ቅዱሳት መጻሕፍት
7.46K subscribers
1.36K photos
61 videos
332 files
804 links
በዚህ ቻናል

👉ቅዱሳት መጻሕፍት ይጠናሉ::
👉መጽሐፍ ቅዱሳዊ ትምህርቶች ይቀርባሉ::
👉 ለቅዱሳት መጽሐፍት ጥናት የሚያግዙ መጻሕፍት ይለቀቃሉ።

⭐️⭐️⭐️⭐️⭐️

@Holy_scriptures
Download Telegram
Fruitful Life
Nigusse Denano
#መጻሕፍትን_በድምጽ

📔ርዕስ፦ ፍሬያማ ሕይወት
👤ጸሐፊ፦ ጥላሁን ኃይሌ
👉ክፍል-14


ይቀጥላል...


ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
#እራሳችንን_እንመርምር

ክርስቲያን ሆነን ስንኖር እውነተኛ ወንድሞች እንዳሉን ሁሉ ሐሰተኛ ወንድሞችም አሉን። ሐሰተኞችን እንዴት እንለያቸው? እራሳችን ሐሰተኛ ብንሆንስ? እንዴት እንወቅ?


“ነገር ግን ባሪያዎች ሊያደርጉን በክርስቶስ ኢየሱስ ያለንን አርነታችንን ይሰልሉ ዘንድ ሾልከው በስውር ስለ ገቡ ስለ ሐሰተኞች ወንድሞች ነበረ።”
ገላትያ 2፥4


"ቀድሞውንም ቢሆን፣ 'ክርስቲያን ከእኛ ወዲያ ለአሳር ነው' ብለው የሚመጻደቁ አንዳንድ ሐሰተኞች፥ የአይሁድን ሕግና ሥርዓት እንዳለ የምንጠብቅ መሆን አለመሆናችንን ለመሰለልና በክርስቶስ ኢየሱስ ያገኘነውን ነፃነት ለመንፈግ በመካከላችን ሾልከው ባይገቡ ኖሮ፥ አገር አቋርጦ መጥቶ ማስረዳቱ ባላስፈለገን ነበር።"
ገላትያ 2፥4 (ሕያው ቃል)



ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
7🤯1
.       ──•◈•─────•◈•─
                          የዕለቱ ጥቅስ
        ──•◈•─────•◈•─
“የማታስተውሉ የገላትያ ሰዎች ሆይ፥ በዓይናችሁ ፊት ኢየሱስ ክርስቶስ እንደ ተሰቀለ ሆኖ ተሥሎ ነበር፤ ለእውነት እንዳትታዘዙ አዚም ያደረገባችሁ ማን ነው?”
ገላትያ 3፥1



ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
6🥰1
Fruitful life
Nigusse Denano
#መጻሕፍትን_በድምጽ

📔ርዕስ፦ ፍሬያማ ሕይወት
👤ጸሐፊ፦ ጥላሁን ኃይሌ
👉ክፍል-15


ይቀጥላል...


ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
3
ቅዱሳት መጻሕፍት
#እምነት                  ክፍል-11 እምነት እና ሥራ አብርሃም የተገረዘው እምነቱ ጽድቅ ሆኖ ከተቈጠረለት ከ13 ዓመታት በኋላ በመሆኑ መገረዙም ቢሆን በእግዚአብሔር ዘንድ ለመጽደቁ ምክንያት አልነበረም(ሮሜ4፥9‐12)፤ ነገር ግን ይህ መገረዙ «ሳይገረዝ በነበረው እምነት ያገኘው የጽድቅ ማኅተም» የሆነ ምልክት ወይም ማረጋገጫ ነበር (ሮሜ4፥11)፡፡ እንዲሁም ሕግ የተሰጠው ከ430 ዓመታት…
#እምነት


                 ክፍል-12


እምነት እና ሥራ


የእውነተኛ እምነት ትክክለኛ ገጽታ በጊዜውም ይሁን ቈይቶ በሥራ ሊገለጥ የሚችል መሆኑ ነው፡፡ የእስራኤል አባት በሆነው በአብርሃም እምነት የተመለከትነውም ይህንን ነው፡፡ ከአሕዛብ በሆነችው በረዓብ እምነትም የምንማረው ይህንኑ እውነታ ነው፤ ስለዚህ በመቀጠል የረዓብ ማስረጃነት ቀርቧል፤

«እንደዚሁም ጋለሞታይቱ ረዓብ ደግሞ መልእክተኛቹን ተቀብላ በሌላ መንገድ በሰደደቻቸው ጊዜ በሥራ አልጸደቀችምን?» ይላል(ቊ.25)፡፡ ከኢያሱ 2፡!፥9‐11 ባለው ክፍል ረዓብ ለመልእክተኞቹ የተናገረችውን ስናነብ እርስዋ በእስራኤል አምላክ ያመነችው እግዚአብሔር የኤርትራን ባሕር በእስራኤል ልጆች ፊት እንዳደረቀና ጠላቶቻቸውን ሁሉ እንዳጠፋላቸው እርስዋና ወገኖችዋ በሰሙ ጊዜ መሆኑን እንረዳለን፤ ይህንንም ስትገልጥ:-

«እግዚአብሔር ምድሪቱን እንደሰጣችሁ እናንተንም መፍራት በላይችን እንደወደቀ፣ በምድሪቱ የሚኖሩት ሁሉ ከፊታችሁ እንደቀለጡ አወቅሁ፤ ከግብፅ ምድር በወጣችሁ ጊዜ እግዚአብሔር የኤርትራን ባሕር ባደረቀ ጊዜ በዮርዳኖስ ማዶ በነበሩት እናንተም ፈጽማችሁ ባጠፋችኋቸው በሁለቱ በአሞራውያን ነገሥታት በሴዎንና በዐግ ያደረጋችሁትን ሰምተናል፤ ይህንንም ሰምተን ልባችን ቀለጠ» ብላለች (ቊ.9)፡፡ እንዲሁም በመቀጠል «አምላካችሁ በላይ በሰማይ በታችም በምድር እርሱ አምላክ ነውና ከእናንተ የተነሣ ከዚያ ወዲያ ማንም ነፍስ አልቀረለትም» ብላለች፤ በዚህ ቃል ረዓብ በእግዚአብሔር ያመነችው መልእክተኞቹን ተቀብላ በሌላ መንገድ ከመስደድዋ በፊት መሆኑን እናውቃለን፤ ስለሆነም በእግዚአብሔር ዘንድ እርስዋ እንደ አብርሃም ሁሉ ባመነች ጊዜ የጸደቀች ወይም ተቀባይነት ያገኘች እንደሆነች እንገነዘባለን፤ እንዲሁም ደግሞ መልእክተኞቹን ተቀብላ በሌላ መንገድ በሰደደቻቸው ጊዜ በሥራም ጸድቃለች ወይም ተረጋግጦላታል፤ በእርስዋም ሕይወት እምነት ከሥራ ጋር ያደርግ እንደነበር እናስተውላለን፤ ይህ አባባል ሥራ ከእምነት ጋር ያደርግ ነበር ከሚለው አባባል የተለየ ነው፤ በዋናነት እየተነገረለት ያለው እምነት ነው፤ እምነት ከሥራ ጋር ያደርግ ነበር ሲባል ያ እምነት በውስጡ ሰውሮ የያዘው ያልተገለጠ ሥራ እንዳለው የሚያሳይ ነው፤ ይህ እምነት ግን በውስጡ ይህን ሥራ ካልያዘ ማለትም ሥራ የተዋሐደው ካልሆነ የሞተ እምነት ነው፤ በቊ 26 ላይ ይህን በተመለከተ ሲናገር «ከነፍስ የተለየ ሥጋ የሞተ እንደሆነ እንዲሁ ደግሞ ከሥራ የተለየ እምነት የሞተ ነው» ይላል፤ በእግዚአብሔር ዘንድ መዳን በእምነት ነው ሲባልም በእንዲህ ያለ የሞተ እምነት ነው ማለት አይደለም፤ በውስጡ ሥራ በተዋሐደው እውነተኛ እምነት ነው ማለት ነው እንጂ፤ ይህ በእምነት ውስጥ በሐሳብ ደረጃ ተሰውሮ የነበረ ሥራ የሚገለጥበትን መስክ ሲያገኝ ከዚያ እምነት ውስጥ ወጥቶ በሰው ዘንድ በሚታይ መልኩ ይገለጣል፤ ነገር ግን ያን ጊዜ ያ ሰው እንደ አዲስ በእግዚአብሔር ፊት ገና መጽደቁ አይደለም፤ ቀደም ብሎ የጸደቀው ሰው አሁንም የጸደቀ መሆኑ በሥራው በሰው ፊት ይረጋገጥለታል ማለት ነው እንጂ፤ በሰማይም የሥራው ዋጋ የሆነውን የጽድቅ ብድራቱንም በቅዱሳን ሁሉ ፊት ያገኛል፡፡

በቀጣይ እምነታችንን እንዴት ከጥፋት እንጠብቅ የሚለውን እንመለከታለን


ይቀጥላል...



ምንጭ፦ 1bible.page



ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
6🥰1
.       ──•◈•─────•◈•─
                          የዕለቱ ጥቅስ
        ──•◈•─────•◈•─
“የደቀ መዛሙርቱንም ልብ በማበረታታትና በእምነታቸው ጸንተው እንዲኖሩ በመምከር፣ “ወደ እግዚአብሔር መንግሥት ለመግባት በብዙ መከራ ማለፍ አለብን” አሏቸው።”
ሐዋርያት 14፥22 (አዲሱ መ.ት)




ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
🙏32🥰1
Fruitful life
Nigusse Denano
#መጻሕፍትን_በድምጽ

📔ርዕስ፦ ፍሬያማ ሕይወት
👤ጸሐፊ፦ ጥላሁን ኃይሌ
👉ክፍል-16


ይቀጥላል...


ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
3🥰2
ቅዱሳት መጻሕፍት
የሐዋርያት የሃይማኖት መግለጫ የሐዋርያት የሃይማኖት መግለጫ እጅግ ጥንታዊ እና በሰፊው ጥቅም ላይ ከሚውሉት የክርስትና እምነት መግለጫዎች አንዱ ነው። በተለይም በምዕራቡ ክርስትና (የሮማ ካቶሊክ፣ የአንግሊካን፣ የሉተራን እና ብዙ የተሐድሶ አብያተ ክርስቲያናት)። በሐዋርያት የተጻፈ ባይሆንም ሐዋሪያዊ አስተምህሮውን ጠቅለል አድርጎ የሚገልጽ የእምነት መግለጫ ነው። ታሪካዊ ዳራ ይህ የሃይማኖት መግለጫ…
የሐዋርያት የሃይማኖት መግለጫ በኢንግሊዝኛው እንደሚከተለው ይነበባል፦

I believe in God, the Father Almighty,
Creator of heaven and earth.

I believe in Jesus Christ, His only Son, our Lord,
who was conceived by the Holy Spirit,
born of the Virgin Mary,
suffered under Pontius Pilate,
was crucified, died, and was buried;
He descended to the dead.
On the third day He rose again;
He ascended into heaven,
He is seated at the right hand of the Father,
and He will come to judge the living and the dead.

I believe in the Holy Spirit,
the holy catholic Church,
the communion of saints,
the forgiveness of sins,
the resurrection of the body,
and the life everlasting. Amen.

2. "በአንዲት ቅድስት ቤተ ክርስቲያን" (በእንግሊዝኛው “the holy catholic Church”)

ክርክር፡-

አንዳንድ ፕሮቴስታንቶች "ካቶሊክ" የሮማ ካቶሊክ ቤተ ክርስቲያንን እንደሚያመለክት በተሳሳተ መንገድ ተረድተው ይህን ሐረግ ውድቅ ያደርጉታል።

ምላሽ
“ካቶሊክ” (ከግሪክ ካቶሊኮስ) የሚለው ቃል “ዓለም አቀፋዊ” ማለት ነው። የሚያመለክተውም ያለ ጊዜ እና ቦታ ገደብ ያሉትን የአማኞችን ነው እንጂ የሮማ ካቶሊክ ቤተ ክርስቲያንን አይወክልም።

3. "በቅዱሳን አንድነት"

ክርክር፡-


አንዳንዶች ይህንን ለሞቱ ቅዱሳን ጸሎት እንደ ማድረግ ይተረጉማሉ ይህም በብዙ የፕሮቴስታንት እምነት ተከታዮች ዘንድ ተቀባይነት የለውም።

በፕሮቴስታንት አተረጓጎም ውስጥ፣ የሁሉም አማኞች (ሕያዋን እና ሙታን) በክርስቶስ ያላቸውን መንፈሳዊ አንድነት ነው የሚያመለክተው የቅዱሳንን አምልኮ ወይም ጥሪ አይደለም።
በፕሮቴስታንት አተረጓጎም ውስጥ፣ የሁሉም አማኞች (ሕያዋን እና ሙታን) በክርስቶስ ያላቸውን መንፈሳዊ አንድነት ነው የሚያመለክተው እንጂ የቅዱሳንን አምልኮ ወይም ጥሪ አይደለም።


ይቀጥላል...


ምንጭ፦

Berkhof, L. (1996). Systematic Theology. Eerdmans Publishing.
Berkhof explains that “communion of saints” refers to the spiritual bond among all Christians and does not imply communication with the dead.

Pelikan, J. (2005). Credo: Historical and Theological Guide to Creeds and Confessions of Faith in the Christian Tradition. Yale University Press


ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️👉 @TME_bible_study
8❤‍🔥3
.       ──•◈•─────•◈•─
                          የዕለቱ ጥቅስ
        ──•◈•─────•◈•─
“ኤፍሬም፦ ቀጣኸኝ እኔም እንዳልተገራ ወይፈን ተቀጣሁ፤ አንተ እግዚአብሔር አምላኬ ነህና መልሰኝ እኔም እመለሳለሁ።”
ኤርምያስ 31፥18



ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
10
fruitful life
Nigusse Denano
#መጻሕፍትን_በድምጽ

📔ርዕስ፦ ፍሬያማ ሕይወት
👤ጸሐፊ፦ ጥላሁን ኃይሌ
👉ክፍል-17


ይቀጥላል...


ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
3
የህጻናት_ጥምቀት_በሉተራን_አስተምህሮ_መሠረት.pdf
6.9 MB
ርዕስ፦ የህጻናት ጥምቀት በሉተራን አስተምህሮ መሠረት



ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️👉 @TME_bible_study
❤‍🔥32🥰1
#ከተማ_ወይም_ቦታ_በቅዱሳት_መጻሕፍት

ቅፍርናሆም


#ቅፍርናሆም ( ዕብራይስጥ : כְּפַר נַחוּם፣ Kfar Nachum) "የናሆም መንደር" ወይም "የመጽናናት መንደር" ማለት ነው። "ናሆም" ማንን እንደሚያመለክት ግልጽ አይደለም። ምናልባት ከብሉይ ኪዳን የመጣው ነቢዩ ናሆም ላይሆን ይችላል ነገር ግን ስሙ አሁንም ከማጽናናት ወይም ከርህራሄ ጋር የተያያዘ ትርጉሙን ይይዛል።

ቅፍርናሆም በገሊላ ባሕር ዳር በስተሰሜን ያለች ከተማ። ክርስቶስ እየተዘዋወረ ሲሰብክ መኖሪያው በቅፍርናሆም ነበር፤ ማቴ. 4፥13-16። የዘብዴዎስና የጴጥሮስ አገር (ማር. 1፥29-31)፥ ማቴዎስም ከቅፍርናሆም ተጠራ፤ ማቴ. 9፡9። በቅፍርናሆም በአንድ መቶ አለቃ የተሠራ ምኵራብ ነበር፤ ሉቃ. 7፥1-9። ከምኵራብ አለቆች አንዱ ኢያኢሮስ ነበረ፤ ማር. 5፥22። በቅፍርናሆም ክርስቶስ ብዙ አስደናቂ ተአምራትን አደረገ (ማቴ. 8፥5-13፤ ማር. 2፥1-12፤ ዮሐ. 4፥46-54)፥ አስፈላጊ እና ውጤታማ የአሳ ማጥመጃና የንግድ ዋና ቦታ የነበረችው፣ የአህዛብ እና የአይሁድ መኖሪያ ነበር። የመጀመሪያው መቶ አመት የህዝብ ብዛት ከ፩ ሺህ በላይ አልነበሩም። ቅፍርናሆም በለማ ቦታ ተከብቦ፣ የአስፈላጊ የንግድ መንገድ የሚገኝበት ነበር። የሮሜ ወታደሮች ገንዳ መታጠቢያ እና ማከማቻ ቦታዎችን በእዚህ ገነቡ። ከጊዜ በኋላም፣ ቅፍርናሆም ተሰባበረች እናም በእዚያ የሚኖሩትም ወጥተው ሄዱ።

ታላቅ ድርጊቶች፥ ቅፍርናሆም የአዳኝ የእርሱ ከተማ ነበር ተብሎ ይታወቃል (ማቴ. 9፥1–2፤ ማር. 2፥1–5)። በእዚህ ቦታ ብዙ ተዓምራትሰራ። ለምሳሌ፣ ከመቶ አለቃ አገልጋይ (ሉቃ. 7፥1–10)፣ ከጴጥሮስ አማች (ማር. 1፥21፣ 29–31)፣ በጣራ በኩል መኝታው ከወረደው ሽባ (ማር. 2፥1–12)፣ እና እጁ ከሰለለች ሰው (ማቴ. 12፥9–13) በተጨማሪ ብዙ ሰዎችን ፈወሰ (ማር. 1፥32–34 )። በዚህም ብዙ እርኩስ መንፈሶችን አስወጣ (ማር. 1፥21–28፣ 32–34)፣ የኢያኢሮስ ሴት ልጅን ከሞት አስነሳ (ማቴ. 9፥18–19፣ 23–26፤ ማር. 5፥22-24፣ 35-43)፣ እና በቅፍርናሆም ምኩራብ የህይወት-እንጀራ የሚለውን ስብከትን ሰጠ (ዮሐ. 6፥24–59)። አዳኝ ጴጥሮስን ከገሊላ ባህር አሳ እንዲያጠምድ፣ አፉን እንዲከፍት፣ እና ቀረጥ የሚከፍልበት ሳንቲም እንዲያገኝ አዘዘው (ማቴ. 17፥24-27)። ነገር ግን የቅፍርናሆም ሰዎች አላመኑምና ክርስቶስ በቅፍርናሆም ላይ የፍርድ ትንቢት ተናገረባት፤ ማቴ. 11፥23:24። ዛሬ ሰው አይኖርባትም።



ምንጭ፦
የመጽሐፍ ቅዱስ መዝገበ ቃላት ገጽ 98፣
Elwell, W. A., & Beitzel, B. J. (1988). Baker encyclopedia of the Bible (Vol. 1, pp. 381–382). Baker Book House.
www.churchofjesuschrist.org




ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
11👍1
.       ──•◈•─────•◈•─
                          የዕለቱ ጥቅስ
        ──•◈•─────•◈•─
“ዓይኖቻቸውም ተከፈቱ።”
ማቴዎስ 9፥30



ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
10
Fruitful life
Nigusse Denano
#መጻሕፍትን_በድምጽ

📔ርዕስ፦ ፍሬያማ ሕይወት
👤ጸሐፊ፦ ጥላሁን ኃይሌ
👉ክፍል-18


ይቀጥላል...


ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
4
ብሉይ ኪዳን.zip
943.1 MB
🎧የብሉይን መጽሐፍ ቅዱስ በድምጽ


ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
5
ከሚከተሉት በቅዱሳት መጻሕፍት ከሚገኙ በሐዋርያው ጳውሎስ ከተጻፉ መጻሕፍት ውስጥ በእስር ቤት ያልተጻፈው መጽሐፍ የቱ ነው?
Anonymous Quiz
23%
ሀ. ኤፌሶን
48%
ለ. ቲቶ
13%
ሐ. ፊልጵስዩስ
16%
መ. ቆላስይስ
3
.       ──•◈•─────•◈•─
                          የዕለቱ ጥቅስ
        ──•◈•─────•◈•─
“ክርስቶስ በእጅ ወደ ተሰራች፥ የእውነተኛይቱ ምሳሌ ወደ ምትሆን ቅድስት አልገባምና፥ ነገር ግን በእግዚአብሔር ፊት ስለ እኛ አሁን ይታይ ዘንድ ወደ እርስዋ ወደ ሰማይ ገባ።”
ዕብራውያን 9፥24



ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
11❤‍🔥1
Fruitful life
Nigusse Denano
#መጻሕፍትን_በድምጽ

📔ርዕስ፦ ፍሬያማ ሕይወት
👤ጸሐፊ፦ ጥላሁን ኃይሌ
👉ክፍል-19


ይቀጥላል...


ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
አዲስ ኪዳን.zip
290.8 MB
አዲስ ኪዳን በድምፅ


ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
#የእግዚአብሔር_ቃል_ምን_ይላል?


መዝሙር 27
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
¹ እግዚአብሔር ብርሃኔና መድኃኒቴ ነው፤ የሚያስፈራኝ ማን ነው? እግዚአብሔር የሕይወቴ መታመኛዋ ነው፤ የሚያስደነግጠኝ ማን ነው?
² ክፉዎች፥ አስጨናቂዎቼ ጠላቶቼም፥ ሥጋዬን ይበሉ ዘንድ በቀረቡ ጊዜ፥ እነርሱ ተሰናከሉና ወደቁ።
³ ሠራዊትም ቢሰፍርብኝ ልቤ አይፈራም፤ ሰልፍም ቢነሣብኝ በዚህ እተማመናለሁ።
⁴ እግዚአብሔርን አንዲት ነገር ለመንሁት እርስዋንም እሻለሁ፤ በሕይወቴ ዘመን ሁሉ በእግዚአብሔር ቤት እኖር ዘንድ፥ እግዚአብሔርን ደስ የሚያሰኘውንም አይ ዘንድ፥ መቅደሱንም እመለከት ዘንድ።
⁵ በመከራዬ ቀን በድንኳኑ ሰውሮኛልና፥ በድንኳኑም መሸሸጊያ ሸሽጎኛልና፥ በዓለት ላይ ከፍ ከፍ አድርጎኛልና።
⁶ እነሆ፥ አሁን በዙሪያ ባሉ በጠላቶቼ ላይ ራሴን ከፍ ከፍ አደረገ፤ በድንኳኑም የእልልታ መሥዋዕትን ሠዋሁ፥ ለእግዚአብሔር እቀኛለሁ እዘምርለትማለሁ።
⁷ አቤቱ፥ ወደ አንተ የጮኽሁትን ቃሌን ስማኝ፤ ማረኝና አድምጠኝ።
⁸ አንተ ፊቴን እሹት ባልህ ጊዜ፦ አቤቱ፥ ፊትህን እሻለሁ ልቤ አንተን አለ።
⁹ ፊትህን ከእኔ አትሰውር፥ ተቈጥተህ ከባሪያህ ፈቀቅ አትበል፤ ረዳት ሁነኝ፥ አትጣለኝም፥ የመድኃኒቴም አምላክ ሆይ፥ አትተውኝ።
¹⁰ አባቴና እናቴ ትተውኛልና፥ እግዚአብሔር ግን ተቀበለኝ።
¹¹ አቤቱ፥ መንገድህን አስተምረኝ፥ ስለ ጠላቶቼም በቀና መንገድ ምራኝ።
¹² የሐሰት ምስክሮችና ዓመፀኞች ተነሥተውብኛልና ለጠላቶቼ ፈቃድ አትስጠኝ።
¹³ የእግዚአብሔርን ቸርነት በሕያዋን ምድር አይ ዘንድ አምናለሁ።
¹⁴ እግዚአብሔርን ተስፋ አድርግ፤ በርታ፥ ልብህም ይጽና፤ እግዚአብሔርን ተስፋ አድርግ።



ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
11👍1