. ──•◈•─────•◈•─
የዕለቱ ጥቅስ
──•◈•─────•◈•─
“ስለዚህም በሙሴ ሕግ መጽሐፍ የተጻፈውን ሁሉ ለመጠበቅና ለማድረግ በጣም በርቱ፥ ከእርሱም ወደ ቀኝም ወደ ግራም ፈቀቅ አትበሉ።”
ኢያሱ 23፥6
ወደ ቻናሉ ለመ🀄️ላ🀄️ል፦ @Holy_scriptures

🙏5❤2👏1
አራቱ ደስታችንን ሊጠብቁ የሚችሉ አመለካከቶች
1. አንድ አሳብ - ፊልጵስዩስ 1
«ሁለት አሳብ ላለው በመንገዱ ሁሉ ለሚወላውል ... አንዳች እንዲያገኝ አይምሰለው» (ያዕ. 1፡8)። ወይንም በጥንት ላቲን ቋንቋ፥ «የመርከቡ ነጂ የሚያርፍበትን ወደብ ካላወቀ የትኛውም ነፋስ አይረዳውም» የሚል ምሳሌ አለ። ለብዙ ክርስቲያኖች በሁኔታዎች አለመሳካት የብስጭት ምክንያት የሚሆነው በ«አንድ አሳብ» ስለማይረጉ ነው። ጳውሎስ ለክርስቶስ፥ በአንድ ልብ የመሰጠትን አመለካከት ሲገልጽ፤ «ለእኔ ሕይወት ክርስቶስ ሞትም ጥቅም ነውና» (1፡21) ብሏል።
በምዕራፍ አንድ ጳውሎስ የገጠሙትን አስቸጋሪ ሁኔታዎች በታማኝነት እንደተጋፈጠ አስረድቷል። ግን የገጠሙት ሁኔታዎች ያለውን ደስታ ሊያሳጡት አልቻሉም። ምክንያቱም እርሱ የሚኖረው በሁኔታዎች ውጤት ለመደሰት ሳይሆን ኢየሱስ ክርስቶስን ለማገልገል በመሆኑ ነው። እርሱ ዓላማ ያለው ሰው ነው። «አንድ ነገር አደርጋለሁ» (3፡13)። የሚገጥሙትን ነገሮች ሁሉ ከክርስቶስ ጋር በማያያዝ እንጂ ነገሮችን ብቻቸውን አይመለከትም። ጳውሎስ የሮም እስረኛ አይደለም፥ ነገር ግን እራሱም «የክርስቶስ እስረኛ የሆንሁ» (ኤፌ. 3፡1) በማለት ገልጾታል። እስራቱንም «እስራቴ ለክርስቶስ» (ፊልጵ. 1፡13) ነው ይላል። የተራ ሰው ክስ አልተጋፈጠም፤ እርሱ ግን «ወንጌልን መመከቻ ለማድረግ እንደተሾምሁ» (1፡17) አውቃለሁ ይላል። በችግሮቹ ውስጥ ሆኖ ክርስቶስን አያይም፤ ነገር ግን በክርስቶስ ውስጥ ሆኖ ችግሮቹን ይመለከታል። ይህ ደግሞ ሁሉን ለውጧል።
ክርስቲያን በአንድ አሳብ ሲሆን፥ ስለወንጌል አንድነት (1፥1 - 11) ፣ ስለ ወንጌል መስፋፋት (1፡12-26)፥ እና ስለ ወንጌል እምነት (1፡27-30) ያስባል፤ ጳውሎስ በአስቸጋሪ ሁኔታዎች ውስጥ ሁሉ ሆኖ ይደሰታል። ችግሩ ከሌሎች ክርስቲያኖች ጋር ያለውን ኅብረት ለማጠናከር ረድቶታል፥ ሌሎችንም ደግሞ ወደ ክርስቶስ ለማምጣት ዕድል አግኝቷል፥ እንዲሁም ስለወንጌል በሮማ ፍርድ ቤት ፊት ቆሞ ማስረዳት ችሏል። አንድ ልብ ካላችሁ የሚገጥሟችሁ ችግሮች ሁሉ በማብቂያው መልካም ውጤት ያስገኙላችኋል እንጂ ለጥፋት አይዳርጓችሁም።
ይቀጥላል...
ምንጭ፦ ዋረን ደብልዩ ዌርዝ ቢ፤ ደስተኛ ሁን፤ የፊልጵስዩስ መልእክት ፤ ገጽ 6-7

❤11🥰1👏1
በአዲስ ኪዳን ከሚገኙ ቅዱሳት መጻሕፍት ውስጥ የትኛው መጽሐፍ ስለጌታችን ዳግመኛ መምጣት እና ሙታን ትንሣኤ በስፋት ያትታል?
Anonymous Quiz
8%
ሀ. 2ኛ ጢሞቴዎስ
59%
ለ. 1ኛ ተሰሎንቄ
27%
ሐ. 2ኛ ቆሮንቶስ
6%
መ. ይሁዳ
❤11
. ──•◈•─────•◈•─
የዕለቱ ጥቅስ
──•◈•─────•◈•─
“እግዚአብሔርም፦ ሰላም ለአንተ ይሁን አትፍራ አትሞትም አለው።”
መሳፍንት 6፥23
ወደ ቻናሉ ለመ🀄️ላ🀄️ል፦ @Holy_scriptures
የዕለቱ ጥቅስ
──•◈•─────•◈•─
“እግዚአብሔርም፦ ሰላም ለአንተ ይሁን አትፍራ አትሞትም አለው።”
መሳፍንት 6፥23
ወደ ቻናሉ ለመ🀄️ላ🀄️ል፦ @Holy_scriptures
❤12
ቅዱሳት መጻሕፍት
አራቱ ደስታችንን ሊጠብቁ የሚችሉ አመለካከቶች 1. አንድ አሳብ - ፊልጵስዩስ 1 «ሁለት አሳብ ላለው በመንገዱ ሁሉ ለሚወላውል ... አንዳች እንዲያገኝ አይምሰለው» (ያዕ. 1፡8)። ወይንም በጥንት ላቲን ቋንቋ፥ «የመርከቡ ነጂ የሚያርፍበትን ወደብ ካላወቀ የትኛውም ነፋስ አይረዳውም» የሚል ምሳሌ አለ። ለብዙ ክርስቲያኖች በሁኔታዎች አለመሳካት የብስጭት ምክንያት የሚሆነው በ«አንድ አሳብ» ስለማይረጉ…
የቀጠለ...
አራቱ ደስታችንን ሊጠብቁ የሚችሉ አመለካከቶች
2. የሚገዛ አሳብ - ፊልጵስዩስ 2
ይህ ምዕራፍ የሚያተኩረው በሰዎች ላይ ነው፥ መሪ ጥቅሱም «ለወገኔ ይጠቅማል በማለት ወይም በከንቱ ውዳሴ ምክንያት አንድ እንኳ አታድርጉ፥ ነገር ግን እያንዳንዱ ባልንጀራው ከራሱ ይልቅ እንዲሻል በትሕትና ይቁጠር» (2፡3)። በምዕራፍ 1 ላይ ጳውሎስ ክርስቶስን የመጀመሪያው መሻቱ ሲያደርግ፥ በዚህ ምዕራፍ፥ ደግሞ ሌሎችን በሁለተኛ ደረጃ አስቀምጧቸዋል። ይህም የሚያሳየን ራሱን መጨረሻ ማድረጉ ነው! ብዙ ጊዜ በሰዎች ላይ የምንቆጣበት ምክንያት በእኛ አሳብ ስለማይመሩልን ነው። በሕይወት በምንጓዝበት ወቅት እራሳችንን መጀመሪያ ካደረግን፥ እንዲሁም ሌሎችም ራሳቸውን መጀመሪያ ካደረጉ፥ ያንጊዜ በብዙ ነጥቦች ላይ ኃይለኛ ግጭት ይፈጠራል።
አንዲት እናት እና ወንድ ልጇ ወደ ሐኪም ቢሮ ለመሄድ ወደ አሳንሰሩ (ሊፍት) ውስጥ ገቡ። ከሁለተኛው ፎቅ ላይ እንደደረሱም ሌሎች ሰዎች ተጨመሩ። ከእነርሱም መሀል አንዲት ወፍራም ሴት ነበረች። አሳንሰሩም ወደ ላይ መውጣቱን እንደቀጠለ ጸጥታው በወፍራሟ ሴት ጩኸት ደፈረሰ። ወደ ልጁም እናት ዘወር ብላ «ልጅሽ ነከሰኝ እኮ!» አለቻት።
እናትየው በጣም ተሳቀቀች፥ ልጁ ግን ማብራሪያ ነበረው «ፊቴን በቂጧ ስላጣበቀችኝ ነው የነከስኳት» ብሎ አስረዳት።
በአሳንሰሩ ውስጥ የተከሰተው ድርጊት በዓለም ዙሪያ ሁሉ ሲፈፀም የምንመለከተው ነው። ሕዝብ ከሕዝብ፥ መንግሥታት ከመንግሥታት ይነካከሳሉ፥ ምክንያቱም ተፋፍገው ስለሚኖሩ ነው።
ነገር ግን የሚገዛ ትሑት ልብ ያለው ክርስቲያን ሌሎችን ያገለግላል እንጂ ሌላ ሰው እርሱን መጥቶ እንዲያገለግለው አይጠብቅም። ከራሱ ፍላጎትና እቅድ ይልቅ ለሌሎች ምኞት መሟላት ቅድሚያ ይሰጣል። በምዕራፍ 2 ውስጥ በትሑት ልቦናቸው ምሳሌ ሊሆኑን የሚችሉ 4 አስገራሚ ሰዎች እናገኛለን። እነርሱም ኢየሱስ ክርስቶስ (2፡1-11)፥ ጳውሎስ (2፡12-18)፥ ጢሞቴዎስ (2፡19-24) እና አፍሮዲጡን (2፡25-30) ናቸው። እነዚህ ምሳሌዎች «ራሱን ከፍ የሚያደርግ ሁሉ ይዋረዳልና፤ ራሱንም የሚያዋርድ ከፍ ይላል» (ሉቃ. 14፡11) የሚለውን መርሆ ያረጋግጡልናል።
ይቀጥላል...
ምንጭ፦ ዋረን ደብልዩ ዌርዝ ቢ፤ ደስተኛ ሁን፤ የፊልጵስዩስ መልእክት ፤ ገጽ 7-8

❤8
. ──•◈•─────•◈•─
የዕለቱ ጥቅስ
──•◈•─────•◈•─
“ሀብትህን ሰባት ቦታ፣ እንዲያውም ስምንት ቦታ ከፍለህ አስቀምጥ፤ በምድሪቱ ላይ የሚመጣውን ጥፋት አታውቅምና።”
መክብብ 11፥2 (አዲሱ መ.ት)

❤8🔥2🤝1
ቅዱሳት መጻሕፍት
የቀጠለ... አራቱ ደስታችንን ሊጠብቁ የሚችሉ አመለካከቶች 2. የሚገዛ አሳብ - ፊልጵስዩስ 2 ይህ ምዕራፍ የሚያተኩረው በሰዎች ላይ ነው፥ መሪ ጥቅሱም «ለወገኔ ይጠቅማል በማለት ወይም በከንቱ ውዳሴ ምክንያት አንድ እንኳ አታድርጉ፥ ነገር ግን እያንዳንዱ ባልንጀራው ከራሱ ይልቅ እንዲሻል በትሕትና ይቁጠር» (2፡3)። በምዕራፍ 1 ላይ ጳውሎስ ክርስቶስን የመጀመሪያው መሻቱ ሲያደርግ፥ በዚህ ምዕራፍ፥…
የቀጠለ...
አራቱ ደስታችንን ሊጠብቁ የሚችሉ አመለካከቶች
3. መንፈሳዊ አሳብ - ፊልጵስዩስ 3
በዚህ ምዕራፍ ውስጥ ጳውሎስ ወደ አሥራ አንድ ጊዜ ያህል «ነገር» የሚለውን ቃል ሲጠቀም ታገኛላችሁ። የአብዛኛዎቹ ሰዎች «አሳባቸው ምድራዊ» (3፡19) ለሆኑ ነገሮች ሲሆን፥ መንፈሳዊ ልብ ያላቸው ክርስቲያኖች ግን የሚጨነቁት ስለ ሰማያዊ ነገሮች መሆኑን ያሳየናል። «እኛ አገራችን በሰማይ ነውና፥ ከዚያም ደግሞ የሚመጣ መድኃኒት እርሱም ጌታን ኢየሱስ ክርስቶስን እንጠባበቃለን» (3፡20)። መንፈሳዊ ልብ ያለው ሰው የዚህን ዓለም ነገሮች የሚያያቸው በሰማያዊ አመለካከት አንፃር ነው - ታዲያ ይህ ምን ያህል ትልቅ ልዩነት ያመጣል!
በኢኳዶር ኡካስ ውስጥ አምስት ሚሲዮናዊያን በተገደሉበት ጊዜ አሳዛኝ የሆነው አሟሟታቸውን አንዳንድ ጋዜጦችና መጽሔቶች ታላቅ የሕይወት ጥፋት በማለት ገልጸውታል። በዚያን ጊዜ ለጓደኞቻቸውና ለወዳጆቻቸው ታላቅ ሀዘንና ቁጭት ቢያደርስባቸውም የኋላ ኋላ ግን ሞታቸው ለእነርሱም ሆነ ለዓለም «ጥፋት» እንዳልሆነ ተረጋገጠ። ጅም እልይት የተባለው ሰባኪ፥ «ሰው መያዝ የማይችለውን በመስጠት፥ ማጣት የማይችለውን ካገኘ ሞኝ አያሰኘውም» ሲል የተናገረው በእውነትም ትክክለኛ ነበር።
«ምድራዊ ነገርን» ፍለጋ መሮጥ የሰዎችን ደስታ ይሰርቃል፥ እና ይህ ደግሞ ክርስቲያኖችንም ይጨምራል። እኛ አንድን ነገር ለመያዝ እንፈልጋለን፥ በኋላ ግን እርሱ እኛን ተቆጣጥሮን እናገኘዋለን። ለዕድልና ለደስታ ብቸኛው መንገድ መንፈሳዊ ልብ መኖርና ነገሮችን ከእግዚአብሔር ወገን ሆኖ ማየት ነው። እንደ ጳውሎስ፥ ለነገሮች ትክክለኛ ሚዛን ያለን ሰዎች (3፡1-11)፥ ትክክለኛ ወኔ ያለን ሯጮች (3፡12-16) ወገናዊነት የማያጠቃን ትክክለኛ ራእይ ያለን ተቆርቋሪዎች (3፡17-21) መሆን አለብን። «እቆጥራለሁ ... እፈጥናለሁ ... እመለከታለሁ» የሚሉት ግሦች መንፈሳዊ ልብ (አስተሳሰብ) ያለውን ሰው ይገልጻሉ።
ይቀጥላል...
ምንጭ፦ ዋረን ደብልዩ ዌርዝ ቢ፤ ደስተኛ ሁን፤ የፊልጵስዩስ መልእክት ፤ ገጽ 8

❤9
Audio
🥰1
. ──•◈•─────•◈•─
የዕለቱ ጥቅስ
──•◈•─────•◈•─
“ሐሰትን ይናገር ዘንድ እግዚአብሔር ሰው አይደለም፥ ይጸጸትም ዘንድ የሰው ልጅ አይደለም። እርሱ ያለውን አያደርገውምን? የተናገረውንስ አይፈጽመውምን?”
ዘኍልቁ 23፥19

❤7🔥3👎1
ቅዱሳት መጻሕፍት
የቀጠለ... አራቱ ደስታችንን ሊጠብቁ የሚችሉ አመለካከቶች 3. መንፈሳዊ አሳብ - ፊልጵስዩስ 3 በዚህ ምዕራፍ ውስጥ ጳውሎስ ወደ አሥራ አንድ ጊዜ ያህል «ነገር» የሚለውን ቃል ሲጠቀም ታገኛላችሁ። የአብዛኛዎቹ ሰዎች «አሳባቸው ምድራዊ» (3፡19) ለሆኑ ነገሮች ሲሆን፥ መንፈሳዊ ልብ ያላቸው ክርስቲያኖች ግን የሚጨነቁት ስለ ሰማያዊ ነገሮች መሆኑን ያሳየናል። «እኛ አገራችን በሰማይ ነውና፥ ከዚያም…
የቀጠለ...
አራቱ ደስታችንን ሊጠብቁ የሚችሉ አመለካከቶች
4. የተጠበቀ ልብ - ፊልጵስዩስ 4
በእውነቱ ጭንቀት ስለአጋጣሚዎች፥ ስለሰዎች እንዲሁም ስለነገሮች የተሳሳተ አመለካከት (በአእምሮአችን) ሲጸነስ እና ትክክለኛ ያልሆነ ስሜት (በልባችን) ሲሰርፅ የሚፈጠር ነው። ስለዚህ፥ አንድ አሳብ፥ ማለትም በትሕትና ላይ የተመሠረተ አሳብ፥ እና መንፈሳዊ አሳብ ካለን፥ ለጭንቀት ያን ያህል ክብደት ልንሰጠው አይገባም። የሚያስፈልገን ነገር ቢኖር ጭንቀት ወደውስጣችን እንዳይገባ አእምሮአችንንና ልባችንን የሚጠብቅ መከላከያ ማግኘት ነው። ጳውሎስ ስለተጠበቀ አሳብ ሲያስረዳ
«አእምሮን ሁሉ የሚያልፍ የእግዚአብሔር ሰላም ልባችሁንና አሳባችሁን በክርስቶስ ኢየሱስ ይጠብቃል» (4፡7) ብሏል።
ጠበቀ የሚለው ወታደራዊ ቃል ነው፤ ይኸውም «ምሽግን ከአደጋ ለመከላከል ዘብ መቆምን» የሚያመለክት ነው። (እንደምናስታውሰው ጳውሎስ በታሠረበት ጊዜ ከአንድ ወታደር ጋር በሰንሰለት ተቆራኝቶ ነበር)።
ምዕራፍ 4 አማኝ በክርስቶስ ስላለው መንፈሳዊ ሀብቶች የሚያስረዳ ነው፤ እነርሱም የእግዚአብሔር ሰላም (4፡1-9)፥ የእግዚአብሔር ኃይል (4፡10-13)፥ እና የእግዚአብሔር እርዳታ (4፡14-23) ናቸው። እነዚህ ሁሉ ሀብቶች ካሉን ታዲያ ለምን እንጨነቃለን? የሚጠብቀን የእግዚአብሔር ሰላም (4፡7) እንዲሁም የሚመራን የሰላም አምላክ (4፡9) አለን። የእግዚአብሔር ሰላም ወደ እኛ የሚመጣው ትክክለኛ የሆነ ጸሎት ስንለማመድ (4፡6-7)፥ ትክክለኛ የሆነ አስተሳሰብ ስናራምድ (4፡8)፥ እና ትክክለኛ የሆነ ኑሮን ስንኖር (4፡9) ነው። ይህም በጭንቀት ሁሉ ላይ ድል የሚሰጠን የእግዚአብሔር ምሥጢር ነው።
ምንጭ፦ ዋረን ደብልዩ ዌርዝ ቢ፤ ደስተኛ ሁን፤ የፊልጵስዩስ መልእክት ፤ ገጽ 8-9

❤3👏1
The_Expositors_Bible_Commentary_Old_&_New_Testament_12_volumes.pdf
103.5 MB
THE EXPOSITOR'S BIBLE COMMENTARY
with The New International Version of The Holy Bible
General Editor: FRANK E. GAEBELEIN
Associate Editor: J. D. DOUGLAS
Consulting Editors, Old Testament: WALTER C. KAISER, JR. BRUCE K. WALTKE
Consulting Editors, New Testament: JAMES MONTGOMERY BOICE, MERRILL C.TENNEY
Manuscript Editor: GERARD H. TERPSTRA

❤2
. ──•◈•─────•◈•─
የዕለቱ ጥቅስ
──•◈•─────•◈•─
“እንግዲህ ምሕረት ለወደደ ወይም ለሮጠ አይደለም፥ ከሚምር ከእግዚአብሔር ነው እንጂ።”
ሮሜ 9፥16

🥰7❤6
#እራሳችንን_እንመርምር
የዘውትር ውሎአችን እና የቆምንበት ሥፍራ ምን ይመስላል? ቃሉና ድምጹ ያለበት? በማስተዋል የተሞላ ወይስ በእልከኝነት የደደረ? ቃሉን ለመብላት ፍላጎታችን የበረታ ነው ወይስ የእግዚአብሔር ቃል ትኩረት የማንሰጠው ነገር ከሆነ ሰንብቷል?
“በኢየሩሳሌም የሚኖሩ ሰዎችና አለቆቻቸው እርሱንና በየሰንበቱ የሚነበቡትን የነቢያትን ድምፆች ስላላወቁ በፍርዳቸው ፈጽመዋልና፤”
ሐዋርያት 13፥27

👍4❤2
. ──•◈•─────•◈•─
የዕለቱ ጥቅስ
──•◈•─────•◈•─
“ዛሬ ድምፁን ብትሰሙት፥ አባቶቻችሁ እኔን የፈተኑበት የመረመሩበትም አርባ ዓመትም ሥራዬን ያዩበት በምድረ በዳ በፈተና ቀን በማስመረር እንደ ሆነ፥ ልባችሁን እልከኛ አታድርጉ።”
ዕብራውያን 3፥8-9

❤🔥4❤4👍2