ቅዱሳት መጻሕፍት
7.45K subscribers
1.36K photos
61 videos
332 files
807 links
በዚህ ቻናል

👉ቅዱሳት መጻሕፍት ይጠናሉ::
👉መጽሐፍ ቅዱሳዊ ትምህርቶች ይቀርባሉ::
👉 ለቅዱሳት መጽሐፍት ጥናት የሚያግዙ መጻሕፍት ይለቀቃሉ።

⭐️⭐️⭐️⭐️⭐️

@Holy_scriptures
Download Telegram
ራስህን አድን!


ክፍል ሁለት  



17) አሳባቸውን፣ ስሕተታቸውንና ፍላጎታቸውን ለመረዳት ትችል ዘንድ ስለመዳን ባላቸው ጥያቄ ላይ ከሁሉም ዓይነት አድማጮችህ ጋር አብዝተህ ተነጋገር። ትምህርትህን ከነርሱ ፍላጎት ጋር ለማዛመድ ትችል ዘንድ አመለካከታቸውንና ስሜታቸውን አጢን። ልማዶቻቸውን ልብ በል። ምን እንደተጋረደባቸውም አስተውል። ማወቅ የሚገባህን ሁሉ እወቅ።

18) ሥራዬ ብለህ የምታደርጋቸው ሁሉ ትክክል መሆናቸውን አያያዝህም ርጋታ ያለተለየው መሆኑን:አጢን። ከትንባሆ፤ የአልኮል መጠጥና አደንዛዥ ዕፆች ሌሎችም አንተን ሊያሳፍሩ ሌሎችንም ሊያሰናክሉ ከሚችሉ ነገሮች እድፍና ጠረን ነፃ መሆንህን ርግጠኛ ሁን።

19) ቁርጠኝነት አይጉደልህ፤ ነገር ግን ሁልጊዜ እግዚአብሔርን አስቀድም (መዝ. 16:8)።

20) ለአንደበትህ ልጓም አብጅለት፤ ለከንቱና ዋጋ ቢስ ንግግር ራስህን አሳልፈህ አትስጥ።

21) መድረክ ላይ ስትወጣም ይሁን ከዚያ ስትወርድ ቁርጠኛና እርግጠኛ መሆንህንሰዎች ይረዱት። ከእነርሱ ጋር ያለህ የዕለት ተዕለት ግንኙነት በሰንበት ቀን የምታቀርበውን ወሳኝ ትምህርት ዋጋ ቢስ አያድርገው።

22) ከተሰቀለው ኢየሱስ ክርስቶስ በቀር ሌላ እንደማታውቅ ለሚቀርቡህ ሁሉ ይታወቅ። በክርስቶስ አምባሣደርነትህ ከእነርሱ ጋር ያለህ ሕብረት ስለነፍሳቸው መዳን ብቻ መሆኑን ይረዱት።     

23) መሆን አለበት:ብለህ የምታስተምረውን በምሳሌነት አሳይ። የምትሰብከውን ኑር።

24) ያልሆነ አሳብ ወይም ጥርጣሬ እንዳያስከትልና ንጽሕናህን እንዳይነካ በተለይ ከሴቶች ጋር ስለሚኖርህ ግንኙነት ተጠንቀቅ።

25) ደካማ ጎኖችህን ተከላከል። አላስፈላጊ ወደሆነ ነገርም ይሁን ርካሽ ፈንጠዝያ ፍለጋ  ወደዚያ አቅጣጫ ከሚያዘሙህ አጋጣሚዎች ተጠንቀቅ።

26) በተፈጥሮህ ኮስታራ ወይም ገለልተኛ  ከሆንክ መራራና ሰዎችን የማትቀርብ ሆነህ እንዳትቆጠር ተጠንቀቅ።

27) የሰውን ጆሮ ለማግኘት ብቻ የሚደረግን ጥረትና ካባ የለበሰ ውሸትን አስወግድ። ያኔ የማስመሰል ድርጊት ለመፈጸም አትፈተንም።

28) ጽናት፣ እውነተኝነትና ክርስቲያናዊ ባለቤትነት የሁለንተናዊ ኑሮህ መለያ ይሁኑ።

29) በቀንም ይሁን በማታ ሁልጊዜ ለጸሎትና ከእግዚአብሔር ጋር ሕብረት ለማድረግ ብዙ ጊዜ ውሰድ። ይህም ለማዳን ብዙ ኃይል ይሆንልሃል። የዚህን ሕብረት መታጣት ግን የትኛውም ዓይነት ትምህርት ይሁን ጥናት ሊያካካሰው አይችልም። ከእግዚአብሔር ጋር ሕብረት ከሌለህ እንደማንኛውም ሰው ደካማ ነህ።

30) ዳግም ልደት የለም የሚለውንና ያንንም ተከትሎ የነፍሳትን መዳን የሚጠራጠረውን ስሕተት አስወግድ።

31) ዳግም ልደት የሞራልና ይልቁንም የፍቃደኝነት ለውጥ መሆኑን ልብ በል።

32) ወንጌል የሰዎችን ልብ መለወጥ እንደሚችል ሆኖ ተዘጋጅቷል። ያንን በጥበብ ስትሰብከው ደግሞ ከመንፈስ ቅዱስ ውጤታማ እገዛ እንደምታገኝ ጠብቅ።


ይቀጥላል.....


ምንጭ:- alemayehuwrites.blogspot.com



ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
7👏1
.       ──•◈•─────•◈•─
                          የዕለቱ ጥቅስ
        ──•◈•─────•◈•─
“የዚያን ጊዜ እግዚአብሔርን የሚፈሩ እርስ በእርሳቸው ተነጋገሩ፤ እግዚአብሔርም አደመጠ፥ ሰማም፥ እግዚአብሔርንም ለሚፈሩ ስሙንም ለሚያስቡ የመታሰቢያ መጽሐፍ በፊቱ ተጻፈ።”
ሚልክያስ 3፥16




ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
❤‍🔥111
Spiritual Leadrship
Nigusse Denano
#መጻሕፍትን_በድምጽ

📔ርዕስ፦ መንፈሳዊ መሪ
👤ጸሐፊ፦ J.Oswald Sanders
👉ክፍል-6


ይቀጥላል...


ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
2
#እራሳችንን_እንመርምር


“አቤቱ፥ ፍጻሜዬን አስታውቀኝ፥ የዘመኔ ቍጥሮች ምን ያህል እንደ ሆኑ፥ እኔ ምን ያህል ወደ ኋላ እንደምቀር አውቅ ዘንድ።”
መዝሙር 39፥4

“እግዚአብሔር ሆይ፤ የሕይወቴን ፍጻሜ፣ የዘመኔንም ቍጥር አስታውቀኝ፤ አላፊ ጠፊ መሆኑንም ልረዳ።”
መዝሙር 39፥4 (አዲሱ መ.ት)

እግዚአብሔር ሆይ ፥ የሕይወቴ ፍጻሜ መቼ እንደ ሆነና የዕድሜዬ ልክ ስንት እንደ ሆነ ግለጽልኝ፤ በዚህ ዓለም የምኖረው ዘመን ፈጥኖ የሚያልፍ መሆኑን ለማወቅ አስችለኝ።"
መዝሙር 39፥4 (ሕያው ቃል)



ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
8👏4
.       ──•◈•─────•◈•─
                          የዕለቱ ጥቅስ
        ──•◈•─────•◈•─
“አካሄድን እንደ ቃልህ አቅና፤ ኃጢአትም ሁሉ አይግዛኝ።”
መዝሙር 119፥133



ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
7👏1
እንደሚታወቀው ከፈረንጆቹ October 1-31 የተሐድሶ ወር በመባል በሉተራዊያን ዘንድ ወር በሙሉ ስለተሐድሶ ይወሳል፣ ውይይት ይደረጋል ይዘከራልም። ይህን በማስመልከት እኛም ይህን ወር በልዩ ሁኔታ ለማስታወስ በተለያዩ ትምህርቶች፣ ውይይቶች፣ እጅግ ለየት ያሉ ፕሮግራሞችን አዘጋጅተን ጨርሰናል። በቅርብ ቀን በዚህ ቻናል ብቻ ይጠብቁን

#ተሐድሶ
#reformation


ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️👉 @TME_bible_study
👍93👏3
Spiritual Leadership
Nigusse Denano
#መጻሕፍትን_በድምጽ

📔ርዕስ፦ መንፈሳዊ መሪ
👤ጸሐፊ፦ J.Oswald Sanders
👉ክፍል-7


ይቀጥላል...


ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
👍54👎1
ራስህን አድን!


         ክፍል ሦስት  


33) ዐውድህን ስትመርጥና ስታዘጋጅ በመንፈስ ቅዱስ ለሚመጣው ትምህርት ሁነኛ ቦታ ስጠው።

34) ስብከቶችህ  ከልብ የመነጩ እንጂ  የጭንቅላት እውቀት አይሁኑ።

35) ጥልቀት በሌለው ንባብና ጥናት ወይም በሰሚ ሰሚ ሳይሆን የተለማመድከውን ስበክ።

36) ሁሌም መንፈስ ቅዱስ ልብህ ላይ የሚያስቀምጠውን የወቅቱን ቃል አቅርብ። እርሱ የሚያቀብልህን ነጥቦች አጥብቀህ ያዝና በተቻለህ መጠን በቀጥታ ለጉባዔው አድርስ።

37) ሁሌም ልትሰብክ ስትነሣ ከጓዳህ በጸሎት ተሞልተህ መንፈስ ቅዱስ በውስጥህ እየቃተተና በከንፈሮችህም ሊናገር እየፈለገ ሳለ ወደ መድረኩ ዝለቅ።

38) አፍህን ስትከፍት ንግግርህ ይፈጥንና እንደጎርፍ ይወርድ ዘንድ አእምሮህ በርዕሰ ጉዳይህ ላይ እንዲነሣሣ አድርግ።

39) ወጥመድን የሚያመጣው ሰውን መፍራት (ምሳ.29:25) በአንተ ላይ አይኑር። እግዚአብሔርን እጅግ ከመፍራትህ የተነሣ ሰዎችን መፍራት እንደማይሆንልህ ሰሚዎችህ ይወቁ።

40) የምትሰብካቸው ሰዎች ስላንተ ያላቸው ዕውቀት በስብከትህ ላይ ተፅዕኖ እንዲያሳድር አትፍቀድ።

41) የቀለብ ጥያቄ “ሰዎች ቢሰሙትም ባይሰሙትም የእግዚአብሔርን እውነት ከማወጅ” አይከልክልህ።

42) በሕዝብህ ዘንድ ያለህን መታመን ስለሚያሳጣህና እንዳይድኑም ስለሚያደርግ አታመንታ። እንደ ክርስቶስ አምባሣደር ተልዕኮህን የመወጣት ቁርጠኝነት ካላዩብህ እንደሚገባ  አያከብሩህም።

43) እውነትን በመግለጥ ግን በእግዚአብሔር ፊትና ለሰው ሕሊና ሁሉ ራስህን ብቁ አድርገህ ማቅረብን አትርሳ (2 ቆሮ.4:2)።

44)  “ያለልክ ገንዘብ ወዳድ” አትሁን።

45)  ከንቱ የሆነ አቀራረብን አስወግድ።

46) እውነተኛነትና መንፈሳዊ ጥበብህን እንዲያከብሩ ገፋፋቸው።

47)  አፍታም እንኳ ቢሆን የሚሰፈርልህ ቀለብ በጥቂቱም ይሁን ሙሉ በሙሉ ስብከትህን ያስቀይራል ብለው እንዳያስቡ አድርግ።


ይቀጥላል.....


ምንጭ:- alemayehuwrites.blogspot.com




ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
11
ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
4
ሚዛን_የጠበቀ_ሕይወት_እና_አገልግሎት.pdf
1.5 MB
👉ርዕስ፦ ሚዛን የጠበቀ ሕይወት እና አገልግሎት
👤ጸሐፊ፦ ከበደ በከሬ
📑የገጽ ብዛት፦ 166


ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
.       ──•◈•─────•◈•─
                          የዕለቱ ጥቅስ
        ──•◈•─────•◈•─
“ኃጢአት አይገዛችሁምና፤ ከጸጋ በታች እንጂ ከሕግ በታች አይደላችሁምና።”
ሮሜ 6፥14



ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
15
Spiritual Leadership
Nigusse Denano
#መጻሕፍትን_በድምጽ

📔ርዕስ፦ መንፈሳዊ መሪ
👤ጸሐፊ፦ J.Oswald Sanders
👉ክፍል-8


ይቀጥላል...


ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
4
.       ──•◈•─────•◈•─
                          የዕለቱ ጥቅስ
        ──•◈•─────•◈•─
“ነገር ግን ስሜን ለምትፈሩት ለእናንተ የጽድቅ ፀሐይ ትወጣላችኋለች፥ ፈውስም በክንፎችዋ ውስጥ ይሆናል፤ እናንተም ትወጣላችሁ፥ እንደ ሰባም እምቦሳ ትፈነጫላችሁ።”
ሚልክያስ 4፥2


ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
8
የሮሜ መንገድ

#የሮሜ_መንገድ


ብዙ የወንጌል አማኝ ክርስቲያኖች የመዳንን መንገድ ወይም እንዴት እንደምንድን ለማብራራት ከሮሜ መልእክት የጥቅሶችን ስብስብ ይጠቀማሉ፣ በተለምዶ “የሮሜ መንገድ” እየተባለ የሚጠራውን የደኅንነት እቅድ ለማስረዳት፦

ሮሜ 3፡23፦ ሁሉም ኃጢአት ሠርተዋል

“ሁሉ ኃጢአትን ሠርተዋልና የእግዚአብሔርም ክብር ጎድሎአቸዋል፤”
ሮሜ 3፥23

ሮሜ 6፡23፦ የኃጢአት ደመወዝ ሞት ነው።

“የኃጢአት ደመወዝ ሞት ነውና፤ የእግዚአብሔር የጸጋ ስጦታ ግን በክርስቶስ ኢየሱስ በጌታችን የዘላለም ሕይወት ነው።”
ሮሜ 6፥23

ሮሜ 5፡8፦ እግዚአብሔር ለእኛ ያለውን ፍቅር አሳይቷል።

“ነገር ግን ገና ኃጢአተኞች ሳለን ክርስቶስ ስለ እኛ ሞቶአልና እግዚአብሔር ለእኛ ያለውን የራሱን ፍቅር ያስረዳል።”
ሮሜ 5፥8

ሮሜ 10፡9፦ ለመዳን ተናዘዙ እና እመኑ።

“ኢየሱስ ጌታ እንደ ሆነ በአፍህ ብትመሰክር እግዚአብሔርም ከሙታን እንዳስነሣው በልብህ ብታምን ትድናለህና፤”
ሮሜ 10፥9


እነዚህ መልእክቶች የሮሜ መልእክት እንዴት በሥነ-መለኮት የበለጸገ እና በታሪክ ተደማጭነት ያለው፣ የግለሰቦችን ሕይወት የሚነካ እና የክርስቲያን አስተምህሮዎችን ለዘመናት የሚቀርጹ መሆኑን ያሳያል።





ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
12
Spiritual Leadership
Jun 5, 2013
#መጻሕፍትን_በድምጽ

📔ርዕስ፦ መንፈሳዊ መሪ
👤ጸሐፊ፦ J.Oswald Sanders
👉ክፍል-9


ይቀጥላል...


ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
"የዋጀህ ማን መሆኑን አትንገረኝ፤ የተዋጀ ሕይወትህን አሳየኝና እኔ የዋጀህን ፈልጌ ላግኘው።"
ቮልቴር



ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
👍7👎1
.       ──•◈•─────•◈•─
                          የዕለቱ ጥቅስ
        ──•◈•─────•◈•─
“ሞታችኋልና፥ ሕይወታችሁም በእግዚአብሔር ከክርስቶስ ጋር ተሰውሮአልና፤”
ቆላስይስ 3፥3



ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
8
#አዲስ_ዓመት
#New_Year

መጽሐፍ ቅዱስን እንዴት እናንብብ? ጠቃሚ መርሆች




             ክፍል-1



መጽሐፍ ቅዱስ ማዕከላዊ መልዕክቱ ለማንኛውም ሰው ግልፅ ሊሆን በሚችልበት ሁኔታ የተቀመጠ ስለሆነ በሁሉም የዕድሜ ክልሎችና በየትኛውም የትምህርት ደረጃ ላይ ላሉ ሰዎች መናገር የሚችል መጽሐፍ ነው፡፡ 2ኛ ጢሞቴዎስ 3፡14-15 ላይ ህጻናት እንኳ የመጽሐፍ ቅዱስን ዋና መልዕክት መረዳት እንደሚችሉ ይናገራል፡፡ ይህ ማለት ግን ሁሉም የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍሎች እኩል በሆነ ሁኔታ ግልፅ ናቸው ወይንም ደግሞ በቀላሉ ለመረዳት የሚያዳግቱ ክፍሎች የሉም ማለት አይደለም፡፡ ነገር ግን ማንኛውም ሰው የዘላለምን ሕይወት ማግኘት እንዲችል ማዕከላዊ መልእክቱ ብዙ ጊዜ በመደጋገምና እጅግ ግልጽ በሆነ ሁኔታ ተቀምጧል፡፡

መጽሐፍ ቅዱስ የተጻፈው እንድናነበው እንጂ እንደ ምትሃታዊ መጽሐፍ በመቁጠር ተንተርሰነው እንድንተኛ ወይንም ደግሞ ሊነካካ በማይችልበት ስፍራ በጥንቃቄ እንድናስቀምጠው አይደለም፡፡ የእግዚአብሔር ቃል በሕይወታችን ውስጥ ሊሠራ የሚችለው ሲነበብ ነው፡፡ የእግዚአብሔር ቃል እንደ አድካሚ ኃይማኖታዊ ሕግጋት ስብስብ ሊታሰብ አይገባም፡፡ የእግዚአብሔር ቃል የሕይወት ቃል ነው፤ ሕያውና የሚሠራም ነው፡፡ ስናነበው እምነትን በውስጣችን ይፈጥራል፣ ነፍሳችንን ያድሳል፤ ይለውጠናልም፡፡ በውስጡ የተቀመጡትን ሕግጋት በራሳችን ኃይልና ጥረት ልንፈፅማቸው እንደምንችል መቁጠር አይኖርብንም፡፡ በእግዚአብሔር ቃል ሐሳብ ለመኖር መጀመርያ ቃሉ በውስጣችን በሚፈጥረው እምነት በክርስቶስ ኢየሱስ አዳኝነት በማመን አዲስ ፍጥረት መሆን ያስፈልገናል፤ ከዚያም ኃይል የሚሰጠውን የክርስቶስን መንፈስ መቀበል ያስፈልገናል፡፡

የእግዚአብሔርን ቃል አንብበን የምንረዳው ሰዎች ባወጡት ቀመር መሠረት ባይሆንም ነገር ግን ሊታወቁ የሚገባቸው መርሆች አሉ፡፡ በማስከተል እነዚህን መርሆች እንዳስሳለን፡፡

የልብ ዝግጅት

አንዳድ ሰዎች በተደጋጋሚ የሚናገሩት የተለመደ ነገር ቢኖር መጽሐፍ ቅዱስን በማንበባቸው ሳብያ ትክክል አለመሆኑን እንደተገነዘቡና በቀደመው ሃይማኖታቸው እንዲፀኑ እንደረዳቸው ነው፡፡ እነዚህ ወገኖቻችን ያልተገነዘቡት አንድ እውነት ቢኖር የእግዚአብሔር ቃል ተልዕኮ ሁለት ገጽታ ያለው መሆኑን ነው፡፡ መጽሐፍ ቅዱስ እውነትን ለሚጠሙ ሰዎች የሕይወት ቃል ሲሆን በእውነት ላይ ለሚያምጹ ሰዎች ደግሞ የፍርድ ቃል ነው፡፡ የእግዚአብሔር ቃል ሰዎችን ወደ እምነት ያመጣል አለዚያም ደግሞ ልባቸውን በማደንደን ይገፈትራቸዋል፡፡ ሁለቱም ውጤቶች ግን ከሰዎቹ የልብ ዝግጅት አንጻር የሚከወኑ ናቸው፡፡ የእግዚአብሔር ቃል ሕይወት አልባ ንግግር ሳይሆን የሚሠራ ነው፡-

“የእግዚአብሔር ቃል ሕያው ነውና፥ የሚሠራም፥ ሁለትም አፍ ካለው ሰይፍ ሁሉ ይልቅ የተሳለ ነው፥ ነፍስንና መንፈስንም ጅማትንና ቅልጥምንም እስኪለይ ድረስ ይወጋል፥ የልብንም ስሜትና አሳብ ይመረምራል”
    (ዕብ. 4፡12)

ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ እንደተናገረው በመጨረሻው ቀን በኛ ላይ የሚፈርደው ቃሉ ነው፡-

“ዓለምን ላድን እንጂ በዓለም ልፈርድ አልመጣሁምና ቃሌን ሰምቶ የማይጠብቀው ቢኖር የምፈርድበት እኔ አይደለሁም። የሚጥለኝ ቃሌንም የማይቀበለው እርሱ የሚፈርድበት አለው፤ እኔ የተናገርሁት ቃል እርሱ በመጨረሻው ቀን ይፈርድበታል።”
  (ዮሐ. 12፡47-48)

ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ በ2ኛ ቆሮንቶስ መልዕክቱ ላይ የሚከተለውን ይናገራል፡-

“በሚድኑቱና በሚጠፉቱ ዘንድ ለእግዚአብሔር የክርስቶስ መዓዛ ነንና፤ ለእነዚህ ለሞት የሚሆን የሞት ሽታ ለእነዚያም ለሕይወት የሚሆን የሕይወት ሽታ ነን። ለዚህም ነገር የሚበቃ ማን ነው?” 2ኛ ቆሮንቶስ 2፡15-16

ሐዋርያው እያለ ያለው ነገር ቢኖር ወንጌል ዝም ብለን የምንቀበለው ወይንም ደግሞ የምንጥለው ነገር ሳይሆን ብንቀበለው ወይንም ደግሞ ባንቀበለው በሕይወታችን ላይ ተፅዕኖ ማምጣቱ ግድ መሆኑን ነው፡፡ ስለዚህ ሰዎች የእግዚአብሔርን ቃል ሲንቁ፣ መዘባበቻ ሲያደርጉና ሲያምጹበት የተሸነፉት እነርሱ እንጂ ቃሉ አይደለም፡፡ በዚህም ሆነ በዚያ የእግዚአብሔር ቃል አሸናፊ ነው፡፡ ለተቀበሉት የዘላለምን ሕይወት ሲሰጥ ባልተቀበሉት ላይ ግን ይፈርዳል፡፡ የወንጌል መልዕክት እውነትን ለማወቅ ለሚፈልጉ ሰዎች የሕይወት ዜና ነው፤ ለዘባቾች ግን የሞት ዜና ነው፡፡ ውድ አንባቢያን እናንተ የእግዚአብሔርን ቃል እውነትን በሚፈልግ ልብ ከሚያነቡት ወገን ናችሁ ወይንስ ከቃሉ ውስጥ “ስህተቶችን” ነቅሰው ለማውጣት ከሚያነቡት ሰዎች ወገን ናችሁ? ቀና በሆነ ልብ ቃሉን በማንበብ የዘላለምን ሕይወት ታገኙ ዘንድ ምኞታችንና ጸሎታችን ነው፡፡

ሥነ ፍታቴ (Hermeneutics)

የሥነ ፍታቴ ጥቅም መጽሐፍ ቅዱስ በተጻፈበት ዘመን ለመጀመርያዎቹ ተቀባዮች የነበረውን ትርጉምና ዛሬም ደግሞ ለኛ ምን ማለት እንደሆነ እንድንረዳ ማገዝ ነው፡፡ በዘመናት መካከል ሰዎች ይህንን ቃል ብዙ ክፉ ሥራዎቻቸውን ለማጽደቅ ጠቅሰውታል፡፡ በዚህ ዘመንም ብዙ ሰዎች በመልካምም ሆነ በእኩይ ፍላጎት በመነሳሳት መጽሐፍ ቅዱስ ያላለውን ነገር ሲያስብሉት እናያለን፡፡  በቤተ ክርስቲያን ውስጥ የሚገኙ ብዙ ሰባኪያን ትግላቸው በአንድ ጥቅስ ውስጥ ያለን ልዩ ትርጉም ማግኘት ይመስላል፡፡ የስህተት አስተማሪዎችና ከክርስትና ውጪ ያሉ የአንዳንድ ሃይማኖቶች ተከታዮችም ደግሞ የራሳቸውን አስተምህሮ ለመደገፍ ወይንም ደግሞ መጽሐፍ ቅዱስ ስህተት እንዳለበት ለማሳየት በማለም ጥቅሶችን ይጠመዝዛሉ፡፡

መጽሐፍ ቅዱስን በምናጠናበት ሰዓት ከመሠረታዊ የሥነ ፍታቴ መርሆች ጋራ የሚጣረስ አተረጓጎም የምንጠቀም ከሆነ ወደ ስህተት እንገባለን፡፡ ስለዚህ ማንኛውም መጽሐፍ ቅዱስን ለግል ሕይወቱም ሆነ ሌሎችን ለማስተማር ማጥናት የሚፈልግ ሰው እነዚህን ጠቃሚ መርሆች ማወቅ ይኖርበታል፡፡

ጎርደን ዲ. ፊ. እና ዳግላስ ስቱዋርት የተባሉ ክርስቲያን ጸሐፍት የሥነ ፍታቴን አስፈላጊነት በተመለከተ የሚከተለውን ብለዋል፡-

ሥነ ፍታቴ አስፈላጊ መሆኑን የሚያሳይ መርህ በመጽሐፍ ቅዱስ ባሕርይ ውስጥ ይገኛል፡፡ ቤተክርስቲያን የመጽሐፍ ቅዱስን ባሕርይ የክርስቶስን ባሕርይ በምትረዳበት ሁኔታ ስትረዳ እንደኖረች ታሪክ ያሳያል፡፡ መጽሐፍ ቅዱስ በአንድ ጊዜ ሰብዓዊም መለኮታዊም ነው፡፡ ፕሮፌሰር ጆርጅ ላድ አንድ ጊዜ እንደተናገሩት፦ “መጽሐፍ ቅዱስ በሰዎች ቃላት በታሪክ ውስጥ የተሰጠ የእግዚአብሔር ቃል ነው፡፡” እንግዲህ ይህ ሁለትዮሽያዊ የመጽሐፍ ቅዱስ ባሕርይ ነው እንድንተረጉመው የሚያስገድደን፡፡


ይቀጥላል...


ምንጭ:- www.ewnetlehulu.org




ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
10🥰2👍1
Spiritual Leadership
Nigusse Denano
#መጻሕፍትን_በድምጽ

📔ርዕስ፦ መንፈሳዊ መሪ
👤ጸሐፊ፦ J.Oswald Sanders
👉ክፍል-10


ይቀጥላል...


ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
2
.       ──•◈•─────•◈•─
                          የዕለቱ ጥቅስ
        ──•◈•─────•◈•─
“ያልወለደችውን እንደምታቅፍ ቆቅ፥ እንዲሁ በቅን ሳይሆን ባለጠግነትን የሚሰበስብ ሰው ነው፤ በእኩሌታ ዘመኑ ይተወዋል፥ በፍጻሜውም ሰነፍ ይሆናል።”
ኤርምያስ 17፥11



ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
3👍3