ቅዱሳት መጻሕፍት
7.45K subscribers
1.37K photos
61 videos
332 files
808 links
በዚህ ቻናል

👉ቅዱሳት መጻሕፍት ይጠናሉ::
👉መጽሐፍ ቅዱሳዊ ትምህርቶች ይቀርባሉ::
👉 ለቅዱሳት መጽሐፍት ጥናት የሚያግዙ መጻሕፍት ይለቀቃሉ።

⭐️⭐️⭐️⭐️⭐️

@Holy_scriptures
Download Telegram
"ጻድቅ በእምነት ይኖራል" የሚለው ጥቅስ የት ይገኛል?
Anonymous Quiz
52%
ሀ. ሮሜ
14%
ለ. ገላትያ
18%
ሐ. ዕብራውያን
16%
መ. ሁሉም
👍9
.    ==❀❀❀===❀❀❀==      
              የዕለቱ ጥቅስ 
     ==❀❀❀===❀❀❀==
“የእግዚአብሔርን ጸጋ አልጥልም፤ ጽድቅስ በሕግ በኩል ከሆነ እንኪያስ ክርስቶስ በከንቱ ሞተ።”
ገላትያ 2፥21




ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
👍5
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ቅዱሳት መጻሕፍት
የፕሮቴስታንት ተሐድሶ አምስቱ ምሶሶያት የፕሮቴስታንት ተሐድሶ መሪዎች ማርቲን ሉተር፣ ጆን ካልቪን፣ ኡልሪች ዝዊንግሊ፣ ጆን ኖክስ በዘመኑ ከነበረችው ከሮም ካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን ልዩ የሚያደርጋቸውን አምስት ነገረ መለኮታዊ ቁልፍ የአስተምህሮ ምሶሶያት አስቀምጠዋል። እነዚህ የተሐድሶ ምሶሶያት “አምስቱ ሶላዎች” (Five solas) ተብለው ይታወቃሉ። ሶላ (sola) ማለት የላቲን ቃል ሲሆን ትርጉሙም…
የቀጠለ...



፫. ድነት በእምነት ብቻ “Sola Fide,”
“Salivation by Faith Alone”


ለጸጋ ያለን ምላሽ እምነት ነው። እምነት እጅግ ቀላል የሚመስል ከባድ ነገር ነው። እምነት ከባድ ያደረገው ለማመን አስቸጋሪ የሆነውን ነገር እንድናምን እኛን መጠየቁ ነው። በአዲስ ኪዳን ውስጥ 150 ጊዜ ኃጢአተኛ ድነት የሚያገኘው በእምነት ብቻ እንደሆነ ተገልጿል። የሰውን ነፍስ ማዳን የሚችለው እግዚአብሔር ብቻ ሲሆን ይህን እውን የሚያደርገው ሰዎች በልጁ የመስቀል ሥራ ሲያምኑ ብቻ ነው። እምነት ሥራ ሳይሆን በጌታ በኢየሱስ ክርስቶስ ሥራ ሙሉ በሙሉ መደገፍ ማለት ነው።

በሮማን ካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን ድነት ሂደት ነው። ድነት በኢየሱስ ክርስቶስ ባለን እምነት፣ በሥራና ቅዱስ ሚስጢራትን በመፈጸም እንደሚገኝ ያምናሉ። እምነትና ሥራም ለድነት አስፈላጊነታቸው ላይ ያሰምራሉ። ማርቲን ሉተር ሲናገር፦ “እምነትና ሥራ እንደ እሳትና ሙቀት የማይለያዩ ቢሆኑም ለነፍስ ድነት በክርስቶስ እናምናለን እንጂ ለመዳን መልካም ሥራ አንሰራም። እምነትና ሥራ አንድ ባይሆኑም በፍጹም ማለያየት አይቻልም፤ መልካም ሥራ እምነታችንን የማይከተል ከሆነ የሚያድን እምነት እንደሌለን ያመለክታል። የዳነው በእምነት ብቻ ነው፤ ነገር ግን ብቻውን በሆነ እምነት ግን አይደለም። ያለ ሥራ እምነት ሙት ነውና (ያዕ. 2፡17-20)። እንደዚሁም ሥራ የእምነት ውጤት እንጂ እምነት የሥራ ውጤት አይደለም። መልካም ሥራ የመዳናችን መሠረት ሳይሆን ማስረጃ ነው (ኤፌ. 2፡10)። መልካም ሥራ የመዳናችን ምልክት እንጂ ምክንያት አይደለም። ስለዚህ ለመዳን እናምናለን እንጂ አንሠራም፤” ብሏል።

ድነት ነጻ ስጦታ ነው። ድነት በጾምና ጸሎት፣ ለደሃ በመወጽወት፣ በባሕታዊነት፣ ራስን በማጎሳቆል፣ በመገርጣትና በመራብ፣ በተዝካር ድግስ፣ አማላጆችና ቅዱሳን በተባሉ ልዩ ሰዎች መካከለኛነት፣ በቤተ ክርስቲያን አባልነት ሳይሆን በኢየሱስ ክርስቶስ በመስቀል ሥራ በማመን ብቻ ነው።

#እምነት_ምንድነው? ለሚለው ቃሉ መልስ አለው፦ “እምነት ተስፋ ስለምናደርገው ነገር የሚያስረግጠን የማናየውንም ነገር የሚያስረዳን ነው” (ዕብ. 11፡1)። በዚህ ክፍል ስለ መጽሐፍ ቅዱሳዊ እምነት የሚያስረዱን ሁለት ቁልፍ ቃሎች “ማስረገጥ” እና “ማስረዳት” የሚሉት ናቸው። ማስረገጥ ማለት፦ “ምርኩዝ መሆን” “መደገፍ” ማለት ነው። እምነት ለድነታችን እንደ ጠንካራ ምርኩዝ በክርስቶስ እንድንደገፍ ይረዳናል። ሁለተኛው ቃል “ማስረዳት” የሚል ሲሆን ይህም እምነት አንድ ግልጽ ያልሆነውን ነገር የመረዳት አቅም እንደሚሰጠን ያመለክታል።

“በእርሱ የሚያምን ሁሉ የዘላለም ሕይወት እንዲኖረው እንጂ እንዳይጠፋ እግዚአብሔር አንድያ ልጁን እስኪሰጥ ድረስ ዓለሙን እንዲሁ ወዶአልና።” (ዮሐ. 3፡16)

፬. ድነት በኢየሱስ ክርስቶስ ብቻ “Solus Christus,” “In Christ Alone”

“እንግዲህ በክርስቶስ ኢየሱስ ላሉት አሁን ኵነኔ የለባቸውም።” (ሮሜ. 8፡1) ኃጢአት የሌለበት ፍጹም ጽድቅና ቅዱስ የእግዚአብሔር ልጅ ኢየሱስ ክርስቶስ በሰው ልጆች ሁሉ ምትክ መሞቱና መነሳቱ ከአብ ጋር መታረቅ ሆኖልናል። ኢየሱስ ክርስቶስ በሞቱ ለብዙዎች ቤዛ እንደ ሆነ ተናግሯል። ስለዚህ ድነት በእርሱ ብቻ ነው።

“ኢየሱስም፦ እኔ መንገድና እውነት ሕይወትም ነኝ፤ በእኔ በቀር ወደ አብ የሚመጣ የለም።” (ዮሐ. 14፡6)

“የዘላለም ሕይወት እንዳላችሁ ታውቁ ዘንድ በእግዚአብሔር ልጅ ስም ለምታምኑ ይህን ጽፌላችኋለሁ።” (1ዮሐ. 5፡13)

“መጽሐፉን ትወስድ ዘንድ ማኅተሞቹንም ትፈታ ዘንድ ይገባሃል፥ ታርደሃልና፥ በደምህም ለእግዚአብሔር ከነገድ ሁሉ ከቋንቋም ሁሉ ከወገንም ሁሉ ከሕዝብም ሁሉ ሰዎችን ዋጅተህ ለአምላካችን መንግሥትና ካህናት ይሆኑ ዘንድ አደረግሃቸው፥ በምድርም ላይ ይነግሣሉ እያሉ አዲስን ቅኔ ይዘምራሉ።” (ራዕ. 5፡9-10)

፭. ለእግዚአብሔር ክብር ብቻ “Soli Deo Gloria,” “For the Glory of God Alone”

የዳንነው በእግዚአብሔር ኃይል ለእግዚአብሔር ክብር ብቻ እንደሆነ በማወቅ በእርሱ ፊት በእውነተኛ ቅድስናና አምልኮ መኖር ይገባናል። በእግዚአብሔር ፊት፣ በእግዚአብሔር ሥልጣን ሥር ለእግዚአብሔር ክብር ብቻ መኖር አለብን።

“የእግዚአብሔርንም መሠዊያ ደግሞ አደሰ፥ የደኅንነትና የምስጋናም መሥዋዕት ሠዋበት ይሁዳም የእስራኤልን አምላክ እግዚአብሔርን እንዲያመልኩ አዘዘ። ሕዝቡ ግን ገና በኮረብታው መስገጃዎች ይሠዋ ነበር ቢሆንም ለአምላኩ ለእግዚአብሔር ብቻ ነበር።” (2ዜና 33፡16-17)



ምንጭ፦ "ተሐድሶ" ቅጽ-1 በጸጋአብ በቀለ ከገጽ 243-248
       



ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
👍105🔥1
መግቢያ በቃሉ ብቻ.pdf
3.3 MB
ርዕስ፦ ቅዱሳት መጻሕፍት ብቻ (ቃሉ ብቻ)
ብራና ሴሚናር 2016፣ ወደ ተነሳንበት መመለስ፣ የተሐድሷውያን አምስቱ "ብቻዎች"


ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
7🔥2👍1👏1
በእምነት ብቻ.pdf
2.1 MB
ርዕስ፦ በእምነት ብቻ
ብራና ሴሚናር 2016፣ ወደ ተነሳንበት መመለስ፣ የተሐድሷውያን አምስቱ "ብቻዎች"


ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
6🔥1👏1
በክርስቶስ ብቻ.pdf
2.3 MB
ርዕስ፦ ክርስቶስ ብቻ
ብራና ሴሚናር 2016፣ ወደ ተነሳንበት መመለስ፣ የተሐድሷውያን አምስቱ "ብቻዎች"


ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
9🔥1👏1
በጸጋ ብቻ.pdf
2.2 MB
ርዕስ፦ በጸጋ ብቻ
ብራና ሴሚናር 2016፣ ወደ ተነሳንበት መመለስ፣ የተሐድሷውያን አምስቱ "ብቻዎች"


ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
8🔥1👏1
ክብር ለእግዚአብሔር ብቻ.pdf
1.6 MB
ርዕስ፦ ክብር ለእግዚአብሔር ብቻ
ብራና ሴሚናር 2016፣ ወደ ተነሳንበት መመለስ፣ የተሐድሷውያን አምስቱ "ብቻዎች"


ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
9🔥2👍1👏1
.    ==❀❀❀===❀❀❀==      
              የዕለቱ ጥቅስ 
     ==❀❀❀===❀❀❀==
“ስለዚህ፥ የተወደዳችሁ ወንድሞቼ ሆይ፥ ሰው ሁሉ ለመስማት የፈጠነ ለመናገርም የዘገየ ለቍጣም የዘገየ ይሁን፤”
ያዕቆብ 1፥19



ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
👍83
ሃይማኖትስ ይታደሳል?
      


ክርስትና በአስተርእዮተ እግዚአብሔር ላይ የተመሰረተ እምነት ነው (ለምሳሌ ዮሐ. 1፥18፤ ገላ. 2፥2)። ጌታ እግዚአብሔር በዘመናት ሁሉ የገለጠው እውነትና የሰጣቸው ተስፋዎች ሁሉ ፍጻሜም ነው። በክርስቶስ መገለጥ ያልተፈጸመ ምንም የለም፤ "በእግዚአብሔር የተሰጡ ተስፋዎች ሁሉ 'አዎን' የሚኾኑት በእርሱ ነውና" (2ቆሮ. 1፥20 ዐ.መ.ት)። በእግዚአብሔር ልጅ በጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ አማካይነት የመጣው አስተርእዮ የቀዳሚዎቹ ፍጻሜ ብቻ ሳይኾን፣ የመጨረሻውና ከሁሉ በላይ የላቀ መገለጥ ነው (ዕብ. 1)። እንግዲህ ይህ መገለጥና እምነት እውነተኛ ፍጹም ቢኾንም፣ እኛ ሰዎች በምንሰጠው ምላሽና ተግባር ላይ ግን ጉድለት ሊከሠት መቻሉ እውነት ነው፤ የሰው ልጅ መሳሳቱ አይቀርም። የመታረሙና መታደሱ አስፈላጊነትም የሚመነጨው ከዚሁ የሰው ድካም ውስጥ ነው።

የሰው ልጅ እውነተኛን እምነት በመበረዝ በኑፋቄ ጮረቃ ሲያልኮሰኩሰው እግዚአብሔር በተሐድሶ ውሃ ያጠራዋል። በዚያን ጊዜ ምርቱን ከግርዱ መለየት ይኖራል። ፍሬውን ከገለባው ማበጠር ይከተላል። ለዚህም ዐላማ ሲል እግዚአብሔር በምሕረቱ የተሐድሶ ነፋስ ያነፍስበታል። በዚህ ማጥራትና ማንፈስ ሂደት ደግሞ የሚሠራ ብቻ ሳይኾን የሚፈርስ የቁሻሻ ክምር ይኖራል። ይህን መሳይ ታላቅ ተግባር ለማከናወን ብሩህ አእምሮ የታደሉ ዐዳሾች ያስፈልጋሉ ማለት ነው። ፕሮፌሰር ጌታቸው ኃይሌ እንዳሉት፣ "አሕይዎና ተሐድሶ (Revival and Renewal or Reformation) ተደላድሎና ተመቻችቶ በተቀመጠ ሥርዐት (Establishement) ውስጥ የዛገና የሚራገፍ ነገር የሚያይ የአእምሮ ችሎታና የተፈጥሮ ተሰጥዎ ካላቸው ታላላቅ ሰዎች ዘንድ የሚመጡ ሐሳቦች ናቸው።"

ስለዚህ ሃይማኖትም ቢኾን "በዛገና በሚራገፍ ነገር" ብልሽት ከገጠመው ይታደሳል። እግዚአብሔር ራሱ አሮጌውን በዐዲሱ ዐድሷል። አሮጌውን በዐዲሱ ሰው ተክቶታል (ኤፌ. 4፥24፤ ቆላ. 3፥10)። ነቀፋ የተገኘበትን ፊተኛውን ኪዳን  (ኤር. 31፥ 31-34) ለዐዲሱ ስፍራ አስለቅቆታል (ዕብ. 8፥6-7)። ስለዚህም፣ "ዐዲስ በማለቱ ፊተኛውን አስረጅቶአል፤ አሮጌውና ውራጅ የሆነውስ ሊጠፋ ቀርቦአል" (ዕብ.8፥13) የተባለው ቃል ተጻፈ። አዎን! ሃይማኖትም ቢኾን ቅይጥነት ሲገዳደረው፣ አደፋ ሲጠናወተው መለኮተ መድኀኒት ያዝዝለታል።

"ማፍረስም መስራት ነው" ከሚለው ጽሁፍ የተቀነጨቡ ሃሳቦች

ከእግዚአብሔር የተቀበልናቸውን ጠቃሚ ሀብታት አንድም በማበላሸት ካቆሸሽናቸው፣ ደግሞም ለእርሱ ክብር ከማድረግ ይልቅ ለሥጋዊ ትምክሕትና ሌላውን ወገን ለማክፋፋት ካዋልናቸው ዐላማቸውን ስተዋልና የተሐድሶ ነፋስ ያሻቸዋል። 

መጽሐፍ ቅዱሳችን ራሱ የተሐድሶ መጽሐፍ ነው።  እግዚአብሔር በታሪከ ድነት ውስጥ ያቆመው ዋነኛ መርሕም የተሐድሶ ምልሰት ነው።      

ቅዱሱን መጽሐፍ የልብ ዐይኖቻችን ተከፍተውልን ካነበብነው ተሐድሶን እንናፍቀው እንደኾነ እንጂ እናክፋፋው ዘንድ ዐቅም አይኖረንም። ይህም[በክርስቶስ የሆነው ድነት] በእግዚአብሔር ምሕረትና ጸጋ አማካይነት ወደ ቀደመው ክብር፣ ጸጋና ቦታ የመመለስና የመታደስ ወንጌል ነው። ከውድቀት በኃላ ለአዳም የተሰጠው ያ ተስፋ ቤዝዎታዊ ተሐድሶ ነበር።     

ተሐድሶን ለማምጣትና ወደ እውነቱ ለመመለስ ሲባል የሐሰት ትምህርት ላይ መጨከን ግዴታ ነው እንጂ፣ አማራጭ አልነበረም፤ ዛሬም ሊሆን አይችልም።

"ልዩ ወንጌል" ወደ ቤተ እግዚአብሔር ሲያቀና እንቢ ማለትና አዋኪዎች ያስገቡትን ኑፋቄና የአጋንንት ትምህርት ማፍረስ ተሐድሶ ነው። ይህ ሊኮነን ሳይኾን ሊወደስ የሚገባው ዘመቻ ነው። ጥያቄው ለምን፣ መቼ፣ የት፣ ምንና እንዴት ይታደስ የሚለው እንጂ "ዝንቡ እሽ የሚባል የለም" ብሎ ማፍጠጥ መፍትሔ አይኾንም። በደፈናው "ሃይማኖት አይታደስም" እያልን ከማገንገን፣ ለምን እንደማይታደስ ብናስረዳ ጥሩ ነበር። ጌታ ኢየሱስ አዳሽ አልነበረምን? ሐዋርያቱስ? የአሮጌው መነካት ባይመቸንም እንኳ፣ ለተሻለው ስፍራ እንዲለቅ ውራጅ የኾነው ትምህርትና ልምምድ ይፈርሳል።

ማንኛውንም ነገር በደባልነት ደርበን ለማምለክ ብንሞክር፣ ይህ ብክለት ነውና ሃይማኖት ይታደሳል። ማንኛውም ነገር ከመለኮታዊው አስተምህሮ በተፃሮ ሲቆም፣ ወይም ቅይጥነት ሲዳበለው ተሐድሶ ያስፈልጋል። የእግዚአብሔር ሰው ነኝ የሚል ሁሉ አምልኮተ ባዕድን፣ ርኩሰትን፣ ጥንቆላን፣ ኑፋቄን። በወንጌል ስም መነገድን፣ ወዘተ. ማፍረስ ግድ ይለዋል። በእግዚአብሔር ከተሰጠው መመሪያ ውጭ በሰው የተገነቡ መሠዊያዎች እስከሚሰነጠቁና ዐመዳቸው እስከሚፈስ ድረስ ቢሰነጣጠቁ እንደነቃለንን(1ነገ. 13)?     



ምንጭ፦ ሰሎሞን  አበበ ገብረ መድሕን፤ የትሩፋን ናፍቆት፣ ማፍረስም መስራት ነው፣ ጌታቸው ኃይሌ ፤ ደቂቀ እስጢፋኖስ:- በሕግ አምላክ




ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
6👍5🥰1
.    ==❀❀❀===❀❀❀==      
              የዕለቱ ጥቅስ 
     ==❀❀❀===❀❀❀==
“ንቁ፥ በሃይማኖት ቁሙ፥ ጎልምሱ ጠንክሩ።”
1ኛ ቆሮንቶስ 16፥13



ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
👍52🔥2
ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
2
የኢትዮጵያ ቤተክርስቲያን ተሐድሶ.pdf
11.1 MB
👉ርዕስ፦ የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን ተሐድሶ፣ ቅጽ 1፣ ሳታድግ ያረጀች የኢትዮጵያ ቤተክርስቲያን
ጸሐፊ፦ ወ/ዊ ጸጋአብ በቀለ
🗓 የታተመበት ዓመት፦ 2006 ዓ.ም


ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
6👍6👎1
በአባቱ በዳዊት መንገድ እንደሄደ የተነገረለት፣ እስራኤላዊያን ያጥኑለት የነበረውን ሙሴ የሰራውን የናሱ እባብ የሰባበረ፣ በኮረብታ ያሉትን መስገጃዎች ያስወገደው ንጉሥ ማን ነው?
Anonymous Quiz
27%
ሀ. ሰሎሞን
11%
ለ. ምናሴ
22%
ሐ. አሳ
39%
መ. ሕዝቅያስ
👏64
.    ==❀❀❀===❀❀❀==      
              የዕለቱ ጥቅስ 
     ==❀❀❀===❀❀❀==
“ነገር ግን ሩጫዬንና ከጌታ ከኢየሱስ የተቀበልሁትን አገልግሎት እርሱም የእግዚአብሔርን ጸጋ ወንጌልን መመስከር እፈጽም ዘንድ ነፍሴን በእኔ ዘንድ እንደማትከብር እንደ ከንቱ ነገር እቆጥራለሁ።”
ሐዋርያት 20፥24



ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
👍62
ፕሮቴስታንት ማለት ምን ማለት ነው?




ፕሮቴስታንት የሚለው ቃል በላቲን ፕሮቴስታሪ ከሚል የተገኘ ሲሆን ትርጉሙም "በአደባባይ ማወጅ" ወይም "ተቃውሞ ማድረግ" ማለት ነው። ቃሉ በመጀመሪያ እ.ኤ.አ በ1529 በስፔየር አመጋገብ ላይ በፖለቲካዊ አውድ ውስጥ ጥቅም ላይ ዋለ። ከዚህ በመቀጠል በስብሰባ ላይ የጀርመን መሳፍንት እና የንጉሠ ነገሥት ከተሞች ቡድን የለውጥ አራማጁን ማርቲን ሉተርን ያወገዘውን የዎርምስን አዋጅ ለመደገፍ የተላለፈውን ውሳኔ ተቃወሙ። እነዚህ ተቃዋሚዎች የሀይማኖት ነፃነት መብት እና የእምነታቸው ተግባር ላይ የሚጣሉ ገደቦችን በመቃወም የካቶሊክ አብላጫውን ድንጋጌ በመቃወም መደበኛ የሆነ “ተቃውሞ” አቅርበዋል።

እንቅስቃሴው በሃይማኖታዊ ገጽታው ብቻ ሳይሆን በተሃድሶ ላይ በማተኮር እና በተቋቋሙት የሃይማኖት ባለስልጣናት ላይ በማተኮር "ፕሮቴስታንቲዝም" በመባል ይታወቃል። በጊዜ ሂደት፣ “ፕሮቴስታንቶች” ከተሃድሶ የተነሱትን እና ከሮማ ካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን የተለየ ማንነት ያለው የትኛውንም የክርስቲያን ቤተ እምነት በሰፊው ለማመልከት የሚውል ቃል ሆነ።


ምንጭ፦
👉MacCulloch, Diarmaid. The Reformation: A History. Viking, 2003.
👉Bainton, Roland H. Here I Stand: A Life of Martin Luther. Abingdon-Cokesbury, 1950.
👉The Oxford Dictionary of the Christian Church, edited by F.L. Cross and E.A. Livingstone, 2005.



ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
👍71🙏1
ተሐድሶ መቼ ይጠበቃል?


፩. በክርስቲያን ነን ባዮች መሃል ወንድማዊ ፍቅርና ክርስቲያናዊ መተማመን ሊኖር ግድ ሲል።

፪. የአሳብ መለያየት፣ ቅናት እና ክፉ ንግግር በክርስቲያን ነን ባዮች ቦታ ሲይዝ።

፫. በቤተ ክርስቲያን ውስጥ ዓለማዊ መንፈስ ሲኖር። ክርስቲያኖች በአለባበስ፣ ሀብት በመሰብሰብና በጭፈራ በዓለም መደነቅን በመፈለግ የዓለምን ነገር ሲመርጡ ሲታይ።

፬. ቤተ ክርስቲያን ምዕመኖቿ በኃጢአት ሲዘፈቁና ወደ ኃጢአት ሲገቡ።

፭. አገልጋይ በየትኛውም ደረጃ የሚያገለግለውን ሕዝብ አመኔታ ባጣ ጊዜ።

፮. ሰው በተሰበከው መጠን ልቡ ንስሃ ከመግባት ይልቅ የሚደነድን ከሆነ።

፯. አማኞች የጌታ መልክ የማይታይባቸው ከሆነ።

፰. ጸጋ የማያድግበት ከሆነ እና አማኙ ከሳምንት ሳምንት ለክርስትና ግዴታው የማይነሳሳ ከሆነ

፱. መጸለይ ከባድና አስቸጋሪ ሲሆን።

፲. ክርስቲያኖች ኃጢአታቸውን እርስ በእርሳቸው መናዘዝ ሲያቅታቸው

፲፩. ክርስቲያኖች መስዋዕትነት መክፈል በሚያስፈልግበት መስዋዕትነትን ለመክፈል ፈቃደኛ መሆን ሲያቅታቸው




ምንጭ፦ ቻርለስ ፊኒ፤ ተሐድሶ እንዲሆን፤ ከገጽ 6-10




ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
👍6🔥21👏1
.    ==❀❀❀===❀❀❀==      
              የዕለቱ ጥቅስ 
     ==❀❀❀===❀❀❀==
“ያን መንፈስም፥ በጸጋው ጸድቀን በዘላለም ሕይወት ተስፋ ወራሾች እንድንሆን፥ በመድኃኒታችን በኢየሱስ ክርስቶስ በእኛ ላይ አትርፎ አፈሰሰው።”
ቲቶ 3፥6-7




ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
3👍3🔥1
Audio
👉ርዕስ፦ የመናኝ ጉዞ
ጸሐፊ፦ ዮሐንስ ቡንያን
🔈ክፍል ስድስት


ይቀጥላል...


ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
1👍1🥰1