ቅዱሳት መጻሕፍት
7.46K subscribers
1.36K photos
61 videos
332 files
802 links
በዚህ ቻናል

👉ቅዱሳት መጻሕፍት ይጠናሉ::
👉መጽሐፍ ቅዱሳዊ ትምህርቶች ይቀርባሉ::
👉 ለቅዱሳት መጽሐፍት ጥናት የሚያግዙ መጻሕፍት ይለቀቃሉ።

⭐️⭐️⭐️⭐️⭐️

@Holy_scriptures
Download Telegram
#እንወያይ

ስለምንገኝበት አጥቢያ ቤተክርስቲያን ወይም ማኅበረ ምዕመናን መሠረታዊ አስተምህሮ (doctrine) ማወቅን እንዴት ትመለከቱታላችሁ? በጣም አስፈላጊ ነው ወይስ እምብዛም ጥቅም የለውም? በዚህ ዙሪያ ብዙ የእውቀት ክፍተት ያለብን አይመስላችሁም?


ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
19
.       ──•◈•─────•◈•─
                          የዕለቱ ጥቅስ
        ──•◈•─────•◈•─
“ከእንግዲህስ ወዲያ ለኃጢአት እንዳንገዛ የኃጢአት ሥጋ ይሻር ዘንድ አሮጌው ሰዋችን ከእርሱ ጋር እንደ ተሰቀለ እናውቃለን፤ የሞተስ ከኃጢአቱ ጸድቋልና።”
ሮሜ 6፥6



ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
4👍4
#ከተማ_ወይም_ቦታ_በቅዱሳት_መጻሕፍት



#ኢይዝራኤል

የቃሉ ትርጒም እግዚአብሔር ይበትናል ወይም «እግዚአብሔር ይዘራል» ማለት ነው። የሆሴዕ ታላቅ ልጅ ስያሜም ነው። ከቦታው ስንጀምር የይሁዳ ከተማ፤ ኢያሱ 15፥56፤ 1ሳሙ. 25፥43። በይሳኮር ርስት ድርሻ ውስጥ ነበረ። በከተማውም አቅራቢያ ያለው ሰፊ ሸለቆ በዚህ ስም ተጠራ፤ ኢያሱ 19፥18፤ ሆሴዕ 1፥5። የናቡቴ ወይን ቦታ በዚያ ነበረ፤ 1ነገ. 20። በዚያም ኢዩ የአክዓብን ቤተ ሰዎችና አለቆች አስፈጀ፤ 2ነገ. 9፥ 17-10፥11። በዚህ ስፍራ በገዦች ላይ ይፈጸም ዘንድ የተነገረውን ፍርድ የሚያጸና ነው፡፡ ዳግማዊ ኢዮርብዓም፣ የአክአብን ልጅ የኢዮራምን መንግሥት በመገልበጥ (2ነገ 9፥14-37፤ ከ1ነገ19፥16-17) በኢይዝራኤል ከተመሠረተው ከኢዩ ሥርወ መንግሥት የመጣ ነው (በ841-814 ዓመተ ቅድመ ክርስቶስ)፤ የኢዩ ሥርወ መንግሥት ያከተመው ዘካርያስ በተገደለበት በ753 ዓመተ ቅድመ ክርስቶስ ነው (2ነገ 15፥8-10)፡፡

ለሆሴዕና ለጎሜር ሦስት ልጆች ተወለዱ፤ ለእያንዳንዳቸውም ትእምርታዊ ስም ተሰጥቶአቸዋል፡፡ “ኢይዝራኤል” የሚለው ስም የሚያመለክተው፣ ኢዩ ያፈሰሰውን “ደም” ለመበቀል እግዚአብሔር በቅጣት የሚነሣበትን የወደፊቱን ቀን ነው፡፡ ኢዩ የእግዚአብሔርን ትእዛዝ በመፈጸሙ መልካም ቢያደርግም (2ነገ 9፥1-10)፣ እግዚአብሔር ካዘዘው በላይ ብዙ ሰዎችን ገድሎ ነበር፡፡ የኢዩ ኀጢአት የተቀጣው እስራኤል መንግሥት መሆኗ እንዲቆም በመደረጉ ነበር (ይህ በ722 ዓመተ ቅድመ ክርስቶስ ሆኖአል)፡፡



ምንጭ፦ የመጽሐፍ ቅዱስ መዝገበ ቃላት፤ ገጽ 170፣ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከማጥኛ ጹሑፍ ጋር፤ ገጽ 1318፣ የብሉይ ኪዳን ማብራሪያ፤ ገጽ 1005



ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
4👏1
.       ──•◈•─────•◈•─
                          የዕለቱ ጥቅስ
        ──•◈•─────•◈•─
“ነገር ግን በጌታችንና በመድኃኒታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ጸጋና እውቀት እደጉ።”
2ኛ ጴጥሮስ 3፥18



ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
9👍1
#መጻሕፍትን_በድምጽ

በቀጣይ

📔ርዕስ፦ ፍሬያማ ሕይወት
👤ጸሐፊ፦ ጥላሁን ኃይሌ


ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
4👍2
ክርስትና በ ፓልስቲን ሲጀምር ሕይወት ነበረ ፣ ወደ ግሪክ ሲደርስ ፍልስፍና ሆነ ፣ሮም ሲገባ ተቋም ሆነ ፣ አውሮፓና አሜሪካ ሲደርስ ንግድ ሆነ!!
#በእኛ_ህይወትስ?🤔
ዶክተር ማሙሻ ፈንታ



ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
8🤔8😢2👏1🤯1
#የእግዚአብሔር_ቃል_ምን_ይላል


ሚልክያስ 1
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
¹⁰ በመሠዊያዬ ላይ እሳትን በከንቱ እንዳታቃጥሉ ከእናንተ ዘንድ ደጅ የሚዘጋ ሰው ምነው በተገኘ! በእናንተ ደስ አይለኝም፥ ቍርባንንም ከእጃችሁ አልቀበልም፥ ይላል የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር።
¹¹ ከፀሐይ መውጫ ጀምሮ እስከ መግቢያዋ ድረስ ስሜ በአሕዛብ ዘንድ ታላቅ ይሆናልና፤ በየስፍራውም ለስሜ ዕጣን ያጥናሉ፥ ንጹሕም ቍርባን ያቀርባሉ፤ ስሜ በአሕዛብ ዘንድ ታላቅ ይሆናልና፥ ይላል የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር።
¹² እናንተ ግን፦ የእግዚአብሔር ገበታ ርኩስ ነው፤ ፍሬውና መብሉም የተናቀ ነው በማለታችሁ አስነቀፋችሁት።
¹³ እናን፦ እነሆ፥ ይህ ድካም ነው ብላችሁ ጢቅ አላችሁበት፥ ይላል የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር፤ በቅሚያ የያዛችሁትንም አንካሳውንም የታመመውንም አቅርባችኋል፤ እንዲሁ ቍርባንን ታመጣላችሁ በውኑ ከእጃችሁ ይህን ልቀበለውን? ይላል እግዚአብሔር።
¹⁴ እኔ ታላቅ ንጉሥ ነኝና፥ ይላል የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር፥ ስሜም በአሕዛብ ዘንድ የተፈራ ነውና በመንጋው ውስጥ ተባት እያለው ለጌታ ተስሎ ነውረኛውን የሚሠዋ ሸንጋይ ሰው ርጉም ይሁን።




ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
👍52🙏1
.       ──•◈•─────•◈•─
                          የዕለቱ ጥቅስ
        ──•◈•─────•◈•─
“አካሄዳችሁ ገንዘብን ያለ መውደድ ይሁን፥ ያላችሁም ይብቃችሁ፤ እርሱ ራሱ፦ አልለቅህም ከቶም አልተውህም ብሎአልና፤”
ዕብራውያን 13፥5



ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
12
ቅዱሳት መጻሕፍት
.       ──•◈•─────•◈•─                           የዕለቱ ጥቅስ         ──•◈•─────•◈•─ “አካሄዳችሁ ገንዘብን ያለ መውደድ ይሁን፥ ያላችሁም ይብቃችሁ፤ እርሱ ራሱ፦ አልለቅህም ከቶም አልተውህም ብሎአልና፤” ዕብራውያን 13፥5 ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
"የገንዘብ ፍቅር አይግዛችሁ ፤ ባላችሁ ነገር ረክታችሁ ለመኖር ጣሩ። ምክንያቱም እግዚአብሔር፥ 'ምን ጊዜም ቢሆን በችግራችሁ እደርስላችኋለሁ ፤ ምን ጊዜም ቢሆን አልተዋችሁም' ብሎ ተናግሮአልና።"
ዕብራውያን 13፥5 (ሕያው ቃል)
11🥰7🔥1
#እራሳችንን_እንመርምር


ኃጢአትን እንዴት አድርገን ነው የምንመለከተው? ይዘናት፣ አቅፈናት እና አሽሞንሙነናት ወይስ ተጸይፈን፣ ትተን እና ነግሰንባት ነው ያለነው?

“ኃጢአቱን የሚሰውር አይለማም፤ የሚናዘዝባትና የሚተዋት ግን ምሕረትን ያገኛል።”
ምሳሌ 28፥13



ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
7🙏4
.       ──•◈•─────•◈•─
                          የዕለቱ ጥቅስ
        ──•◈•─────•◈•─
“የዚህ ሕግ መጽሐፍ ከአፍህ አይለይ፥ ነገር ግን የተጻፈበትን ሁሉ ትጠብቅና ታደርግ ዘንድ በቀንም በሌሊትም አስበው፤ የዚያን ጊዜም መንገድህ ይቀናልሃል ይከናወንልሃልም።”
ኢያሱ 1፥8



ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
11
Friutful Life
Nigusse Denano
#መጻሕፍትን_በድምጽ

📔ርዕስ፦ ፍሬያማ ሕይወት
👤ጸሐፊ፦ ጥላሁን ኃይሌ
👉ክፍል-1


ይቀጥላል...


ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
4
እንዴት ሐሰተኛ መምህራንና ሐሰተኛ ነብያትን መለየት እችላለው?


ኢየሱስ ክርስቶሰ ሐሰተኛ ክርስቶሶችና ሐሰተኛ ነብያት እንደሚመጡና የተመረጡትን እንኳ ሊያስቱ እንደሚችሉ አስጠንቅቋል (ማቴ 24፥23-27፤ እንዲሁም 2 ጴጥ 3፥3 እና ይሁዳ 17-18). ከሐሰተኛ ልምምድ ከስህተት አስተምህሮ ራስህን የምትጠብቅበት ትልቁ መንገድ እውነትን ማወቅ ነው፡፡ አስመስሎ የተሰራውን ውሸት ለይቶ አውቆ ለመቃወም እውነተኛውን ማወቅ፡፡ ማንኛውም አማኝ እውነትን ‹‹በትክክል የያዘ›› (2 ጢሞ 2፥15) እና ቃሉን በጥንቃቄ የሚያጠና ሐሰተኛ አስተምህሮን ለይቶ ማወቅ ይችላል፡፡ ለምሳሌ በማቴ 3፥16-17 ያለውን የአባትነት (የእግዚአብሔርን) የልጅ (የኢየሱስ ክርስቶስን) እና የመንፈስ ቅዱስን ስራ ያነበበ ሰው ማንም የስላሴን ትምህርት ቢክድ ወዲያውኑ ጥያቄን ይጠይቃል፡፡ እንግዲያው የመጀመሪያው እርምጃ መጽሐፍ ቅዱስ በማጥናት ሁሉንም ትምህርት ቃሉ እንደሚለው መዳኘት ነው፡፡

ኢየሰስ እንዲህ ብሎአል ‹‹ዛፍ በፍሬው ይታወቃል›› (ማቴ 12፥33)። ፍሬን በሚመለከት ማንኛውም አስተማሪ የትምህርቱን ትክክለኝነት ለመመዘን ሊጠቅምባቸው የሚችልባቸው ሶስት መመዘኛዎች፡-

#1 ይህ አስተማሪ ስለ ኢየሱስ ምን አለ? በማቴ 16፥15-16 ኢየሱስ ‹‹ስለ እኔ ምን ትላላችሁ‹‹ ብሎ ጠየቀ፤ ጴጥሮስ ሲመልስ ‹‹አንተ የህያው የእግዚአብሔር ልጅ ነህ›› አለ፡፡ ጴጥሮስ ለዚህ መልሱ የተባረክህ ነህ ተባለ፡፡ በ 2ኛ ዮሐ 9 ይህን እናነባለን፡- ‹‹ ለሚወጣ ሁሉ በክርስቶስም ትምህርት ለማይኖር ሰው አምላክ የለውም፤ በክርስቶስ ትምህርት ለሚኖር አብና ወልድ አሉት።›› በሌላ አባባል ኢየሱስ ክርስቶስና የእርሱ የመዋጀት ስራ የመጨረሻው ዋና ነገር ነው። ኢየሱስ ከእግዚአብሔር ጋር እኩል አይደለም ብሎ የሚክደውን የኢየሱስን የመስዋዕትነት ሞት የሚያቃልለውን የኢየሱስ ክርስቶስን ሰው መሆን የሚቃወመውን ነቅተን እንጠብቀው፡፡ 1ኛ ዮሐ 2፥22፡- ‹‹ክርስቶስ አይደለም ብሎ ኢየሱስን ከሚክድ በቀር ውሸተኛው ማን ነው? አብንና ወልድን የሚክድ ይህ የክርስቶስ ተቃዋሚ ነው።››

#2 ይህ አስተማሪ ወንጌልን ነው የሚሰብከው? እንደ እግዚአብሔር ቃል የወንጌል ትርጓሜ የኢየሱስ ሞት መቀበር እና መነሳት መልካም ወሬ ነው(1 ቆሮ 15፥1-4)፡፡ መልካም ጥሩ ቢመስሉም ‹‹እግዚአብሔር ይወድሃል›› ‹‹እግዚአብሔር የተራቡትን እንድናበላ ይፈልጋል›› እና ‹‹እግዚአብሔር ባለጠጋ እንድትሆን ይፈልጋል›› የሚሉ አረፍተ ነገሮች ሙሉ የወንጌል መልዕክት አይደሉም፡፡ ጳውሎስ በገላቲያ 1፥7 አስጠንቅቆአል፡- ‹‹እርሱ ግን ሌላ ወንጌል አይደለም፤ የሚያናውጡአችሁ የክርስቶስንም ወንጌል ሊያጣምሙ የሚወዱ አንዳንዶች አሉ እንጂ።›› ማንም ሰው ምንም አይነት የታወቀ ሰባኪ እግዚአብሔር የሰጠንን መልዕክት መለወጥ መብት የለውም፡፡ ገላ 1፥9፡- ‹‹አስቀድመን እንዳልን እንዲሁ አሁን ሁለተኛ እላለሁ፥ ከተቀበላችሁት የተለየውን ማንም ቢሰብክላችሁ የተረገመ ይሁን።››

#3 ይህ አስተማሪ እግዚአብሔርን የሚያከብር ባሕሪ ይታይበታል? ስለ ሐሰተኛ አስተማሪዎች ይሁዳ 11 እንዲህ ይላል፡- ‹‹ወዮላቸው፥ በቃየል መንገድ ሄደዋልና ስለ ደመወዝም ለበለዓም ስሕተት ራሳቸውን አሳልፈው ሰጥተዋል በቆሬም መቃወም ጠፍተዋል።›› በሌላ አባባል የሐሰተኛ አስተማሪ በትእቢት ተለይቶ ይተወቃል፤ (ቃየን የእግዚአብሔርን እቅድ ተቃወመ) ስስታምነት (በልአም ለገንዘብ ብሎ ተነበየ) አመጽ (የቆሬ ልጆች ራሳቸውን ከሙሴ በላይ ከፍ ማድረግ ፈለጉ) ኢየሱስ ክርስቶስ ከእነዚህ ሰዎች እንዲጠበቁ እና በፍሬያቸው እንደሚታወቁ ተናግሮአል፡፡ (ማቴ 7፡15-20)

ለተጨማሪ ጥናት በቤተክርስቲያን ውስጥ የስህተት አስተምሮዎችን ለመወጋት የተጻፉ የመጽሐፍ ቅዱስ መጽሐፍትን እንደነዚህ ያሉትን ተመልከቱ ገላቲያ፤ 2ኛ ጴጥ፤ 1ኛ ዮሐ፤ 2ኛ ዮሐ፤ እና ይሁዳ፡፡ በአብዛኛው የሐሰተኛ ነብያትን ትንቢት ለይቶ ማወቅ አስቸጋሪ ነው፡፡ ሰይጣን ራሱን የብርሃን መልአክ እስኪመስል ራሱን ይለውጣል(2 ቆሮ 11:14) የእርሱ አገልጋዮች የጽድቅ አገልጋዮች መስለው ራሳቸውን ይለውጣሉ (2 ቆሮ 11:15)፡፡ ከእውነት ጋር በመቀራረብ ብቻ ማስመሰሉን ልንለየው እንችላለን፡፡


ምንጭ:- www.gotquestions.org



ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
12👍3
.       ──•◈•─────•◈•─
                          የዕለቱ ጥቅስ
        ──•◈•─────•◈•─
“ካህኑ የሠራዊት ጌታ የእግዚአብሔር መልእክተኛ ነውና ከንፈሮቹ እውቀትን ይጠብቁ ዘንድ ይገባቸዋል፥ ሰዎችም ሕግን ከአፉ ይፈልጉ ዘንድ ይገባቸዋል።”
ሚልክያስ 2፥7



ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
7
Fruitful Life
Nigusse Denano
#መጻሕፍትን_በድምጽ

📔ርዕስ፦ ፍሬያማ ሕይወት
👤ጸሐፊ፦ ጥላሁን ኃይሌ
👉ክፍል-2


ይቀጥላል...


ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
"ኑና እንዋቀስ"


ሕይወት ትሠምር ዘንድ፣ሰው ከአምላኩ ምሪትን፣ኃይልን፣ምክርን ወዘተ ሊቀበል ይገባዋል፡፡አለበለዚያ ሕይወት መደዴ ይሆናል፤ፍሬ አልባም፡፡መኪና ወደ ጋራዥ ለእድሳት እንደሚወሰድ ሁሉ፣ወደ ጸጋ ዙፋኑ በመምጣት ምሕረቱንና ጸጋውን ልንቀበል ያስፈልገናል፤አንዴ ብቻ ሳይሆን ሳናቋርጥ፡፡ የእግዚአብሔር ቃል “ውኃውንም ከመድኃኒት ምንጮች በደስታ ትቀዳላችሁ”(ኢሳይያስ 12:3) የሚለውም ለዚህ ነው፤ወደ ምንጩ መጥተን የመቅዳቱ ኀላፊነት የኛ እንደ ሆነ ሲያመለክት፣ያለ ማቋረጥ መሆኑንም፡፡

ሰው ወደ ጌታው ሕልውና ሲመጣ፣ራሱን የማየት ጊዜ ያገኛል፡፡በሕይወቱ ያላስተዋላቸውን መሠረታዊ ችግሮች የመረዳትና የመገንዘብም ዕድል ይኖረዋል::ቃሉ “የተሰወረውን ኃጢአታችንን በፊትህ ብርሃን፥ በደላችንንም በፊትህአስቀመጥህ” (መዝሙር 90፡8) እንደሚል፣ ከሕሊናችን የተሰወሩና ያልተናዘዝናቸው ኃጢአቶችን (እንዳሉም ያላሰብናቸውን) የማየት አጋጣሚው ይኖረናል፡፡

በጌታ ፊት የምንሆንባቸው ጊዜያት የባከኑ እንደ ሆኑ ልናስብ አይገባም፤እንዳውም ጥሩ የሕክምና ጊዜ፣ጥሩ የመሠሪያ ጊዜ እንደ ሆነ እንጂ፡፡ታዲያ በትሕትና የውስጣችንን ችግሮች ዘክዝከን፣ነፍሳችን አፍስሰን፣ከምር በሚፈስ እንባ ጥልቅ ንስሐዎችን ብንገባ፣የሚመጣው መታደስ ቀላል አይሆንም፡፡እንዲህ ዓይነት ጊዜዎች ሲበዙልን ነው፣ለውጣችን የሚበዛው፤እድገታችንም ብዥታ የማይኖረው፡፡

ራሳችንን ለመመርመር ጊዜያትን ማመቻቸት አስተዋይነት ይመስለኛል፡፡ጨክኖ ግላዊ ፍተሻ(personal inventory) ማድረግና ከጌታ ጋር ለመሄድ መስማማት ጥበብ ሲሆን፣ወደ ፈጣሪ ሕልውና እየመጣ “ኑና እንዋቀስ” (ኢሳይያስ 1፡18) በሚለው መንፈሳዊ መርሕ ያልተጎበኘ ሕይወት ችግር አለው፡፡ቃሉ “በመመለስና በማረፍ ትድናላችሁ፣በጸጥታና በመታመን ኃይል ይሆንላችኋል”(ኢሳይያስ 30፡15) ይላልና፡፡


አዎ! የጸጥታ ጊዜ፣የእረፍት ጊዜ፣የመመለስና የንስሐ ጊዜያት ለሕይወታችን እጅግ አስፈላጊዎች ናቸው፡፡ያኔ ኃይላችን ይታደሳል፣መንፈሳችን ይጠነክራል፡፡ያኔ በአዲስ አተያይና ምልከታ፣ተግዳሮቶቻችን እንገጥማለን፡፡መታከትም ይወገዳል፡፡በታደሰ ሕይወትም የሚሠራው ሥራም ብዙ ፍሬን ያፈራል።


ምንጭ:- Divine Wisdom4


    

ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
10
የሐዋርያት የእምነት መግለጫ


እኔ ሁሉን በሚችል፣ ሰማይንና ምድርን በፈጠረ በእግዚአብሔር አብ አምናለሁ፡፡
ደግሞም በአንድ ልጁ፣
በመንፈስ ቅዱስ በተፀነሰ፣
ከድንግል ማርያም በተወለደ፣
በጴንጤናዊው በጲላጦስ ዘመን መከራን በተቀበለ፣
በተሰቀለ፣ በሞተ እና በተቀበረ፤
ወደ ሲዖልም በወረደ፡፡
በሦስተኛውም ቀን ከሙታን በተነሣ፡፡
ወደ ሰማይም በወጣ
ሁሉን በሚችል በእግዚአብሔር አብ ቀኝ በተቀመጠ፣
በሕያዋንና በሙታን ሊፈርድ ከዚያም በሚመለስ፣
በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ አምናለሁ፡፡
ደግሞም በመንፈስ ቅዱስ፣
በአንዲት ቅድስት የሐዋርያት ቤተክርስቲያን፣
በቅዱሳን አንድነት፣
በኀጢአት ስርየት፣
በሥጋ ትንሣኤ፣
በዘላለም ሕይወት አምናለሁ፡፡ አሜን፡፡


ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️👉 @TME_bible_study
27🔥12👍1
.       ──•◈•─────•◈•─
                          የዕለቱ ጥቅስ
        ──•◈•─────•◈•─
“ስለዚህ፥ እነሆ፥ የሰላሜን ቃል ኪዳን እሰጠዋለሁ።”
ዘኍልቁ 25፥12



ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
8👏1
Friutful Life
Nigusse Denano
#መጻሕፍትን_በድምጽ

📔ርዕስ፦ ፍሬያማ ሕይወት
👤ጸሐፊ፦ ጥላሁን ኃይሌ
👉ክፍል-3


ይቀጥላል...


ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
2
ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
1
የምናምነውን እንወቅ.pdf
1.6 MB
ርዕስ፦ የምናምነው እንወቅ አውቀን ያመንነውን አንልቀቅ
ጸሐፊ፦ ዶ/ር መለሰ ወጉ

ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
5