ቅዱሳት መጻሕፍት
7.45K subscribers
1.36K photos
61 videos
332 files
806 links
በዚህ ቻናል

👉ቅዱሳት መጻሕፍት ይጠናሉ::
👉መጽሐፍ ቅዱሳዊ ትምህርቶች ይቀርባሉ::
👉 ለቅዱሳት መጽሐፍት ጥናት የሚያግዙ መጻሕፍት ይለቀቃሉ።

⭐️⭐️⭐️⭐️⭐️

@Holy_scriptures
Download Telegram
#የእግዚአብሔር_ቃል_ምን_ይላል?


መዝሙር 11
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
¹ በእግዚአብሔር ታመንሁ፤ ነፍሴን፦ እንደ ወፍ ወደ ተራሮች ተቅበዝበዢ እንዴት ትሉአታላችሁ?
² ኃጢአተኞች እነሆ ቀስታቸውን ገትረዋልና፥ ፍላጻቸውንም በአውታር አዘጋጅተዋልና፥ ልበ ቅኖችን በስውር ይነድፉ ዘንድ።
³ አንተ የሠራኸውን እነሆ እነርሱ አፍርሰዋልና፤ ጻድቅ ግን ምን አደረገ?
⁴ እግዚአብሔር በተቀደሰው መቅደሱ ነው፤ እግዚአብሔር፥ ዙፋኑ በሰማይ ነው፤ ዓይኖቹ ወደ ድሃ ይመለከታሉ፥ ቅንድቦቹም የሰው ልጆችን ይመረምራሉ።
⁵ እግዚአብሔር ጻድቅንና ኅጥእን ይመረምራል፤ ዓመፃን የወደዳት ግን ነፍሱን ጠልቶአል።
⁶ ወጥመድ በኅጥኣን ላይ ያዘንባል እሳትና ዲን ዐውሎ ነፋስም የጽዋቸው እድል ፈንታ ነው።
⁷ እግዚአብሔር ጻድቅ ነውና፥ ጽድቅንም ይወድዳል፤ ቅንነት ግን ፊቱን ታየዋለች።




ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
3
.       ──•◈•─────•◈•─
                          የዕለቱ ጥቅስ
        ──•◈•─────•◈•─
“ብቻ እግዚአብሔርን ፍሩ፥ ያደረገላችሁንም ታላቅ ነገር አይታችኋልና በፍጹም ልባችሁ በእውነት አምልኩት።”
1ኛ ሳሙኤል 12፥24



ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
8🔥3
ቅዱሳት መጻሕፍት
የቀጠለ... ⏱️ቢዚ - ቢዚ፤ ለሁሉ ጊዜ አለው ወይስ አለን?                                      በጋሽ ንጉሤ ቡልቻ ይረዳን እንደ ሆነ እስቲ መላ ልምታ፡፡ በጎ ትብብራችሁን ስጡኝና ይህን ጥያቄ በጥሞና መልሱልኝ “ለመሞት አንድ ወር ቀርቶሃል የምትሠራውን ሁሉ በነዚህ ሠላሳ ቀናት ጨርስ” ብትባሉ ቀኖቹንና ሌሊቶቹን ምን ታደርጉባቸው ነበር?   ብጣሽ ወረቀት አውጡና የምታደርጓቸውን…
የቀጠለ...

⏱️ቢዚ - ቢዚ፤ ለሁሉ ጊዜ አለው ወይስ አለን?



                                     በጋሽ ንጉሤ ቡልቻ


እነዚህን የጊዜ ሌቦች እንዴት ነቅተህ እንደምትጠብቅ ከራስህ ጋር ተመካከር፡፡
 
ሦስተኛው ርምጃ ለሕይወትህ ዓላማ መሳካት የሚረዳ ከአንተ ባህርይና ሁናቴ ጋር የሚጣጣም የጊዜ ሰሌዳ መንደፍ ነው፡፡ የጊዜ መርሃ ግብር እንደሚያወጡት ቀላልነት ሳያዛንፉ መከተሉ ቀላል አይደለም፡፡ ላወጣኸው የጊዜ ሰሌዳ መገዛት ቢያቅትህ እንደገና መከለስና ማሻሻል ምንም ነውር የለበትም፡፡
 
ይህን ሁሉ ስታደርግ ልብ ማለት የሚገባህ ሕይወት ሥራ ብቻ÷ የግል ኑሮ ብቻ እንዳይደለ መገንዘብ ነው፡፡ የሥራና የዕረፍትን ሚዛን፣ የግልና የማኅበር ኑሮን ሚዛን፣ የዕለቱንና የዘላለሙን ሚዛን የሚጠብቅ የሕይወት ስልት መቀየስ ሁሉ ጎናዊ ስምረት እንዲኖረን ይረዳል፡፡
 
ወገኖቼ ጤናችን እስኪዛባ ደስታችን እስኪጠፋ ቢዚ ከሆንን እየቆየ ወደ ክስመት (burn out) ልንሄድ እንችላለን፡፡ በእምነት እጦት ሰበብ ሩጫ ያበዙትን ሕዝበ እስራኤል እግዚአብሔር እንደገሰጻቸውና እንደመከራቸው እኛንም ያስጠነቅቀናል፡፡
 
“የእስራኤል ቅዱስ ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላልና በመመለስና በማረፍ ትድናላችሁ፣ በፀጥታና በመታመን ኃይል ይሆንላችኋል፡፡”
(ኢሳ 30፡15)

ቁምላቸው ፈንታሁን ወደ አማርኛ ተርጉሞት በቃለ እግዚአብሔር አንባቢዎች ማኅበር በኩል ከታተመው መጽሐፍ ይህን አስተዋይ ጸሎት ልብ እንድንለው አብረንም እንድንጸልየው እጋብዛለሁ፡፡
 
ሰከን አርገኝ ጌታ!
ለአእምሮዬ ፀጥታ ለግሰህ፣ የልቤን ድውድውታ ቀንሰው፡፡
በጊዜ ውስጥ የዘላለምን አፅናፍ ራእይ ስጠኝና ጥድፊያዬ ልጓም ይበጅለት፡፡
በቀናት ዑደት ቱማታና ግርግር መካከል፣
የዘላለም ዓለም ኮረብቶች ግርማዊ አርምሞ በኔ ላይ ያርብብ፡፡
የሠራ አካላቴ ውጥረት በትውስታዬ በሚኖሩ
ዘማሪ ጅረቶች የሚያሳርፍ ሙዚቃ ይርገብ፡፡
የእንቅልፍን አስማታዊ አዳሽ ኃይል እንድገነዘብ እርዳኝ፡፡
ጥበብን አካፍለኝና የደቂቃ እርፍቶች በየመካከሉ እየወሰድኩ፡-
አበቦችን ልመልከት፣ ከወዳጅ ጋር ልጫወት፣
በጫካው መካከል ልመላለስ፣ ሸረሪት ድሯን ስትሸምን ልያት
ህፃኗን በፈገግታ ልቀበላት፣ እንባዎቿንም ላብስላት፡፡
ሩጫ ሁልጊዜ ለፈጣኖች እንዳይደለ፣
የኑሮ ሁለንተና ፍጥነት እየጨመሩ መኖጥ እንዳይደለ በየዕለቱ አስታውሰኝ፡፡
ቀና ብዬ ደመኖቹንና ሰማዩን
እንዲሁም ያዘመመን ዛፍ ልመልከታቸው፣
ዛፉ ዛሬ ይህን አክሎ ያደረገው፣ የበረታው በሕይወት ሰጪ ፀሐይህ ሙቀት
በዝግታ በማደጉ መሆኑን ልገንዘብ፡፡
ሰከን አርገኝ ጌታ ከአንተ ጋር ኅብረት በማድረግ በጥልቅ እኔነቴ የሚያሹኝን ሰላምና እረፍት ልጎናጸፍ፡፡


ምንጭ :- semayawithought.com




ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
10
.       ──•◈•─────•◈•─
                          የዕለቱ ጥቅስ
        ──•◈•─────•◈•─
“በባልንጀራህ ግፍ አታድርግ፥ አትቀማውም። የሞያተኛው ዋጋ እስከ ነገ ድረስ በአንተ ዘንድ አይደርብህ።”
ዘሌዋውያን 19፥13



ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
4🙏2
ቅዱሳት መጻሕፍት
#እምነት                  ክፍል-14 የሕሊና ዓይነቶች  በቅዱሳት መጻሕፍት በተለይም በአዲስ ኪዳን ይባስ ብሎም ደግሞ በሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ ትምህርት "#ሕሊና" የሚለው አሳብ ተደጋግሞ ይነሳል። ለምሳሌ ሐዋርያው እንዲህ ይላል፦ “ስለዚህ እኔ ደግሞ በእግዚአብሔርና በሰው ፊት ሁልጊዜ ነውር የሌለባት ሕሊና ትኖረኝ ዘንድ እተጋለሁ።”            ሐዋርያት 24፥16 በአዲስ ኪዳን…
#እምነት


                 ክፍል-15


በጎ ሕሊናን ማግኘት እንዴት ይቻላል?

ሀ. በኢየሱስ ክርስቶስ አምኖ በመዳን

በጎ ሕሊና የሚጀምረው በዳግም ልደት ነው። ሕሊናችንን ከጥፋተኝነት የሚያነጻው የኢየሱስ ደም ብቻ ነው።

“ነውር የሌለው ሆኖ በዘላለም መንፈስ ራሱን ለእግዚአብሔር ያቀረበ የክርስቶስ ደም እንዴት ይልቅ ሕያውን እግዚአብሔርን ልታመልኩ ከሞተ ሥራ ሕሊናችሁን ያነጻ ይሆን?”
           ዕብራውያን 9፥14

መዳን ንጹህ ሕሊናን ያስከትላል። ከእንግዲህ በደለኛ ሳይሆን ሕሊናችን ይነጻል (ቲቶ 3፥5)።

ለ. የእግዚአብሔርን ቃል በመታዘዝ

የእግዚአብሔር ቃል ሕሊናን ያሠለጥናል፡-

“የእግዚአብሔር ሰው ፍጹምና ለበጎ ሥራ ሁሉ የተዘጋጀ ይሆን ዘንድ፥ የእግዚአብሔር መንፈስ ያለበት መጽሐፍ ሁሉ ለትምህርትና ለተግሣጽ ልብንም ለማቅናት በጽድቅም ላለው ምክር ደግሞ ይጠቅማል።”
           2ኛ ጢሞቴዎስ 3፥16-17

በጎ ሕሊና የሚዳበረው በስሜት ወይም በባሕል ሳይሆን በእውነተኛ መንፈስ በመኖር ነው።

ሐ.በንስሐና በመናዘዝ

ኃጢአት ስንሠራ ሕሊናችን ይረክሳል። መታደስ የሚመጣው በኑዛዜ ነው፡-

“በኃጢአታችን ብንናዘዝ ኃጢአታችንን ይቅር ሊለን ከዓመፃም ሁሉ ሊያነጻን የታመነና ጻድቅ ነው።”
         1ኛ ዮሐንስ 1፥9

መ. ግብዝነትን ማስወገድ

ጳውሎስ በ1ኛ ጢሞቴዎስ 4፥2 ላይ ስለ ደነዘዘ ሕሊና፦ በኃጢአት ወይም በሐሰት ትምህርት ስለደነዘዙ አስጠንቅቋል። በጎ ኅሊና ሐቀኛና ቅን እንጂ ግብዝነትን ያለው አይደለም።

ሠ. በክርስትና እና በመልካም ሥራ በመጽናት

“በክርስቶስ ያለውን መልካሙን ኑሮአችሁን የሚሳደቡ ሰዎች ክፉን እንደምታደርጉ በሚያሙበት ነገር እንዲያፍሩ በጎ ሕሊና ይኑራችሁ።”
        1ኛ ጴጥሮስ 3፥16


ይቀጥላል. . .



ምንጭ፦


MacArthur, J. (2001). The MacArthur Study Bible. Thomas Nelson.

Grudem, W. (1994). Systematic Theology: An Introduction to Biblical Doctrine. Inter-Varsity Press.

Elwell, W. A., & Beitzel, B. J. (1988). Baker Encyclopedia of the Bible. Baker Book House.




ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
3❤‍🔥1
“በማለዳ ምሕረትህን እንጠግባለን፤ በዘመናችን ሁሉ ደስ ይለናል ሐሤትም እናደርጋለን።”
መዝሙር 90፥14


“በዘመናችን ሁሉ ደስ እንዲለን፣ ሐሤትም እንድናደርግ፣ ምሕረትህን በማለዳ አጥግበን።”
መዝሙር 90፥14 (አዲሱ መ.ት)



ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
🥰92
.       ──•◈•─────•◈•─
                          የዕለቱ ጥቅስ
        ──•◈•─────•◈•─
“ስለ እነርሱም ሊያማልድ ዘወትር በሕይወት ይኖራልና ስለዚህ ደግሞ በእርሱ ወደ እግዚአብሔር የሚመጡትን ፈጽሞ ሊያድናቸው ይችላል።”
ዕብራውያን 7፥25



ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
9
የአጥር ላይ ተጓዥ


ድንገት ስናወራ ስለ አንድ ሰውዬ
ባህሪውን ሳወራ “አቋም የለሽ” ብዬ
“አጥር ላይ ተጓዥ ነው” አለኝ ጓደኛዬ።
ገርሞኝ ንግግሩ አብራራልኝ ስለው
የአቋም የለሹን ሰው እቅዱን ገለጠው።
የሚያዋጣውን አይቶ ወደ አንዱ ይዘላል
ወይ ግቢ ወይ ውጪ አይቶ ይወረወራል።
ብሎ ቢገልጥልኝ የአጥሩን ላይ ኗሪ
ትዝ አለኝ ብዙ ሰው በየ አጥሩ አዳሪ።
የአጥር ላይ ኗሪዎች ወደ አንዱ ዝለሉ
ወይ “ልክ አይደለንም” ወይ “ልክ ነን” በሉ።
ለሁሉ አትሳቁ ወይ ኣንዱን ተቆጡ
ሁሉን አትደባብሱ አንዳንዴም ቆንጥጡ።
አጥር ላጥር ጉዞ እድሜ እስኪሟጠጥ
በጣም ያሳፍራል ለምግብ ለመጠጥ።
ወዳንዱ ሳይወስን አጥር ላይ ለኖረ
አጥሩ ላይ ሰብኮ እዛው ለዘመረ
ምን ይሆን ክፍያው እያልኩ ሳሰላስል
ያ ሮቤል ትዝ አለኝ እንደ ውሀ ሚዋልል።
እውነትም አጥር ላይ የከረመ ዘዋሪ
አይሆንም አለቃ ቆራጥ ጀግና መሪ
ምክንያቱም ውሳኔ ስለሌለው ልቡ
ወደ አጥሩ ይወጣል ሲጮህበት ህዝቡ።
እርሶ የቱ ጋ ኖት እባኮት አስቡ?
ለማን እጅ አጠፉ ለማ አጨበጨቡ?
እንደ አስቆሮቱ ሁለት አይውደዱ
ሳይደወልቦት ከአጥርዎ ይውረዱ።

ጥቅምት 18 2004



ምንጭ፦ ደረጀ ሙላቱ፤ ይዳኘን መጽሐፉ፤ ገጽ 86



ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️👉 @TME_bible_study
11🔥3🙏3
መጽሐፈ መክብብ The Book of Ecclesiastes
BibleProject - Amharic / አማርኛ
👉ርዕስ፦ መጽሐፈ መክብብ
በባይብል ፕሮጀክት፣ በአማርኛ ቋንቋ የተዘጋጀ


ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
2
.       ──•◈•─────•◈•─
                          የዕለቱ ጥቅስ
        ──•◈•─────•◈•─
“የምዋቹን ሞት አልፈቅድምና፥ ይላል ጌታ እግዚአብሔር፤ ስለዚህ ተመለሱና በሕይወት ኑሩ።”
ሕዝቅኤል 18፥32



ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
11🔥1
.       ──•◈•─────•◈•─
                          የዕለቱ ጥቅስ
        ──•◈•─────•◈•─
“የምድርም አሥራት፥ ወይም የምድር ዘር ወይም የዛፍ ፍሬ ቢሆን፥ የእግዚአብሔር ነው ለእግዚአብሔር የተቀደሰ ነው።”
ዘሌዋውያን 27፥30



ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
5🔥3🙏2
#እራሳችንን_እንመርምር

“አንተ እንድትበልጥ ማን አድርጎሃል? ያልተቀበልኸውስ ምን አለህ? የተቀበልህ ከሆንህ ግን እንዳልተቀበልህ የምትመካ ስለ ምንድር ነው?”
1ኛ ቆሮንቶስ 4፥7



ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
5
.       ──•◈•─────•◈•─
                          የዕለቱ ጥቅስ
        ──•◈•─────•◈•─
“እርሱ ከእግዚአብሔር ዘንድ በረከትን ከመድኃኒቱ አምላክም ምሕረትን ይቀበላል።”
መዝሙር 24፥5



ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
11
መንፈሳዊ ዲሲፕሊንና በረከቱ



ይህ ጹሑፍ የሚያተኩረው ምሳ 2፥1-2 ላይ ሲሆን ሙሉ ምዕራፍ ቢነበብ ደግሞ መልካም ነው፡፡በዚህ ምእራፍ ላይ ምሳ 2፥6 እንደ መግቢያ ሆኖ ሊያገለግል ይችላል ብዬ አስባለሁ፡፡ቃሉ አንዲህ ይነበባል፡- ‹‹እግዚአብሄር ጥበብን ይሰጣልና ከአፉም እውቀትና ማስተዋል ይወጣሉ›› ከዚህ ቃል ጋር ኢሳ 55፥10-11 ተመሳሳይነት አለውና ያንቡት፡፡እጅግ መልካም የሆነ የተስፋ ቃል ነው ነገር ግን መጠየቅ ያለብን እንዴት ነው ጥበብንና ማስተዋልን የምንቀበለው የሚለውን ነው፡፡ መንገዶቹ በጥቅሉ ሶስት፡-

👉ከቃሉ ጋር ጠበቅ ያለ ህብረትና ግንኙነት ሲኖረን
👉የጌታን ፊት በጸሎት አጥብቀን ስንፈልግ
👉ቃሉን በህይወታችን በተግባር ስንፈጽም

እነዚህን ከላይ የተጠቀሱትን ሶስት መንገዶች በሚገባ ደጋግመን ስናደርግ መንፈሳዊ ማስተዋላችንና መረዳታችን እየጨመረ ስለሚሄድ ወደ ህይወታችን የሚመጣው እድገትና ለውጥ ቀላል አይሆንም፡፡

ምሳ 2፥1-4 ላይ ቃሉ በህይወታችን መውሰድ ስለሚገባን ወሳኝ እርምጃዎችና የምንከፍላቸውን ዋጋዎች ያሳየናል፡፡እነዚህንም በዝርዝር ስንመለከት ፡-

👉ቃሉን ብትቀበል
👉ጆሮህ ጥበብን ብታደምጥ
👉ልብህን ወደ ማስተዋል ብታዘነብል
👉በአንተ ዘንድ ሸሽገህ ብትይዛት
👉ረቂቅ እውቀትን ብትጠራት
👉ለማስተዋል ድምጽህን ብታነሳ
👉እንደ ብር ብትፈላልጋት
👉እንደ ተቀበረ ገንዘብ ብትሻት

እነዚህ ከላ ያሉት ስምንት ትእዛዞች በሁለት ሊጠቃለሉ ይችላሉ፡-

1ኛ፡-ከቃሉ ጋር የጠበቀ ቁርኝትና ጥናት

2ኛ፡-ከቃል ጥናቱ ጋር አብሮ የሚሄድ የጠበቀ ጸሎት

የእግዚአብሄር ቃል መርህ እንደሚያስተምረን ፡-ትእዛዝ -----------›በረከት

የእግዚአብሄር ቃል ትእዛዝንና በረከትን አጣምሮ የያዘ ነው፤ስለዚህ ትእዛዞቹን ሳናደርግ የቃሉ በረከት ወደ ህይወታችን አይመጣም፡፡ከላይ ያሉትን ስምንት ተግባሮች በህይወታችን ስንለማመድ ወደ ህይወታችን የሚመጡትን በረከቶች እንይ፡-

👉በዚያን ጊዜ እግዚአብሄርን መፍራት ታውቃለህ

የአምላክህን እውቀት ታገኛለህ/አምላክን በግል በሚገባ ታውቀዋለህ (በእንግሊዝኛው ‹‹you will gain knowledge of God>>)

👉መለኮታዊ ጥበቃው በህይወትህ ይበዛል

👉ነፍስህ በመንፈሳዊ ደስታ ትጥለቀለቃለች

👉ጽድቅንና ፍርድን መልካም መንገድን ታስተውላለህ (discernment)

👉በደጋግ ሰዎች መንገድ ትሄዳለህ(success)

በተግባር ደረጃ የቃሉ ብርሀን በህይወታችን ሲበዛና እንደ ቃሉ ስንኖር ከሶስት ትልልቅ ጥፋቶች እንድናለን፡-

1ኛ፡-ከክፉ መንገድ  እናመልጣለን  (ወደ ስድስት ጥፋቶች ከቁጥር 12 እስከ 15 ተዘርዝረዋል)

2ኛ፡-በቀጥታ ከዝሙት (sexual sins) እና ከሚያመጣብን ጥፋት እንድናለን

3ኛ፡-ክፉ ከሆነውና ወደ ጥፋት ከሚወስደው የአለም አሰራር እናመልጣለን

ስለዚህ ለቃሉ ያልተከፋፈለ ልብን እንስጥ፤ ፊቱን ሳናሰልስ እንፈልግ፤ አድርጉ የሚለንም ለማድረግ እንጨክን !



ምንጭ :- belacheb6.blogspot.com




ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
15
.       ──•◈•─────•◈•─
                          የዕለቱ ጥቅስ
        ──•◈•─────•◈•─
“ጴጥሮስ ግን እንዲህ አለው፦ የእግዚአብሔርን ስጦታ በገንዘብ እንድታገኝ አስበሃልና ብርህ ከአንተ ጋር ይጥፋ።”
ሐዋርያት 8፥20



ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
4
ቅዱሳት መጻሕፍት
#እምነት                  ክፍል-15 በጎ ሕሊናን ማግኘት እንዴት ይቻላል? ሀ. በኢየሱስ ክርስቶስ አምኖ በመዳን በጎ ሕሊና የሚጀምረው በዳግም ልደት ነው። ሕሊናችንን ከጥፋተኝነት የሚያነጻው የኢየሱስ ደም ብቻ ነው። “ነውር የሌለው ሆኖ በዘላለም መንፈስ ራሱን ለእግዚአብሔር ያቀረበ የክርስቶስ ደም እንዴት ይልቅ ሕያውን እግዚአብሔርን ልታመልኩ ከሞተ ሥራ ሕሊናችሁን ያነጻ ይሆን?”…
#እምነት


                 ክፍል-16


በየእለቱ በጎ ህሊናችንን ይዘን ለመቆየት ምን ማድረግ አለብን?

👉በእግዚአብሔር ቃል ላይ ሥር መስደድ (መዝሙር 119፥11)
👉ማስተዋልን እና ትሕትናን ለማግኘት መጸለይ (ፊልጵስዩስ 1፥9-11)
👉ዘወትር ኃጢአትን መናዘዝ እና ልባችን እንዲነጻ እግዚአብሔርን መለመን (መዝሙረ ዳዊት 51፥10)
👉ከአማኞች ጋር ኅብረት ማድረግ (ዕብ 10፥24-25)
👉እግዚአብሔርን በመፍራት መኖር (ምሳሌ 1፥7)
👉ሕሊናን ከሚያረክሰው የድፍረት ኃጢአት መራቅ (ቲቶ 1፥15)

በአገልግሎትና በሕይወት በጎ ሕሊና አስፈላጊ የሆነው ለምንድን ነው?

👉እግዚአብሔርን በትክክል እንድናመልከው ይረዳናል (ዕብ 10፥22)
👉በፈተና እንዳንወድቅ ይጠብቀናል (1ኛ ጢሞቴዎስ 1፥19)
👉በሌሎች ፊት በድፍረት እንድንመሰክር ያስችለናል (የሐዋርያት ሥራ 24፥16)
👉ውስጣዊ ሰላማችንን ይጠብቅልናል (ፊልጵስዩስ 4፥7)
👉መንፈሳዊ እድገታችንንና እና ጤናማ አስተምህሮአችንን ይጠብቅልናል (1 ጢሞቴዎስ 1፥5)

ይቀጥላል. . .



ምንጭ፦


MacArthur, J. (2001). The MacArthur Study Bible. Thomas Nelson.

Grudem, W. (1994). Systematic Theology: An Introduction to Biblical Doctrine. Inter-Varsity Press.

Elwell, W. A., & Beitzel, B. J. (1988). Baker Encyclopedia of the Bible. Baker Book House.




ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
3👍1
.       ──•◈•─────•◈•─
                          የዕለቱ ጥቅስ
        ──•◈•─────•◈•─
“ታንኳዎችንም ወደ ምድር አድርሰው ሁሉን ትተው ተከተሉት።”
ሉቃስ 5፥11



ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
6
"በእውነት ሃይማኖት በእግሮቻችንና ቅልጥሞቻችን ውስጥ ያለውን ያህል በልባችንና በነፍሳችን ውስጥ ቢኖር ዓለምን ይቀይር ነበር::"
     #ማርቲን_ሉተር_ኪንግ



ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
7👍1💯1
#መጻሕፍትን_በድምጽ

በቀጣይ

ርዕስ፦ መንፈሳዊ መሪ
ጸሐፊ፦ J.Oswald Sanders
ተርጓሚ፦ ተስፋዬ መስፍን


ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
👍7