ቅዱሳት መጻሕፍት
7.45K subscribers
1.36K photos
61 videos
332 files
804 links
በዚህ ቻናል

👉ቅዱሳት መጻሕፍት ይጠናሉ::
👉መጽሐፍ ቅዱሳዊ ትምህርቶች ይቀርባሉ::
👉 ለቅዱሳት መጽሐፍት ጥናት የሚያግዙ መጻሕፍት ይለቀቃሉ።

⭐️⭐️⭐️⭐️⭐️

@Holy_scriptures
Download Telegram
#ከተማ_ወይም_ቦታ_በቅዱሳት_መጻሕፍት

ቅፍርናሆም


#ቅፍርናሆም ( ዕብራይስጥ : כְּפַר נַחוּם፣ Kfar Nachum) "የናሆም መንደር" ወይም "የመጽናናት መንደር" ማለት ነው። "ናሆም" ማንን እንደሚያመለክት ግልጽ አይደለም። ምናልባት ከብሉይ ኪዳን የመጣው ነቢዩ ናሆም ላይሆን ይችላል ነገር ግን ስሙ አሁንም ከማጽናናት ወይም ከርህራሄ ጋር የተያያዘ ትርጉሙን ይይዛል።

ቅፍርናሆም በገሊላ ባሕር ዳር በስተሰሜን ያለች ከተማ። ክርስቶስ እየተዘዋወረ ሲሰብክ መኖሪያው በቅፍርናሆም ነበር፤ ማቴ. 4፥13-16። የዘብዴዎስና የጴጥሮስ አገር (ማር. 1፥29-31)፥ ማቴዎስም ከቅፍርናሆም ተጠራ፤ ማቴ. 9፡9። በቅፍርናሆም በአንድ መቶ አለቃ የተሠራ ምኵራብ ነበር፤ ሉቃ. 7፥1-9። ከምኵራብ አለቆች አንዱ ኢያኢሮስ ነበረ፤ ማር. 5፥22። በቅፍርናሆም ክርስቶስ ብዙ አስደናቂ ተአምራትን አደረገ (ማቴ. 8፥5-13፤ ማር. 2፥1-12፤ ዮሐ. 4፥46-54)፥ አስፈላጊ እና ውጤታማ የአሳ ማጥመጃና የንግድ ዋና ቦታ የነበረችው፣ የአህዛብ እና የአይሁድ መኖሪያ ነበር። የመጀመሪያው መቶ አመት የህዝብ ብዛት ከ፩ ሺህ በላይ አልነበሩም። ቅፍርናሆም በለማ ቦታ ተከብቦ፣ የአስፈላጊ የንግድ መንገድ የሚገኝበት ነበር። የሮሜ ወታደሮች ገንዳ መታጠቢያ እና ማከማቻ ቦታዎችን በእዚህ ገነቡ። ከጊዜ በኋላም፣ ቅፍርናሆም ተሰባበረች እናም በእዚያ የሚኖሩትም ወጥተው ሄዱ።

ታላቅ ድርጊቶች፥ ቅፍርናሆም የአዳኝ የእርሱ ከተማ ነበር ተብሎ ይታወቃል (ማቴ. 9፥1–2፤ ማር. 2፥1–5)። በእዚህ ቦታ ብዙ ተዓምራትሰራ። ለምሳሌ፣ ከመቶ አለቃ አገልጋይ (ሉቃ. 7፥1–10)፣ ከጴጥሮስ አማች (ማር. 1፥21፣ 29–31)፣ በጣራ በኩል መኝታው ከወረደው ሽባ (ማር. 2፥1–12)፣ እና እጁ ከሰለለች ሰው (ማቴ. 12፥9–13) በተጨማሪ ብዙ ሰዎችን ፈወሰ (ማር. 1፥32–34 )። በዚህም ብዙ እርኩስ መንፈሶችን አስወጣ (ማር. 1፥21–28፣ 32–34)፣ የኢያኢሮስ ሴት ልጅን ከሞት አስነሳ (ማቴ. 9፥18–19፣ 23–26፤ ማር. 5፥22-24፣ 35-43)፣ እና በቅፍርናሆም ምኩራብ የህይወት-እንጀራ የሚለውን ስብከትን ሰጠ (ዮሐ. 6፥24–59)። አዳኝ ጴጥሮስን ከገሊላ ባህር አሳ እንዲያጠምድ፣ አፉን እንዲከፍት፣ እና ቀረጥ የሚከፍልበት ሳንቲም እንዲያገኝ አዘዘው (ማቴ. 17፥24-27)። ነገር ግን የቅፍርናሆም ሰዎች አላመኑምና ክርስቶስ በቅፍርናሆም ላይ የፍርድ ትንቢት ተናገረባት፤ ማቴ. 11፥23:24። ዛሬ ሰው አይኖርባትም።



ምንጭ፦
የመጽሐፍ ቅዱስ መዝገበ ቃላት ገጽ 98፣
Elwell, W. A., & Beitzel, B. J. (1988). Baker encyclopedia of the Bible (Vol. 1, pp. 381–382). Baker Book House.
www.churchofjesuschrist.org




ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
11👍1
.       ──•◈•─────•◈•─
                          የዕለቱ ጥቅስ
        ──•◈•─────•◈•─
“ዓይኖቻቸውም ተከፈቱ።”
ማቴዎስ 9፥30



ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
10
Fruitful life
Nigusse Denano
#መጻሕፍትን_በድምጽ

📔ርዕስ፦ ፍሬያማ ሕይወት
👤ጸሐፊ፦ ጥላሁን ኃይሌ
👉ክፍል-18


ይቀጥላል...


ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
4
ብሉይ ኪዳን.zip
943.1 MB
🎧የብሉይን መጽሐፍ ቅዱስ በድምጽ


ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
5
ከሚከተሉት በቅዱሳት መጻሕፍት ከሚገኙ በሐዋርያው ጳውሎስ ከተጻፉ መጻሕፍት ውስጥ በእስር ቤት ያልተጻፈው መጽሐፍ የቱ ነው?
Anonymous Quiz
23%
ሀ. ኤፌሶን
48%
ለ. ቲቶ
13%
ሐ. ፊልጵስዩስ
16%
መ. ቆላስይስ
3
.       ──•◈•─────•◈•─
                          የዕለቱ ጥቅስ
        ──•◈•─────•◈•─
“ክርስቶስ በእጅ ወደ ተሰራች፥ የእውነተኛይቱ ምሳሌ ወደ ምትሆን ቅድስት አልገባምና፥ ነገር ግን በእግዚአብሔር ፊት ስለ እኛ አሁን ይታይ ዘንድ ወደ እርስዋ ወደ ሰማይ ገባ።”
ዕብራውያን 9፥24



ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
11❤‍🔥1
Fruitful life
Nigusse Denano
#መጻሕፍትን_በድምጽ

📔ርዕስ፦ ፍሬያማ ሕይወት
👤ጸሐፊ፦ ጥላሁን ኃይሌ
👉ክፍል-19


ይቀጥላል...


ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
አዲስ ኪዳን.zip
290.8 MB
አዲስ ኪዳን በድምፅ


ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
#የእግዚአብሔር_ቃል_ምን_ይላል?


መዝሙር 27
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
¹ እግዚአብሔር ብርሃኔና መድኃኒቴ ነው፤ የሚያስፈራኝ ማን ነው? እግዚአብሔር የሕይወቴ መታመኛዋ ነው፤ የሚያስደነግጠኝ ማን ነው?
² ክፉዎች፥ አስጨናቂዎቼ ጠላቶቼም፥ ሥጋዬን ይበሉ ዘንድ በቀረቡ ጊዜ፥ እነርሱ ተሰናከሉና ወደቁ።
³ ሠራዊትም ቢሰፍርብኝ ልቤ አይፈራም፤ ሰልፍም ቢነሣብኝ በዚህ እተማመናለሁ።
⁴ እግዚአብሔርን አንዲት ነገር ለመንሁት እርስዋንም እሻለሁ፤ በሕይወቴ ዘመን ሁሉ በእግዚአብሔር ቤት እኖር ዘንድ፥ እግዚአብሔርን ደስ የሚያሰኘውንም አይ ዘንድ፥ መቅደሱንም እመለከት ዘንድ።
⁵ በመከራዬ ቀን በድንኳኑ ሰውሮኛልና፥ በድንኳኑም መሸሸጊያ ሸሽጎኛልና፥ በዓለት ላይ ከፍ ከፍ አድርጎኛልና።
⁶ እነሆ፥ አሁን በዙሪያ ባሉ በጠላቶቼ ላይ ራሴን ከፍ ከፍ አደረገ፤ በድንኳኑም የእልልታ መሥዋዕትን ሠዋሁ፥ ለእግዚአብሔር እቀኛለሁ እዘምርለትማለሁ።
⁷ አቤቱ፥ ወደ አንተ የጮኽሁትን ቃሌን ስማኝ፤ ማረኝና አድምጠኝ።
⁸ አንተ ፊቴን እሹት ባልህ ጊዜ፦ አቤቱ፥ ፊትህን እሻለሁ ልቤ አንተን አለ።
⁹ ፊትህን ከእኔ አትሰውር፥ ተቈጥተህ ከባሪያህ ፈቀቅ አትበል፤ ረዳት ሁነኝ፥ አትጣለኝም፥ የመድኃኒቴም አምላክ ሆይ፥ አትተውኝ።
¹⁰ አባቴና እናቴ ትተውኛልና፥ እግዚአብሔር ግን ተቀበለኝ።
¹¹ አቤቱ፥ መንገድህን አስተምረኝ፥ ስለ ጠላቶቼም በቀና መንገድ ምራኝ።
¹² የሐሰት ምስክሮችና ዓመፀኞች ተነሥተውብኛልና ለጠላቶቼ ፈቃድ አትስጠኝ።
¹³ የእግዚአብሔርን ቸርነት በሕያዋን ምድር አይ ዘንድ አምናለሁ።
¹⁴ እግዚአብሔርን ተስፋ አድርግ፤ በርታ፥ ልብህም ይጽና፤ እግዚአብሔርን ተስፋ አድርግ።



ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
11👍1
Audio
👉ርዕስ፦ መጽሐፈ ኢዮብ
በባይብል ፕሮጀክት፣ በአማርኛ ቋንቋ የተዘጋጀ


ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
2
.       ──•◈•─────•◈•─
                          የዕለቱ ጥቅስ
        ──•◈•─────•◈•─
“በመከራዬ ቀን በድንኳኑ ሰውሮኛልና፥ በድንኳኑም መሸሸጊያ ሸሽጎኛልና፥ በዓለት ላይ ከፍ ከፍ አድርጎኛልና።”
መዝሙር 27፥5


ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
🔥64
Fruitful Life
Nigusse Denano
#መጻሕፍትን_በድምጽ

📔ርዕስ፦ ፍሬያማ ሕይወት
👤ጸሐፊ፦ ጥላሁን ኃይሌ
👉ክፍል-20


ይቀጥላል...


ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
3
አምላካችን ማን ነዉ?


“እረሱ (ክርስቶስ) የማይታየዉ አምላክ አምሳል ነዉ፤ ከፍጥረትም ሁሉ በፊት በኩር ነዉ፤ ሁሉ ነገር በእርሱ ተፈጥሮአል፤ በሰማይና በምድር ያሉ፣ የሚታዩና የማይታዩ፣ ዙፋናት ቢሆኑ ወይም ኀይላት፣ ገዦች ቢሆኑ ወይም ባለሥልጣናት፣ ሁሉም ነገር በእርሱና ለእርሱ ተፈጥሮአል። እርሱ ከሁሉ በፊት ነዉ፤ ሁሉ ነገር በአንድ ላይ ተያይዞ የጸናዉ በእርሱ ነዉ። እርሱ አካሉ የሆነችዉ የቤተክርስቲያን ራስ ነዉ፤ በሁሉ ነገር የበላይነት ይኖረዉ ዘንድ እርሱ የመጀመሪያ፣ ከሙታን መካከልም በኩር ነዉ።” (ቆላስያስ 1፡15-18)

እግዚአብሔር “ሕዝቤን ልቀቅ” ባለ ጊዜ ፈርኦን የተናገረዉ ሁልጊዜ ተገዳዳሪዎቻችን በህሊናችን የሚያቃጭሉት ጥያቄ ነዉ። ፈርኦን “ቃሉን እሰማ ዘንድ እስራኤልንስ እለቅቅ ዘንድ እግዚአብሔር ማን ነዉ?” ነበር ያለዉ (ዘጸ 5፡2)። ዛሬም “አምላክህ/ሽ  ማን ነዉ?” ለሚለን ቆላ 1 አስደናቂ እዉነታ ነዉ። አምላካችን ክርስቶስ ፍጥረተ ዓለሙን ካለመኖር ወደ መኖር ያመጣ ብቻ ሳይሆን አሁንም ፍጥረት ሥርዐት ይዞ እንዲቀጥል ሁሉን በአንድ ላይ አያይዞ ያስቀጥለዋል፣ ያጸናዋል። ፍጥረት ምን እንደሚያክል፣ በቢሊዮኖች የሚቆጠሩ ግዙፍ ከዋክብትና ክምችቶቻቸውም ምን እንደሚመስሉ ለማሰብ ያስቸግራል። እነኝህን ሁሉ በእጆቹ ይዞ የሚያጸናቸዉ… አምላካችን ነው (ኢሳ 40፡27-31)። ክርስቶስ የሁሉ ፈጣሪና የበላይ ነዉ።
የኛ ችግርና ተግዳሮትማ ለእርሱ እንዴት ቀላል ነዉ? ስለሆነም  አማኝ ነፍሱን 

“እረፊ፣ አትጨነቂ፣ አትታወኪ፣ ዝም ብለሽ በኃያሉ አምላክሽ ታመኚ” ይበል፡፡



ምንጭ :- mamushafenta.com




ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
14🙏1
.       ──•◈•─────•◈•─
                          የዕለቱ ጥቅስ
        ──•◈•─────•◈•─
“አንተ ግን፥ የሰው ልጅ ሆይ፥ የምነግርህን ስማ፤ እንደዚያ እንደ ዓመፀኛው ቤት ዓመፀኛ አትሁን፤ አፍህን ክፈት የምሰጥህንም ብላ።”
ሕዝቅኤል 2፥8



ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
10
Fuitful Lif
Nigusse Denano
#መጻሕፍትን_በድምጽ

📔ርዕስ፦ ፍሬያማ ሕይወት
👤ጸሐፊ፦ ጥላሁን ኃይሌ
👉ክፍል-21


ይቀጥላል...


ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
2
#እራሳችንን_እንመርምር



"ታዲያ እግዚአብሔር ጸጋውን ያበዛልናል በማለት ኃጢአት መሥራታችንን መቀጠል አለብን ማለት ነውን? እግዚአብሔርም አይበለው! ከእርሱ ጋር ሕብረት እንዲኖረን በጌታችን በኢየሱስ ስም በተጠመቅንበት ጊዜ ፥ ኃጢአት መሥራት የሚቀናው አሮጌው ባሕርያችን ከእርሱ ጋር የሞተ መሆኑን እንዴት ዘነጋችሁት?"
ሮሜ 6፥1-3 (ሕያው ቃል)



ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
14
.       ──•◈•─────•◈•─
                          የዕለቱ ጥቅስ
        ──•◈•─────•◈•─
“ከእግዚአብሔር ጋር አብረን የምንሠራ እንደ መሆናችን መጠን፣ የተቀበላችሁትን የእግዚአብሔርን ጸጋ ከንቱ እንዳታደርጉት ዐደራ እንላችኋለን።”
2ኛ ቆሮንቶስ 6፥1 (አዲሱ መ.ት)



ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
7
Fruitful life
Nigusse Denano
#መጻሕፍትን_በድምጽ

📔ርዕስ፦ ፍሬያማ ሕይወት
👤ጸሐፊ፦ ጥላሁን ኃይሌ
👉ክፍል-22 (የመጨረሻ ክፍል)


ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
5🔥1
ባለራእይነት.pdf
2.8 MB
ርዕስ፦ ባለራእይነት
ጸሐፊ፦ ወ/ዊ ጸጋአብ በቀለ



ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
👏61