ቅዱሳት መጻሕፍት
#እምነት ክፍል-13 እምነታችንን እንዴት ከጥፋት እንጠብቅ? “እምነትና በጎ ሕሊና ይኑርህ፥ አንዳንዶች ሕሊናን ጥለው፥ መርከብ አለ መሪ እንደሚጠፋ፥ በእምነት ነገር ጠፍተዋልና፤” 1ኛ ጢሞቴዎስ 1፥19 በዚህ ዐውደ-ጽሑፍ ውስጥ “እምነት” የሚያመለክተው ሙሉውን የክርስትና እምነት ነው ሁለቱም ማለትም በእግዚአብሔር እና በወንጌል መሠረታዊ እውነቶች…
#እምነት
ክፍል-14
የሕሊና ዓይነቶች
በቅዱሳት መጻሕፍት በተለይም በአዲስ ኪዳን ይባስ ብሎም ደግሞ በሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ ትምህርት "#ሕሊና" የሚለው አሳብ ተደጋግሞ ይነሳል። ለምሳሌ ሐዋርያው እንዲህ ይላል፦
“ስለዚህ እኔ ደግሞ በእግዚአብሔርና በሰው ፊት ሁልጊዜ ነውር የሌለባት ሕሊና ትኖረኝ ዘንድ እተጋለሁ።”
ሐዋርያት 24፥16
በአዲስ ኪዳን ሕሊና በተለያየ ሥፍራና ቦታ በተለያየ አውድ ተጠቅሷል። ከእነዚህ መካከል የሚከተሉትን እነሆ፦
1. ክፉ ሕሊና
ክፉ ሕሊና ተበላሽቶ ወደ ሥነ ምግባር ዝቅጠት የሚመራ ነው። ይህ ሕሊና የእግዚአብሔርን ፈቃድ የሚጻረር እና የኃጢያት ባህሪን የሚያበረታታ ነው። (ዕብ. 10፥22)
2. የረከሰ ሕሊና
የረከሰ ሕሊና በኃጢአት የረከሰና ግልጽ የሆነ የሞራል ልዩነት ማድረግ የማይችል ነው። ትክክል እና ስህተት መካከል ወደ ግራ መጋባት ይመራል። (ቲቶ. 1፥15)
3. የደነዘዘ ሕሊና
የደነዘዘ ሕሊና ማለት በድግግሞሽ ኃጢአት የተዳከመ ወይም የደነደነ ነው። ከጊዜ በኋላ
ሰውየው ለጥፋተኝነት ወይም ለጥፋተኝነት ግድየለሽ ይሆናል። ኃጢአትን እንደ ስህተት አይገነዘብም። (1ኛ ጢሞ. 4፥2)
4. ደካማ ሕሊና
ደካማ ሕሊና የሚያመለክተው ኃጢአት በሌለበት አካባቢም እንኳ በቀላሉ ሊኮነን የሚችል ያልበሰለ ወይም ከልክ ያለፈ ስስ ሕሊና ነው። ይህ ሊሆን የሚችለው አንድ ሰው በተፈጥሮ ኃጢአተኛ ያልሆኑ የሥነ ምግባር ጉዳዮች ላይ እርግጠኛ ካልሆነ ነው። (1ኛ ቆሮ. 8፥7)
5. ንጹሕ ሕሊና
ንፁህ ህሊና ማለት ከጥፋተኝነት እና ከነቀፋ በጸዳ መልኩ በእግዚአብሔርና በሰው ፊት መኖር ፣ በታማኝነት እና በመታዘዝ መመላለስ ማለት ነው። (ሐዋ. 24፥16)
6. በጎ ሕሊና
በጎ ሕሊና ከእግዚአብሔር እውነት ጋር የሚስማማ እና ወደ ጽድቅ ሕይወት የሚመራ ነው። ግለሰቡ ይቅርታን እንዲጠይቅ እና የሞራል ህይወት እንዲጠብቅ የሚገፋፋው ለኃጢያት እና የጥፋተኝነትን ድንበር በማወቅ ለእነዚህ ነገሮች ንቁ የሆነ ነው። (1 ጢሞ. 1፥19)
ይቀጥላል. . .
ወደ ቻናሉ ለመ🀄️ላ🀄️ል፦ @Holy_scriptures

❤8🔥4
. ──•◈•─────•◈•─
የዕለቱ ጥቅስ
──•◈•─────•◈•─
“የአባቶቻቸውም አምላክ እግዚአብሔር ለሕዝቡና ለማደሪያው ስላዘነ ማለዳ ተነሥቶ በመልእክተኞቹ እጅ ወደ እነርሱ ይልክ ነበር።”
2 ዜና 36፥15

❤4🔥3
የጸጋ መቀበያ መንገድ በሉተራን አስተምህሮ
ክፍል-1
በሉተራን አስተምህሮ፣ “የጸጋ መቀበያ መንገድ” የሚለው ቃል የሚያመለክተው በመለኮት የተመሰረተ እና የተቋቋመ እግዚአብሔር ጸጋን የሚሰጥበትን መንገዶችን ነው። እግዚአብሔር ጸጋውን የሚሰጠው የኃጢያት ይቅርታን፣ ህይወትን እና ድነትን ለሰው ለመስጠት ነው። እነዚህ ዘዴዎች ምሳሌያዊ ብቻ አይደሉም። ይልቁኑ በእግዚአብሔር ቃልና በተስፋው ቃል መሠረት ጸጋውን የምናገኝበት መንገድ ነው። በሉተራን ሥነ-መለኮት ሦስት ዋና የጸጋ መቀበያ መንገዶች አሉ፦
👉የእግዚአብሔር ቃል (በተለይም ወንጌል)
👉ቅዱስ ጥምቀት
👉የጌታ እራት (ቅዱስ ቁርባን)
በነገራችን ላይ ማርቲን ሉተር በመጀመሪያ ጽሑፎቹ እንደ መደበኛ ሥነ-መለኮታዊ ቃል “የጸጋ መቀበያ መንገድ” ("media gratiae" በላቲን ወይንም "Gnadenmittel በጀርመንኛ) ከሚለው ትክክለኛ የላቲን ወይም የጀርመንኛ አቻ ቃል አልተጠቀመም። ነገር ግን፣ የጸጋ መቀበያ መንገዶች ጽንሰ-ሀሳብ እና አስተምህሮ በስራው በሙሉ፣ በተለይም በቃሉ እና በቅዱስ ቁርባን አስተምህሮ ውስጥ በጥልቅ ተካተዋል። “የጸጋ መቀበያ መንገድ” የሚለው መደበኛ ቃል በሉተራን የሃይማኖት ምሁራን በተለይም በሉተራን ኦርቶዶክስ ዘመን (17ኛው ክፍለ ዘመን) በደንብ እያበበ መጣ። ይህ ሲባል ግን ይህ አገላለጽ በሉተር ሥነ-መለኮት ላይ የተመሠረተ አይደለም ማለት አይደለም።
1. የፅንሰ ሀሳቡ መሠረት በሉተር ፅሁፎች
ሉተር ሐረጉን የፈጠረው ላይሆን ይችላል፣ ግን ሐሳቡን በግልፅ አስቀምጧል፡-
“For God does not want to deal with us in any other way than through the spoken Word and the Sacraments. Whatever is attributed to the Spirit apart from such Word and Sacrament is of the devil”
ይቀጥላል...
ምንጭ፦
Kolb, R., & Wengert, T. J. (Eds.). (2000). The Book of Concord: The Confessions of the Evangelical Lutheran Church. Fortress Press.
Luther, M. (1537). Smalcald Articles. In Kolb, R., & Wengert, T. J. (Eds.), The Book of Concord (pp. 301–320). Fortress Press.
ወደ ቻናሉ ለመ🀄️ላ🀄️ል👉 @TME_bible_study

❤11🔥1
. ──•◈•─────•◈•─
የዕለቱ ጥቅስ
──•◈•─────•◈•─
“ከአንድ አፍ በረከትና መርገም ይወጣሉ። ወንድሞቼ ሆይ፥ ይህ እንዲህ ሊሆን አይገባም።”
ያዕቆብ 3፥10
ወደ ቻናሉ ለመ🀄️ላ🀄️ል፦ @Holy_scriptures
የዕለቱ ጥቅስ
──•◈•─────•◈•─
“ከአንድ አፍ በረከትና መርገም ይወጣሉ። ወንድሞቼ ሆይ፥ ይህ እንዲህ ሊሆን አይገባም።”
ያዕቆብ 3፥10
ወደ ቻናሉ ለመ🀄️ላ🀄️ል፦ @Holy_scriptures
👍3❤1👏1
#እራሳችንን_እንመርምር
እኔምለው አብዛኛዎቻችን እግዚአብሔርን ስለጽድቅ እና ፍትህ የምንወቅሰው በእውነት ገዶ ነው ወይስ እሱን እንደሰበብ ወስደን በአመጽ ለመቀጠል ነው?🤔 ፍትህንና ጽድቅ የሚፈልግ ሰው እራሱ በፍትህ መንገድ እየሄደ ቢጠይቅስ?
“እግዚአብሔርን በቃላችሁ አታክታችኋል። እናንተም፦ ያታከትነው በምንድር ነው? ብላችኋል። ክፉን የሚያደርግ ሁሉ በእግዚአብሔር ዘንድ መልካም ነው፥ እርሱም በእነርሱ ደስ ይለዋል፤ ወይስ፦ የፍርድ አምላክ ወዴት አለ? በማለታችሁ ነው።”
ሚልክያስ 2፥17

❤2
. ──•◈•─────•◈•─
የዕለቱ ጥቅስ
──•◈•─────•◈•─
“እግዚአብሔርም ከሩቅ ተገለጠልኝ እንዲህም አለኝ፦ በዘላለም ፍቅር ወድጄሻለሁ ስለዚህ በቸርነት ሳብሁሽ።”
ኤርምያስ 31፥3

❤10
ቅዱሳት መጻሕፍት
የቀጠለ... ⏱️ቢዚ - ቢዚ፤ ለሁሉ ጊዜ አለው ወይስ አለን? በጋሽ ንጉሤ ቡልቻ እንዴት እንደዚህ ስክን ያለ ሕይወትና አገልግሎት አገኘ? እጅግ ብዙ የእርሱን ርዳታ የሚሹ ፍጡራን ባሉበት ዓለም ውስጥ በቀኝና በግራ ሊያዋክቡት የሚችሉ አስባታሊ ተግባራት በነበሩበት ሁኔታ እንደምን ርጋታ አገኘ? መጽሐፉ ላይ እንደ ተጠቆምን ከሆነ መልሱ ውስብስብ…
የቀጠለ...
⏱️ቢዚ - ቢዚ፤ ለሁሉ ጊዜ አለው ወይስ አለን?
በጋሽ ንጉሤ ቡልቻ
ይረዳን እንደ ሆነ እስቲ መላ ልምታ፡፡ በጎ ትብብራችሁን ስጡኝና ይህን ጥያቄ በጥሞና መልሱልኝ “ለመሞት አንድ ወር ቀርቶሃል የምትሠራውን ሁሉ በነዚህ ሠላሳ ቀናት ጨርስ” ብትባሉ ቀኖቹንና ሌሊቶቹን ምን ታደርጉባቸው ነበር?
ብጣሽ ወረቀት አውጡና የምታደርጓቸውን ነገሮች በቅደም ተከተል ጻፉዋቸው፡፡ ልምምዱ ምናልባት ዋና የምትሉትን ዋና ካልሆኑት ለመለየት ይረዳችሁ ይሆናል፡፡
የሕይወታችሁ ዋና ዓላማ ምንድን ነው? የደም ግፊታችሁን እየጨመረ፣ ናላችሁን እያዞረ፣ ትንፋሽ አሳጥቶ የሚያስሮጣችሁን ነገር ሁሉ ከዚህ ዋና ዓላማ አንጻር ፈትሹት፡፡ ወደ ዓላማው የሚፈስ ነባር ወንዝ ነው ወይስ በየመስኩ የፈነዳ መድረሻው ያልታወቀ የውሃ ምንጭ? የክርስቶስ ተከታይ ዋና ዓላማ ምንድን ነው የተባለ እንደሆነ ሐዋርያው ጳውሎስ ባጭሩና በግልጽ ከተናገረው ከዚህ ጥቅስ የተሻለ መግለጫ አላገኘሁም፡፡ “አንዱ ስለ ሁሉ ሞተ፣ እንግዲያውስ ሁሉ ሞቱ በሕይወትም ያሉትም ስለ እነርሱ ለሞተውና ለተነሣው እንጂ ወደ ፊት ለራሳቸው እንዳይኖሩ ስለ ሁሉ ሞተ፡፡” 2ኛ ቆሮ 5፡13
የክርስቶስ ተከታይ ግለ ሰብም ሆነ ማኅበረ ሰብ የሕይወት ዓላማው ንድፍ ተሠርቶለት አልቋል፡፡ የምንሠራው ሁሉ የምናስበው ሁሉ የዚህ ዋና ንድፍ (Master Plan) አካል ካልሆነ ሕገ ወጥ ግንባታ ነው፤ ለፍቶ መና ነው፡፡ እያንዳንዱዋ የእንቅስቃሴ ቅንጣት መፈተሸ ዋጋዋም መተመን አለባት፡፡ መሮጥ ብቻውን ዋጋ ቢስ ነው፤ ሕይወት መሮጫ ግብ ይሻል፤ ግቡም በአንጻሩ የመገስገሻ መስመር አለው፡፡ ሐዋርያው ትንፋሽ ሊሰበስብ ሲቃረብ ሩጫ ጨረስኩ ሳይሆን ‹‹ሩጫውን ጨረስኩ›› ማለቱ የተሰመረ መንገድ፣ የሚደረስበት ግብ መኖሩን ሲያመለክተን ነው፡፡
የቢዚነት ጉዳይ ግን ከዓላማ አንጻር ብቻ ሳይሆን በጊዜ አስተዳደር አንጻርም ሊታይ ይገባል፡፡ ጊዜ ከፈጣሪ የተሰጠን ሀብት ነው፡፡ ጊዜ ሀብት ከሆነ እንግዲያው እያንዳንዳችን “መጋቤ ጊዜያት” ሆነን በዚህ ሀብት ላይ ተሹመናል፡፡ የጊዜ መጋቢነት እንዴት ይከወን ስንል ባለ ሙያዎች ከሚመክሩን መካከል ሦስቱን ብቻ ልጥቀስ፡-
ጊዜዬ የት ጠፋ? ምን አደረግሁት? እያልክ የምትጠይቅ ከሆነ ሥራዬ ብለህ የዕለት ዕለት እንቅስቃሴህን ለተከታታይ ሰባት ቀናት ያደረግከውን ነገር ስም እየሰጠህ ልትጽፈው ትችላለህ፡፡ ከሳምንቱ በኋላ የጊዜ አጠቃቀምህን በዐይነቱ ስትሰድረው ጊዜህ ምን ላይ እንደዋለ የጊዜ ምጋቤ ባህርይህን ትረዳዋለህ፡፡ ያኔ ያላግባብ የባከነ ወይም በቂ ጊዜ ያልተሰጠው ምን እንደሆነ ግልጽ ይሆናል፡፡
ይህ የጊዜ ውሎ ግምጋሜ ወደ ሁለተኛው ዋና ነገር ይመራሃል ይህም ጊዜህን የሚሰርቁ የጊዜ መንታፊዎቸን ለይቶ ማወቅ ነው፡፡ ከታወቁት የጊዜ መንታፊዎች መካከል፡-
👉መወላወል (የቱን ላንሳ የቱን ልጣል)
👉ዝርክርክነት (ካርዱን የት ነበር ያደረግኩት)
👉መግቻ የሌላቸው የስልክ ጥሪዎች
👉ነገ ይደርሳል እያሉ መሳነፍ
👉ተራ/ወረፋ ጥበቃ
👉ጥድፊያ (ጥድፊያ ሲበዛ ፍጥነት ይቀንሳል ይባላል)
👉ድንገት የሚከሰቱ መስተጓጉሎች ይገኙበታል፡፡
ይቀጥላል...
ምንጭ :- semayawithought.com

❤8
. ──•◈•─────•◈•─
የዕለቱ ጥቅስ
──•◈•─────•◈•─
“በእሳት ስለሚገለጥ ያ ቀን ያሳያልና፥ የእያንዳንዱም ሥራ እንዴት መሆኑን እሳቱ ይፈትነዋል።”
1ኛ ቆሮንቶስ 3፥13

❤3👍3🙏2
"በሥጋ ትንሣኤ"
በሐዋርያት የሃይማኖት መግለጫ ውስጥ ያለው “በሥጋ ትንሣኤ” የሚለው ሐረግ ብዙ ጊዜ ከሚያከራክሩ የሃይማኖት መግለጫው ክፍሎች ውስጥ አንዱ ነው። እሱም የሚያመለክተው በዘመኑ መጨረሻ ሙታን ሁሉ በአካል ይነሳሉ እና በክርስቶስ ያሉትም በታደሰ፣ በከበረ አካል ለዘላለም ይኖራሉ የሚለውን የክርስትና እምነት ነው።
የሥጋ ትንሣኤ ከሞት በኋላ ያለውን ሕይወት ብቻ ሳይሆን ከሞት በኋላ ካለው ሕይወት በኋላ ያለውን ሕይወት ያረጋግጣል። ይህ ሐረግ ከትንሣኤ በኋላ የንጹሕ መንፈሳዊ ወይም የአካል-አልባ ሕልውናን ሐሳብ ውድቅ ያደርጋል።
አማኞች በአዲስ ሰማይና አዲስ ምድር ከእግዚአብሔር ጋር ለዘለአለም ኅብረት ለማድረግ የሚሆን አዲስ፣ የከበረ፣ የማይበላሽ አካልን ይቀበላሉ (ራዕይ 21፥1-4)።
በቀደመችው ቤተክርስቲያን ይህ እምነት ክርስቲያኖችን ከግሪክ ፈላስፋዎች የሚለይ ሲሆን ግሪኮች አካልን እንደ እስር ቤት እና መዳን ከእሱ ለማምለጥ እንደ ጥሩ መንገድ አድርገው ይመለከቱ ነበር። ኖስቲኮች የአካልን ትንሣኤ አይቀበሉም ነበር ከሞት በኋላ መንፈስ ብቻ እንደሚኖር ያስተምሩ ነበር እናም የሐዋርያት የሃይማኖት መግለጫም ዓላማው ከዚህ ትምህርት ለመከላከል ነበር።
“የሙታን ትንሣኤ ደግሞ እንዲሁ ነው። በመበስበስ ይዘራል፥ ባለመበስበስ ይነሣል፤”
1ኛ ቆሮንቶስ 15፥42
“እርሱም ሁሉን እንኳ ለራሱ ሊያስገዛ እንደሚችልበት አሠራር፥ ክቡር ሥጋውን እንዲመስል የተዋረደውን ሥጋችንን ይለውጣል።”
ፊልጵስዩስ 3፥21
“ነገር ግን ኢየሱስን ከሙታን ያስነሣው የእርሱ መንፈስ በእናንተ ዘንድ ቢኖር፥ ክርስቶስ ኢየሱስን ከሙታን ያስነሣው እርሱ በእናንተ በሚኖረው በመንፈሱ፥ ለሚሞተው ሰውነታችሁ ደግሞ ሕይወትን ይሰጠዋል።”
ሮሜ 8፥11
ምንጭ፦
Wright, N. T. (2003). The resurrection of the Son of God. Fortress Press.
Grudem, W. (1994). Systematic theology: An introduction to biblical doctrine. Zondervan.
McGrath, A. E. (2011). Christian theology: An introduction (5th ed.). Wiley-Blackwell.

👍4❤3🔥3
#የእግዚአብሔር_ቃል_ምን_ይላል?
መዝሙር 11
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
¹ በእግዚአብሔር ታመንሁ፤ ነፍሴን፦ እንደ ወፍ ወደ ተራሮች ተቅበዝበዢ እንዴት ትሉአታላችሁ?
² ኃጢአተኞች እነሆ ቀስታቸውን ገትረዋልና፥ ፍላጻቸውንም በአውታር አዘጋጅተዋልና፥ ልበ ቅኖችን በስውር ይነድፉ ዘንድ።
³ አንተ የሠራኸውን እነሆ እነርሱ አፍርሰዋልና፤ ጻድቅ ግን ምን አደረገ?
⁴ እግዚአብሔር በተቀደሰው መቅደሱ ነው፤ እግዚአብሔር፥ ዙፋኑ በሰማይ ነው፤ ዓይኖቹ ወደ ድሃ ይመለከታሉ፥ ቅንድቦቹም የሰው ልጆችን ይመረምራሉ።
⁵ እግዚአብሔር ጻድቅንና ኅጥእን ይመረምራል፤ ዓመፃን የወደዳት ግን ነፍሱን ጠልቶአል።
⁶ ወጥመድ በኅጥኣን ላይ ያዘንባል እሳትና ዲን ዐውሎ ነፋስም የጽዋቸው እድል ፈንታ ነው።
⁷ እግዚአብሔር ጻድቅ ነውና፥ ጽድቅንም ይወድዳል፤ ቅንነት ግን ፊቱን ታየዋለች።

❤3
. ──•◈•─────•◈•─
የዕለቱ ጥቅስ
──•◈•─────•◈•─
“ብቻ እግዚአብሔርን ፍሩ፥ ያደረገላችሁንም ታላቅ ነገር አይታችኋልና በፍጹም ልባችሁ በእውነት አምልኩት።”
1ኛ ሳሙኤል 12፥24

❤8🔥3
ቅዱሳት መጻሕፍት
የቀጠለ... ⏱️ቢዚ - ቢዚ፤ ለሁሉ ጊዜ አለው ወይስ አለን? በጋሽ ንጉሤ ቡልቻ ይረዳን እንደ ሆነ እስቲ መላ ልምታ፡፡ በጎ ትብብራችሁን ስጡኝና ይህን ጥያቄ በጥሞና መልሱልኝ “ለመሞት አንድ ወር ቀርቶሃል የምትሠራውን ሁሉ በነዚህ ሠላሳ ቀናት ጨርስ” ብትባሉ ቀኖቹንና ሌሊቶቹን ምን ታደርጉባቸው ነበር? ብጣሽ ወረቀት አውጡና የምታደርጓቸውን…
የቀጠለ...
⏱️ቢዚ - ቢዚ፤ ለሁሉ ጊዜ አለው ወይስ አለን?
በጋሽ ንጉሤ ቡልቻ
እነዚህን የጊዜ ሌቦች እንዴት ነቅተህ እንደምትጠብቅ ከራስህ ጋር ተመካከር፡፡
ሦስተኛው ርምጃ ለሕይወትህ ዓላማ መሳካት የሚረዳ ከአንተ ባህርይና ሁናቴ ጋር የሚጣጣም የጊዜ ሰሌዳ መንደፍ ነው፡፡ የጊዜ መርሃ ግብር እንደሚያወጡት ቀላልነት ሳያዛንፉ መከተሉ ቀላል አይደለም፡፡ ላወጣኸው የጊዜ ሰሌዳ መገዛት ቢያቅትህ እንደገና መከለስና ማሻሻል ምንም ነውር የለበትም፡፡
ይህን ሁሉ ስታደርግ ልብ ማለት የሚገባህ ሕይወት ሥራ ብቻ÷ የግል ኑሮ ብቻ እንዳይደለ መገንዘብ ነው፡፡ የሥራና የዕረፍትን ሚዛን፣ የግልና የማኅበር ኑሮን ሚዛን፣ የዕለቱንና የዘላለሙን ሚዛን የሚጠብቅ የሕይወት ስልት መቀየስ ሁሉ ጎናዊ ስምረት እንዲኖረን ይረዳል፡፡
ወገኖቼ ጤናችን እስኪዛባ ደስታችን እስኪጠፋ ቢዚ ከሆንን እየቆየ ወደ ክስመት (burn out) ልንሄድ እንችላለን፡፡ በእምነት እጦት ሰበብ ሩጫ ያበዙትን ሕዝበ እስራኤል እግዚአብሔር እንደገሰጻቸውና እንደመከራቸው እኛንም ያስጠነቅቀናል፡፡
“የእስራኤል ቅዱስ ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላልና በመመለስና በማረፍ ትድናላችሁ፣ በፀጥታና በመታመን ኃይል ይሆንላችኋል፡፡”
(ኢሳ 30፡15)
ቁምላቸው ፈንታሁን ወደ አማርኛ ተርጉሞት በቃለ እግዚአብሔር አንባቢዎች ማኅበር በኩል ከታተመው መጽሐፍ ይህን አስተዋይ ጸሎት ልብ እንድንለው አብረንም እንድንጸልየው እጋብዛለሁ፡፡
ሰከን አርገኝ ጌታ!
ለአእምሮዬ ፀጥታ ለግሰህ፣ የልቤን ድውድውታ ቀንሰው፡፡
በጊዜ ውስጥ የዘላለምን አፅናፍ ራእይ ስጠኝና ጥድፊያዬ ልጓም ይበጅለት፡፡
በቀናት ዑደት ቱማታና ግርግር መካከል፣
የዘላለም ዓለም ኮረብቶች ግርማዊ አርምሞ በኔ ላይ ያርብብ፡፡
የሠራ አካላቴ ውጥረት በትውስታዬ በሚኖሩ
ዘማሪ ጅረቶች የሚያሳርፍ ሙዚቃ ይርገብ፡፡
የእንቅልፍን አስማታዊ አዳሽ ኃይል እንድገነዘብ እርዳኝ፡፡
ጥበብን አካፍለኝና የደቂቃ እርፍቶች በየመካከሉ እየወሰድኩ፡-
አበቦችን ልመልከት፣ ከወዳጅ ጋር ልጫወት፣
በጫካው መካከል ልመላለስ፣ ሸረሪት ድሯን ስትሸምን ልያት
ህፃኗን በፈገግታ ልቀበላት፣ እንባዎቿንም ላብስላት፡፡
ሩጫ ሁልጊዜ ለፈጣኖች እንዳይደለ፣
የኑሮ ሁለንተና ፍጥነት እየጨመሩ መኖጥ እንዳይደለ በየዕለቱ አስታውሰኝ፡፡
ቀና ብዬ ደመኖቹንና ሰማዩን
እንዲሁም ያዘመመን ዛፍ ልመልከታቸው፣
ዛፉ ዛሬ ይህን አክሎ ያደረገው፣ የበረታው በሕይወት ሰጪ ፀሐይህ ሙቀት
በዝግታ በማደጉ መሆኑን ልገንዘብ፡፡
ሰከን አርገኝ ጌታ ከአንተ ጋር ኅብረት በማድረግ በጥልቅ እኔነቴ የሚያሹኝን ሰላምና እረፍት ልጎናጸፍ፡፡

“በባልንጀራህ ግፍ አታድርግ፥ አትቀማውም። የሞያተኛው ዋጋ እስከ ነገ ድረስ በአንተ ዘንድ አይደርብህ።”
ዘሌዋውያን 19፥13

❤4🙏2
ቅዱሳት መጻሕፍት
#እምነት ክፍል-14 የሕሊና ዓይነቶች በቅዱሳት መጻሕፍት በተለይም በአዲስ ኪዳን ይባስ ብሎም ደግሞ በሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ ትምህርት "#ሕሊና" የሚለው አሳብ ተደጋግሞ ይነሳል። ለምሳሌ ሐዋርያው እንዲህ ይላል፦ “ስለዚህ እኔ ደግሞ በእግዚአብሔርና በሰው ፊት ሁልጊዜ ነውር የሌለባት ሕሊና ትኖረኝ ዘንድ እተጋለሁ።” ሐዋርያት 24፥16 በአዲስ ኪዳን…
#እምነት
ክፍል-15
በጎ ሕሊናን ማግኘት እንዴት ይቻላል?
ሀ. በኢየሱስ ክርስቶስ አምኖ በመዳን
በጎ ሕሊና የሚጀምረው በዳግም ልደት ነው። ሕሊናችንን ከጥፋተኝነት የሚያነጻው የኢየሱስ ደም ብቻ ነው።
“ነውር የሌለው ሆኖ በዘላለም መንፈስ ራሱን ለእግዚአብሔር ያቀረበ የክርስቶስ ደም እንዴት ይልቅ ሕያውን እግዚአብሔርን ልታመልኩ ከሞተ ሥራ ሕሊናችሁን ያነጻ ይሆን?”
ዕብራውያን 9፥14
መዳን ንጹህ ሕሊናን ያስከትላል። ከእንግዲህ በደለኛ ሳይሆን ሕሊናችን ይነጻል (ቲቶ 3፥5)።
ለ. የእግዚአብሔርን ቃል በመታዘዝ
የእግዚአብሔር ቃል ሕሊናን ያሠለጥናል፡-
“የእግዚአብሔር ሰው ፍጹምና ለበጎ ሥራ ሁሉ የተዘጋጀ ይሆን ዘንድ፥ የእግዚአብሔር መንፈስ ያለበት መጽሐፍ ሁሉ ለትምህርትና ለተግሣጽ ልብንም ለማቅናት በጽድቅም ላለው ምክር ደግሞ ይጠቅማል።”
2ኛ ጢሞቴዎስ 3፥16-17
በጎ ሕሊና የሚዳበረው በስሜት ወይም በባሕል ሳይሆን በእውነተኛ መንፈስ በመኖር ነው።
ሐ.በንስሐና በመናዘዝ
ኃጢአት ስንሠራ ሕሊናችን ይረክሳል። መታደስ የሚመጣው በኑዛዜ ነው፡-
“በኃጢአታችን ብንናዘዝ ኃጢአታችንን ይቅር ሊለን ከዓመፃም ሁሉ ሊያነጻን የታመነና ጻድቅ ነው።”
1ኛ ዮሐንስ 1፥9
መ. ግብዝነትን ማስወገድ
ጳውሎስ በ1ኛ ጢሞቴዎስ 4፥2 ላይ ስለ ደነዘዘ ሕሊና፦ በኃጢአት ወይም በሐሰት ትምህርት ስለደነዘዙ አስጠንቅቋል። በጎ ኅሊና ሐቀኛና ቅን እንጂ ግብዝነትን ያለው አይደለም።
ሠ. በክርስትና እና በመልካም ሥራ በመጽናት
“በክርስቶስ ያለውን መልካሙን ኑሮአችሁን የሚሳደቡ ሰዎች ክፉን እንደምታደርጉ በሚያሙበት ነገር እንዲያፍሩ በጎ ሕሊና ይኑራችሁ።”
1ኛ ጴጥሮስ 3፥16
ይቀጥላል. . .
ምንጭ፦
MacArthur, J. (2001). The MacArthur Study Bible. Thomas Nelson.
Grudem, W. (1994). Systematic Theology: An Introduction to Biblical Doctrine. Inter-Varsity Press.
Elwell, W. A., & Beitzel, B. J. (1988). Baker Encyclopedia of the Bible. Baker Book House.

❤3❤🔥1
“በማለዳ ምሕረትህን እንጠግባለን፤ በዘመናችን ሁሉ ደስ ይለናል ሐሤትም እናደርጋለን።”
መዝሙር 90፥14
“በዘመናችን ሁሉ ደስ እንዲለን፣ ሐሤትም እንድናደርግ፣ ምሕረትህን በማለዳ አጥግበን።”
መዝሙር 90፥14 (አዲሱ መ.ት)
ወደ ቻናሉ ለመ🀄️ላ🀄️ል፦ @Holy_scriptures
መዝሙር 90፥14
“በዘመናችን ሁሉ ደስ እንዲለን፣ ሐሤትም እንድናደርግ፣ ምሕረትህን በማለዳ አጥግበን።”
መዝሙር 90፥14 (አዲሱ መ.ት)
ወደ ቻናሉ ለመ🀄️ላ🀄️ል፦ @Holy_scriptures
🥰9❤2
. ──•◈•─────•◈•─
የዕለቱ ጥቅስ
──•◈•─────•◈•─
“ስለ እነርሱም ሊያማልድ ዘወትር በሕይወት ይኖራልና ስለዚህ ደግሞ በእርሱ ወደ እግዚአብሔር የሚመጡትን ፈጽሞ ሊያድናቸው ይችላል።”
ዕብራውያን 7፥25

❤9
የአጥር ላይ ተጓዥ
ድንገት ስናወራ ስለ አንድ ሰውዬ
ባህሪውን ሳወራ “አቋም የለሽ” ብዬ
“አጥር ላይ ተጓዥ ነው” አለኝ ጓደኛዬ።
ገርሞኝ ንግግሩ አብራራልኝ ስለው
የአቋም የለሹን ሰው እቅዱን ገለጠው።
የሚያዋጣውን አይቶ ወደ አንዱ ይዘላል
ወይ ግቢ ወይ ውጪ አይቶ ይወረወራል።
ብሎ ቢገልጥልኝ የአጥሩን ላይ ኗሪ
ትዝ አለኝ ብዙ ሰው በየ አጥሩ አዳሪ።
የአጥር ላይ ኗሪዎች ወደ አንዱ ዝለሉ
ወይ “ልክ አይደለንም” ወይ “ልክ ነን” በሉ።
ለሁሉ አትሳቁ ወይ ኣንዱን ተቆጡ
ሁሉን አትደባብሱ አንዳንዴም ቆንጥጡ።
አጥር ላጥር ጉዞ እድሜ እስኪሟጠጥ
በጣም ያሳፍራል ለምግብ ለመጠጥ።
ወዳንዱ ሳይወስን አጥር ላይ ለኖረ
አጥሩ ላይ ሰብኮ እዛው ለዘመረ
ምን ይሆን ክፍያው እያልኩ ሳሰላስል
ያ ሮቤል ትዝ አለኝ እንደ ውሀ ሚዋልል።
እውነትም አጥር ላይ የከረመ ዘዋሪ
አይሆንም አለቃ ቆራጥ ጀግና መሪ
ምክንያቱም ውሳኔ ስለሌለው ልቡ
ወደ አጥሩ ይወጣል ሲጮህበት ህዝቡ።
እርሶ የቱ ጋ ኖት እባኮት አስቡ?
ለማን እጅ አጠፉ ለማ አጨበጨቡ?
እንደ አስቆሮቱ ሁለት አይውደዱ
ሳይደወልቦት ከአጥርዎ ይውረዱ።
ጥቅምት 18 2004
ምንጭ፦ ደረጀ ሙላቱ፤ ይዳኘን መጽሐፉ፤ ገጽ 86
ወደ ቻናሉ ለመ🀄️ላ🀄️ል👉 @TME_bible_study
ድንገት ስናወራ ስለ አንድ ሰውዬ
ባህሪውን ሳወራ “አቋም የለሽ” ብዬ
“አጥር ላይ ተጓዥ ነው” አለኝ ጓደኛዬ።
ገርሞኝ ንግግሩ አብራራልኝ ስለው
የአቋም የለሹን ሰው እቅዱን ገለጠው።
የሚያዋጣውን አይቶ ወደ አንዱ ይዘላል
ወይ ግቢ ወይ ውጪ አይቶ ይወረወራል።
ብሎ ቢገልጥልኝ የአጥሩን ላይ ኗሪ
ትዝ አለኝ ብዙ ሰው በየ አጥሩ አዳሪ።
የአጥር ላይ ኗሪዎች ወደ አንዱ ዝለሉ
ወይ “ልክ አይደለንም” ወይ “ልክ ነን” በሉ።
ለሁሉ አትሳቁ ወይ ኣንዱን ተቆጡ
ሁሉን አትደባብሱ አንዳንዴም ቆንጥጡ።
አጥር ላጥር ጉዞ እድሜ እስኪሟጠጥ
በጣም ያሳፍራል ለምግብ ለመጠጥ።
ወዳንዱ ሳይወስን አጥር ላይ ለኖረ
አጥሩ ላይ ሰብኮ እዛው ለዘመረ
ምን ይሆን ክፍያው እያልኩ ሳሰላስል
ያ ሮቤል ትዝ አለኝ እንደ ውሀ ሚዋልል።
እውነትም አጥር ላይ የከረመ ዘዋሪ
አይሆንም አለቃ ቆራጥ ጀግና መሪ
ምክንያቱም ውሳኔ ስለሌለው ልቡ
ወደ አጥሩ ይወጣል ሲጮህበት ህዝቡ።
እርሶ የቱ ጋ ኖት እባኮት አስቡ?
ለማን እጅ አጠፉ ለማ አጨበጨቡ?
እንደ አስቆሮቱ ሁለት አይውደዱ
ሳይደወልቦት ከአጥርዎ ይውረዱ።
ጥቅምት 18 2004
ምንጭ፦ ደረጀ ሙላቱ፤ ይዳኘን መጽሐፉ፤ ገጽ 86
ወደ ቻናሉ ለመ🀄️ላ🀄️ል👉 @TME_bible_study
❤11🔥3🙏3
. ──•◈•─────•◈•─
የዕለቱ ጥቅስ
──•◈•─────•◈•─
“የምዋቹን ሞት አልፈቅድምና፥ ይላል ጌታ እግዚአብሔር፤ ስለዚህ ተመለሱና በሕይወት ኑሩ።”
ሕዝቅኤል 18፥32