ቅዱሳት መጻሕፍት
7.45K subscribers
1.36K photos
61 videos
332 files
806 links
በዚህ ቻናል

👉ቅዱሳት መጻሕፍት ይጠናሉ::
👉መጽሐፍ ቅዱሳዊ ትምህርቶች ይቀርባሉ::
👉 ለቅዱሳት መጽሐፍት ጥናት የሚያግዙ መጻሕፍት ይለቀቃሉ።

⭐️⭐️⭐️⭐️⭐️

@Holy_scriptures
Download Telegram
.       ──•◈•─────•◈•─
                          የዕለቱ ጥቅስ
        ──•◈•─────•◈•─
“ታዳጊህ፥ የእስራኤል ቅዱስ፥ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ እኔ የሚረባህን ነገር የማስተምርህ በምትሄድባትም መንገድ የምመራህ አምላክህ እግዚአብሔር ነኝ።”
ኢሳይያስ 48፥17



ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
21🙏2
Spiritual Leadership
Nigusse Denano
#መጻሕፍትን_በድምጽ

📔ርዕስ፦ መንፈሳዊ መሪ
👤ጸሐፊ፦ J.Oswald Sanders
👉ክፍል-3


ይቀጥላል...


ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
1
ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
2
Watchman Nee.pdf
1.1 MB
ርዕስ፦ ከእምነት ወደ እምነት
ጸሐፊ፦ ዎችማን ኒ


ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
👎4
.       ──•◈•─────•◈•─
                          የዕለቱ ጥቅስ
        ──•◈•─────•◈•─
“ሕይወትና ቸርነት አደረግህልኝ፤ መጐብኘትህም መንፈሴን ጠበቀች።”
ኢዮብ 10፥12


ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
10
Spiritual Leadership
Nigusse Denano
#መጻሕፍትን_በድምጽ

📔ርዕስ፦ መንፈሳዊ መሪ
👤ጸሐፊ፦ J.Oswald Sanders
👉ክፍል-4


ይቀጥላል...


ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
2
ራስህን አድን!



         ክፍል-1

"ለራስህና ለትምህርትህ ተጠንቀቅ፣ በእነዚህም ጽና፣ ይህን ብታደርግ ራስህንም የሚሰሙህንም ታድናለህና" የሚለውና በ1ኛ ጢሞ.4፥16 ላይ የተመሠረተው የፊኒ ስብከት እንደሚከተለው ነው። “አነሣሴ ሰባኪዎችን ለመስበክ አይደለም። ይልቁንስ በመነሻ ንባቡ ላይ ቃል የተገባውን ደኅንነት በእርግጠኝነት ይጨብጡት ዘንድ አንዳንድ ነጥቦችን ለማመላከት ነው” በማለት የጀመረው ታላቁ ወንጌላዊ ቻርልስ ፊኒ መልእክቱን በተራ ቁጥሮች በመደርደር እንዲህ አስቀምጧቸዋል።

1) ወንጌልን የምትሰብከው ልክ እንደ ክርስቶስ ፍቅር ግድ ብሎህ እንደሆነ እርግጠኛ ሁን።

2) ኃይል እንደወረደብህ በመንፈስ ቅዱስም እንደተጠመቅህ አረጋግጥ። 

3) ወንጌልን መስበክ ወደአእምሮህ ሽው ያለ አሳብ ሳይሆን ውስጥህን የሞላ ነገር መሆኑን እርግጠኛ ሁን። ይህንን ስል የሌሎች መዳን ልብህን የሞላ በጽኑ ምኞትም የተደገፈ ይሁን ማለቴ ነው። ልብህ ያላረፈበትን አታድርግ።

4) ከእግዚአብሔር ጋር ተጣብቀህ መራመድን አታቋርጥ።

5) መጽሐፍ ቅዱስ ቁጥር አንድ መጽሐፍህ ይሁን። መለኮታዊውን ብርሃን እየተጠባበቅህ ተንበርክከህና አብዝተህ አጥናው።

6)ማብራሪያዎችን ስታጠና ተጠንቀቅ። እንደ አመቺነቱ አንብባቸው። ግን የራስህን ሚዛህ በመንፈስ ቅዱስ ብርሃን ጠብቅ።

7)ስትናገርም ይሁን ስትሠራ ፍቃድህን፤ አሳብና ድርጊትህን በንጽሕና ጠብቅ።

8) ይድኑ ዘንድ ያለህ ፍላጎት እንዲበረታ ኃጢአተኞች የሚጋፈጡት አደጋና ፀፀት ከአሳብህ አይጥፋ።

9) ደግሞም ክርስቶስ ለኃጢአተኞች ያለውን ገደብ የለሽ ርኅራኄና ፍቅር አሰላስል።

10) ስለዚህ አንተም ልትሞትላቸው እስከመፍቀድ ድረስ ውደዳቸው።

11) መላ አስተሳሰብህን ሰዎችን እንዴት ማዳን እንደምትችል ለማሰላሰል አውለው።  ትልቁና የምታተኩርበት የጥናትህ ክፍልም ይሄ ይሁን።

12)ከጽኑ መሻትህ ሊጎትትህ ከሚሞክር ማንኛውም ፈተና ራስህን ጠብቅ። ከዚህ ተልዕኮ አሳብህ እንዲነሣ ከቶም አትፍቀድ።

13) ለዚህ ሥራ በሚያስፈልግህ ሁሉ ይረዳህ ዘንድ ክርስቶስ ሁልጊዜና በሁሉም ሥፍራ አብሮህ እንዳለ ጽኑ እምነት ይኑርህ።

14)"ነፍሶችንም የሚሰበስብ እርሱ ጠቢብ ነው" (ምሳ11፥30)። "ከእናንተ ግን ማንም ጥበብ ቢጎድለው፥ ሳይነቅፍ በልግስና ለሁሉ የሚሰጠውን እግዚአብሔርን ይለምን፥ ለእርሱም ይሰጠዋል"(ያዕ1፥5) ተብሎ ተጽፎአል። ስለሆነም ይህን አስታውስ። ነፍሳትን ለክርስቶስ ማሸነፍ የሚያስችል ጥበብ ይኑርህ።

15) በእግዚአብሔር ለሥራው ከተጠራህ ከእርሱ ጋር የምትሟገተው ለስኬታማነት የሚያስፈልግህን ሁሉ ታገኝ ዘንድ ይሁን።

16)  በጊዜውም ያለጊዜውም (2 ጢሞ.4፥2) ጠንቃቃና ትጉ ሁን። 



ይቀጥላል.....


ምንጭ:- alemayehuwrites.blogspot.com



ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
13
.       ──•◈•─────•◈•─
                          የዕለቱ ጥቅስ
        ──•◈•─────•◈•─
“እኔም የዘላለም ሕይወትን እሰጣቸዋለሁ፥ ለዘላለምም አይጠፉም፥ ከእጄም ማንም አይነጥቃቸውም።”
ዮሐንስ 10፥28



ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
8
Spiritual Leadrship
Nigusse Denano
#መጻሕፍትን_በድምጽ

📔ርዕስ፦ መንፈሳዊ መሪ
👤ጸሐፊ፦ J.Oswald Sanders
👉ክፍል-5


ይቀጥላል...


ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
2
ራስህን አድን!


ክፍል ሁለት  



17) አሳባቸውን፣ ስሕተታቸውንና ፍላጎታቸውን ለመረዳት ትችል ዘንድ ስለመዳን ባላቸው ጥያቄ ላይ ከሁሉም ዓይነት አድማጮችህ ጋር አብዝተህ ተነጋገር። ትምህርትህን ከነርሱ ፍላጎት ጋር ለማዛመድ ትችል ዘንድ አመለካከታቸውንና ስሜታቸውን አጢን። ልማዶቻቸውን ልብ በል። ምን እንደተጋረደባቸውም አስተውል። ማወቅ የሚገባህን ሁሉ እወቅ።

18) ሥራዬ ብለህ የምታደርጋቸው ሁሉ ትክክል መሆናቸውን አያያዝህም ርጋታ ያለተለየው መሆኑን:አጢን። ከትንባሆ፤ የአልኮል መጠጥና አደንዛዥ ዕፆች ሌሎችም አንተን ሊያሳፍሩ ሌሎችንም ሊያሰናክሉ ከሚችሉ ነገሮች እድፍና ጠረን ነፃ መሆንህን ርግጠኛ ሁን።

19) ቁርጠኝነት አይጉደልህ፤ ነገር ግን ሁልጊዜ እግዚአብሔርን አስቀድም (መዝ. 16:8)።

20) ለአንደበትህ ልጓም አብጅለት፤ ለከንቱና ዋጋ ቢስ ንግግር ራስህን አሳልፈህ አትስጥ።

21) መድረክ ላይ ስትወጣም ይሁን ከዚያ ስትወርድ ቁርጠኛና እርግጠኛ መሆንህንሰዎች ይረዱት። ከእነርሱ ጋር ያለህ የዕለት ተዕለት ግንኙነት በሰንበት ቀን የምታቀርበውን ወሳኝ ትምህርት ዋጋ ቢስ አያድርገው።

22) ከተሰቀለው ኢየሱስ ክርስቶስ በቀር ሌላ እንደማታውቅ ለሚቀርቡህ ሁሉ ይታወቅ። በክርስቶስ አምባሣደርነትህ ከእነርሱ ጋር ያለህ ሕብረት ስለነፍሳቸው መዳን ብቻ መሆኑን ይረዱት።     

23) መሆን አለበት:ብለህ የምታስተምረውን በምሳሌነት አሳይ። የምትሰብከውን ኑር።

24) ያልሆነ አሳብ ወይም ጥርጣሬ እንዳያስከትልና ንጽሕናህን እንዳይነካ በተለይ ከሴቶች ጋር ስለሚኖርህ ግንኙነት ተጠንቀቅ።

25) ደካማ ጎኖችህን ተከላከል። አላስፈላጊ ወደሆነ ነገርም ይሁን ርካሽ ፈንጠዝያ ፍለጋ  ወደዚያ አቅጣጫ ከሚያዘሙህ አጋጣሚዎች ተጠንቀቅ።

26) በተፈጥሮህ ኮስታራ ወይም ገለልተኛ  ከሆንክ መራራና ሰዎችን የማትቀርብ ሆነህ እንዳትቆጠር ተጠንቀቅ።

27) የሰውን ጆሮ ለማግኘት ብቻ የሚደረግን ጥረትና ካባ የለበሰ ውሸትን አስወግድ። ያኔ የማስመሰል ድርጊት ለመፈጸም አትፈተንም።

28) ጽናት፣ እውነተኝነትና ክርስቲያናዊ ባለቤትነት የሁለንተናዊ ኑሮህ መለያ ይሁኑ።

29) በቀንም ይሁን በማታ ሁልጊዜ ለጸሎትና ከእግዚአብሔር ጋር ሕብረት ለማድረግ ብዙ ጊዜ ውሰድ። ይህም ለማዳን ብዙ ኃይል ይሆንልሃል። የዚህን ሕብረት መታጣት ግን የትኛውም ዓይነት ትምህርት ይሁን ጥናት ሊያካካሰው አይችልም። ከእግዚአብሔር ጋር ሕብረት ከሌለህ እንደማንኛውም ሰው ደካማ ነህ።

30) ዳግም ልደት የለም የሚለውንና ያንንም ተከትሎ የነፍሳትን መዳን የሚጠራጠረውን ስሕተት አስወግድ።

31) ዳግም ልደት የሞራልና ይልቁንም የፍቃደኝነት ለውጥ መሆኑን ልብ በል።

32) ወንጌል የሰዎችን ልብ መለወጥ እንደሚችል ሆኖ ተዘጋጅቷል። ያንን በጥበብ ስትሰብከው ደግሞ ከመንፈስ ቅዱስ ውጤታማ እገዛ እንደምታገኝ ጠብቅ።


ይቀጥላል.....


ምንጭ:- alemayehuwrites.blogspot.com



ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
7👏1
.       ──•◈•─────•◈•─
                          የዕለቱ ጥቅስ
        ──•◈•─────•◈•─
“የዚያን ጊዜ እግዚአብሔርን የሚፈሩ እርስ በእርሳቸው ተነጋገሩ፤ እግዚአብሔርም አደመጠ፥ ሰማም፥ እግዚአብሔርንም ለሚፈሩ ስሙንም ለሚያስቡ የመታሰቢያ መጽሐፍ በፊቱ ተጻፈ።”
ሚልክያስ 3፥16




ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
❤‍🔥111
Spiritual Leadrship
Nigusse Denano
#መጻሕፍትን_በድምጽ

📔ርዕስ፦ መንፈሳዊ መሪ
👤ጸሐፊ፦ J.Oswald Sanders
👉ክፍል-6


ይቀጥላል...


ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
2
#እራሳችንን_እንመርምር


“አቤቱ፥ ፍጻሜዬን አስታውቀኝ፥ የዘመኔ ቍጥሮች ምን ያህል እንደ ሆኑ፥ እኔ ምን ያህል ወደ ኋላ እንደምቀር አውቅ ዘንድ።”
መዝሙር 39፥4

“እግዚአብሔር ሆይ፤ የሕይወቴን ፍጻሜ፣ የዘመኔንም ቍጥር አስታውቀኝ፤ አላፊ ጠፊ መሆኑንም ልረዳ።”
መዝሙር 39፥4 (አዲሱ መ.ት)

እግዚአብሔር ሆይ ፥ የሕይወቴ ፍጻሜ መቼ እንደ ሆነና የዕድሜዬ ልክ ስንት እንደ ሆነ ግለጽልኝ፤ በዚህ ዓለም የምኖረው ዘመን ፈጥኖ የሚያልፍ መሆኑን ለማወቅ አስችለኝ።"
መዝሙር 39፥4 (ሕያው ቃል)



ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
8👏4
.       ──•◈•─────•◈•─
                          የዕለቱ ጥቅስ
        ──•◈•─────•◈•─
“አካሄድን እንደ ቃልህ አቅና፤ ኃጢአትም ሁሉ አይግዛኝ።”
መዝሙር 119፥133



ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
7👏1
እንደሚታወቀው ከፈረንጆቹ October 1-31 የተሐድሶ ወር በመባል በሉተራዊያን ዘንድ ወር በሙሉ ስለተሐድሶ ይወሳል፣ ውይይት ይደረጋል ይዘከራልም። ይህን በማስመልከት እኛም ይህን ወር በልዩ ሁኔታ ለማስታወስ በተለያዩ ትምህርቶች፣ ውይይቶች፣ እጅግ ለየት ያሉ ፕሮግራሞችን አዘጋጅተን ጨርሰናል። በቅርብ ቀን በዚህ ቻናል ብቻ ይጠብቁን

#ተሐድሶ
#reformation


ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️👉 @TME_bible_study
👍93👏3
Spiritual Leadership
Nigusse Denano
#መጻሕፍትን_በድምጽ

📔ርዕስ፦ መንፈሳዊ መሪ
👤ጸሐፊ፦ J.Oswald Sanders
👉ክፍል-7


ይቀጥላል...


ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
👍54👎1
ራስህን አድን!


         ክፍል ሦስት  


33) ዐውድህን ስትመርጥና ስታዘጋጅ በመንፈስ ቅዱስ ለሚመጣው ትምህርት ሁነኛ ቦታ ስጠው።

34) ስብከቶችህ  ከልብ የመነጩ እንጂ  የጭንቅላት እውቀት አይሁኑ።

35) ጥልቀት በሌለው ንባብና ጥናት ወይም በሰሚ ሰሚ ሳይሆን የተለማመድከውን ስበክ።

36) ሁሌም መንፈስ ቅዱስ ልብህ ላይ የሚያስቀምጠውን የወቅቱን ቃል አቅርብ። እርሱ የሚያቀብልህን ነጥቦች አጥብቀህ ያዝና በተቻለህ መጠን በቀጥታ ለጉባዔው አድርስ።

37) ሁሌም ልትሰብክ ስትነሣ ከጓዳህ በጸሎት ተሞልተህ መንፈስ ቅዱስ በውስጥህ እየቃተተና በከንፈሮችህም ሊናገር እየፈለገ ሳለ ወደ መድረኩ ዝለቅ።

38) አፍህን ስትከፍት ንግግርህ ይፈጥንና እንደጎርፍ ይወርድ ዘንድ አእምሮህ በርዕሰ ጉዳይህ ላይ እንዲነሣሣ አድርግ።

39) ወጥመድን የሚያመጣው ሰውን መፍራት (ምሳ.29:25) በአንተ ላይ አይኑር። እግዚአብሔርን እጅግ ከመፍራትህ የተነሣ ሰዎችን መፍራት እንደማይሆንልህ ሰሚዎችህ ይወቁ።

40) የምትሰብካቸው ሰዎች ስላንተ ያላቸው ዕውቀት በስብከትህ ላይ ተፅዕኖ እንዲያሳድር አትፍቀድ።

41) የቀለብ ጥያቄ “ሰዎች ቢሰሙትም ባይሰሙትም የእግዚአብሔርን እውነት ከማወጅ” አይከልክልህ።

42) በሕዝብህ ዘንድ ያለህን መታመን ስለሚያሳጣህና እንዳይድኑም ስለሚያደርግ አታመንታ። እንደ ክርስቶስ አምባሣደር ተልዕኮህን የመወጣት ቁርጠኝነት ካላዩብህ እንደሚገባ  አያከብሩህም።

43) እውነትን በመግለጥ ግን በእግዚአብሔር ፊትና ለሰው ሕሊና ሁሉ ራስህን ብቁ አድርገህ ማቅረብን አትርሳ (2 ቆሮ.4:2)።

44)  “ያለልክ ገንዘብ ወዳድ” አትሁን።

45)  ከንቱ የሆነ አቀራረብን አስወግድ።

46) እውነተኛነትና መንፈሳዊ ጥበብህን እንዲያከብሩ ገፋፋቸው።

47)  አፍታም እንኳ ቢሆን የሚሰፈርልህ ቀለብ በጥቂቱም ይሁን ሙሉ በሙሉ ስብከትህን ያስቀይራል ብለው እንዳያስቡ አድርግ።


ይቀጥላል.....


ምንጭ:- alemayehuwrites.blogspot.com




ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
11
ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
4
ሚዛን_የጠበቀ_ሕይወት_እና_አገልግሎት.pdf
1.5 MB
👉ርዕስ፦ ሚዛን የጠበቀ ሕይወት እና አገልግሎት
👤ጸሐፊ፦ ከበደ በከሬ
📑የገጽ ብዛት፦ 166


ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
.       ──•◈•─────•◈•─
                          የዕለቱ ጥቅስ
        ──•◈•─────•◈•─
“ኃጢአት አይገዛችሁምና፤ ከጸጋ በታች እንጂ ከሕግ በታች አይደላችሁምና።”
ሮሜ 6፥14



ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
15