ቅዱሳት መጻሕፍት
7.46K subscribers
1.36K photos
61 videos
332 files
802 links
በዚህ ቻናል

👉ቅዱሳት መጻሕፍት ይጠናሉ::
👉መጽሐፍ ቅዱሳዊ ትምህርቶች ይቀርባሉ::
👉 ለቅዱሳት መጽሐፍት ጥናት የሚያግዙ መጻሕፍት ይለቀቃሉ።

⭐️⭐️⭐️⭐️⭐️

@Holy_scriptures
Download Telegram
ቅዱሳት መጻሕፍት
#በዓለ_ኀምሳ #ጰራቅሊጦስ የቀጠለ... የጉባኤ ኒቂያ ዘመን የኒቂያ ጉባኤ መነሻ ምክንያት የሆነው አርዮስ የተባለ የኑፋቄ መምህር ወልድ እና መንፈስ ቅዱስ ከእግዚአብሔር አብ ጋር በባሕርይ አንድ ያልሆኑ እና ፍጡራን ናቸው ብሎ በማስተማሩ ምክንያት ነው። በመጨረሻም ለአሪዮስ መንፈስ ቅዱስ በእግዚአብሔር ወልድ የተፈጠረ፣ በተፈጠረ አካል የተፈጠረ ፍጡር (የፍጡር ፍጡር) ነው። የአሪዮስ ኑፋቄያዊ አስተምህሮ…
#በዓለ_ኀምሳ
#ጰራቅሊጦስ

የቀጠለ...



የፕሮቴስታን ተሓድሶ ዘመን

የሮም ካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን በቅድመ ተሓድሶ ዘመን ከቅዱስ አውግስጢኖስ ሐሳብ ዞር በማለት የቶማስ አኳይናስን የሥነ መለኮት አስተምህሮ የቤተ ክርስቲያንቷ የእምነት አቋም ምሰሶ አድርጋ ይዛ ነበር። ይሁን እንጂ በፕሮቴስታንት ተሓድሶ ዘመን ቤተ ክርስቲያን በቅድመ ተሓድሶ ዘመን ተዘንግቶ ወደ ነበረው ወደ የቅዱስ አውግስጢኖስ ሐሳብ የተመለሰችበት ዘመን ነው። ሆኖም በፕሮቴስታንት የተሓድሶ ዘመን ቅዱሳት መጻሕፍትን አንብቦ መረዳት ላይ ከፍተኛ ትኩረት የተሰጠበት ዘመን ከመሆኑ የተነሣ፣ እንደ ማርቲን ሉተር ያሉት የፕሮቴስታንት የተሓድሶ አራማጆች፣ “አንድ ሰው በክርስቶስ የሚያምነው ቅዱሳት መጻሕፍትን አንብቦ መረዳት ሲችል ብቻ ነው” ብለው ያስተምሩና ለዚህ አስተምህሮ ከፍተኛ አጽንዖት ይሰጡ ስለ ነበር ሰዎችን በማዳን ሂደት ውስጥ መንፈስ ቅዱስ ያለው ሚና ምን እንደ ሆነ የተዘነጋ ይመስላል። ይሁን እንጂ ከተሓድሶ አራማጆች መካከል የሆነው ጆን ካልቪን በሮም ቤተ ክርስቲያን ውስጥ በቅድመ ተሓድሶ ዘመን ተዘንግቶ የነበረውን የቅዱስ አውግስጢኖስ አስተምህሮ፣ ማለትም መንፈስ ቅዱስ በሰዎች ድነት ውስጥ ያለውን ሚና እንደገና አነቃቅቷል።

የድኅረ ተሓድሶ ዘመን

በድኅረ ተሓድሶ ዘመን የመንፈስ ቅዱስ ኀይል ሰዎችን በማዳን ረገድ የሚያከናውናቸው ሁለት ነገሮች ጎልተው ወጥተዋል፤ እነዚህም የውሸት ብህትውና (False Mystcism) እና የውሸት አመክኑያዊነት (False Rationalism) ናቸው። ጆን ዊስሊ ከተሓድሶ ዘመን በኋላ በመንፈስ ቅዱስን አስተምህሮ ላይ ትልቅ ብርሃን የፈነጠቀው በዚህ ወቅት ነበር። ከዚያን ጊዜ ጀምሮ ቤተ ክርስቲያን ስለ መንፈስ ቅዱስ ይበልጥ መረዳት ጀመረች። ምንም እንኳ የጆን ዊስሊ ሥነ መለኮት ፍጹም ባይሆንም ቤተ ክርስቲያን ስለ መንፈስ ቅዱስ በደንብ መረዳት የጀመረችው ግን በእርሱ ዘመን መሆኑን መካድ አይቻልም።

መንፈስ ቅዱስ በዘመናችን

ከዚህ በላይ በተመለከትነው የቤተ ክርስቲያን ታሪክ ውስጥ ከመንፈስ ቅዱስ ጋር ተያያዥነት ያላቸው ኑፋቄዎች አብዛኞቹ በመንፈስ ቅዱስ ማንነት የሚያጠነጥኑ የአስተምህሮዊ ኑፋቄዎች ናቸው። ይሁን እንጂ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በኢትዮጵያ ውስጥ ከፍተኛ ትኩረት የሚሰጠው ለአስተምህሮ ሳይሆን ለክንዋኔ ሆኗል። በአተገባበርም ወቅት የሚፈጠሩ ስሕተቶች በብዛት በኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን ውስጥ ይስተዋላሉ። እነዚህን ስሕተቶች እንደ ኑፋቄ መመልከት አለብን ወይስ የለብንም? እነዚህ በአስተምህሮ ሊገሩ የሚችሉ ቀላል ስሕተቶች በመሆናቸው በኑፋቄ ጎራ ሊፈረጁ አይገባም የሚል
ሙግት ሊነሣ ይችላል። ይሁን እንጂ አንዳንድ ከመንፈስ ቅዱስ ጋር ከፍተኛ ቁርኝት ያላቸው የኢትዮጵያን ቤተ ክርስቲያን ልምምዶች ታሳቢ የሚያደርጉት ምንጫቸውን (አስተምህሯቸውን) በመሆኑ ልምምዶቹም የነፈቁ ናቸው ለማለት ያስደፍራል።



ምንጭ:- hintset.org



ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
9🔥1
.       ──•◈•─────•◈•─
                          የዕለቱ ጥቅስ
        ──•◈•─────•◈•─
“እነሆ፥ እግዚአብሔር የሚገሥጸው ሰው ምስጉን ነው፤ ስለዚህ ሁሉን የሚችለውን የአምላክን ተግሣጽ አትናቅ።”
ኢዮብ 5፥17



ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
10
Pilgrm's progress
Nigusse Denano
#መጻሕፍትን_በድምጽ

📔ርዕስ፦ የመናኝ ጉዞ
👤ጸሐፊ፦ ዮሐንስ ቡንያን
👉ክፍል-12

ይቀጥላል. . .


ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
የእግዚአብሔርን ፀጋ የምንጥልባቸው አራቱ መንገዶች


የእግዚአብሄርን ፀጋ የምናጣበት ሃይል አልባ የሚያደርጉን አራቱ መንገዶች

1. ትህትናን መጣል  

ሰው ትህትናን ከጣለ የጊዜ ጉዳይ ነው እንጂ እንደሚወድቅ ምንም ጥርጥር የለውም፡፡ ሰው እግዚአብሄር ከሰጠው ደረጃ በላይ ራሱን ከፍ አድርጎ ሲያይ ከእግዚአብሄር ጋር ይተላለፋል፡፡ እግዚአብሄር ፀጋን መስጠትና ማንሳት ከፍ ማድረግ እየፈለገ በራሱ ነገሮችን ማደርግ እንደሚችል የሚያስበውን ትእቢተኛን ሰው ግን ከመቃወም ውጭ ምንም ሊያደርገው አይችልም፡፡  

“ነገር ግን ጸጋን አብልጦ ይሰጣል፤ ስለዚህ፦ እግዚአብሔር ትዕቢተኞችን ይቃወማል፥ ለትሑታን ግን ጸጋን ይሰጣል ይላል።”
ያዕቆብ 4፥6

2. እውቀትን መጣል

ሰው ከመሬት ተነስቶ አውቆ የጨረሰ ከመሰለው በህይወቱ ማደግና መለወጥ አቁሟል ማለት ነው፡፡ ይህ ሰው ለአዲስ ተግዳሮት በእውቀት ራሱን ካላስታጠቀ መውደቁ አይቀሬ ነው፡፡ ይህ ሰው ያወቀና የጨረሰ ከመሰለው እጅግ አሰቃቂ ነው፡፡

"ለጣዖት ስለ ተሠዋ ሥጋም፥ ሁላችን እውቀት እንዳለን እናውቃለን። እውቀት ያስታብያል ፍቅር ግን ያንጻል። ማንም አንዳች የሚያውቅ ቢመስለው ሊያውቅ እንደሚገባው ገና አላወቀም፤" (1ኛ ቆሮ. 8፡1-2)

“ሕዝቤ እውቀት ከማጣቱ የተነሣ ጠፍቶአል፤ አንተም እውቀትን ጠልተሃልና እኔ ካህን እንዳትሆነኝ እጠላሃለሁ፤ የአምላክህንም ሕግ ረስተሃልና እኔ ደግሞ ልጆችህን እረሳለሁ።”
ሆሴዕ 4፥6

"በእግዚአብሔርና በጌታችን በኢየሱስ እውቀት ጸጋና ሰላም ይብዛላችሁ።"( 2ኛ ጴጥ. 1፥2)

3. እምነትን መጣል

ሰው በእግዚአብሄር ላይ መደገፍን ትቶ በራሱ ስራ ላይ ሲደገፍ ከእግዚአብሄር ፀጋ ይጎድላል፡፡ ሰው ለመዳንም ሆነ ከዳነ በኋላ ለመቀደስ ፣ ለእግዚአብሄር መንግስት ለመስራትና እግዚአብሄርን ለማስደሰት በራሱ ጉልበትና ቅልጥፍና ላይ ሲደገፍ ከእግዚአብሄር ፀጋ ይጎድላል፡፡

"በሕግ ልትጸድቁ የምትፈልጉ ከክርስቶስ ተለይታችሁ ከጸጋው ወድቃችኋል።" (ገላ. 5፥4)

4. ምስጋናን መጣል

ሰው ምንም ከማይወጣለት መልካም አምላክ ጋር እየኖረ ካጉረመረመና ማመስገን ካቃተው ከእግዚአብሄር ፀጋ ይጎድላል፡፡ ሰው በእግዚአብሄር አሰራር ላይ አቃቂር ማውጣት ከቻለ የሆነ የሳተው ነገር አለ ማለት ነው፡፡ ሰው ከእግዚአብሄር በላይ የሚያውቅ ከመሰለው የሆነ የተዛባ ነገር አለ ማለት ነው፡፡ ሰው በእግዚአብሄር አሰራር ካልታመነ ከእግዚአብሄር ጋር በየዋህነት መኖር ፣ ራሱን መስጠት ፣ ለእግዚአብሄር በየዋህነት መስራትና ፍሬያማ መሆን ያቅተዋል፡፡   

"አንድ መክሊትም የተቀበለው ደግሞ ቀርቦ፦ ጌታ ሆይ፥ካልዘራህባት የምታጭድ ካልበተንህባትም የምትሰበስብ ጨካኝ ሰው መሆንህን አውቃለሁ፤ ፈራሁም ሄጄም መክሊትህን በምድር ቀበርሁት፤ እነሆ፥ መክሊትህ አለህ አለ።"(ማቴ. 25፥24-25)

"ከእነርሱም አንዳንዶቹ እንዳንጎራጎሩ በሚያጠፋውም እንደጠፉ አታንጐርጕሩ።" (1ኛ ቆሮ. 10፥10)


ምንጭ:- አብይ ዋቁማ



ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
8🙏4👍2🔥2
ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
5
ተግተህ አገልግል.pdf
6.5 MB
👉ርዕስ፦ ተግተህ አገልግል
የማርቆስ ወንጌል
ከአገልጋዩ ጌታ ጋር ስትጓዝ ሌሎችንም አገልግል
✍️ጸሐፊ፦ ዋረን ደብልዩ ዌርዝቢ
🗣ትርጉም፦ ግርማዊ
✏️እርማት፦ ኃይሌ ጀናይ


ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
9
.       ──•◈•─────•◈•─
                          የዕለቱ ጥቅስ
        ──•◈•─────•◈•─
“በሰይፋቸው ምድርን አልወረሱም ክንዳቸውም አላዳናቸው፤ ቀኝህና ክንድህ የፊትህም ብርሃን ነው እንጂ፤ ወድደሃቸዋልና።”
መዝሙር 44፥3



ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
👍51
PPlgims Progress
Nigusse Denano
#መጻሕፍትን_በድምጽ

📔ርዕስ፦ የመናኝ ጉዞ
👤ጸሐፊ፦ ዮሐንስ ቡንያን
👉ክፍል-13

ይቀጥላል. . .


ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
ለጌታ-የተገዛህ ሁን.pdf
9.5 MB
👉ርዕስ፦ ለጌታ-የተገዛህ ሁን
የማቴዎስ ወንጌል
የክብር ንጉሥን በማወቅና በማገልገል ሐሤት አድርግ
✍️ጸሐፊ፦ ዋረን ደብልዩ ዌርዝቢ
🗣ትርጉም፦ ግርማዊ
✏️እርማት፦ ዐብይ ደምሴ እና ኃይሌ ጀናይ


ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
8🥰3
#እራሳችንን_እንመርምር



በየትኛውም በሕይወት መስክ፣ ምንም ይሁን የትም የምንሰራው እንዴት ነው? በቸልተኝነት? በዋዛ ፈዛዛ? በሙሉ ልብ?

“ለሰው ሳይሆን ለጌታ እንደምታደርጉ፥ የምታደርጉትን ሁሉ በትጋት አድርጉት፥”
ቆላስይስ 3፥23



ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
👍61🤔1
.       ──•◈•─────•◈•─
                          የዕለቱ ጥቅስ
        ──•◈•─────•◈•─
“ጌታቸው በመጣ ጊዜ ሲተጉ የሚያገኛቸው እነዚያ ባሪያዎች ብፁዓን ናቸው፤ እውነት እላችኋለሁ፥ ታጥቆ በማዕድ ያስቀምጣቸዋል ቀርቦም ያገለግላቸዋል።”
ሉቃስ 12፥37



ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
👍3
Plgrim's progress
Nigusse Denano
#መጻሕፍትን_በድምጽ

📔ርዕስ፦ የመናኝ ጉዞ
👤ጸሐፊ፦ ዮሐንስ ቡንያን
👉ክፍል-14

ይቀጥላል. . .


ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
ቅዱሳት መጻሕፍት
ክርስቲያናዊ ዓቅብተ እምነት – CHRISTIAN APOLOGETICS           ክፍል-2 1.2. የክርስቲያን ዓቅብተ እምነት ታሪክ የክርስቲያን ዓቅብተ እምነት ታሪክ ከመጀመርያው ክፍለ ዘመን የሚጀምር ቢሆንም እንደ አንድ የጥናት ዘርፍ የጎለበተውና ወጥ የሆነ መልክ የያዘው ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ነው፡፡ ክርስቲያናዊው ዓቅብተ እምነት በተለያዩ የዕድገት ደረጃዎች ውስጥ አልፏል፡፡ ክርስትና በተጀመረበት…
ክርስቲያናዊ ዓቅብተ እምነት – CHRISTIAN APOLOGETICS


            ክፍል-3


በክርስቲያን ዓቅብተ እምነት ታሪክ ውስጥ የእስክንድሪያ ክርስቲያኖች ያበረከቱት አስተዋጽዖ ከሁሉም የላቀ ነበር፡፡ የእስክንድሪያው ቀለሜንጦስ “ፕሮትሬፕቲከስ” (ልባዊ ምክር) በሚል ርዕስ የጻፈው ዓቃቤ እምነታዊ ጽሑፍ በሁለተኛው ክፍለ ዘመን ከተጻፉ ተመሳሳይ ጽሑፎች ሁሉ የላቀ ነበር፡፡

በሦስተኛው ክፍለ ዘመን ከተነሱት ክርስቲያን አቃቤ እምነታውያን መካከል ኦሪጎን (185-254 ዓ.ም.) ቀዳሚውን ስፍራ ይይዛል፡፡ ሴልሰስ የተባለ ሰው በክርስትና ላይ ላቀረበው ፍልስፍናዊ፣ ግብረ ገባዊና ታሪካዊ ትችት ምላሽ ለመስጠት “ኮንትራ ሴልሰስ” በሚል ርዕስ የጻፈው ረዘም ያለ ጽሑፉ እስከ አሁኑ ዘመን ድረስ ጠቃሚ የመረጃ ምንጭ በመሆን እያገለገለ ይገኛል፡፡ በዚህ ጽሑፉ ኦሪጎን ኢየሱስ ተዓምራቱን በአስማት እንዳላደረገና የአረማውያን የተዓምራት ታሪኮች ከኢየሱስ ታሪኮች እጅግ ያነሰ ተዓማኒነት እንዳላቸው ተሟግቷል፡፡ የኢየሱስን ትንሣኤ ታሪካዊነት “ከቁም ቅዠት” (Hallucination) መላ ምት በመከላከል ረገድም የሚደነቅ የመከላከያ ሐሳብ አቅርቧል፡፡

የሂፖ ሬጊዩስ ሊቀ ጳጳስ የነበረው ቅዱስ አውጉስጢኖስ (354-430 ዓ.ም.) ክርስቲያኖች በንጉሥ ቆስጠንጢኖስ አዋጅ ነጻነትን ከተጎናጸፉ በኋላ ከተነሱት ክርስቲያን ዓቃቤ እምነታውያን መካከል ቀዳሚውን ስፍራ ይይዛል፡፡ ክርስትና ከአረማዊነት የላቀ መሆኑን የሚያሳዩ፣ የስህተት ትምህርቶችን የሚያጋልጡና የክርስትናን አስተምህሮዎች ቀና በሆነ መንገድ የሚያስተምሩ ብዙ ጽሑፎችን የጻፈ ታላቅ ሊቅ ነበር፡፡ የአውጉስጢኖስ ክርስቲያናዊ ፍልስፍና የበለጠ ሰፋ ባለ መልኩ ሰፍሮ የምናገኘው በምዕራቡ ዓለም ውስጥ ከተጻፉ አስር በጣም ጠቃሚ መጻሕፍት መካከል አንዱ ተደርጎ በሚቆጠረው “የእግዚአብሔር ከተማ” በሚል ርዕስ በጻፈው የመጨረሻ መጽሐፉ ውስጥ ነው፡፡ አውጉስጢኖስ ስለ ዓቅብተ እምነት ያስተማረው ትምህርት ከርሱ ዘመን ጀምሮ እስከዚህ ዘመን ድረስ ለብዙ ክርስቲያን ዓቃቤ እምነታውያንና የነገረ መለኮት ምሑራን መነሳት ምክንያት ሆኗል፡፡

ቤተ ክርስቲያን ካፈራቻቸው ታላላቅ ሊቃውንት መካከል የካንቴርበሪ ሊቀ ጳጳስ የነበረው አንሴልም (1033-1109 ዓ.ም.) ይጠቀሳል፡፡ ከርሱ በፊት ያልተነገሩ የራሱ የሆኑ አዳዲስ ሐሳቦችን በማመንጨት የሚታወቅ ሲሆን አውጉስጢኖስ ስለ እምነትና ምክንያት ያስተማራቸውን ነገሮች በማጉላትም ይታወቃል፡፡ ስለ እምነትና ስለ ምክንያት ከተናገራቸው ነገሮች መካከል የሚከተለው ይገኝበታል፦ “ለማመን መረዳት እንዲኖረኝ ጥረት አላደርግም ነገር ግን ለመረዳት እምነት እንዲኖረኝ ጥረት አደርጋለሁ፡፡” አንሴልም ፈላስፎች “Ontological Argument” በማለት ለሚጠሩት የእግዚአብሔርን መኖር ለሚያስረዳ እጅግ ጠቃሚ ሐሳብ መሠረት የጣለ ሰው ነበር፡፡ “ኩር ዴኡስ ሆሞ” (አምላክ ሰው የሆነበት ምክንያት) በሚለው መጽሐፉ ውስጥ የኢየሱስ በሰው ሥጋ መምጣት ለምን እንዳስፈለገ አመክንዮአዊ በሆነ መንገድ በማስረዳት ለክርስቲያን ዓቅብተ እምነት ከፍተኛ አስተዋጽዖ አበርክቷል፡፡

በአስራ ሦስተኛው ክፍለ ዘመን አቬሮስ በተባለ የእስፔን አረብ አማካይነት የአርስጣጣሊስ (አርስቶትል) ፍልስፍና በመላው አውሮፓ በሚገኙ ዩኒቨርሲቲዎች ውስጥ ከመሰራጨቱ የተነሳ ክርስቲያናዊው ንፅረተ ዓለም ከፍተኛ ቀውስ ገጥሞት ነበር፡፡ ሊቃውንት ያለ ምንም ምርመራ የአርስጣጣሊስን አስተሳሰብ የተቀበሉ ሲሆኑ የቤተ ክርስቲያን መሪዎችም ያለ ምንም ምርመራ ከአርስጣጣሊስ ፍልስፍና ጋር የተያያዙትን ነገሮች ሁሉ ይቃወሙ ነበር፡፡ ታላቁ አልበርት የተባለ ክርስቲያን ሊቅ ለአቬሮስ ምላሽ የሚሆን ጽሑፍ የጻፈ ቢሆንም ነገር ግን ለዚህ ተግዳሮት ምላሽን በመስጠት የክርስቲያናዊውን ፍልስፍናና ዓቅብተ እምነት አቅጣጫ ማስለወጥ የቻለው የአልበርት ደቀ መዝሙር የነበረው ቶማስ አኳይነስ (1225-1274) ነበር፡፡ ለአቬሮስ ምላሽ ሊሆን የሚችል ጽሑፍ የአርስጣጣሊስን ቋንቋ በመጠቀም ከመጻፉ ሌላ ለክርስቲያን ተማሪዎች ሊሆን የሚችል የሥነ መለኮት መጽሐፍም አበርክቷል፡፡ አኳይነስ በቤተ ክርስቲያን ታሪክ ከተነሱ ታላላቅ ፈላስፎች መካከል አንዱ ነበር፡፡


ይቀጥላል...


ምንጭ:- ewnetlehulu.org



ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
9
.       ──•◈•─────•◈•─
                          የዕለቱ ጥቅስ
        ──•◈•─────•◈•─
“እግዚአብሔር ስለ ጽድቁ ሕጉን ታላቅ ያደርግና ያከብር ዘንድ ወደደ።”
ኢሳይያስ 42፥21



ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
8
Plgrim's Progress
Nigusse Denano
#መጻሕፍትን_በድምጽ

📔ርዕስ፦ የመናኝ ጉዞ
👤ጸሐፊ፦ ዮሐንስ ቡንያን
👉ክፍል-15

ይቀጥላል. . .


ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
2
ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
1
የገላጭ ስብከት አዘገጃጀት.pdf
7.6 MB
👉ርዕስ፦ የገላጭ ስብከት አዘገጃጀት
✍️ጸሐፊ፦ ዶክተር ራሜሽ ሪቻርድ
🗣ተርጓሚ፦ ገበየሁ አየለ
✏️ኤዲተርና ልዩ ረዳት፦ ስምዖን ሙላቱ


ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
👍83🔥1
.       ──•◈•─────•◈•─
                          የዕለቱ ጥቅስ
        ──•◈•─────•◈•─
“ስለዚህም በሙሴ ሕግ መጽሐፍ የተጻፈውን ሁሉ ለመጠበቅና ለማድረግ በጣም በርቱ፥ ከእርሱም ወደ ቀኝም ወደ ግራም ፈቀቅ አትበሉ።”
ኢያሱ 23፥6


ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
🙏52👏1
Plggrim's Pogress
Nigusse Denano
#መጻሕፍትን_በድምጽ

📔ርዕስ፦ የመናኝ ጉዞ
👤ጸሐፊ፦ ዮሐንስ ቡንያን
👉ክፍል-16

ይቀጥላል. . .


ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
አራቱ ደስታችንን ሊጠብቁ የሚችሉ አመለካከቶች


1. አንድ አሳብ - ፊልጵስዩስ 1

«ሁለት አሳብ ላለው በመንገዱ ሁሉ ለሚወላውል ... አንዳች እንዲያገኝ አይምሰለው» (ያዕ. 1፡8)። ወይንም በጥንት ላቲን ቋንቋ፥ «የመርከቡ ነጂ የሚያርፍበትን ወደብ ካላወቀ የትኛውም ነፋስ አይረዳውም» የሚል ምሳሌ አለ። ለብዙ ክርስቲያኖች በሁኔታዎች አለመሳካት የብስጭት ምክንያት የሚሆነው በ«አንድ አሳብ» ስለማይረጉ ነው። ጳውሎስ ለክርስቶስ፥ በአንድ ልብ የመሰጠትን አመለካከት ሲገልጽ፤ «ለእኔ ሕይወት ክርስቶስ ሞትም ጥቅም ነውና» (1፡21) ብሏል።

በምዕራፍ አንድ ጳውሎስ የገጠሙትን አስቸጋሪ ሁኔታዎች በታማኝነት እንደተጋፈጠ አስረድቷል። ግን የገጠሙት ሁኔታዎች ያለውን ደስታ ሊያሳጡት አልቻሉም። ምክንያቱም እርሱ የሚኖረው በሁኔታዎች ውጤት ለመደሰት ሳይሆን ኢየሱስ ክርስቶስን ለማገልገል በመሆኑ ነው። እርሱ ዓላማ ያለው ሰው ነው። «አንድ ነገር አደርጋለሁ» (3፡13)። የሚገጥሙትን ነገሮች ሁሉ ከክርስቶስ ጋር በማያያዝ እንጂ ነገሮችን ብቻቸውን አይመለከትም። ጳውሎስ የሮም እስረኛ አይደለም፥ ነገር ግን እራሱም «የክርስቶስ እስረኛ የሆንሁ» (ኤፌ. 3፡1) በማለት ገልጾታል። እስራቱንም «እስራቴ ለክርስቶስ» (ፊልጵ. 1፡13) ነው ይላል። የተራ ሰው ክስ አልተጋፈጠም፤ እርሱ ግን «ወንጌልን መመከቻ ለማድረግ እንደተሾምሁ» (1፡17) አውቃለሁ ይላል። በችግሮቹ ውስጥ ሆኖ ክርስቶስን አያይም፤ ነገር ግን በክርስቶስ ውስጥ ሆኖ ችግሮቹን ይመለከታል። ይህ ደግሞ ሁሉን ለውጧል።

ክርስቲያን በአንድ አሳብ ሲሆን፥ ስለወንጌል አንድነት (1፥1 - 11) ፣ ስለ ወንጌል መስፋፋት (1፡12-26)፥ እና ስለ ወንጌል እምነት (1፡27-30) ያስባል፤ ጳውሎስ በአስቸጋሪ ሁኔታዎች ውስጥ ሁሉ ሆኖ ይደሰታል። ችግሩ ከሌሎች ክርስቲያኖች ጋር ያለውን ኅብረት ለማጠናከር ረድቶታል፥ ሌሎችንም ደግሞ ወደ ክርስቶስ ለማምጣት ዕድል አግኝቷል፥ እንዲሁም ስለወንጌል በሮማ ፍርድ ቤት ፊት ቆሞ ማስረዳት ችሏል። አንድ ልብ ካላችሁ የሚገጥሟችሁ ችግሮች ሁሉ በማብቂያው መልካም ውጤት ያስገኙላችኋል እንጂ ለጥፋት አይዳርጓችሁም።


ይቀጥላል...



ምንጭ፦ ዋረን ደብልዩ ዌርዝ ቢ፤ ደስተኛ ሁን፤ የፊልጵስዩስ መልእክት ፤ ገጽ 6-7




ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
11🥰1👏1