ቅዱሳት መጻሕፍት
7.46K subscribers
1.36K photos
61 videos
332 files
802 links
በዚህ ቻናል

👉ቅዱሳት መጻሕፍት ይጠናሉ::
👉መጽሐፍ ቅዱሳዊ ትምህርቶች ይቀርባሉ::
👉 ለቅዱሳት መጽሐፍት ጥናት የሚያግዙ መጻሕፍት ይለቀቃሉ።

⭐️⭐️⭐️⭐️⭐️

@Holy_scriptures
Download Telegram
ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
1
የምናምነውን እንወቅ.pdf
1.6 MB
ርዕስ፦ የምናምነው እንወቅ አውቀን ያመንነውን አንልቀቅ
ጸሐፊ፦ ዶ/ር መለሰ ወጉ

ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
5
.       ──•◈•─────•◈•─
                          የዕለቱ ጥቅስ
        ──•◈•─────•◈•─
“ስለ ሥጋ ማሰብ ሞት ነውና፥ ስለ መንፈስ ማሰብ ግን ሕይወትና ሰላም ነው።”
ሮሜ 8፥6



ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
10
Friuful Life
Nigusse Denano
#መጻሕፍትን_በድምጽ

📔ርዕስ፦ ፍሬያማ ሕይወት
👤ጸሐፊ፦ ጥላሁን ኃይሌ
👉ክፍል-4


ይቀጥላል...


ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
ለዕረፍት ተጠርተናል


ጌታ በተለያየ በሚገባን መንገድ “ዕረፍት” እንዲህ ነው ብሎ ያሳየናል፣ይጠቁመናል፣ ያቀምሰናል፡፡ቢሆንም ሙሉ የሆነ ዕረፍት የሚመጣው፣ በትጋት በፊቱ በመሆን የጌታ ጸጋ በሕይወታችን እየጨመረ ሲመጣ እንደ ሆነ ልብ ይሏል፡፡

ጌታችን የዕረፍት አምላክ ነውና ሊያሳርፈን ይፈልጋል፡፡ለእኛ ያለው ግልጽ የሆነው የልብ ሐሳቡም እንዲህ የሚል ነው፡-

“እኔ ሕይወት እንዲሆንላችሁ እንዲበዛላችሁ መጣሁ” (ዮሐንስ 10፡10)

ነገር ግን የብዙዎቻችን አኗኗር ሲታይ የዚህን አስደናቂ የተስፋ ቃል ምንነትና በውስጡ የያዘውን በረከት በሚገባ የተረዳነው አይመስልም፡፡ ዋናው ችግራችንም ልባችን ስቷል፡፡ ልባችን መሳቱን የሚያረጋግጥልን ደግሞ በማያሳርፉ ነገሮች ለማረፍ ሲቧጥጥና ሲያልም ማደሩ ነው፡፡ የእግዚአብሔር ቃል ስለ እስራኤላውያን የምድረ በዳ ሕይወት ሲናገር “ሁል ጊዜ ልባቸው ይስታል፤ እነርሱም መንገዴን አላወቁም አልሁ፡፡ወደ ዕረፍቴም እንዳይገቡ በቁጣዬ ማልሁ” (መዝ 95 ፥10-11) ይላል፡፡ አዎ ልባችን ስቷል እንጂ ሌላ ምን ሊሆን ይችላል? የጌታ መንፈስ በተለያየ መንገድ “ዕረፍት ይህች ናት የደከመውንም አሳርፉ ይህችም ማረፊያ ናት አላቸው እነርሱ መስማትን እንቢ አሉ” (ኢሳ 28፥12) እንደሚል ሆኖብናል፡፡

የእግዚአብሔር ቃል “ይሳኮር አጥንተ ብርቱ አህያ ነው፤በበጎች ጉረኖም መካከል ያርፋል፡፡ዕረፍትም መልካም መሆንዋን አየ” (ዘፍጥረት 49፥14-15) ይለናል፡፡ የውስጣዊ ዕረፍት መልካምነት ምንም አያጠያይቅም፤ በሁሉም መልኩ ይጠቅማል፡፡መንፈሳችን ከእግዚአብሔር ለመስማት ይመቻቻል፤ የአእምሮአችንን የመሥራት እና የፈጠራ ችሎታ ይጨምረዋል፤ የእግዚአብሔርን ሥራ በቅጡ እንድሠራ ያስችለናል፤ ማኅበራዊ ሕይወታችንን እንዲስተካከል አመቺ ሁኔታን ይፈጥራል፤ ዕረፍቱ በራሱ ለሰዎች የሚታይ ጠንካራ መልዕክት ነው (በተለይ ለማያምኑ ሰዎች) ፡፡

ከጌታቸው የተማሩ እና ያረፉ ሰዎች ከሕይወት ምልልሳቸው ይታወቃሉ፡፡ሲቅበጠበጡና ሲባዝኑ አይታዩም፡፡እንዳውም ሕይወታቸው ከሩቅ ይናገራል፡፡በጌታቸው ያረፉ ሰዎች በቃሉ ጉልበት ውስጣቸው ስለተለወጠ ከማንኛውም ቀንበር ነጻ ናቸው፡፡ቅድሚያ የሚሰጡትን የሚያውቁ ሲሆን፣ ምርጫዎቻቸውም ውሱን ይሆናሉ፡፡ መረጋጋትና ሰላም የሚታይባቸው እና የምሥጋና ሕይወት ያላቸው (የማይነጫነጩ፣ የማያጉረመርሙ) ስለሆነ፣የምድር ጨው ወይም የዓለም ብርሃን ናቸው፡፡ ሰው እነርሱን አይቶ ልቡ ይነካል፡፡ሰው እነርሱን አይቶ የተለወጡበትን ምንጭ ያስተውላል፡፡ሰው እነርሱን አይቶ ወደ እዚህ ድንቅ የዕረፍት አምላክም ይመጣል፡፡


ይቀጥላል...


ምንጭ:- bekedesa7.blogspot.com



ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
7👍6
.       ──•◈•─────•◈•─
                          የዕለቱ ጥቅስ
        ──•◈•─────•◈•─
“ሳትጨልም እግራችሁም በጨለመችው ተራራ ላይ ሳትሰናከል፥ በተስፋ የምትጠባበቁትን ብርሃን ለሞት ጥላና ለድቅድቅ ጨለማ ሳይለውጠው ለአምላካችሁ ለእግዚአብሔር ክብርን ስጡ።”
ኤርምያስ 13፥16



ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
8🙏2
Fruitful Life
Nigusse Denano
#መጻሕፍትን_በድምጽ

📔ርዕስ፦ ፍሬያማ ሕይወት
👤ጸሐፊ፦ ጥላሁን ኃይሌ
👉ክፍል-5


ይቀጥላል...


ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
4👏1
ፈሪሳውያንና ሰዱቃውያን እነማን ናቸው?


ሰዱቃውያን

በኢየሱስ ዘመን በአይሁድ መካከል ከሚገኙት ትልልቅ ቡድኖች መካከል አንዱ ሰዱቃውያን ናቸው፡፡ ጌታ በምድር በነበረበት ዘመን ተቀባይነታቸውና ክብራቸው እየቀነሰ በመሔድ ላይ ነበር፡፡

ቀደም ሲል በፖለቲካው ውስጥ ከፍ ያለ ስፍራን መያዝ በመቻላቸው ሰዱቃውያን ሐብታም ከሆኑት የመሬት ባላባቶች ሊሆኑ ችለዋል፡፡ በአይሁድ ሸንጎ ውስጥ ከፈሪሳውያን ያልተናነሰ ወንበር ነበራቸው፡፡ ሐዋ.ሥ 23፥6-10 አብዛኛዎቹ ዋና ዋና ካህናትም ሰዱቃውያን ነበሩ፡፡

እምነታቸው፡-

አፈ ታሪክ አይቀበሉም፣ ትንሳኤ ሙታንና ፍርድ መኖሩን አያምኑም፣ የመላዕክትን ሥልጣን ተዋረድ አያምኑም /አይቀበሉም/፣ የኦሪትን መጽሐፍት ብቻ ይቀበላሉ እንዲሁም ቀጥታ ትርጉምን ይከተላሉ፡፡

ፈሪሳውያን

ፈሪሳውያን ከክርስቶስ ልደት በፊት በሁለተኛው ክፍለ ዘመን ላይ ይኖሩ ከነበሩ ሐሲድም ከተባሉ ሰዎች ውስጥ የወጡ ናቸው፡፡ ጅማሬያቸው በግሪኮች ዘመን ለእምነታቸው ከነበራቸው ከፍተኛ ቅናት የመነጨ ነበር፡፡ ሕጉንና ወጉን እጅግ ዝርዝር በሆነ መንገድ አጥብቀው ለመጠበቅ የሚጣጣሩ ሰዎች ነበሩ፡፡

ብዙዎች ጸሐፍት ከፈሪሳውያን ወገን ናቸው፡፡ ከሌሎች ሰዎች እስኪርቁ ድረስ እራሳቸውን ይጠብቁ ነበር፡፡ ይህ አመለካከታቸው ነበር እራሳቸውን ከሌሎች የተለዩና ጻድቅ አድርገው የመቁጠር ፈተና ውስጥ የጣላቸው ፈሪሳውያን ከሰዶቃውያን ጋር የማይስማሙ ናቸው፡፡ ካህን ሳይሆኑ ተራ ሰዎች ናቸው፡፡

እምነታቸው:-

ከአባቶች የተላለፈውን ወግ ይጠብቃሉ፣ ትንሳኤ ሙታንና የፍርድም ቀን እንዳለ ያምናሉ፣ የኦሪትን፣ የታሪክ መጻሕፍትንና የነቢያትንም መጽሐፍት 39ኙንም መጽሐፍት በእኩልነት ሥልጣን ይቀበላሉ፤ ከቅዱስ ስፍራ /ከመቅደስ/ በላይ በቅዱስ ሕዝብ ላይ ያተኩራሉ ማለትም ቅዱሳንን ይከታተላሉ፣ የመሢሑን መምጣት ያምናሉ በ70 ዓ.ም መቅደስ ቢፈርስም እስከ ሁለተኛው 100 ክፍለ ዘመን ቀጣይነት ነበራቸው፡፡ ጳውሎስ ፈሪሳዊ ነበር::


ምንጭ:- iyesus. com



ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️👉 @TME_bible_study
14
.       ──•◈•─────•◈•─
                          የዕለቱ ጥቅስ
        ──•◈•─────•◈•─
“እግዚአብሔርም ብርሃኑ መልካም እንደ ሆነ አየ፥ እግዚአብሔርም ብርሃንንና ጨለማን ለየ።”
ዘፍጥረት 1፥4



ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
7
Friutful Life
Nigusse Denano
#መጻሕፍትን_በድምጽ

📔ርዕስ፦ ፍሬያማ ሕይወት
👤ጸሐፊ፦ ጥላሁን ኃይሌ
👉ክፍል-6


ይቀጥላል...


ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
2
ሰባቱ ኢየሱስ ክርስቶስ በዮሐንስ ወንጌል "እኔ ...ነኝ" ያላቸው ቦታዎች



1. የሕይወት እንጀራ እኔ ነኝ

“ኢየሱስም እንዲህ አላቸው፦ የሕይወት እንጀራ እኔ ነኝ፤ ወደ እኔ የሚመጣ ከቶ አይራብም በእኔ የሚያምንም ሁልጊዜ ከቶ አይጠማም።”
                ዮሐንስ 6፥35


2. እኔ የዓለም ብርሃን ነኝ

“ደግሞም ኢየሱስ፦ እኔ የዓለም ብርሃን ነኝ፤ የሚከተለኝ የሕይወት ብርሃን ይሆንለታል እንጂ በጨለማ አይመላለስም ብሎ ተናገራቸው።”
                  ዮሐንስ 8፥12


3. እኔ የበጎች በር ነኝ

“ኢየሱስም ደግሞ አላቸው፦ እውነት እውነት እላችኋለሁ፥ እኔ የበጎች በር ነኝ።”
                 ዮሐንስ 10፥7


4. መልካም እረኛ እኔ ነኝ

“መልካም እረኛ እኔ ነኝ። መልካም እረኛ ነፍሱን ስለ በጎቹ ያኖራል።”
            ዮሐንስ 10፥11


5. ትንሣኤና ሕይወት እኔ ነኝ

“ኢየሱስም፦ ትንሣኤና ሕይወት እኔ ነኝ፤ የሚያምንብኝ ቢሞት እንኳ ሕያው ይሆናል፤”
             ዮሐንስ 11፥25


6. እኔ መንገድና እውነት ሕይወትም ነኝ

“ኢየሱስም፦ እኔ መንገድና እውነት ሕይወትም ነኝ፤ በእኔ በቀር ወደ አብ የሚመጣ የለም።”
                     ዮሐንስ 14፥6


7. እውነተኛ የወይን ግንድ እኔ ነኝ

“እውነተኛ የወይን ግንድ እኔ ነኝ፤ ገበሬውም አባቴ ነው።”
                     ዮሐንስ 15፥1





ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
10👍5
.       ──•◈•─────•◈•─
                          የዕለቱ ጥቅስ
        ──•◈•─────•◈•─
“አንተ በደልን የማትወድድ አምላክ ነህና፤ ክፉ ከአንተ ጋር አያድርም።”
መዝሙር 5፥4



ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
3🔥3
Fruitful Life
Nigusse Denano
#መጻሕፍትን_በድምጽ

📔ርዕስ፦ ፍሬያማ ሕይወት
👤ጸሐፊ፦ ጥላሁን ኃይሌ
👉ክፍል-7


ይቀጥላል...


ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
1
የሐዋርያት የሃይማኖት መግለጫ


የሐዋርያት የሃይማኖት መግለጫ እጅግ ጥንታዊ እና በሰፊው ጥቅም ላይ ከሚውሉት የክርስትና እምነት መግለጫዎች አንዱ ነው። በተለይም በምዕራቡ ክርስትና (የሮማ ካቶሊክ፣ የአንግሊካን፣ የሉተራን እና ብዙ የተሐድሶ አብያተ ክርስቲያናት)። በሐዋርያት የተጻፈ ባይሆንም ሐዋሪያዊ አስተምህሮውን ጠቅለል አድርጎ የሚገልጽ የእምነት መግለጫ ነው።

ታሪካዊ ዳራ

ይህ የሃይማኖት መግለጫ በ 2ኛው እና በ 9ኛው ክፍለ ዘመን መካከል የተጻፈ እንደሆነ ይገመታል። ነገር ግን አሁን ያለው ቅርፅ ይዟል ተብሎ የሚታመነው በ 8ኛው ክፍለ ዘመን ነው። ይህ የሃይማኖት መግለጫም የተዘጋጀው ለጥምቀት፣ ለክርስትና ትምህርት እና በአምልኮ ወቅት ጥቅም ላይ እንዲውል የክርስትና እምነት ማጠቃለያ ሆኖ የቀረበ ነው።

የዚህ የሃይማኖት መግለጫ አወዛጋቢ ሐረጎች

1. “ወደ ሲኦል ወረደ”

ይህ ከተለያዩ ትርጓሜዎች ጋር በጣም አከራካሪ ከሆነ ክፍል ውስጥ አንዱ ነው።

ሀ. የሐረጉ የመጀመሪያ ወይም የጥንቱ እይታ (ባህላዊ ትርጓሜ)፡-

ጌታችን እና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ወደ ሲኦል ወረደ፤ ሲኦል የሙታን ቦታ ነው። ዓላማውም በሞት ላይ ድልን ማወጅ ወይም ከትንሣኤው በፊት የሞቱትን ጻድቃን ነጻ ማውጣት ነው።

ለዚህ አመለካከት የሚጠቀሰው የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅስ፦
“በእርሱም ደግሞ ሄዶ በወኅኒ ለነበሩ ነፍሳት ሰበከላቸው፤”
1ኛ ጴጥሮስ 3፥19

“ወደ ምድር ታችኛ ክፍል ደግሞ ወረደ ማለት ካልሆነ፥ ይህ ወጣ ማለትስ ምን ማለት ነው?”
ኤፌሶን 4፥9

ለ. ዘይቤያዊ እይታ፡-

“ሲኦል” ማለት ኢየሱስ የሞትን ጥልቀት፣ ከእግዚአብሔር መለየቱን ወይም መከራን መቀበሉን ያመለክታል።

ሉተር እና ካልቪን የተለያዩ ትርጓሜዎች ነበሯቸው።
👉ሉተር የክርስቶስን መውረድ እንደ አሸናፊነት ድል አድርጎ ይቆጥር ነበር።
👉ካልቪን የክርስቶስን የመስቀል ላይ መንፈሳዊ ስቃይ እንጂ የቁልቁለት መውረድን አይደለም ብሎ ያምን ነበር።

ሐ. በዚህ ሐረግ ላይ ዘመናዊው ማስተካከያ

አንዳንድ አብያተ ክርስቲያናት ሐረጉን ያስወግዱታል ወይም ቀየር አድርገው ይጠቀሙታል።

ለምሳሌ፡- “ወደ ሞት በወረደ” (በአንግሊካን ወይም በዘመናዊ ፕሮቴስታንት አጠቃቀም የተለመደ ነው)።
ይህ አገላለጽ "ሲኦል" ተብሎ ከተገለጸው ቃል ጋር የተከሰተውን ግራ መጋባትን ያስወግዳል።


ይቀጥላል...



ምንጭ፦
González, J. L. (2010). The story of Christianity: Volume 1: The early church to the dawn of the Reformation (Rev. ed.). HarperOne.

Kelly, J. N. D. (1972). Early Christian creeds (3rd ed.). Longman.

Pelikan, J. (1971). The Christian tradition: A history of the development of doctrine (Vol. 1: The emergence of the Catholic tradition, 100–600). University of Chicago Press.

Schaff, P. (1885). The creeds of Christendom, with a history and critical notes (Vol. 1–3). Harper & Brothers.



ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️👉 @TME_bible_study
8🔥1
#እራሳችንን_እንመርምር

እንደ አማኝ፣ በዚህ ምድር ላይም እንደሚኖር ሰው ነገሮችን በልክ ማድረግ ላይ እንዴት ነን?

“አንተ ግን ነገርን ሁሉ በልክ አድርግ”
2ኛ ጢሞቴዎስ 4፥5



ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
5👍1
.       ──•◈•─────•◈•─
                          የዕለቱ ጥቅስ
        ──•◈•─────•◈•─
“በይሁዳም ሁሉና በገሊላ በሰማርያም የነበሩት አብያተ ክርስቲያናት በሰላም ኖሩ ታነጹም፤ በእግዚአብሔርም ፍርሃትና በመንፈስ ቅዱስ መጽናናት እየሄዱ ይበዙ ነበር።”
ሐዋርያት 9፥31



ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
11
Friutful Life
Nigusse Denano
#መጻሕፍትን_በድምጽ

📔ርዕስ፦ ፍሬያማ ሕይወት
👤ጸሐፊ፦ ጥላሁን ኃይሌ
👉ክፍል-8


ይቀጥላል...


ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
👏1
ቅዱሳት መጻሕፍት
#እምነት                  ክፍል-10 እምነት እና ሥራ እግዚአብሔር ይህ እምነት እውነተኛ መሆን አለመሆኑን በራሱ አምላካዊ እውቀት ያውቃል፤ ሰው ግን ይህን የሚያውቀው ሥራውን አይቶ ነው፤ እዚህ ላይ የተጠቀሰው «እምነት አለኝ» ባዩ ሰው ደግሞ ሥራ እንደሌለው ታውቋል፤ ስለዚህ በቊ.17 ላይ «ሥራ የሌለው እምነት ቢኖር በራሱ የሞተ ነው» ተብሏል፡፡ በእግዚአብሔር ዘንድ እውነተኛ እንደሆነ…
#እምነት


                 ክፍል-11


እምነት እና ሥራ

አብርሃም የተገረዘው እምነቱ ጽድቅ ሆኖ ከተቈጠረለት ከ13 ዓመታት በኋላ በመሆኑ መገረዙም ቢሆን በእግዚአብሔር ዘንድ ለመጽደቁ ምክንያት አልነበረም(ሮሜ4፥9‐12)፤ ነገር ግን ይህ መገረዙ «ሳይገረዝ በነበረው እምነት ያገኘው የጽድቅ ማኅተም» የሆነ ምልክት ወይም ማረጋገጫ ነበር (ሮሜ4፥11)፡፡ እንዲሁም ሕግ የተሰጠው ከ430 ዓመታት በኋላ በሙሴ ጊዜ በመሆኑ አብርሃም በዘመኑ በሕግ ሥራ ሊጸድቅ አይችልም፡፡ ስለዚህ አብርሃም የጸደቀው በሕግ ሥራ ሳይሆን በእምነት ነበር፡፡ ዛሬም ቢሆን ሰው የሚጸድቀው በሥራ ሳይሆን በእምነት እንደሆነ ለማወቅ «ለማይሠራ ኃጢአተኛውን በሚያጸድቅ ለሚያምን ሰው» እምነቱ ጽድቅ ሆኖ እንደሚቈጠርለት የተነገረውን ማስተዋል ያስፈልጋል፡፡ በተጨማሪም ጽድቅ በእምነት የመቈጠሩ ጉዳይ ለአብርሃም ብቻ ሳይሆን ለእኛም እንደሆነ መጽሐፍ ቅዱስ ሲናገር «ነገር ግን ተቈጠረለት የሚለው ቃል ስለ እርሱ ብቻ የተጻፈ አይደለም ስለእኛም ነው እንጂ፤ ስለ በደላችን አልፎ የተሰጠውን እኛን ስለማጽደቅም የተነሣውን ጌታችንን ኢየሱስን ከሙታን ባስነሳው ለምናምን ይቈጠርልን ዘንድ አለው» ይላል (ሮሜ 4፥23‐25)፡፡

በእምነት የጸደቀ ሰው ግን በሥራም ይጸድቃል፤ ይህ ማለት ግን ሥራ በእግዚአብሔር ዘንድ ያጸድቃል ከማለት በፍጹም የተለየ ነው፤ በሥራ መጽደቅ በእምነት የተገኘው ጽድቅ በሰው ዘንድ በሚታይ ሥራ መረጋጡን የሚያመለክት ነው፡፡ እንዲሁም እውነተኛ እምነትን ተከትሎ ለሚሠራው መልካም ሥራ በክርስቶስ የፍርድ ወንበር ፊት የጽድቅ አክሊልን በብድራት መቀበልን የሚያሳይ ነው፡፡ ይህም በእምነት የጸደቁ ሰዎች የሥራቸውን ዋጋ ይቀበላሉ ማለት ነው እንጂ ሰዎች የሚጸድቁት ገና ያን ጊዜ ነው ማለት አይደለም፡፡ ነገር ግን በእግዚአብሔር ፊት ሰውን የሚያጸድቀው እምነት ቀድሞውኑ ከሥራው ጋር አብሮ ያደርግ እንደነበር እንመለከታለን፤ ይህም ማለት በኋላ ይገለጥ ዘንድ ያለው ሥራ በእምነት ውስጥ ተሰውሮ እንደነበር እናያለን ማለት ነው።

«ሰው በእምነት ብቻ ሳይሆን በሥራም እንዲጸድቅ ታያላችሁ» ማለትም በሥራ ሊገለጥ በሚችል እውነተኛ እምነት የጸደቀ ሰው በኋላ በሥራውም ይጸድቃል ወይም መጽደቁ በድጋሚ ይረጋገጣል፣ ብድራትን ይቀበላል፣ ይሸለማል ማለት ነው እንጂ በእግዚአብሔር ዘንድ ለመጽደቅ ሰው በክርስቶስ ማመኑ ብቻውን በቂ ስለማይሆን ሥራም መሥራት ያስፈልገዋል ማለት አይደለም፡፡


ይቀጥላል...


ምንጭ፦ 1bible.page




ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
10👍2
.       ──•◈•─────•◈•─
                          የዕለቱ ጥቅስ
        ──•◈•─────•◈•─
“እስራኤልም ብዙ ዘመን ያለ እውነተኛ አምላክ፥ ያለ አስተማሪም ካህን፥ ያለ ሕግም ይኖሩ ነበር።”
2 ዜና 15፥3



ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
4👍1👏1🤔1
Friutful Life
Nigusse Denano
#መጻሕፍትን_በድምጽ

📔ርዕስ፦ ፍሬያማ ሕይወት
👤ጸሐፊ፦ ጥላሁን ኃይሌ
👉ክፍል-9


ይቀጥላል...


ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
3
.       ──•◈•─────•◈•─
                          የዕለቱ ጥቅስ
        ──•◈•─────•◈•─
“መልካም ምክር ከሌለ ዘንድ ሕዝብ ይወድቃል፤ በመካሮች ብዛት ግን ደኅንነት ይሆናል።”
ምሳሌ 11፥14




ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
5