ቅዱሳት መጻሕፍት
7.91K subscribers
1.5K photos
61 videos
365 files
855 links
በዚህ ቻናል

👉ቅዱሳት መጻሕፍት ይጠናሉ::
👉መጽሐፍ ቅዱሳዊ ትምህርቶች ይቀርባሉ::
👉 ለቅዱሳት መጽሐፍት ጥናት የሚያግዙ መጻሕፍት ይለቀቃሉ።

⭐️⭐️⭐️⭐️⭐️

@Holy_scriptures
Download Telegram
በቅዱሳት መጻሕፍት ካሉ ወንጌላት ውስጥ ስለመንግሥተ ሰማያት ትኩረት የሚያደርገው መጽሐፍ የቱ ነው?
Anonymous Quiz
55%
ማቴዎስ
10%
ማርቆስ
8%
ሉቃስ
27%
ዮሐንስ
👍4❤1🔥1
በክርስትና ብስለት ማደግ


"እውነትን በፍቅር እየያዝን በነገር ሁሉ 
ወደ እርሱ ራስ ወደሚሆን ወደ ክርስቶስ እንደግ፤"
         ኤፌ. 4፡15

መንፈሳዊ ብስለት ይጠበቅብናል ወይ?

•ኤፌ. 4:11-13 "እርሱም አንዳንዶቹ ሐዋርያት፣ ሌሎቹም ነቢያት፣ ሌሎቹም ወንጌልን ሰባኪዎች፣ ሌሎቹም እረኞችና አስተማሪዎች እንዲሆኑ ሰጠ፤ ሁላችን የእግዚአብሔርን ልጅ በማመንና በማወቅ ወደሚገኝ አንድነት፣ ሙሉ ሰውም ወደ መሆን/to a mature 
man፣ የክርስቶስም ሙላቱ ወደሚሆን ወደ ሙላቱ ልክ እስክንደርስ ድረስ፣ ቅዱሳን አገልግሎትን ለመሥራትና ለክርስቶስ አካል ሕንጻ ፍጹማን ይሆኑ ዘንድ፡፡"

•ቆላ. 1፡28-29 "እኛም በክርስቶስ ፍጹም የሚሆን ሰውን ሁሉ እናቀርብ ዘንድ ሰውን ሁሉ እየገሠጽን ሰውንም ሁሉ በጥበብ ሁሉ እያስተማርን የምንሰብከው እርሱ ነው፡፡ ለዚህም ነገር ደግሞ፣ በእኔ በኃይል እንደሚሠራ እንደ አሠራሩ እየተጋደልሁ፣ እደክማለሁ፡፡"

•ቆላ. 1፡9 "ስለዚሁ እኛ ደግሞ ይህን ከሰማንበት ቀን ጀምረን የፈቃዱ እውቀት መንፈሳዊ ጥበብንና አእምሮን ሁሉ እንዲሞላባችሁ እየለመንን፥ ስለ እናንተ ጸሎትን አልተውንም።"

•ፊሊ. 1:9-11 "ለእግዚአብሔርም ክብርና ምስጋና ከኢየሱስ ክርስቶስ የሚገኝ የጽድቅ ፍሬ ሞልቶባችሁ፥ ለክርስቶስ ቀን ተዘጋጅታችሁ ቅኖችና አለ ነውር እንድትሆኑ የሚሻለውን ነገር 
ፈትናችሁ ትወዱ ዘንድ፥ ፍቅራችሁ በእውቀትና በማስተዋል ሁሉ ከፊት ይልቅ እያደገ እንዲበዛ ይህን እጸልያለሁ። "

•2 ተሰ. 1:3 - "ወንድሞች ሆይ፥ እምነታችሁ እጅግ ስለሚያድግ የሁላችሁም የእያንዳንዳችሁ ፍቅር እርስ በርሳችሁ ስለሚበዛ፥ ሁልጊዜ ስለ እናንተ እግዚአብሔርን እንደሚገባ ልናመሰግን ግድ አለብን፤ "

•2 ጴጥ. 3:18 - "ነገር ግን በጌታችንና በመድኃኒታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ጸጋና እውቀት እደጉ።"

• ኤፌ. 4:14፣15 - "እንደ ስሕተት ሽንገላ ባለ ተንኮል በሰዎችም ማታለል ምክንያት በትምህርት ነፋስ  ሁሉ እየተፍገመገምን ወዲያና ወዲህም እየተንሳፈፍን ሕፃናት መሆን ወደ ፊት አይገባንም፥ ነገር ግን እውነትን በፍቅር እየያዝን በነገር ሁሉ ወደ እርሱ ራስ ወደሚሆን ወደ ክርስቶስ እንደግ፤"

•1ቆሮ. 14፡20 "ወንድሞች ሆይ፥ በአእምሮ ሕፃናት አትሁኑ፤ ለክፋት ነገር ሕፃናት ሁኑ እንጂ በአእምሮ የበሰሉ ሁኑ።"

• ዕብ. 6፡1-2 "ስለዚህ የክርስቶስን ነገር መጀመሪያ የሚናገረውን ቃል ትተን ወደ ፍጻሜ እንሂድ፤…(አ.መ.ት) ስለዚህ ስለ ክርስቶስ የተሰጠውን የመጀመሪያ ትምህርት ትተን ወደ  ብስለት እንሂድ"

• ቆላ. 2፡6-7 "እንግዲህ ጌታን ክርስቶስ ኢየሱስን እንደ ተቀበላችሁት በእርሱ ተመላለሱ። ሥር ሰዳችሁ በእርሱ ታነጹ፥ እንደ ተማራችሁም በሃይማኖት ጽኑ፥ ምስጋናም ይብዛላችሁ።"

• 2ጴጥ. 3፡17-18 "…በዓመፀኞቹ ስሕተት ተስባችሁ ከራሳችሁ ጽናት እንዳትወድቁ ተጠንቀቁ፤ ነገር ግን በጌታችንና በመድኃኒታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ጸጋና እውቀት እደጉ።"

• 1ቆሮ. 13፡11 "ልጅ ሳለሁ እንደ ልጅ እናገር ነበር፥ እንደ ልጅም አስብ ነበር፥ እንደ ልጅም እቈጥር ነበር፤ ጎልማሳ ሆኜ ግን የልጅነትን ጠባይ ሽሬአለሁ።"

• ዕብ. 5፡13-14 "ወተት የሚጋት ሁሉ ሕፃን ስለ ሆነ የጽድቅን ቃል አያውቅምና፤ ጠንካራ ምግብ ግን መልካሙንና ክፉውን ለመለየት በስራቸው የለመደ ልቡና ላላቸው ለፍጹማን ሰዎች ነው። …(አ.መ.ት) መልካሙን ከክፉው ለመለየት ራሳቸውን ላስለመዱ፥ ለበሰሉ ሰዎች ነው"


ይቀጥላል...


ምንጭ:- tsegaewnet.files.wordpress.com



ወደ ቻናሉ ለመ🀄️ላ🀄️ል፦ @Holy_scriptures
❤9🔥1🥰1
ደቀ መዝሙርነት.pdf
1.4 MB
👤ከ ዳንኤል መኰንን
📘 ርዕስ:- "ደቀ መዝሙርነት"


ወደ ቻናሉ ለመ🀄️ላ🀄️ል፦ @Holy_scriptures
❤5👎1
.       ──•◈•─────•◈•─
                 የዕለቱ ጥቅስ 
        ──•◈•─────•◈•─
“የሰው ስንፍና መንገዱን ታጣምምበታለች፥ ልቡም በእግዚአብሔር ላይ ይቈጣል።”
ምሳሌ 19፥3



ወደ ቻናሉ ለመ🀄️ላ🀄️ል፦ @Holy_scriptures
❤13
በቅዱሳት መጻሕፍት ውስጥ ካሉ ወንጌላት መካከል ጥቂት ምሳሌዎችን፣ 7 ምልክቶችና ሰፊ ትምህርት የያዘ መጽሐፍ የቱ ነው?
Anonymous Quiz
16%
ማቴዎስ
14%
ማርቆስ
10%
ሉቃስ
60%
ዮሐንስ
❤7
ልጁና ልጅነታችን.pdf
2 MB
ርዕስ፦ ልጁና ልጅነታችን
የጉዲፈቻ ዘይቤ ቋንቋዊና መጽሐፍ ቅዱሳዊ ትርጓሜ
ጸሐፊ፦በሳምሶን ጥላሁን


ወደ ቻናሉ ለመ🀄️ላ🀄️ል፦ @Holy_scriptures
❤4🙏2
.       ──•◈•─────•◈•─
                 የዕለቱ ጥቅስ 
        ──•◈•─────•◈•─
“እንግዲህ ከወዴት እንደ ወደቅህ አስብ ንስሐም ግባ የቀደመውንም ሥራህን አድርግ፤ አለዚያ እመጣብሃለሁ ንስሐም ባትገባ መቅረዝህን ከስፍራው እወስዳለሁ።”
ራእይ 2፥5



ወደ ቻናሉ ለመ🀄️ላ🀄️ል፦ @Holy_scriptures
❤11
በቅዱሳት መጻሕፍት ካሉት ወንጌላት መካከል የብሉይ ኪዳን ትንቢት መፈጸም ላይ ትኩረት የሚያደርገው የቱ ነው?
Anonymous Quiz
16%
ዮሐንስ
15%
ሉቃስ
6%
ማርቆስ
64%
ማቴዎስ
👍6❤2
Audio
ርዕስ፦ የቅዱስ አውግስቲን ኑዛዜ
ክፍል፦ 9
ምንጭ፦ @Reading_Life_1


ወደ ቻናሉ ለመ🀄️ላ🀄️ል፦ @Holy_scriptures
❤1
የይሁዳ መልእክት ጥናት.pdf
302.9 KB
ርዕስ፦ የይሁዳ መልእክት ጥናት

በኢትዮጵያ ወንጌላዊት ቤተክርስቲያን መካነ ኢየሱስ ታቦር ማኅበረ ምእመናን የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት ዝግጅት አገልግሎት ቡድን የተዘጋጀ

ወደ ቻናሉ ለመ🀄️ላ🀄️ል👉 @TME_bible_study
.       ──•◈•─────•◈•─
                 የዕለቱ ጥቅስ 
        ──•◈•─────•◈•─
“እግዚአብሔር ፊቱን ያብራልህ፥ ይራራልህም፤”
ዘኍልቁ 6፥25


ወደ ቻናሉ ለመ🀄️ላ🀄️ል፦ @Holy_scriptures
🥰9🙏5👍2❤1
በቅዱሳት መጻሕፍት ካሉት ወንጌላት ውስጥ ኢየሱስ ክርስቶስን እንደስቅዩ(እንደተሰቃየ) አገልጋይ የሚያስተዋውቀን መጽሐፍ የቱ ነው
Anonymous Quiz
15%
ዮሐንስ
31%
ሉቃስ
41%
ማርቆስ
13%
ማቴዎስ
❤7👍1
ቅዱሳት መጻሕፍት
በክርስትና ብስለት ማደግ "እውነትን በፍቅር እየያዝን በነገር ሁሉ  ወደ እርሱ ራስ ወደሚሆን ወደ ክርስቶስ እንደግ፤"          ኤፌ. 4፡15 መንፈሳዊ ብስለት ይጠበቅብናል ወይ? •ኤፌ. 4:11-13 "እርሱም አንዳንዶቹ ሐዋርያት፣ ሌሎቹም ነቢያት፣ ሌሎቹም ወንጌልን ሰባኪዎች፣ ሌሎቹም እረኞችና አስተማሪዎች እንዲሆኑ ሰጠ፤ ሁላችን የእግዚአብሔርን ልጅ በማመንና በማወቅ ወደሚገኝ አንድነት፣ ሙሉ…
...የቀጠለ
በክርስትና ብስለት ማደግ


ወዴት ነው የምናድገው? የእድገታችን መለኪያው ማን ነው?

"…እውነትን በፍቅር እየያዝን በነገር ሁሉ 
ወደ እርሱ ራስ ወደሚሆን ወደ ክርስቶስ 
እንደግ፤" ኤፌ. 4:15

በመካከላችን ምሳሌ የሚሆኑ ሰዎችና ማህበራት ቢኖሩም…

• "እኔ ክርስቶስን እንደምመስል…"1ቆሮ. 11፡1

• "…እኛንና ጌታን የምትመስሉ ሆናችሁ" 1ኛ ተሰ. 1፡6

• "በይሁዳ የሚኖሩትን በክርስቶስ ኢየሱስ ያሉትን የእግዚአብሔርን ማኅበሮች የምትመስሉ ሆናችኋልና" 1ተሰ. 2፡14

• ሮሜ. 8፡29 "ልጁ በብዙ ወንድሞች መካከል በኵር ይሆን ዘንድ፣ አስቀድሞ ያወቃቸው የልጁን መልክ እንዲመስሉ አስቀድሞ ደግሞ ወስኖአልና፤"

ይህን ጉዞ መቼ ጀመርን? መቼስ ይጠናቀቃል?

• ጌታ ኢየሱስን በተቀበልን ጊዜ ወደዚህ ብስለት የምናደርገው ጉዞ ይጀመራል።

• ፊሊ. 3፡12-14 "አሁን እንዳገኘሁ ወይም አሁን ፍጹም እንደ ሆንሁ አይደለም፥ ነገር ግን ስለ እርሱ በክርስቶስ ኢየሱስ የተያዝሁበትን ያን ደግሞ እይዛለሁ ብዬ እፈጥናለሁ።
ወንድሞች ሆይ፥ እኔ ገና እንዳልያዝሁት እቈጥራለሁ፤ ነገር ግን አንድ ነገር አደርጋለሁ፤ በኋላዬ ያለውን እየረሳሁ በፊቴ ያለውን ለመያዝ እዘረጋለሁ፥ በክርስቶስ ኢየሱስ ከፍ ከፍ 
ያለውን የእግዚአብሔርን መጥራት ዋጋ እንዳገኝ ምልክትን እፈጥናለሁ።"

መንፈሳዊ ብስለት ያልሆነው ነገር ምንድን ነው?

1. መንፈሳዊ ብስለት የእድሜ ጉዳይ አይደለም።

• መንፈሳዊ እድገት ጊዜ፣ ጥረት፣ ወዘተ የሚጠይቅ ጉዳይ መሆኑ የሚስተባበል አይደለም። ማንም ሰው በአንድ ምሽት በሳል አይሆንም (ሉቃ. 2፡52)።

• ማስጠንቀቂያ፦ ሆኖም ግን በጌታ ቤት ረጅም አመታት አስቆጥሮ ሳይበስሉ መክረም ይኖራል። በእግዚአብሔር ቤት 50 እና 60 አመት ያስቆጠሩ መንፈሳዊ ሕጻናት ይኖራሉ። መንፈሳዊ ብስለት በእግዚአብሔር ቤት ጊዚያትን ከመቁጠር ያለፈ ነው።

• ዕብ. 5፥12 "ከጊዜው የተነሳ አስተማሪዎች ልትሆኑ ሲገባችሁ፥ አንድ ሰው ስለ እግዚአብሔር ቃላት መጀመሪያ ያለውን የሕፃንነትን ትምህርት እንዲያስተምራችሁ እንደ ገና ያስፈልጋችኋልና፤ 
የሚያስፈልጋችሁም ወተት ነው እንጂ ጠንካራ ምግብ አይደለም።"

2. መንፈሳዊ ብስለት ውጫዊ ጉዳይ አይደለም።

አንዳንድ ሰዎች በውጫዊ ይዘታቸው (ንግግራቸው) በሳል መንፈሳዊያን ሊመስሉ ይችላሉ። መንፈሳዊ ብስለት የኑሮ ጉዳይ እንጂ የንግግር ጉዳይ አይደለም። የመለወጥ እንጂ የመምሰል ጉዳይ አይደለም::

• ሉቃ. 11፡39-42 "ጌታም እንዲህ አለው፦ አሁን እናንተ ፈሪሳውያን የጽዋውንና የወጭቱን ውጭ ታጠራላችሁ፥ ውስጣችሁ ግን ቅሚያና ክፋት ሞልቶበታል እናንት ደንቆሮዎች፥ 
የውጭውን የፈጠረ የውስጡን ደግሞ አልፈጠረምን? ነገር ግን በውስጥ ያለውን ምጽዋት አድርጋችሁ ስጡ፥ እነሆም፥ ሁሉ ንጹሕ ይሆንላችኋል።…"

3. መንፈሳዊ ብስለት የክንውን ጉዳይ አይደለም።

• የአገልግሎት ቦታና የሃላፊነት ብዛትም የብስለት መለኪያዎች አይደሉም።

• ብስለት እውቀት የማከማቸት ጉዳይም አይደለም።

• ሉቃ. 11፡52 "እናንተ ሕግ አዋቂዎች፥ የእውቀትን መክፈቻ ስለ ወሰዳችሁ፥ ወዮላችሁ ራሳችሁ አልገባችሁም የሚገቡትንም ከለከላችሁ።"

4. በመንፈሳዊ ስጦታዎች መሞላት፣ በመንፈሳዊ ስጦታዎች ማገልገል/መጠቀም ማለት አይደለም።

• መንፈስ ቅዱስን መግለጥ፣ ጥበብን መናገር፥ እውቀትን መናገር፣ የመፈወስ ስጦታ፥ ተአምራትን ማድረግ፣ ትንቢትን መናገር፥ መናፍስትን መለየት፥ በልዩ ዓይነት ልሳን መናገር፥ በልሳኖች 
የተነገረውን መተርጎም…….የመንፈሳዊ ብስለት መለኪያዎች አይደሉም።

ንጽጽር

• 1ቆሮ. 1፡7 "እንደዚህ የጌታችንን የኢየሱስ ክርስቶስን መገለጥ ስትጠባበቁ አንድ የጸጋ ስጦታ እንኳ አይጎድልባችሁም፤"

• 1ቆሮ. 3፡1-3 "እኔም፥ ወንድሞች ሆይ፥ የሥጋ እንደ መሆናችሁ፥ በክርስቶስም ሕፃናት እንደ መሆናችሁ እንጂ መንፈሳውያን እንደ መሆናችሁ ልናገራችሁ አልቻልሁም። ገና ጽኑ መብል ለመብላት አትችሉም ነበርና ወተት 
ጋትኋችሁ፤ ገና ሥጋውያን ናችሁና እስከ አሁን ድረስ ገና አትችሉም። ቅናትና ክርክር ስለሚገኝባችሁ ሥጋውያን መሆናችሁ አይደላችሁምን?"


ይቀጥላል...


ምንጭ:- tsegaewnet.files.wordpress.com



ወደ ቻናሉ ለመ🀄️ላ🀄️ል፦ @Holy_scriptures
❤5
Audio
👉ርዕስ፦ የካታኮምቡ ሰማዕት
🗣ትርጉም፦ በአማረ ማሞ
መካነ ኢየሱስ ሥነ ጽሑፍ ክፍል።
📻ሙሉ ትረካ
⏱️አጠቃላይ የሚፈጀው ሰዓት፦ 3:49:45


ወደ ቻናሉ ለመ🀄️ላ🀄️ል👉 @TME_bible_study
👍5❤1
.       ──•◈•─────•◈•─
                 የዕለቱ ጥቅስ 
        ──•◈•─────•◈•─
“እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ በመንገድ ላይ ቁሙ ተመልከቱም፥ የቀደመችውንም መንገድ ጠይቁ፤ መልካሚቱ መንገድ ወዴት እንደ ሆነች እወቁ፥ በእርስዋም ላይ ሂዱ፥ ለነፍሳችሁም ዕረፍት ታገኛላችሁ፤ እነርሱ ግን፦ አንሄድባትም አሉ።”
ኤርምያስ 6፥16



ወደ ቻናሉ ለመ🀄️ላ🀄️ል፦ @Holy_scriptures
❤10🙏2
በቅዱሳት መጻሕፍት ውስጥ በትንቢተ ኢሳይያስ "አማኑኤል" ስለሚባለው ልጅ ምልክት እንዲጠይቅ የተነገረ የይሁዳ ንጉሥ ማን ነው?
Anonymous Quiz
9%
ምናሴ
39%
ሕዝቅያስ
28%
አካዝ
23%
ኢዮሳፍጥ
❤4
AI_in_Church_Haylat_032026.pdf
199.1 KB
"ለቤተክርስቲያን የቀረበ መልእክት: AI በአማኞች ልብ ውስጥ እያደረገ ያለው ድምፅ አልባ ወረራ" በዶ/ር ኃይለልዑል ጥበቡ

በዚህ አጭር ጽሁፍ ሰው ሰራሽ አስተውሎት(AI) ለቤተ ክርስቲያን ይዞ የመጣውን ጋሬጣ በማጋራት ፥ ለቤተ ክርስቲያን መጋቢያን አማራጭ መፍትሄ በማቅረብ ቤተ ክርስቲያን በኋላ ይዞ የሚመጣውን እኩይ ነቅሶ በማውጣት በንቃትና በማስተዋል ቴክኖሎጂን እንድትጠቀም ይመክራሉ። ዶ/ር ኃይለልዑል ጥበቡ በአሜሪካ በሚገኝ ዩኒቨርሲቲ የAI ፕሮፌሰር ሲሆኑ፣ በዘርፉም የዶክትሬት (PhD) ዲግሪ አላቸው።


ወደ ቻናሉ ለመ🀄️ላ🀄️ል፦ @Holy_scriptures
.       ──•◈•─────•◈•─
                 የዕለቱ ጥቅስ 
        ──•◈•─────•◈•─
“ስትሄድም ይመራሃል፤ ስትተኛ ይጠብቅሃል፤ ስትነሣ ያነጋግርሃል።”
ምሳሌ 6፥22


ወደ ቻናሉ ለመ🀄️ላ🀄️ል፦ @Holy_scriptures
❤13👏1
#እራሳችንን_እንመርምር


“የሎጥን ሚስት አስቡአት።”
ሉቃስ 17፥32

የእግዚአብሔር መንግሥት በሙላት ልትመጣ ነው። ጌታችንም ይህን ታላቅ መምጣቱን ሲያወሳ መጠንቀቅና መትጋት እንደሚገባ ሊያሳስበን የሎጥን ሚስት እንደምሳሌ ይጠቅስልናል። እርሷ ለዚህ ነገር ለምን እንደማስጠንቀቂያ ተጠቀሰች? እስቲ ከእርሷ ጋር ሕይወታችንን እያስተያየን እራሳችንን እንመርምር።


ወደ ቻናሉ ለመ🀄️ላ🀄️ል፦ @Holy_scriptures
❤8👍3
.       ──•◈•─────•◈•─
                 የዕለቱ ጥቅስ 
        ──•◈•─────•◈•─
“ከክፉ የጎልማሳነት ምኞት ግን ሽሽ፥ በንጹሕም ልብ ጌታን ከሚጠሩ ጋር ጽድቅን እምነትን ፍቅርን ሰላምን አጥብቀህ ተከተል።”
2ኛ ጢሞቴዎስ 2፥22



ወደ ቻናሉ ለመ🀄️ላ🀄️ል፦ @Holy_scriptures
❤14
በቅዱሳት መጻሕፍት ውስጥ በነቢዩ ኢሳይያስ “በፊትህ እሄዳለሁ ተራሮችንም ትክክል አደርጋለሁ፥ . . .” ተብሎ ትንቢት የተነገረለት ንጉሥ ማን ነው?
Anonymous Quiz
10%
ኢየሱስ
24%
ዘሩባቤል
50%
ቂሮስ
2%
ሴዴቅያስ
14%
ሕዝቅያስ
❤3👍1