ቅዱሳት መጻሕፍት
7.45K subscribers
1.36K photos
61 videos
332 files
806 links
በዚህ ቻናል

👉ቅዱሳት መጻሕፍት ይጠናሉ::
👉መጽሐፍ ቅዱሳዊ ትምህርቶች ይቀርባሉ::
👉 ለቅዱሳት መጽሐፍት ጥናት የሚያግዙ መጻሕፍት ይለቀቃሉ።

⭐️⭐️⭐️⭐️⭐️

@Holy_scriptures
Download Telegram
#መጻሕፍትን_በድምጽ

በቀጣይ

ርዕስ፦ መንፈሳዊ መሪ
ጸሐፊ፦ J.Oswald Sanders
ተርጓሚ፦ ተስፋዬ መስፍን


ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
👍7
.       ──•◈•─────•◈•─
                          የዕለቱ ጥቅስ
        ──•◈•─────•◈•─
“ሰው ሁሉ በእሳት ይቀመማልና፥ መሥዋዕትም ሁሉ በጨው ይቀመማል።”
ማርቆስ 9፥49



ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
7
#ከተማ_ወይም_ቦታ_በቅዱሳት_መጻሕፍት


#አንጾኪያ

1. የሶርያ አንጾኪያ 301 ከክርስቶስ ልደት በፊት በአሮንቴስ ወንዝ የተቋቋመች ከተማ ናት። 65 ከክርስቶስ ልደት በፊት የሮም መንግሥት የሶሪያ መናገሻ ከተማ አደረጋት። ትልቅም ከተማ ሆነች። የመጀመሪያዋ የአሕዛብ ቤ.ክ. እዚያ ተመሠረተች፤ ሐ.ሥ. 11፥19-26። ጳውሎስና በርናባስ እዚያ ወንጌልን አስተማሩ፤ ሐሥ 15፥35። ጳውሎስና ጓደኞቹ ለሦስቱ የስብከተ ወንጌል ጕዞ ከአንጾኪያ ቤ.ክ. ተላኩ፤ ሐ.ሥ.13፥1-4፤ 15፥35-41፤ 18፥22:23። ስለ አሕዛብ መገረዝ በተነሣው ክርክር ምክንያት እነጳውሎስ ከአንጾኪያ ወደ ኢየሩሳሌም ተላኩ፤ ሐ.ሥ. 15።

2. በጲስድያ ተራራማ አገር አጠገብ ያለች አንጾኪያ በትንሹ እስያ ክፍለ አገር የምትገኝ ከተማ። በመጀመሪያ ጕዞው ጳውሎስ ከበርናባስ ጋር በአንጾኪያ ወንጌልን አስተማረ፤ ሐ.ሥ. 13፥14-14፥19። በሁለተኛና በሦስተኛ ጕዞውም አንጾኪያን ሳይጐበኛት አልቀረም፤ ሐ.ሥ. 16፥6፤ 18፥22-23። ዛሬ አንጾኪያ ባድማ ሆናለች።



ምንጭ፦ የመጽሐፍ ቅዱስ መዝገበ ቃላት፤ ገጽ 156




ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
❤‍🔥53👏1
.       ──•◈•─────•◈•─
                          የዕለቱ ጥቅስ
        ──•◈•─────•◈•─
“ለባሪያህ ከሠራኸው ከምሕረትህና ከእውነትህም ሁሉ ትንሽ ስንኳ የማይገባኝ ነኝ፤ በትሬን ብቻ ይዤ ይህን ዮርዳኖስን ተሻግሬ ነበርና፥ አሁን ግን የሁለት ክፍል ሠራዊት ሆንሁ።”
ዘፍጥረት 32፥10



ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
7🔥1
Spiritual Leadership
Nigusse Denano
#መጻሕፍትን_በድምጽ

📔ርዕስ፦ መንፈሳዊ መሪ
👤ጸሐፊ፦ J.Oswald Sanders
👉ክፍል-1


ይቀጥላል...


ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
2
#የእግዚአብሔር_ቃል_ምን_ይላል?


ማቴዎስ 4
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
¹⁸ በገሊላ ባሕር አጠገብ ሲመላለስም ሁለት ወንድማማች ጴጥሮስ የሚሉትን ስምዖንን ወንድሙንም እንድርያስን መረባቸውን ወደ ባሕር ሲጥሉ አየ፥ ዓሣ አጥማጆች ነበሩና።
¹⁹ እርሱም፦ በኋላዬ ኑና ሰዎችን አጥማጆች እንድትሆኑ አደርጋችኋለሁ አላቸው።
²⁰ ወዲያውም መረባቸውን ትተው ተከተሉት።
²¹ ከዚያም እልፍ ብሎ ሌሎችን ሁለት ወንድማማች የዘብዴዎስን ልጅ ያዕቆብን ወንድሙንም ዮሐንስን ከአባታቸው ከዘብዴዎስ ጋር በታንኳ መረባቸውን ሲያበጁ አየ፤ ጠራቸውም።
²² እነርሱም ወዲያው ታንኳይቱንና አባታቸውን ትተው ተከተሉት።



ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
7
.       ──•◈•─────•◈•─
                          የዕለቱ ጥቅስ
        ──•◈•─────•◈•─
“ጻድቅ ግን መንገዱን ያጠነክራል፥ እጁም ንጹሕ የሆነ ሰው ኃይልን እየጨመረ ይሄዳል።”
ኢዮብ 17፥9



ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
8
የድመት እና የውሻ ነገረ መለኮት (Cat and Dog Theology)



ውሻው ባለቤቱን በማሞካሸት እንዲህ ይላል፦ "እርሱ ይመግበኛል፣ ይንከባከበኛል፣ይወደኛል፣ መጠለያ ሆኖኛል...ስለዚህ በእርግጥ እርሱ አምላክ ነው" አለ።

ድመት በተራዋ፦ "እርሱ ይመግበኛል፣ ይንከባከበኛል፣ይወደኛል፣ መጠለያ ሆኖኛል...ስለዚህ እንዲህ የሚያደርገኝ አምላክ ስለሆንኩ ነው" አለች።

ድመትና ውሻ ነገረ መለኮት እንዴት ይኖራቸዋል የሚል አይጠፋም። ነገሩ ወዲህ ነው። በድመትና በውሻ ተመሰለ እንጂ የብዙ አማኞች አስተሳሰብ እንደዚህ ነው።

በውሻ የተመሠለው አማኝ፦ "እግዚአብሔርን ማገልገል እና ደስ ማሰኘት እሻለው። እርሱን ምን ደስ ያሰኘው ይሆን?" ይላል።

በድመት የተመሠለው አማኝ፦ "እግዚአብሔር እኔን ያገለግለኛል። እርሱ እኔን መባረክ ይፈልጋል። ከእግዚአብሔር ምን አገኝ ይሆን?" ይላል።

የሁለቱ አይነት አማኞች ንጽጽር (መጀመሪያ የውሻው ከዚያም የድመት)


ጌታው ወደ ሄደበት ሁሉ ይከተለዋል።
ጌታውን ጥሩ ሲሰማው እና ጥቅሙ ያልተነካበት ሲመስለው ብቻ ይከተለዋል።

እግዚአብሔርን አምላክ ስለሆነ ያመልከዋል። እግዚአብሔርን የሚያመልከው ጥሩ ሲሰማው እና መልካም ካደረገለት ብቻ ነው።

የጌታውን ፈቃድ ይከተላል።
የእርሱ ምኞት የጌታ ፈቃድ ማዕከል እንደሆነ ያስባል።

ጸሎት ከእግዚአብሔር ጋር ኅብረት የሚያደርግበትና ከእርሱ የሚሰማበት መንገድ እንደሆነ ከዚያም በተረፈ ለሌሎች የሚማለድበት እንደሆነ ይገነዘባል።

ጸሎት ከእግዚአብሔር የሆነ ነገር የሚቀበልበት፣ ለወዳጆቹ ወይም ለእርሱ ከሆነ ችግር መውጫ እግዚአብሔር መፍትሄ እንዲያመጣ የሚጠየቅበት ነው።



ምንጭ፦ "Bob Sjogren and Gerald Robison, Cat and Dog Theology" መጽሐፍ ማጠቃለያ የተወሰደ




ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️👉 @TME_bible_study
8
.       ──•◈•─────•◈•─
                          የዕለቱ ጥቅስ
        ──•◈•─────•◈•─
“ነገር ግን ቃሉን የሚማር ከሚያስተምረው ጋር መልካምን ነገር ሁሉ ይከፋፈል።”
ገላትያ 6፥6


ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
12
#እራሳችንን_እንመርምር

ጌታችን ማን ነው?

“ለሁለት ጌቶች መገዛት የሚቻለው ማንም የለም፤ ወይም አንዱን ይጠላል ሁለተኛውንም ይወዳል፤ ወይም ወደ አንዱ ይጠጋል ሁለተኛውንም ይንቃል፤ ለእግዚአብሔርና ለገንዘብ መገዛት አትችሉም።”
ማቴዎስ 6፥24


ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
8👍3
.       ──•◈•─────•◈•─
                          የዕለቱ ጥቅስ
        ──•◈•─────•◈•─
“የእምነትህም ኅብረት፥ በእኛ ዘንድ ያለውን በጎ ነገር ሁሉ በማወቅ፥ ለክርስቶስ ኢየሱስ ፍሬ እንዲያፈራ እለምናለሁ፤”
ፊልሞና 1፥6



ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
11
Spiritual Leadrship
Nigusse Denano
#መጻሕፍትን_በድምጽ

📔ርዕስ፦ መንፈሳዊ መሪ
👤ጸሐፊ፦ J.Oswald Sanders
👉ክፍል-2


ይቀጥላል...


ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
👍31🔥1
.       ──•◈•─────•◈•─
                          የዕለቱ ጥቅስ
        ──•◈•─────•◈•─
“ነገር ግን መናፍስት ስለ ተገዙላችሁ በዚህ ደስ አይበላችሁ፥ ስማችሁ ግን በሰማያት ስለ ተጻፈ ደስ ይበላችሁ።”
ሉቃስ 10፥20



ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
11👍6
#ከተማ_ወይም_ቦታ_በቅዱሳት_መጻሕፍት

#ኬብሮን

ኅብረት ማለት ነው። ከኢየሩሳሌም በስተደቡብ 30 ኪ.ሜ. ርቆ ያለ የከነዓናውያን ከተማ። አስቀድሞ ቂርያት አርባቅ ይባል ነበር፤ ኢያሱ 14፥15። ኬብሮን ከባሕሩ ጠለል 927 ሜትር ከፍ ይላል። ከኢየሩሳሌምና ከሌሎች የከነዓን ከተማዎች ከፍታ አለው። አብርሃም በኬብሮን ሰፈረ (ዘፍ. 13፥18)፥ የመቃብርም ቦታ በኬብሮን ገዛ፤ አብርሃምና ሣራ ይስሐቅና ርብቃ፥ ያዕቆብና ልያ በኬብሮን ተቀበሩ፤ ዘፍ. 23፤ 49፥31፤ 50፥13። ዛሬ በመቃብሮቹ ላይ መስጊድ ተሠርቷል። የእስልምና ተከታዮች ቦታውን ይጠብቃሉ። ኢያሱ ኬብሮንን ለካሌብ ሰጠ፤ ኢያሱ 14፥6-15። ኬብሮን ለ7 ዓመት የዳዊት መናገሻ ከተማ ነበረ፤ 2ሳሙ. 5፥5። አቤሴሎም በኬብሮን ተወለደ፥ በዚያም በዳዊት ላይ ዐመፀ፤ 2ሳሙ. 15፥10።


ምንጭ፦ የመጽሐፍ ቅዱስ መዝገበ ቃላት፣ ገጽ 193




ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
4👍2
.       ──•◈•─────•◈•─
                          የዕለቱ ጥቅስ
        ──•◈•─────•◈•─
“ታዳጊህ፥ የእስራኤል ቅዱስ፥ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ እኔ የሚረባህን ነገር የማስተምርህ በምትሄድባትም መንገድ የምመራህ አምላክህ እግዚአብሔር ነኝ።”
ኢሳይያስ 48፥17



ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
21🙏2
Spiritual Leadership
Nigusse Denano
#መጻሕፍትን_በድምጽ

📔ርዕስ፦ መንፈሳዊ መሪ
👤ጸሐፊ፦ J.Oswald Sanders
👉ክፍል-3


ይቀጥላል...


ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
1
ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
2
Watchman Nee.pdf
1.1 MB
ርዕስ፦ ከእምነት ወደ እምነት
ጸሐፊ፦ ዎችማን ኒ


ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
👎4
.       ──•◈•─────•◈•─
                          የዕለቱ ጥቅስ
        ──•◈•─────•◈•─
“ሕይወትና ቸርነት አደረግህልኝ፤ መጐብኘትህም መንፈሴን ጠበቀች።”
ኢዮብ 10፥12


ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
10
Spiritual Leadership
Nigusse Denano
#መጻሕፍትን_በድምጽ

📔ርዕስ፦ መንፈሳዊ መሪ
👤ጸሐፊ፦ J.Oswald Sanders
👉ክፍል-4


ይቀጥላል...


ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
2
ራስህን አድን!



         ክፍል-1

"ለራስህና ለትምህርትህ ተጠንቀቅ፣ በእነዚህም ጽና፣ ይህን ብታደርግ ራስህንም የሚሰሙህንም ታድናለህና" የሚለውና በ1ኛ ጢሞ.4፥16 ላይ የተመሠረተው የፊኒ ስብከት እንደሚከተለው ነው። “አነሣሴ ሰባኪዎችን ለመስበክ አይደለም። ይልቁንስ በመነሻ ንባቡ ላይ ቃል የተገባውን ደኅንነት በእርግጠኝነት ይጨብጡት ዘንድ አንዳንድ ነጥቦችን ለማመላከት ነው” በማለት የጀመረው ታላቁ ወንጌላዊ ቻርልስ ፊኒ መልእክቱን በተራ ቁጥሮች በመደርደር እንዲህ አስቀምጧቸዋል።

1) ወንጌልን የምትሰብከው ልክ እንደ ክርስቶስ ፍቅር ግድ ብሎህ እንደሆነ እርግጠኛ ሁን።

2) ኃይል እንደወረደብህ በመንፈስ ቅዱስም እንደተጠመቅህ አረጋግጥ። 

3) ወንጌልን መስበክ ወደአእምሮህ ሽው ያለ አሳብ ሳይሆን ውስጥህን የሞላ ነገር መሆኑን እርግጠኛ ሁን። ይህንን ስል የሌሎች መዳን ልብህን የሞላ በጽኑ ምኞትም የተደገፈ ይሁን ማለቴ ነው። ልብህ ያላረፈበትን አታድርግ።

4) ከእግዚአብሔር ጋር ተጣብቀህ መራመድን አታቋርጥ።

5) መጽሐፍ ቅዱስ ቁጥር አንድ መጽሐፍህ ይሁን። መለኮታዊውን ብርሃን እየተጠባበቅህ ተንበርክከህና አብዝተህ አጥናው።

6)ማብራሪያዎችን ስታጠና ተጠንቀቅ። እንደ አመቺነቱ አንብባቸው። ግን የራስህን ሚዛህ በመንፈስ ቅዱስ ብርሃን ጠብቅ።

7)ስትናገርም ይሁን ስትሠራ ፍቃድህን፤ አሳብና ድርጊትህን በንጽሕና ጠብቅ።

8) ይድኑ ዘንድ ያለህ ፍላጎት እንዲበረታ ኃጢአተኞች የሚጋፈጡት አደጋና ፀፀት ከአሳብህ አይጥፋ።

9) ደግሞም ክርስቶስ ለኃጢአተኞች ያለውን ገደብ የለሽ ርኅራኄና ፍቅር አሰላስል።

10) ስለዚህ አንተም ልትሞትላቸው እስከመፍቀድ ድረስ ውደዳቸው።

11) መላ አስተሳሰብህን ሰዎችን እንዴት ማዳን እንደምትችል ለማሰላሰል አውለው።  ትልቁና የምታተኩርበት የጥናትህ ክፍልም ይሄ ይሁን።

12)ከጽኑ መሻትህ ሊጎትትህ ከሚሞክር ማንኛውም ፈተና ራስህን ጠብቅ። ከዚህ ተልዕኮ አሳብህ እንዲነሣ ከቶም አትፍቀድ።

13) ለዚህ ሥራ በሚያስፈልግህ ሁሉ ይረዳህ ዘንድ ክርስቶስ ሁልጊዜና በሁሉም ሥፍራ አብሮህ እንዳለ ጽኑ እምነት ይኑርህ።

14)"ነፍሶችንም የሚሰበስብ እርሱ ጠቢብ ነው" (ምሳ11፥30)። "ከእናንተ ግን ማንም ጥበብ ቢጎድለው፥ ሳይነቅፍ በልግስና ለሁሉ የሚሰጠውን እግዚአብሔርን ይለምን፥ ለእርሱም ይሰጠዋል"(ያዕ1፥5) ተብሎ ተጽፎአል። ስለሆነም ይህን አስታውስ። ነፍሳትን ለክርስቶስ ማሸነፍ የሚያስችል ጥበብ ይኑርህ።

15) በእግዚአብሔር ለሥራው ከተጠራህ ከእርሱ ጋር የምትሟገተው ለስኬታማነት የሚያስፈልግህን ሁሉ ታገኝ ዘንድ ይሁን።

16)  በጊዜውም ያለጊዜውም (2 ጢሞ.4፥2) ጠንቃቃና ትጉ ሁን። 



ይቀጥላል.....


ምንጭ:- alemayehuwrites.blogspot.com



ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
13