ቅዱሳት መጻሕፍት
7.91K subscribers
1.5K photos
61 videos
365 files
855 links
በዚህ ቻናል

👉ቅዱሳት መጻሕፍት ይጠናሉ::
👉መጽሐፍ ቅዱሳዊ ትምህርቶች ይቀርባሉ::
👉 ለቅዱሳት መጽሐፍት ጥናት የሚያግዙ መጻሕፍት ይለቀቃሉ።

⭐️⭐️⭐️⭐️⭐️

@Holy_scriptures
Download Telegram
#እራሳችንን_እንመርምር


አዲስ ዓመትስ አይደል? እግዚአብሔር ሰፍሮና መዝኖ በሰጠን ዕድሜና ዘመን ምን ያህል ውጤታማ ነን?

“አቤቱ፥ ፍጻሜዬን አስታውቀኝ፥ የዘመኔ ቍጥሮች ምን ያህል እንደ ሆኑ፥ እኔ ምን ያህል ወደ ኋላ እንደምቀር አውቅ ዘንድ።”
መዝሙር 39፥4

“እግዚአብሔር ሆይ፤ የሕይወቴን ፍጻሜ፣ የዘመኔንም ቍጥር አስታውቀኝ፤ አላፊ ጠፊ መሆኑንም ልረዳ።”
መዝሙር 39፥4 (አዲሱ መ.ት)


ወደ ቻናሉ ለመ🀄️ላ🀄️ል፦ @Holy_scriptures
❤15👏1
.       ──•◈•─────•◈•─
                 የዕለቱ ጥቅስ 
        ──•◈•─────•◈•─
“የእግዚአብሔርን ፈቃድ አድርጋችሁ የተሰጣችሁን የተስፋ ቃል እንድታገኙ መጽናት ያስፈልጋችኋልና።”
ዕብራውያን 10፥36



ወደ ቻናሉ ለመ🀄️ላ🀄️ል፦ @Holy_scriptures
❤17🔥3🤝1
በቅዱሳት መጻሕፍት ውስጥ የክርስቶስን የበላይነት የሚያጎላውና የኖስትሲዝምን ትምህርት በመቃወም የተጻፈው የትኛው መልእክት ወይም መጽሐፍ ነው?
Anonymous Quiz
11%
ኤፌሶን
16%
ሮሜ
63%
ቆላስይስ
11%
ፊልጵስዩስ
❤‍🔥4❤3🔥3
እየጨመረ የሚሄድ ሕይወት
                
             

የጠለቀ መንፈሳዊ ጉዞ ለመጓዝና እየጨመረ የሚሄድ ርካታና እረፍት እንድናይ ካስፈለገ፣የክርስትና ሕይወት ትጋትን ይጠይቀናል(ዕብ 4፥11)፡፡ በተለያየ ቦታ በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ቃሉ እንደሚያስተምረን ትጋታችን እየጨመረ ሲሄድ፣የእግዚአብሔር ጸጋም በሕይወታችን እየጨመረ ይሄዳል፡፡ በእንደዚህ ዓይነት ግሥገሣ ውስጥ ባለማሰለስ ስንገኝ፣እሱን ለማወቅ ያለን ራብ እየተቀጣጠለ ስለሚመጣ፣እየጨመረ ለሚሄድ ፍለጋ እንጠናከራለን፡፡ ይህንን በእንግሊዝኛው አገላለጽ positive vicious cycle ይሉታል፡፡ ማለትም ትጋቱ የጨመረ መንፈሳዊ ራብን ይወልዳል፤የጨመረው መንፈሳዊ ራብ ደግሞ ሌላ ከፍ ያለ ትጋትንና ግሥገሣን ይወልዳል፡፡ መቼም ይሄ ኡደት ማቆሚያ የለውም እኛ በሥጋዊ አካሄዶች እስካላጠፋነው ድረስ!

በነገራችን ላይ እየጨመረ የሚሄድ የክርስትና ሕይወት ብዙ ግብዓቶችን ይፈልጋል ፡፡ መልካም የእምነት ውጊያንና ዲያቢሎስን በኃይል ጸንቶ መቃወም ይጠይቃል ፡፡ የእግዚአብሔርን ቃል ሳይታክቱ ማሰላሰልና በፊቱ ጥሩ የሆኑ ጊዜዎችን ማሳለፍ ግድ ይለናል ፡፡ ሁኔታዎችንና ሥጋችንን ሳናዳምጥ የሚከፈሉ ዋጋዎችን እንደ ጌታ ፈቃድ መክፈልን ይጠይቀናል፡፡ የእግዚአብሔር ቃል ትእዛዝ አለው፤ደግሞም በረከት አለው፡፡ ትእዛዙን በእግዚአብሔር ጸጋ ተደግፈን ሳንፈጽምና ሳናከናውን፣በረከት መጠበቅ ሞኝነት ነው ፡፡ ስለዚህ ጌታ በምናደርጋቸው ነገሮች ሁሉ እንዲባርከን፣ መታዘዝ ልንወስደው የሚገባን እርምጃ ነው፡፡

ከዚህ ጋር በተያያዘ አንድ መርሕ እዚህ ጋ ልጥቀስ፡፡ሦስት በተሰናሰለ መንገድ የተቀመጡ ድርጊቶች በውጤት ሂደት እንዲህ ተቀምጠዋል፡-

ድርጊት(Action)——->ልማድ(Habit)——->ጠባይ(character)

ይህንን መርሕ ለመግለጽ ጸሎትን እንደ ምሳሌ ልውሰድ ፡፡ ጸሎትን ደጋግመን ስናደርገው ወደ ልማድነት ይቀየራል ፡፡ በሕይወታችን ልማድ እየሆነ የመጣውን ተግባር እየጨመርን ደጋግመን ስናደርገው፣ጠባያችን ወይም መገለጫ ባሕርያችን ይሆናል ፡፡ ከዚያማ ውጤቱ እንዲህ ይሆናል፡-

“መጸለይ እንጂ አለመጸለይ አንችልም፡፡”

“በፊቱ መሆን እንጂ አለመሆን ያቅተናል፡፡”

እጅግ ሊጓጓለት የሚገባ ድንቅ ለውጥ!

የላይኛውን ሐሳብ የሚደግፉና የክርስትና ሕይወት እየተቀጣጠለ፣እያደገና እየጨመረ የሚሄድ ሕይወት እንደ ሆነ የሚጠቁሙ ብዙ ክፍሎች አሉ ፡፡ ለምሳሌ ሦስቱን ልጥቀስ፡-

“እስከ እግዚአብሔር ፍጹም ሙላት ደርሳችሁ ትሞሉ ዘንድ” (ኤፌሶን 3፥19)
“በመንፈስ የምትቃጠሉ ሁኑ” (ሮሜ 12፥11)

“መንፈስ ይሙላባችሁ እንጂ በወይን ጠጅ አትስከሩ ይህ ማባከን ነውና” /ብዙ የሚያሰክሩ ነገሮች እንዳሉ ልብ ይሏል/(ኤፌሶን 5፥16-20)

የእግዚአብሔር ሰው ስሚዝ ዊግልስዎርዝ እንዲህ ብሎ ነበር፡-“If you are in the same place today as you were yesterday, you are a backslider.”(ትርጉሙ፡-በዛሬው ቀን ትላንትና የነበርክበት ቦታ ላይ ከተገኘህ የኋሊት እየሄድክ ነው)

በተሰጠ ማንነት፣ልባችን መሉ በሙሉ በጌታ ላይ ሆኖ ከላይ በተጠቀሰው ዓይነት ፍለጋ(craving) እና ትጋት ስንቀጥል፣የጌታ አብሮሆት ከመቸው በሚበልጥ ሁኔታ በሕይወታችን ዕውን ይሆናል ፡፡ ከዚህም የተነሣ የምናገኘው የመጀመሪያው በረከት በቃላት ልንገልጸው የማንችለው ሰላም፣መረጋጋትና ደስታ ይሆናል ፡፡ መንፈሳዊ መረዳታችንም እየጨመረ ስለሚሄድ፣ጌታን በሚገባ እያወቅነው እንመጣለን፡፡ስለዚህ ለውጣችን ወደ ኋላ የማይቀለበስና ዘላቂ ይሆናል ፡፡ መንፈሳዊ ዓይኖቻችን በጨመረ ሁኔታ እየተከፈቱ ስለሚመጡ፣ብዙ ረብ የሌላቸውን ነገሮች የመጣል መነሣሣትና አቅም እያገኘን እንመጣለን ፡፡

እንደዚህ በጽናት ሳናሰልስ የጌታን ፊት በጨመረ ሁኔታ በፈለግን ቁጥር፣የእግዚአብሔር ኃይል በውስጣችን እየጨመረ ስለሚሄድ፣ብዙ ቀንበሮች ከሕይወታችን ይሰበራሉ ፡፡ ስለዚህም“ሸክሙ ከጫንቃህ ቀንበሩም ከትከሻህ ላይ ይሰበራል” የሚለው ቃል በሕይወታችን ይፈጸማል (ኢሳ.10፡27)፡፡ እናም ከበፊቱ ይልቅ በሕልውናው ውስጥ መቆየት አያስቸግረንም ፡፡ ብዙ ሰዓት በፊቱ መሆንም ያለ ጥርጥር ፈቃዳችን ይሆናል ፡፡ እሱን በአካል ባናየውም እንኳ፣በመንፈስ እያየነው በጨመረ ሁኔታ እንወደዋለን፡፡ ቃሉ እንዲህ ይላልና፡-

“እርሱንም ሳታዩት ትወዱታላችሁ፤ አሁንም ምንም ባታዩት በእርሱ አምናችሁ የእምነታችሁን ፍጻሜ እርሱም የነፍሳችሁን መዳን እየተቀበላችሁ በማይነገርና ክብር በሞላበት ሐሤት ደስ ይላችኋል” (1 ጴጥሮስ 1፥8-9)

አዎ፣በጨመረ ሁኔታ በመንፈስ እያየነው ሰንቀጥል፣ልባችንም በፍቅሩ እሳት በጨመረ ሁኔታ ስለሚጋይ፣ጉገታችንና ቅድሚያ የምንሰጠው ነገር ሁልጊዜም በፊቱ መገኘት ይሆናል ፡፡ ቢሆንም ይሄ ውጤት በቀላል እንደሚመጣ ማሰብ የለብንም ፡፡ በጌታ ጸጋ ብዙ ትጋት፣ብዙ ፍለጋ፣ብዙ ቁፈራ፣በጌታ ፊት አዘውትሮ መሆንን ይጠይቀናል ፡፡

ለዚህ ሐሳቤ ጥሩ እይታ የሚሰጠን ኢዮብ 28፥1-11 ነው ፡፡ ይህ የምንባብ ክፍል የማዕድን ሠራተኛ ከባዶ ተነሥቶ የሚያደርገውን ግሥገሣ ነው የሚያሳየው ፡፡ “ዓይኑ ዕንቁን እስክታይ ድረስ” ፣ “የተሸፈነው ነገር ወደ ብርሃን እስኪወጣ ድረስ” ይተጋል ፡፡ እጁን ወደ ቡላድ ድንጋይ ይዘረጋል ፡፡ መጨረሻ ላይ ከብዙ እልህ አስጨራሽ ትግልና ጉዞ በኋላ የከበሩ ማዕድናትን ያገኛል፤ክፍሉ የልፋቱን ውጤት እንዲህ ይገልጸዋልና ፡-

“ሰው ወደ ቡላድ ድንጋይ እጁን ይዘረጋል፤ተራራውንም ከመሠረቱይገለብጣል። ከድንጋይ ውስጥ መንዶልዶያ ይወቅራል፤ ዓይኑምዕንቍን ሁሉ ታያለች።   ፈሳሹም እንዳይንጠባጠብ ይገድባል፤የተሰወረውንም ነገር ወደ ብርሃን ያወጣል።”(ቁ.9-11)

አዎ ይህ ክፍል ምሳሌያዊ በሆነ አገላለጽ፣እንደ ማዕድን ሠራተኛው ያለ መታከት እንድንተጋና የጌታን ፊት እንድንፈልግ ያስተምረናል ፡፡ በቃሉ ውስጥ፣በጸሎት ኅብረት ውስጥ፣በትምህርት ውስጥ፣በጥሞና ጊዜና በተለያዩ ፕሮግራሞች ውስጥ፣ሳናሰልስ እንድንፈልገው ይጠቁመናል፡፡

የእግዚአብሔር ቃል ተግተው “የሚሹኝ ምስጉኖች/የተባረኩ ናቸው”(ምሳሌ 8፡34) ይላልና፤ “እናንተም ትጠሩኛለችሁ፤ሄዳችሁም ወደ እኔትጸልያላችሁ፣እኔም እሰማችኋለሁ። እናንተ ትሹኛላችሁ፣በፍጹምልባችሁም ከሻችሁኝ ታገኙኛላችሁ። ከእናንተም ዘንድ እገኛለሁ፡፡”(ኤር.29፥13-14) ይላልና ጨክኖ የጌታን ፊት የሚፈልግ ሰው ይዋል ይደር እንጂ፣የእግዚአብሔር በረከት ታገኘዋለች፡፡

አዎ፣ጌታ አጥብቀው ለሚሹት ሰዎች በእርግጥ ይገለጣል ፡፡ ጉብኝቱ ደግሞ ልባችን ላይ የሚያመጣው ለውጥ ቀላል አይሆንም ፡፡ የበለጠ እንድናየው፣የበለጠ በእርሱ ላይ እንድንደገፍና እንድንጠጋው ያደርገናል ፡፡ በተጨማሪም ጌታ ተገልጦ ሕይወታችንን ሲጎበኝ የሚመጣው ለውጥ ለሌሎች በረከት ያደርገናልና በትጋትና በጨመረ ሁኔታ ተግተን እንፈልገው!

“አሁን እንዳገኘሁ ወይም አሁን ፍጹም እንደ ሆንሁ አይደለም፣ነገር ግን ስለ እርሱ በክርስቶስ ኢየሱስ የተያዝሁበትን ያን ደግሞ እይዛለሁ ብዬ እፈጥናለሁ ። ወንድሞች ሆይ፣እኔ ገና እንዳልያዝሁት እቈጥራለሁ፤ ነገር ግን አንድ ነገር አደርጋለሁ፤ በኋላዬ ያለውን እየረሳሁ በፊቴ ያለውን ለመያዝ እዘረጋለሁ” ፊልጵስዩስ 3፡7-13)


ምንጭ:-ባለጸጋ ክርስትያን መጽሔት



ወደ ቻናሉ ለመ🀄️ላ🀄️ል፦ @Holy_scriptures
👍7❤5👎2
.       ──•◈•─────•◈•─
                 የዕለቱ ጥቅስ 
        ──•◈•─────•◈•─
“አንተ እጅህን ትከፍታለህ፥ ሕይወት ላለውም ሁሉ መልካምን ታጠግባለህ።”
መዝሙር 145፥16



ወደ ቻናሉ ለመ🀄️ላ🀄️ል፦ @Holy_scriptures
👍9🥰6❤4
በቅዱሳት መጻሕፍት ካሉ ወንጌላት ውስጥ ስለመንግሥተ ሰማያት ትኩረት የሚያደርገው መጽሐፍ የቱ ነው?
Anonymous Quiz
55%
ማቴዎስ
10%
ማርቆስ
8%
ሉቃስ
27%
ዮሐንስ
👍4❤1🔥1
በክርስትና ብስለት ማደግ


"እውነትን በፍቅር እየያዝን በነገር ሁሉ 
ወደ እርሱ ራስ ወደሚሆን ወደ ክርስቶስ እንደግ፤"
         ኤፌ. 4፡15

መንፈሳዊ ብስለት ይጠበቅብናል ወይ?

•ኤፌ. 4:11-13 "እርሱም አንዳንዶቹ ሐዋርያት፣ ሌሎቹም ነቢያት፣ ሌሎቹም ወንጌልን ሰባኪዎች፣ ሌሎቹም እረኞችና አስተማሪዎች እንዲሆኑ ሰጠ፤ ሁላችን የእግዚአብሔርን ልጅ በማመንና በማወቅ ወደሚገኝ አንድነት፣ ሙሉ ሰውም ወደ መሆን/to a mature 
man፣ የክርስቶስም ሙላቱ ወደሚሆን ወደ ሙላቱ ልክ እስክንደርስ ድረስ፣ ቅዱሳን አገልግሎትን ለመሥራትና ለክርስቶስ አካል ሕንጻ ፍጹማን ይሆኑ ዘንድ፡፡"

•ቆላ. 1፡28-29 "እኛም በክርስቶስ ፍጹም የሚሆን ሰውን ሁሉ እናቀርብ ዘንድ ሰውን ሁሉ እየገሠጽን ሰውንም ሁሉ በጥበብ ሁሉ እያስተማርን የምንሰብከው እርሱ ነው፡፡ ለዚህም ነገር ደግሞ፣ በእኔ በኃይል እንደሚሠራ እንደ አሠራሩ እየተጋደልሁ፣ እደክማለሁ፡፡"

•ቆላ. 1፡9 "ስለዚሁ እኛ ደግሞ ይህን ከሰማንበት ቀን ጀምረን የፈቃዱ እውቀት መንፈሳዊ ጥበብንና አእምሮን ሁሉ እንዲሞላባችሁ እየለመንን፥ ስለ እናንተ ጸሎትን አልተውንም።"

•ፊሊ. 1:9-11 "ለእግዚአብሔርም ክብርና ምስጋና ከኢየሱስ ክርስቶስ የሚገኝ የጽድቅ ፍሬ ሞልቶባችሁ፥ ለክርስቶስ ቀን ተዘጋጅታችሁ ቅኖችና አለ ነውር እንድትሆኑ የሚሻለውን ነገር 
ፈትናችሁ ትወዱ ዘንድ፥ ፍቅራችሁ በእውቀትና በማስተዋል ሁሉ ከፊት ይልቅ እያደገ እንዲበዛ ይህን እጸልያለሁ። "

•2 ተሰ. 1:3 - "ወንድሞች ሆይ፥ እምነታችሁ እጅግ ስለሚያድግ የሁላችሁም የእያንዳንዳችሁ ፍቅር እርስ በርሳችሁ ስለሚበዛ፥ ሁልጊዜ ስለ እናንተ እግዚአብሔርን እንደሚገባ ልናመሰግን ግድ አለብን፤ "

•2 ጴጥ. 3:18 - "ነገር ግን በጌታችንና በመድኃኒታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ጸጋና እውቀት እደጉ።"

• ኤፌ. 4:14፣15 - "እንደ ስሕተት ሽንገላ ባለ ተንኮል በሰዎችም ማታለል ምክንያት በትምህርት ነፋስ  ሁሉ እየተፍገመገምን ወዲያና ወዲህም እየተንሳፈፍን ሕፃናት መሆን ወደ ፊት አይገባንም፥ ነገር ግን እውነትን በፍቅር እየያዝን በነገር ሁሉ ወደ እርሱ ራስ ወደሚሆን ወደ ክርስቶስ እንደግ፤"

•1ቆሮ. 14፡20 "ወንድሞች ሆይ፥ በአእምሮ ሕፃናት አትሁኑ፤ ለክፋት ነገር ሕፃናት ሁኑ እንጂ በአእምሮ የበሰሉ ሁኑ።"

• ዕብ. 6፡1-2 "ስለዚህ የክርስቶስን ነገር መጀመሪያ የሚናገረውን ቃል ትተን ወደ ፍጻሜ እንሂድ፤…(አ.መ.ት) ስለዚህ ስለ ክርስቶስ የተሰጠውን የመጀመሪያ ትምህርት ትተን ወደ  ብስለት እንሂድ"

• ቆላ. 2፡6-7 "እንግዲህ ጌታን ክርስቶስ ኢየሱስን እንደ ተቀበላችሁት በእርሱ ተመላለሱ። ሥር ሰዳችሁ በእርሱ ታነጹ፥ እንደ ተማራችሁም በሃይማኖት ጽኑ፥ ምስጋናም ይብዛላችሁ።"

• 2ጴጥ. 3፡17-18 "…በዓመፀኞቹ ስሕተት ተስባችሁ ከራሳችሁ ጽናት እንዳትወድቁ ተጠንቀቁ፤ ነገር ግን በጌታችንና በመድኃኒታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ጸጋና እውቀት እደጉ።"

• 1ቆሮ. 13፡11 "ልጅ ሳለሁ እንደ ልጅ እናገር ነበር፥ እንደ ልጅም አስብ ነበር፥ እንደ ልጅም እቈጥር ነበር፤ ጎልማሳ ሆኜ ግን የልጅነትን ጠባይ ሽሬአለሁ።"

• ዕብ. 5፡13-14 "ወተት የሚጋት ሁሉ ሕፃን ስለ ሆነ የጽድቅን ቃል አያውቅምና፤ ጠንካራ ምግብ ግን መልካሙንና ክፉውን ለመለየት በስራቸው የለመደ ልቡና ላላቸው ለፍጹማን ሰዎች ነው። …(አ.መ.ት) መልካሙን ከክፉው ለመለየት ራሳቸውን ላስለመዱ፥ ለበሰሉ ሰዎች ነው"


ይቀጥላል...


ምንጭ:- tsegaewnet.files.wordpress.com



ወደ ቻናሉ ለመ🀄️ላ🀄️ል፦ @Holy_scriptures
❤9🔥1🥰1
ደቀ መዝሙርነት.pdf
1.4 MB
👤ከ ዳንኤል መኰንን
📘 ርዕስ:- "ደቀ መዝሙርነት"


ወደ ቻናሉ ለመ🀄️ላ🀄️ል፦ @Holy_scriptures
❤5👎1
.       ──•◈•─────•◈•─
                 የዕለቱ ጥቅስ 
        ──•◈•─────•◈•─
“የሰው ስንፍና መንገዱን ታጣምምበታለች፥ ልቡም በእግዚአብሔር ላይ ይቈጣል።”
ምሳሌ 19፥3



ወደ ቻናሉ ለመ🀄️ላ🀄️ል፦ @Holy_scriptures
❤13
በቅዱሳት መጻሕፍት ውስጥ ካሉ ወንጌላት መካከል ጥቂት ምሳሌዎችን፣ 7 ምልክቶችና ሰፊ ትምህርት የያዘ መጽሐፍ የቱ ነው?
Anonymous Quiz
16%
ማቴዎስ
14%
ማርቆስ
10%
ሉቃስ
59%
ዮሐንስ
❤7
ልጁና ልጅነታችን.pdf
2 MB
ርዕስ፦ ልጁና ልጅነታችን
የጉዲፈቻ ዘይቤ ቋንቋዊና መጽሐፍ ቅዱሳዊ ትርጓሜ
ጸሐፊ፦በሳምሶን ጥላሁን


ወደ ቻናሉ ለመ🀄️ላ🀄️ል፦ @Holy_scriptures
❤4🙏2
.       ──•◈•─────•◈•─
                 የዕለቱ ጥቅስ 
        ──•◈•─────•◈•─
“እንግዲህ ከወዴት እንደ ወደቅህ አስብ ንስሐም ግባ የቀደመውንም ሥራህን አድርግ፤ አለዚያ እመጣብሃለሁ ንስሐም ባትገባ መቅረዝህን ከስፍራው እወስዳለሁ።”
ራእይ 2፥5



ወደ ቻናሉ ለመ🀄️ላ🀄️ል፦ @Holy_scriptures
❤11
በቅዱሳት መጻሕፍት ካሉት ወንጌላት መካከል የብሉይ ኪዳን ትንቢት መፈጸም ላይ ትኩረት የሚያደርገው የቱ ነው?
Anonymous Quiz
16%
ዮሐንስ
15%
ሉቃስ
6%
ማርቆስ
64%
ማቴዎስ
👍6❤2
Audio
ርዕስ፦ የቅዱስ አውግስቲን ኑዛዜ
ክፍል፦ 9
ምንጭ፦ @Reading_Life_1


ወደ ቻናሉ ለመ🀄️ላ🀄️ል፦ @Holy_scriptures
❤1
የይሁዳ መልእክት ጥናት.pdf
302.9 KB
ርዕስ፦ የይሁዳ መልእክት ጥናት

በኢትዮጵያ ወንጌላዊት ቤተክርስቲያን መካነ ኢየሱስ ታቦር ማኅበረ ምእመናን የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት ዝግጅት አገልግሎት ቡድን የተዘጋጀ

ወደ ቻናሉ ለመ🀄️ላ🀄️ል👉 @TME_bible_study
.       ──•◈•─────•◈•─
                 የዕለቱ ጥቅስ 
        ──•◈•─────•◈•─
“እግዚአብሔር ፊቱን ያብራልህ፥ ይራራልህም፤”
ዘኍልቁ 6፥25


ወደ ቻናሉ ለመ🀄️ላ🀄️ል፦ @Holy_scriptures
🥰9🙏5👍2❤1
በቅዱሳት መጻሕፍት ካሉት ወንጌላት ውስጥ ኢየሱስ ክርስቶስን እንደስቅዩ(እንደተሰቃየ) አገልጋይ የሚያስተዋውቀን መጽሐፍ የቱ ነው
Anonymous Quiz
16%
ዮሐንስ
30%
ሉቃስ
41%
ማርቆስ
13%
ማቴዎስ
❤7👍1
ቅዱሳት መጻሕፍት
በክርስትና ብስለት ማደግ "እውነትን በፍቅር እየያዝን በነገር ሁሉ  ወደ እርሱ ራስ ወደሚሆን ወደ ክርስቶስ እንደግ፤"          ኤፌ. 4፡15 መንፈሳዊ ብስለት ይጠበቅብናል ወይ? •ኤፌ. 4:11-13 "እርሱም አንዳንዶቹ ሐዋርያት፣ ሌሎቹም ነቢያት፣ ሌሎቹም ወንጌልን ሰባኪዎች፣ ሌሎቹም እረኞችና አስተማሪዎች እንዲሆኑ ሰጠ፤ ሁላችን የእግዚአብሔርን ልጅ በማመንና በማወቅ ወደሚገኝ አንድነት፣ ሙሉ…
...የቀጠለ
በክርስትና ብስለት ማደግ


ወዴት ነው የምናድገው? የእድገታችን መለኪያው ማን ነው?

"…እውነትን በፍቅር እየያዝን በነገር ሁሉ 
ወደ እርሱ ራስ ወደሚሆን ወደ ክርስቶስ 
እንደግ፤" ኤፌ. 4:15

በመካከላችን ምሳሌ የሚሆኑ ሰዎችና ማህበራት ቢኖሩም…

• "እኔ ክርስቶስን እንደምመስል…"1ቆሮ. 11፡1

• "…እኛንና ጌታን የምትመስሉ ሆናችሁ" 1ኛ ተሰ. 1፡6

• "በይሁዳ የሚኖሩትን በክርስቶስ ኢየሱስ ያሉትን የእግዚአብሔርን ማኅበሮች የምትመስሉ ሆናችኋልና" 1ተሰ. 2፡14

• ሮሜ. 8፡29 "ልጁ በብዙ ወንድሞች መካከል በኵር ይሆን ዘንድ፣ አስቀድሞ ያወቃቸው የልጁን መልክ እንዲመስሉ አስቀድሞ ደግሞ ወስኖአልና፤"

ይህን ጉዞ መቼ ጀመርን? መቼስ ይጠናቀቃል?

• ጌታ ኢየሱስን በተቀበልን ጊዜ ወደዚህ ብስለት የምናደርገው ጉዞ ይጀመራል።

• ፊሊ. 3፡12-14 "አሁን እንዳገኘሁ ወይም አሁን ፍጹም እንደ ሆንሁ አይደለም፥ ነገር ግን ስለ እርሱ በክርስቶስ ኢየሱስ የተያዝሁበትን ያን ደግሞ እይዛለሁ ብዬ እፈጥናለሁ።
ወንድሞች ሆይ፥ እኔ ገና እንዳልያዝሁት እቈጥራለሁ፤ ነገር ግን አንድ ነገር አደርጋለሁ፤ በኋላዬ ያለውን እየረሳሁ በፊቴ ያለውን ለመያዝ እዘረጋለሁ፥ በክርስቶስ ኢየሱስ ከፍ ከፍ 
ያለውን የእግዚአብሔርን መጥራት ዋጋ እንዳገኝ ምልክትን እፈጥናለሁ።"

መንፈሳዊ ብስለት ያልሆነው ነገር ምንድን ነው?

1. መንፈሳዊ ብስለት የእድሜ ጉዳይ አይደለም።

• መንፈሳዊ እድገት ጊዜ፣ ጥረት፣ ወዘተ የሚጠይቅ ጉዳይ መሆኑ የሚስተባበል አይደለም። ማንም ሰው በአንድ ምሽት በሳል አይሆንም (ሉቃ. 2፡52)።

• ማስጠንቀቂያ፦ ሆኖም ግን በጌታ ቤት ረጅም አመታት አስቆጥሮ ሳይበስሉ መክረም ይኖራል። በእግዚአብሔር ቤት 50 እና 60 አመት ያስቆጠሩ መንፈሳዊ ሕጻናት ይኖራሉ። መንፈሳዊ ብስለት በእግዚአብሔር ቤት ጊዚያትን ከመቁጠር ያለፈ ነው።

• ዕብ. 5፥12 "ከጊዜው የተነሳ አስተማሪዎች ልትሆኑ ሲገባችሁ፥ አንድ ሰው ስለ እግዚአብሔር ቃላት መጀመሪያ ያለውን የሕፃንነትን ትምህርት እንዲያስተምራችሁ እንደ ገና ያስፈልጋችኋልና፤ 
የሚያስፈልጋችሁም ወተት ነው እንጂ ጠንካራ ምግብ አይደለም።"

2. መንፈሳዊ ብስለት ውጫዊ ጉዳይ አይደለም።

አንዳንድ ሰዎች በውጫዊ ይዘታቸው (ንግግራቸው) በሳል መንፈሳዊያን ሊመስሉ ይችላሉ። መንፈሳዊ ብስለት የኑሮ ጉዳይ እንጂ የንግግር ጉዳይ አይደለም። የመለወጥ እንጂ የመምሰል ጉዳይ አይደለም::

• ሉቃ. 11፡39-42 "ጌታም እንዲህ አለው፦ አሁን እናንተ ፈሪሳውያን የጽዋውንና የወጭቱን ውጭ ታጠራላችሁ፥ ውስጣችሁ ግን ቅሚያና ክፋት ሞልቶበታል እናንት ደንቆሮዎች፥ 
የውጭውን የፈጠረ የውስጡን ደግሞ አልፈጠረምን? ነገር ግን በውስጥ ያለውን ምጽዋት አድርጋችሁ ስጡ፥ እነሆም፥ ሁሉ ንጹሕ ይሆንላችኋል።…"

3. መንፈሳዊ ብስለት የክንውን ጉዳይ አይደለም።

• የአገልግሎት ቦታና የሃላፊነት ብዛትም የብስለት መለኪያዎች አይደሉም።

• ብስለት እውቀት የማከማቸት ጉዳይም አይደለም።

• ሉቃ. 11፡52 "እናንተ ሕግ አዋቂዎች፥ የእውቀትን መክፈቻ ስለ ወሰዳችሁ፥ ወዮላችሁ ራሳችሁ አልገባችሁም የሚገቡትንም ከለከላችሁ።"

4. በመንፈሳዊ ስጦታዎች መሞላት፣ በመንፈሳዊ ስጦታዎች ማገልገል/መጠቀም ማለት አይደለም።

• መንፈስ ቅዱስን መግለጥ፣ ጥበብን መናገር፥ እውቀትን መናገር፣ የመፈወስ ስጦታ፥ ተአምራትን ማድረግ፣ ትንቢትን መናገር፥ መናፍስትን መለየት፥ በልዩ ዓይነት ልሳን መናገር፥ በልሳኖች 
የተነገረውን መተርጎም…….የመንፈሳዊ ብስለት መለኪያዎች አይደሉም።

ንጽጽር

• 1ቆሮ. 1፡7 "እንደዚህ የጌታችንን የኢየሱስ ክርስቶስን መገለጥ ስትጠባበቁ አንድ የጸጋ ስጦታ እንኳ አይጎድልባችሁም፤"

• 1ቆሮ. 3፡1-3 "እኔም፥ ወንድሞች ሆይ፥ የሥጋ እንደ መሆናችሁ፥ በክርስቶስም ሕፃናት እንደ መሆናችሁ እንጂ መንፈሳውያን እንደ መሆናችሁ ልናገራችሁ አልቻልሁም። ገና ጽኑ መብል ለመብላት አትችሉም ነበርና ወተት 
ጋትኋችሁ፤ ገና ሥጋውያን ናችሁና እስከ አሁን ድረስ ገና አትችሉም። ቅናትና ክርክር ስለሚገኝባችሁ ሥጋውያን መሆናችሁ አይደላችሁምን?"


ይቀጥላል...


ምንጭ:- tsegaewnet.files.wordpress.com



ወደ ቻናሉ ለመ🀄️ላ🀄️ል፦ @Holy_scriptures
❤5
Audio
👉ርዕስ፦ የካታኮምቡ ሰማዕት
🗣ትርጉም፦ በአማረ ማሞ
መካነ ኢየሱስ ሥነ ጽሑፍ ክፍል።
📻ሙሉ ትረካ
⏱️አጠቃላይ የሚፈጀው ሰዓት፦ 3:49:45


ወደ ቻናሉ ለመ🀄️ላ🀄️ል👉 @TME_bible_study
👍5❤1
.       ──•◈•─────•◈•─
                 የዕለቱ ጥቅስ 
        ──•◈•─────•◈•─
“እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ በመንገድ ላይ ቁሙ ተመልከቱም፥ የቀደመችውንም መንገድ ጠይቁ፤ መልካሚቱ መንገድ ወዴት እንደ ሆነች እወቁ፥ በእርስዋም ላይ ሂዱ፥ ለነፍሳችሁም ዕረፍት ታገኛላችሁ፤ እነርሱ ግን፦ አንሄድባትም አሉ።”
ኤርምያስ 6፥16



ወደ ቻናሉ ለመ🀄️ላ🀄️ል፦ @Holy_scriptures
❤10🙏2
በቅዱሳት መጻሕፍት ውስጥ በትንቢተ ኢሳይያስ "አማኑኤል" ስለሚባለው ልጅ ምልክት እንዲጠይቅ የተነገረ የይሁዳ ንጉሥ ማን ነው?
Anonymous Quiz
9%
ምናሴ
39%
ሕዝቅያስ
28%
አካዝ
23%
ኢዮሳፍጥ
❤4