ቅዱሳት መጻሕፍት
7.45K subscribers
1.36K photos
61 videos
332 files
806 links
በዚህ ቻናል

👉ቅዱሳት መጻሕፍት ይጠናሉ::
👉መጽሐፍ ቅዱሳዊ ትምህርቶች ይቀርባሉ::
👉 ለቅዱሳት መጽሐፍት ጥናት የሚያግዙ መጻሕፍት ይለቀቃሉ።

⭐️⭐️⭐️⭐️⭐️

@Holy_scriptures
Download Telegram
የአጥር ላይ ተጓዥ


ድንገት ስናወራ ስለ አንድ ሰውዬ
ባህሪውን ሳወራ “አቋም የለሽ” ብዬ
“አጥር ላይ ተጓዥ ነው” አለኝ ጓደኛዬ።
ገርሞኝ ንግግሩ አብራራልኝ ስለው
የአቋም የለሹን ሰው እቅዱን ገለጠው።
የሚያዋጣውን አይቶ ወደ አንዱ ይዘላል
ወይ ግቢ ወይ ውጪ አይቶ ይወረወራል።
ብሎ ቢገልጥልኝ የአጥሩን ላይ ኗሪ
ትዝ አለኝ ብዙ ሰው በየ አጥሩ አዳሪ።
የአጥር ላይ ኗሪዎች ወደ አንዱ ዝለሉ
ወይ “ልክ አይደለንም” ወይ “ልክ ነን” በሉ።
ለሁሉ አትሳቁ ወይ ኣንዱን ተቆጡ
ሁሉን አትደባብሱ አንዳንዴም ቆንጥጡ።
አጥር ላጥር ጉዞ እድሜ እስኪሟጠጥ
በጣም ያሳፍራል ለምግብ ለመጠጥ።
ወዳንዱ ሳይወስን አጥር ላይ ለኖረ
አጥሩ ላይ ሰብኮ እዛው ለዘመረ
ምን ይሆን ክፍያው እያልኩ ሳሰላስል
ያ ሮቤል ትዝ አለኝ እንደ ውሀ ሚዋልል።
እውነትም አጥር ላይ የከረመ ዘዋሪ
አይሆንም አለቃ ቆራጥ ጀግና መሪ
ምክንያቱም ውሳኔ ስለሌለው ልቡ
ወደ አጥሩ ይወጣል ሲጮህበት ህዝቡ።
እርሶ የቱ ጋ ኖት እባኮት አስቡ?
ለማን እጅ አጠፉ ለማ አጨበጨቡ?
እንደ አስቆሮቱ ሁለት አይውደዱ
ሳይደወልቦት ከአጥርዎ ይውረዱ።

ጥቅምት 18 2004



ምንጭ፦ ደረጀ ሙላቱ፤ ይዳኘን መጽሐፉ፤ ገጽ 86



ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️👉 @TME_bible_study
11🔥3🙏3
መጽሐፈ መክብብ The Book of Ecclesiastes
BibleProject - Amharic / አማርኛ
👉ርዕስ፦ መጽሐፈ መክብብ
በባይብል ፕሮጀክት፣ በአማርኛ ቋንቋ የተዘጋጀ


ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
2
.       ──•◈•─────•◈•─
                          የዕለቱ ጥቅስ
        ──•◈•─────•◈•─
“የምዋቹን ሞት አልፈቅድምና፥ ይላል ጌታ እግዚአብሔር፤ ስለዚህ ተመለሱና በሕይወት ኑሩ።”
ሕዝቅኤል 18፥32



ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
11🔥1
.       ──•◈•─────•◈•─
                          የዕለቱ ጥቅስ
        ──•◈•─────•◈•─
“የምድርም አሥራት፥ ወይም የምድር ዘር ወይም የዛፍ ፍሬ ቢሆን፥ የእግዚአብሔር ነው ለእግዚአብሔር የተቀደሰ ነው።”
ዘሌዋውያን 27፥30



ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
5🔥3🙏2
#እራሳችንን_እንመርምር

“አንተ እንድትበልጥ ማን አድርጎሃል? ያልተቀበልኸውስ ምን አለህ? የተቀበልህ ከሆንህ ግን እንዳልተቀበልህ የምትመካ ስለ ምንድር ነው?”
1ኛ ቆሮንቶስ 4፥7



ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
5
.       ──•◈•─────•◈•─
                          የዕለቱ ጥቅስ
        ──•◈•─────•◈•─
“እርሱ ከእግዚአብሔር ዘንድ በረከትን ከመድኃኒቱ አምላክም ምሕረትን ይቀበላል።”
መዝሙር 24፥5



ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
11
መንፈሳዊ ዲሲፕሊንና በረከቱ



ይህ ጹሑፍ የሚያተኩረው ምሳ 2፥1-2 ላይ ሲሆን ሙሉ ምዕራፍ ቢነበብ ደግሞ መልካም ነው፡፡በዚህ ምእራፍ ላይ ምሳ 2፥6 እንደ መግቢያ ሆኖ ሊያገለግል ይችላል ብዬ አስባለሁ፡፡ቃሉ አንዲህ ይነበባል፡- ‹‹እግዚአብሄር ጥበብን ይሰጣልና ከአፉም እውቀትና ማስተዋል ይወጣሉ›› ከዚህ ቃል ጋር ኢሳ 55፥10-11 ተመሳሳይነት አለውና ያንቡት፡፡እጅግ መልካም የሆነ የተስፋ ቃል ነው ነገር ግን መጠየቅ ያለብን እንዴት ነው ጥበብንና ማስተዋልን የምንቀበለው የሚለውን ነው፡፡ መንገዶቹ በጥቅሉ ሶስት፡-

👉ከቃሉ ጋር ጠበቅ ያለ ህብረትና ግንኙነት ሲኖረን
👉የጌታን ፊት በጸሎት አጥብቀን ስንፈልግ
👉ቃሉን በህይወታችን በተግባር ስንፈጽም

እነዚህን ከላይ የተጠቀሱትን ሶስት መንገዶች በሚገባ ደጋግመን ስናደርግ መንፈሳዊ ማስተዋላችንና መረዳታችን እየጨመረ ስለሚሄድ ወደ ህይወታችን የሚመጣው እድገትና ለውጥ ቀላል አይሆንም፡፡

ምሳ 2፥1-4 ላይ ቃሉ በህይወታችን መውሰድ ስለሚገባን ወሳኝ እርምጃዎችና የምንከፍላቸውን ዋጋዎች ያሳየናል፡፡እነዚህንም በዝርዝር ስንመለከት ፡-

👉ቃሉን ብትቀበል
👉ጆሮህ ጥበብን ብታደምጥ
👉ልብህን ወደ ማስተዋል ብታዘነብል
👉በአንተ ዘንድ ሸሽገህ ብትይዛት
👉ረቂቅ እውቀትን ብትጠራት
👉ለማስተዋል ድምጽህን ብታነሳ
👉እንደ ብር ብትፈላልጋት
👉እንደ ተቀበረ ገንዘብ ብትሻት

እነዚህ ከላ ያሉት ስምንት ትእዛዞች በሁለት ሊጠቃለሉ ይችላሉ፡-

1ኛ፡-ከቃሉ ጋር የጠበቀ ቁርኝትና ጥናት

2ኛ፡-ከቃል ጥናቱ ጋር አብሮ የሚሄድ የጠበቀ ጸሎት

የእግዚአብሄር ቃል መርህ እንደሚያስተምረን ፡-ትእዛዝ -----------›በረከት

የእግዚአብሄር ቃል ትእዛዝንና በረከትን አጣምሮ የያዘ ነው፤ስለዚህ ትእዛዞቹን ሳናደርግ የቃሉ በረከት ወደ ህይወታችን አይመጣም፡፡ከላይ ያሉትን ስምንት ተግባሮች በህይወታችን ስንለማመድ ወደ ህይወታችን የሚመጡትን በረከቶች እንይ፡-

👉በዚያን ጊዜ እግዚአብሄርን መፍራት ታውቃለህ

የአምላክህን እውቀት ታገኛለህ/አምላክን በግል በሚገባ ታውቀዋለህ (በእንግሊዝኛው ‹‹you will gain knowledge of God>>)

👉መለኮታዊ ጥበቃው በህይወትህ ይበዛል

👉ነፍስህ በመንፈሳዊ ደስታ ትጥለቀለቃለች

👉ጽድቅንና ፍርድን መልካም መንገድን ታስተውላለህ (discernment)

👉በደጋግ ሰዎች መንገድ ትሄዳለህ(success)

በተግባር ደረጃ የቃሉ ብርሀን በህይወታችን ሲበዛና እንደ ቃሉ ስንኖር ከሶስት ትልልቅ ጥፋቶች እንድናለን፡-

1ኛ፡-ከክፉ መንገድ  እናመልጣለን  (ወደ ስድስት ጥፋቶች ከቁጥር 12 እስከ 15 ተዘርዝረዋል)

2ኛ፡-በቀጥታ ከዝሙት (sexual sins) እና ከሚያመጣብን ጥፋት እንድናለን

3ኛ፡-ክፉ ከሆነውና ወደ ጥፋት ከሚወስደው የአለም አሰራር እናመልጣለን

ስለዚህ ለቃሉ ያልተከፋፈለ ልብን እንስጥ፤ ፊቱን ሳናሰልስ እንፈልግ፤ አድርጉ የሚለንም ለማድረግ እንጨክን !



ምንጭ :- belacheb6.blogspot.com




ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
15
.       ──•◈•─────•◈•─
                          የዕለቱ ጥቅስ
        ──•◈•─────•◈•─
“ጴጥሮስ ግን እንዲህ አለው፦ የእግዚአብሔርን ስጦታ በገንዘብ እንድታገኝ አስበሃልና ብርህ ከአንተ ጋር ይጥፋ።”
ሐዋርያት 8፥20



ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
4
ቅዱሳት መጻሕፍት
#እምነት                  ክፍል-15 በጎ ሕሊናን ማግኘት እንዴት ይቻላል? ሀ. በኢየሱስ ክርስቶስ አምኖ በመዳን በጎ ሕሊና የሚጀምረው በዳግም ልደት ነው። ሕሊናችንን ከጥፋተኝነት የሚያነጻው የኢየሱስ ደም ብቻ ነው። “ነውር የሌለው ሆኖ በዘላለም መንፈስ ራሱን ለእግዚአብሔር ያቀረበ የክርስቶስ ደም እንዴት ይልቅ ሕያውን እግዚአብሔርን ልታመልኩ ከሞተ ሥራ ሕሊናችሁን ያነጻ ይሆን?”…
#እምነት


                 ክፍል-16


በየእለቱ በጎ ህሊናችንን ይዘን ለመቆየት ምን ማድረግ አለብን?

👉በእግዚአብሔር ቃል ላይ ሥር መስደድ (መዝሙር 119፥11)
👉ማስተዋልን እና ትሕትናን ለማግኘት መጸለይ (ፊልጵስዩስ 1፥9-11)
👉ዘወትር ኃጢአትን መናዘዝ እና ልባችን እንዲነጻ እግዚአብሔርን መለመን (መዝሙረ ዳዊት 51፥10)
👉ከአማኞች ጋር ኅብረት ማድረግ (ዕብ 10፥24-25)
👉እግዚአብሔርን በመፍራት መኖር (ምሳሌ 1፥7)
👉ሕሊናን ከሚያረክሰው የድፍረት ኃጢአት መራቅ (ቲቶ 1፥15)

በአገልግሎትና በሕይወት በጎ ሕሊና አስፈላጊ የሆነው ለምንድን ነው?

👉እግዚአብሔርን በትክክል እንድናመልከው ይረዳናል (ዕብ 10፥22)
👉በፈተና እንዳንወድቅ ይጠብቀናል (1ኛ ጢሞቴዎስ 1፥19)
👉በሌሎች ፊት በድፍረት እንድንመሰክር ያስችለናል (የሐዋርያት ሥራ 24፥16)
👉ውስጣዊ ሰላማችንን ይጠብቅልናል (ፊልጵስዩስ 4፥7)
👉መንፈሳዊ እድገታችንንና እና ጤናማ አስተምህሮአችንን ይጠብቅልናል (1 ጢሞቴዎስ 1፥5)

ይቀጥላል. . .



ምንጭ፦


MacArthur, J. (2001). The MacArthur Study Bible. Thomas Nelson.

Grudem, W. (1994). Systematic Theology: An Introduction to Biblical Doctrine. Inter-Varsity Press.

Elwell, W. A., & Beitzel, B. J. (1988). Baker Encyclopedia of the Bible. Baker Book House.




ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
3👍1
.       ──•◈•─────•◈•─
                          የዕለቱ ጥቅስ
        ──•◈•─────•◈•─
“ታንኳዎችንም ወደ ምድር አድርሰው ሁሉን ትተው ተከተሉት።”
ሉቃስ 5፥11



ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
6
"በእውነት ሃይማኖት በእግሮቻችንና ቅልጥሞቻችን ውስጥ ያለውን ያህል በልባችንና በነፍሳችን ውስጥ ቢኖር ዓለምን ይቀይር ነበር::"
     #ማርቲን_ሉተር_ኪንግ



ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
7👍1💯1
#መጻሕፍትን_በድምጽ

በቀጣይ

ርዕስ፦ መንፈሳዊ መሪ
ጸሐፊ፦ J.Oswald Sanders
ተርጓሚ፦ ተስፋዬ መስፍን


ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
👍7
.       ──•◈•─────•◈•─
                          የዕለቱ ጥቅስ
        ──•◈•─────•◈•─
“ሰው ሁሉ በእሳት ይቀመማልና፥ መሥዋዕትም ሁሉ በጨው ይቀመማል።”
ማርቆስ 9፥49



ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
7
#ከተማ_ወይም_ቦታ_በቅዱሳት_መጻሕፍት


#አንጾኪያ

1. የሶርያ አንጾኪያ 301 ከክርስቶስ ልደት በፊት በአሮንቴስ ወንዝ የተቋቋመች ከተማ ናት። 65 ከክርስቶስ ልደት በፊት የሮም መንግሥት የሶሪያ መናገሻ ከተማ አደረጋት። ትልቅም ከተማ ሆነች። የመጀመሪያዋ የአሕዛብ ቤ.ክ. እዚያ ተመሠረተች፤ ሐ.ሥ. 11፥19-26። ጳውሎስና በርናባስ እዚያ ወንጌልን አስተማሩ፤ ሐሥ 15፥35። ጳውሎስና ጓደኞቹ ለሦስቱ የስብከተ ወንጌል ጕዞ ከአንጾኪያ ቤ.ክ. ተላኩ፤ ሐ.ሥ.13፥1-4፤ 15፥35-41፤ 18፥22:23። ስለ አሕዛብ መገረዝ በተነሣው ክርክር ምክንያት እነጳውሎስ ከአንጾኪያ ወደ ኢየሩሳሌም ተላኩ፤ ሐ.ሥ. 15።

2. በጲስድያ ተራራማ አገር አጠገብ ያለች አንጾኪያ በትንሹ እስያ ክፍለ አገር የምትገኝ ከተማ። በመጀመሪያ ጕዞው ጳውሎስ ከበርናባስ ጋር በአንጾኪያ ወንጌልን አስተማረ፤ ሐ.ሥ. 13፥14-14፥19። በሁለተኛና በሦስተኛ ጕዞውም አንጾኪያን ሳይጐበኛት አልቀረም፤ ሐ.ሥ. 16፥6፤ 18፥22-23። ዛሬ አንጾኪያ ባድማ ሆናለች።



ምንጭ፦ የመጽሐፍ ቅዱስ መዝገበ ቃላት፤ ገጽ 156




ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
❤‍🔥53👏1
.       ──•◈•─────•◈•─
                          የዕለቱ ጥቅስ
        ──•◈•─────•◈•─
“ለባሪያህ ከሠራኸው ከምሕረትህና ከእውነትህም ሁሉ ትንሽ ስንኳ የማይገባኝ ነኝ፤ በትሬን ብቻ ይዤ ይህን ዮርዳኖስን ተሻግሬ ነበርና፥ አሁን ግን የሁለት ክፍል ሠራዊት ሆንሁ።”
ዘፍጥረት 32፥10



ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
7🔥1
Spiritual Leadership
Nigusse Denano
#መጻሕፍትን_በድምጽ

📔ርዕስ፦ መንፈሳዊ መሪ
👤ጸሐፊ፦ J.Oswald Sanders
👉ክፍል-1


ይቀጥላል...


ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
2
#የእግዚአብሔር_ቃል_ምን_ይላል?


ማቴዎስ 4
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
¹⁸ በገሊላ ባሕር አጠገብ ሲመላለስም ሁለት ወንድማማች ጴጥሮስ የሚሉትን ስምዖንን ወንድሙንም እንድርያስን መረባቸውን ወደ ባሕር ሲጥሉ አየ፥ ዓሣ አጥማጆች ነበሩና።
¹⁹ እርሱም፦ በኋላዬ ኑና ሰዎችን አጥማጆች እንድትሆኑ አደርጋችኋለሁ አላቸው።
²⁰ ወዲያውም መረባቸውን ትተው ተከተሉት።
²¹ ከዚያም እልፍ ብሎ ሌሎችን ሁለት ወንድማማች የዘብዴዎስን ልጅ ያዕቆብን ወንድሙንም ዮሐንስን ከአባታቸው ከዘብዴዎስ ጋር በታንኳ መረባቸውን ሲያበጁ አየ፤ ጠራቸውም።
²² እነርሱም ወዲያው ታንኳይቱንና አባታቸውን ትተው ተከተሉት።



ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
7
.       ──•◈•─────•◈•─
                          የዕለቱ ጥቅስ
        ──•◈•─────•◈•─
“ጻድቅ ግን መንገዱን ያጠነክራል፥ እጁም ንጹሕ የሆነ ሰው ኃይልን እየጨመረ ይሄዳል።”
ኢዮብ 17፥9



ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
8
የድመት እና የውሻ ነገረ መለኮት (Cat and Dog Theology)



ውሻው ባለቤቱን በማሞካሸት እንዲህ ይላል፦ "እርሱ ይመግበኛል፣ ይንከባከበኛል፣ይወደኛል፣ መጠለያ ሆኖኛል...ስለዚህ በእርግጥ እርሱ አምላክ ነው" አለ።

ድመት በተራዋ፦ "እርሱ ይመግበኛል፣ ይንከባከበኛል፣ይወደኛል፣ መጠለያ ሆኖኛል...ስለዚህ እንዲህ የሚያደርገኝ አምላክ ስለሆንኩ ነው" አለች።

ድመትና ውሻ ነገረ መለኮት እንዴት ይኖራቸዋል የሚል አይጠፋም። ነገሩ ወዲህ ነው። በድመትና በውሻ ተመሰለ እንጂ የብዙ አማኞች አስተሳሰብ እንደዚህ ነው።

በውሻ የተመሠለው አማኝ፦ "እግዚአብሔርን ማገልገል እና ደስ ማሰኘት እሻለው። እርሱን ምን ደስ ያሰኘው ይሆን?" ይላል።

በድመት የተመሠለው አማኝ፦ "እግዚአብሔር እኔን ያገለግለኛል። እርሱ እኔን መባረክ ይፈልጋል። ከእግዚአብሔር ምን አገኝ ይሆን?" ይላል።

የሁለቱ አይነት አማኞች ንጽጽር (መጀመሪያ የውሻው ከዚያም የድመት)


ጌታው ወደ ሄደበት ሁሉ ይከተለዋል።
ጌታውን ጥሩ ሲሰማው እና ጥቅሙ ያልተነካበት ሲመስለው ብቻ ይከተለዋል።

እግዚአብሔርን አምላክ ስለሆነ ያመልከዋል። እግዚአብሔርን የሚያመልከው ጥሩ ሲሰማው እና መልካም ካደረገለት ብቻ ነው።

የጌታውን ፈቃድ ይከተላል።
የእርሱ ምኞት የጌታ ፈቃድ ማዕከል እንደሆነ ያስባል።

ጸሎት ከእግዚአብሔር ጋር ኅብረት የሚያደርግበትና ከእርሱ የሚሰማበት መንገድ እንደሆነ ከዚያም በተረፈ ለሌሎች የሚማለድበት እንደሆነ ይገነዘባል።

ጸሎት ከእግዚአብሔር የሆነ ነገር የሚቀበልበት፣ ለወዳጆቹ ወይም ለእርሱ ከሆነ ችግር መውጫ እግዚአብሔር መፍትሄ እንዲያመጣ የሚጠየቅበት ነው።



ምንጭ፦ "Bob Sjogren and Gerald Robison, Cat and Dog Theology" መጽሐፍ ማጠቃለያ የተወሰደ




ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️👉 @TME_bible_study
8