#አዲስ_ዓመት
የመፅሃፍ ቅዱስ ባለ ሥልጣንነት እና ማእከልነት
የእግዚአብሔር ቃል እውነታን ያሳየናል፤ እውነትን ያሳውቀናል፣ ማስተዋልን ያላብሰናል። መልካሙንና ክፉውን ይለይልናል፤ ስለ ፍጥረት፣ ስለ ፈጣሪ፣ ፈጣሪ ከፍጥረቱ ጋር ስላለው መስተጋብር፣ ስለ ስፍነ ተክል እና እንስሳ፣ ስለ ሰው አበጃጀት ወይም አፈጣጠር፣ ስለ ሰማይ ሠራዊት፣ ስለ መንፈሳዊ አካላት ይነግረናል፤ እግዚአብሔር ከሰው ጋር ስላለው አምላካዊ ኪዳን ይተርክልናል። ሰው ከእግዚአብሔር ጋርና ሰው ከሰው ጋር ሊኖረው ስለሚገባ አኗኗር መመሪያ መመርመርያ ይሰጠናል። ስለ ውድቀት ያስረዳናል፣ ስለ ድነት መንገድ ይገልጥልናል፤ ስለ ዘላለም ሕይወትና ስለ እግዚአብሔር መንግሥት እውነታ ያወሳልናል መግቢያ መንገዱንም ያሳየናል።
ቅዱስ ቃሉ የእምነትና የአስተምህሮ መርሕ፣ የሞራል ሕይወት መለኪያ ነው። መጽሐፍ ቅዱስ የሕይወት መሠረት፣ የመንፈሳዊ ሕይወት ምንነት፣ ዕውቀት መገብያ የትክክለኛና የጠራ አስተምህሮ ምንጭና ሚዛን፣ የፍትሐዊ አመራር ጥበብ መመንጫ፣ ለተሰጠ መሪነት ልብ መታነጫ እንዲሁም የሕያው እምነት መሠረትና መገንቢያ ነው።
እንግዲያስ ቃሉ
የነባራዊ እውነታ መሠረት፣
የእውነትና የሥርዐተ እምነታችን መገንቢያ
የሥርዐተ እሤታችን መዋቀሪያ
የልቡናችን መታደሻ፣ የአደራረጋችን፣ የአካሄዳችን፣ የአኗኗራችን መመሪያ ነው፤ በጥቅሉ የርዕዮተ ዓለማችን መታነጫ ነው።
ቃሉ እስትንፋሰ መለኮት ያደረበት በመሆኑ ለእግዚአብሔር ሕዝብ የተሰጡ ትእዛዛትን፣ መመሪያዎችንና መርሖዎችን የያዘ መጽሐፍ ነው። ስለሆነም ከወጋችን፣ ከልማዳችን ከዕሳቤዎቻችንና ከባህላችን ጋር ባይስማማም ፍጹም ሥልጣናዊነቱ አይሻርም።
መጽሐፍ ቅዱስ በቂ መገለጥ ነው፤ ይህም ማለት የእግዚአብሔር ቃል ሰዎች እግዚአብሔርን ለማወቅ፤ ለድነትና ለእርሱ ክብር ለመኖር የሚያስችል የተሟላ መልእክት ያለው ነው።
ባህል፣ የግል ልምምድ (ተሞክሮ) ስሜታዊ ማንነታችን፣ የወቅቱ ሁኔታ ሁሉ በጎም ክፉም ተጽእኖ ሊያሳድሩብን ቢችሉም እነዚህ ሁሉ ለቃሉ መገዛት ለሥልጣኑም ማደር ይኖርባቸዋል።
ነገሩ እንዲህ ሆኖ እያለ ግን ዛሬ በአብዛኛው ምእመናንና አገልጋዮች ዘንድ ያለው እምነት ከቃሉ ይልቅ በልምምድና በስሜታዊነት ላይ የተመሠረተ ሆኗል። በትምህርትም ሆነ በዕለታዊው ኑሮ ʻምን ታየህ?ʼ፣ ʻምን ተሰማህ?ʼ ማለት እጅግ ይበዛል፣ ይዘወተራል። ከእግዚአብሔር ቃል ዳኝነት ይልቅ ተሞክሮና ልምምድ የብዙኀንም ድምፅ ይገናል። ለአስተምህሮ ትክክለኛነት ከተጨባጭና ከነባራዊ መጽሐፍ ቅዱሳዊ ማስረጃዎች ይልቅ ልምምዳዊ የሆኑ ማስረጃዎች ስፍራ ይሰጣቸዋል። ቃሉን ማሰብ፣ ማጤን፣ ማስተዋልን መጥላት፣ ገሸሽ ማድረግ ይታያል። ጸረ ተምህሮት (an -intellect) እና ጥራዝ ነጠቅ (quasi-intellect) የሆነ አቋም በእጅጉ እየተንጸባረቀ እውነትን ለማስተዋል የማሰብ ተግባር ቀስ በቀስ እየተኮላሸ፣ እንዲጨፈለቅ እየተደረገ ነው።
ዛሬ በሚያስደነግጥና በሚያሳዝን ሁኔታ፣ ይህ የከበረው የአምላካችን ቃል የማይለውን ʻይላልʼ የሚለውን ʻአይልምʼ ብሎ ተርጒሞ ማስተማር እጅግ እየተበራከተ መጥቷል። አንዳንዶቻችን ግልጽ ከሆነው የመጽሐፍ ቅዱስ መልእክት ይልቅ፣ ከቀጥተኛው ትምህርት (መልእክት) በስተ ጀርባ ፈለፈልን ብለን የምናወጣውን ትርጉም እናከብራለን። ከዐውዱ ጋር ወይም በመንፈስ ቅዱስ አማካኝነት ተመርተው መጽሐፍ ቅዱስን ከጻፉት ሰዎች መልእክት ይዘት ጋር ባይጣጣምም አይገደንም። ይህ ያለንበት ጊዜ በሰዎች ምናባዊ ዓለም የተወለደ ትርጒም፣ ከእግዚአብሔር የመጣ መገለጥ እየተባለ የሚሰበክበት፣ አዳማጩም ʻአሜን አሜንʼ እያለ ያለ ምንም ፍተሻ፣ ያለ ምንም መጽሐፍ ቅዱሳዊ ሚዛን እንዲወስድ የሚደረግበት ጊዜ ሆኗል። ከዚህም የተነሣ ብዙዎቻችን የዘመኑ ሰባኪያንና አስተማሪዎች ራሳችንን ከመጽሐፍ ቅዱስና በመንፈስ ተመርተው ከጻፉት ነቢያትና ሐዋርያት በላይ በማድረጋችን ከእውነተኛው የመጽሐፍ ቅዱስ መልእክት ጋር ተጣልተናል፤ ለሐሰተኛ ትምህርት በሩን ወለል አድርገን አስከፍተናል።
ጊዜ ወስደን የእግዚአብሔርን ቃል ከማጥናት ይልቅ፣ ሁሉን ነገር መንፈስ ቅዱስ ይገልጥልኛል የሚለውን አባባል ለስንፍናችን መመከቻ እያደረግን ቃሉን ከፍተን ሳናነብ፣ ሳናጤን በመድረክ ላይ የምንቆም ብዙዎች አለን። አንዳንዶቻችን ደግሞ አንድን ጥቅስ ወይም አንድን ምንባብ ዐውዱን ባላገናዘበ ሁኔታ ዘንጥለን በማውጣት፣ የራሳችንን ፍላጎት ሐሳብና አእምሯችን የወለደውን ትርጒም መደገፊያ፣ እንደ መዋኛ ስፍራ መወናጨፊያ ማማ አድርገን እንጠቀምበታለን። ያነበብነውን ክፍል ገልጦ ማብራራት ይቅርና ዳግመኛ ወደ ክፍሉ ሳንመለስ እንዳሻን ጋልበን እንደ ወጣን እንቀራለን።
ለዚህ ዐይነት ፈሩን ለለቀቀና የመጽሐፍ ቅዱስን ትርጒም አዛብቶ ለመስበክና ለማስተማር የዳረገን አንደኛው ምክንያት ሰባኪዎችና አስተማሪዎች የሆንነው የመጽሐፍ ቅዱስን ምንነት በአግባቡ ረጋ ብለን ያለመረዳትና እንዴት አድርገን በትክክለኛው መንገድ መተርጐም እንዳለብን ያለማወቅ ወይም ያለመፈለግ ነው። እግዚአብሔር የማዳን ታሪኩን የሰዎችን ባህልና ቋንቋም ተጠቅሞ ስለ ገለጠው መጽሐፍ ቅዱሳችንን ስናጠና የቋንቋ፣ የታሪክ፣ የመልክዓ ምድራዊና ባህላዊ ዳራውን እንዲሁም ሥነ ጽሑፋዊ ዐውዱን፣ ሥነ ቃላቱንና ሰዋሰዉን ባስተዋለ ሁኔታ ልንተረጒመው ይገባል፤ የጽሑፉን ጾታና የአነጋገር ዘይቤውንም ልናጤን ያስፈልጋል። ዛሬ ብዙዎቻችንን የሥነ መለኮት ትምህርት ወይም የሥነ አፈታት ትምህርት ባንማርም፣ በቀላሉ የአስተውሎት ሕግ (common sense) ብቻ በቀጥተኛ ሁኔታ ሊተረጐሙ የሚችሉትን ክፍሎች እንኳ አዛብተን እንግዳ ትርጒም ስንሰጥ እንገኛለን።
በኤፌሶን 6 ላይ እንደ ተጻፈው የመንፈስ ሰይፍ የሆነው የእግዚአብሔር ቃል ነውና ሁለቱን ማለትም መንፈሱንና ቃሉን ማፋታት የማይገባና ለስሕተት የሚዳርግ ነው። እኛን የሞላ/የሚሞላ መንፈስ ቅዱስ፣ መጽሐፍ ቅዱስን የጻፈው/የደረሰው ያው መንፈስ ቅዱስ መሆኑን ዘወትር አበክረን ማስተዋል አለብን። ʻጌታ ተናገረኝ፣ መንፈስ ቅዱስ ነው የሚያን ቀሳቅሰኝʼ እያልን መጽሐፍ ቅዱስ ከሚሰጠን መመሪያ ውጭ ብንመላለስ ልምምዳችን በጥያቄ ውስጥ ይወድቃል እንጂ ቃሉ አይወድቅም። ልምምዳችን ከመንፈስ ቅዱስ ከሆነ ከእግዚአብሔር ቃል ጋር ይስማማል፤ አለበለዚያ ልምምዳችን ከራሳችን ስሜት ወይም ከክፉ አስመሳይ መንፈስ ወይም የሆነ ጥቅምን በመፈለግ ከሽንገላ ወይም ከአእምሮ ጤና ቀውስ ወይም ከዕውቀት ማነስ ሆኖ ይገኛል፤ ምክንያቱም መንፈስ ቅዱስ ራሱን አይቃረንምና።
የእውነት መንፈስ የሆነው፣ ወደ እውነት ሁሉ የሚመራው መንፈስ ቅዱስ የቃሉ ደራሲ ነው። ስለሆነም ቃሉ የሕይወት፣ የእምነት፣ የአስተምህሮና የአምልኮ ማእከል መሆኑ በሁሉ ሁኔታ መረጋገጥ አለበት።
ምንጭ:- semayawi thought
ወደ ቻናሉ ለመ🀄️ላ🀄️ል፦ @Holy_scriptures

❤5
. ──•◈•─────•◈•─
የዕለቱ ጥቅስ
──•◈•─────•◈•─
“ለእርሱ ለራሱ እንዲሆን ሕዝብን ይቤዥ ዘንድ ለእርሱ ለራሱም ስም ያደርግ ዘንድ፥ በአሕዛብና በአምላኮቻቸውም ፊት ከግብጽ በተቤዠው ሕዝብ ፊት ተአምራትንና ድንቅን ያደርግ ዘንድ እግዚአብሔር እንደ ሄደለት እንደ ሕዝብህ እንደ እስራኤል ያለ በምድር ላይ ምን ሕዝብ አለ?”
2ኛ ሳሙኤል 7፥23

❤10👍1
በቅዱሳት መጻሕፍት ውስጥ እምነት ያለ ሥራ የሞተ ነው ከሚለው አሳብ ጋር የተያያዘው የትኛው መልእክት ነው?
Anonymous Quiz
10%
ሮሜ
7%
ገላትያ
78%
ያዕቆብ
4%
ይሁዳ
❤4👍4
የመፅሐፍ_ቅዱስ_ማጥኛ_እቅድ_bible_reading.pdf
182.9 KB
#አዲስ_ዓመት
#ወደ_ቃሉ_እንመለስ
#BackToBible
መጽሐፍ ቅዱስን በአንድ ዓመት ውስጥ አጥንቶ ለመጨረስ የሚረዳ የጥናት እቅድ
👉 እያንዳንዱ ወር 25 የማጥኛ ቀናቶች አሉት:: ቀሪዎቹ 5 ቀናት ምናልባትም
የተዘለለ ቀን ካለ ወይም ለክለሳ የሚሆን ነው::
👉 እያንዳንዱ ቀን ከ ብሉይ ኪዳን እና ከ አዲስ ኪዳን ሁለቱንም ያጠቃለለ ሲሆን
የመፅሐፍ ቅዱስ ውህደቱንም በሚገባ እንድንረዳ ይረዳናል::
👉ይሄ pdf የተዘጋጀው ከ JUNE - M A Y /ሰኔ-ግንቦት) ግን ከማንኛውም ወር መጀመር ይቻላል::
በአክሊሉ ተፈራ

❤8🔥1👏1
. ──•◈•─────•◈•─
🌼 የዕለቱ ጥቅስ 🌼
──•◈•─────•◈•─
“ፊቴም ወደ እናንተ ይሆናል፥ እንድታፈሩም አደርጋችኋለሁ፥ አበዛችሁማለሁ፤ ቃል ኪዳኔንም ከእናንተ ጋር አጸናለሁ።”
ዘሌዋውያን 26፥9

❤16🔥3👍1
Forwarded from Tabor Bible Study (ሐዋሳ ታቦር መካነ ኢየሱስ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት)
አራቱ የሃይማኖት መግለጫዎች.pdf
514.2 KB
አራቱ የሃይማኖት መግለጫዎች በአማርኛ
👉የሐዋርያት
👉የኒቅያ
👉የአትናቴዎስ
👉ያልተለወጠው የኦግስቡርግ የሃይማኖት መግለጫ
በኢትዮጵያ ወንጌላዊት ቤተክርስቲያን መካነ ኢየሱስ ታቦር ማኅበረ ምእመናን የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት ዝግጅት አገልግሎት ቡድን የተዘጋጀ
ወደ ቻናሉ ለመ🀄️ላ🀄️ል👉 @TME_bible_study
👉የሐዋርያት
👉የኒቅያ
👉የአትናቴዎስ
👉ያልተለወጠው የኦግስቡርግ የሃይማኖት መግለጫ
በኢትዮጵያ ወንጌላዊት ቤተክርስቲያን መካነ ኢየሱስ ታቦር ማኅበረ ምእመናን የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት ዝግጅት አገልግሎት ቡድን የተዘጋጀ
ወደ ቻናሉ ለመ🀄️ላ🀄️ል👉 @TME_bible_study
❤5
. ──•◈•─────•◈•─
የዕለቱ ጥቅስ
──•◈•─────•◈•─
“እንዲህም አለኝ፦ እነሆ ፍሬያማ አደርግሃለሁ፥ አበዛሃለሁም፥ ለብዙም ሕዝብ ጉባኤ አደርግሃለሁ፤ ይህችንም ምድር ከአንተ በኋላ ለዘላለም ርስት ለዘርህ እሰጣታለሁ።”
ዘፍጥረት 48፥4
ወደ ቻናሉ ለመ🀄️ላ🀄️ል፦ @Holy_scriptures
የዕለቱ ጥቅስ
──•◈•─────•◈•─
“እንዲህም አለኝ፦ እነሆ ፍሬያማ አደርግሃለሁ፥ አበዛሃለሁም፥ ለብዙም ሕዝብ ጉባኤ አደርግሃለሁ፤ ይህችንም ምድር ከአንተ በኋላ ለዘላለም ርስት ለዘርህ እሰጣታለሁ።”
ዘፍጥረት 48፥4
ወደ ቻናሉ ለመ🀄️ላ🀄️ል፦ @Holy_scriptures
❤14
❤5👍1😁1
Audio
❤1
#የእግዚአብሔር_ቃል_ምን_ይላል?
ዘካርያስ 8
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
¹ የሠራዊትም ጌታ የእግዚአብሔር ቃል ወደ እኔ እንዲህ ሲል መጣ፦
² የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ስለ ጽዮን ታላቅ ቅንዓት ቀንቻለሁ፥ በታላቅም ቍጣ ስለ እርስዋ ቀንቻለሁ።
³ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ወደ ጽዮን ተመልሻለሁ፥ በኢየሩሳሌምም መካከል እኖራለሁ፤ ኢየሩሳሌምም የእውነት ከተማ ትባላለች፤ የሠራዊትም ጌታ የእግዚአብሔር ተራራ የተቀደሰ ተራራ ይባላል።
⁴ የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ዳግመኛ ሽማግሌዎችና ባልቴቶች በኢየሩሳሌም አደባባይ ይቀመጣሉ፤ ሰውም ሁሉ ከዕድሜው ብዛት የተነሣ ምርኩዝ በእጁ ይይዛል።
⁵ የከተማይቱም አደባባዮች በእነዚያ በሚጫወቱ ወንዶችና ሴቶች ልጆች ይሞላሉ።
⁶ የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ በዚህ ወራት በዚህ ሕዝብ ቅሬታ ዓይን ዘንድ ድንቅ ቢሆን፥ በውኑ በእኔ ዓይን ዘንድ ደግሞ ድንቅ ይሆናልን? ይላል የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር።
⁷ የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ እነሆ፥ ሕዝቤን ከምሥራቅ ምድርና ከምዕራብ ምድር አድነዋለሁ፤
⁸ አመጣቸዋለሁም፥ በኢየሩሳሌምም ውስጥ ይኖራሉ፤ እነርሱም ሕዝብ ይሆኑኛል፥ እኔም በእውነትና በጽድቅ አምላክ እሆናቸዋለሁ።
⁹ የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ መቅደሱ ይሠራ ዘንድ የሠራዊት ጌታ የእግዚአብሔር ቤት ከተመሠረተበት ቀን ጀምሮ ከነቢያት አፍ ይህን ቃል በዚህ ዘመን የሰማችሁ እናንተ ሆይ፥ እጃችሁን አበርቱ።
¹⁰ ከዚያ ወራት አስቀድሞ ለሰውና ለእንስሳ ዋጋ አልነበረምና፤ እኔም ሰውን ሁሉ በወንድሙ ላይ አስነሥቼ ነበርና ከአስጨናቂው የተነሣ ለሚገባውና ለሚወጣው ሰላም አልነበረም።
¹¹ አሁን ግን እንደ ቀደመው ዘመን በዚህ ሕዝብ ቅሬታ ላይ አልሆንም፥ ይላል የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር።
¹² ነገር ግን ሰላምን እዘራለሁ፤ ወይኑ ፍሬውን ይሰጣል፥ ምድርም አዝመራዋን ታወጣለች፥ ሰማያትም ጠላቸውን ይሰጣሉ፤ ለዚህም ሕዝብ ቅሬታ ይህን ነገር ሁሉ አወርሳለሁ።
¹³ የይሁዳ ቤትና የእስራኤል ቤት ሆይ፥ በአሕዛብ ዘንድ እርግማን እንደ ነበራችሁ፥ እንዲሁ አድናችኋለሁ፥ በረከትም ትሆናላችሁ አትፍሩ፥ እጃችሁንም አበርቱ።
¹⁴ የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላልና፦ አባቶቻችሁ እጅግ ባስቈጡኝ ጊዜ ክፉ ለማድረግ እንዳሰብሁ፥ እንዳልተጸጸትሁም፥ ይላል የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር፥
¹⁵ እንዲሁ ዳግመኛ ለኢየሩሳሌምና ለይሁዳ ቤት በዚህ ወራት በጎነትን አደርግ ዘንድ አስቤአለሁ አትፍሩ።
¹⁶ የምትሠሩት ነገር ይህ ነው፤ እያንዳንዳችሁ ከባልንጀራችሁ ጋር እውነትን ተነጋገሩ፤ በበር አደባባያችሁም የእውነትንና የሰላምን ፍርድ ፍረዱ፤
¹⁷ ሁላችሁም በባልንጀራችሁ ላይ ክፉን ነገር በልባችሁ አታስቡ፤ የሐሰትንም መሐላ አትውደዱ፤ ይህን ነገር ሁሉ እጠላለሁና፥ ይላል እግዚአብሔር።
¹⁸ የሠራዊት ጌታ የእግዚአብሔር ቃል ወደ እኔ እንዲህ ሲል መጣ፦
¹⁹ የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ የአራተኛው ወር ጾም የአምስተኛውም የሰባተኛውም የአሥረኛውም ወር ጾም ለይሁዳ ቤት ደስታና ተድላ የሐሤትም በዓላት ይሆናል፤ ስለዚህም እውነትንና ሰላምን ውደዱ።
²⁰ የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ በብዙ ከተሞች የሚቀመጡ አሕዛብ ገና ይመጣሉ፤
²¹ በአንዲትም ከተማ የሚኖሩ ሰዎች፦ እግዚአብሔርን እንለምን ዘንድ፥ የሠራዊትንም ጌታ እግዚአብሔርን እንፈልግ ዘንድ ኑ እንሂድ፤ እኔም እሄዳለሁ እያሉ ወደ ሌላ ከተማ ይሄዳሉ።
²² ብዙ ወገኖችና ኃይለኞች አሕዛብ በኢየሩሳሌም የሠራዊትን ጌታ እግዚአብሔርን ይፈልጉ ዘንድ፥ እግዚአብሔርንም ይለምኑ ዘንድ ይመጣሉ።
²³ የሠራዊትም ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ በዚያ ዘመን ከአሕዛብ ቋንቋ ሁሉ አሥር ሰዎች የአንዱን አይሁዳዊ ሰው ልብስ ዘርፍ ይዘው፦ እግዚአብሔር ከእናንተ ጋር እንዳለ ሰምተናልና ከእናንተ ጋር እንሂድ ይላሉ።

👍6❤3🔥1
. ──•◈•─────•◈•─
የዕለቱ ጥቅስ
──•◈•─────•◈•─
“ነቅቶም ነፋሱን ገሠጸው ባሕሩንም፦ ዝም በል፥ ፀጥ በል አለው። ነፋሱም ተወ ታላቅ ፀጥታም ሆነ።”
ማርቆስ 4፥39

❤24
#እራሳችንን_እንመርምር
አዲስ ዓመትስ አይደል? እግዚአብሔር ሰፍሮና መዝኖ በሰጠን ዕድሜና ዘመን ምን ያህል ውጤታማ ነን?
“አቤቱ፥ ፍጻሜዬን አስታውቀኝ፥ የዘመኔ ቍጥሮች ምን ያህል እንደ ሆኑ፥ እኔ ምን ያህል ወደ ኋላ እንደምቀር አውቅ ዘንድ።”
መዝሙር 39፥4
“እግዚአብሔር ሆይ፤ የሕይወቴን ፍጻሜ፣ የዘመኔንም ቍጥር አስታውቀኝ፤ አላፊ ጠፊ መሆኑንም ልረዳ።”
መዝሙር 39፥4 (አዲሱ መ.ት)

❤15👏1
. ──•◈•─────•◈•─
የዕለቱ ጥቅስ
──•◈•─────•◈•─
“የእግዚአብሔርን ፈቃድ አድርጋችሁ የተሰጣችሁን የተስፋ ቃል እንድታገኙ መጽናት ያስፈልጋችኋልና።”
ዕብራውያን 10፥36

❤18🔥3🤝1
በቅዱሳት መጻሕፍት ውስጥ የክርስቶስን የበላይነት የሚያጎላውና የኖስትሲዝምን ትምህርት በመቃወም የተጻፈው የትኛው መልእክት ወይም መጽሐፍ ነው?
Anonymous Quiz
11%
ኤፌሶን
16%
ሮሜ
63%
ቆላስይስ
11%
ፊልጵስዩስ
❤🔥4❤3🔥3
እየጨመረ የሚሄድ ሕይወት
የጠለቀ መንፈሳዊ ጉዞ ለመጓዝና እየጨመረ የሚሄድ ርካታና እረፍት እንድናይ ካስፈለገ፣የክርስትና ሕይወት ትጋትን ይጠይቀናል(ዕብ 4፥11)፡፡ በተለያየ ቦታ በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ቃሉ እንደሚያስተምረን ትጋታችን እየጨመረ ሲሄድ፣የእግዚአብሔር ጸጋም በሕይወታችን እየጨመረ ይሄዳል፡፡ በእንደዚህ ዓይነት ግሥገሣ ውስጥ ባለማሰለስ ስንገኝ፣እሱን ለማወቅ ያለን ራብ እየተቀጣጠለ ስለሚመጣ፣እየጨመረ ለሚሄድ ፍለጋ እንጠናከራለን፡፡ ይህንን በእንግሊዝኛው አገላለጽ positive vicious cycle ይሉታል፡፡ ማለትም ትጋቱ የጨመረ መንፈሳዊ ራብን ይወልዳል፤የጨመረው መንፈሳዊ ራብ ደግሞ ሌላ ከፍ ያለ ትጋትንና ግሥገሣን ይወልዳል፡፡ መቼም ይሄ ኡደት ማቆሚያ የለውም እኛ በሥጋዊ አካሄዶች እስካላጠፋነው ድረስ!
በነገራችን ላይ እየጨመረ የሚሄድ የክርስትና ሕይወት ብዙ ግብዓቶችን ይፈልጋል ፡፡ መልካም የእምነት ውጊያንና ዲያቢሎስን በኃይል ጸንቶ መቃወም ይጠይቃል ፡፡ የእግዚአብሔርን ቃል ሳይታክቱ ማሰላሰልና በፊቱ ጥሩ የሆኑ ጊዜዎችን ማሳለፍ ግድ ይለናል ፡፡ ሁኔታዎችንና ሥጋችንን ሳናዳምጥ የሚከፈሉ ዋጋዎችን እንደ ጌታ ፈቃድ መክፈልን ይጠይቀናል፡፡ የእግዚአብሔር ቃል ትእዛዝ አለው፤ደግሞም በረከት አለው፡፡ ትእዛዙን በእግዚአብሔር ጸጋ ተደግፈን ሳንፈጽምና ሳናከናውን፣በረከት መጠበቅ ሞኝነት ነው ፡፡ ስለዚህ ጌታ በምናደርጋቸው ነገሮች ሁሉ እንዲባርከን፣ መታዘዝ ልንወስደው የሚገባን እርምጃ ነው፡፡
ከዚህ ጋር በተያያዘ አንድ መርሕ እዚህ ጋ ልጥቀስ፡፡ሦስት በተሰናሰለ መንገድ የተቀመጡ ድርጊቶች በውጤት ሂደት እንዲህ ተቀምጠዋል፡-
ድርጊት(Action)——->ልማድ(Habit)——->ጠባይ(character)
ይህንን መርሕ ለመግለጽ ጸሎትን እንደ ምሳሌ ልውሰድ ፡፡ ጸሎትን ደጋግመን ስናደርገው ወደ ልማድነት ይቀየራል ፡፡ በሕይወታችን ልማድ እየሆነ የመጣውን ተግባር እየጨመርን ደጋግመን ስናደርገው፣ጠባያችን ወይም መገለጫ ባሕርያችን ይሆናል ፡፡ ከዚያማ ውጤቱ እንዲህ ይሆናል፡-
“መጸለይ እንጂ አለመጸለይ አንችልም፡፡”
“በፊቱ መሆን እንጂ አለመሆን ያቅተናል፡፡”
እጅግ ሊጓጓለት የሚገባ ድንቅ ለውጥ!
የላይኛውን ሐሳብ የሚደግፉና የክርስትና ሕይወት እየተቀጣጠለ፣እያደገና እየጨመረ የሚሄድ ሕይወት እንደ ሆነ የሚጠቁሙ ብዙ ክፍሎች አሉ ፡፡ ለምሳሌ ሦስቱን ልጥቀስ፡-
“እስከ እግዚአብሔር ፍጹም ሙላት ደርሳችሁ ትሞሉ ዘንድ” (ኤፌሶን 3፥19)
“በመንፈስ የምትቃጠሉ ሁኑ” (ሮሜ 12፥11)
“መንፈስ ይሙላባችሁ እንጂ በወይን ጠጅ አትስከሩ ይህ ማባከን ነውና” /ብዙ የሚያሰክሩ ነገሮች እንዳሉ ልብ ይሏል/(ኤፌሶን 5፥16-20)
የእግዚአብሔር ሰው ስሚዝ ዊግልስዎርዝ እንዲህ ብሎ ነበር፡-“If you are in the same place today as you were yesterday, you are a backslider.”(ትርጉሙ፡-በዛሬው ቀን ትላንትና የነበርክበት ቦታ ላይ ከተገኘህ የኋሊት እየሄድክ ነው)
በተሰጠ ማንነት፣ልባችን መሉ በሙሉ በጌታ ላይ ሆኖ ከላይ በተጠቀሰው ዓይነት ፍለጋ(craving) እና ትጋት ስንቀጥል፣የጌታ አብሮሆት ከመቸው በሚበልጥ ሁኔታ በሕይወታችን ዕውን ይሆናል ፡፡ ከዚህም የተነሣ የምናገኘው የመጀመሪያው በረከት በቃላት ልንገልጸው የማንችለው ሰላም፣መረጋጋትና ደስታ ይሆናል ፡፡ መንፈሳዊ መረዳታችንም እየጨመረ ስለሚሄድ፣ጌታን በሚገባ እያወቅነው እንመጣለን፡፡ስለዚህ ለውጣችን ወደ ኋላ የማይቀለበስና ዘላቂ ይሆናል ፡፡ መንፈሳዊ ዓይኖቻችን በጨመረ ሁኔታ እየተከፈቱ ስለሚመጡ፣ብዙ ረብ የሌላቸውን ነገሮች የመጣል መነሣሣትና አቅም እያገኘን እንመጣለን ፡፡
እንደዚህ በጽናት ሳናሰልስ የጌታን ፊት በጨመረ ሁኔታ በፈለግን ቁጥር፣የእግዚአብሔር ኃይል በውስጣችን እየጨመረ ስለሚሄድ፣ብዙ ቀንበሮች ከሕይወታችን ይሰበራሉ ፡፡ ስለዚህም“ሸክሙ ከጫንቃህ ቀንበሩም ከትከሻህ ላይ ይሰበራል” የሚለው ቃል በሕይወታችን ይፈጸማል (ኢሳ.10፡27)፡፡ እናም ከበፊቱ ይልቅ በሕልውናው ውስጥ መቆየት አያስቸግረንም ፡፡ ብዙ ሰዓት በፊቱ መሆንም ያለ ጥርጥር ፈቃዳችን ይሆናል ፡፡ እሱን በአካል ባናየውም እንኳ፣በመንፈስ እያየነው በጨመረ ሁኔታ እንወደዋለን፡፡ ቃሉ እንዲህ ይላልና፡-
“እርሱንም ሳታዩት ትወዱታላችሁ፤ አሁንም ምንም ባታዩት በእርሱ አምናችሁ የእምነታችሁን ፍጻሜ እርሱም የነፍሳችሁን መዳን እየተቀበላችሁ በማይነገርና ክብር በሞላበት ሐሤት ደስ ይላችኋል” (1 ጴጥሮስ 1፥8-9)
አዎ፣በጨመረ ሁኔታ በመንፈስ እያየነው ሰንቀጥል፣ልባችንም በፍቅሩ እሳት በጨመረ ሁኔታ ስለሚጋይ፣ጉገታችንና ቅድሚያ የምንሰጠው ነገር ሁልጊዜም በፊቱ መገኘት ይሆናል ፡፡ ቢሆንም ይሄ ውጤት በቀላል እንደሚመጣ ማሰብ የለብንም ፡፡ በጌታ ጸጋ ብዙ ትጋት፣ብዙ ፍለጋ፣ብዙ ቁፈራ፣በጌታ ፊት አዘውትሮ መሆንን ይጠይቀናል ፡፡
ለዚህ ሐሳቤ ጥሩ እይታ የሚሰጠን ኢዮብ 28፥1-11 ነው ፡፡ ይህ የምንባብ ክፍል የማዕድን ሠራተኛ ከባዶ ተነሥቶ የሚያደርገውን ግሥገሣ ነው የሚያሳየው ፡፡ “ዓይኑ ዕንቁን እስክታይ ድረስ” ፣ “የተሸፈነው ነገር ወደ ብርሃን እስኪወጣ ድረስ” ይተጋል ፡፡ እጁን ወደ ቡላድ ድንጋይ ይዘረጋል ፡፡ መጨረሻ ላይ ከብዙ እልህ አስጨራሽ ትግልና ጉዞ በኋላ የከበሩ ማዕድናትን ያገኛል፤ክፍሉ የልፋቱን ውጤት እንዲህ ይገልጸዋልና ፡-
“ሰው ወደ ቡላድ ድንጋይ እጁን ይዘረጋል፤ተራራውንም ከመሠረቱይገለብጣል። ከድንጋይ ውስጥ መንዶልዶያ ይወቅራል፤ ዓይኑምዕንቍን ሁሉ ታያለች። ፈሳሹም እንዳይንጠባጠብ ይገድባል፤የተሰወረውንም ነገር ወደ ብርሃን ያወጣል።”(ቁ.9-11)
አዎ ይህ ክፍል ምሳሌያዊ በሆነ አገላለጽ፣እንደ ማዕድን ሠራተኛው ያለ መታከት እንድንተጋና የጌታን ፊት እንድንፈልግ ያስተምረናል ፡፡ በቃሉ ውስጥ፣በጸሎት ኅብረት ውስጥ፣በትምህርት ውስጥ፣በጥሞና ጊዜና በተለያዩ ፕሮግራሞች ውስጥ፣ሳናሰልስ እንድንፈልገው ይጠቁመናል፡፡
የእግዚአብሔር ቃል ተግተው “የሚሹኝ ምስጉኖች/የተባረኩ ናቸው”(ምሳሌ 8፡34) ይላልና፤ “እናንተም ትጠሩኛለችሁ፤ሄዳችሁም ወደ እኔትጸልያላችሁ፣እኔም እሰማችኋለሁ። እናንተ ትሹኛላችሁ፣በፍጹምልባችሁም ከሻችሁኝ ታገኙኛላችሁ። ከእናንተም ዘንድ እገኛለሁ፡፡”(ኤር.29፥13-14) ይላልና ጨክኖ የጌታን ፊት የሚፈልግ ሰው ይዋል ይደር እንጂ፣የእግዚአብሔር በረከት ታገኘዋለች፡፡
አዎ፣ጌታ አጥብቀው ለሚሹት ሰዎች በእርግጥ ይገለጣል ፡፡ ጉብኝቱ ደግሞ ልባችን ላይ የሚያመጣው ለውጥ ቀላል አይሆንም ፡፡ የበለጠ እንድናየው፣የበለጠ በእርሱ ላይ እንድንደገፍና እንድንጠጋው ያደርገናል ፡፡ በተጨማሪም ጌታ ተገልጦ ሕይወታችንን ሲጎበኝ የሚመጣው ለውጥ ለሌሎች በረከት ያደርገናልና በትጋትና በጨመረ ሁኔታ ተግተን እንፈልገው!
“አሁን እንዳገኘሁ ወይም አሁን ፍጹም እንደ ሆንሁ አይደለም፣ነገር ግን ስለ እርሱ በክርስቶስ ኢየሱስ የተያዝሁበትን ያን ደግሞ እይዛለሁ ብዬ እፈጥናለሁ ። ወንድሞች ሆይ፣እኔ ገና እንዳልያዝሁት እቈጥራለሁ፤ ነገር ግን አንድ ነገር አደርጋለሁ፤ በኋላዬ ያለውን እየረሳሁ በፊቴ ያለውን ለመያዝ እዘረጋለሁ” ፊልጵስዩስ 3፡7-13)
ምንጭ:-ባለጸጋ ክርስትያን መጽሔት

👍7❤5👎2
. ──•◈•─────•◈•─
የዕለቱ ጥቅስ
──•◈•─────•◈•─
“አንተ እጅህን ትከፍታለህ፥ ሕይወት ላለውም ሁሉ መልካምን ታጠግባለህ።”
መዝሙር 145፥16
ወደ ቻናሉ ለመ🀄️ላ🀄️ል፦ @Holy_scriptures
የዕለቱ ጥቅስ
──•◈•─────•◈•─
“አንተ እጅህን ትከፍታለህ፥ ሕይወት ላለውም ሁሉ መልካምን ታጠግባለህ።”
መዝሙር 145፥16
ወደ ቻናሉ ለመ🀄️ላ🀄️ል፦ @Holy_scriptures
👍9🥰6❤4
በቅዱሳት መጻሕፍት ካሉ ወንጌላት ውስጥ ስለመንግሥተ ሰማያት ትኩረት የሚያደርገው መጽሐፍ የቱ ነው?
Anonymous Quiz
55%
ማቴዎስ
10%
ማርቆስ
8%
ሉቃስ
27%
ዮሐንስ
👍4❤1🔥1
በክርስትና ብስለት ማደግ
"እውነትን በፍቅር እየያዝን በነገር ሁሉ
ወደ እርሱ ራስ ወደሚሆን ወደ ክርስቶስ እንደግ፤"
ኤፌ. 4፡15
መንፈሳዊ ብስለት ይጠበቅብናል ወይ?
•ኤፌ. 4:11-13 "እርሱም አንዳንዶቹ ሐዋርያት፣ ሌሎቹም ነቢያት፣ ሌሎቹም ወንጌልን ሰባኪዎች፣ ሌሎቹም እረኞችና አስተማሪዎች እንዲሆኑ ሰጠ፤ ሁላችን የእግዚአብሔርን ልጅ በማመንና በማወቅ ወደሚገኝ አንድነት፣ ሙሉ ሰውም ወደ መሆን/to a mature
man፣ የክርስቶስም ሙላቱ ወደሚሆን ወደ ሙላቱ ልክ እስክንደርስ ድረስ፣ ቅዱሳን አገልግሎትን ለመሥራትና ለክርስቶስ አካል ሕንጻ ፍጹማን ይሆኑ ዘንድ፡፡"
•ቆላ. 1፡28-29 "እኛም በክርስቶስ ፍጹም የሚሆን ሰውን ሁሉ እናቀርብ ዘንድ ሰውን ሁሉ እየገሠጽን ሰውንም ሁሉ በጥበብ ሁሉ እያስተማርን የምንሰብከው እርሱ ነው፡፡ ለዚህም ነገር ደግሞ፣ በእኔ በኃይል እንደሚሠራ እንደ አሠራሩ እየተጋደልሁ፣ እደክማለሁ፡፡"
•ቆላ. 1፡9 "ስለዚሁ እኛ ደግሞ ይህን ከሰማንበት ቀን ጀምረን የፈቃዱ እውቀት መንፈሳዊ ጥበብንና አእምሮን ሁሉ እንዲሞላባችሁ እየለመንን፥ ስለ እናንተ ጸሎትን አልተውንም።"
•ፊሊ. 1:9-11 "ለእግዚአብሔርም ክብርና ምስጋና ከኢየሱስ ክርስቶስ የሚገኝ የጽድቅ ፍሬ ሞልቶባችሁ፥ ለክርስቶስ ቀን ተዘጋጅታችሁ ቅኖችና አለ ነውር እንድትሆኑ የሚሻለውን ነገር
ፈትናችሁ ትወዱ ዘንድ፥ ፍቅራችሁ በእውቀትና በማስተዋል ሁሉ ከፊት ይልቅ እያደገ እንዲበዛ ይህን እጸልያለሁ። "
•2 ተሰ. 1:3 - "ወንድሞች ሆይ፥ እምነታችሁ እጅግ ስለሚያድግ የሁላችሁም የእያንዳንዳችሁ ፍቅር እርስ በርሳችሁ ስለሚበዛ፥ ሁልጊዜ ስለ እናንተ እግዚአብሔርን እንደሚገባ ልናመሰግን ግድ አለብን፤ "
•2 ጴጥ. 3:18 - "ነገር ግን በጌታችንና በመድኃኒታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ጸጋና እውቀት እደጉ።"
• ኤፌ. 4:14፣15 - "እንደ ስሕተት ሽንገላ ባለ ተንኮል በሰዎችም ማታለል ምክንያት በትምህርት ነፋስ ሁሉ እየተፍገመገምን ወዲያና ወዲህም እየተንሳፈፍን ሕፃናት መሆን ወደ ፊት አይገባንም፥ ነገር ግን እውነትን በፍቅር እየያዝን በነገር ሁሉ ወደ እርሱ ራስ ወደሚሆን ወደ ክርስቶስ እንደግ፤"
•1ቆሮ. 14፡20 "ወንድሞች ሆይ፥ በአእምሮ ሕፃናት አትሁኑ፤ ለክፋት ነገር ሕፃናት ሁኑ እንጂ በአእምሮ የበሰሉ ሁኑ።"
• ዕብ. 6፡1-2 "ስለዚህ የክርስቶስን ነገር መጀመሪያ የሚናገረውን ቃል ትተን ወደ ፍጻሜ እንሂድ፤…(አ.መ.ት) ስለዚህ ስለ ክርስቶስ የተሰጠውን የመጀመሪያ ትምህርት ትተን ወደ ብስለት እንሂድ"
• ቆላ. 2፡6-7 "እንግዲህ ጌታን ክርስቶስ ኢየሱስን እንደ ተቀበላችሁት በእርሱ ተመላለሱ። ሥር ሰዳችሁ በእርሱ ታነጹ፥ እንደ ተማራችሁም በሃይማኖት ጽኑ፥ ምስጋናም ይብዛላችሁ።"
• 2ጴጥ. 3፡17-18 "…በዓመፀኞቹ ስሕተት ተስባችሁ ከራሳችሁ ጽናት እንዳትወድቁ ተጠንቀቁ፤ ነገር ግን በጌታችንና በመድኃኒታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ጸጋና እውቀት እደጉ።"
• 1ቆሮ. 13፡11 "ልጅ ሳለሁ እንደ ልጅ እናገር ነበር፥ እንደ ልጅም አስብ ነበር፥ እንደ ልጅም እቈጥር ነበር፤ ጎልማሳ ሆኜ ግን የልጅነትን ጠባይ ሽሬአለሁ።"
• ዕብ. 5፡13-14 "ወተት የሚጋት ሁሉ ሕፃን ስለ ሆነ የጽድቅን ቃል አያውቅምና፤ ጠንካራ ምግብ ግን መልካሙንና ክፉውን ለመለየት በስራቸው የለመደ ልቡና ላላቸው ለፍጹማን ሰዎች ነው። …(አ.መ.ት) መልካሙን ከክፉው ለመለየት ራሳቸውን ላስለመዱ፥ ለበሰሉ ሰዎች ነው"
ይቀጥላል...
ምንጭ:- tsegaewnet.files.wordpress.com

❤9🔥1🥰1
ደቀ መዝሙርነት.pdf
1.4 MB
❤5👎1