. ──•◈•─────•◈•─
የዕለቱ ጥቅስ
──•◈•─────•◈•─
“በጠሩህ ጊዜ ሁሉ ትሰማቸው ዘንድ ለባሪያህና ለሕዝብህ ለእስራኤል ልመና ዓይኖችህ የተገለጡ ይሁኑ።”
1ኛ ነገሥት 8፥52
ወደ ቻናሉ ለመ🀄️ላ🀄️ል፦ @Holy_scriptures

❤12
በቅዱሳት መጻሕፍት ውስጥ የትኛው ተራራ ከበረከት፣ የትኛውስ ተራራ ከእርግማን ጋር የተያያዘ ነው?
Anonymous Quiz
22%
ሲና-----ቀርሜሎስ
16%
ታቦር-----ጊልቦዓ
22%
ሲና------ጌባል
41%
ገሪዛን-----ጌባል
❤4🥰1
#የእግዚአብሔር_ቃል_ምን_ይላል
ዘዳግም 11
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
²⁶ እነሆ፥ እኔ ዛሬ በፊታችሁ በረከትንና መርገምን አኖራለሁ፤
²⁷ በረከትም፥ እኔ ዛሬ ለእናንተ የማዝዘውን የአምላካችሁን የእግዚአብሔርን ትእዛዝ ብትሰሙ፤
²⁸ መርገምም፥ የአምላካችሁን የእግዚአብሔርን ትእዛዝ ባትሰሙ፥ ዛሬም ካዘዝኋችሁ መንገድ ፈቀቅ ብትሉ፥ ሌሎችንም የማታውቋቸውን አማልክት ብትከተሉ ነው።
²⁹ አምላክህም እግዚአብሔር ትወርሳት ዘንድ አንተን ወደምትሄድባት ምድር ባገባህ ጊዜ፥ በረከቱን በገሪዛን ተራራ መርገሙንም በጌባል ተራራ ታኖራለህ።
³⁰ እነርሱም በዮርዳኖስ ማዶ፥ ከፀሐይ መግቢያ ካለችው መንገድ በኋላ፥ በዓረባ በተቀመጡት በከነዓናውያን ምድር፥ በጌልገላ ፊት ለፊት በሞሬ የአድባር ዛፍ አጠገብ ናቸው።
³¹ አምላካችሁ እግዚአብሔር የሚሰጣችሁን ምድር ትወርሱ ዘንድ ዮርዳኖስን ትሻገራላችሁ፥ ትወርሱአታላችሁም፥ ትቀመጡባታላችሁም።
³² እኔም ዛሬ በፊታችሁ የማኖራትን ሥርዓትና ፍርድ ሁሉ ታደርጉ ዘንድ ጠብቁ።
ወደ ቻናሉ ለመ🀄️ላ🀄️ል፦ @Holy_scriptures
ዘዳግም 11
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
²⁶ እነሆ፥ እኔ ዛሬ በፊታችሁ በረከትንና መርገምን አኖራለሁ፤
²⁷ በረከትም፥ እኔ ዛሬ ለእናንተ የማዝዘውን የአምላካችሁን የእግዚአብሔርን ትእዛዝ ብትሰሙ፤
²⁸ መርገምም፥ የአምላካችሁን የእግዚአብሔርን ትእዛዝ ባትሰሙ፥ ዛሬም ካዘዝኋችሁ መንገድ ፈቀቅ ብትሉ፥ ሌሎችንም የማታውቋቸውን አማልክት ብትከተሉ ነው።
²⁹ አምላክህም እግዚአብሔር ትወርሳት ዘንድ አንተን ወደምትሄድባት ምድር ባገባህ ጊዜ፥ በረከቱን በገሪዛን ተራራ መርገሙንም በጌባል ተራራ ታኖራለህ።
³⁰ እነርሱም በዮርዳኖስ ማዶ፥ ከፀሐይ መግቢያ ካለችው መንገድ በኋላ፥ በዓረባ በተቀመጡት በከነዓናውያን ምድር፥ በጌልገላ ፊት ለፊት በሞሬ የአድባር ዛፍ አጠገብ ናቸው።
³¹ አምላካችሁ እግዚአብሔር የሚሰጣችሁን ምድር ትወርሱ ዘንድ ዮርዳኖስን ትሻገራላችሁ፥ ትወርሱአታላችሁም፥ ትቀመጡባታላችሁም።
³² እኔም ዛሬ በፊታችሁ የማኖራትን ሥርዓትና ፍርድ ሁሉ ታደርጉ ዘንድ ጠብቁ።
ወደ ቻናሉ ለመ🀄️ላ🀄️ል፦ @Holy_scriptures
. ──•◈•─────•◈•─
የዕለቱ ጥቅስ
──•◈•─────•◈•─
“ዳዊትም እግዚአብሔርን፦ ይህን በማድረግ እጅግ በድያለሁ፤ አሁን ግን ታላቅ ስንፍና አድርጌአለሁና የባሪያህን ኃጢአት ታስወግድ ዘንድ እለምንሃለሁ አለው።”
1 ዜና 21፥8

❤10🙏1
በቅዱሳት መጻሕፍት ውስጥ ንጉሥ አንኩስ ለዳዊት ለመኖሪያነት የሰጠው የፍልስጥኤማውያን ከተማ የትኛው ነበር?
Anonymous Quiz
23%
ጋዛ
18%
ጌት
49%
ጺቅላግ
10%
አዛጦን
❤3
ቅዱሳት መጻሕፍት
#አዲስ_ዓመት #New_Year መጽሐፍ ቅዱስን እንዴት እናንብብ? ጠቃሚ መርሆች ክፍል-4 #ትረካዎች – መጽሐፍ ቅዱስ በብዙ ታሪኮች የተሞላ መጽሐፍ ነው፡፡ አንድ ታሪክ በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ስለተጻፈ ብቻ እንደ እግዚአብሔር ሐሳብ የተፈጸመ ትክክለኛ ድርጊት ነው ማለት አይደለም፡፡ ነገር ግን የተጻፈው እያንዳንዱ ታሪክ ለትምህርታችን ተጽፏል፡፡ የብሉይ ኪዳን ታሪኮች እግዚአብሔር…
#አዲስ_ዓመት
#New_Year
መጽሐፍ ቅዱስን እንዴት እናንብብ? ጠቃሚ መርሆች
ክፍል-5
(የመጨረሻ ክፍል)
#ትንቢቶች- የትንቢት መጻሕፍት ስለወደፊቱ ሁኔታዎች የሚናገሩ ናቸው፡፡ ቅዱሳት መጻሕፍትን በምንተረጉበት ሰዓት ከፍተኛ የሆነ ጥንቃቄ ልናደርግባቸው ከሚገቡ ክፍሎች መካከል ትንቢቶች የመጀመርያዎቹ ናቸው፡፡ የሚከተሉት ጥያቄዎች የትንቢት መጽሐፍትን ለመረዳት ያግዛሉ፡-
👉የቋንቋ አጠቃቀሙ ምን ዓይነት ነው? (ትዕምርታዊ፣ ቅኔያዊ፣ ራዕያዊ፣ አቡቀለምሲሳዊ፥ ወዘተ.)
👉የምንባብ አውዱ ምንድነው?
👉የትንቢቱና የተናጋሪው ታሪካዊ ዳራ ምንድነው?
👉የተሰጠው ተስፋ አኳኋናዊ (conditional) ነው ወይንስ ኢ-አኳኋናዊ (unconditional)?
👉የተነገረው ትንቢት የተፈፀመ፣ እየተፈፀመ ያለ ወይንስ ወደፊት የሚፈፀም?
#ምሳሌዎች- ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ትምህርቶቹን ብዙ ጊዜ በምሳሌዎች ያስተምር ነበር፡፡ እነዚህ ምሳሌዎች ትምህርቶቹን ይበልጥ ያብራራሉ ወይንም ደግሞ ከሰዎች አዕምሮ እንዳይጠፉ ያደርጋሉ፡፡ እነዚህን ምሳሌዎች በምናነብበት ሰዓት ከእነርሱ በፊት ወይንም በኋላ የተነገሩትን ነገሮች ልብ ብሎ ማንበብ አስፈላጊ ነው፡፡ የምሳሌ እያንዳንዱ ነጥብ ትርጉም ባለው መልኩ ከፍቺው ጋር ላይገናኝ ስለሚችል ጥንቃቄ ማድረግም ያስፈልጋል፡፡ ለምሳሌ ያህል ስለ ወይን እርሻ ገበሬዎች በተሰጠው ምሳሌ ውስጥ ከተዘረዘሩ የወይኑ ጌታ ባህርያት መካከል ከእግዚአብሔር ባሕርት ጋር የማይገጥሙ አሉ (ማቴዎስ 21፡33-43)፡፡ ምሳሌዎች ደግሞ በክፍሉ ላይ ከተጠቀሰው ፍቺ ውጪ ሌላ የተደበቀ ትርጉም ይኖራቸዋል ብሎ ማሰብ ስህተት ነው፤ ስለዚህ በወቅቱ ምሳሌው የተነገረበትን ትክክለኛ ነጥብ ካገኘን ዘንዳ ሌላ አላስፈላጊ ሐተታ ውስጥ መግባት አያሻንም፡፡
#መልዕክቶች- መልዕክቶች እንደስማቸው ከሰዎች ወደ ሌሎች የተላኩ ደብዳቤዎች ናቸው፡፡ ነገር ግን እነዚህ ደብዳቤዎች ተራ ደብዳቤዎች ሳይሆኑ ቅዱሳን ሐዋርያት በመንፈስ ቅዱስ ተመርተው የጻፏቸው ናቸው፡፡ የእነዚህን መልዕክቶች አጻጻፍ በምናይበት ጊዜ በአብዛኛው ተመሳሳይ የሆነ ቅርፅ እንዳላቸው እናስተውላለን፡፡ እነዚህም፡-
👉ጸሐፊው
👉የተቀባዩ ስም
👉ሰላምታ
👉ጸሎት፣ መልካም ምኞት ወይንም ምስጋና
👉የመልዕክቱ ዋና አካል
👉የመጨረሻ የስንብት ሰላምታ ናቸው፡፡
መልዕክቶችን በምንተረጉምበት ሰዓት ታሪካዊና ምንባባዊ አውዳቸውን ተከትለን የማጥናት መርህ እንደተጠበቀ ሆኖ በተጨማሪም መልዕክቶች እንደመሆናቸው ሳናቆራርጥ የንባብ ሂደቱን መጨረስ ይገባናል፡፡
3. ማዛመድ
ዕብራውያን 4፡2 ላይ የእግዚአብሔር ቃል ሲናገር “ዳሩ ግን የሰሙት ቃል ከሰሚዎቹ ጋር በእምነት ስላልተዋሐደ አልጠቀማቸውም” ይላል፡፡ ያጠናነው ቃል ከሕይወታችን ጋር ካልተዛመደ ከላይ የተጠቀሱትን ሁለቱን መንገዶች ተጠቅመን መጽሐፍ ቅዱስን ብንመረምር ለአዕምሯችን ዕውቀትን ከማግኘት ያለፈ ለመንፈሳችን የሚሆን በረከት ልናገኝ አንችልም፡፡ መጽሐፍ ቅዱስ ከብዙ ዘመናት በፊት ለነበሩ ሰዎች የተሰጠ ቃል ነው፤ ነገርግን በሐቲትና በመተርጎም በእኛና በእነርሱ መካከል የሚገኙትን የማንነት፣ የቋንቋ፣ የባሕል፣ የታሪክ፣ የቦታ፣ የአጻጻፍ፣ የዘመን፣ ወዘተ... ልዩነቶችን አስወግደን በየትኛውም ዘመንና በሁሉም ቦታ ሊሠራ የሚችል ለሁሉም ሕዝቦች ጠቃሚ የሆነን መልዕክት እናገኛለን፡፡ ማዛመድ ማለት በአጭር ቋንቋ ያጠናነው ቃል አሁን ስላለንበት ሁኔታ ወይንም ደግሞ ስለ ሕይወታችን ምን እንደሚልና ቃሉን ተግባራዊ ማድርግ የምንችለው እንዴት እንደሆነ በማወቅ በቃሉ መሠረት መኖር ማለት ነው፡፡ ዕለት ዕለት ይህንን ማድረግ ከቻልን የእግዚአብሔርን ኃይልና አብሮነት በሕይወታችን ውስጥ እንለማመዳለን፡፡
ይህንን ጽሑፍ ስንደመድም አፅንዖት ሰጥተን ልንናገረው የምንፈልገው የመጨረሻው ነጥብ ቢኖር መጽሐፍ ቅዱስን ስናጠና የመንፈስ ቅዱስን ድርሻ ልንዘነጋ እንደማይገባን ነው፡፡ እርሱ ከማንኛውም መዝገበ ቃላት፣ ሐተታ ወይንም ደግሞ አስተማሪ ይልቅ ሊያስተምረን የሚችል ሕልውናው እውን የሆነ መምህር ነው፡፡ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ እርሱ በመጣ ጊዜ ወደ እውነት ሁሉ እንደሚመራን ነግሮናል (ዮሐንስ 16፡13)፡፡ ጴጥሮስና ሌሎቹ ሐዋርያት ቅዱሳት መጻሕፍትን ያልተማሩ ሰዎች ቢሆኑም እንኳ መንፈስ ቅዱስ እራሱ ስላስተማራቸው ስለ ቅዱሳት መጻሕፍት የነበራቸው ጥልቅ ዕውቀት በወቅቱ የነበሩትን የአይሁድ መምህራን ሳይቀር አስገርሞ ነበር (የሐዋርያት ሥራ 3፡13)፡፡ መጽሐፍ ቅዱሳችንን ስናነብ እኔና እናንተንም መንፈስ ቅዱስ እንዲያስተምረን በጸሎት ልንጠይቀው ይገባል፡፡
“አብ በስሜ የሚልከው ግን መንፈስ ቅዱስ የሆነው አጽናኝ እርሱ ሁሉን ያስተምራችኋል እኔም የነገርኋችሁን ሁሉ ያሳስባችኋል።” (ዮሐንስ 14፡26)
ምንጭ:- www.ewnetlehulu.org

❤4
. ──•◈•─────•◈•─
የዕለቱ ጥቅስ
──•◈•─────•◈•─
“በውኑ ለእግዚአብሔር የሚሳነው ነገር አለን? የዛሬ ዓመት እንደ ዛሬው ጊዜ ወደ አንተ እመለሳለሁ፤ ሣራም ልጅን ታገኛለች።”
ዘፍጥረት 18፥14

❤15🔥1👏1🙏1
በቅዱሳት መጻሕፍት ውስጥ ሙሴ የትኛው ቦታ ላይ ነው ዐለቱን ሁለት ጊዜ የመታውና በዚህም ምክንያት እግዚአብሔር በእርሱ ላይ ፍርድ እንዲያስተላልፍ ያደረገው?
Anonymous Quiz
6%
ራፊዲም
24%
ቃዴስ
24%
ሲና
38%
መሪባ
7%
ማሳህ
❤3
የዘላለም ኪዳን.pdf
3.7 MB
📔ርዕስ፦ የዘላለም ኪዳን/The Better Covenant
👤ጸሐፊ፦ ዎችማን ኒ/Watchman nee
🗣 ትርጉም፦ ጳውሎስ ፈቃዱ
📑የገጽ ብዛት፦140
ወደ ቻናሉ ለመ🀄️ላ🀄️ል፦ @Holy_scriptures
👤ጸሐፊ፦ ዎችማን ኒ/Watchman nee
🗣 ትርጉም፦ ጳውሎስ ፈቃዱ
📑የገጽ ብዛት፦140
ወደ ቻናሉ ለመ🀄️ላ🀄️ል፦ @Holy_scriptures
❤1
. ──•◈•─────•◈•─
የዕለቱ ጥቅስ
──•◈•─────•◈•─
“እነዚህም ጌታን ሲያመልኩና ሲጦሙ መንፈስ ቅዱስ፦ በርናባስንና ሳውልን ለጠራኋቸው ሥራ ለዩልኝ አለ።”
ሐዋርያት 13፥2
ወደ ቻናሉ ለመ🀄️ላ🀄️ል፦ @Holy_scriptures
የዕለቱ ጥቅስ
──•◈•─────•◈•─
“እነዚህም ጌታን ሲያመልኩና ሲጦሙ መንፈስ ቅዱስ፦ በርናባስንና ሳውልን ለጠራኋቸው ሥራ ለዩልኝ አለ።”
ሐዋርያት 13፥2
ወደ ቻናሉ ለመ🀄️ላ🀄️ል፦ @Holy_scriptures
❤4🔥1
በቅዱሳት መጻሕፍት ውስጥ ሙሴ ከመሞቱ በፊት የተስፋይቱን ምድር ከየትኛው ተራራ ላይ ሆኖ አየ?
Anonymous Quiz
28%
ሲና
14%
ቀርሜሎስ
33%
ሞሪያ
25%
ናባው