ክርስትና በ ፓልስቲን ሲጀምር ሕይወት ነበረ ፣ ወደ ግሪክ ሲደርስ ፍልስፍና ሆነ ፣ሮም ሲገባ ተቋም ሆነ ፣ አውሮፓና አሜሪካ ሲደርስ ንግድ ሆነ!!
#በእኛ_ህይወትስ?🤔
ዶክተር ማሙሻ ፈንታ
ወደ ቻናሉ ለመ🀄️ላ🀄️ል፦ @Holy_scriptures
#በእኛ_ህይወትስ?🤔
ዶክተር ማሙሻ ፈንታ
ወደ ቻናሉ ለመ🀄️ላ🀄️ል፦ @Holy_scriptures
❤8🤔8😢2👏1🤯1
#የእግዚአብሔር_ቃል_ምን_ይላል
ሚልክያስ 1
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
¹⁰ በመሠዊያዬ ላይ እሳትን በከንቱ እንዳታቃጥሉ ከእናንተ ዘንድ ደጅ የሚዘጋ ሰው ምነው በተገኘ! በእናንተ ደስ አይለኝም፥ ቍርባንንም ከእጃችሁ አልቀበልም፥ ይላል የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር።
¹¹ ከፀሐይ መውጫ ጀምሮ እስከ መግቢያዋ ድረስ ስሜ በአሕዛብ ዘንድ ታላቅ ይሆናልና፤ በየስፍራውም ለስሜ ዕጣን ያጥናሉ፥ ንጹሕም ቍርባን ያቀርባሉ፤ ስሜ በአሕዛብ ዘንድ ታላቅ ይሆናልና፥ ይላል የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር።
¹² እናንተ ግን፦ የእግዚአብሔር ገበታ ርኩስ ነው፤ ፍሬውና መብሉም የተናቀ ነው በማለታችሁ አስነቀፋችሁት።
¹³ እናን፦ እነሆ፥ ይህ ድካም ነው ብላችሁ ጢቅ አላችሁበት፥ ይላል የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር፤ በቅሚያ የያዛችሁትንም አንካሳውንም የታመመውንም አቅርባችኋል፤ እንዲሁ ቍርባንን ታመጣላችሁ በውኑ ከእጃችሁ ይህን ልቀበለውን? ይላል እግዚአብሔር።
¹⁴ እኔ ታላቅ ንጉሥ ነኝና፥ ይላል የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር፥ ስሜም በአሕዛብ ዘንድ የተፈራ ነውና በመንጋው ውስጥ ተባት እያለው ለጌታ ተስሎ ነውረኛውን የሚሠዋ ሸንጋይ ሰው ርጉም ይሁን።

👍5❤2🙏1
. ──•◈•─────•◈•─
የዕለቱ ጥቅስ
──•◈•─────•◈•─
“አካሄዳችሁ ገንዘብን ያለ መውደድ ይሁን፥ ያላችሁም ይብቃችሁ፤ እርሱ ራሱ፦ አልለቅህም ከቶም አልተውህም ብሎአልና፤”
ዕብራውያን 13፥5

❤12
ቅዱሳት መጻሕፍት
. ──•◈•─────•◈•─ የዕለቱ ጥቅስ ──•◈•─────•◈•─ “አካሄዳችሁ ገንዘብን ያለ መውደድ ይሁን፥ ያላችሁም ይብቃችሁ፤ እርሱ ራሱ፦ አልለቅህም ከቶም አልተውህም ብሎአልና፤” ዕብራውያን 13፥5 ወደ ቻናሉ ለመ🀄️ላ🀄️ል፦ @Holy_scriptures
"የገንዘብ ፍቅር አይግዛችሁ ፤ ባላችሁ ነገር ረክታችሁ ለመኖር ጣሩ። ምክንያቱም እግዚአብሔር፥ 'ምን ጊዜም ቢሆን በችግራችሁ እደርስላችኋለሁ ፤ ምን ጊዜም ቢሆን አልተዋችሁም' ብሎ ተናግሮአልና።"
ዕብራውያን 13፥5 (ሕያው ቃል)
ዕብራውያን 13፥5 (ሕያው ቃል)
❤11🥰7🔥1
#እራሳችንን_እንመርምር
ኃጢአትን እንዴት አድርገን ነው የምንመለከተው? ይዘናት፣ አቅፈናት እና አሽሞንሙነናት ወይስ ተጸይፈን፣ ትተን እና ነግሰንባት ነው ያለነው?
“ኃጢአቱን የሚሰውር አይለማም፤ የሚናዘዝባትና የሚተዋት ግን ምሕረትን ያገኛል።”
ምሳሌ 28፥13
ወደ ቻናሉ ለመ🀄️ላ🀄️ል፦ @Holy_scriptures
ኃጢአትን እንዴት አድርገን ነው የምንመለከተው? ይዘናት፣ አቅፈናት እና አሽሞንሙነናት ወይስ ተጸይፈን፣ ትተን እና ነግሰንባት ነው ያለነው?
“ኃጢአቱን የሚሰውር አይለማም፤ የሚናዘዝባትና የሚተዋት ግን ምሕረትን ያገኛል።”
ምሳሌ 28፥13
ወደ ቻናሉ ለመ🀄️ላ🀄️ል፦ @Holy_scriptures
❤7🙏4
. ──•◈•─────•◈•─
የዕለቱ ጥቅስ
──•◈•─────•◈•─
“የዚህ ሕግ መጽሐፍ ከአፍህ አይለይ፥ ነገር ግን የተጻፈበትን ሁሉ ትጠብቅና ታደርግ ዘንድ በቀንም በሌሊትም አስበው፤ የዚያን ጊዜም መንገድህ ይቀናልሃል ይከናወንልሃልም።”
ኢያሱ 1፥8

❤11
እንዴት ሐሰተኛ መምህራንና ሐሰተኛ ነብያትን መለየት እችላለው?
ኢየሱስ ክርስቶሰ ሐሰተኛ ክርስቶሶችና ሐሰተኛ ነብያት እንደሚመጡና የተመረጡትን እንኳ ሊያስቱ እንደሚችሉ አስጠንቅቋል (ማቴ 24፥23-27፤ እንዲሁም 2 ጴጥ 3፥3 እና ይሁዳ 17-18). ከሐሰተኛ ልምምድ ከስህተት አስተምህሮ ራስህን የምትጠብቅበት ትልቁ መንገድ እውነትን ማወቅ ነው፡፡ አስመስሎ የተሰራውን ውሸት ለይቶ አውቆ ለመቃወም እውነተኛውን ማወቅ፡፡ ማንኛውም አማኝ እውነትን ‹‹በትክክል የያዘ›› (2 ጢሞ 2፥15) እና ቃሉን በጥንቃቄ የሚያጠና ሐሰተኛ አስተምህሮን ለይቶ ማወቅ ይችላል፡፡ ለምሳሌ በማቴ 3፥16-17 ያለውን የአባትነት (የእግዚአብሔርን) የልጅ (የኢየሱስ ክርስቶስን) እና የመንፈስ ቅዱስን ስራ ያነበበ ሰው ማንም የስላሴን ትምህርት ቢክድ ወዲያውኑ ጥያቄን ይጠይቃል፡፡ እንግዲያው የመጀመሪያው እርምጃ መጽሐፍ ቅዱስ በማጥናት ሁሉንም ትምህርት ቃሉ እንደሚለው መዳኘት ነው፡፡
ኢየሰስ እንዲህ ብሎአል ‹‹ዛፍ በፍሬው ይታወቃል›› (ማቴ 12፥33)። ፍሬን በሚመለከት ማንኛውም አስተማሪ የትምህርቱን ትክክለኝነት ለመመዘን ሊጠቅምባቸው የሚችልባቸው ሶስት መመዘኛዎች፡-
#1 ይህ አስተማሪ ስለ ኢየሱስ ምን አለ? በማቴ 16፥15-16 ኢየሱስ ‹‹ስለ እኔ ምን ትላላችሁ‹‹ ብሎ ጠየቀ፤ ጴጥሮስ ሲመልስ ‹‹አንተ የህያው የእግዚአብሔር ልጅ ነህ›› አለ፡፡ ጴጥሮስ ለዚህ መልሱ የተባረክህ ነህ ተባለ፡፡ በ 2ኛ ዮሐ 9 ይህን እናነባለን፡- ‹‹ ለሚወጣ ሁሉ በክርስቶስም ትምህርት ለማይኖር ሰው አምላክ የለውም፤ በክርስቶስ ትምህርት ለሚኖር አብና ወልድ አሉት።›› በሌላ አባባል ኢየሱስ ክርስቶስና የእርሱ የመዋጀት ስራ የመጨረሻው ዋና ነገር ነው። ኢየሱስ ከእግዚአብሔር ጋር እኩል አይደለም ብሎ የሚክደውን የኢየሱስን የመስዋዕትነት ሞት የሚያቃልለውን የኢየሱስ ክርስቶስን ሰው መሆን የሚቃወመውን ነቅተን እንጠብቀው፡፡ 1ኛ ዮሐ 2፥22፡- ‹‹ክርስቶስ አይደለም ብሎ ኢየሱስን ከሚክድ በቀር ውሸተኛው ማን ነው? አብንና ወልድን የሚክድ ይህ የክርስቶስ ተቃዋሚ ነው።››
#2 ይህ አስተማሪ ወንጌልን ነው የሚሰብከው? እንደ እግዚአብሔር ቃል የወንጌል ትርጓሜ የኢየሱስ ሞት መቀበር እና መነሳት መልካም ወሬ ነው(1 ቆሮ 15፥1-4)፡፡ መልካም ጥሩ ቢመስሉም ‹‹እግዚአብሔር ይወድሃል›› ‹‹እግዚአብሔር የተራቡትን እንድናበላ ይፈልጋል›› እና ‹‹እግዚአብሔር ባለጠጋ እንድትሆን ይፈልጋል›› የሚሉ አረፍተ ነገሮች ሙሉ የወንጌል መልዕክት አይደሉም፡፡ ጳውሎስ በገላቲያ 1፥7 አስጠንቅቆአል፡- ‹‹እርሱ ግን ሌላ ወንጌል አይደለም፤ የሚያናውጡአችሁ የክርስቶስንም ወንጌል ሊያጣምሙ የሚወዱ አንዳንዶች አሉ እንጂ።›› ማንም ሰው ምንም አይነት የታወቀ ሰባኪ እግዚአብሔር የሰጠንን መልዕክት መለወጥ መብት የለውም፡፡ ገላ 1፥9፡- ‹‹አስቀድመን እንዳልን እንዲሁ አሁን ሁለተኛ እላለሁ፥ ከተቀበላችሁት የተለየውን ማንም ቢሰብክላችሁ የተረገመ ይሁን።››
#3 ይህ አስተማሪ እግዚአብሔርን የሚያከብር ባሕሪ ይታይበታል? ስለ ሐሰተኛ አስተማሪዎች ይሁዳ 11 እንዲህ ይላል፡- ‹‹ወዮላቸው፥ በቃየል መንገድ ሄደዋልና ስለ ደመወዝም ለበለዓም ስሕተት ራሳቸውን አሳልፈው ሰጥተዋል በቆሬም መቃወም ጠፍተዋል።›› በሌላ አባባል የሐሰተኛ አስተማሪ በትእቢት ተለይቶ ይተወቃል፤ (ቃየን የእግዚአብሔርን እቅድ ተቃወመ) ስስታምነት (በልአም ለገንዘብ ብሎ ተነበየ) አመጽ (የቆሬ ልጆች ራሳቸውን ከሙሴ በላይ ከፍ ማድረግ ፈለጉ) ኢየሱስ ክርስቶስ ከእነዚህ ሰዎች እንዲጠበቁ እና በፍሬያቸው እንደሚታወቁ ተናግሮአል፡፡ (ማቴ 7፡15-20)
ለተጨማሪ ጥናት በቤተክርስቲያን ውስጥ የስህተት አስተምሮዎችን ለመወጋት የተጻፉ የመጽሐፍ ቅዱስ መጽሐፍትን እንደነዚህ ያሉትን ተመልከቱ ገላቲያ፤ 2ኛ ጴጥ፤ 1ኛ ዮሐ፤ 2ኛ ዮሐ፤ እና ይሁዳ፡፡ በአብዛኛው የሐሰተኛ ነብያትን ትንቢት ለይቶ ማወቅ አስቸጋሪ ነው፡፡ ሰይጣን ራሱን የብርሃን መልአክ እስኪመስል ራሱን ይለውጣል(2 ቆሮ 11:14) የእርሱ አገልጋዮች የጽድቅ አገልጋዮች መስለው ራሳቸውን ይለውጣሉ (2 ቆሮ 11:15)፡፡ ከእውነት ጋር በመቀራረብ ብቻ ማስመሰሉን ልንለየው እንችላለን፡፡
ምንጭ:- www.gotquestions.org

❤12👍3
. ──•◈•─────•◈•─
የዕለቱ ጥቅስ
──•◈•─────•◈•─
“ካህኑ የሠራዊት ጌታ የእግዚአብሔር መልእክተኛ ነውና ከንፈሮቹ እውቀትን ይጠብቁ ዘንድ ይገባቸዋል፥ ሰዎችም ሕግን ከአፉ ይፈልጉ ዘንድ ይገባቸዋል።”
ሚልክያስ 2፥7

❤7
"ኑና እንዋቀስ"
ሕይወት ትሠምር ዘንድ፣ሰው ከአምላኩ ምሪትን፣ኃይልን፣ምክርን ወዘተ ሊቀበል ይገባዋል፡፡አለበለዚያ ሕይወት መደዴ ይሆናል፤ፍሬ አልባም፡፡መኪና ወደ ጋራዥ ለእድሳት እንደሚወሰድ ሁሉ፣ወደ ጸጋ ዙፋኑ በመምጣት ምሕረቱንና ጸጋውን ልንቀበል ያስፈልገናል፤አንዴ ብቻ ሳይሆን ሳናቋርጥ፡፡ የእግዚአብሔር ቃል “ውኃውንም ከመድኃኒት ምንጮች በደስታ ትቀዳላችሁ”(ኢሳይያስ 12:3) የሚለውም ለዚህ ነው፤ወደ ምንጩ መጥተን የመቅዳቱ ኀላፊነት የኛ እንደ ሆነ ሲያመለክት፣ያለ ማቋረጥ መሆኑንም፡፡
ሰው ወደ ጌታው ሕልውና ሲመጣ፣ራሱን የማየት ጊዜ ያገኛል፡፡በሕይወቱ ያላስተዋላቸውን መሠረታዊ ችግሮች የመረዳትና የመገንዘብም ዕድል ይኖረዋል::ቃሉ “የተሰወረውን ኃጢአታችንን በፊትህ ብርሃን፥ በደላችንንም በፊትህአስቀመጥህ” (መዝሙር 90፡8) እንደሚል፣ ከሕሊናችን የተሰወሩና ያልተናዘዝናቸው ኃጢአቶችን (እንዳሉም ያላሰብናቸውን) የማየት አጋጣሚው ይኖረናል፡፡
በጌታ ፊት የምንሆንባቸው ጊዜያት የባከኑ እንደ ሆኑ ልናስብ አይገባም፤እንዳውም ጥሩ የሕክምና ጊዜ፣ጥሩ የመሠሪያ ጊዜ እንደ ሆነ እንጂ፡፡ታዲያ በትሕትና የውስጣችንን ችግሮች ዘክዝከን፣ነፍሳችን አፍስሰን፣ከምር በሚፈስ እንባ ጥልቅ ንስሐዎችን ብንገባ፣የሚመጣው መታደስ ቀላል አይሆንም፡፡እንዲህ ዓይነት ጊዜዎች ሲበዙልን ነው፣ለውጣችን የሚበዛው፤እድገታችንም ብዥታ የማይኖረው፡፡
ራሳችንን ለመመርመር ጊዜያትን ማመቻቸት አስተዋይነት ይመስለኛል፡፡ጨክኖ ግላዊ ፍተሻ(personal inventory) ማድረግና ከጌታ ጋር ለመሄድ መስማማት ጥበብ ሲሆን፣ወደ ፈጣሪ ሕልውና እየመጣ “ኑና እንዋቀስ” (ኢሳይያስ 1፡18) በሚለው መንፈሳዊ መርሕ ያልተጎበኘ ሕይወት ችግር አለው፡፡ቃሉ “በመመለስና በማረፍ ትድናላችሁ፣በጸጥታና በመታመን ኃይል ይሆንላችኋል”(ኢሳይያስ 30፡15) ይላልና፡፡
አዎ! የጸጥታ ጊዜ፣የእረፍት ጊዜ፣የመመለስና የንስሐ ጊዜያት ለሕይወታችን እጅግ አስፈላጊዎች ናቸው፡፡ያኔ ኃይላችን ይታደሳል፣መንፈሳችን ይጠነክራል፡፡ያኔ በአዲስ አተያይና ምልከታ፣ተግዳሮቶቻችን እንገጥማለን፡፡መታከትም ይወገዳል፡፡በታደሰ ሕይወትም የሚሠራው ሥራም ብዙ ፍሬን ያፈራል።
ምንጭ:- Divine Wisdom4

❤10
የሐዋርያት የእምነት መግለጫ
እኔ ሁሉን በሚችል፣ ሰማይንና ምድርን በፈጠረ በእግዚአብሔር አብ አምናለሁ፡፡
ደግሞም በአንድ ልጁ፣
በመንፈስ ቅዱስ በተፀነሰ፣
ከድንግል ማርያም በተወለደ፣
በጴንጤናዊው በጲላጦስ ዘመን መከራን በተቀበለ፣
በተሰቀለ፣ በሞተ እና በተቀበረ፤
ወደ ሲዖልም በወረደ፡፡
በሦስተኛውም ቀን ከሙታን በተነሣ፡፡
ወደ ሰማይም በወጣ
ሁሉን በሚችል በእግዚአብሔር አብ ቀኝ በተቀመጠ፣
በሕያዋንና በሙታን ሊፈርድ ከዚያም በሚመለስ፣
በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ አምናለሁ፡፡
ደግሞም በመንፈስ ቅዱስ፣
በአንዲት ቅድስት የሐዋርያት ቤተክርስቲያን፣
በቅዱሳን አንድነት፣
በኀጢአት ስርየት፣
በሥጋ ትንሣኤ፣
በዘላለም ሕይወት አምናለሁ፡፡ አሜን፡፡
ወደ ቻናሉ ለመ🀄️ላ🀄️ል👉 @TME_bible_study

❤27🔥12👍1
. ──•◈•─────•◈•─
የዕለቱ ጥቅስ
──•◈•─────•◈•─
“ስለዚህ፥ እነሆ፥ የሰላሜን ቃል ኪዳን እሰጠዋለሁ።”
ዘኍልቁ 25፥12
ወደ ቻናሉ ለመ🀄️ላ🀄️ል፦ @Holy_scriptures
የዕለቱ ጥቅስ
──•◈•─────•◈•─
“ስለዚህ፥ እነሆ፥ የሰላሜን ቃል ኪዳን እሰጠዋለሁ።”
ዘኍልቁ 25፥12
ወደ ቻናሉ ለመ🀄️ላ🀄️ል፦ @Holy_scriptures
❤8👏1
. ──•◈•─────•◈•─
የዕለቱ ጥቅስ
──•◈•─────•◈•─
“ስለ ሥጋ ማሰብ ሞት ነውና፥ ስለ መንፈስ ማሰብ ግን ሕይወትና ሰላም ነው።”
ሮሜ 8፥6

ለዕረፍት ተጠርተናል
ጌታ በተለያየ በሚገባን መንገድ “ዕረፍት” እንዲህ ነው ብሎ ያሳየናል፣ይጠቁመናል፣ ያቀምሰናል፡፡ቢሆንም ሙሉ የሆነ ዕረፍት የሚመጣው፣ በትጋት በፊቱ በመሆን የጌታ ጸጋ በሕይወታችን እየጨመረ ሲመጣ እንደ ሆነ ልብ ይሏል፡፡
ጌታችን የዕረፍት አምላክ ነውና ሊያሳርፈን ይፈልጋል፡፡ለእኛ ያለው ግልጽ የሆነው የልብ ሐሳቡም እንዲህ የሚል ነው፡-
“እኔ ሕይወት እንዲሆንላችሁ እንዲበዛላችሁ መጣሁ” (ዮሐንስ 10፡10)
ነገር ግን የብዙዎቻችን አኗኗር ሲታይ የዚህን አስደናቂ የተስፋ ቃል ምንነትና በውስጡ የያዘውን በረከት በሚገባ የተረዳነው አይመስልም፡፡ ዋናው ችግራችንም ልባችን ስቷል፡፡ ልባችን መሳቱን የሚያረጋግጥልን ደግሞ በማያሳርፉ ነገሮች ለማረፍ ሲቧጥጥና ሲያልም ማደሩ ነው፡፡ የእግዚአብሔር ቃል ስለ እስራኤላውያን የምድረ በዳ ሕይወት ሲናገር “ሁል ጊዜ ልባቸው ይስታል፤ እነርሱም መንገዴን አላወቁም አልሁ፡፡ወደ ዕረፍቴም እንዳይገቡ በቁጣዬ ማልሁ” (መዝ 95 ፥10-11) ይላል፡፡ አዎ ልባችን ስቷል እንጂ ሌላ ምን ሊሆን ይችላል? የጌታ መንፈስ በተለያየ መንገድ “ዕረፍት ይህች ናት የደከመውንም አሳርፉ ይህችም ማረፊያ ናት አላቸው እነርሱ መስማትን እንቢ አሉ” (ኢሳ 28፥12) እንደሚል ሆኖብናል፡፡
የእግዚአብሔር ቃል “ይሳኮር አጥንተ ብርቱ አህያ ነው፤በበጎች ጉረኖም መካከል ያርፋል፡፡ዕረፍትም መልካም መሆንዋን አየ” (ዘፍጥረት 49፥14-15) ይለናል፡፡ የውስጣዊ ዕረፍት መልካምነት ምንም አያጠያይቅም፤ በሁሉም መልኩ ይጠቅማል፡፡መንፈሳችን ከእግዚአብሔር ለመስማት ይመቻቻል፤ የአእምሮአችንን የመሥራት እና የፈጠራ ችሎታ ይጨምረዋል፤ የእግዚአብሔርን ሥራ በቅጡ እንድሠራ ያስችለናል፤ ማኅበራዊ ሕይወታችንን እንዲስተካከል አመቺ ሁኔታን ይፈጥራል፤ ዕረፍቱ በራሱ ለሰዎች የሚታይ ጠንካራ መልዕክት ነው (በተለይ ለማያምኑ ሰዎች) ፡፡
ከጌታቸው የተማሩ እና ያረፉ ሰዎች ከሕይወት ምልልሳቸው ይታወቃሉ፡፡ሲቅበጠበጡና ሲባዝኑ አይታዩም፡፡እንዳውም ሕይወታቸው ከሩቅ ይናገራል፡፡በጌታቸው ያረፉ ሰዎች በቃሉ ጉልበት ውስጣቸው ስለተለወጠ ከማንኛውም ቀንበር ነጻ ናቸው፡፡ቅድሚያ የሚሰጡትን የሚያውቁ ሲሆን፣ ምርጫዎቻቸውም ውሱን ይሆናሉ፡፡ መረጋጋትና ሰላም የሚታይባቸው እና የምሥጋና ሕይወት ያላቸው (የማይነጫነጩ፣ የማያጉረመርሙ) ስለሆነ፣የምድር ጨው ወይም የዓለም ብርሃን ናቸው፡፡ ሰው እነርሱን አይቶ ልቡ ይነካል፡፡ሰው እነርሱን አይቶ የተለወጡበትን ምንጭ ያስተውላል፡፡ሰው እነርሱን አይቶ ወደ እዚህ ድንቅ የዕረፍት አምላክም ይመጣል፡፡
ይቀጥላል...
ምንጭ:- bekedesa7.blogspot.com

❤7👍6
. ──•◈•─────•◈•─
የዕለቱ ጥቅስ
──•◈•─────•◈•─
“ሳትጨልም እግራችሁም በጨለመችው ተራራ ላይ ሳትሰናከል፥ በተስፋ የምትጠባበቁትን ብርሃን ለሞት ጥላና ለድቅድቅ ጨለማ ሳይለውጠው ለአምላካችሁ ለእግዚአብሔር ክብርን ስጡ።”
ኤርምያስ 13፥16

❤8🙏2