ቅዱሳት መጻሕፍት
6.53K subscribers
921 photos
33 videos
264 files
664 links
በዚህ ቻናል

👉ቅዱሳት መጻሕፍት ይጠናሉ::
👉መጽሐፍ ቅዱሳዊ ትምህርቶች ይቀርባሉ::
👉 ለቅዱሳት መጽሐፍት ጥናት የሚያግዙ መጻሕፍት ይለቀቃሉ።

⭐️⭐️⭐️⭐️⭐️

@Holy_scriptures
Download Telegram
" የሚያዝኑ ብፁዓን ናቸው፥ መፅናናትን ያገኛሉና።"
(የማቴዎስ ወንጌል 5:4)

"ብፁዕ" ማለት ምን ማለት እንደ ሆነ በማቴ.5:3 ላይ የተማርነውን ክፍል ይመልከቱ::

💥በዚህ ቁጥር ንጉሡ ኢየሱስ "የሚያዝኑ ደስተኞች ናቸው::" በማለት አወዛጋቢና የሚቃረን የሚመስል ነገር ይናገራል:: በዓለም አስተሳሰብ ሰው ደስተኛ ይሆን ዘንድ በቅድሚያ ደስ የሚያሰኘውን ነገር እንዲያደርግ ይመከራል:: በእግዚአብሔር መንግስት ግን በቅድሚያ በማዘንህ በኋላ ትጽናናለህ እንዲሁም ትደሰታለህ:: " እንደ እግዚአብሔር ፈቃድ የሆነ ኀዘን ጸጸት የሌለበትን፥ ወደ መዳንም የሚያደርሰውን ንስሐ ያደርጋልና፤ የዓለም ኀዘን ግን ሞትን ያመጣል።"
(2ኛ ቆሮ. 7:10)

💥በእግዚአብሔር መንግሥት ውስጥ በእግዚአብሔር የሆነ ሃዘን በእውነት ወደሚያጽናናው ወደ እርሱ በንስሐ እንድንቀርብ ያደርገናል:: እንዴት ከተባለ "ማዘን" ማለት ለእግዚአብሔር የጽድቅ መለኪያ ለመንግስቱ ኃይል የማንበቃ መሆናችንን በመረዳት ስለራሳችን ሆነ ስለሌሎች ድካም በእጅጉ መጸጸትና ማዘንን ያመለክታል(መዝ. 119:136):: ማዘን ሲባል እግዚአብሔር በሚያዝንባቸው ነገሮች አብሮ ማዘን:: የእግዚአብሔርን ስሜት መጋራትን ያመለክታል:: ስለራስ ሆነ ስለሌሎች ኃጢአት ከእግዚአብሔር ጋር ተባብሮ በእግዚአብሔር ፊት ማልቀስ መባረክ ነው:: ምክንያቱም በፍቅር የማደግ ምልክት ነውና(1ኛ ቆሮ. 13:6):: የመንግስቱ ዜጎች ለዚህ ሕይወት ተመርጠዋል:: እንዲህ መኖርም ይጠበቅባቸዋል::



📜ምንጭ:- የተለያዩ የመጽሐፍ
ቅዱስ ማብራሪያ መጽሐፍት



Join us
@Holy_scriptures
@Holy_scriptures
🔺🀄️🀄️ሉን🔺
. 🔱የመንፈሳዊ ራብ በረከት


መንፈሳዊ ራብ ጌታን መናፈቅን፣እሱን ለማግኘት መጓጓትን፣ወደ እሱ ለመጠጋት ማሰብን ወዘተ ያመለክታል፡፡


በግለሰብ ይሁን በወል ደረጃ መንፈሳዊ ራብና ጥማት ለእግዚአብሔር መለኮታዊ ጉብኝት እጅግ ወሳኝ ናቸው፡፡አውነተኛ የሆነ መንፈሳዊ ራብና ጥማት እግዚአብሔርን እንድንሻው፣እንድንፈልገውና እንድንጠጋው ኃይል ይሆኑናል፡፡ ቃሉ “ጽድቅን የሚራቡና የሚጠሙ ብፁዓን ናቸው” (ማቴዎስ 5፡6) የሚለን ለዚህ ነው፡፡ “ብፁዓን” የሚለውን ቃል ድረ-ገጽ ላይ ያገኘሁት አምሊፋይድ መጽሐፍ ቅዱስ ደስተኞች፣በመንፈስ ባለጸጋ የሆኑ፣የረኩ፣የተባረኩ ወዘተ ብሎ ነው የሚገልጸው፡፡በነዚህ ቃሎችም መንፈሳዊ ራብ ሊያመጣ የሚችለውን የበረከት ሰፊነት ተገንዝቤአለሁ፡፡


ሐና መንፈሳዊ ራብ ያላቸው ሰዎች በጌታ ፊት ዋጋ ያላቸውና የማይረሱ እንደ ሆነ ስትናገር “ተርበው የነበሩ ከራብ አርፈዋል” (1 ሳሙኤል 2:5) ብላለች፤ አምላኳ የሚያረካ፣የሚያጠግብና የሚያሳርፍ መሆኑን በማወደስ፡፡


መንፈሳዊ ራብ በራሱ ትልቅ በረከት ነው፤ወደ ፊት እንድንዘረጋ፣እንድንቃትት፣ፊቱን አንድንፈልግ ያደርገናል፡፡የምር የሆነ መንፈሳዊ ራብ የሚመነጨው ደግሞ ያለንበትን ሁኔታ የእግዚአብሔር መንፈስ ሲያሳየንና ያለንበትን አዘቅት ስንጠላው ነው፡፡መንፈሳዊ ራብ ይጐተጉተናል፣አያስተኛንም፤ቃሉ“የሠራተኛ ራብ ለርሱ ይሠራል አፉ ይጐተጉተዋል” (ምሳሌ 16፡26) ይላልና ፡፡“ለርሱ ይሠራል” የሚለውን አስምሩልኝ፡፡ለማን? ለርሱ! አያስተኛውማ! ሳያገኝ አያሳርፈውማ! ለዚህ ነው መንፈሳዊ ራብ በራሱ የሚጓጓለት በረከት የሆነው፡፡


መንፈሳዊ ራብ ልክ እንደ ኤርምያስ ጌታን በትጋት እንድንፈልገው ያደርገናል፡፡ኤርምያስ ከብዙ ፍለጋ በኋላ ሕይወት የሚሰጠውን፣መንፈስ የሆነውን፣የጊዜውን ቃል ሲያገኝ እንዲህ ብሎ ተናገረ፡-


▪️“ቃልህ ተገኝቷል እኔም በልቼዋለሁ፤አቤቱ የሠራዊት ጌታ ሆይ በስምህ ተጠርቻለሁና ቃል ሐሤትና የልብ ደስታ ሆነኝ”(ኤርምያስ 15፡16)


▪️ከዚህ ምንባብ በጥቂቱ እንደምንረዳው፣ኤርምያስ ቃሉን በትጋትና በተራበ መንፈስ ሲፈልግ የቆየ ይመስላል፡፡ባገኘውም ጊዜ ከነበረው ናፍቆት የተነሣ ለመብላት ፋታ ያገኘም አይመስልም፡፡እናም እስከሚረካና በሐሤት እስኪጥለቀለቅ ድረስ በላው፡፡


ንጉሥ ዳዊት እውነተኛ መንፈሳዊ ራብ ያላቸውን ሰዎች እግዚአብሔር እንዴት እንደሚባርክ ሲገልጽ፣ “የተራበችን ነፍስ አጥግቦአልና፤የተራቈተችንም ነፍስ በበረከት ሞልቶአልና”(መዝ 107፡9) ብሎ ተናግሯል፡፡አዎ መንፈሳዊ ራብ የገባበት ሰው ሲቆፍር፣ሲፈልግ፣ሲቃትት ወዘተ ያድራል፤ዕረፍት አይኖረውም ያንን ራብ ሳያስታግስ፡፡ራቡ ጐትጓች ነውና፣አያስተኛውምና፡፡


🔔ይህን መንፈሳዊ ራብ የሚያቀጣጥሉ ሦስት የታወቁ ነገሮች አሉ፡፡እነሱም፡-


1⃣የእግዚአብሔር ቃል አብዝቶ ማጥናትና ማሰላሰል

2⃣ደጋግሞ ለረጅም ጊዜ መጾም

3⃣በጌታ ፊት በውሳኔ መውደቅ


ጌታ እንደ ተስፋ ቃሉ መንፈሳዊን ነገር በሚራቡና በሚጠሙ ሰዎች ሕይወት፣ ከብዙ መሻት በኋላ ሲገለጥ አስደናቂ ነገር የሚሆነው፡፡ለዚህ ነው ሰፋ ካለ መንፈሳዊ መነቃቃት በፊት በቤተ ክርስትያን እርሱን የሚራቡና የሚጠሙ፣እናም በጓዳ እሱን የሚሹና የሚፈልጉ ሰዎች አስቀድሞ የሚያስነሣው፡፡


አንድ ክርስትያን ይህ ራብ በውስጡ ለረጅም ጊዜ ከጠፋ፣ለመውደቅ እየተንሸራተተ እንደ ሆነ ሊያስብ ይገባዋል የሚል አመለካከት አለኝ፡፡


በጌታ ቤት በቆየሁበት ዘመን መንፈሳዊ ራብ የሚያስደንቅ ኡደት (positive cycle) እንዳለው ተገንዝቤአለሁ፡፡መንፈሳዊ ራቡ ልባችንን ባሰፋነው መጠን ያድጋል፡፡ አብዝተን እንድንቃትት ያደርገናል፡፡አብዝተን ስንጸልይ ደግሞ ጸሎቱ ሌላ ከፍ ያለ መንፈሳዊ ራብን ይወልዳል፡፡የሚመጣው መንፈሳዊ ራብ ደግሞ አብዝተን እንድንጸልይ ያደርገናል፡፡ወገኖቼ አንዱ አንዱን እየጨመረ ማብቂያ የሌለው አስደናቂ ነገር ውስጥ ነው የምንገባው፤እኛ በሥጋዊ አካሄዶች መንፈስን እስካላጠፋን ድረስ፡፡


ጌታ ሆይ ከፍ ያለ አንተን የሚሻና የሚፈልግ ልብ ስጠን !  



📜 ምንጭ:-Divine Wisdom4


Join us
@Holy_scriptures
@Holy_scriptures
🔺🀄️🀄️ሉን🔺
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ውድ የቻናላችን ቤተሰቦች እስካሁን ከእኛ ጋር ስላላችሁ እና በማጋራት (ሼር) በማድረግ እየተባበራችሁ ስለሆነ እናመሰግናለን:: በቻናሉ ከተጠቀማችሁ ለዘመድ ጓደኛ ሼር በማድረግ ተባበሩን:: በተጨማሪም በፌስቡክ በተመሳሳይ ስም(ቅዱሳት መጽሐፍት) ያገኙናል::
አሳብ አስተያየት ካላችሁ በ @fasik137 እና @yididii

Join us
@Holy_scriptures
@Holy_scriptures
🔺🀄️🀄️ሉን🔺
" የዋሆች ብፁዓን ናቸው፥ ምድርን ይወርሳሉና።"
(የማቴዎስ ወንጌል 5:5)


Amplified Bible
Blessed (happy, blithesome, joyous, spiritually prosperous--with life-joy and satisfaction in God's favor and salvation, regardless of their outward conditions) are the meek (the mild, patient, long-suffering), for they shall inherit the earth!



The Message...
"You're blessed when you're content with just who you are - no more, no less. That's the moment you find yourselves proud owners of everything that can't be bought.

Join us
@Holy_scriptures
@Holy_scriptures
🔺🀄️🀄️ሉን🔺
" የዋሆች ብፁዓን ናቸው፥ ምድርን ይወርሳሉና።"
(የማቴዎስ ወንጌል 5:5)


"ብፁዕ" ማለት ምን ማለት እንደ ሆነ በማቴ.5:3 ላይ የተማርነውን ክፍል ይመልከቱ::

" የዋሆች ብፁዓን ናቸው፥ ምድርን ይወርሳሉና።" ለመሆኑ የዋህ ማለት ምን ማለት? የዋህ የሚለው በግሪኩ "ትሁት" ይለዋል:: እናም "ትሁት" ተብሎ የተተረጎመው ቃል በግሪኮች ዘንድ የተገራ ፈረስ ለማመልከት ያገለግል ነበር:: በአጭሩ ከቁጥጥር ስር የዋለ ኃይልን ያሳያል:: ወይም የዋህነት ነገሮችን በራሳችን መንገድ ከማከናወንና የምንፈልገውን የማያደርጉትን ከመቃወም ይልቅ በገር መንፈስ መመላለስ ነው::

ሰው የዋህ እንዴት ሊሆን ይችላል?

1⃣በመንፈሱ ደሃ ሲሆን(ማቴ.5:3)

2⃣ስለኃጢአቱ ሲያዝን(ማቴ.5:4)

3⃣እምነቱን በኢየሱስ ላይ ሲያደርግ

የየዋህ ሰው ምልክቶች

💠ለራሱ መብት ወይንም ከሌሎች
ይልቅ ለራሱ ቅድሚያ አይሰጥም::

💠ሌላ ሰው ስህተት ሲፈጽምበት
አይከፋም::

💠ለራሱ ክብር ግድ የለውም::

💠ራሱን ነጻ ለማውጣት አይከራከርም::

💠የሰራውን ኃጢአት ለመደበቅ
ምክንያት አያበዛም::

💠ሰውን መበቀል አይፈልግም::(ሮሜ.
12:19)

💠ሁል ጊዜ ለመማር ፈቃደኛ ነው::

💠በራሱ ፈቃድ ለመመራት
አይፈልግም::

ሰው የዋህ ከሆነ ምን ያገኛል?

"ምድርን ይወርሳል::" ስለዚህ የዋሆች የተባረኩ ናቸው:: ምን አይነት ምድር ነው የሚወርሱት? ከተባለ በመንግሥተ ሰማይ ንጉሡ በሙሉ ስልጣን የሚገዛትን አዲስ ምድር ነው የሚወርሱት:: ልጅ ከሆነ ደግሞ ወራሽ ነውና የዋሆች የመንግስቱ ዜጎች የንጉሡ ልጆች ናቸው::



📜ምንጭ:- የተለያዩ የመጽሐፍ
ቅዱስ ማብራሪያ መጽሐፍት



Join us
@Holy_scriptures
@Holy_scriptures
🔺🀄️🀄️ሉን🔺
🛐ትህትና

ከእግዚአብሄር ጋር ለመኖርና አሸናፊ ለመሆን ትህትና እጅግ አስፈላጊ ባህሪ ነው፡፡ ካለ ትህትና ከእግዚአብሄ ጋር እንጣላለን፡፡ እግዚአብሄር ከእኛ ወገን አይሆንም፡፡ እንዲያውም እግዚአብሄር ትዕቢተኛውን ይቃወማል፡፡

"ነገር ግን ጸጋን አብልጦ ይሰጣል፤ ስለዚህ፦ እግዚአብሔር ትዕቢተኞችን ይቃወማል፥ ለትሑታን ግን ጸጋን ይሰጣል ።" ያዕቆብ 4፡6

ትህትና ይህን ያህል አስፈላጊ ከሆነ ትህትና ግን ምንድነው ብለን መጠየቅ ጥበብ ነው፡፡ ትህትናን በደንብ ልንማረውና ልናጠናው ተግተንም ልንለማመደው የሚገባ የተወደደ ባህሪ ነው፡፡ ሰዎች ትህትና ብለው የሚያደርጉዋቸው ብዙ ነገሮች አሉ፡፡ እውነተኛ ትህትና ግን ምንድነው፡፡

♻️ትህትና ለሁሉም ሰው ያለ አክብሮት ነው፡፡ ትሁት ሰው ለወገኔ ይጠቅማል በማለት አንዱን ከሌላው ሰው በወገናዊነት አያበላልጥም፡፡ ትሁት ሰው ለሁሉም ከፍ ያለ አክብሮት ያለው ሰው ሲሆን ሁሉንም ለማገልገልና ለመጥቀም የተዘጋጀ ነው፡፡

"ለወገኔ ይጠቅማል በማለት ወይም በከንቱ ውዳሴ ምክንያት አንድ እንኳ አታድርጉ::" ፊልጵስዩስ 2፡3

♻️ትሁት ሰው ሌላው ሰው ከእርሱ እንደሚሻል በቅንነትና በእውነት የሚያምን ነው፡፡ ትሁት ሰው ራሱን ብቻ አስፈላጊ አድርጎ የማይመለከት ሰው ነው፡፡ ትሁት ሰው የሰውን ሁሉ አስፈላጊነት የሚረዳ ሰው ነው፡፡ ትሁት ሰው በሌላው ሰው ስጦታ ጥሪና ጠቃሚነት የሚያምን ነው፡፡

"ነገር ግን እያንዳንዱ ባልንጀራው ከራሱ ይልቅ እንዲሻል በትሕትና ይቍጠር::" ፊልጵስዩስ 2፡3

♻️ትሁት ሰው የራሱን ብቻ የማይፈልግ ሰው ነው፡፡ ትሁት ሰው ሌላውንም የሚጠቅመውን ነገር ለማድረግ የሚፈልግ ሰው ነው፡፡ ትሁት ሰው ራስ ወዳድ አይደለም፡፡ ትሁት ሰው ለሌላው ጥቅም በትጋት የሚሰራ ሰው ነው፡፡

"እያንዳንዱ ለራሱ የሚጠቅመውን አይመልከት፥ ለባልንጀራው ደግሞ እንጂ" ፊልጵስዩስ 2፡4

♻️ትህትና እንደ ክርስቶስ ራስን አዋርዶ መኖር ነው፡፡ የሰው ትህትና የሚጀምረው ከሃሳብ ነው፡፡ ሰው ገና በሃሳብ ደረጃ ራሱን ካላዋረደ በትህትና ሊመላለስ አይችልም፡፡ ትሁት ሰው የትህትና መልክ ብቻ ሳይሆን የትህትና ሃሳብና ውሳኔ ያለው ነው፡፡

"በክርስቶስ ኢየሱስ የነበረ ይህ አሳብ በእናንተ ዘንድ ደግሞ ይሁን።" ፊልጵስዩስ 2፡5

♻️ከኢየሱስ የምንማረው ትሁት ሰው ለደረጃ ግድ እንደሌለው ነው፡፡ ትሁት ሰው ስለደረጃ አይጣላም አይጨቃጨቅም፡፡ ትሁት ሰው ትኩረቱ ማገልገል ሰውም መጥቀም በሰው ላይ ዋጋን መጨመር ሰውን ማንሳት ላይ እንጂ ስለስምና ስለስልጣን ወይም ጥቅም አይደለም፡፡ ትሁት ሰው የትም ማገልገል ስለሚችል መቼም ለመውረድ የተዘጋጀ ነው፡፡

"እርሱ በእግዚአብሔር መልክ ሲኖር ሳለ ከእግዚአብሔር ጋር መተካከልን መቀማት እንደሚገባ ነገር አልቈጠረውም፥" ፊልጵስዩስ 2፡6

♻️ትሁት ሰው እግዚአብሄርም እንዲያዋርደው የማያደርግ ቀድሞ ራሱን የሚያዋርድ ነው፡፡ ትሁትን ሰው የምናውቀው ሁኔታ ስላልተመቸው በመዋረዱ ሳይሆን ከፍ የሚያደርግ ሁኔታ እያለ በራሱ ፈቃድ ራሱን የሚያዋርድ ሰው ነው፡፡

♻️ትሁት ሰው ሰዎችን ለመጥቀም በምድር ላይ እንዳለ የሚያውቅ ሰው ሲሆን ሰዎች ሲጠቀሙበት እንደ እድል እንጂ እንደ ሽንፈት የማይቆጥር ሰው ነው፡፡ ትሁት ሰው ሰዎች እንደተጠቀሙበት የሚሰማውን አፍራሽ ስሜት የማይቀበል ሰዎች እንዲጠቀሙበት የሚፈቅድ የባሪያ ልብ ያለው ለራሱ የማይሰስት ሰው ነው፡፡

"ነገር ግን የባሪያን መልክ ይዞ በሰውም ምሳሌ ሆኖ ራሱን ባዶ አደረገ፥" ፊልጵስዩስ 2፡7

♻️ትሁት ሰው ነገሮችን ካደረገ በኋላ ክፍያውን የማይተምን በትህትናው የማይመካ ስላደረገው ስራ ዋጋውን ራሱ የማይተምን ሃላፊነቱን ብቻ እንደተወጠ የሚሰማው ሰው ነው፡፡ ትሁት ሰው ምንጩ እግዚአብሄር እንደሆነ የሚረዳ እንካ በእንካ አገልግሎት የሌለው ሰው ነው፡፡

"እንዲሁ እናንተ ደግሞ የታዘዛችሁትን ሁሉ ባደረጋችሁ ጊዜ፦ የማንጠቅም ባሪያዎች ነን፥ ልናደርገው የሚገባንን አድርገናል በሉ።" ሉቃስ 17፡10

♻️ትሁት ሰው ማንነቱን ጠንቅቆ የተረዳ ፣ ክብሩን የሚያውቅ ፣ የእርሱ ዝቅ ብሎ ማገልገል ምንም እንደማያዋርደው የሚያውቅ ሰው ነው፡፡ ትሁት ሰው በእግዚአብሄር ካለው ክብር እርሱን ሊያዋርደው የሚችል ምንም ነገር እንደሌለ የተረዳ ነው፡፡

"ኢየሱስ አብ ሁሉን በልጁ እንደ ሰጠው ከእግዚአብሔርም እንደ ወጣ ወደ እግዚአብሔርም እንዲሄድ አውቆ፥ ከእራት ተነሣ ልብሱንም አኖረ፥ ማበሻም ጨርቅ ወስዶ ታጠቀ፤ በኋላም በመታጠቢያው ውኃ ጨመረ፥ የደቀ መዛሙርቱንም እግር ሊያጥብና በታጠቀበትም ማበሻ ጨርቅ ሊያብስ ጀመረ።" ዮሐንስ 13፡3-5

"ለወገኔ ይጠቅማል በማለት ወይም በከንቱ ውዳሴ ምክንያት አንድ እንኳ አታድርጉ፥ ነገር ግን እያንዳንዱ ባልንጀራው ከራሱ ይልቅ እንዲሻል በትሕትና ይቍጠር፤ እያንዳንዱ ለራሱ የሚጠቅመውን አይመልከት፥ ለባልንጀራው ደግሞ እንጂ። በክርስቶስ ኢየሱስ የነበረ ይህ አሳብ በእናንተ ዘንድ ደግሞ ይሁን። እርሱ በእግዚአብሔር መልክ ሲኖር ሳለ ከእግዚአብሔር ጋር መተካከልን መቀማት እንደሚገባ ነገር አልቈጠረውም፥ ነገር ግን የባሪያን መልክ ይዞ በሰውም ምሳሌ ሆኖ ራሱን ባዶ አደረገ፥ በምስሉም እንደ ሰው ተገኝቶ ራሱን አዋረደ፥ ለሞትም ይኸውም የመስቀል ሞት እንኳ የታዘዘ ሆነ።" ፊልጵስዩስ 2፡3-8



🗞ምንጭ:- አብይ ዋኩማ


Join us
@Holy_scriptures
@Holy_scriptures
🔺🀄️🀄️ሉን🔺
. 👑ኢየሱስ እና ትህትና

ኢየሱስ ለእኛ ሰው ሆኖ ወደምርድ ስለመጣ ፍፁም ምሳሌያችን ነው፡፡ ማንንም ባንከተል ኢየሱስን መከተል አለብን፡፡ ማንም ምንም የሚጎድለው ባህሪ ቢኖር ኢየሱስ በባህሪው ፍፁም ነው፡፡ ኢየሱስ ሙሉ ለሙሉ ልንከተለው የምንችለው አስተማማኝ ምሳሌያችን ነው፡፡

እኛም እንድንከተለው ከታዘዝነው የኢየሱስ ባህሪያት አንዱ ትህትናው ነው፡፡ ኢየሱስ ትሁት ነው፡፡ ከኢየሱስ ትህትና ብዙ ነገሮችን መማር እንችላለን፡፡

♻️የኢየሱስ ትህትና የመነጨው ራሱን ከማወቁ ነው፡፡ ሰው ትሁት መሆን ካቃተው የበታችነት ስሜት እየተሰቃየ ነው ማለት ነው፡፡ ሰው የበታችነት ስሜት ካለበት ያንን ለማካካስ ራሱን ይኮፍሳል ትእቢተኛም ይሆናል፡፡ በእግዚአብሄር ዘንድ ያለውን የክብር ቦታ የተረዳ ሰው ግን እርሱን ሊያዋርደው የሚችል ምንም ዝቅታ እንደሌለ ስለሚያምን ራሱን ማዋረድ አይቸግረውም፡፡ ስለማንነቱ እርግጠኛ ካልሆነ ሁልጊዜ በትእቢት ይነፋል፡፡

"ኢየሱስ አብ ሁሉን በልጁ እንደ ሰጠው ከእግዚአብሔርም እንደ ወጣ ወደ እግዚአብሔርም እንዲሄድ አውቆ፥ ከእራት ተነሣ ልብሱንም አኖረ፥ ማበሻም ጨርቅ ወስዶ ታጠቀ፤ በኋላም በመታጠቢያው ውኃ ጨመረ፥ የደቀ መዛሙርቱንም እግር ሊያጥብና በታጠቀበትም ማበሻ ጨርቅ ሊያብስ ጀመረ።" ዮሐንስ 13፡3-5

♻️ትህትና ከላይ ከላይ የምናሳየው ሳይሆን የልብ ጉዳይ ነው፡፡ ሰው በልቡ ትእቢተኛ ሆኖ በአንደበቱ የትህትና ቃሎችን ተለማምዶ ሊናገራቸው ይችላል፡፡ ሰው በልቡ ትእቢተኛ ሆኖ በአካሄዱ ትሁት ሊመስል ይችላል፡፡ እውነተኛው ትህትና የልብ ትህትና ነው፡፡ እወነተኛው ትህትና ማንም ሳይሰማን በምንናገረው ነገር ይታወቃል፡፡ የልብ ትህትና ማንም በማያየን ጊዜ በምናደርገው ነገር ይታያል፡፡

"ቀንበሬን በላያችሁ ተሸከሙ ከእኔም ተማሩ፥ እኔ የዋህ በልቤም ትሑት ነኝና፥ ለነፍሳችሁም ዕረፍት ታገኛላችሁ፤" ማቴዎስ 11፡29

♻️ትሁት ሰው ስለ ደህንነቱና ስለ ማግኘቱ በእግዚአብሄር ይታመናል፡፡ ትሁት ሰው ለመተው ለመልቀቅ ዝግጁ ነው፡፡ ትሁት ሰው የራሱ ክብር ሳይሆን የሌላውን ጥቅም ያስቀድማል፡፡ ትሁት በሚሰጠው በእግዚአብሄር ስለሚታመን ለማጣት ዝግጁ ነው፡፡ ትህትና የማይገባንን ሳይሆን የሚገባንን መተው ነው፡፡ ትህትና ንጉስ በአህያ ውርንጭላ ሲሄድ ነው፡፡

"ለጽዮን ልጅ፦ እነሆ፥ ንጉሥሽ የዋህ ሆኖ በአህያ ላይና በአህያይቱ ግልገል በውርንጫይቱ ላይ ተቀምጦ ወደ አንቺ ይመጣል በሉአት ተብሎ በነቢይ የተነገረው ይፈጸም ዘንድ ይህ ሆነ።" ማቴዎስ 21፡4-5

"ተጨነቀ ተሣቀየም አፉንም አልከፈተም፤ ለመታረድ እንደሚነዳ ጠቦት፥ በሸላቶቹም ፊት ዝም እንደሚል በግ፥ እንዲሁ አፉን አልከፈተም።" ኢሳይያስ 53፡7

♻️ትህትና እግዚአብሄርን ብቸኛ ምንጭ ከማድረግ ይመጣል፡፡ ትህትና በስሜት አለመመራት ነው፡፡ ትህትና ሃያልነት እንጂ ሽንፈት አይደለም፡፡ ትህትና ሃይልን ለክፋት ላለመጠቀም ከመወሰን ጥበብ ይመጣል፡፡

"አይከራከርም አይጮህምም፥ ድምፁንም በአደባባይ የሚሰማ የለም። ፍርድን ድል ለመንሣት እስኪያወጣ፥ የተቀጠቀጠን ሸምበቆ አይሰብርም የሚጤስን የጥዋፍ ክርም አያጠፋም።" ማቴዎስ 12፡19-20

♻️ትህትና ሰዎችን አንድናከብር እንደ እግዚአብሄር ለሰዎች ታላቅ ዋጋ እንድንሰጥ ያደርገናል፡፡ ትህትና ሰዎችን ከመናቅ ትእቢት ነፃ ያወጣናል፡፡

"ለወገኔ ይጠቅማል በማለት ወይም በከንቱ ውዳሴ ምክንያት አንድ እንኳ አታድርጉ፥ ነገር ግን እያንዳንዱ ባልንጀራው ከራሱ ይልቅ እንዲሻል በትሕትና ይቍጠር፤" ፊልጵስዩስ 2፡3

♻️ትሁት ሰው ልታይ ልታይ አይልም፡፡ ትሁት ሰው ራሱን ይደብቃል፡፡ ትሁት ሰው ለስሙ አይጋደልም፡፡ ኢየሱስ ሰዎችን ከፈወሰ በኋላ ለማንም አትንገሩ ይል ነበር፡፡ የኢየሱስ ትኩረት የሰዎች መጠቀም እንጂ የራሱ ስም ዝና አልነበረም፡፡

"ከተራራውም በወረዱ ጊዜ ኢየሱስ፦ የሰው ልጅ ከሙታን እስኪነሣ ድረስ ያያችሁትን ለማንም አትንገሩ ብሎ አዘዛቸው።" ማቴዎስ 17፡9

♻️ትሁት ሰው እግዚአብሄር በሌላው እንደሚጠቀም ያምናል፡፡ ትሁት ሰው ራሱን አንድ ለእናቱ (ሱፐር ስታር) አድርጎ አያይም፡፡ ትሁት ሰው ሌሎችን በማገልገል በማንሳትና በመጥቀም ይረካል፡፡

"እርሱም፦ እናንተ እምነት የጎደላችሁ፥ ስለ ምን ትፈራላችሁ? አላቸው፤ ከዚህ በኋላ ተነሥቶ ነፋሱንና ባሕሩን ገሠጸ፥ ታላቅ ጸጥታም ሆነ።" ማቴዎስ 8፡26

♻️ትሁት ሰው ያለው ነገር ሁሉ የእግዚአብሄር እንደሆነ ስለሚያምን ስለማጣት ምንም አይሰጋም፡፡ ትሁት ሰው ቀድሞ ራሱን ስላዋረደ ማንም ሊያዋርደው አይችልም፡፡ ትሁት ሰው ህይወቱን ቀለል ስላደረገና ውስብስብ የቅንጦትን ህይወት ስለሚሸሽ ለእግዚአብሄር የሚመች አገልጋይ ይሆናል፡፡

"ኢየሱስም፦ ለቀበሮዎች ጕድጓድ ለሰማይም ወፎች መሳፈሪያ አላቸው፥ ለሰው ልጅ ግን ራሱን የሚያስጠጋበት የለውም አለው።" ሉቃስ 9፡58

♻️ትህትና ገመናን ይሸፍናል፡፡ ትህትና ከውድ ልብስ በላይ ሞገስ የሚሰጥ ልብስ ነው፡፡

"እንዲሁም፥ ጐበዞች ሆይ፥ ለሽማግሌዎች ተገዙ፤ ሁላችሁም እርስ በርሳችሁ እየተዋረዳችሁ ትሕትናን እንደ ልብስ ታጠቁ፥ እግዚአብሔር ትዕቢተኞችን ይቃወማልና፥ ለትሑታን ግን ጸጋን ይሰጣል።" 1ኛ ጴጥሮስ 5፡5

♻️ትሁትና የእግዚአብሄርን መንፈስ ይስባል፡፡ ካለን ምንም ነገር በላይ ትህትናችን እግዚአብሄርን ይማርከዋል፡፡

"እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ሰማይ ዙፋኔ ነው፥ ምድርም የእግሬ መረገጫ ናት፤ የምትሠሩልኝ ቤት ምን ዓይነት ነው? የማርፍበትስ ስፍራ ምንድር ነው? እነዚህን ሁሉ እጄ ሠርታለችና እነዚህ ሁሉ የእኔ ናቸው፥ ይላል እግዚአብሔር፤ ነገር ግን ወደዚህ ወደ ትሑት፥ መንፈሱም ወደ ተሰበረ፥ በቃሌም ወደሚንቀጠቀጥ ሰው እመለከታለሁ።" ኢሳይያስ 66፡1-2

♻️እንደ ትህትና የተሻለ አስተማማኝ ዋስትና የለም፡፡ እግዚአብሄር ከትሁቱ ጋር ይወግናል፡፡ እግዚአብሄር ለተዋረደው ይዋጋል፡፡ እግዚአብሄር ለትሁታን ፀጋን ይሰጣል፡፡

"ብልህ ሰው ክፉን አይቶ ይሸሸጋል፤ አላዋቂዎች ግን አልፈው ይጐዳሉ። ትሕትናና እግዚአብሔርን መፍራት ባለጠግነት ክብር ሕይወትም ነው።" ምሳሌ 22፡4

"በፌዘኞች እርሱ ያፌዛል፥ ለትሑታን ግን ሞገስን ይሰጣል።" ምሳሌ 3፡34

♻️ትህትና ከእግዚአብሄር የሆነን ክብር መቀበያ ብቸኛ መንገድ ነው፡፡ ትህትና በህይወታችን እንዲሆንልን የምንፈልገውን ነገር መጠየቂያ መንገድ ነው፡፡

"በዚህ ምክንያት ደግሞ እግዚአብሔር ያለ ልክ ከፍ ከፍ አደረገው፥ ከስምም ሁሉ በላይ ያለውን ስም ሰጠው፤" ፊልጵስዩስ 2፡9

"እንግዲህ በጊዜው ከፍ እንዲያደርጋችሁ ከኃይለኛው ከእግዚአብሔር እጅ በታች ራሳችሁን አዋርዱ፤" 1ኛ ጴጥሮስ 5፡6


🗞ምንጭ:- አብይ ዋኩማ


Join us
@Holy_scriptures
@Holy_scriptures
🔺🀄️🀄️ሉን🔺
" ጽድቅን የሚራቡና የሚጠሙ ብፁዓን ናቸው፥ ይጠግባሉና።"
(የማቴዎስ ወንጌል 5:6)


Amplified Bible
Blessed and fortunate and happy and spiritually prosperous (in that state in which the born-again child of God enjoys His favor and salvation) are those who hunger and thirst for righteousness (uprightness and right standing with God), for they shall be completely satisfied!


The Message...
"You're blessed when you've worked up a good appetite for God. He's food and drink in the best meal you'll ever eat.



Join us
@Holy_scriptures
@Holy_scriptures
🔺🀄️🀄️ሉን🔺
   🍲  የሰው ልጅ እንጀራ


አገልግሎት አንድ አካል ብቻውን የሚያደርገው ነገር ሳይሆን ሁሉም ምዕመን ተገናዝቦና ተባብሮ የሚያከናውነው ተግባር ነው፡፡ ቤተ ክርስቲያን እንደ ክርስቶስ አካል በምትተረጎምበት ሁኔታ እኛ ሁላችን የክርስቶስ አካል ብልቶች ነን (ሮሜ. 12÷5)፡፡ ሁላችንም በአንዱ ክርስቶስ አንድ ልብ አለን (1 ቆሮ. 2÷16) አንዲሁም አንዱን ምግብ (የእግዚአብሔር ቃል) ሁላችን እየተመገብን በህብረት እናድጋለን፡፡ ነገር ግን ጤነኛ ምግብ መመገባችንን እርግጠኛ ልንሆን ይገባል፡፡ መመገብ ውድቀትን ተከትሎ የመጣ እርግማን አይደለም፡፡ ከሰው ተፈጥሮ ጋር የተያያዘ የእለት ከእለት ተግባር እንጂ፡፡ በውኑ ምንድነው የምንመገበው? ክርስቶስ በምድር  ላይ ሲመላለስ በአንድ ወቅት በሰማርያ ደክሞት አረፍ ብሎ ነበር፡፡ ያን ጊዜ ደቀ መዛሙርቱ እንጀራ ሊገዙ ሄደው ነበር መጥተውም ብላ ብለው ይለምኑት ጀመር፡፡ እርሱም የበላ መሆኑን ሲገልጽላቸው ሰው አምጥቶለት ይሆንን ተባባሉ እርሱ ግን የእኔስ መብል የላከኝን ፈቃድ አደርግ ዘንድ ሥራውንም እፈጽም ዘንድ ነው አላቸው (ዮሐ. 4÷34)፡፡


         እንግዲህ ክርስቶስ ሊያገለግል እንጂ ሊገለገል አልመጣም (ማቴ. 20÷8) እንደተባለው እርሱ በምድር በተመላለሰበት የሥጋው ወራት ሁሉ የአባቱን ፈቃድ ማድረግ ቋሚ ትጋቱ ነበረ፡፡ ወደዚህ ዓለም የመጣበትን እውነተኛ ዓላማ እስኪፈጽም ድረስም እረፍት አልነበረውም፡፡ መብሉ የአብን ፈቃድ መፈጸም ነበርና መንፈሳዊ ርሀብ አልነበረበትም፡፡ ጌታ በቃልና በኑሮ አባቱን ደስ ያሰኘ ልጅ ነበር፡፡ በሙላት የተመገበ ሰው ለአባቱ ደስታ ነው፡፡ እኛም ይሄ ነው! የተጠራንለት ዓላማ ሁሌም ፈቃዱን መፈጸም ሁሌም ቃሉን መመገብና በቃሉ መሞላት፡፡



         በዚህ ዘመን የምናየው ግን ከዚህ በተለየ መልኩ አንድ በላተኛ ብዙ ተመልካች ነው፡፡ አንድ አገልጋይ ቆሞ ይሰብካል ሌላው ተቀምጦ ያዳምጣል፤ እድገት የለም፡፡ ምክንያቱም ሁሉም የበይ ተመልካች ነው፡፡ በአዲስ ኪዳን ሁሉም አማኝ አገልጋይ ነው፡፡ ምክንያቱም ሁሉም አካል ነውና እግርም፣ እጅም የየራሳቸው ሥራ አላቸው፡፡ እግር ከተያዘ መራመድ የለም፡፡ እጅ ከተያዘች መጉረስ የለም፡፡ የእግዚአብሔር ቤት ሁሉም እንደተሰጠው ጸጋ እርስበርስ ተያይዞ የሚያድግበት ስፍራ እንጂ አንዱ አፍጥጦ ሌላው የሚቀለብበት የባሪያና አሳዳሪ ኑሮ አይደለም፡፡ አገልግሎት የሕይወት ምስክርነት ጭምር ነው፡፡ የተለወጠው ሕይወታችን የሚገለጥበት ስፍራ፣ የሚታይበት መድረክ አገልግሎት ነው፡፡ ያመነውን ጌታ በሰው ሁሉ ፊት የምናሳይበት ቦታ ነው፡፡


         በመጀመሪያይቱ ቤተክርስቲያን እለት እለት መጨመርና መብዛት የነበረው ሁሉም በተለወጠና በአዲሱ ሰው ማንነት ይንቀሳቀሱ ስለ ነበረ ነው፡፡ ስናገለግል ሁሌም እናድጋለን፡፡ የሰማርያዋ ሴት ከነበረችበት ከንቱ ኑሮና የሕይወት እንቆቅልሽ አላቆ በአዲስ ሕይወት ዓይኗን ከፍቶ፣ እንስራዋን አስጥሎ፣ አለማመኗን ገፎ፣ በአገልጋይ ሥልጣን የወጣችው፤ |ያዳነኝን ኑና እዩ እስክትል ድረስ መንፈሳዊ ድፍረት ያገኘችው የአባቱን ፈቃድ ሊፈጽም በመጣው (መብል) በክርስቶስ ነበር፡፡ ከሕይወት ውሀ ወንዝ የሰዎችን በርሃ ኑሮ ማርካት፣ የሰውና የእግዚአብሔርን ግንኙነት እንደ ገና ማደስ፣ በእውነትና በመንፈስ የሆነውን አምልኮ መግለጥ፣ የዓለም ቤዛ እርሱ የሚመጣው መሲሁ ክርስቶስ እንደ ሆነ ማሳመን፣ ልዩነትን ማስወገድ(የአይሁድና የሳምራውያንን በጊዜው)፣ ሁሉን በፍቅር ማየት፣ ራስን ዝቅ ማድረግ፣ ከአንዲት ውሃ ልትቀዳ ከመጣች ሴት ጋር ማውራት የእርሱ መብል ይህን ነበር፡፡ጌታ ደቀ መዛሙርቱን የጠበቃቸው እንግዲህ ባለ አገልግሎት ነው፡፡ ትህትና፣ ፍቅር፣ የዋህንት፣ ምስክርነት ነው፡፡


          አገልግሎት እንጀራ መግዛት ሳይሆን ቁጭ ብሎ መብላት ነው፡፡  አንድ አገልጋይም በጌታ እግር ስር ያረፈና ቃሉን ያጣጣመ መሆን አለበት፡፡ በአንድ ወቅት ጌታ በአላዛር ቤት በተገኘ ጊዜ ማርታ በብዙ ትደክም ነበር፡፡ ማርያም ግን ከእግሩ ስር ተቀምጣ ቃሉን ታደምጥ ነበር፡፡ ጌታም ማርታ በብዙ አትድከሚ ነበር ያላት፡፡ ማርያምን ግን በጎ እድልን መረጥሽ ነው ያላት፡፡ የዚህ ዓለም እንጀራ ድካም ብቻ መሆኑን ነው የሚያስተምረን፡፡ ማረፍ ቃሉንም መመገብ በውበትም ሳይጠወልጉ ጌታን መስበክ እንዴት ነፍስን በሀሴት ይሞላል? እንደዛ እንደ ኤማሁስ መንገደኞች እየጠወለግን አይደለም በመንገድ ስለ ጌታ መመስከር ያለብን፡፡ እንደጌታ አረፍ ብለን በፍቅር እንጂ፡፡ አገልግሎታችን ከጌታ ፍቅር የተነሣ ከሆነ ዘመን ይሻገራል፡፡ ምክንያቱም ጌታ ፍቀር ነውና!!



🗞 ምንጭ:- ቤተ ፍቅር


Join us
@Holy_scriptures
@Holy_scriptures
🔺🀄️🀄️ሉን🔺
" ጽድቅን የሚራቡና የሚጠሙ ብፁዓን ናቸው፥ ይጠግባሉና።"
(የማቴዎስ ወንጌል 5:6)

መራብና መጠማት በዓለም ከሚገኙ ጠንካራ ስሜት መካከል ዋናዎቹ ናቸው:: ሰው እነዚህ ስሜቶች ከሌሉት የመታመሙ ምልክት ነው:: በዚህ ከቀጠለ ወደ ሞት እያመራ ነው ማለት ነው:: በመንፈሳዊ ሕይወትም እውነታው እንደዚህ ነው:: የመንግስቱ ዜጋና አምባሳደር የሚራበው እና የሚጠማው ደግሞ ጽድቅን ነው::

💥"ብፁእ" የሚለው ቃል ቀጥተኛ ትርጉሙ ደስተኛ ማለት ነው። ቃሉ ግን ለአይሁዳዊያን ከዚህ የጠለቀ ትርጉም አለው። ይህ ቃል በእግዚአብሔር ዘንድ ተቀባይነትን ማግኘትንና የበረከቱ ተካፋይ መሆንን ያሳያል። "ብፁእ" መባል ሌላኛው ትርጉሙ "የተባረከ" ማለት ነው። የተባረከ ሰው ከእግዚአብሔር ጋር የጠበቀ ግንኙነት ያለው ማለት ነው። የተባረከ የሚለው ቃል የተረገመ ከሚለው ቃል ጋር ተቃራኒ መሆኑን ልብ ይበሉ።

ጽድቅ ማለት ከእግዚአብሔር ጋር ትክክለኛ ግንኙነት ማድረግ ማለት ነው:: ወይንም ሙሉ በሙሉ እንደ እግዚአብሔር ፈቃድ መመላለስ ማለት ነው:: የክርስቲያኖች መንፈሳዊ ሁኔታ በኑሯቸው ሁሉ የሚወሰነው ለሚከተሉት ጉዳዮች ባላቸው ረሃብና ጥማት ነው:-

ሀ. ለእግዚአብሔር ሀልዎት/ህልውና
(ዘዳ. 4:29)

ለ. ለእግዚአብሔር ቃል(መዝ. 119)

ሐ. ከክርስቶስ ጋር ሕብረት ለማድረግ
(ፊል.3:8-10)

መ. ለመንፈስ ቅዱስ ሕብረት (ዮሐ.
7:37-39)

ሠ.ለጽድቅ(ማቴ. 5:6)

ረ.ለእግዚአብሔር መንግስት ኃይል
(ማቴ.6:33)::

ሰ. ለጌታ ዳግም ምጽአት(2ጢሞ. 4:8)




📜ምንጭ:- የተለያዩ የመጽሐፍ
ቅዱስ ማብራሪያ መጽሐፍት



Join us
@Holy_scriptures
@Holy_scriptures
🔺🀄️🀄️ሉን🔺
" የሚምሩ ብፁዓን ናቸው፥ ይማራሉና።"
(የማቴዎስ ወንጌል 5:7)


Amplified Bible
Blessed (happy, to be envied, and spiritually prosperous--with life-joy and satisfaction in God's favor and salvation, regardless of their outward conditions) are the merciful, for they shall obtain mercy!


The Message...
"You're blessed when you care. At the moment of being 'carefull,' you find yourselves cared for.



Join us
@Holy_scriptures
@Holy_scriptures
🔺🀄️🀄️ሉን🔺
🛐የእግዚአብሔርን ምሕረት እንዴት ማግኘት ይቻላል?

የሐዋርያት ሥራ ፲፫፥፴፰ እነደሚያውጀው፣ “እንግዲህ ወንድሞች ሆይ፤ የኀጢአት ይቅርታ የሚገኘው በኢየሱስ በኩል መሆኑ እንደ ተሰበከላችሁ ዕወቁ።”

✝️ምሕረት ምን ድነው? ለምንስ ያስፈልገናል?

“መማር” የሚለው ቃል ማስተሰርይ ወይም ዕዳን መሰረዝ ማለት ነው። አንድን ሰው ስንበድል፣ ያጣነውን ወዳጅነት ለማስተካከል ይቅርታ እንጠይቃለን። ምሕረት የሚሰጠው ግን በዳዩ ስለሚገባው አይደለም። ይቅርታ የሚገባው ግን ማንም የለም። ምሕረት የፍቅር፣ የርህራሄና የጸጋ ተግባር ነው። ምሕረት ስንል ምን ያህል በደል ቢደርስብንም በዳዩ ላይ ቂም አለመያዝ ማለት ነው።

መጽሐፍ ቅዱስ ሁላችንም የእግዚአብሔር ምሕረት እንደሚያስፈልገን ይነግረናል። ሁላችንም ኀጢአት ሠርተናል። መክብብ ፯፥፳ እነደሚያውጀው፣ “ትክክለኛውን ነገር የሚያደርግና ፈጽሞ ኀጢአት የማይሠራ፣ ጻድቅ ሰው በምድር ላይ የለም።” ፩ኛ ዮሐንስ ፩፥፰ እነደሚለን፣ “ኀጢአት የለብንም ብንል፣ ራሳችንን እናስታለን፤ እውነትም በኛ ውስጥ የለም።” ኀጢአት ሁሉ በእግዚአብሔር ላይ የሚፈጸም ዐምፃ ነው (መዝሙር ፶፩፥፬). ስለዚህም የእግዚአብሔር ምሕረት በጣምኑ ያሰፈልገናል። ኀጢአታችንን ካለተስረየልን ግን የኀጢአታችን ፍሬ ለዘለዓለሙ ሲያማቅቀን ይኖራል (ማቴዎስ ፳፭፥፵፮፤ ዮሐንስ ፫፥፴፮)። 

✝️እንዴት ምሕርትን ማግኘት እንችላለን?

ምስጋና ይድረሰውና እግዚአብሔር መሀሪና አፍቃሪ ስለሆነ፣ ኀጢአታችንን ሊያስተሰርይልን ጉጉ ነው! ፪ኛ ጴጥሮስ ፫፥፱ እንደሚነግረን፣ “…ነግር ግን ማንም እንዳይጠፋ፣ ሁሉ ለንስሓ እንዲበቃ ስለ እናንት ይታገሣል።” እግዚአብሔር ሊምረን ስለሚፈልግ፣ ምሕረት የምናገኝበትን መንገድ አመቻቸልን።

ለኀጢአት ተገቢ ቅጣት ሞት ብቻ ነው። ለዚህ ድጋፍ ሮሜ ፮፥፳፫ እንዲህ ያውጃል፣ “የኀጢአት ደመወዝ ሞት ነውና…።” የኀጢአታችን ዋጋ የዘለዓለም ሞት ነው። እግዚአብሔር ፍጹም በሆነ ጥበቡ ሰው የሆነው ልጁ ኢየሱስ ክርስቶስን ላከልን (ዮሐንስ ፩፥፩፣ ፲፬)። የኀጢአታችን ደመወዝ የሆነው ሞትንም ኢየሱስ በመስቀል ሞቶ ተቀበለልን! ፪ኛ ቆሮንቶስ ፭፥፳፩ እነደሚያስተምረን፣ “እኛ በእርሱ ሆነን የእግዚአብሔር ጽድቅ እንዲሆን፣ ኀጢአት የሌለበት እርሱን እግዚአብሔር ስለ እኛ ኀጢአት አደረገው።” በአምላክነቱም የኢየሱስ ሞት የምድርን ሁሉ ኀጢአት አስተሰረየ። ፩ኛ ዮሐንስ ፪፥፪ እነዲህ ያውጃል፣ “እርሱም የኀጢአታችን ማስተስረያ ነው። ይኸውም ለዓለም ሁሉ ኀጢአት እንጂ ለእኛ ብቻ አይደለም።” ኢየሱስ ኀጢአትንና ሞትን አሸንፎ ከሙታን ተነሣ (፩ኛ ቆሮንቶስ ፲፭፥፩-፳፰)። ለእግዚአብሔር ምስጋና ይግባውና በኢየሱስ ክርስቶስ ሞትና መነሣት፣ በሮሜ ፮፥፳፫ የተባለው እውነት ሆነ፤ “…የእግዚአብሔር ስጦታ ግን በጌታችን በክርስቶስ ኢየሱስ የዘለዓለም ሕይወት ነው።”

ኀጢአትህ እንዲሰረይልህ ትሻለህ? የጥፋተኝነት ሰሜትንስ ሁሌ ይነዘንዘሃል? የኢየሱስ ክርስቶስ አዳኝነት አምነኽ ከተቀበልክ፣ ምሕረትን ታገኛህ። ኤፌሶን ፩፥፯ እነደሚለው፣ “በእርሱም እነደ እግዚአብሔር ጸጋ ባለጠግነት መጠን፣ በደሙ በተደረገ ቤዛነት፣ የኀጢአትን ይቅርታ አገኘን።” ይቅርታን እናገኝ ዘንድ ኢየሱስ ክርስቶስ ዕዳችንን ከፈለልን። ስለዚህም፣ ምሕረትን ለማግኘት በኢየሱስ አዳኝነት አምነን እግዚአብሔርን ይቅርታ መጠየቅ ብቻ ነው የሚጠበቅብን። እግዚአብሔርም ይምረናል። ዮሐንስ ፫፥ ፲፮-፲፯ ይህንን ግሩም የሆነ መልእክት ይዟል፣ “በእርሱ የሚያምን ሁሉ የዘለዓለም ሕይወት እንዲኖረው እንጂ እንዳይጠፋ እግዚአብሔር አንድያ ልጁን እስከ መስጠት ድረስ ዓለምን እንዲሁ ወዶአልና፤ እግዚአብሔር ልጁን ወደ ዓለም የላከው በዓለም ለመፍረድ ሳይሆን፣ ዓለምን በእርሱ ለማዳን ነው።”

✝️ምሕረት ማግኘት እንዲህ ቀላል ነውን?

አዎን በጣም ቀላል ነው! ምሕረትን በሥራህ ከእግዚአብሔር ልታገኝ አትችልም። ከእግዚአብሔር ለምታገኘው ምሕረትንም ዋጋ መክፈል አትችልም። የኢየሱስ ክርስቶስ አዳኝነትና የእግዚአብሔርንም ምሕረት መቀበል ስትፈልግ የሚከተለውን ጸሎት መጸለይ ትችላለህ። ይህንን ወይንም ሌላ ጸሎት መድገም በራሱ አያድንህም። ኀጢአትህ ይቅር የሚባልልህ በኢየሱስ ክርስቶስ ካመንክ ብቻ ነው። ይህ ጸሎት በእግዚአብሔር ያለህን እምነት ለመግለጽና ስለ ምሕረቱንም ምስጋና ለማቅረብ ብቻ ነው የሚረዳህ። “እግዚአብሔር ሆይ፤ ባነተ ላይ ኀጢአት መሥራቴንና ለኀጢአቴም ዋጋ ቅጣት እንደሚገባኝ አውቃለሁ። ይሁን እንጂ እኔ እድን ዘንድ፣ ኢየሱስ ክርስቶስ ቅጣቴን ተቀብሎልኛል። ከኀጢአቴም በመራቅ እምነቴ በምሕረተህ አኖራለሁ። ድነቅ ለሆነው ጸጋህንና ይቅር ባይነትህን አመሰግንሃለሁ! አሜን!”


ምንጭ:- gotquestions. org


Join us
@Holy_scriptures
@Holy_scriptures
🔺🀄️🀄️ሉን🔺
" የሚምሩ ብፁዓን ናቸው፥ ይማራሉና።"
(የማቴዎስ ወንጌል 5:7)


"ብፁዕ" ማለት ምን ማለት እንደ ሆነ
በማቴ.5:3 እና 5:6 ላይ
የተማርነውን ክፍል ይመልከቱ::

"ምሕረት" የሚለው ቃል በመጽሐፍ
ቅዱስ መዝገበ ቃላት እንዲህ ተብሎ
ተተርጉሟል:: "የእግዚአብሔር
የርኅራሄ ባህርይ:: ቅጣት ለሚገባው
የሚሰጥ ይቅርታ... ለደካሞች,
ለበሽተኞች, ለድሆችም ቸርነትና
እርዳታን ማድረግ ነው::" ይለዋል::
ምሕረት ከኃጢአት ጋር የሚታገሉትን
ወይም አንድ ችግር
የሚጋፈጡትንም ወገኖች
መርዳትም ያመለክታል:: ምሕረት
የርኅራሄ ስሜት ብቻ ሳይሆን
ተግባራዊም ነው::

ብዙውን ጊዜ ጽድቅ ከፍርድ ጋር
ይያያዛል:: ምክንያቱም ጽድቅ
ከትክክለኝነት ጋር አብሮ ስለሚሄድ::
ምሕረት ደግሞ ለማይገባው ርኅራሄን
ማድረግን:: የሚገርመው ነገር
እግዚአብሔር እነዚህን ተቃራኒ
የሚመስሉ ነገሮችን ሚዛናዊ አድርጎ
አጣምሮ መያዙ ነው:: ደቀ
መዝሙሩም የንጉሡ ፈለግ ሊከተል
ይገባዋል:: በራሱ ላይ አብልጦ
በመፍረድ በባልንጀራው ዘንድ
አብዝቶ በምሕረት መመላለስ
ይገባዋል::

ምሕረት የእግዚአብሔር ስጦታ ነው::
በነጻ ተሰቶናልና በነጻ ልንሰጥ
ይገባል:: ይህ ሲሆን ምህረቱ በእኛ
ላይ ይበዛል ኡደቱም ይቀጥላል::
ለመሆኑ ሰውን አንምርም ምሕረቱን
አንለግስም ለማለት እኛ ማን ነን?

በመጨረሻም በዚህ የተራራው
ስብከት ውስጥ ንጉሡ የናዝሬቱ
ኢየሱስ የሚያዘን እንድንሆን እንጂ
እንድናደርግ አይደለም:: ቅርጫፉ
ከወይኑ ግንድ ጋር ሕብረት ካለው
ወይንም በዚህ ትምህርት መሠረት
ብፁእ/የተባረከ ከሆነ ይህ ባለፈው
ጀምሮ የተማርነው ነገር በአንድ
የመንግስቱ ዜጋ/ ደቀ መዝሙር
ሕይወቱ ውስጥ ይታያሉ:: ከእኛ
የሚጠበቀው በግንዱ ላይ ሆኖ
ገበሬው አባታችን
እኔነታችንን እንዲገድልና አብዝቶ
እንዲያጠራን መለመን ነው::




📜ምንጭ:- የተለያዩ የመጽሐፍ
ቅዱስ ማብራሪያ መጽሐፍት



Join us
@Holy_scriptures
@Holy_scriptures
🔺🀄️🀄️ሉን🔺
" ልበ ንጹሖች ብፁዓን ናቸው፥ እግዚአብሔርን ያዩታልና።"
(የማቴዎስ ወንጌል 5:8)


Amplified Bible
Blessed (happy, enviably fortunate, and spiritually prosperous--possessing the happiness produced by the experience of God's favor and especially conditioned by the revelation of His grace, regardless of their outward conditions) are the pure in heart, for they shall see God!


The Message...
"You're blessed when you get your inside world - your mind and heart - put right. Then you can see God in the outside world.


Join us
@Holy_scriptures
@Holy_scriptures
🔺🀄️🀄️ሉን🔺
ውድ የቅዱሳት መጻሕፍት ቤተሰቦች ዛሬ ከምሽቱ 3:00 ጀምሮ አዲስ ዓመቱን ምክንያት በማድረግ የሞባይል ካርድ እንፍቃለን:: ስለዚህ "online" በመሆን እንድትጠባበቁ::

Join us
@Holy_scriptures
@Holy_scriptures
🔺🀄️🀄️ሉን🔺
447 969 5559 2427
የሞላለት እስክሪን ሸት አድርጎ በኢንቦክስ @fasik137 ላይ ይላክልን::


Join us
@Holy_scriptures
@Holy_scriptures
🔺🀄️🀄️ሉን🔺
Woow Dersognal bale 15 nw gn screan shoot alarekutm kemr
የሞላለት ሰው እንደገባለት ምልክት በ @fasik137 ላይ በመስጠት ይተባበረን:: ሁለተኛው ከጥቂት ደቂቃዎች በኋላ ይጠብቁን::

Join us
@Holy_scriptures
@Holy_scriptures
🔺🀄️🀄️ሉን🔺
የኢትዮጵያ ዘመን አቆጣጠር የኢትዮጵያ (እንዲሁም በኤርትራ አብያተ ክርስትያናት) ዋና ካሌንደር ነው። አዲስ ዓመት በጁሊያን ካሌንደር አቆጣጠር በኦገስት 29 ወይም 30 የሚጀምር ሲሆን በግሪጎሪያን ካሌንደር ደግሞ ከ1901 እ.ኤ.አ. እስከ 2099 እ.ኤ.አ. ድረስ በሴፕቴምበር 11ወይም 12 ይጀምራል። በየአራት ዓመቱ አንድ ቀን ይጨመራል። በአንድ ዓመት ውስጥ አስራ-ሁለት ባለሠላሣ ቀናት እና አንድ ባለ አምስት (ስድስት በአራት ዓመት) ቀናት ያሉባቸው ወራት አሉ።

በኢትዮጵያ ዘመን አቆጣጠር ዓመታት ሁሉ በአራት መደባት ይዞራሉ፤ እነሱም ስለ ሐዋርያት ስሞች ዘመነ ማቴዎስ፣ ዘመነ ማርቆስ፣ ዘመነ ሉቃስ (ተጨማሪ የጳጉሜ ቀን የሚቀበለው) እና ዘመነ ዮሐንስ ይባላሉ።

የአመተ ምህረት ዘመናት ከጎርጎርዮስ 'አኖ ዶሚኒ' በ7 ወይም 8 አመታት የሚለይበት ምክንያት፣ ከኢየሱስ ክርስቶስ ልደት 400 አመት ያህል በኋላ አኒያኖስ እስክንድራዊ ዘመኑን ሲቆጥረው ትስብዕቱ በመጋቢት 29 1ዓ.ም. እንደ ሆነ ስለ ገመተ ይህ በትስብዕት ዘመን 1ኛ አመት ሆኗል። ይህ አቆጣጠር በምሥራቅ ክርስቲያን አገራት ከተቀበለ በኋላም በ443 ዓ.ም. ከሮማ ፓፓና ከምሥራቅ አቡናዎች መካከል ልዩነት ደርሶባቸው፤ በ517ሌላ መነኩሴ ዲዮኒሲዮስ ኤክሲጉዎስ ሌላ አቆጣጠር (አኖ ዶሚኒ) አቀረበ። በሱ ግምት ትስብዕቱ የተከሠተበት ቀን ከአኒያኖስ ግምት በፊት በ8 አመታት አስቀደመው። የአኖ ዶሚኒ አቆጣጠር በምዕራብ አውሮፓ ላይኛነት በማግኘቱ የትስብእት ዘመን 1 አመተ ምህረት በአኖ ዶሚኒ 9 እ.ኤ.አ.ሆነ።

የኢትዮጵያ ዘመን ኣቆጣጠር የጁልያን ዘመን ኣቆጣጠር ኣይደለም። በኣሁኑ ጊዜ በጁልያና በጎርጎርዮስ ካለንደሮች መካከል ያለው የ13 ቀናት ልዩነት ሲሆን የዓመታቱ ቍጥሮች ልዩ ኣይደሉም።

በ525 ዓ.ም. ዲኖስዮስ ኤክሲጅዮስ (Dionysius Exiguus) የሚባል የሩስያ መነኩሴ የሮማው ጳጳስ መልዕክተኛም በመሆን የፋሲካን በዓል ኣወሳሰን ከግብጻውያን እንዲማር ተልኮ ነበር። እንደሚመስለኝና ኣንዳንድ ፀሓፊዎችም እንደሚሉት ኤክሲጅዮስ በ525 ዓ.ም. 532 ዓመትን ሳይጠቀም ኣልቀረም ይላሉ ዶክተር ኣበራ ሞላ።  ዲኖስየስ ኣኖ ዶሚኒ (Anno Domini ወይም ኤ.ዲ.) የሚባለውን ካለንደር በጃንዋሪ 1 ፣ 1 ኤ.ዲ. እንዲጀምር በ525 ቢወስንም በኋላም ፀሓፊዎች ጁልያን (ዩልዮስ) ካለንደር ያሉት የግብጾችንና የኢትዮጵያን ዘመን መቈጠርያዎች ስለማይመለከት እራሱን የቻለ ካለንደር ሆኖ ቆይቷል። ኤክሲጅዮስ ወደኋላ በመቍጠር ሲጀምር ይመስለኛል ኣዲሱ ካለንደር ላይ ሰባት ዓመታት ግድም የጨመረበት። የዓመታቱም ቍጥር ከግብጽ ይልቅ ወደ ኢትዮጵያ የቀረበ ነው። ጨረቃ መሬትን ስትዞርና መሬት ፀሓይን ስትዞር የሚወስዱት 532 ዓመታት (19 X 28) ተደጋጋሚ ናቸው። 


ምንጭ:- አበራ ሞላ


Join us
@Holy_scriptures
@Holy_scriptures
🔺🀄️🀄️ሉን🔺