ለጌታ-የተገዛህ ሁን.pdf
9.5 MB
👉ርዕስ፦ ለጌታ-የተገዛህ ሁን
የማቴዎስ ወንጌል
የክብር ንጉሥን በማወቅና በማገልገል ሐሤት አድርግ
✍️ጸሐፊ፦ ዋረን ደብልዩ ዌርዝቢ
🗣ትርጉም፦ ግርማዊ
✏️እርማት፦ ዐብይ ደምሴ እና ኃይሌ ጀናይ
ወደ ቻናሉ ለመ🀄️ላ🀄️ል፦ @Holy_scriptures
የማቴዎስ ወንጌል
የክብር ንጉሥን በማወቅና በማገልገል ሐሤት አድርግ
✍️ጸሐፊ፦ ዋረን ደብልዩ ዌርዝቢ
🗣ትርጉም፦ ግርማዊ
✏️እርማት፦ ዐብይ ደምሴ እና ኃይሌ ጀናይ
ወደ ቻናሉ ለመ🀄️ላ🀄️ል፦ @Holy_scriptures
❤8🥰3
#እራሳችንን_እንመርምር
በየትኛውም በሕይወት መስክ፣ ምንም ይሁን የትም የምንሰራው እንዴት ነው? በቸልተኝነት? በዋዛ ፈዛዛ? በሙሉ ልብ?
“ለሰው ሳይሆን ለጌታ እንደምታደርጉ፥ የምታደርጉትን ሁሉ በትጋት አድርጉት፥”
ቆላስይስ 3፥23

👍6❤1🤔1
. ──•◈•─────•◈•─
የዕለቱ ጥቅስ
──•◈•─────•◈•─
“ጌታቸው በመጣ ጊዜ ሲተጉ የሚያገኛቸው እነዚያ ባሪያዎች ብፁዓን ናቸው፤ እውነት እላችኋለሁ፥ ታጥቆ በማዕድ ያስቀምጣቸዋል ቀርቦም ያገለግላቸዋል።”
ሉቃስ 12፥37

👍3
ቅዱሳት መጻሕፍት
ክርስቲያናዊ ዓቅብተ እምነት – CHRISTIAN APOLOGETICS ክፍል-2 1.2. የክርስቲያን ዓቅብተ እምነት ታሪክ የክርስቲያን ዓቅብተ እምነት ታሪክ ከመጀመርያው ክፍለ ዘመን የሚጀምር ቢሆንም እንደ አንድ የጥናት ዘርፍ የጎለበተውና ወጥ የሆነ መልክ የያዘው ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ነው፡፡ ክርስቲያናዊው ዓቅብተ እምነት በተለያዩ የዕድገት ደረጃዎች ውስጥ አልፏል፡፡ ክርስትና በተጀመረበት…
ክርስቲያናዊ ዓቅብተ እምነት – CHRISTIAN APOLOGETICS
ክፍል-3
በክርስቲያን ዓቅብተ እምነት ታሪክ ውስጥ የእስክንድሪያ ክርስቲያኖች ያበረከቱት አስተዋጽዖ ከሁሉም የላቀ ነበር፡፡ የእስክንድሪያው ቀለሜንጦስ “ፕሮትሬፕቲከስ” (ልባዊ ምክር) በሚል ርዕስ የጻፈው ዓቃቤ እምነታዊ ጽሑፍ በሁለተኛው ክፍለ ዘመን ከተጻፉ ተመሳሳይ ጽሑፎች ሁሉ የላቀ ነበር፡፡
በሦስተኛው ክፍለ ዘመን ከተነሱት ክርስቲያን አቃቤ እምነታውያን መካከል ኦሪጎን (185-254 ዓ.ም.) ቀዳሚውን ስፍራ ይይዛል፡፡ ሴልሰስ የተባለ ሰው በክርስትና ላይ ላቀረበው ፍልስፍናዊ፣ ግብረ ገባዊና ታሪካዊ ትችት ምላሽ ለመስጠት “ኮንትራ ሴልሰስ” በሚል ርዕስ የጻፈው ረዘም ያለ ጽሑፉ እስከ አሁኑ ዘመን ድረስ ጠቃሚ የመረጃ ምንጭ በመሆን እያገለገለ ይገኛል፡፡ በዚህ ጽሑፉ ኦሪጎን ኢየሱስ ተዓምራቱን በአስማት እንዳላደረገና የአረማውያን የተዓምራት ታሪኮች ከኢየሱስ ታሪኮች እጅግ ያነሰ ተዓማኒነት እንዳላቸው ተሟግቷል፡፡ የኢየሱስን ትንሣኤ ታሪካዊነት “ከቁም ቅዠት” (Hallucination) መላ ምት በመከላከል ረገድም የሚደነቅ የመከላከያ ሐሳብ አቅርቧል፡፡
የሂፖ ሬጊዩስ ሊቀ ጳጳስ የነበረው ቅዱስ አውጉስጢኖስ (354-430 ዓ.ም.) ክርስቲያኖች በንጉሥ ቆስጠንጢኖስ አዋጅ ነጻነትን ከተጎናጸፉ በኋላ ከተነሱት ክርስቲያን ዓቃቤ እምነታውያን መካከል ቀዳሚውን ስፍራ ይይዛል፡፡ ክርስትና ከአረማዊነት የላቀ መሆኑን የሚያሳዩ፣ የስህተት ትምህርቶችን የሚያጋልጡና የክርስትናን አስተምህሮዎች ቀና በሆነ መንገድ የሚያስተምሩ ብዙ ጽሑፎችን የጻፈ ታላቅ ሊቅ ነበር፡፡ የአውጉስጢኖስ ክርስቲያናዊ ፍልስፍና የበለጠ ሰፋ ባለ መልኩ ሰፍሮ የምናገኘው በምዕራቡ ዓለም ውስጥ ከተጻፉ አስር በጣም ጠቃሚ መጻሕፍት መካከል አንዱ ተደርጎ በሚቆጠረው “የእግዚአብሔር ከተማ” በሚል ርዕስ በጻፈው የመጨረሻ መጽሐፉ ውስጥ ነው፡፡ አውጉስጢኖስ ስለ ዓቅብተ እምነት ያስተማረው ትምህርት ከርሱ ዘመን ጀምሮ እስከዚህ ዘመን ድረስ ለብዙ ክርስቲያን ዓቃቤ እምነታውያንና የነገረ መለኮት ምሑራን መነሳት ምክንያት ሆኗል፡፡
ቤተ ክርስቲያን ካፈራቻቸው ታላላቅ ሊቃውንት መካከል የካንቴርበሪ ሊቀ ጳጳስ የነበረው አንሴልም (1033-1109 ዓ.ም.) ይጠቀሳል፡፡ ከርሱ በፊት ያልተነገሩ የራሱ የሆኑ አዳዲስ ሐሳቦችን በማመንጨት የሚታወቅ ሲሆን አውጉስጢኖስ ስለ እምነትና ምክንያት ያስተማራቸውን ነገሮች በማጉላትም ይታወቃል፡፡ ስለ እምነትና ስለ ምክንያት ከተናገራቸው ነገሮች መካከል የሚከተለው ይገኝበታል፦ “ለማመን መረዳት እንዲኖረኝ ጥረት አላደርግም ነገር ግን ለመረዳት እምነት እንዲኖረኝ ጥረት አደርጋለሁ፡፡” አንሴልም ፈላስፎች “Ontological Argument” በማለት ለሚጠሩት የእግዚአብሔርን መኖር ለሚያስረዳ እጅግ ጠቃሚ ሐሳብ መሠረት የጣለ ሰው ነበር፡፡ “ኩር ዴኡስ ሆሞ” (አምላክ ሰው የሆነበት ምክንያት) በሚለው መጽሐፉ ውስጥ የኢየሱስ በሰው ሥጋ መምጣት ለምን እንዳስፈለገ አመክንዮአዊ በሆነ መንገድ በማስረዳት ለክርስቲያን ዓቅብተ እምነት ከፍተኛ አስተዋጽዖ አበርክቷል፡፡
በአስራ ሦስተኛው ክፍለ ዘመን አቬሮስ በተባለ የእስፔን አረብ አማካይነት የአርስጣጣሊስ (አርስቶትል) ፍልስፍና በመላው አውሮፓ በሚገኙ ዩኒቨርሲቲዎች ውስጥ ከመሰራጨቱ የተነሳ ክርስቲያናዊው ንፅረተ ዓለም ከፍተኛ ቀውስ ገጥሞት ነበር፡፡ ሊቃውንት ያለ ምንም ምርመራ የአርስጣጣሊስን አስተሳሰብ የተቀበሉ ሲሆኑ የቤተ ክርስቲያን መሪዎችም ያለ ምንም ምርመራ ከአርስጣጣሊስ ፍልስፍና ጋር የተያያዙትን ነገሮች ሁሉ ይቃወሙ ነበር፡፡ ታላቁ አልበርት የተባለ ክርስቲያን ሊቅ ለአቬሮስ ምላሽ የሚሆን ጽሑፍ የጻፈ ቢሆንም ነገር ግን ለዚህ ተግዳሮት ምላሽን በመስጠት የክርስቲያናዊውን ፍልስፍናና ዓቅብተ እምነት አቅጣጫ ማስለወጥ የቻለው የአልበርት ደቀ መዝሙር የነበረው ቶማስ አኳይነስ (1225-1274) ነበር፡፡ ለአቬሮስ ምላሽ ሊሆን የሚችል ጽሑፍ የአርስጣጣሊስን ቋንቋ በመጠቀም ከመጻፉ ሌላ ለክርስቲያን ተማሪዎች ሊሆን የሚችል የሥነ መለኮት መጽሐፍም አበርክቷል፡፡ አኳይነስ በቤተ ክርስቲያን ታሪክ ከተነሱ ታላላቅ ፈላስፎች መካከል አንዱ ነበር፡፡
ይቀጥላል...
ምንጭ:- ewnetlehulu.org

❤9
. ──•◈•─────•◈•─
የዕለቱ ጥቅስ
──•◈•─────•◈•─
“እግዚአብሔር ስለ ጽድቁ ሕጉን ታላቅ ያደርግና ያከብር ዘንድ ወደደ።”
ኢሳይያስ 42፥21

❤8
የገላጭ ስብከት አዘገጃጀት.pdf
7.6 MB
👉ርዕስ፦ የገላጭ ስብከት አዘገጃጀት
✍️ጸሐፊ፦ ዶክተር ራሜሽ ሪቻርድ
🗣ተርጓሚ፦ ገበየሁ አየለ
✏️ኤዲተርና ልዩ ረዳት፦ ስምዖን ሙላቱ
ወደ ቻናሉ ለመ🀄️ላ🀄️ል፦ @Holy_scriptures
✍️ጸሐፊ፦ ዶክተር ራሜሽ ሪቻርድ
🗣ተርጓሚ፦ ገበየሁ አየለ
✏️ኤዲተርና ልዩ ረዳት፦ ስምዖን ሙላቱ
ወደ ቻናሉ ለመ🀄️ላ🀄️ል፦ @Holy_scriptures
👍8❤3🔥1
. ──•◈•─────•◈•─
የዕለቱ ጥቅስ
──•◈•─────•◈•─
“ስለዚህም በሙሴ ሕግ መጽሐፍ የተጻፈውን ሁሉ ለመጠበቅና ለማድረግ በጣም በርቱ፥ ከእርሱም ወደ ቀኝም ወደ ግራም ፈቀቅ አትበሉ።”
ኢያሱ 23፥6

🙏5❤2👏1
አራቱ ደስታችንን ሊጠብቁ የሚችሉ አመለካከቶች
1. አንድ አሳብ - ፊልጵስዩስ 1
«ሁለት አሳብ ላለው በመንገዱ ሁሉ ለሚወላውል ... አንዳች እንዲያገኝ አይምሰለው» (ያዕ. 1፡8)። ወይንም በጥንት ላቲን ቋንቋ፥ «የመርከቡ ነጂ የሚያርፍበትን ወደብ ካላወቀ የትኛውም ነፋስ አይረዳውም» የሚል ምሳሌ አለ። ለብዙ ክርስቲያኖች በሁኔታዎች አለመሳካት የብስጭት ምክንያት የሚሆነው በ«አንድ አሳብ» ስለማይረጉ ነው። ጳውሎስ ለክርስቶስ፥ በአንድ ልብ የመሰጠትን አመለካከት ሲገልጽ፤ «ለእኔ ሕይወት ክርስቶስ ሞትም ጥቅም ነውና» (1፡21) ብሏል።
በምዕራፍ አንድ ጳውሎስ የገጠሙትን አስቸጋሪ ሁኔታዎች በታማኝነት እንደተጋፈጠ አስረድቷል። ግን የገጠሙት ሁኔታዎች ያለውን ደስታ ሊያሳጡት አልቻሉም። ምክንያቱም እርሱ የሚኖረው በሁኔታዎች ውጤት ለመደሰት ሳይሆን ኢየሱስ ክርስቶስን ለማገልገል በመሆኑ ነው። እርሱ ዓላማ ያለው ሰው ነው። «አንድ ነገር አደርጋለሁ» (3፡13)። የሚገጥሙትን ነገሮች ሁሉ ከክርስቶስ ጋር በማያያዝ እንጂ ነገሮችን ብቻቸውን አይመለከትም። ጳውሎስ የሮም እስረኛ አይደለም፥ ነገር ግን እራሱም «የክርስቶስ እስረኛ የሆንሁ» (ኤፌ. 3፡1) በማለት ገልጾታል። እስራቱንም «እስራቴ ለክርስቶስ» (ፊልጵ. 1፡13) ነው ይላል። የተራ ሰው ክስ አልተጋፈጠም፤ እርሱ ግን «ወንጌልን መመከቻ ለማድረግ እንደተሾምሁ» (1፡17) አውቃለሁ ይላል። በችግሮቹ ውስጥ ሆኖ ክርስቶስን አያይም፤ ነገር ግን በክርስቶስ ውስጥ ሆኖ ችግሮቹን ይመለከታል። ይህ ደግሞ ሁሉን ለውጧል።
ክርስቲያን በአንድ አሳብ ሲሆን፥ ስለወንጌል አንድነት (1፥1 - 11) ፣ ስለ ወንጌል መስፋፋት (1፡12-26)፥ እና ስለ ወንጌል እምነት (1፡27-30) ያስባል፤ ጳውሎስ በአስቸጋሪ ሁኔታዎች ውስጥ ሁሉ ሆኖ ይደሰታል። ችግሩ ከሌሎች ክርስቲያኖች ጋር ያለውን ኅብረት ለማጠናከር ረድቶታል፥ ሌሎችንም ደግሞ ወደ ክርስቶስ ለማምጣት ዕድል አግኝቷል፥ እንዲሁም ስለወንጌል በሮማ ፍርድ ቤት ፊት ቆሞ ማስረዳት ችሏል። አንድ ልብ ካላችሁ የሚገጥሟችሁ ችግሮች ሁሉ በማብቂያው መልካም ውጤት ያስገኙላችኋል እንጂ ለጥፋት አይዳርጓችሁም።
ይቀጥላል...
ምንጭ፦ ዋረን ደብልዩ ዌርዝ ቢ፤ ደስተኛ ሁን፤ የፊልጵስዩስ መልእክት ፤ ገጽ 6-7

❤11🥰1👏1
በአዲስ ኪዳን ከሚገኙ ቅዱሳት መጻሕፍት ውስጥ የትኛው መጽሐፍ ስለጌታችን ዳግመኛ መምጣት እና ሙታን ትንሣኤ በስፋት ያትታል?
Anonymous Quiz
8%
ሀ. 2ኛ ጢሞቴዎስ
59%
ለ. 1ኛ ተሰሎንቄ
27%
ሐ. 2ኛ ቆሮንቶስ
6%
መ. ይሁዳ
❤11
. ──•◈•─────•◈•─
የዕለቱ ጥቅስ
──•◈•─────•◈•─
“እግዚአብሔርም፦ ሰላም ለአንተ ይሁን አትፍራ አትሞትም አለው።”
መሳፍንት 6፥23
ወደ ቻናሉ ለመ🀄️ላ🀄️ል፦ @Holy_scriptures
የዕለቱ ጥቅስ
──•◈•─────•◈•─
“እግዚአብሔርም፦ ሰላም ለአንተ ይሁን አትፍራ አትሞትም አለው።”
መሳፍንት 6፥23
ወደ ቻናሉ ለመ🀄️ላ🀄️ል፦ @Holy_scriptures
❤12
ቅዱሳት መጻሕፍት
አራቱ ደስታችንን ሊጠብቁ የሚችሉ አመለካከቶች 1. አንድ አሳብ - ፊልጵስዩስ 1 «ሁለት አሳብ ላለው በመንገዱ ሁሉ ለሚወላውል ... አንዳች እንዲያገኝ አይምሰለው» (ያዕ. 1፡8)። ወይንም በጥንት ላቲን ቋንቋ፥ «የመርከቡ ነጂ የሚያርፍበትን ወደብ ካላወቀ የትኛውም ነፋስ አይረዳውም» የሚል ምሳሌ አለ። ለብዙ ክርስቲያኖች በሁኔታዎች አለመሳካት የብስጭት ምክንያት የሚሆነው በ«አንድ አሳብ» ስለማይረጉ…
የቀጠለ...
አራቱ ደስታችንን ሊጠብቁ የሚችሉ አመለካከቶች
2. የሚገዛ አሳብ - ፊልጵስዩስ 2
ይህ ምዕራፍ የሚያተኩረው በሰዎች ላይ ነው፥ መሪ ጥቅሱም «ለወገኔ ይጠቅማል በማለት ወይም በከንቱ ውዳሴ ምክንያት አንድ እንኳ አታድርጉ፥ ነገር ግን እያንዳንዱ ባልንጀራው ከራሱ ይልቅ እንዲሻል በትሕትና ይቁጠር» (2፡3)። በምዕራፍ 1 ላይ ጳውሎስ ክርስቶስን የመጀመሪያው መሻቱ ሲያደርግ፥ በዚህ ምዕራፍ፥ ደግሞ ሌሎችን በሁለተኛ ደረጃ አስቀምጧቸዋል። ይህም የሚያሳየን ራሱን መጨረሻ ማድረጉ ነው! ብዙ ጊዜ በሰዎች ላይ የምንቆጣበት ምክንያት በእኛ አሳብ ስለማይመሩልን ነው። በሕይወት በምንጓዝበት ወቅት እራሳችንን መጀመሪያ ካደረግን፥ እንዲሁም ሌሎችም ራሳቸውን መጀመሪያ ካደረጉ፥ ያንጊዜ በብዙ ነጥቦች ላይ ኃይለኛ ግጭት ይፈጠራል።
አንዲት እናት እና ወንድ ልጇ ወደ ሐኪም ቢሮ ለመሄድ ወደ አሳንሰሩ (ሊፍት) ውስጥ ገቡ። ከሁለተኛው ፎቅ ላይ እንደደረሱም ሌሎች ሰዎች ተጨመሩ። ከእነርሱም መሀል አንዲት ወፍራም ሴት ነበረች። አሳንሰሩም ወደ ላይ መውጣቱን እንደቀጠለ ጸጥታው በወፍራሟ ሴት ጩኸት ደፈረሰ። ወደ ልጁም እናት ዘወር ብላ «ልጅሽ ነከሰኝ እኮ!» አለቻት።
እናትየው በጣም ተሳቀቀች፥ ልጁ ግን ማብራሪያ ነበረው «ፊቴን በቂጧ ስላጣበቀችኝ ነው የነከስኳት» ብሎ አስረዳት።
በአሳንሰሩ ውስጥ የተከሰተው ድርጊት በዓለም ዙሪያ ሁሉ ሲፈፀም የምንመለከተው ነው። ሕዝብ ከሕዝብ፥ መንግሥታት ከመንግሥታት ይነካከሳሉ፥ ምክንያቱም ተፋፍገው ስለሚኖሩ ነው።
ነገር ግን የሚገዛ ትሑት ልብ ያለው ክርስቲያን ሌሎችን ያገለግላል እንጂ ሌላ ሰው እርሱን መጥቶ እንዲያገለግለው አይጠብቅም። ከራሱ ፍላጎትና እቅድ ይልቅ ለሌሎች ምኞት መሟላት ቅድሚያ ይሰጣል። በምዕራፍ 2 ውስጥ በትሑት ልቦናቸው ምሳሌ ሊሆኑን የሚችሉ 4 አስገራሚ ሰዎች እናገኛለን። እነርሱም ኢየሱስ ክርስቶስ (2፡1-11)፥ ጳውሎስ (2፡12-18)፥ ጢሞቴዎስ (2፡19-24) እና አፍሮዲጡን (2፡25-30) ናቸው። እነዚህ ምሳሌዎች «ራሱን ከፍ የሚያደርግ ሁሉ ይዋረዳልና፤ ራሱንም የሚያዋርድ ከፍ ይላል» (ሉቃ. 14፡11) የሚለውን መርሆ ያረጋግጡልናል።
ይቀጥላል...
ምንጭ፦ ዋረን ደብልዩ ዌርዝ ቢ፤ ደስተኛ ሁን፤ የፊልጵስዩስ መልእክት ፤ ገጽ 7-8

“ሀብትህን ሰባት ቦታ፣ እንዲያውም ስምንት ቦታ ከፍለህ አስቀምጥ፤ በምድሪቱ ላይ የሚመጣውን ጥፋት አታውቅምና።”
መክብብ 11፥2 (አዲሱ መ.ት)

❤8🔥2🤝1
ቅዱሳት መጻሕፍት
የቀጠለ... አራቱ ደስታችንን ሊጠብቁ የሚችሉ አመለካከቶች 2. የሚገዛ አሳብ - ፊልጵስዩስ 2 ይህ ምዕራፍ የሚያተኩረው በሰዎች ላይ ነው፥ መሪ ጥቅሱም «ለወገኔ ይጠቅማል በማለት ወይም በከንቱ ውዳሴ ምክንያት አንድ እንኳ አታድርጉ፥ ነገር ግን እያንዳንዱ ባልንጀራው ከራሱ ይልቅ እንዲሻል በትሕትና ይቁጠር» (2፡3)። በምዕራፍ 1 ላይ ጳውሎስ ክርስቶስን የመጀመሪያው መሻቱ ሲያደርግ፥ በዚህ ምዕራፍ፥…
የቀጠለ...
አራቱ ደስታችንን ሊጠብቁ የሚችሉ አመለካከቶች
3. መንፈሳዊ አሳብ - ፊልጵስዩስ 3
በዚህ ምዕራፍ ውስጥ ጳውሎስ ወደ አሥራ አንድ ጊዜ ያህል «ነገር» የሚለውን ቃል ሲጠቀም ታገኛላችሁ። የአብዛኛዎቹ ሰዎች «አሳባቸው ምድራዊ» (3፡19) ለሆኑ ነገሮች ሲሆን፥ መንፈሳዊ ልብ ያላቸው ክርስቲያኖች ግን የሚጨነቁት ስለ ሰማያዊ ነገሮች መሆኑን ያሳየናል። «እኛ አገራችን በሰማይ ነውና፥ ከዚያም ደግሞ የሚመጣ መድኃኒት እርሱም ጌታን ኢየሱስ ክርስቶስን እንጠባበቃለን» (3፡20)። መንፈሳዊ ልብ ያለው ሰው የዚህን ዓለም ነገሮች የሚያያቸው በሰማያዊ አመለካከት አንፃር ነው - ታዲያ ይህ ምን ያህል ትልቅ ልዩነት ያመጣል!
በኢኳዶር ኡካስ ውስጥ አምስት ሚሲዮናዊያን በተገደሉበት ጊዜ አሳዛኝ የሆነው አሟሟታቸውን አንዳንድ ጋዜጦችና መጽሔቶች ታላቅ የሕይወት ጥፋት በማለት ገልጸውታል። በዚያን ጊዜ ለጓደኞቻቸውና ለወዳጆቻቸው ታላቅ ሀዘንና ቁጭት ቢያደርስባቸውም የኋላ ኋላ ግን ሞታቸው ለእነርሱም ሆነ ለዓለም «ጥፋት» እንዳልሆነ ተረጋገጠ። ጅም እልይት የተባለው ሰባኪ፥ «ሰው መያዝ የማይችለውን በመስጠት፥ ማጣት የማይችለውን ካገኘ ሞኝ አያሰኘውም» ሲል የተናገረው በእውነትም ትክክለኛ ነበር።
«ምድራዊ ነገርን» ፍለጋ መሮጥ የሰዎችን ደስታ ይሰርቃል፥ እና ይህ ደግሞ ክርስቲያኖችንም ይጨምራል። እኛ አንድን ነገር ለመያዝ እንፈልጋለን፥ በኋላ ግን እርሱ እኛን ተቆጣጥሮን እናገኘዋለን። ለዕድልና ለደስታ ብቸኛው መንገድ መንፈሳዊ ልብ መኖርና ነገሮችን ከእግዚአብሔር ወገን ሆኖ ማየት ነው። እንደ ጳውሎስ፥ ለነገሮች ትክክለኛ ሚዛን ያለን ሰዎች (3፡1-11)፥ ትክክለኛ ወኔ ያለን ሯጮች (3፡12-16) ወገናዊነት የማያጠቃን ትክክለኛ ራእይ ያለን ተቆርቋሪዎች (3፡17-21) መሆን አለብን። «እቆጥራለሁ ... እፈጥናለሁ ... እመለከታለሁ» የሚሉት ግሦች መንፈሳዊ ልብ (አስተሳሰብ) ያለውን ሰው ይገልጻሉ።
ይቀጥላል...
ምንጭ፦ ዋረን ደብልዩ ዌርዝ ቢ፤ ደስተኛ ሁን፤ የፊልጵስዩስ መልእክት ፤ ገጽ 8

Audio
🥰1