ቅዱሳት መጻሕፍት
7.46K subscribers
1.36K photos
61 videos
332 files
802 links
በዚህ ቻናል

👉ቅዱሳት መጻሕፍት ይጠናሉ::
👉መጽሐፍ ቅዱሳዊ ትምህርቶች ይቀርባሉ::
👉 ለቅዱሳት መጽሐፍት ጥናት የሚያግዙ መጻሕፍት ይለቀቃሉ።

⭐️⭐️⭐️⭐️⭐️

@Holy_scriptures
Download Telegram
.       ──•◈•─────•◈•─
                          የዕለቱ ጥቅስ
        ──•◈•─────•◈•─
“ካህኑ የሠራዊት ጌታ የእግዚአብሔር መልእክተኛ ነውና ከንፈሮቹ እውቀትን ይጠብቁ ዘንድ ይገባቸዋል፥ ሰዎችም ሕግን ከአፉ ይፈልጉ ዘንድ ይገባቸዋል።”
ሚልክያስ 2፥7



ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
7
Fruitful Life
Nigusse Denano
#መጻሕፍትን_በድምጽ

📔ርዕስ፦ ፍሬያማ ሕይወት
👤ጸሐፊ፦ ጥላሁን ኃይሌ
👉ክፍል-2


ይቀጥላል...


ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
"ኑና እንዋቀስ"


ሕይወት ትሠምር ዘንድ፣ሰው ከአምላኩ ምሪትን፣ኃይልን፣ምክርን ወዘተ ሊቀበል ይገባዋል፡፡አለበለዚያ ሕይወት መደዴ ይሆናል፤ፍሬ አልባም፡፡መኪና ወደ ጋራዥ ለእድሳት እንደሚወሰድ ሁሉ፣ወደ ጸጋ ዙፋኑ በመምጣት ምሕረቱንና ጸጋውን ልንቀበል ያስፈልገናል፤አንዴ ብቻ ሳይሆን ሳናቋርጥ፡፡ የእግዚአብሔር ቃል “ውኃውንም ከመድኃኒት ምንጮች በደስታ ትቀዳላችሁ”(ኢሳይያስ 12:3) የሚለውም ለዚህ ነው፤ወደ ምንጩ መጥተን የመቅዳቱ ኀላፊነት የኛ እንደ ሆነ ሲያመለክት፣ያለ ማቋረጥ መሆኑንም፡፡

ሰው ወደ ጌታው ሕልውና ሲመጣ፣ራሱን የማየት ጊዜ ያገኛል፡፡በሕይወቱ ያላስተዋላቸውን መሠረታዊ ችግሮች የመረዳትና የመገንዘብም ዕድል ይኖረዋል::ቃሉ “የተሰወረውን ኃጢአታችንን በፊትህ ብርሃን፥ በደላችንንም በፊትህአስቀመጥህ” (መዝሙር 90፡8) እንደሚል፣ ከሕሊናችን የተሰወሩና ያልተናዘዝናቸው ኃጢአቶችን (እንዳሉም ያላሰብናቸውን) የማየት አጋጣሚው ይኖረናል፡፡

በጌታ ፊት የምንሆንባቸው ጊዜያት የባከኑ እንደ ሆኑ ልናስብ አይገባም፤እንዳውም ጥሩ የሕክምና ጊዜ፣ጥሩ የመሠሪያ ጊዜ እንደ ሆነ እንጂ፡፡ታዲያ በትሕትና የውስጣችንን ችግሮች ዘክዝከን፣ነፍሳችን አፍስሰን፣ከምር በሚፈስ እንባ ጥልቅ ንስሐዎችን ብንገባ፣የሚመጣው መታደስ ቀላል አይሆንም፡፡እንዲህ ዓይነት ጊዜዎች ሲበዙልን ነው፣ለውጣችን የሚበዛው፤እድገታችንም ብዥታ የማይኖረው፡፡

ራሳችንን ለመመርመር ጊዜያትን ማመቻቸት አስተዋይነት ይመስለኛል፡፡ጨክኖ ግላዊ ፍተሻ(personal inventory) ማድረግና ከጌታ ጋር ለመሄድ መስማማት ጥበብ ሲሆን፣ወደ ፈጣሪ ሕልውና እየመጣ “ኑና እንዋቀስ” (ኢሳይያስ 1፡18) በሚለው መንፈሳዊ መርሕ ያልተጎበኘ ሕይወት ችግር አለው፡፡ቃሉ “በመመለስና በማረፍ ትድናላችሁ፣በጸጥታና በመታመን ኃይል ይሆንላችኋል”(ኢሳይያስ 30፡15) ይላልና፡፡


አዎ! የጸጥታ ጊዜ፣የእረፍት ጊዜ፣የመመለስና የንስሐ ጊዜያት ለሕይወታችን እጅግ አስፈላጊዎች ናቸው፡፡ያኔ ኃይላችን ይታደሳል፣መንፈሳችን ይጠነክራል፡፡ያኔ በአዲስ አተያይና ምልከታ፣ተግዳሮቶቻችን እንገጥማለን፡፡መታከትም ይወገዳል፡፡በታደሰ ሕይወትም የሚሠራው ሥራም ብዙ ፍሬን ያፈራል።


ምንጭ:- Divine Wisdom4


    

ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
10
የሐዋርያት የእምነት መግለጫ


እኔ ሁሉን በሚችል፣ ሰማይንና ምድርን በፈጠረ በእግዚአብሔር አብ አምናለሁ፡፡
ደግሞም በአንድ ልጁ፣
በመንፈስ ቅዱስ በተፀነሰ፣
ከድንግል ማርያም በተወለደ፣
በጴንጤናዊው በጲላጦስ ዘመን መከራን በተቀበለ፣
በተሰቀለ፣ በሞተ እና በተቀበረ፤
ወደ ሲዖልም በወረደ፡፡
በሦስተኛውም ቀን ከሙታን በተነሣ፡፡
ወደ ሰማይም በወጣ
ሁሉን በሚችል በእግዚአብሔር አብ ቀኝ በተቀመጠ፣
በሕያዋንና በሙታን ሊፈርድ ከዚያም በሚመለስ፣
በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ አምናለሁ፡፡
ደግሞም በመንፈስ ቅዱስ፣
በአንዲት ቅድስት የሐዋርያት ቤተክርስቲያን፣
በቅዱሳን አንድነት፣
በኀጢአት ስርየት፣
በሥጋ ትንሣኤ፣
በዘላለም ሕይወት አምናለሁ፡፡ አሜን፡፡


ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️👉 @TME_bible_study
27🔥12👍1
.       ──•◈•─────•◈•─
                          የዕለቱ ጥቅስ
        ──•◈•─────•◈•─
“ስለዚህ፥ እነሆ፥ የሰላሜን ቃል ኪዳን እሰጠዋለሁ።”
ዘኍልቁ 25፥12



ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
8👏1
Friutful Life
Nigusse Denano
#መጻሕፍትን_በድምጽ

📔ርዕስ፦ ፍሬያማ ሕይወት
👤ጸሐፊ፦ ጥላሁን ኃይሌ
👉ክፍል-3


ይቀጥላል...


ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
2
ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
1
የምናምነውን እንወቅ.pdf
1.6 MB
ርዕስ፦ የምናምነው እንወቅ አውቀን ያመንነውን አንልቀቅ
ጸሐፊ፦ ዶ/ር መለሰ ወጉ

ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
5
.       ──•◈•─────•◈•─
                          የዕለቱ ጥቅስ
        ──•◈•─────•◈•─
“ስለ ሥጋ ማሰብ ሞት ነውና፥ ስለ መንፈስ ማሰብ ግን ሕይወትና ሰላም ነው።”
ሮሜ 8፥6



ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
10
Friuful Life
Nigusse Denano
#መጻሕፍትን_በድምጽ

📔ርዕስ፦ ፍሬያማ ሕይወት
👤ጸሐፊ፦ ጥላሁን ኃይሌ
👉ክፍል-4


ይቀጥላል...


ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
ለዕረፍት ተጠርተናል


ጌታ በተለያየ በሚገባን መንገድ “ዕረፍት” እንዲህ ነው ብሎ ያሳየናል፣ይጠቁመናል፣ ያቀምሰናል፡፡ቢሆንም ሙሉ የሆነ ዕረፍት የሚመጣው፣ በትጋት በፊቱ በመሆን የጌታ ጸጋ በሕይወታችን እየጨመረ ሲመጣ እንደ ሆነ ልብ ይሏል፡፡

ጌታችን የዕረፍት አምላክ ነውና ሊያሳርፈን ይፈልጋል፡፡ለእኛ ያለው ግልጽ የሆነው የልብ ሐሳቡም እንዲህ የሚል ነው፡-

“እኔ ሕይወት እንዲሆንላችሁ እንዲበዛላችሁ መጣሁ” (ዮሐንስ 10፡10)

ነገር ግን የብዙዎቻችን አኗኗር ሲታይ የዚህን አስደናቂ የተስፋ ቃል ምንነትና በውስጡ የያዘውን በረከት በሚገባ የተረዳነው አይመስልም፡፡ ዋናው ችግራችንም ልባችን ስቷል፡፡ ልባችን መሳቱን የሚያረጋግጥልን ደግሞ በማያሳርፉ ነገሮች ለማረፍ ሲቧጥጥና ሲያልም ማደሩ ነው፡፡ የእግዚአብሔር ቃል ስለ እስራኤላውያን የምድረ በዳ ሕይወት ሲናገር “ሁል ጊዜ ልባቸው ይስታል፤ እነርሱም መንገዴን አላወቁም አልሁ፡፡ወደ ዕረፍቴም እንዳይገቡ በቁጣዬ ማልሁ” (መዝ 95 ፥10-11) ይላል፡፡ አዎ ልባችን ስቷል እንጂ ሌላ ምን ሊሆን ይችላል? የጌታ መንፈስ በተለያየ መንገድ “ዕረፍት ይህች ናት የደከመውንም አሳርፉ ይህችም ማረፊያ ናት አላቸው እነርሱ መስማትን እንቢ አሉ” (ኢሳ 28፥12) እንደሚል ሆኖብናል፡፡

የእግዚአብሔር ቃል “ይሳኮር አጥንተ ብርቱ አህያ ነው፤በበጎች ጉረኖም መካከል ያርፋል፡፡ዕረፍትም መልካም መሆንዋን አየ” (ዘፍጥረት 49፥14-15) ይለናል፡፡ የውስጣዊ ዕረፍት መልካምነት ምንም አያጠያይቅም፤ በሁሉም መልኩ ይጠቅማል፡፡መንፈሳችን ከእግዚአብሔር ለመስማት ይመቻቻል፤ የአእምሮአችንን የመሥራት እና የፈጠራ ችሎታ ይጨምረዋል፤ የእግዚአብሔርን ሥራ በቅጡ እንድሠራ ያስችለናል፤ ማኅበራዊ ሕይወታችንን እንዲስተካከል አመቺ ሁኔታን ይፈጥራል፤ ዕረፍቱ በራሱ ለሰዎች የሚታይ ጠንካራ መልዕክት ነው (በተለይ ለማያምኑ ሰዎች) ፡፡

ከጌታቸው የተማሩ እና ያረፉ ሰዎች ከሕይወት ምልልሳቸው ይታወቃሉ፡፡ሲቅበጠበጡና ሲባዝኑ አይታዩም፡፡እንዳውም ሕይወታቸው ከሩቅ ይናገራል፡፡በጌታቸው ያረፉ ሰዎች በቃሉ ጉልበት ውስጣቸው ስለተለወጠ ከማንኛውም ቀንበር ነጻ ናቸው፡፡ቅድሚያ የሚሰጡትን የሚያውቁ ሲሆን፣ ምርጫዎቻቸውም ውሱን ይሆናሉ፡፡ መረጋጋትና ሰላም የሚታይባቸው እና የምሥጋና ሕይወት ያላቸው (የማይነጫነጩ፣ የማያጉረመርሙ) ስለሆነ፣የምድር ጨው ወይም የዓለም ብርሃን ናቸው፡፡ ሰው እነርሱን አይቶ ልቡ ይነካል፡፡ሰው እነርሱን አይቶ የተለወጡበትን ምንጭ ያስተውላል፡፡ሰው እነርሱን አይቶ ወደ እዚህ ድንቅ የዕረፍት አምላክም ይመጣል፡፡


ይቀጥላል...


ምንጭ:- bekedesa7.blogspot.com



ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
7👍6
.       ──•◈•─────•◈•─
                          የዕለቱ ጥቅስ
        ──•◈•─────•◈•─
“ሳትጨልም እግራችሁም በጨለመችው ተራራ ላይ ሳትሰናከል፥ በተስፋ የምትጠባበቁትን ብርሃን ለሞት ጥላና ለድቅድቅ ጨለማ ሳይለውጠው ለአምላካችሁ ለእግዚአብሔር ክብርን ስጡ።”
ኤርምያስ 13፥16



ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
8🙏2
Fruitful Life
Nigusse Denano
#መጻሕፍትን_በድምጽ

📔ርዕስ፦ ፍሬያማ ሕይወት
👤ጸሐፊ፦ ጥላሁን ኃይሌ
👉ክፍል-5


ይቀጥላል...


ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
4👏1
ፈሪሳውያንና ሰዱቃውያን እነማን ናቸው?


ሰዱቃውያን

በኢየሱስ ዘመን በአይሁድ መካከል ከሚገኙት ትልልቅ ቡድኖች መካከል አንዱ ሰዱቃውያን ናቸው፡፡ ጌታ በምድር በነበረበት ዘመን ተቀባይነታቸውና ክብራቸው እየቀነሰ በመሔድ ላይ ነበር፡፡

ቀደም ሲል በፖለቲካው ውስጥ ከፍ ያለ ስፍራን መያዝ በመቻላቸው ሰዱቃውያን ሐብታም ከሆኑት የመሬት ባላባቶች ሊሆኑ ችለዋል፡፡ በአይሁድ ሸንጎ ውስጥ ከፈሪሳውያን ያልተናነሰ ወንበር ነበራቸው፡፡ ሐዋ.ሥ 23፥6-10 አብዛኛዎቹ ዋና ዋና ካህናትም ሰዱቃውያን ነበሩ፡፡

እምነታቸው፡-

አፈ ታሪክ አይቀበሉም፣ ትንሳኤ ሙታንና ፍርድ መኖሩን አያምኑም፣ የመላዕክትን ሥልጣን ተዋረድ አያምኑም /አይቀበሉም/፣ የኦሪትን መጽሐፍት ብቻ ይቀበላሉ እንዲሁም ቀጥታ ትርጉምን ይከተላሉ፡፡

ፈሪሳውያን

ፈሪሳውያን ከክርስቶስ ልደት በፊት በሁለተኛው ክፍለ ዘመን ላይ ይኖሩ ከነበሩ ሐሲድም ከተባሉ ሰዎች ውስጥ የወጡ ናቸው፡፡ ጅማሬያቸው በግሪኮች ዘመን ለእምነታቸው ከነበራቸው ከፍተኛ ቅናት የመነጨ ነበር፡፡ ሕጉንና ወጉን እጅግ ዝርዝር በሆነ መንገድ አጥብቀው ለመጠበቅ የሚጣጣሩ ሰዎች ነበሩ፡፡

ብዙዎች ጸሐፍት ከፈሪሳውያን ወገን ናቸው፡፡ ከሌሎች ሰዎች እስኪርቁ ድረስ እራሳቸውን ይጠብቁ ነበር፡፡ ይህ አመለካከታቸው ነበር እራሳቸውን ከሌሎች የተለዩና ጻድቅ አድርገው የመቁጠር ፈተና ውስጥ የጣላቸው ፈሪሳውያን ከሰዶቃውያን ጋር የማይስማሙ ናቸው፡፡ ካህን ሳይሆኑ ተራ ሰዎች ናቸው፡፡

እምነታቸው:-

ከአባቶች የተላለፈውን ወግ ይጠብቃሉ፣ ትንሳኤ ሙታንና የፍርድም ቀን እንዳለ ያምናሉ፣ የኦሪትን፣ የታሪክ መጻሕፍትንና የነቢያትንም መጽሐፍት 39ኙንም መጽሐፍት በእኩልነት ሥልጣን ይቀበላሉ፤ ከቅዱስ ስፍራ /ከመቅደስ/ በላይ በቅዱስ ሕዝብ ላይ ያተኩራሉ ማለትም ቅዱሳንን ይከታተላሉ፣ የመሢሑን መምጣት ያምናሉ በ70 ዓ.ም መቅደስ ቢፈርስም እስከ ሁለተኛው 100 ክፍለ ዘመን ቀጣይነት ነበራቸው፡፡ ጳውሎስ ፈሪሳዊ ነበር::


ምንጭ:- iyesus. com



ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️👉 @TME_bible_study
14
.       ──•◈•─────•◈•─
                          የዕለቱ ጥቅስ
        ──•◈•─────•◈•─
“እግዚአብሔርም ብርሃኑ መልካም እንደ ሆነ አየ፥ እግዚአብሔርም ብርሃንንና ጨለማን ለየ።”
ዘፍጥረት 1፥4



ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
7
Friutful Life
Nigusse Denano
#መጻሕፍትን_በድምጽ

📔ርዕስ፦ ፍሬያማ ሕይወት
👤ጸሐፊ፦ ጥላሁን ኃይሌ
👉ክፍል-6


ይቀጥላል...


ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
2
ሰባቱ ኢየሱስ ክርስቶስ በዮሐንስ ወንጌል "እኔ ...ነኝ" ያላቸው ቦታዎች



1. የሕይወት እንጀራ እኔ ነኝ

“ኢየሱስም እንዲህ አላቸው፦ የሕይወት እንጀራ እኔ ነኝ፤ ወደ እኔ የሚመጣ ከቶ አይራብም በእኔ የሚያምንም ሁልጊዜ ከቶ አይጠማም።”
                ዮሐንስ 6፥35


2. እኔ የዓለም ብርሃን ነኝ

“ደግሞም ኢየሱስ፦ እኔ የዓለም ብርሃን ነኝ፤ የሚከተለኝ የሕይወት ብርሃን ይሆንለታል እንጂ በጨለማ አይመላለስም ብሎ ተናገራቸው።”
                  ዮሐንስ 8፥12


3. እኔ የበጎች በር ነኝ

“ኢየሱስም ደግሞ አላቸው፦ እውነት እውነት እላችኋለሁ፥ እኔ የበጎች በር ነኝ።”
                 ዮሐንስ 10፥7


4. መልካም እረኛ እኔ ነኝ

“መልካም እረኛ እኔ ነኝ። መልካም እረኛ ነፍሱን ስለ በጎቹ ያኖራል።”
            ዮሐንስ 10፥11


5. ትንሣኤና ሕይወት እኔ ነኝ

“ኢየሱስም፦ ትንሣኤና ሕይወት እኔ ነኝ፤ የሚያምንብኝ ቢሞት እንኳ ሕያው ይሆናል፤”
             ዮሐንስ 11፥25


6. እኔ መንገድና እውነት ሕይወትም ነኝ

“ኢየሱስም፦ እኔ መንገድና እውነት ሕይወትም ነኝ፤ በእኔ በቀር ወደ አብ የሚመጣ የለም።”
                     ዮሐንስ 14፥6


7. እውነተኛ የወይን ግንድ እኔ ነኝ

“እውነተኛ የወይን ግንድ እኔ ነኝ፤ ገበሬውም አባቴ ነው።”
                     ዮሐንስ 15፥1





ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
10👍5
.       ──•◈•─────•◈•─
                          የዕለቱ ጥቅስ
        ──•◈•─────•◈•─
“አንተ በደልን የማትወድድ አምላክ ነህና፤ ክፉ ከአንተ ጋር አያድርም።”
መዝሙር 5፥4



ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
3🔥3
Fruitful Life
Nigusse Denano
#መጻሕፍትን_በድምጽ

📔ርዕስ፦ ፍሬያማ ሕይወት
👤ጸሐፊ፦ ጥላሁን ኃይሌ
👉ክፍል-7


ይቀጥላል...


ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
1
የሐዋርያት የሃይማኖት መግለጫ


የሐዋርያት የሃይማኖት መግለጫ እጅግ ጥንታዊ እና በሰፊው ጥቅም ላይ ከሚውሉት የክርስትና እምነት መግለጫዎች አንዱ ነው። በተለይም በምዕራቡ ክርስትና (የሮማ ካቶሊክ፣ የአንግሊካን፣ የሉተራን እና ብዙ የተሐድሶ አብያተ ክርስቲያናት)። በሐዋርያት የተጻፈ ባይሆንም ሐዋሪያዊ አስተምህሮውን ጠቅለል አድርጎ የሚገልጽ የእምነት መግለጫ ነው።

ታሪካዊ ዳራ

ይህ የሃይማኖት መግለጫ በ 2ኛው እና በ 9ኛው ክፍለ ዘመን መካከል የተጻፈ እንደሆነ ይገመታል። ነገር ግን አሁን ያለው ቅርፅ ይዟል ተብሎ የሚታመነው በ 8ኛው ክፍለ ዘመን ነው። ይህ የሃይማኖት መግለጫም የተዘጋጀው ለጥምቀት፣ ለክርስትና ትምህርት እና በአምልኮ ወቅት ጥቅም ላይ እንዲውል የክርስትና እምነት ማጠቃለያ ሆኖ የቀረበ ነው።

የዚህ የሃይማኖት መግለጫ አወዛጋቢ ሐረጎች

1. “ወደ ሲኦል ወረደ”

ይህ ከተለያዩ ትርጓሜዎች ጋር በጣም አከራካሪ ከሆነ ክፍል ውስጥ አንዱ ነው።

ሀ. የሐረጉ የመጀመሪያ ወይም የጥንቱ እይታ (ባህላዊ ትርጓሜ)፡-

ጌታችን እና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ወደ ሲኦል ወረደ፤ ሲኦል የሙታን ቦታ ነው። ዓላማውም በሞት ላይ ድልን ማወጅ ወይም ከትንሣኤው በፊት የሞቱትን ጻድቃን ነጻ ማውጣት ነው።

ለዚህ አመለካከት የሚጠቀሰው የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅስ፦
“በእርሱም ደግሞ ሄዶ በወኅኒ ለነበሩ ነፍሳት ሰበከላቸው፤”
1ኛ ጴጥሮስ 3፥19

“ወደ ምድር ታችኛ ክፍል ደግሞ ወረደ ማለት ካልሆነ፥ ይህ ወጣ ማለትስ ምን ማለት ነው?”
ኤፌሶን 4፥9

ለ. ዘይቤያዊ እይታ፡-

“ሲኦል” ማለት ኢየሱስ የሞትን ጥልቀት፣ ከእግዚአብሔር መለየቱን ወይም መከራን መቀበሉን ያመለክታል።

ሉተር እና ካልቪን የተለያዩ ትርጓሜዎች ነበሯቸው።
👉ሉተር የክርስቶስን መውረድ እንደ አሸናፊነት ድል አድርጎ ይቆጥር ነበር።
👉ካልቪን የክርስቶስን የመስቀል ላይ መንፈሳዊ ስቃይ እንጂ የቁልቁለት መውረድን አይደለም ብሎ ያምን ነበር።

ሐ. በዚህ ሐረግ ላይ ዘመናዊው ማስተካከያ

አንዳንድ አብያተ ክርስቲያናት ሐረጉን ያስወግዱታል ወይም ቀየር አድርገው ይጠቀሙታል።

ለምሳሌ፡- “ወደ ሞት በወረደ” (በአንግሊካን ወይም በዘመናዊ ፕሮቴስታንት አጠቃቀም የተለመደ ነው)።
ይህ አገላለጽ "ሲኦል" ተብሎ ከተገለጸው ቃል ጋር የተከሰተውን ግራ መጋባትን ያስወግዳል።


ይቀጥላል...



ምንጭ፦
González, J. L. (2010). The story of Christianity: Volume 1: The early church to the dawn of the Reformation (Rev. ed.). HarperOne.

Kelly, J. N. D. (1972). Early Christian creeds (3rd ed.). Longman.

Pelikan, J. (1971). The Christian tradition: A history of the development of doctrine (Vol. 1: The emergence of the Catholic tradition, 100–600). University of Chicago Press.

Schaff, P. (1885). The creeds of Christendom, with a history and critical notes (Vol. 1–3). Harper & Brothers.



ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️👉 @TME_bible_study
8🔥1
#እራሳችንን_እንመርምር

እንደ አማኝ፣ በዚህ ምድር ላይም እንደሚኖር ሰው ነገሮችን በልክ ማድረግ ላይ እንዴት ነን?

“አንተ ግን ነገርን ሁሉ በልክ አድርግ”
2ኛ ጢሞቴዎስ 4፥5



ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
5👍1