ቅዱሳት መጻሕፍት
7.46K subscribers
1.36K photos
61 videos
332 files
802 links
በዚህ ቻናል

👉ቅዱሳት መጻሕፍት ይጠናሉ::
👉መጽሐፍ ቅዱሳዊ ትምህርቶች ይቀርባሉ::
👉 ለቅዱሳት መጽሐፍት ጥናት የሚያግዙ መጻሕፍት ይለቀቃሉ።

⭐️⭐️⭐️⭐️⭐️

@Holy_scriptures
Download Telegram
Friutful Life
Nigusse Denano
#መጻሕፍትን_በድምጽ

📔ርዕስ፦ ፍሬያማ ሕይወት
👤ጸሐፊ፦ ጥላሁን ኃይሌ
👉ክፍል-6


ይቀጥላል...


ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
2
ሰባቱ ኢየሱስ ክርስቶስ በዮሐንስ ወንጌል "እኔ ...ነኝ" ያላቸው ቦታዎች



1. የሕይወት እንጀራ እኔ ነኝ

“ኢየሱስም እንዲህ አላቸው፦ የሕይወት እንጀራ እኔ ነኝ፤ ወደ እኔ የሚመጣ ከቶ አይራብም በእኔ የሚያምንም ሁልጊዜ ከቶ አይጠማም።”
                ዮሐንስ 6፥35


2. እኔ የዓለም ብርሃን ነኝ

“ደግሞም ኢየሱስ፦ እኔ የዓለም ብርሃን ነኝ፤ የሚከተለኝ የሕይወት ብርሃን ይሆንለታል እንጂ በጨለማ አይመላለስም ብሎ ተናገራቸው።”
                  ዮሐንስ 8፥12


3. እኔ የበጎች በር ነኝ

“ኢየሱስም ደግሞ አላቸው፦ እውነት እውነት እላችኋለሁ፥ እኔ የበጎች በር ነኝ።”
                 ዮሐንስ 10፥7


4. መልካም እረኛ እኔ ነኝ

“መልካም እረኛ እኔ ነኝ። መልካም እረኛ ነፍሱን ስለ በጎቹ ያኖራል።”
            ዮሐንስ 10፥11


5. ትንሣኤና ሕይወት እኔ ነኝ

“ኢየሱስም፦ ትንሣኤና ሕይወት እኔ ነኝ፤ የሚያምንብኝ ቢሞት እንኳ ሕያው ይሆናል፤”
             ዮሐንስ 11፥25


6. እኔ መንገድና እውነት ሕይወትም ነኝ

“ኢየሱስም፦ እኔ መንገድና እውነት ሕይወትም ነኝ፤ በእኔ በቀር ወደ አብ የሚመጣ የለም።”
                     ዮሐንስ 14፥6


7. እውነተኛ የወይን ግንድ እኔ ነኝ

“እውነተኛ የወይን ግንድ እኔ ነኝ፤ ገበሬውም አባቴ ነው።”
                     ዮሐንስ 15፥1





ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
10👍5
.       ──•◈•─────•◈•─
                          የዕለቱ ጥቅስ
        ──•◈•─────•◈•─
“አንተ በደልን የማትወድድ አምላክ ነህና፤ ክፉ ከአንተ ጋር አያድርም።”
መዝሙር 5፥4



ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
3🔥3
Fruitful Life
Nigusse Denano
#መጻሕፍትን_በድምጽ

📔ርዕስ፦ ፍሬያማ ሕይወት
👤ጸሐፊ፦ ጥላሁን ኃይሌ
👉ክፍል-7


ይቀጥላል...


ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
1
የሐዋርያት የሃይማኖት መግለጫ


የሐዋርያት የሃይማኖት መግለጫ እጅግ ጥንታዊ እና በሰፊው ጥቅም ላይ ከሚውሉት የክርስትና እምነት መግለጫዎች አንዱ ነው። በተለይም በምዕራቡ ክርስትና (የሮማ ካቶሊክ፣ የአንግሊካን፣ የሉተራን እና ብዙ የተሐድሶ አብያተ ክርስቲያናት)። በሐዋርያት የተጻፈ ባይሆንም ሐዋሪያዊ አስተምህሮውን ጠቅለል አድርጎ የሚገልጽ የእምነት መግለጫ ነው።

ታሪካዊ ዳራ

ይህ የሃይማኖት መግለጫ በ 2ኛው እና በ 9ኛው ክፍለ ዘመን መካከል የተጻፈ እንደሆነ ይገመታል። ነገር ግን አሁን ያለው ቅርፅ ይዟል ተብሎ የሚታመነው በ 8ኛው ክፍለ ዘመን ነው። ይህ የሃይማኖት መግለጫም የተዘጋጀው ለጥምቀት፣ ለክርስትና ትምህርት እና በአምልኮ ወቅት ጥቅም ላይ እንዲውል የክርስትና እምነት ማጠቃለያ ሆኖ የቀረበ ነው።

የዚህ የሃይማኖት መግለጫ አወዛጋቢ ሐረጎች

1. “ወደ ሲኦል ወረደ”

ይህ ከተለያዩ ትርጓሜዎች ጋር በጣም አከራካሪ ከሆነ ክፍል ውስጥ አንዱ ነው።

ሀ. የሐረጉ የመጀመሪያ ወይም የጥንቱ እይታ (ባህላዊ ትርጓሜ)፡-

ጌታችን እና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ወደ ሲኦል ወረደ፤ ሲኦል የሙታን ቦታ ነው። ዓላማውም በሞት ላይ ድልን ማወጅ ወይም ከትንሣኤው በፊት የሞቱትን ጻድቃን ነጻ ማውጣት ነው።

ለዚህ አመለካከት የሚጠቀሰው የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅስ፦
“በእርሱም ደግሞ ሄዶ በወኅኒ ለነበሩ ነፍሳት ሰበከላቸው፤”
1ኛ ጴጥሮስ 3፥19

“ወደ ምድር ታችኛ ክፍል ደግሞ ወረደ ማለት ካልሆነ፥ ይህ ወጣ ማለትስ ምን ማለት ነው?”
ኤፌሶን 4፥9

ለ. ዘይቤያዊ እይታ፡-

“ሲኦል” ማለት ኢየሱስ የሞትን ጥልቀት፣ ከእግዚአብሔር መለየቱን ወይም መከራን መቀበሉን ያመለክታል።

ሉተር እና ካልቪን የተለያዩ ትርጓሜዎች ነበሯቸው።
👉ሉተር የክርስቶስን መውረድ እንደ አሸናፊነት ድል አድርጎ ይቆጥር ነበር።
👉ካልቪን የክርስቶስን የመስቀል ላይ መንፈሳዊ ስቃይ እንጂ የቁልቁለት መውረድን አይደለም ብሎ ያምን ነበር።

ሐ. በዚህ ሐረግ ላይ ዘመናዊው ማስተካከያ

አንዳንድ አብያተ ክርስቲያናት ሐረጉን ያስወግዱታል ወይም ቀየር አድርገው ይጠቀሙታል።

ለምሳሌ፡- “ወደ ሞት በወረደ” (በአንግሊካን ወይም በዘመናዊ ፕሮቴስታንት አጠቃቀም የተለመደ ነው)።
ይህ አገላለጽ "ሲኦል" ተብሎ ከተገለጸው ቃል ጋር የተከሰተውን ግራ መጋባትን ያስወግዳል።


ይቀጥላል...



ምንጭ፦
González, J. L. (2010). The story of Christianity: Volume 1: The early church to the dawn of the Reformation (Rev. ed.). HarperOne.

Kelly, J. N. D. (1972). Early Christian creeds (3rd ed.). Longman.

Pelikan, J. (1971). The Christian tradition: A history of the development of doctrine (Vol. 1: The emergence of the Catholic tradition, 100–600). University of Chicago Press.

Schaff, P. (1885). The creeds of Christendom, with a history and critical notes (Vol. 1–3). Harper & Brothers.



ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️👉 @TME_bible_study
8🔥1
#እራሳችንን_እንመርምር

እንደ አማኝ፣ በዚህ ምድር ላይም እንደሚኖር ሰው ነገሮችን በልክ ማድረግ ላይ እንዴት ነን?

“አንተ ግን ነገርን ሁሉ በልክ አድርግ”
2ኛ ጢሞቴዎስ 4፥5



ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
5👍1
.       ──•◈•─────•◈•─
                          የዕለቱ ጥቅስ
        ──•◈•─────•◈•─
“በይሁዳም ሁሉና በገሊላ በሰማርያም የነበሩት አብያተ ክርስቲያናት በሰላም ኖሩ ታነጹም፤ በእግዚአብሔርም ፍርሃትና በመንፈስ ቅዱስ መጽናናት እየሄዱ ይበዙ ነበር።”
ሐዋርያት 9፥31



ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
11
Friutful Life
Nigusse Denano
#መጻሕፍትን_በድምጽ

📔ርዕስ፦ ፍሬያማ ሕይወት
👤ጸሐፊ፦ ጥላሁን ኃይሌ
👉ክፍል-8


ይቀጥላል...


ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
👏1
ቅዱሳት መጻሕፍት
#እምነት                  ክፍል-10 እምነት እና ሥራ እግዚአብሔር ይህ እምነት እውነተኛ መሆን አለመሆኑን በራሱ አምላካዊ እውቀት ያውቃል፤ ሰው ግን ይህን የሚያውቀው ሥራውን አይቶ ነው፤ እዚህ ላይ የተጠቀሰው «እምነት አለኝ» ባዩ ሰው ደግሞ ሥራ እንደሌለው ታውቋል፤ ስለዚህ በቊ.17 ላይ «ሥራ የሌለው እምነት ቢኖር በራሱ የሞተ ነው» ተብሏል፡፡ በእግዚአብሔር ዘንድ እውነተኛ እንደሆነ…
#እምነት


                 ክፍል-11


እምነት እና ሥራ

አብርሃም የተገረዘው እምነቱ ጽድቅ ሆኖ ከተቈጠረለት ከ13 ዓመታት በኋላ በመሆኑ መገረዙም ቢሆን በእግዚአብሔር ዘንድ ለመጽደቁ ምክንያት አልነበረም(ሮሜ4፥9‐12)፤ ነገር ግን ይህ መገረዙ «ሳይገረዝ በነበረው እምነት ያገኘው የጽድቅ ማኅተም» የሆነ ምልክት ወይም ማረጋገጫ ነበር (ሮሜ4፥11)፡፡ እንዲሁም ሕግ የተሰጠው ከ430 ዓመታት በኋላ በሙሴ ጊዜ በመሆኑ አብርሃም በዘመኑ በሕግ ሥራ ሊጸድቅ አይችልም፡፡ ስለዚህ አብርሃም የጸደቀው በሕግ ሥራ ሳይሆን በእምነት ነበር፡፡ ዛሬም ቢሆን ሰው የሚጸድቀው በሥራ ሳይሆን በእምነት እንደሆነ ለማወቅ «ለማይሠራ ኃጢአተኛውን በሚያጸድቅ ለሚያምን ሰው» እምነቱ ጽድቅ ሆኖ እንደሚቈጠርለት የተነገረውን ማስተዋል ያስፈልጋል፡፡ በተጨማሪም ጽድቅ በእምነት የመቈጠሩ ጉዳይ ለአብርሃም ብቻ ሳይሆን ለእኛም እንደሆነ መጽሐፍ ቅዱስ ሲናገር «ነገር ግን ተቈጠረለት የሚለው ቃል ስለ እርሱ ብቻ የተጻፈ አይደለም ስለእኛም ነው እንጂ፤ ስለ በደላችን አልፎ የተሰጠውን እኛን ስለማጽደቅም የተነሣውን ጌታችንን ኢየሱስን ከሙታን ባስነሳው ለምናምን ይቈጠርልን ዘንድ አለው» ይላል (ሮሜ 4፥23‐25)፡፡

በእምነት የጸደቀ ሰው ግን በሥራም ይጸድቃል፤ ይህ ማለት ግን ሥራ በእግዚአብሔር ዘንድ ያጸድቃል ከማለት በፍጹም የተለየ ነው፤ በሥራ መጽደቅ በእምነት የተገኘው ጽድቅ በሰው ዘንድ በሚታይ ሥራ መረጋጡን የሚያመለክት ነው፡፡ እንዲሁም እውነተኛ እምነትን ተከትሎ ለሚሠራው መልካም ሥራ በክርስቶስ የፍርድ ወንበር ፊት የጽድቅ አክሊልን በብድራት መቀበልን የሚያሳይ ነው፡፡ ይህም በእምነት የጸደቁ ሰዎች የሥራቸውን ዋጋ ይቀበላሉ ማለት ነው እንጂ ሰዎች የሚጸድቁት ገና ያን ጊዜ ነው ማለት አይደለም፡፡ ነገር ግን በእግዚአብሔር ፊት ሰውን የሚያጸድቀው እምነት ቀድሞውኑ ከሥራው ጋር አብሮ ያደርግ እንደነበር እንመለከታለን፤ ይህም ማለት በኋላ ይገለጥ ዘንድ ያለው ሥራ በእምነት ውስጥ ተሰውሮ እንደነበር እናያለን ማለት ነው።

«ሰው በእምነት ብቻ ሳይሆን በሥራም እንዲጸድቅ ታያላችሁ» ማለትም በሥራ ሊገለጥ በሚችል እውነተኛ እምነት የጸደቀ ሰው በኋላ በሥራውም ይጸድቃል ወይም መጽደቁ በድጋሚ ይረጋገጣል፣ ብድራትን ይቀበላል፣ ይሸለማል ማለት ነው እንጂ በእግዚአብሔር ዘንድ ለመጽደቅ ሰው በክርስቶስ ማመኑ ብቻውን በቂ ስለማይሆን ሥራም መሥራት ያስፈልገዋል ማለት አይደለም፡፡


ይቀጥላል...


ምንጭ፦ 1bible.page




ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
10👍2
.       ──•◈•─────•◈•─
                          የዕለቱ ጥቅስ
        ──•◈•─────•◈•─
“እስራኤልም ብዙ ዘመን ያለ እውነተኛ አምላክ፥ ያለ አስተማሪም ካህን፥ ያለ ሕግም ይኖሩ ነበር።”
2 ዜና 15፥3



ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
4👍1👏1🤔1
Friutful Life
Nigusse Denano
#መጻሕፍትን_በድምጽ

📔ርዕስ፦ ፍሬያማ ሕይወት
👤ጸሐፊ፦ ጥላሁን ኃይሌ
👉ክፍል-9


ይቀጥላል...


ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
3
.       ──•◈•─────•◈•─
                          የዕለቱ ጥቅስ
        ──•◈•─────•◈•─
“መልካም ምክር ከሌለ ዘንድ ሕዝብ ይወድቃል፤ በመካሮች ብዛት ግን ደኅንነት ይሆናል።”
ምሳሌ 11፥14




ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
5
Fruitful Life
Nigusse Denano
#መጻሕፍትን_በድምጽ

📔ርዕስ፦ ፍሬያማ ሕይወት
👤ጸሐፊ፦ ጥላሁን ኃይሌ
👉ክፍል-10


ይቀጥላል...


ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
3
ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
የጥንት ቤተክርስቲያን ታሪክ.pdf
4.6 MB
ርዕስ፦ የጥንት ቤተክርስቲያን ታሪክ
ጸሐፊ፦ ዮሐንስ ሳንድቬድ


ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
17
.       ──•◈•─────•◈•─
                          የዕለቱ ጥቅስ
        ──•◈•─────•◈•─
“እንግዲህ ለንስሐ የሚገባ ፍሬ አድርጉ፤”
ማቴዎስ 3፥8


ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
7👍1🙏1
Fruitful Life
Nigusse Denano
#መጻሕፍትን_በድምጽ

📔ርዕስ፦ ፍሬያማ ሕይወት
👤ጸሐፊ፦ ጥላሁን ኃይሌ
👉ክፍል-11


ይቀጥላል...


ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
3
በክፉ ቀን..!

'' ስለዚህ በክፉው ቀን ለመቃወም ሁሉንም ፈጽማችሁ ለመቆም እንድትችሉ የእግዚአብሔርን እቃ ጦር ሁሉ አንሱ፡፡'' ኤፌ. 6፤10-19

   "የክፉው ቀን" የቱ ነው?  የክፉው ቀን መቼስ ነው?

ልክ እንደ አሁኑ ጊዜ ማለት ነው ፡፡ ብዙ ፈተና የበዛበት፣ የጸለዩት የማይሰማበት የሚመስልበት ቀን፤ ለጠላት የተፈቀደለት ቀን ይመስላል፡፡ ምናልባትም የዓለም ፍጻሜ ቀን የመጨረሻዎቹ ደቂቃ ላይ እንገኛለን፡፡ በፍጹም ያልጠበቅነው ነገር ገጥሞናል፡፡ በዚህ ክፉ ቀን የብዙዎች አቅም የሚፈተሽበት ፣ ጉልበታቸው የሚላላበት፣ እምነታቸውን የሚፈትን ነገር የሚገጥምበት ... ጊዜ ነው፡፡

 በሕይወት ያልታሰበ  ነገር ሲገጥም ያስደነግጣል፤ ቢሆንም የመጨረሻው ዘመን ባህሪ በመሆኑ ልንታገስ ደግሞ ይገባል፡፡ ሐዋርያው ጳውሎስ ለልጁ ለጢሞቴዎስ እንደጻፈለት '' ነገር ግን በመጨረሻ ቀን የሚያስጨንቅ ዘመን እንዲመጣ ይህን እወቅ ሰዎች ራሳቸውን የሚወዱ ይሆናሉና ፣ገንዘብን የሚወዱ፣ ትምክህተኞች፣ ትዕቢተኞች፣ ተሳዳቢዎች፣ ለወላጆቻቸው የማይታዘዙ፣ የማያመሰግኑ፣ ቅድስና የሌላቸው፣ ፍቅር የሌላቸው፣ ዕርቅን የማይሰሙ፣ ሐሜተኞች፣ ራሳቸውን የማይገዙ፣ ጨካኞች፣ መልካም የሆነውን የማይወዱ፣ ከዳተኞች፤ ችኩሎች፣ በትዕቢት የተነፉ፣ ከእግዚአብሔር ይልቅ ተድላን የሚወዱ፣ ይሆናሉ፤ የአምልኮት መልክ አላቸው ኀይሉን ግን ክደዋል ከእነዚህ ደግሞ ራቅ፡፡" 2ኛ ጢሞ.3፤1-5 

አንዳንዱ ነገር ለምን እንደሆነብን እና እንደሚሆን ላይገባን ይችላል፡፡ አንገታቸውን በሰይፍ የሚቀሉ ሰዎች ብዛት፣ በህክምና ስህተት ያሳደጉዋቸውን ወላጆች የሚያጡ ሰዎች ብዛት፣ ጽኑ ወዳጅነት ወደ ጠላትነት መቀየር፣ ልጆችን በተለያየ አደጋ ማጣት፣ ክፉ ዘዴኛነት ፣ ብልጠት፣ ራስ ወዳድነት፣ ማታለል አስገራሚ ጭካኔዎች ሲሆኑ፤ ለምን ? እንዴት ማለታችን አልቀረም፡፡ ጌታ  የት ሄዶ ነው ይህ  ሁሉ የሚሆንብን ትሉ ይሆናል፡፡
 
 የብሉይ ኪዳን የመጨረሻው ነብይ መጥምቁ ዮሐንስ እንዲህ ዓይነት ጥያቄ ተፈጥሮበት ነበረ '' የምትመጣው መሲህ አንተ ነህ  ወይስ ሌላ እንጠብቅ ?'' ብሎ ወደ ኢየሱስ መልዕክተኞችን ላከ፡፡ወንጀል ሳይሰራ እስር ቤት መግባቱ ፣ በዚህም ላይ ብዙ የመሰከረለት ብርቱው ኢየሱስ በርሱ ጉዳይ ጣልቃ ገብቶ ፣ አልያም አንዳች ተአምራት ሰርቶ እርሱን ከእስር አለማስፈታቱ አደናግሮት ይሆናል፤ ነገር ግን ከዚህም የከፋ ሆነ፡፡ በእስራቱ ጊዜ ዝም ማለቱ ሲገርመን ጭራሽ በሔሮደስ ልደት ላይ ለዘፈነች አንዲት ወጣት ብላቴና ጥያቄ መሰረት አንገቱ ተቆርጦ በወጪት ቀረበ፡፡ ጌታስ? ዝም! በቃ ዝም!

አንዳንዱ ጉዳይ ከእኛ አዕምሮ በላይ ነው፡፡ ምናልባት ከጌታ ጋር መግባባት ስለማንችል ይሆን ዝም የሚለን? እስጢፋኖስን በድንጋይ ወግረው ሲገድሉት ሁሉን የሚችለው ጌታ በዙፋኑ ላይ ቆሞ እያየው ነበር፤ ለምን እንዳላስጣለው አይታወቅም፣ የታመነው ምስክሩ አንቲጳስ ሲገደል ጌታ ጣልቃ አልገባም ፣ ሐዋርያቱ በዘይት ተጠብሰው ሲሞቱ፣ ህዝብ በተሰበሰበበት አናብስት ቦጫጭቀው ሲገድሉዋቸው የጠራቸው ጌታ በዙፋኑ ላይ ነበር፡፡ ለአንዳንዱ ጥያቄ መልስ በእጃችን የለም፡፡ አንድ የእግዚአብሔር ሰው እንዳሉት በፊሊፒንስ የጭቃ ጎርፍ 250 ህጻናትን ለምን ከድኖ እንደገደለ አናውቅም፡፡ በቅርብ ጊዜ አንድ የምታሳሳ ወጣት ከሲያትል ለሚሽን ጉዞ ወደ ህንድ ሄዳ በተመሳሳይ ለአገልግሎት ወደ ኢትዮጵያ የሄደው መጋቢ አባት ከጥቂት ቀናት በሁዋላ ተጠርቶ የመጣው ፡ ልጅህ ድንገት ሞታለች ተብሎ ተረድቶ ነበር፡፡ በጣም አሳዛኝ ነበረ፡፡ በሌላ ጊዜ አንድ  ዘማሪት እህት እናቱዋን በሞት ያጣችው ኦፕራሲዎን ልታስደርጋቸው ወስዳ በወቅቱ ሐኪሞቹ መቀስና ሌሎች ነገሮች ሆዳቸው ውስጥ ረስተው ስለ ሰፉአቸው ነበር፡ ነገሩ ኢንፌክሽን ፈጥሮባቸው ዳግመኛ ሲደረጉ  እንደሞቱ ነው ለቅሶ ስደርስ የነገረችኝ፤

ወገኖች ለእኛ የሚበጀን ወደ እግዚአብሔር መቅረብ ነው ፤ ጥያቄያችን ባይመለስም እናመልከዋለን ፣እንወደዋለን፡፡ እንደዚህ የመሰሉ ቀናትን ልናሸንፍ  / ልንቋቋም / እንችላለን ፤የምንችለው ግን የእግዚአብሔርን ዕቃ ጦር በመልበስ  / በማንሳት/ ነው፡፡ መሳሪያው ሰው ሰራሽ መሳሪያ ሳይሆን የእግዚአብሔር ዕቃ ጦር ይለዋል፡፡ እግዚአብሔር ለዚህ ክፉ ጊዜ እንዲሆነን ያዘጋጀልን መከላከያ እና ማሸነፊያ ዕቃ ጦር ነው፡፡ ቢያንስ ስድስት ነገሮች ናቸው ፤ቀጥለን እናያቸዋለን፡-
 

1-  የእምነት መታጠቂያ- ወገባችን ላይ
2-  የጽድቅ ጥሩር- ደረታችን አካባቢ
3-  የሰላም ወንጌል- እግሮቻችን ላይ
4-  የእምነት ጋሻ- በአንደኛው እጃችና ላይ
5-  የመዳን ራስ ቁር- በጭንቅላታችን ላይ የሚደረግ
6-  የመንፈስ ሰይፍ /የእግዚአብሔር ቃል ነው/- በቀኝ እጃችን ይዘን የምናጠቃበት ነው፡፡

  ከራስ እስከ እግራችን ድረስ መሸፈን ያስፈለገን ምክንያት ጠላት እኛን ለመጉዳት ወይም ለመግደል ከጭንቅላታችን ጀምሮ ወርውሮ ስለሚሞክረን ነው፡፡ መዳኑ አስተማማኝ የሆነን ክርስቲያን ጭንቅላቱን መትቶ ሊጎዳው አይችልም፡፡ ነገር ግን ደረቱን በጥሩር ካልታጠቀ ማለትም ጽድቅ ላይ ገና የሚያመቻምች ሆኖ ካገኘው ይጎዳዋል፡፡ ነገር ግን እርሱም ከተሸፈነበት ቢያንስ እግሩን ስበሩት ብሎ መልዕክተኛ ይልካል:: ይህን ጊዜ ጠንካራ የወንጌል ከስክስ ያላደረገ  ሆኖ ከተገኘ ባይሞትም እንኩዋ ዘመኑን ሁሉ በመንፈስ እያነከሰ ይኖራል ስለዚህ ሙሉውን ትጥቅ መታጠቅና መመላለስ አለብን፡፡ እንደሚታወቀው ሰይጣን ትንሽ ቀዳዳ ፈልጎ  ነው የሚያጠቃን ፤ያልተሸፈነ አካላችንን ፈትሸን እንልበስ  /እንታጠቅ/፡፡

የእስራኤል ንጉስ አክአብ የሞተው በጥሩርና በጥሩር መጋጠሚያ በኩል ከጠላት ወገን በተወረወረ ቀስት ተወግቶ ነው፡፡ ምናልባት ሁሉን ታጥቆ ነበር፤ ይሁንና  መቀነት ግን አላደረገም እንደማለት ነው፡፡ ምንም እንኩዋ በእርሱ ሞት ላይ ፍርድ ከእግዚአብሔር ዘንድ የወጣም ቢሆን፡፡ጥቃት የደረሰበትና ለሞት የበቃው ግን በተገኘው ክፍተት በኩል ነበር፡፡

 ወገኖች ሙሉ የእግዚአብሔርን ትጥቅ ታጥቀን በዚህ ዘመን እንድንኖር አሳስባችሁዋለሁ! እስቲ የላሉትን ጠበቅ እናድርጋቸው፤ ከትናንሽ ጥያቄዎቻችን እንውጣና ኩርፊያውን ትተን በእግዚአብሔር ፊት በጽድቅ ፣ በእውነት እንመላለስ!! የሚመጣልን መድኃኒት እርሱም ክርስቶስ ወደ ልዩ እረፍት ቦታ ይወስደናል፡፡ ብንጸና እንወርሳለን፡፡ በነገር ሁሉ ጌታ ከሁላችን ጋር ይሁን ፡፡ አሜን!!!


ምንጭ:- lemekeru.com



ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
17👍3🥰1
ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
3🔥1
የፍርድ መንፈስ.PDF
3.2 MB
📙 ርዕስ:- "የፍርድ መንፈስ"
👤 ጸሐፊ:- ዎች ማን ኒ
👥 ተርጓሚዎች:- ጌዲዮን ኃይሉ እና ይድነቃቸው ወርቁ
📄 የገጽ ብዛት:- 153
📠 አሳታሚ:- ራዕይ


ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
3
.       ──•◈•─────•◈•─
                          የዕለቱ ጥቅስ
        ──•◈•─────•◈•─
“እናንተንም ነውርና ነቀፋ የሌላችሁና ቅዱሳን አድርጎ በእርሱ ፊት ያቀርባችሁ ዘንድ፥ በፊት የተለያችሁትን ክፉ ሥራችሁንም በማድረግ በአሳባችሁ ጠላቶች የነበራችሁትን አሁን በሥጋው ሰውነት በሞቱ በኩል አስታረቃችሁ።”
ቆላስይስ 1፥21-22




ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
9❤‍🔥3