ቅዱሳት መጻሕፍት
7.77K subscribers
1.46K photos
61 videos
349 files
848 links
በዚህ ቻናል

👉ቅዱሳት መጻሕፍት ይጠናሉ::
👉መጽሐፍ ቅዱሳዊ ትምህርቶች ይቀርባሉ::
👉 ለቅዱሳት መጽሐፍት ጥናት የሚያግዙ መጻሕፍት ይለቀቃሉ።

⭐️⭐️⭐️⭐️⭐️

@Holy_scriptures
Download Telegram
በቅዱሳት መጻሕፍት ውስጥ ኤልያስ ከንጉሥ አክዓብ ጋር ከተገናኘ በኋላ በየትኛው ተራራ ነው የበኣልን ነቢያት የተጋፈጠው?
Anonymous Quiz
14%
ገለዓድ
49%
ቀርሜሎስ
7%
አራራት
22%
ኮሬብ
7%
ሞሪያ
5👏1
.       ──•◈•─────•◈•─
                 የዕለቱ ጥቅስ 
        ──•◈•─────•◈•─
“ንፍታሌም የተፈታ ሚዳቋ ነው፤ መልካም ቃልን ይሰጣል።”
ዘፍጥረት 49፥21



ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
7
በቅዱሳት መጻሕፍት የኖኅ መርከብ ከጥፋት ውሃው በኋላ በየትኛው ተራራ ላይ አረፈ?
Anonymous Quiz
8%
ሞሪያ
7%
ሲና
5%
ቀርሜሎስ
76%
አራራት
4%
ጽዮን
6
.       ──•◈•─────•◈•─
                 የዕለቱ ጥቅስ 
        ──•◈•─────•◈•─
“ሰዎችን ሁሉ የሚያድን የእግዚአብሔር ጸጋ ተገልጦአልና፤”
ቲቶ 2፥11



ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
13🙏1
#እራሳችንን_እንመርምር


አንዳንድ በጣም ያስጨነቁንና ግራ ያጋቡን ነገሮች አቅማቸው ተገፎ የእኛን አሻቅቦ ማየት ብቻ እየጠበቁ ያለ ቢሆንስ?🤷‍♂

"እርስ በርሳቸውም፦ ድንጋዩን ከመቃብር ደጃፍ ማን ያንከባልልልናል? ይባባሉ ነበር፤ ድንጋዩ እጅግ ትልቅ ነበርና፤ አሻቅበውም አይተው ድንጋዩ ተንከባሎ እንደ ነበር ተመለከቱ።"
ማርቆስ 16፥3-4


ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
11🙏1
.       ──•◈•─────•◈•─
                 የዕለቱ ጥቅስ 
        ──•◈•─────•◈•─
“ጌታቸው በመጣ ጊዜ ሲተጉ የሚያገኛቸው እነዚያ ባሪያዎች ብፁዓን ናቸው፤ እውነት እላችኋለሁ፥ ታጥቆ በማዕድ ያስቀምጣቸዋል ቀርቦም ያገለግላቸዋል።”
ሉቃስ 12፥37



ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
16🙏2
በቅዱሳት መጻሕፍት ውስጥ ሳኦልና ዮናታን የሞቱት በየትኛው ተራራ ላይ ነው?
Anonymous Quiz
14%
ቀርሜሎስ
51%
ጊልቦዓ
11%
ገሪዛን
24%
ገለዓድ
2
ቅዱሳት መጻሕፍት
#አዲስ_ዓመት #New_Year መጽሐፍ ቅዱስን እንዴት እናንብብ? ጠቃሚ መርሆች             ክፍል-3 የአንድን የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል የምንባብ አውድ ለመረዳት የሚከተሉትን ጥያቄዎች ልናነሳ እንችላለን፡- 👉ተናጋሪው ማነው? 👉ለማነው የተናገረው? 👉ጸሐፊው ለምን ይህንን በዚህ ስፍራ አስገባው? 👉ከፊት ምን ተባለ? 👉ከኋላ ምን ተባለ? 👉ይህ ቃል፣ ሐረግ ወይም አረፍተ ነገር በዚህ ስፍራ…
#አዲስ_ዓመት
#New_Year


መጽሐፍ ቅዱስን እንዴት እናንብብ? ጠቃሚ መርሆች


            ክፍል-4


#ትረካዎች – መጽሐፍ ቅዱስ በብዙ ታሪኮች የተሞላ መጽሐፍ ነው፡፡ አንድ ታሪክ በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ስለተጻፈ ብቻ እንደ እግዚአብሔር ሐሳብ የተፈጸመ ትክክለኛ ድርጊት ነው ማለት አይደለም፡፡ ነገር ግን የተጻፈው እያንዳንዱ ታሪክ ለትምህርታችን ተጽፏል፡፡ የብሉይ ኪዳን ታሪኮች እግዚአብሔር በፍጥረቱ ውስጥ እንዴት እንደሠራና ሰዎች ደግሞ ለእርሱ የሰጡትን ምላሽ የሚያሳዩ ናቸው፡፡ እነዚህን ታሪኮች ባሉበት ሁኔታ ከመረዳት ይልቅ ስውር ትርጉሞችን በመፈለግ ልንተነትናቸው አይገባም፡፡ በአጠቃላይ በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የሚገኙ ትረካዎችን ስናጠና የሚከተሉትን ነጥቦች ማስታወስ ያሻናል፡-

👉ትረካዎች እውነተኛ ታሪኮችን የሚናገሩ ናቸው ነገር ግን የእያንዳንዱን ክንውን ዝርዝር ሁኔታ የመናገር ዓላማ ላይኖራቸው ይችላል፡፡

👉ትረካዎች መጽሐፍ ቅዱስ በሌሎች ስፍራዎች ላይ የሚያስተምራቸውን እውነታዎች የሚያብራሩ ናቸው፡፡

👉ትረካዎች ብዙ ጊዜ የሚዘግቡት የተፈፀመውን እንጂ ሊፈፀም የሚገባውን ላይሆን ይችላል፡፡

👉ትረካዎች ልንከተላቸው የሚገቡ በጎ ምሳሌዎችን ወይንም ደግሞ ልንርቃቸው የሚገቡት መጥፎ ምሳሌዎችን ሊይዙ ይችላሉ፡፡

👉የሁሉም ትረካዎች ዋና ባለታሪክ እግዚአብሔር መሆኑ ሊታወቅ የሚገባው መርህ ነው፡፡

#መዝሙራት– በቅኔ ውስጥ የሚመደቡ ሲሆኑ በተለያዩ ዘመናት የእግዚአብሔር ሰዎች የዘመሯቸውን መዝሙራትና የጸለዩዋቸውን ጸሎቶች ያጠቃልላሉ፡፡ እነዚህም በመዝሙር መጽሐፍ ውስጥ የተሰበሰቡ ሲሆኑ አብዛኞቹ በዳዊት የተጻፉ ናቸው፡፡ ብዙ ጊዜ መዝሙራት ትዕምርታዊ ንግግሮችን ስለሚጠቀሙ እያንዳንዱን ነገር በቀጥታ መተርጎም ትክክል አይደለም፡፡ ለምሳሌ ለእግዚአብሔር የተሰጡ ሰዋዊ ባሕርያትን በቀጥታ በመውሰድ እግዚአብሔርን በዚያ ሁኔታ መሳል ስህተት ነው፡፡ እነዚህ መዝሙራት ከሰው ወደ እግዚአብሔር የቀረቡ ምስጋናዎችና ጸሎቶች እንደመሆናቸው መጠን ዘማርያኑ የግል ስሜቶቻቸውን፣ ቁጣቸውን ወይንም ደግሞ ኀዘናቸውን የሚገልጹባቸውን ክፍሎች በመውሰድ ተግባራዊ ልናደርጋቸው እንደሚገቡ ነገሮች መቁጠርም እንደዚሁ ስህተት ነው፡፡ ሌላው ዘማርያኑ ስለ ተፈጥሮ፣ ስለ ዓለም፣ ባጠቃላይ ስለ አፅናፈ ዓለም ባላቸው መረዳት መጠን መናገራቸውን የመጽሐፍ ቅዱስ ሳይንሳዊ ስህተቶች እንደሆኑ ማሰብ ተገቢ አይደለም፡፡

#የጥበብ_መጻሕፍት- መጽሐፈ ኢዮብ፣ መጽሐፈ ምሳሌ፣ መጽሐፈ መክብብና መኃልየ መኃልይ ሲሆኑ በቅኔ መጻሕፍት ውስጥ ይመደባሉ፡፡ እነዚህን መጻሕፍት ሙሉ በሙሉ ካላነበብን ብዙ ጊዜ በተሳሳተ መንገድ ልንተረጉማቸው እንችላለን፡፡ ለምሳሌ መጽሐፈ መክብብን ከምዕራፍ 11፡9 በፊት የሚገኘውን ብቻ በማንበብ ብንተው ትክክለኛ ነጥቡን ሳናገኝ እንቀራለን፡፡ እነዚህ መጻሕፍት በአብዛኛው ምሳሌያዊ ንግግሮችን፣ ምፀቶችን፣ ቅኔያዊ አገላለፆችን ወዘተ... ይጠቀማሉ፡፡ እነዚህን የንግግር ዓይነቶች መረዳትና መተርጎም ያለብን እንደየባሕርያቸው ነው፡፡ ሌላው የቅኔ መጻሕፍትን ስንተረጉም ልንረዳው የሚገባን ነገር ቢኖር የየዕለት ተግባራዊ የሕይወት መመርያን ከማስተላለፍ በዘለለ ጠንካራ የሥነ መለኮት አስተምህሮዎችን በቀጥታ የማስተላለፍ ሁኔታቸው አነስተኛ መሆኑን ነው፡፡ እንደ ተጨማሪ ድጋፍ ከመጠቀም ያለፈ መሠረታዊ አስተምህሮዎችን በቅኔ መጻሕፍት ውስጥ በሚገኙ ጥቅሶች ላይ ብቻ ሙሉ በሙሉ መመሥረት አይገባንም የሚል አጠቃላይ ግንዛቤ በመጽሐፍ ቅዱስ ምሑራን ዘንድ አለ፡፡

ይቀጥላል...


ምንጭ:- www.ewnetlehulu.org




ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
4👍1
.       ──•◈•─────•◈•─
                 የዕለቱ ጥቅስ 
        ──•◈•─────•◈•─
“በጠሩህ ጊዜ ሁሉ ትሰማቸው ዘንድ ለባሪያህና ለሕዝብህ ለእስራኤል ልመና ዓይኖችህ የተገለጡ ይሁኑ።”
1ኛ ነገሥት 8፥52



ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
11
በቅዱሳት መጻሕፍት ውስጥ የትኛው ተራራ ከበረከት፣ የትኛውስ ተራራ ከእርግማን ጋር የተያያዘ ነው?
Anonymous Quiz
21%
ሲና-----ቀርሜሎስ
14%
ታቦር-----ጊልቦዓ
21%
ሲና------ጌባል
43%
ገሪዛን-----ጌባል
1
#የእግዚአብሔር_ቃል_ምን_ይላል

ዘዳግም 11
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
²⁶ እነሆ፥ እኔ ዛሬ በፊታችሁ በረከትንና መርገምን አኖራለሁ፤
²⁷ በረከትም፥ እኔ ዛሬ ለእናንተ የማዝዘውን የአምላካችሁን የእግዚአብሔርን ትእዛዝ ብትሰሙ፤
²⁸ መርገምም፥ የአምላካችሁን የእግዚአብሔርን ትእዛዝ ባትሰሙ፥ ዛሬም ካዘዝኋችሁ መንገድ ፈቀቅ ብትሉ፥ ሌሎችንም የማታውቋቸውን አማልክት ብትከተሉ ነው።
²⁹ አምላክህም እግዚአብሔር ትወርሳት ዘንድ አንተን ወደምትሄድባት ምድር ባገባህ ጊዜ፥ በረከቱን በገሪዛን ተራራ መርገሙንም በጌባል ተራራ ታኖራለህ።
³⁰ እነርሱም በዮርዳኖስ ማዶ፥ ከፀሐይ መግቢያ ካለችው መንገድ በኋላ፥ በዓረባ በተቀመጡት በከነዓናውያን ምድር፥ በጌልገላ ፊት ለፊት በሞሬ የአድባር ዛፍ አጠገብ ናቸው።
³¹ አምላካችሁ እግዚአብሔር የሚሰጣችሁን ምድር ትወርሱ ዘንድ ዮርዳኖስን ትሻገራላችሁ፥ ትወርሱአታላችሁም፥ ትቀመጡባታላችሁም።
³² እኔም ዛሬ በፊታችሁ የማኖራትን ሥርዓትና ፍርድ ሁሉ ታደርጉ ዘንድ ጠብቁ።


ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
የአዲስ_ኪዳን_ታሪካዊና_ባሕላዊ_መሰረቶች_.pdf
4.1 MB
📔ርዕስ፦የአዲስ ኪዳን ታሪካዊና ባሕላዊ መሠረቶች
📖የገፅ ብዛት ፦87


ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures