#እራሳችንን_እንመርምር
"ታዲያ እግዚአብሔር ጸጋውን ያበዛልናል በማለት ኃጢአት መሥራታችንን መቀጠል አለብን ማለት ነውን? እግዚአብሔርም አይበለው! ከእርሱ ጋር ሕብረት እንዲኖረን በጌታችን በኢየሱስ ስም በተጠመቅንበት ጊዜ ፥ ኃጢአት መሥራት የሚቀናው አሮጌው ባሕርያችን ከእርሱ ጋር የሞተ መሆኑን እንዴት ዘነጋችሁት?"
ሮሜ 6፥1-3 (ሕያው ቃል)
ወደ ቻናሉ ለመ🀄️ላ🀄️ል፦ @Holy_scriptures

❤14
. ──•◈•─────•◈•─
የዕለቱ ጥቅስ
──•◈•─────•◈•─
“ከእግዚአብሔር ጋር አብረን የምንሠራ እንደ መሆናችን መጠን፣ የተቀበላችሁትን የእግዚአብሔርን ጸጋ ከንቱ እንዳታደርጉት ዐደራ እንላችኋለን።”
2ኛ ቆሮንቶስ 6፥1 (አዲሱ መ.ት)

❤7
ባለራእይነት.pdf
2.8 MB
👏6❤1
Forwarded from Tabor Bible Study (ሐዋሳ ታቦር መካነ ኢየሱስ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት)
BIBLE (Basic Instruction Before Leaving Earth)
“እኔ በምድር እንግዳ ነኝ፤ ትእዛዛትህን ከእኔ አትሰውር።”
መዝሙር 119፥19
በምድር ላይ የግድ ልናውቀው የሚገባን መመሪያ የእግዚአብሔር ቃል ነው። ይህን መመሪያ ለማንበብ፣ አልፎ ተርፎም ለመረዳት እንትጋ!
ወደ ቻናሉ ለመ🀄️ላ🀄️ል👉 @TME_bible_study

❤17❤🔥2👏1
. ──•◈•─────•◈•─
የዕለቱ ጥቅስ
──•◈•─────•◈•─
“በክርስቶስ ኢየሱስ ከሆኑት እምነትና ፍቅር ጋርም የጌታችን ጸጋ ተትረፈረፈልኝ።”
1ኛ ጢሞቴዎስ 1፥14 (አዲሱ መ.ት)
ወደ ቻናሉ ለመ🀄️ላ🀄️ል፦ @Holy_scriptures
የዕለቱ ጥቅስ
──•◈•─────•◈•─
“በክርስቶስ ኢየሱስ ከሆኑት እምነትና ፍቅር ጋርም የጌታችን ጸጋ ተትረፈረፈልኝ።”
1ኛ ጢሞቴዎስ 1፥14 (አዲሱ መ.ት)
ወደ ቻናሉ ለመ🀄️ላ🀄️ል፦ @Holy_scriptures
🔥7❤4
⏱ቢዚ - ቢዚ፤ ለሁሉ ጊዜ አለው ወይስ አለን?
በጋሽ ንጉሤ ቡልቻ
ጓዙን ጠቅልሎ ወደ ውጪ አገር የሚሄድ ጓደኛውን ለመሸኘት ከተሰበሰቡት መካከል የሽኝት ፕሮግራሙን ማጠቃለያ ጸሎት የሚጸልየው ሰው እንዲህ ብሎ ጸልዮአል አሉ፡፡
“ጌታ ሆይ ይህ ወንድማችን በሚሄድበት አገር ቢዚ ከሚባል ጋኔን እንድትጠብቀው እንለምንሃለሁ፡፡”
“ቢዚ” የሚባል ጋኔን መኖር አለመኖሩን መመራመራችንን ትተን ባተሌነት “ቢዚነት” የውጪ አገር አበሳ መሆኑ ቀርቶ ውስጥ አገርም የሚያስጨንቀን ጉዳይ እንደ ሆነ እንቀበል፡፡
በቀጠሮ ብዛት፣ በእንቅስቃሴ ብዛት፣ በጉዳይ ብዛት፣ በሥራ ብዛት፣ በሥራ ውጣ ውረድ፣ በማኅበራዊ ግንኙነት ብዛት፣ በሽቅብ ቁልቁል ብዛት፣ የአካላችን አውታር እስኪነዝሩ ተወጣጥረናል፤ ነፍሳችን ብን ትን እስክትል እንማስናለን፡፡ ትንፋሽ አጥሮን ስናለከልክ የሚያየን የሌላ ዓለም ፍጡር ቢኖር “ምን ሥራሥር በጥብጠው ቢጠጡ ነው እንዲህ የሚያዛብታቸው፣ የሚያሽከረክራቸው” ብሎ በጠየቀ፡፡ ለመሆኑ ምን እንዲህ ያባትለናል?
የየዕለቱ ውጣ ውረድ ነዋ! የጉረሮ መድፈን ጥሪ፣ የማኅበረ ሰብ ቦታችንን የማስጠበቅ ጥሪ፣ የነገ ምን ይሆናል ጭንቀት፣ ሌሎችም ይህን የመሳሰሉ ሁሉ፡፡ የሰው ልጅ የሚሠራውንና የሚውልበትን ሁነኛ ጉዳይ አግኝቶ በሥራ መጠመዱ በረከት እንጂ ርግማን አይደለም፡፡ ጊዜ እንደ ጅረት በሚንፎለፎልበት ልማዱ ቢነጉድ የሥራ ቦይ እየቀደዱ ጥቅም ላይ የሚያውሉት የታደሉ ናቸው “ዘመኑን ዋጁ” በሚለው ምክር አብነት፡፡ እንዲህ የሚያደርጉ በሥራው ከሚገኘው ጥቃሞት በላይ ስብእናቸው ይለማል፣ ርካታና ደስታም ያገኛሉ፡፡
አሁን ያነሣነው “ጋኔኑ ቢዚነት” ግን ከሚያለማው የሚያጠፋው የበለጠ፣ ከሚያረካው የሚያቅበዘብዘው የበዛ፣ ደስታችንን ቦጥቡጦ የሚበላ መልቲ ነው፡፡
ሮጠን ሮጠን ልባችን ሊፈነዳ ሲል ስንቆም የትም እንዳልደረስን ስንረዳ፣ ከበሬታ ፍለጋ ብዙ የአንቱታ ካባ ደርበን ድንገት ካባው የወደቀ ቀን የነፍሳችን ክሳት ሲጋለጥ የዚህ ዐይነት ቢዚነት ፍሬ ይታወቅ ይሆናል፡፡
መድኃኒታችን ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ “በአጭር ቁመት በጠባብ ደረት ተወስኖ ወደዚህ ምድር ስለመጣ ልክ እንደ እኛ በቀን ውስጥ 24 ሰዓት ብቻ ነበረው፡፡ ያደረገውን ሁሉ ያደረገው በዚሁ በባለ 24 ሰዓት ቀን ነበር፡፡ የምድር እድሜው ጥቂት ነበረ፤ የይፋ አገልግሎቱ ደግሞ ከሦስት ዓመታት እጅግም ያልዘለለ አጭር ነበር፡፡ ይህ ሁሉ ሆኖ ወደ አባቱ መሄጃው ጊዜ ሲደርስ የጸለየው ጸሎት የተዋከበ፣ የተጨነቀ አልነበረም፤ “ምነው አንድ ዐሥር ዓመት ብትጨምርልኝና የጀመርሁትን በጨረስሁ” የሚል የጊዜ ልመና አልነበረበትም፡፡ “የሰጠኸኝን ሥራ በምድር ላይ ፈጽሜ አከበርሁህ” የሚል ደልዳላ ዘገባ ነበር፡፡
ይቀጥላል ...
ምንጭ :- semayawithought.com

❤16❤🔥1👏1
. ──•◈•─────•◈•─
የዕለቱ ጥቅስ
──•◈•─────•◈•─
“አምላካችን እግዚአብሔር በኮሬብ ከእኛ ጋር ቃል ኪዳን አደረገ።”
ዘዳግም 5፥2

🔥3❤2
ቅዱሳት መጻሕፍት
⏱ቢዚ - ቢዚ፤ ለሁሉ ጊዜ አለው ወይስ አለን? በጋሽ ንጉሤ ቡልቻ ጓዙን ጠቅልሎ ወደ ውጪ አገር የሚሄድ ጓደኛውን ለመሸኘት ከተሰበሰቡት መካከል የሽኝት ፕሮግራሙን ማጠቃለያ ጸሎት የሚጸልየው ሰው እንዲህ ብሎ ጸልዮአል አሉ፡፡ “ጌታ ሆይ ይህ ወንድማችን በሚሄድበት አገር ቢዚ ከሚባል ጋኔን እንድትጠብቀው እንለምንሃለሁ፡፡” “ቢዚ” የሚባል…
የቀጠለ...
⏱️ቢዚ - ቢዚ፤ ለሁሉ ጊዜ አለው ወይስ አለን?
በጋሽ ንጉሤ ቡልቻ
እንዴት እንደዚህ ስክን ያለ ሕይወትና አገልግሎት አገኘ? እጅግ ብዙ የእርሱን ርዳታ የሚሹ ፍጡራን ባሉበት ዓለም ውስጥ በቀኝና በግራ ሊያዋክቡት የሚችሉ አስባታሊ ተግባራት በነበሩበት ሁኔታ እንደምን ርጋታ አገኘ? መጽሐፉ ላይ እንደ ተጠቆምን ከሆነ መልሱ ውስብስብ አይደለም፡፡ ጌታችን ዋናውን ጉዳይ ከአስቸኳዩ የለየ፣ የሕይወት ጥሪውን አሳምሮ ያወቀ፣ ቆፍጣና የዓላማ ሰው ስለነበረ ነው፡፡ “የሰጠኸኝን ሥራ” አለ እንጂ በሜዳ ያለውን ተግባር ሁሉ አላለም፤ ወይም ዘመድ ወዳጅ የጠየቀኝን ኀላፊነት ሁሉ ወይም የተገኘውን ሥራ ሁሉ ፈጸምሁ አላለም፡፡ የአባቱ ፈቃድ የሕይወት ጥሪው ነበረና ያንኑ ፈቃድ በመንፈስ ቅዱስ ኀይል ፈጸመው፡፡ በጸሎቱ ዘገባ በዝርዝር እንዳሰፈረው እያንዳንዱን ቅንጣት ተግባር ከነውጤቱ እንደተከናወነ ርግጠኛ ነበር፡፡ በምድር አገልግሎቱ የነካቸው ሰዎች ሁሉ ሕይወታቸው በጥልቅ ተነክቷል፤ የይድረስ ይድረስ በሽታ ሳይጠናወተው የሚሠራውን ሁሉ ወደ ተገቢው ፍጻሜ አደረሰ፡፡ በዓላማ ጽናት፣ በርግጠኛ ርምጃ፣ በታላቅ ማስተዋል ተራመደ፡፡ ስለዚህ ሞቱ የጸጸት አልነበረም የድልና የስኬት እንጂ፡፡ ሕይወቱ አልተጨናገፈም፤ ውጥኑ ባጭር አልቀረም፤ የሰማይ አባቱን ያስከበረ ወርቃማ ፍጻሜ አገኘ፡፡ የሕይወትን ዋና ጥሪ ለመፈጸም ጊዜን በጥበቡ የመጠቀም ጉልህ አርኣያ ሆነ፡፡ ስሙ ይክበር፡፡ ቻርልስ ሁሜል የተባለ አስተዋይ ጸሐፊ “The Tyranny of the Urgent” ብሎ የጻፈውና ቁምላቸው ፈንታሁን የተረጎመው አንድ ጽሑፍ እንዲህ ይላል፦
/ወደ ኋላ መለስ ብለን ስንመለከት፣ያልተጠናቀቁ ሥራዎች፣ ምላሽ ያልተሰጣቸው ደብዳቤዎች፣ ያልተጎበኙ ወዳጆች ያልተጻፉ መጣጥፎችና ያልተነበቡ መጻሕፍት ይታዩናል፡፡ በሥራ እየባተልን ቢሆንም የምናገኝበት ደስታ እያደር የመነመነ ነው፡፡ ሆኖም ችግር የሚፈጥርብን ተግቶ መሥራት ሳይሆን ጥርጣሬና መወላወል ናቸው፡፡ ትልቁ አደጋ ለአስቸኳዩ ጉዳይ መላ ለመፈለግ ስንጣደፍ ዋነኛውን ጉዳይ መዘንጋቱ ነው፡፡ ችግሩ ደግሞ ዋነናው ጉዳይ ዛሬ ወይም በዚህ ሳምንት ይሠራ የሚያሰኝ አጣዳፊነት የሌለው መሆኑ ነው፡፡ ፈጣን ርምጃ የሚጠይቁን አጣዳፊ ጉዳዮች ናቸው፡፡ በጊዜው በጣም አስፈላጊና ወደ ጎን የማይባሉ ስለሚመስሉን ጉልበታችንን ይመጡታል፡፡ ክርስቲያን ፋታ ወስዶ መንፈሳዊ ሁኔታውን በመፈተሸ፣ የሥራ ኀላፊነት ለመቀበል እንዳይችል ሆኖ በሥራ ከተጠመደ፣ ለአስቸኳዩ ጉዳይ ምላሽ ለመስጠት ሎሌ ያድራል፡፡ በራሱና በሌሎች ዐይን ዋጋ የሚሰጠው የሚመስል ነገር፣ ሌት ተቀን ሠርቶ ማከናወን ቢችልም፣ እግዚአብሔር ያቀደለትን ሥራ ግን ሳያጠናቅቅ ይቀራል/
እንግዲያው በባርነት ቀፍድዶ የያዘን “አስቸኳይ” የሚባል አምባ ገነን የፍዳችን አንዱ ዋና ምክንያት መሆኑ ነው፡፡ አስቸኳዩን ከዋናው ጉዳይ እንዴት እንለያለን? የሚለው ጥያቄ ብርቱ ጥያቄ ነው፡፡ ለዚህ መልስ ካገኘን የፍልሚያው እምብርት ታወቀ ማለት ነው፡፡
ይረዳን እንደ ሆነ እስቲ መላ ልምታ፡፡ በጎ ትብብራችሁን ስጡኝና ይህን ጥያቄ በጥሞና መልሱልኝ “ለመሞት አንድ ወር ቀርቶሃል የምትሠራውን ሁሉ በነዚህ ሠላሳ ቀናት ጨርስ” ብትባሉ ቀኖቹንና ሌሊቶቹን ምን ታደርጉባቸው ነበር?
ብጣሽ ወረቀት አውጡና የምታደርጓቸውን ነገሮች በቅደም ተከተል ጻፉዋቸው፡፡ ልምምዱ ምናልባት ዋና የምትሉትን ዋና ካልሆኑት ለመለየት ይረዳችሁ ይሆናል፡፡
ይቀጥላል...

❤9
. ──•◈•─────•◈•─
የዕለቱ ጥቅስ
──•◈•─────•◈•─
“በውኑ እግዚአብሔር ፍርድን ያጣምማልን? ሁሉንም የሚችል አምላክ ጽድቅን ያጣምማልን?”
ኢዮብ 8፥3

❤5🔥1
ቅዱሳት መጻሕፍት
#እምነት ክፍል-12 እምነት እና ሥራ የእውነተኛ እምነት ትክክለኛ ገጽታ በጊዜውም ይሁን ቈይቶ በሥራ ሊገለጥ የሚችል መሆኑ ነው፡፡ የእስራኤል አባት በሆነው በአብርሃም እምነት የተመለከትነውም ይህንን ነው፡፡ ከአሕዛብ በሆነችው በረዓብ እምነትም የምንማረው ይህንኑ እውነታ ነው፤ ስለዚህ በመቀጠል የረዓብ ማስረጃነት ቀርቧል፤ «እንደዚሁም ጋለሞታይቱ ረዓብ ደግሞ መልእክተኛቹን…
#እምነት
ክፍል-13
እምነታችንን እንዴት ከጥፋት እንጠብቅ?
“እምነትና በጎ ሕሊና ይኑርህ፥ አንዳንዶች ሕሊናን ጥለው፥ መርከብ አለ መሪ እንደሚጠፋ፥ በእምነት ነገር ጠፍተዋልና፤”
1ኛ ጢሞቴዎስ 1፥19
በዚህ ዐውደ-ጽሑፍ ውስጥ “እምነት” የሚያመለክተው ሙሉውን የክርስትና እምነት ነው ሁለቱም ማለትም በእግዚአብሔር እና በወንጌል መሠረታዊ እውነቶች (ዶክትሪን) ላይ መታመንን ያመለክታል። ጳውሎስ ጢሞቴዎስን ይህን እምነት “እንዲይዝ” አዘዘው፣ ይህም ንቁ እና ቀጣይነት ያለው ቁርጠኝነትን እንዲያሳይ በማመልከትም ጭምር ነው። እምነታችንን መጠበቅ ትክክለኛዎቹን ትምህርቶች ማመን ብቻ ሳይሆን ከሐሰት ትምህርቶችና ከመንፈሳዊ ግድየለሽነት መጠበቅንም ይጨምራል።
ጳውሎስ ቀደም ብሎ ጢሞቴዎስን ከወንጌል እውነት ያፈነገጡ አፈ ታሪኮችን እና የዘር ሐረጋቸውን የሚያሰራጩ አንዳንድ አስተማሪዎች እንዲቃወም አስጠንቅቆታል (1 ጢሞ. 1፥3–4)፤ የአስተምህሮ ንጽህና እምነትን የመጠበቅ መሰረታዊ ገጽታ መሆኑን ሐዋሪያው በአንክሮ ይጠቅሳል።
በእምነታችን ላይ የበጎ ሕሊና ሚና
“በጎ ሕሊና” የአንድን ሰው ባሕርይ ከእምነቱ ጋር የሚያስማማ የሥነ ምግባር ኮምፓስ ሆኖ ያገለግላል። በጳውሎስ ጽሑፎች ውስጥ ያለው ሕሊና የሰውን ውስጣዊ ግንዛቤ በወንጌል እውነትና በመንፈስ ቅዱስ እንዲመራ የተነገረውን ያንጸባርቃል። ጳውሎስ ሕሊናን እና እምነትን በጥብቅ ያገናኛል። አንድ አማኝ የህሊናውን ፅኑ ድምጽ ወደ ጎን ሲተው፣ ቀስ በቀስ ራሱን የእግዚአብሔርን ድምጽ ወደ በማጣት ስሕተት እና ለሞራል ውድቀት እንዲዳረግ ያደርገዋል። ለመሆኑ ቅዱሳት መጻሕፍት ውስጥ ሕሊና እንዴት ይታያል? ስንት ዓይነት ሕሊና አለ? በጎ ሕሊና እንዴት ይገኛል? ጌታ ቢፈቅድ በሚቀጥለው ክፍል እንመለስበታለን።
ይቀጥላል...
Knight, G. W. (1992). The Pastoral Epistles: A Commentary on the Greek Text (New International Greek Testament Commentary). Eerdmans.
Towner, P. H. (2006). The Letters to Timothy and Titus (New International Commentary on the New Testament). Eerdmans.

❤7❤🔥1
. ──•◈•─────•◈•─
የዕለቱ ጥቅስ
──•◈•─────•◈•─
“ወደዚህም ስፋራ እስክትመጡ ድረስ በሄዳችሁበት መንገድ ሁሉ፥ ሰው ልጁን እንዲሸከም አምላክህ እግዚአብሔር እንደተሸከመህ አንተ አይተሃል።”
ዘዳግም 1፥31

❤8🙏2
ቅዱሳት መጻሕፍት
#እምነት ክፍል-13 እምነታችንን እንዴት ከጥፋት እንጠብቅ? “እምነትና በጎ ሕሊና ይኑርህ፥ አንዳንዶች ሕሊናን ጥለው፥ መርከብ አለ መሪ እንደሚጠፋ፥ በእምነት ነገር ጠፍተዋልና፤” 1ኛ ጢሞቴዎስ 1፥19 በዚህ ዐውደ-ጽሑፍ ውስጥ “እምነት” የሚያመለክተው ሙሉውን የክርስትና እምነት ነው ሁለቱም ማለትም በእግዚአብሔር እና በወንጌል መሠረታዊ እውነቶች…
#እምነት
ክፍል-14
የሕሊና ዓይነቶች
በቅዱሳት መጻሕፍት በተለይም በአዲስ ኪዳን ይባስ ብሎም ደግሞ በሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ ትምህርት "#ሕሊና" የሚለው አሳብ ተደጋግሞ ይነሳል። ለምሳሌ ሐዋርያው እንዲህ ይላል፦
“ስለዚህ እኔ ደግሞ በእግዚአብሔርና በሰው ፊት ሁልጊዜ ነውር የሌለባት ሕሊና ትኖረኝ ዘንድ እተጋለሁ።”
ሐዋርያት 24፥16
በአዲስ ኪዳን ሕሊና በተለያየ ሥፍራና ቦታ በተለያየ አውድ ተጠቅሷል። ከእነዚህ መካከል የሚከተሉትን እነሆ፦
1. ክፉ ሕሊና
ክፉ ሕሊና ተበላሽቶ ወደ ሥነ ምግባር ዝቅጠት የሚመራ ነው። ይህ ሕሊና የእግዚአብሔርን ፈቃድ የሚጻረር እና የኃጢያት ባህሪን የሚያበረታታ ነው። (ዕብ. 10፥22)
2. የረከሰ ሕሊና
የረከሰ ሕሊና በኃጢአት የረከሰና ግልጽ የሆነ የሞራል ልዩነት ማድረግ የማይችል ነው። ትክክል እና ስህተት መካከል ወደ ግራ መጋባት ይመራል። (ቲቶ. 1፥15)
3. የደነዘዘ ሕሊና
የደነዘዘ ሕሊና ማለት በድግግሞሽ ኃጢአት የተዳከመ ወይም የደነደነ ነው። ከጊዜ በኋላ
ሰውየው ለጥፋተኝነት ወይም ለጥፋተኝነት ግድየለሽ ይሆናል። ኃጢአትን እንደ ስህተት አይገነዘብም። (1ኛ ጢሞ. 4፥2)
4. ደካማ ሕሊና
ደካማ ሕሊና የሚያመለክተው ኃጢአት በሌለበት አካባቢም እንኳ በቀላሉ ሊኮነን የሚችል ያልበሰለ ወይም ከልክ ያለፈ ስስ ሕሊና ነው። ይህ ሊሆን የሚችለው አንድ ሰው በተፈጥሮ ኃጢአተኛ ያልሆኑ የሥነ ምግባር ጉዳዮች ላይ እርግጠኛ ካልሆነ ነው። (1ኛ ቆሮ. 8፥7)
5. ንጹሕ ሕሊና
ንፁህ ህሊና ማለት ከጥፋተኝነት እና ከነቀፋ በጸዳ መልኩ በእግዚአብሔርና በሰው ፊት መኖር ፣ በታማኝነት እና በመታዘዝ መመላለስ ማለት ነው። (ሐዋ. 24፥16)
6. በጎ ሕሊና
በጎ ሕሊና ከእግዚአብሔር እውነት ጋር የሚስማማ እና ወደ ጽድቅ ሕይወት የሚመራ ነው። ግለሰቡ ይቅርታን እንዲጠይቅ እና የሞራል ህይወት እንዲጠብቅ የሚገፋፋው ለኃጢያት እና የጥፋተኝነትን ድንበር በማወቅ ለእነዚህ ነገሮች ንቁ የሆነ ነው። (1 ጢሞ. 1፥19)
ይቀጥላል. . .

❤8🔥4
. ──•◈•─────•◈•─
የዕለቱ ጥቅስ
──•◈•─────•◈•─
“የአባቶቻቸውም አምላክ እግዚአብሔር ለሕዝቡና ለማደሪያው ስላዘነ ማለዳ ተነሥቶ በመልእክተኞቹ እጅ ወደ እነርሱ ይልክ ነበር።”
2 ዜና 36፥15

❤4🔥3
የጸጋ መቀበያ መንገድ በሉተራን አስተምህሮ
ክፍል-1
በሉተራን አስተምህሮ፣ “የጸጋ መቀበያ መንገድ” የሚለው ቃል የሚያመለክተው በመለኮት የተመሰረተ እና የተቋቋመ እግዚአብሔር ጸጋን የሚሰጥበትን መንገዶችን ነው። እግዚአብሔር ጸጋውን የሚሰጠው የኃጢያት ይቅርታን፣ ህይወትን እና ድነትን ለሰው ለመስጠት ነው። እነዚህ ዘዴዎች ምሳሌያዊ ብቻ አይደሉም። ይልቁኑ በእግዚአብሔር ቃልና በተስፋው ቃል መሠረት ጸጋውን የምናገኝበት መንገድ ነው። በሉተራን ሥነ-መለኮት ሦስት ዋና የጸጋ መቀበያ መንገዶች አሉ፦
👉የእግዚአብሔር ቃል (በተለይም ወንጌል)
👉ቅዱስ ጥምቀት
👉የጌታ እራት (ቅዱስ ቁርባን)
በነገራችን ላይ ማርቲን ሉተር በመጀመሪያ ጽሑፎቹ እንደ መደበኛ ሥነ-መለኮታዊ ቃል “የጸጋ መቀበያ መንገድ” ("media gratiae" በላቲን ወይንም "Gnadenmittel በጀርመንኛ) ከሚለው ትክክለኛ የላቲን ወይም የጀርመንኛ አቻ ቃል አልተጠቀመም። ነገር ግን፣ የጸጋ መቀበያ መንገዶች ጽንሰ-ሀሳብ እና አስተምህሮ በስራው በሙሉ፣ በተለይም በቃሉ እና በቅዱስ ቁርባን አስተምህሮ ውስጥ በጥልቅ ተካተዋል። “የጸጋ መቀበያ መንገድ” የሚለው መደበኛ ቃል በሉተራን የሃይማኖት ምሁራን በተለይም በሉተራን ኦርቶዶክስ ዘመን (17ኛው ክፍለ ዘመን) በደንብ እያበበ መጣ። ይህ ሲባል ግን ይህ አገላለጽ በሉተር ሥነ-መለኮት ላይ የተመሠረተ አይደለም ማለት አይደለም።
1. የፅንሰ ሀሳቡ መሠረት በሉተር ፅሁፎች
ሉተር ሐረጉን የፈጠረው ላይሆን ይችላል፣ ግን ሐሳቡን በግልፅ አስቀምጧል፡-
“For God does not want to deal with us in any other way than through the spoken Word and the Sacraments. Whatever is attributed to the Spirit apart from such Word and Sacrament is of the devil”
ይቀጥላል...
ምንጭ፦
Kolb, R., & Wengert, T. J. (Eds.). (2000). The Book of Concord: The Confessions of the Evangelical Lutheran Church. Fortress Press.
Luther, M. (1537). Smalcald Articles. In Kolb, R., & Wengert, T. J. (Eds.), The Book of Concord (pp. 301–320). Fortress Press.

❤11🔥1
. ──•◈•─────•◈•─
የዕለቱ ጥቅስ
──•◈•─────•◈•─
“ከአንድ አፍ በረከትና መርገም ይወጣሉ። ወንድሞቼ ሆይ፥ ይህ እንዲህ ሊሆን አይገባም።”
ያዕቆብ 3፥10
ወደ ቻናሉ ለመ🀄️ላ🀄️ል፦ @Holy_scriptures
የዕለቱ ጥቅስ
──•◈•─────•◈•─
“ከአንድ አፍ በረከትና መርገም ይወጣሉ። ወንድሞቼ ሆይ፥ ይህ እንዲህ ሊሆን አይገባም።”
ያዕቆብ 3፥10
ወደ ቻናሉ ለመ🀄️ላ🀄️ል፦ @Holy_scriptures
👍3❤1👏1
#እራሳችንን_እንመርምር
እኔምለው አብዛኛዎቻችን እግዚአብሔርን ስለጽድቅ እና ፍትህ የምንወቅሰው በእውነት ገዶ ነው ወይስ እሱን እንደሰበብ ወስደን በአመጽ ለመቀጠል ነው?🤔 ፍትህንና ጽድቅ የሚፈልግ ሰው እራሱ በፍትህ መንገድ እየሄደ ቢጠይቅስ?
“እግዚአብሔርን በቃላችሁ አታክታችኋል። እናንተም፦ ያታከትነው በምንድር ነው? ብላችኋል። ክፉን የሚያደርግ ሁሉ በእግዚአብሔር ዘንድ መልካም ነው፥ እርሱም በእነርሱ ደስ ይለዋል፤ ወይስ፦ የፍርድ አምላክ ወዴት አለ? በማለታችሁ ነው።”
ሚልክያስ 2፥17

❤2
. ──•◈•─────•◈•─
የዕለቱ ጥቅስ
──•◈•─────•◈•─
“እግዚአብሔርም ከሩቅ ተገለጠልኝ እንዲህም አለኝ፦ በዘላለም ፍቅር ወድጄሻለሁ ስለዚህ በቸርነት ሳብሁሽ።”
ኤርምያስ 31፥3
ወደ ቻናሉ ለመ🀄️ላ🀄️ል፦ @Holy_scriptures
የዕለቱ ጥቅስ
──•◈•─────•◈•─
“እግዚአብሔርም ከሩቅ ተገለጠልኝ እንዲህም አለኝ፦ በዘላለም ፍቅር ወድጄሻለሁ ስለዚህ በቸርነት ሳብሁሽ።”
ኤርምያስ 31፥3
ወደ ቻናሉ ለመ🀄️ላ🀄️ል፦ @Holy_scriptures
❤10
ቅዱሳት መጻሕፍት
የቀጠለ... ⏱️ቢዚ - ቢዚ፤ ለሁሉ ጊዜ አለው ወይስ አለን? በጋሽ ንጉሤ ቡልቻ እንዴት እንደዚህ ስክን ያለ ሕይወትና አገልግሎት አገኘ? እጅግ ብዙ የእርሱን ርዳታ የሚሹ ፍጡራን ባሉበት ዓለም ውስጥ በቀኝና በግራ ሊያዋክቡት የሚችሉ አስባታሊ ተግባራት በነበሩበት ሁኔታ እንደምን ርጋታ አገኘ? መጽሐፉ ላይ እንደ ተጠቆምን ከሆነ መልሱ ውስብስብ…
የቀጠለ...
⏱️ቢዚ - ቢዚ፤ ለሁሉ ጊዜ አለው ወይስ አለን?
በጋሽ ንጉሤ ቡልቻ
ይረዳን እንደ ሆነ እስቲ መላ ልምታ፡፡ በጎ ትብብራችሁን ስጡኝና ይህን ጥያቄ በጥሞና መልሱልኝ “ለመሞት አንድ ወር ቀርቶሃል የምትሠራውን ሁሉ በነዚህ ሠላሳ ቀናት ጨርስ” ብትባሉ ቀኖቹንና ሌሊቶቹን ምን ታደርጉባቸው ነበር?
ብጣሽ ወረቀት አውጡና የምታደርጓቸውን ነገሮች በቅደም ተከተል ጻፉዋቸው፡፡ ልምምዱ ምናልባት ዋና የምትሉትን ዋና ካልሆኑት ለመለየት ይረዳችሁ ይሆናል፡፡
የሕይወታችሁ ዋና ዓላማ ምንድን ነው? የደም ግፊታችሁን እየጨመረ፣ ናላችሁን እያዞረ፣ ትንፋሽ አሳጥቶ የሚያስሮጣችሁን ነገር ሁሉ ከዚህ ዋና ዓላማ አንጻር ፈትሹት፡፡ ወደ ዓላማው የሚፈስ ነባር ወንዝ ነው ወይስ በየመስኩ የፈነዳ መድረሻው ያልታወቀ የውሃ ምንጭ? የክርስቶስ ተከታይ ዋና ዓላማ ምንድን ነው የተባለ እንደሆነ ሐዋርያው ጳውሎስ ባጭሩና በግልጽ ከተናገረው ከዚህ ጥቅስ የተሻለ መግለጫ አላገኘሁም፡፡ “አንዱ ስለ ሁሉ ሞተ፣ እንግዲያውስ ሁሉ ሞቱ በሕይወትም ያሉትም ስለ እነርሱ ለሞተውና ለተነሣው እንጂ ወደ ፊት ለራሳቸው እንዳይኖሩ ስለ ሁሉ ሞተ፡፡” 2ኛ ቆሮ 5፡13
የክርስቶስ ተከታይ ግለ ሰብም ሆነ ማኅበረ ሰብ የሕይወት ዓላማው ንድፍ ተሠርቶለት አልቋል፡፡ የምንሠራው ሁሉ የምናስበው ሁሉ የዚህ ዋና ንድፍ (Master Plan) አካል ካልሆነ ሕገ ወጥ ግንባታ ነው፤ ለፍቶ መና ነው፡፡ እያንዳንዱዋ የእንቅስቃሴ ቅንጣት መፈተሸ ዋጋዋም መተመን አለባት፡፡ መሮጥ ብቻውን ዋጋ ቢስ ነው፤ ሕይወት መሮጫ ግብ ይሻል፤ ግቡም በአንጻሩ የመገስገሻ መስመር አለው፡፡ ሐዋርያው ትንፋሽ ሊሰበስብ ሲቃረብ ሩጫ ጨረስኩ ሳይሆን ‹‹ሩጫውን ጨረስኩ›› ማለቱ የተሰመረ መንገድ፣ የሚደረስበት ግብ መኖሩን ሲያመለክተን ነው፡፡
የቢዚነት ጉዳይ ግን ከዓላማ አንጻር ብቻ ሳይሆን በጊዜ አስተዳደር አንጻርም ሊታይ ይገባል፡፡ ጊዜ ከፈጣሪ የተሰጠን ሀብት ነው፡፡ ጊዜ ሀብት ከሆነ እንግዲያው እያንዳንዳችን “መጋቤ ጊዜያት” ሆነን በዚህ ሀብት ላይ ተሹመናል፡፡ የጊዜ መጋቢነት እንዴት ይከወን ስንል ባለ ሙያዎች ከሚመክሩን መካከል ሦስቱን ብቻ ልጥቀስ፡-
ጊዜዬ የት ጠፋ? ምን አደረግሁት? እያልክ የምትጠይቅ ከሆነ ሥራዬ ብለህ የዕለት ዕለት እንቅስቃሴህን ለተከታታይ ሰባት ቀናት ያደረግከውን ነገር ስም እየሰጠህ ልትጽፈው ትችላለህ፡፡ ከሳምንቱ በኋላ የጊዜ አጠቃቀምህን በዐይነቱ ስትሰድረው ጊዜህ ምን ላይ እንደዋለ የጊዜ ምጋቤ ባህርይህን ትረዳዋለህ፡፡ ያኔ ያላግባብ የባከነ ወይም በቂ ጊዜ ያልተሰጠው ምን እንደሆነ ግልጽ ይሆናል፡፡
ይህ የጊዜ ውሎ ግምጋሜ ወደ ሁለተኛው ዋና ነገር ይመራሃል ይህም ጊዜህን የሚሰርቁ የጊዜ መንታፊዎቸን ለይቶ ማወቅ ነው፡፡ ከታወቁት የጊዜ መንታፊዎች መካከል፡-
👉መወላወል (የቱን ላንሳ የቱን ልጣል)
👉ዝርክርክነት (ካርዱን የት ነበር ያደረግኩት)
👉መግቻ የሌላቸው የስልክ ጥሪዎች
👉ነገ ይደርሳል እያሉ መሳነፍ
👉ተራ/ወረፋ ጥበቃ
👉ጥድፊያ (ጥድፊያ ሲበዛ ፍጥነት ይቀንሳል ይባላል)
👉ድንገት የሚከሰቱ መስተጓጉሎች ይገኙበታል፡፡

❤8