔑በማንኛውም ጊዜ ሁሉ፤ 1ተሰ. 5፥17።


ይቀጥላል...


ምንጭ፦

👉“የመጽሐፍ ቅዱስ መዝገበ ቃላት”፣ የኢትዮጵያ መጽሐፍ ቅዱስ ማኅበር

👉michaelyemane.blogspot.com



Join us
📚@Holy_scriptures📚
📚@Holy_scriptures📚
🀄️🀄️ሉን