ቅዱሳት መጻሕፍት
#እምነት ክፍል-10 እምነት እና ሥራ እግዚአብሔር ይህ እምነት እውነተኛ መሆን አለመሆኑን በራሱ አምላካዊ እውቀት ያውቃል፤ ሰው ግን ይህን የሚያውቀው ሥራውን አይቶ ነው፤ እዚህ ላይ የተጠቀሰው «እምነት አለኝ» ባዩ ሰው ደግሞ ሥራ እንደሌለው ታውቋል፤ ስለዚህ በቊ.17 ላይ «ሥራ የሌለው እምነት ቢኖር በራሱ የሞተ ነው» ተብሏል፡፡ በእግዚአብሔር ዘንድ እውነተኛ እንደሆነ…
#እምነት
ክፍል-11
እምነት እና ሥራ
አብርሃም የተገረዘው እምነቱ ጽድቅ ሆኖ ከተቈጠረለት ከ13 ዓመታት በኋላ በመሆኑ መገረዙም ቢሆን በእግዚአብሔር ዘንድ ለመጽደቁ ምክንያት አልነበረም(ሮሜ4፥9‐12)፤ ነገር ግን ይህ መገረዙ «ሳይገረዝ በነበረው እምነት ያገኘው የጽድቅ ማኅተም» የሆነ ምልክት ወይም ማረጋገጫ ነበር (ሮሜ4፥11)፡፡ እንዲሁም ሕግ የተሰጠው ከ430 ዓመታት በኋላ በሙሴ ጊዜ በመሆኑ አብርሃም በዘመኑ በሕግ ሥራ ሊጸድቅ አይችልም፡፡ ስለዚህ አብርሃም የጸደቀው በሕግ ሥራ ሳይሆን በእምነት ነበር፡፡ ዛሬም ቢሆን ሰው የሚጸድቀው በሥራ ሳይሆን በእምነት እንደሆነ ለማወቅ «ለማይሠራ ኃጢአተኛውን በሚያጸድቅ ለሚያምን ሰው» እምነቱ ጽድቅ ሆኖ እንደሚቈጠርለት የተነገረውን ማስተዋል ያስፈልጋል፡፡ በተጨማሪም ጽድቅ በእምነት የመቈጠሩ ጉዳይ ለአብርሃም ብቻ ሳይሆን ለእኛም እንደሆነ መጽሐፍ ቅዱስ ሲናገር «ነገር ግን ተቈጠረለት የሚለው ቃል ስለ እርሱ ብቻ የተጻፈ አይደለም ስለእኛም ነው እንጂ፤ ስለ በደላችን አልፎ የተሰጠውን እኛን ስለማጽደቅም የተነሣውን ጌታችንን ኢየሱስን ከሙታን ባስነሳው ለምናምን ይቈጠርልን ዘንድ አለው» ይላል (ሮሜ 4፥23‐25)፡፡
በእምነት የጸደቀ ሰው ግን በሥራም ይጸድቃል፤ ይህ ማለት ግን ሥራ በእግዚአብሔር ዘንድ ያጸድቃል ከማለት በፍጹም የተለየ ነው፤ በሥራ መጽደቅ በእምነት የተገኘው ጽድቅ በሰው ዘንድ በሚታይ ሥራ መረጋጡን የሚያመለክት ነው፡፡ እንዲሁም እውነተኛ እምነትን ተከትሎ ለሚሠራው መልካም ሥራ በክርስቶስ የፍርድ ወንበር ፊት የጽድቅ አክሊልን በብድራት መቀበልን የሚያሳይ ነው፡፡ ይህም በእምነት የጸደቁ ሰዎች የሥራቸውን ዋጋ ይቀበላሉ ማለት ነው እንጂ ሰዎች የሚጸድቁት ገና ያን ጊዜ ነው ማለት አይደለም፡፡ ነገር ግን በእግዚአብሔር ፊት ሰውን የሚያጸድቀው እምነት ቀድሞውኑ ከሥራው ጋር አብሮ ያደርግ እንደነበር እንመለከታለን፤ ይህም ማለት በኋላ ይገለጥ ዘንድ ያለው ሥራ በእምነት ውስጥ ተሰውሮ እንደነበር እናያለን ማለት ነው።
«ሰው በእምነት ብቻ ሳይሆን በሥራም እንዲጸድቅ ታያላችሁ» ማለትም በሥራ ሊገለጥ በሚችል እውነተኛ እምነት የጸደቀ ሰው በኋላ በሥራውም ይጸድቃል ወይም መጽደቁ በድጋሚ ይረጋገጣል፣ ብድራትን ይቀበላል፣ ይሸለማል ማለት ነው እንጂ በእግዚአብሔር ዘንድ ለመጽደቅ ሰው በክርስቶስ ማመኑ ብቻውን በቂ ስለማይሆን ሥራም መሥራት ያስፈልገዋል ማለት አይደለም፡፡
ይቀጥላል...
ምንጭ፦ 1bible.page
ወደ ቻናሉ ለመ🀄️ላ🀄️ል፦ @Holy_scriptures

❤10👍2
. ──•◈•─────•◈•─
የዕለቱ ጥቅስ
──•◈•─────•◈•─
“እስራኤልም ብዙ ዘመን ያለ እውነተኛ አምላክ፥ ያለ አስተማሪም ካህን፥ ያለ ሕግም ይኖሩ ነበር።”
2 ዜና 15፥3

❤4👍1👏1🤔1
. ──•◈•─────•◈•─
የዕለቱ ጥቅስ
──•◈•─────•◈•─
“መልካም ምክር ከሌለ ዘንድ ሕዝብ ይወድቃል፤ በመካሮች ብዛት ግን ደኅንነት ይሆናል።”
ምሳሌ 11፥14

❤5
. ──•◈•─────•◈•─
የዕለቱ ጥቅስ
──•◈•─────•◈•─
“እንግዲህ ለንስሐ የሚገባ ፍሬ አድርጉ፤”
ማቴዎስ 3፥8
ወደ ቻናሉ ለመ🀄️ላ🀄️ል፦ @Holy_scriptures
የዕለቱ ጥቅስ
──•◈•─────•◈•─
“እንግዲህ ለንስሐ የሚገባ ፍሬ አድርጉ፤”
ማቴዎስ 3፥8
ወደ ቻናሉ ለመ🀄️ላ🀄️ል፦ @Holy_scriptures
❤7👍1🙏1
በክፉ ቀን..!
'' ስለዚህ በክፉው ቀን ለመቃወም ሁሉንም ፈጽማችሁ ለመቆም እንድትችሉ የእግዚአብሔርን እቃ ጦር ሁሉ አንሱ፡፡'' ኤፌ. 6፤10-19
"የክፉው ቀን" የቱ ነው? የክፉው ቀን መቼስ ነው?
ልክ እንደ አሁኑ ጊዜ ማለት ነው ፡፡ ብዙ ፈተና የበዛበት፣ የጸለዩት የማይሰማበት የሚመስልበት ቀን፤ ለጠላት የተፈቀደለት ቀን ይመስላል፡፡ ምናልባትም የዓለም ፍጻሜ ቀን የመጨረሻዎቹ ደቂቃ ላይ እንገኛለን፡፡ በፍጹም ያልጠበቅነው ነገር ገጥሞናል፡፡ በዚህ ክፉ ቀን የብዙዎች አቅም የሚፈተሽበት ፣ ጉልበታቸው የሚላላበት፣ እምነታቸውን የሚፈትን ነገር የሚገጥምበት ... ጊዜ ነው፡፡
በሕይወት ያልታሰበ ነገር ሲገጥም ያስደነግጣል፤ ቢሆንም የመጨረሻው ዘመን ባህሪ በመሆኑ ልንታገስ ደግሞ ይገባል፡፡ ሐዋርያው ጳውሎስ ለልጁ ለጢሞቴዎስ እንደጻፈለት '' ነገር ግን በመጨረሻ ቀን የሚያስጨንቅ ዘመን እንዲመጣ ይህን እወቅ ሰዎች ራሳቸውን የሚወዱ ይሆናሉና ፣ገንዘብን የሚወዱ፣ ትምክህተኞች፣ ትዕቢተኞች፣ ተሳዳቢዎች፣ ለወላጆቻቸው የማይታዘዙ፣ የማያመሰግኑ፣ ቅድስና የሌላቸው፣ ፍቅር የሌላቸው፣ ዕርቅን የማይሰሙ፣ ሐሜተኞች፣ ራሳቸውን የማይገዙ፣ ጨካኞች፣ መልካም የሆነውን የማይወዱ፣ ከዳተኞች፤ ችኩሎች፣ በትዕቢት የተነፉ፣ ከእግዚአብሔር ይልቅ ተድላን የሚወዱ፣ ይሆናሉ፤ የአምልኮት መልክ አላቸው ኀይሉን ግን ክደዋል ከእነዚህ ደግሞ ራቅ፡፡" 2ኛ ጢሞ.3፤1-5
አንዳንዱ ነገር ለምን እንደሆነብን እና እንደሚሆን ላይገባን ይችላል፡፡ አንገታቸውን በሰይፍ የሚቀሉ ሰዎች ብዛት፣ በህክምና ስህተት ያሳደጉዋቸውን ወላጆች የሚያጡ ሰዎች ብዛት፣ ጽኑ ወዳጅነት ወደ ጠላትነት መቀየር፣ ልጆችን በተለያየ አደጋ ማጣት፣ ክፉ ዘዴኛነት ፣ ብልጠት፣ ራስ ወዳድነት፣ ማታለል አስገራሚ ጭካኔዎች ሲሆኑ፤ ለምን ? እንዴት ማለታችን አልቀረም፡፡ ጌታ የት ሄዶ ነው ይህ ሁሉ የሚሆንብን ትሉ ይሆናል፡፡
የብሉይ ኪዳን የመጨረሻው ነብይ መጥምቁ ዮሐንስ እንዲህ ዓይነት ጥያቄ ተፈጥሮበት ነበረ '' የምትመጣው መሲህ አንተ ነህ ወይስ ሌላ እንጠብቅ ?'' ብሎ ወደ ኢየሱስ መልዕክተኞችን ላከ፡፡ወንጀል ሳይሰራ እስር ቤት መግባቱ ፣ በዚህም ላይ ብዙ የመሰከረለት ብርቱው ኢየሱስ በርሱ ጉዳይ ጣልቃ ገብቶ ፣ አልያም አንዳች ተአምራት ሰርቶ እርሱን ከእስር አለማስፈታቱ አደናግሮት ይሆናል፤ ነገር ግን ከዚህም የከፋ ሆነ፡፡ በእስራቱ ጊዜ ዝም ማለቱ ሲገርመን ጭራሽ በሔሮደስ ልደት ላይ ለዘፈነች አንዲት ወጣት ብላቴና ጥያቄ መሰረት አንገቱ ተቆርጦ በወጪት ቀረበ፡፡ ጌታስ? ዝም! በቃ ዝም!
አንዳንዱ ጉዳይ ከእኛ አዕምሮ በላይ ነው፡፡ ምናልባት ከጌታ ጋር መግባባት ስለማንችል ይሆን ዝም የሚለን? እስጢፋኖስን በድንጋይ ወግረው ሲገድሉት ሁሉን የሚችለው ጌታ በዙፋኑ ላይ ቆሞ እያየው ነበር፤ ለምን እንዳላስጣለው አይታወቅም፣ የታመነው ምስክሩ አንቲጳስ ሲገደል ጌታ ጣልቃ አልገባም ፣ ሐዋርያቱ በዘይት ተጠብሰው ሲሞቱ፣ ህዝብ በተሰበሰበበት አናብስት ቦጫጭቀው ሲገድሉዋቸው የጠራቸው ጌታ በዙፋኑ ላይ ነበር፡፡ ለአንዳንዱ ጥያቄ መልስ በእጃችን የለም፡፡ አንድ የእግዚአብሔር ሰው እንዳሉት በፊሊፒንስ የጭቃ ጎርፍ 250 ህጻናትን ለምን ከድኖ እንደገደለ አናውቅም፡፡ በቅርብ ጊዜ አንድ የምታሳሳ ወጣት ከሲያትል ለሚሽን ጉዞ ወደ ህንድ ሄዳ በተመሳሳይ ለአገልግሎት ወደ ኢትዮጵያ የሄደው መጋቢ አባት ከጥቂት ቀናት በሁዋላ ተጠርቶ የመጣው ፡ ልጅህ ድንገት ሞታለች ተብሎ ተረድቶ ነበር፡፡ በጣም አሳዛኝ ነበረ፡፡ በሌላ ጊዜ አንድ ዘማሪት እህት እናቱዋን በሞት ያጣችው ኦፕራሲዎን ልታስደርጋቸው ወስዳ በወቅቱ ሐኪሞቹ መቀስና ሌሎች ነገሮች ሆዳቸው ውስጥ ረስተው ስለ ሰፉአቸው ነበር፡ ነገሩ ኢንፌክሽን ፈጥሮባቸው ዳግመኛ ሲደረጉ እንደሞቱ ነው ለቅሶ ስደርስ የነገረችኝ፤
ወገኖች ለእኛ የሚበጀን ወደ እግዚአብሔር መቅረብ ነው ፤ ጥያቄያችን ባይመለስም እናመልከዋለን ፣እንወደዋለን፡፡ እንደዚህ የመሰሉ ቀናትን ልናሸንፍ / ልንቋቋም / እንችላለን ፤የምንችለው ግን የእግዚአብሔርን ዕቃ ጦር በመልበስ / በማንሳት/ ነው፡፡ መሳሪያው ሰው ሰራሽ መሳሪያ ሳይሆን የእግዚአብሔር ዕቃ ጦር ይለዋል፡፡ እግዚአብሔር ለዚህ ክፉ ጊዜ እንዲሆነን ያዘጋጀልን መከላከያ እና ማሸነፊያ ዕቃ ጦር ነው፡፡ ቢያንስ ስድስት ነገሮች ናቸው ፤ቀጥለን እናያቸዋለን፡-
1- የእምነት መታጠቂያ- ወገባችን ላይ
2- የጽድቅ ጥሩር- ደረታችን አካባቢ
3- የሰላም ወንጌል- እግሮቻችን ላይ
4- የእምነት ጋሻ- በአንደኛው እጃችና ላይ
5- የመዳን ራስ ቁር- በጭንቅላታችን ላይ የሚደረግ
6- የመንፈስ ሰይፍ /የእግዚአብሔር ቃል ነው/- በቀኝ እጃችን ይዘን የምናጠቃበት ነው፡፡
ከራስ እስከ እግራችን ድረስ መሸፈን ያስፈለገን ምክንያት ጠላት እኛን ለመጉዳት ወይም ለመግደል ከጭንቅላታችን ጀምሮ ወርውሮ ስለሚሞክረን ነው፡፡ መዳኑ አስተማማኝ የሆነን ክርስቲያን ጭንቅላቱን መትቶ ሊጎዳው አይችልም፡፡ ነገር ግን ደረቱን በጥሩር ካልታጠቀ ማለትም ጽድቅ ላይ ገና የሚያመቻምች ሆኖ ካገኘው ይጎዳዋል፡፡ ነገር ግን እርሱም ከተሸፈነበት ቢያንስ እግሩን ስበሩት ብሎ መልዕክተኛ ይልካል:: ይህን ጊዜ ጠንካራ የወንጌል ከስክስ ያላደረገ ሆኖ ከተገኘ ባይሞትም እንኩዋ ዘመኑን ሁሉ በመንፈስ እያነከሰ ይኖራል ስለዚህ ሙሉውን ትጥቅ መታጠቅና መመላለስ አለብን፡፡ እንደሚታወቀው ሰይጣን ትንሽ ቀዳዳ ፈልጎ ነው የሚያጠቃን ፤ያልተሸፈነ አካላችንን ፈትሸን እንልበስ /እንታጠቅ/፡፡
የእስራኤል ንጉስ አክአብ የሞተው በጥሩርና በጥሩር መጋጠሚያ በኩል ከጠላት ወገን በተወረወረ ቀስት ተወግቶ ነው፡፡ ምናልባት ሁሉን ታጥቆ ነበር፤ ይሁንና መቀነት ግን አላደረገም እንደማለት ነው፡፡ ምንም እንኩዋ በእርሱ ሞት ላይ ፍርድ ከእግዚአብሔር ዘንድ የወጣም ቢሆን፡፡ጥቃት የደረሰበትና ለሞት የበቃው ግን በተገኘው ክፍተት በኩል ነበር፡፡
ወገኖች ሙሉ የእግዚአብሔርን ትጥቅ ታጥቀን በዚህ ዘመን እንድንኖር አሳስባችሁዋለሁ! እስቲ የላሉትን ጠበቅ እናድርጋቸው፤ ከትናንሽ ጥያቄዎቻችን እንውጣና ኩርፊያውን ትተን በእግዚአብሔር ፊት በጽድቅ ፣ በእውነት እንመላለስ!! የሚመጣልን መድኃኒት እርሱም ክርስቶስ ወደ ልዩ እረፍት ቦታ ይወስደናል፡፡ ብንጸና እንወርሳለን፡፡ በነገር ሁሉ ጌታ ከሁላችን ጋር ይሁን ፡፡ አሜን!!!
ምንጭ:- lemekeru.com

❤17👍3🥰1
የፍርድ መንፈስ.PDF
3.2 MB
📙 ርዕስ:- "የፍርድ መንፈስ"
👤 ጸሐፊ:- ዎች ማን ኒ
👥 ተርጓሚዎች:- ጌዲዮን ኃይሉ እና ይድነቃቸው ወርቁ
📄 የገጽ ብዛት:- 153
📠 አሳታሚ:- ራዕይ
ወደ ቻናሉ ለመ🀄️ላ🀄️ል፦ @Holy_scriptures
👤 ጸሐፊ:- ዎች ማን ኒ
👥 ተርጓሚዎች:- ጌዲዮን ኃይሉ እና ይድነቃቸው ወርቁ
📄 የገጽ ብዛት:- 153
📠 አሳታሚ:- ራዕይ
ወደ ቻናሉ ለመ🀄️ላ🀄️ል፦ @Holy_scriptures
❤3
. ──•◈•─────•◈•─
የዕለቱ ጥቅስ
──•◈•─────•◈•─
“እናንተንም ነውርና ነቀፋ የሌላችሁና ቅዱሳን አድርጎ በእርሱ ፊት ያቀርባችሁ ዘንድ፥ በፊት የተለያችሁትን ክፉ ሥራችሁንም በማድረግ በአሳባችሁ ጠላቶች የነበራችሁትን አሁን በሥጋው ሰውነት በሞቱ በኩል አስታረቃችሁ።”
ቆላስይስ 1፥21-22

❤9❤🔥3
. ──•◈•─────•◈•─
የዕለቱ ጥቅስ
──•◈•─────•◈•─
“የሰላምም ጌታ ራሱ በሁሉ መንገድ ዘወትር ሰላምን ይስጣችሁ። ጌታ ከሁላችሁ ጋር ይሁን።”
2ኛ ተሰሎንቄ 3፥16

❤10
የንስሃ ጥቅም
ዴሪክ ፕሪንስ የተባሉ የመፅሃፍ ቅዱስ አስተማሪ በቤተክርስትያን ውስጥ ትልቅ ችግርን የሚፈጥሩ ሰዎች ንስሃ ያልገቡ ሰዎች ናቸው ይላሉ፡፡
ሰው ህይወቱ የሚለወጠው ንስሃ በገባው መጠን ብቻ ነው ፡፡
አንዳንድ ሰው ንስሃን አስፈላጊነት ስለማይረዳ በንስሃ የሚፈታውን ችግሩን በሌላ ነገር ለመፍታት ሲሞክር ይንከራተታል፡፡ አንዳንድ ሰው ራሱን አዋርዶ ንስሃ ከሚገባ ይልቅ በመልካም ስራ የህይወቱን ችግር ሊያሸንፍ ሲጣጣር ህይወቱን ይገፋል፡፡ እግዚአብሄርን የሚያስድስተው ንስሃ የሚገባ ሰው ህይወት ነው፡፡ ንስሃ ያልገባ የማንኛውም ሰው መልካም ስራ እግዚአብሄርን አያስደስተውም፡፡
"እላችኋለሁ፥ እንዲሁ ንስሐ በሚገባ በአንድ ኃጢአተኛ በእግዚአብሔር መላእክት ፊት ደስታ ይሆናል።"
(ሉቃስ 15፡10)
አንዳንድ ሰው ደግሞ ይቅርታ ነፃ እንደሆነ ስለማይረዳ ንስሃ ከመግባትና መንገዱን ከመቀየር ይልቅ ለክፉ ስራው በመልካም ስራ ለመክፈል ይፈልጋል፡፡ ለክፉ ስራ የሚከፈል ምንም አይነት መልካም ስራ የለም፡፡
"ሁላችን እንደ ርኩስ ሰው ሆነናል፥ ጽድቃችንም ሁሉ እንደ መርገም ጨርቅ ነው፤ ሁላችንም እንደ ቅጠል ረግፈናል፥ በደላችንም እንደ ነፋስ ወስዶናል።"
(ኢሳ 64፡6)
ሃጢያትን የሰራ ሰው ያሳዘነው እግዚአብሄርን ነው፡፡ እግዚአብሄር ደግሞ ንስሃን እንጂ መማለጃን አይቀበልም፡፡ ክፉ ስራ ሰርተን እግዚአብሄርን በመልካም ስራ አናታልለውም፡፡ (ዘዳግም 10፡16-17)
ንስሃ ያልገባ ሰው መልካም ስራ በእግዚአብሄር ፊት እንደመርገም ጨርቅ አፀያፊ ነው፡፡
ንስሃ መግባት ማለት ደግሞ ማልቀስ ማለት አይደለም፡፡ ንስሃ መግባት ማለት ደግሞ በሃጢያት ማዘን ማለት ብቻ አይደለም፡፡ ንስሃ መግባት ማለት እግዚአብሄርን የሚያሳዝን የተሳሳተ መንገድ መሆኑን አውቆ ቀኝ ኋላ ዙር ብሎ ወደኋላ መመለስ ነው፡፡ ንስሃ ሃሳብን መለወጥ ነው፡፡ ንስሃ የህይወት ለውጥ ነው፡፡ (ሮሜ 12፡2)
እግዚአብሄር የሚቀበለው ንስሃ የገባ ሰውን የንስሃን ፍሬ ነው፡፡ ሰው ንስሃ ከገባ በኋላ መመለሱን የሚያሳየው በመልካም ስራ ነው፡፡
ከንስሃ ውጭ ሌላ የተሳሳተን ሰው ህይወት የሚለውጥ ምንም ነገር የለም፡፡ የሰው ህይወት የሚያርፈው በንስሃ ነው፡፡
"የእስራኤል ቅዱስ፥ ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላልና፦ በመመለስና በማረፍ ትድናላችሁ፤ በጸጥታና በመታመን ኃይል ይሆንላችኋል፤ እናንተም እንቢ አላችሁ፥"
(ኢሳይያስ 30፡15)
ተመሳሳይ ነገር እያደረግን የሕይወት ለውጥ መጠበቅ ሞኝነት ነው፡፡ አዲሱን ወይን ጠጅ በአሮጌ አቁማዳ እንደማያደርጉት ሁሉ ህይወታችን በአዲስ መንገድ እንዲጀመር አሮጌው መተው አለበት። (ማቴ. 9፡17)
ስኬትና ክንውን ያለው ሃጢያትን በመደበቅ ሳይሆን መተው ላይ ነው፡፡ የምንነፃው ስለሃጢያታችንን ንስሃ ስንገባ ብቻ ነው፡፡
"ኃጢአቱን የሚሰውር አይለማም፤ የሚናዘዝባትና የሚተዋት ግን ምሕረትን ያገኛል።" (ምሳሌ 28፡13)
"በኃጢአታችን ብንናዘዝ ኃጢአታችንን ይቅር ሊለን ከዓመፃም ሁሉ ሊያነጻን የታመነና ጻድቅ ነው።" (1ኛ ዮሐንስ 1፡9)
ንስሃ ሃጢያትን ነቅሎ የመጣል ታላቅ ሃይል አለው፡፡ ንስሃ ህይወትን የመለወጥ እና የማደስ ሃይል አለው፡፡
"እንግዲህ ኀጢአታችሁ እንዲደመሰስ ንስሓ ግቡ፤ ከመንገዳችሁም ተመለሱ፤ ከጌታም ዘንድ የመታደስ ዘመን ይመጣላችኋል፤ ደግሞም አስቀድሞ ለእናንተ የተመደበውን ክርስቶስን እርሱም ኢየሱስን ይልክላችኋል።
ሐዋ 3፡19-20 (አዲሱ መደበኛ ትርጉም)
ምንጭ:- heroaw.wordpress.com

❤11👍3
. ──•◈•─────•◈•─
የዕለቱ ጥቅስ
──•◈•─────•◈•─
“ዳሩ ግን ባለ ጠጎች ሊሆኑ የሚፈልጉ በጥፋትና በመፍረስ ሰዎችን በሚያሰጥምና በሚያሰንፍ በሚጎዳም በብዙ ምኞትና በፈተና በወጥመድም ይወድቃሉ።”
1ኛ ጢሞቴዎስ 6፥9
ወደ ቻናሉ ለመ🀄️ላ🀄️ል፦ @Holy_scriptures
የዕለቱ ጥቅስ
──•◈•─────•◈•─
“ዳሩ ግን ባለ ጠጎች ሊሆኑ የሚፈልጉ በጥፋትና በመፍረስ ሰዎችን በሚያሰጥምና በሚያሰንፍ በሚጎዳም በብዙ ምኞትና በፈተና በወጥመድም ይወድቃሉ።”
1ኛ ጢሞቴዎስ 6፥9
ወደ ቻናሉ ለመ🀄️ላ🀄️ል፦ @Holy_scriptures
❤10
#እራሳችንን_እንመርምር
ክርስቲያን ሆነን ስንኖር እውነተኛ ወንድሞች እንዳሉን ሁሉ ሐሰተኛ ወንድሞችም አሉን። ሐሰተኞችን እንዴት እንለያቸው? እራሳችን ሐሰተኛ ብንሆንስ? እንዴት እንወቅ?
“ነገር ግን ባሪያዎች ሊያደርጉን በክርስቶስ ኢየሱስ ያለንን አርነታችንን ይሰልሉ ዘንድ ሾልከው በስውር ስለ ገቡ ስለ ሐሰተኞች ወንድሞች ነበረ።”
ገላትያ 2፥4
"ቀድሞውንም ቢሆን፣ 'ክርስቲያን ከእኛ ወዲያ ለአሳር ነው' ብለው የሚመጻደቁ አንዳንድ ሐሰተኞች፥ የአይሁድን ሕግና ሥርዓት እንዳለ የምንጠብቅ መሆን አለመሆናችንን ለመሰለልና በክርስቶስ ኢየሱስ ያገኘነውን ነፃነት ለመንፈግ በመካከላችን ሾልከው ባይገቡ ኖሮ፥ አገር አቋርጦ መጥቶ ማስረዳቱ ባላስፈለገን ነበር።"
ገላትያ 2፥4 (ሕያው ቃል)

❤7🤯1