ቅዱሳት መጻሕፍት
አራቱ ደስታችንን ሊጠብቁ የሚችሉ አመለካከቶች 1. አንድ አሳብ - ፊልጵስዩስ 1 «ሁለት አሳብ ላለው በመንገዱ ሁሉ ለሚወላውል ... አንዳች እንዲያገኝ አይምሰለው» (ያዕ. 1፡8)። ወይንም በጥንት ላቲን ቋንቋ፥ «የመርከቡ ነጂ የሚያርፍበትን ወደብ ካላወቀ የትኛውም ነፋስ አይረዳውም» የሚል ምሳሌ አለ። ለብዙ ክርስቲያኖች በሁኔታዎች አለመሳካት የብስጭት ምክንያት የሚሆነው በ«አንድ አሳብ» ስለማይረጉ…
የቀጠለ...
አራቱ ደስታችንን ሊጠብቁ የሚችሉ አመለካከቶች
2. የሚገዛ አሳብ - ፊልጵስዩስ 2
ይህ ምዕራፍ የሚያተኩረው በሰዎች ላይ ነው፥ መሪ ጥቅሱም «ለወገኔ ይጠቅማል በማለት ወይም በከንቱ ውዳሴ ምክንያት አንድ እንኳ አታድርጉ፥ ነገር ግን እያንዳንዱ ባልንጀራው ከራሱ ይልቅ እንዲሻል በትሕትና ይቁጠር» (2፡3)። በምዕራፍ 1 ላይ ጳውሎስ ክርስቶስን የመጀመሪያው መሻቱ ሲያደርግ፥ በዚህ ምዕራፍ፥ ደግሞ ሌሎችን በሁለተኛ ደረጃ አስቀምጧቸዋል። ይህም የሚያሳየን ራሱን መጨረሻ ማድረጉ ነው! ብዙ ጊዜ በሰዎች ላይ የምንቆጣበት ምክንያት በእኛ አሳብ ስለማይመሩልን ነው። በሕይወት በምንጓዝበት ወቅት እራሳችንን መጀመሪያ ካደረግን፥ እንዲሁም ሌሎችም ራሳቸውን መጀመሪያ ካደረጉ፥ ያንጊዜ በብዙ ነጥቦች ላይ ኃይለኛ ግጭት ይፈጠራል።
አንዲት እናት እና ወንድ ልጇ ወደ ሐኪም ቢሮ ለመሄድ ወደ አሳንሰሩ (ሊፍት) ውስጥ ገቡ። ከሁለተኛው ፎቅ ላይ እንደደረሱም ሌሎች ሰዎች ተጨመሩ። ከእነርሱም መሀል አንዲት ወፍራም ሴት ነበረች። አሳንሰሩም ወደ ላይ መውጣቱን እንደቀጠለ ጸጥታው በወፍራሟ ሴት ጩኸት ደፈረሰ። ወደ ልጁም እናት ዘወር ብላ «ልጅሽ ነከሰኝ እኮ!» አለቻት።
እናትየው በጣም ተሳቀቀች፥ ልጁ ግን ማብራሪያ ነበረው «ፊቴን በቂጧ ስላጣበቀችኝ ነው የነከስኳት» ብሎ አስረዳት።
በአሳንሰሩ ውስጥ የተከሰተው ድርጊት በዓለም ዙሪያ ሁሉ ሲፈፀም የምንመለከተው ነው። ሕዝብ ከሕዝብ፥ መንግሥታት ከመንግሥታት ይነካከሳሉ፥ ምክንያቱም ተፋፍገው ስለሚኖሩ ነው።
ነገር ግን የሚገዛ ትሑት ልብ ያለው ክርስቲያን ሌሎችን ያገለግላል እንጂ ሌላ ሰው እርሱን መጥቶ እንዲያገለግለው አይጠብቅም። ከራሱ ፍላጎትና እቅድ ይልቅ ለሌሎች ምኞት መሟላት ቅድሚያ ይሰጣል። በምዕራፍ 2 ውስጥ በትሑት ልቦናቸው ምሳሌ ሊሆኑን የሚችሉ 4 አስገራሚ ሰዎች እናገኛለን። እነርሱም ኢየሱስ ክርስቶስ (2፡1-11)፥ ጳውሎስ (2፡12-18)፥ ጢሞቴዎስ (2፡19-24) እና አፍሮዲጡን (2፡25-30) ናቸው። እነዚህ ምሳሌዎች «ራሱን ከፍ የሚያደርግ ሁሉ ይዋረዳልና፤ ራሱንም የሚያዋርድ ከፍ ይላል» (ሉቃ. 14፡11) የሚለውን መርሆ ያረጋግጡልናል።
ይቀጥላል...
ምንጭ፦ ዋረን ደብልዩ ዌርዝ ቢ፤ ደስተኛ ሁን፤ የፊልጵስዩስ መልእክት ፤ ገጽ 7-8
ወደ ቻናሉ ለመ🀄️ላ🀄️ል፦ @Holy_scriptures

❤8
. ──•◈•─────•◈•─
የዕለቱ ጥቅስ
──•◈•─────•◈•─
“ሀብትህን ሰባት ቦታ፣ እንዲያውም ስምንት ቦታ ከፍለህ አስቀምጥ፤ በምድሪቱ ላይ የሚመጣውን ጥፋት አታውቅምና።”
መክብብ 11፥2 (አዲሱ መ.ት)

❤8🔥2🤝1
ቅዱሳት መጻሕፍት
የቀጠለ... አራቱ ደስታችንን ሊጠብቁ የሚችሉ አመለካከቶች 2. የሚገዛ አሳብ - ፊልጵስዩስ 2 ይህ ምዕራፍ የሚያተኩረው በሰዎች ላይ ነው፥ መሪ ጥቅሱም «ለወገኔ ይጠቅማል በማለት ወይም በከንቱ ውዳሴ ምክንያት አንድ እንኳ አታድርጉ፥ ነገር ግን እያንዳንዱ ባልንጀራው ከራሱ ይልቅ እንዲሻል በትሕትና ይቁጠር» (2፡3)። በምዕራፍ 1 ላይ ጳውሎስ ክርስቶስን የመጀመሪያው መሻቱ ሲያደርግ፥ በዚህ ምዕራፍ፥…
የቀጠለ...
አራቱ ደስታችንን ሊጠብቁ የሚችሉ አመለካከቶች
3. መንፈሳዊ አሳብ - ፊልጵስዩስ 3
በዚህ ምዕራፍ ውስጥ ጳውሎስ ወደ አሥራ አንድ ጊዜ ያህል «ነገር» የሚለውን ቃል ሲጠቀም ታገኛላችሁ። የአብዛኛዎቹ ሰዎች «አሳባቸው ምድራዊ» (3፡19) ለሆኑ ነገሮች ሲሆን፥ መንፈሳዊ ልብ ያላቸው ክርስቲያኖች ግን የሚጨነቁት ስለ ሰማያዊ ነገሮች መሆኑን ያሳየናል። «እኛ አገራችን በሰማይ ነውና፥ ከዚያም ደግሞ የሚመጣ መድኃኒት እርሱም ጌታን ኢየሱስ ክርስቶስን እንጠባበቃለን» (3፡20)። መንፈሳዊ ልብ ያለው ሰው የዚህን ዓለም ነገሮች የሚያያቸው በሰማያዊ አመለካከት አንፃር ነው - ታዲያ ይህ ምን ያህል ትልቅ ልዩነት ያመጣል!
በኢኳዶር ኡካስ ውስጥ አምስት ሚሲዮናዊያን በተገደሉበት ጊዜ አሳዛኝ የሆነው አሟሟታቸውን አንዳንድ ጋዜጦችና መጽሔቶች ታላቅ የሕይወት ጥፋት በማለት ገልጸውታል። በዚያን ጊዜ ለጓደኞቻቸውና ለወዳጆቻቸው ታላቅ ሀዘንና ቁጭት ቢያደርስባቸውም የኋላ ኋላ ግን ሞታቸው ለእነርሱም ሆነ ለዓለም «ጥፋት» እንዳልሆነ ተረጋገጠ። ጅም እልይት የተባለው ሰባኪ፥ «ሰው መያዝ የማይችለውን በመስጠት፥ ማጣት የማይችለውን ካገኘ ሞኝ አያሰኘውም» ሲል የተናገረው በእውነትም ትክክለኛ ነበር።
«ምድራዊ ነገርን» ፍለጋ መሮጥ የሰዎችን ደስታ ይሰርቃል፥ እና ይህ ደግሞ ክርስቲያኖችንም ይጨምራል። እኛ አንድን ነገር ለመያዝ እንፈልጋለን፥ በኋላ ግን እርሱ እኛን ተቆጣጥሮን እናገኘዋለን። ለዕድልና ለደስታ ብቸኛው መንገድ መንፈሳዊ ልብ መኖርና ነገሮችን ከእግዚአብሔር ወገን ሆኖ ማየት ነው። እንደ ጳውሎስ፥ ለነገሮች ትክክለኛ ሚዛን ያለን ሰዎች (3፡1-11)፥ ትክክለኛ ወኔ ያለን ሯጮች (3፡12-16) ወገናዊነት የማያጠቃን ትክክለኛ ራእይ ያለን ተቆርቋሪዎች (3፡17-21) መሆን አለብን። «እቆጥራለሁ ... እፈጥናለሁ ... እመለከታለሁ» የሚሉት ግሦች መንፈሳዊ ልብ (አስተሳሰብ) ያለውን ሰው ይገልጻሉ።
ይቀጥላል...
ምንጭ፦ ዋረን ደብልዩ ዌርዝ ቢ፤ ደስተኛ ሁን፤ የፊልጵስዩስ መልእክት ፤ ገጽ 8

❤9
Audio
🥰1
. ──•◈•─────•◈•─
የዕለቱ ጥቅስ
──•◈•─────•◈•─
“ሐሰትን ይናገር ዘንድ እግዚአብሔር ሰው አይደለም፥ ይጸጸትም ዘንድ የሰው ልጅ አይደለም። እርሱ ያለውን አያደርገውምን? የተናገረውንስ አይፈጽመውምን?”
ዘኍልቁ 23፥19

❤7🔥3👎1
ቅዱሳት መጻሕፍት
የቀጠለ... አራቱ ደስታችንን ሊጠብቁ የሚችሉ አመለካከቶች 3. መንፈሳዊ አሳብ - ፊልጵስዩስ 3 በዚህ ምዕራፍ ውስጥ ጳውሎስ ወደ አሥራ አንድ ጊዜ ያህል «ነገር» የሚለውን ቃል ሲጠቀም ታገኛላችሁ። የአብዛኛዎቹ ሰዎች «አሳባቸው ምድራዊ» (3፡19) ለሆኑ ነገሮች ሲሆን፥ መንፈሳዊ ልብ ያላቸው ክርስቲያኖች ግን የሚጨነቁት ስለ ሰማያዊ ነገሮች መሆኑን ያሳየናል። «እኛ አገራችን በሰማይ ነውና፥ ከዚያም…
የቀጠለ...
አራቱ ደስታችንን ሊጠብቁ የሚችሉ አመለካከቶች
4. የተጠበቀ ልብ - ፊልጵስዩስ 4
በእውነቱ ጭንቀት ስለአጋጣሚዎች፥ ስለሰዎች እንዲሁም ስለነገሮች የተሳሳተ አመለካከት (በአእምሮአችን) ሲጸነስ እና ትክክለኛ ያልሆነ ስሜት (በልባችን) ሲሰርፅ የሚፈጠር ነው። ስለዚህ፥ አንድ አሳብ፥ ማለትም በትሕትና ላይ የተመሠረተ አሳብ፥ እና መንፈሳዊ አሳብ ካለን፥ ለጭንቀት ያን ያህል ክብደት ልንሰጠው አይገባም። የሚያስፈልገን ነገር ቢኖር ጭንቀት ወደውስጣችን እንዳይገባ አእምሮአችንንና ልባችንን የሚጠብቅ መከላከያ ማግኘት ነው። ጳውሎስ ስለተጠበቀ አሳብ ሲያስረዳ
«አእምሮን ሁሉ የሚያልፍ የእግዚአብሔር ሰላም ልባችሁንና አሳባችሁን በክርስቶስ ኢየሱስ ይጠብቃል» (4፡7) ብሏል።
ጠበቀ የሚለው ወታደራዊ ቃል ነው፤ ይኸውም «ምሽግን ከአደጋ ለመከላከል ዘብ መቆምን» የሚያመለክት ነው። (እንደምናስታውሰው ጳውሎስ በታሠረበት ጊዜ ከአንድ ወታደር ጋር በሰንሰለት ተቆራኝቶ ነበር)።
ምዕራፍ 4 አማኝ በክርስቶስ ስላለው መንፈሳዊ ሀብቶች የሚያስረዳ ነው፤ እነርሱም የእግዚአብሔር ሰላም (4፡1-9)፥ የእግዚአብሔር ኃይል (4፡10-13)፥ እና የእግዚአብሔር እርዳታ (4፡14-23) ናቸው። እነዚህ ሁሉ ሀብቶች ካሉን ታዲያ ለምን እንጨነቃለን? የሚጠብቀን የእግዚአብሔር ሰላም (4፡7) እንዲሁም የሚመራን የሰላም አምላክ (4፡9) አለን። የእግዚአብሔር ሰላም ወደ እኛ የሚመጣው ትክክለኛ የሆነ ጸሎት ስንለማመድ (4፡6-7)፥ ትክክለኛ የሆነ አስተሳሰብ ስናራምድ (4፡8)፥ እና ትክክለኛ የሆነ ኑሮን ስንኖር (4፡9) ነው። ይህም በጭንቀት ሁሉ ላይ ድል የሚሰጠን የእግዚአብሔር ምሥጢር ነው።
ምንጭ፦ ዋረን ደብልዩ ዌርዝ ቢ፤ ደስተኛ ሁን፤ የፊልጵስዩስ መልእክት ፤ ገጽ 8-9

❤3👏1
The_Expositors_Bible_Commentary_Old_&_New_Testament_12_volumes.pdf
103.5 MB
THE EXPOSITOR'S BIBLE COMMENTARY
with The New International Version of The Holy Bible
General Editor: FRANK E. GAEBELEIN
Associate Editor: J. D. DOUGLAS
Consulting Editors, Old Testament: WALTER C. KAISER, JR. BRUCE K. WALTKE
Consulting Editors, New Testament: JAMES MONTGOMERY BOICE, MERRILL C.TENNEY
Manuscript Editor: GERARD H. TERPSTRA

❤2
. ──•◈•─────•◈•─
የዕለቱ ጥቅስ
──•◈•─────•◈•─
“እንግዲህ ምሕረት ለወደደ ወይም ለሮጠ አይደለም፥ ከሚምር ከእግዚአብሔር ነው እንጂ።”
ሮሜ 9፥16

🥰7❤6
#እራሳችንን_እንመርምር
የዘውትር ውሎአችን እና የቆምንበት ሥፍራ ምን ይመስላል? ቃሉና ድምጹ ያለበት? በማስተዋል የተሞላ ወይስ በእልከኝነት የደደረ? ቃሉን ለመብላት ፍላጎታችን የበረታ ነው ወይስ የእግዚአብሔር ቃል ትኩረት የማንሰጠው ነገር ከሆነ ሰንብቷል?
“በኢየሩሳሌም የሚኖሩ ሰዎችና አለቆቻቸው እርሱንና በየሰንበቱ የሚነበቡትን የነቢያትን ድምፆች ስላላወቁ በፍርዳቸው ፈጽመዋልና፤”
ሐዋርያት 13፥27

👍4❤2
. ──•◈•─────•◈•─
የዕለቱ ጥቅስ
──•◈•─────•◈•─
“ዛሬ ድምፁን ብትሰሙት፥ አባቶቻችሁ እኔን የፈተኑበት የመረመሩበትም አርባ ዓመትም ሥራዬን ያዩበት በምድረ በዳ በፈተና ቀን በማስመረር እንደ ሆነ፥ ልባችሁን እልከኛ አታድርጉ።”
ዕብራውያን 3፥8-9

❤🔥4❤4👍2
ቅዱሳት መጻሕፍት
#እምነት ክፍል-9 እምነት እና ሥራ በመጽሐፍ ቅዱስ መሠረት ሰው የሚድነው ወይም የሚጸድቀው በእምነት እንጂ በሥራ እንዳልሆነ እርግጥ ነው፤ ይህ በእምነት የመጽደቅ ጉዳይም በሰው ዘንድ ሳይሆን በእግዚአብሔር ዘንድ የሚታየው ነው፡፡ በሮሜ 4፥1‐8 የምናገኘው የእግዚአብሔር ቃል ይህን የሚያረጋግጥ ነው፤ በቊ.1 ላይ «በሥጋ አባታችን የሆነ አብርሃም ምን አገኘ እንላለን?…
#እምነት
ክፍል-10
እምነት እና ሥራ
እግዚአብሔር ይህ እምነት እውነተኛ መሆን አለመሆኑን በራሱ አምላካዊ እውቀት ያውቃል፤ ሰው ግን ይህን የሚያውቀው ሥራውን አይቶ ነው፤ እዚህ ላይ የተጠቀሰው «እምነት አለኝ» ባዩ ሰው ደግሞ ሥራ እንደሌለው ታውቋል፤ ስለዚህ በቊ.17 ላይ «ሥራ የሌለው እምነት ቢኖር በራሱ የሞተ ነው» ተብሏል፡፡ በእግዚአብሔር ዘንድ እውነተኛ እንደሆነ የሚታወቅ እምነት ግን ሥራ የሌለው ሊሆን አይችልም፤ በጊዜው ባይገለጥ እንኳ እግዚአብሔር ጽድቅ አድርጎ የቈጠረው እምነት ከሆነ በሥራ መገለጡ አይቀርም፡፡ ያን ጊዜም በሰው ዘንድ ይታያል፤ ስለዚህ በቊ.18 ላይ እንደተጠቀሰው «አንድ ሰው አንተ እምነት አለህ እኔም ሥራ አለኝ እምነትህን ከሥራህ ለይተህ አሳየኝ እኔም እምነቴን በሥራዬ አሳይሃለሁ ይላል» ተብሎ በሁለት ሰዎች መካከል በዚህ ጉዳይ ሊባል የሚችለው ነገር ተነግሮናል፤ እነዚህ ሁለት ሰዎች አንዱ እምነት አለኝ የሚለው ሰው ሲሆን ሌላው ደግሞ ሥራ ያለውና እምነቱን በሥራው ማሳየት የሚችለው ሰው ነው፤ እየተናገረ ያለውም ይህ እምነቱን በሥራው ማሳየት የሚችለው ሰው ነው፡፡ «እምነቴን በሥራዬ አሳይሃለሁ» በሚለው አገላለጽም ሥራ እውነተኛ እምነት በሰው ዘንድ ወይም ፊት የሚገለጥበት ማሳያ መሆኑን እንረዳለን፤ ይህ እምነቱን በሥራው ማሳየት የሚችለው ሰው ሥራ የሌለው እምነት ያለውን ሰው እንዲህ እያለ ይወቅሰዋል፤
«እግዚአብሔር አንድ እንደሆነ አንተ ታምናለህ መልካም ታደርጋለህ፤ አጋንንት ደግሞ ያምናሉ ይንቀጠቀጡማል፡፡» ይለዋል (ቊ.19)፡፡ በዚህ ቃል ውስጥ ሥራ የሌለው እምነት ያለው ሰው እምነቱ የተነጻጸረው ከአጋንንት እምነት ጋር መሆኑ ሰውየው የዳነ ሰው እንዳልሆነ ያሳያል፤ ምክንያቱም መዳን በእምነት ነው ሲባል በእውነተኛ እምነት እንጂ እንደ አጋንንት እምነት ባለ በዚህ ዓይነት እምነት አይደለም፡፡ በሌላ አገላለጽ "የአጋንንት እምነት" የሚባል አይነት እምነት አለ ማለት ነው። እግዚአብሔር ከዚህ አይነቱ እምነት ይጠብቀን!
በመቀጠልም ለዚህ አፋዊ እምነት ላለው ሰው የአብርሃም እምነትና ሥራ በማስረጃነት ቀርቦለታል፤ «አንተ ከንቱ ሰው እምነት ከሥራ ተለይቶ የሞተ መሆኑን ልታውቅ ትወዳለህን? አባታችን አብርሃም ልጁን ይስሐቅን በመሠዊያው ባቀረበ ጊዜ በሥራ የጸደቀ አልነበረምን? እምነት ከሥራው ጋር አብሮ ያደርግ እንደነበረ በሥራም እምነት እንደተፈጸመ ትመለከታለህን? መጽሐፍም አብርሃም እግዚአብሔርን አመነ ጽድቅም ሆኖ ተቈጠረለት ያለው ተፈጸመ፤ የእግዚአብሔርም ወዳጅ ተባለ፡፡» ይላል (ቊ.20‐23)፡፡ በዚህ ክፍል አብርሃም ልጁን በመሠዊያው ላይ ማቅረቡ የአብርሃም ሥራ ሆኖ ቀርቧል፤ በዚህም ሥራ የአብርሃም እምነት እንደተፈጸመ ወይም ፍጹም እንደተደረገ(ቊ.22 አ.መ.ት.) ተገልጧል፤ ከዘፍ.15፡4‐6 እንደምንረዳው ደግሞ «አብርሃም በእግዚአብሔር አመነ ጽድቅም ሆኖ ተቈጠረለት» የተባለው እግዚአብሔር ለአብርሃም ከጉልበቱ የሚወጣው እንደሚወርሰው በተናገረውና የሰማይ ከዋክብትን አሳይቶ «ዘርህም እንደዚሁ ይሆናል» ባለው ጊዜ ነው፡፡ ከዚህ በኋላ ይስሐቅን በመሠዊያ ላይ እስከሚያቀርብበት ጊዜ ድረስ ብዙ ዓመታት ተቈጥረዋል፤ በ86 ዓመቱ እስማኤልን ወልዷል(ዘፍ.16፡16)፤ ከ13 ዓመታት በኋላ በ99 ዓመቱ ራሱ አብርሃምና ልጁ እስማኤልም ተገርዘዋል(ዘፍ 17፡24‐25)፤ በ100 ዓመቱ ይስሐቅን ወልዷል(ዘፍ.21፡5)፤ ከዚያም በፍልስጥኤም ምድር ብዙ ቀን እንግዳ ሆኖ ተቀምጧል(ዘፍ.21፡34)፤ እንግዲህ ልጁ ይስሐቅን በመሠዊያ ላይ ያቀረበው ከዚህ ሁሉ በኋላ ይስሐቅ ካደገ በኋላ እንደሆነ እንረዳለን፤ በዚህ ጊዜ አብርሃም በሥራም እንደጸደቀ ተነግሮናል፤ አብርሃም በእግዚአብሔር ዘንድ የጸደቀው ግን «ከጉልበትህ የሚወጣው ይወርስሃል፣ ዘርህ እንደዚሁ ይሆናል» የሚለው የተስፋ ቃል በተሰጠው ጊዜ ማለትም ይስሐቅ ገና ባልነበረበት ጊዜ ነው(ሮሜ 4፥18)፡፡ ያን ጊዜ በእግዚአብሔር ስላመነ ጽድቅ ሆኖ ተቈጠረለት፡፡ ከብዙ ዓመታት በኋላ ደግሞ ልጁን ይስሐቅን በመሠዊያው ባቀረበ ጊዜ በሥራም ጸደቀ፤ ይህም ማለት በሰው ዘንድ ታየ ተረጋገጠ ማለት ነው፡፡ እግዚአብሔር ግን ለአብርሃም ጽድቅን ለመቊጠር ልጁ ይስሐቅን በመሠዊያ ላይ እስኪያቀርብ ድረስ መጠበቅ አላስፈለገውም፤ አብርሃም ባመነ ጊዜ እምነቱን ጽድቅ አድርጎ ቈጥሮለታል፡፡
ይቀጥላል...
ምንጭ፦ 1bible.page

❤6👍2
መልእክተ ይሁዳ.pdf
985 KB
👍3❤1
. ──•◈•─────•◈•─
የዕለቱ ጥቅስ
──•◈•─────•◈•─
“በጠበበው በር ለመግባት ተጋደሉ፤ እላችኋለሁና፥ ብዙዎች ሊገቡ ይፈልጋሉ አይችሉምም።”
ሉቃስ 13፥24
ወደ ቻናሉ ለመ🀄️ላ🀄️ል፦ @Holy_scriptures
የዕለቱ ጥቅስ
──•◈•─────•◈•─
“በጠበበው በር ለመግባት ተጋደሉ፤ እላችኋለሁና፥ ብዙዎች ሊገቡ ይፈልጋሉ አይችሉምም።”
ሉቃስ 13፥24
ወደ ቻናሉ ለመ🀄️ላ🀄️ል፦ @Holy_scriptures
❤8🥰1
ትንቢተ_ዳንኤል_የጥናት_መምሪያና_ማብራሪያ.pdf
8 MB
👉ርዕስ፦ ትንቢተ ዳንኤል የጥናት መምሪያና ማብራሪያ፣
በትምህርተ መለኮት ማስፋፊያ (ት.መ.ማ) መልክ የተዘጋጀ
✍ጸሐፊ፦ ቲም ፌሎስ
🖨አሳታሚ፦ ኤስ.አይ.ኤም
ወደ ቻናሉ ለመ🀄️ላ🀄️ል፦ @Holy_scriptures
በትምህርተ መለኮት ማስፋፊያ (ት.መ.ማ) መልክ የተዘጋጀ
✍ጸሐፊ፦ ቲም ፌሎስ
🖨አሳታሚ፦ ኤስ.አይ.ኤም
ወደ ቻናሉ ለመ🀄️ላ🀄️ል፦ @Holy_scriptures
❤14