ቅዱሳት መጻሕፍት
7.45K subscribers
1.36K photos
61 videos
332 files
802 links
በዚህ ቻናል

👉ቅዱሳት መጻሕፍት ይጠናሉ::
👉መጽሐፍ ቅዱሳዊ ትምህርቶች ይቀርባሉ::
👉 ለቅዱሳት መጽሐፍት ጥናት የሚያግዙ መጻሕፍት ይለቀቃሉ።

⭐️⭐️⭐️⭐️⭐️

@Holy_scriptures
Download Telegram
#ጰራቅሊጦስ

ዛሬው ቀን መንፈስ ቅዱስ የወረደበት በዓለ ኀምሳ ነው። በቅዱሳት መጸሕፍት መንፈስ ቅዱስ ጰራቅሊጦስ ተብሎ ተገልጿል። ጰራቅሊጦስ (ግሪክ፡ παράκλητος፣ ላቲን፡ ጰራቅሊጦስ) ጠበቃ ወይም ረዳት ማለት ነው። በክርስትና ውስጥ፣ “ጰራቅሊጦስ” የሚለው ቃል በአብዛኛው የሚያመለክተው መንፈስ ቅዱስን ነው። ጰራቅሊጦስ የመጣው ከኮይኔ የግሪክ ቃል ነው παράκλητος (paráklētos)። ይህ ስያሜ የሁለት ጥምር ቃል ውህደት ነው። “ፓራ” (በጎን/ጎን) እና “ካሌይን” ("to call" ወይም ለመጥራት)። በመጀመሪያ በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ በዮሐንስ 14፥16 ይገኛል።
በአጠቃላይ በአዲስ ኪዳን 5 ጊዜ የተጠቀሰ ሲሆን 4 ጊዜ በዮሐንስ ወንጌል(14፥16፤ 14፥26፤ 15፥26፤ 16፥7) አንድ ጊዜ ደግሞ በ1ኛ ዮሐንስ መልእክት (2፥1) ውስጥ ይገኛል። በ1ኛ ዮሐንስ ያለው ቃል የሚናገረው ስለጌታችን እና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ነው።


ምንጭ፦ lsj.gr/wiki/paracletus



ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
11
.       ──•◈•─────•◈•─
                          የዕለቱ ጥቅስ
        ──•◈•─────•◈•─
“ደግሞም ያተመን የመንፈሱንም መያዣ በልባችን የሰጠን እርሱ ነው።”
2ኛ ቆሮ 1፥22



ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
9🔥2
Pligrim's Progress
Nigusse Denano
#መጻሕፍትን_በድምጽ

📔ርዕስ፦ የመናኝ ጉዞ
👤ጸሐፊ፦ ዮሐንስ ቡንያን
👉ክፍል-8

ይቀጥላል. . .


ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
3
ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
2
የሉቃስ ወንጌል መክፈቻ.pdf
5.5 MB
ርዕስ፦ የሉቃስ ወንጌል መክፈቻ


ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
4❤‍🔥3
.       ──•◈•─────•◈•─
                          የዕለቱ ጥቅስ
        ──•◈•─────•◈•─
“ይህ ሕዝብ ወይም ነቢይ ወይም ካህን፦ የእግዚአብሔር ሸክም ምንድር ነው? ብሎ ቢጠይቅህ፥ አንተ፦ ሸክሙ እናንተ ናችሁ፥ እጥላችሁማለህ፥ ይላል እግዚአብሔር ትላቸዋለህ።”
ኤርምያስ 23፥33



ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
👍2👏1🙏1
Pilgrim's Progress
Nigusse Denano
#መጻሕፍትን_በድምጽ

📔ርዕስ፦ የመናኝ ጉዞ
👤ጸሐፊ፦ ዮሐንስ ቡንያን
👉ክፍል-9

ይቀጥላል. . .


ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
2
ርኅሩኅ ሁን.pdf
5.4 MB
👉ርዕስ፦ ርኅሩኅ ሁን
ሉቃስ ምዕራፍ 1-13
አዳኙን ወደ መምሰል በበለጠ እንድናድግ የቀረበ ጥሪ
✍️ጸሐፊ፦ ዋረን ደብልዩ ዌርዝቢ
🗣ትርጉም፦ ግርማዊ
✏️እርማት፦ ዓለማየሁ ማሞ


ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
5🔥1
ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
1
የበረታህ ሁን.pdf
4.8 MB
👉ርዕስ፦ የበረታህ ሁን
ሉቃስ ምዕራፍ 14-24
የክርስቶስን ምሳሌነት ተከተል
✍️ጸሐፊ፦ ዋረን ደብልዩ ዌርዝቢ
🗣ትርጉም፦ ግርማዊ
✏️እርማት፦ ዓለማየሁ ማሞ


ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
👍74🔥1
.       ──•◈•─────•◈•─
                          የዕለቱ ጥቅስ
        ──•◈•─────•◈•─
“አባቶችህን ወድዶአልና ከእነርሱ በኋላ ዘራቸውን መረጠ፥ ዛሬ እንደ ሆነው ሁሉ ከአንተ የጸኑትን ታላላቆችን አሕዛብ በፊትህ እንዲያወጣ፥ አንተንም እንዲያገባህ፥ ምድራቸውንም ርስት አድርጎ እንዲሰጥህ፥ ከአንተ ጋር ሆኖ በታላቅ ኃይሉ ከግብፅ አወጣህ።”
ዘዳግም 4፥37-38



ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
12
Pilgrim's Progress
Nigusse Denano
#መጻሕፍትን_በድምጽ

📔ርዕስ፦ የመናኝ ጉዞ
👤ጸሐፊ፦ ዮሐንስ ቡንያን
👉ክፍል-10

ይቀጥላል. . .


ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
🔥1
የመንፈሳዊ ራብ በረከት



መንፈሳዊ ራብ ጌታን መናፈቅን፣እሱን ለማግኘት መጓጓትን፣ወደ እሱ ለመጠጋት ማሰብን ወዘተ ያመለክታል፡፡

በግለሰብ ይሁን በወል ደረጃ መንፈሳዊ ራብና ጥማት ለእግዚአብሔር መለኮታዊ ጉብኝት እጅግ ወሳኝ ናቸው፡፡አውነተኛ የሆነ መንፈሳዊ ራብና ጥማት እግዚአብሔርን እንድንሻው፣ እንድንፈልገውና እንድንጠጋው ኃይል ይሆኑናል፡፡ ቃሉ “ጽድቅን የሚራቡና የሚጠሙ ብፁዓን ናቸው” (ማቴዎስ 5፡6) የሚለን ለዚህ ነው፡፡ “ብፁዓን” የሚለውን ቃል አምሊፋይድ መጽሐፍ ቅዱስ (Amplified Bible) ደስተኞች፣ በመንፈስ ባለጸጋ የሆኑ፣ የረኩ፣ የተባረኩ ወዘተ ብሎ ነው የሚገልጸው፡፡

ሐና መንፈሳዊ ራብ ያላቸው ሰዎች በጌታ ፊት ዋጋ ያላቸውና የማይረሱ እንደ ሆነ ስትናገር “ተርበው የነበሩ ከራብ አርፈዋል” (1 ሳሙኤል 2:5) ብላለች፤ አምላኳ የሚያረካ፣የሚያጠግብና የሚያሳርፍ መሆኑን በማወደስ፡፡

መንፈሳዊ ራብ በራሱ ትልቅ በረከት ነው፤ ወደ ፊት እንድንዘረጋ፣ እንድንቃትት፣ ፊቱን አንድንፈልግ ያደርገናል፡፡ የምር የሆነ መንፈሳዊ ራብ የሚመነጨው ደግሞ ያለንበትን ሁኔታ የእግዚአብሔር መንፈስ ሲያሳየንና ያለንበትን አዘቅት ስንጠላው ነው፡፡ መንፈሳዊ ራብ ይጐተጉተናል፣ አያስተኛንም፤ ቃሉ “የሠራተኛ ራብ ለርሱ ይሠራል አፉ ይጐተጉተዋል” (ምሳሌ 16፡26) ይላልና ፡፡ “ለርሱ ይሠራል” የሚለውን አስምሩልኝ፡፡ለማን? ለርሱ! አያስተኛውማ! ሳያገኝ አያሳርፈውማ! ለዚህ ነው መንፈሳዊ ራብ በራሱ የሚጓጓለት በረከት የሆነው፡፡


መንፈሳዊ ራብ ልክ እንደ ኤርምያስ ጌታን በትጋት እንድንፈልገው ያደርገናል፡፡ኤርምያስ ከብዙ ፍለጋ በኋላ ሕይወት የሚሰጠውን፣ መንፈስ የሆነውን፣ የጊዜውን ቃል ሲያገኝ እንዲህ ብሎ ተናገረ፦

“ቃልህ ተገኝቷል እኔም በልቼዋለሁ፤አቤቱ የሠራዊት ጌታ ሆይ በስምህ ተጠርቻለሁና ቃል ሐሤትና የልብ ደስታ ሆነኝ”
            (ኤርምያስ 15፡16)


ከዚህ ምንባብ በጥቂቱ እንደምንረዳው፣ ኤርምያስ ቃሉን በትጋትና በተራበ መንፈስ ሲፈልግ የቆየ ይመስላል፡፡ ባገኘውም ጊዜ ከነበረው ናፍቆት የተነሣ ለመብላት ፋታ ያገኘም አይመስልም፡፡ እናም እስከሚረካና በሐሤት እስኪጥለቀለቅ ድረስ በላው፡፡

ንጉሥ ዳዊት እውነተኛ መንፈሳዊ ራብ ያላቸውን ሰዎች እግዚአብሔር እንዴት እንደሚባርክ ሲገልጽ፦ “የተራበችን ነፍስ አጥግቦአልና፤ የተራቈተችንም ነፍስ በበረከት ሞልቶአልና” (መዝ 107፡9) ብሎ ተናግሯል፡፡ አዎ መንፈሳዊ ራብ የገባበት ሰው ሲቆፍር፣ ሲፈልግ፣ ሲቃትት ወዘተ ያድራል፤ ዕረፍት አይኖረውም ያንን ራብ ሳያስታግስ፡፡ ራቡ ጐትጓች ነውና፣ አያስተኛውምና፡፡

ይህን መንፈሳዊ ራብ የሚያቀጣጥሉ ሦስት የታወቁ ነገሮች አሉ፡፡እነሱም፡-


1⃣የእግዚአብሔር ቃል አብዝቶ ማጥናትና ማሰላሰል

2⃣ደጋግሞ ለረጅም ጊዜ መጾም

3⃣በጌታ ፊት በውሳኔ መውደቅ


ጌታ እንደ ተስፋ ቃሉ መንፈሳዊን ነገር በሚራቡና በሚጠሙ ሰዎች ሕይወት፣ ከብዙ መሻት በኋላ ሲገለጥ አስደናቂ ነገር የሚሆነው፡፡ለዚህ ነው ሰፋ ካለ መንፈሳዊ መነቃቃት በፊት በቤተ ክርስትያን እርሱን የሚራቡና የሚጠሙ፣ እናም በጓዳ እሱን የሚሹና የሚፈልጉ ሰዎች አስቀድሞ የሚያስነሣው፡፡


አንድ ክርስትያን ይህ ራብ በውስጡ ለረጅም ጊዜ ከጠፋ፣ ለመውደቅ እየተንሸራተተ እንደ ሆነ ሊያስብ ይገባዋል፡፡

መንፈሳዊ ራቡ ልባችንን ባሰፋነው መጠን ያድጋል፡፡ አብዝተን እንድንቃትት ያደርገናል፡፡አብዝተን ስንጸልይ ደግሞ ጸሎቱ ሌላ ከፍ ያለ መንፈሳዊ ራብን ይወልዳል፡፡የሚመጣው መንፈሳዊ ራብ ደግሞ አብዝተን እንድንጸልይ ያደርገናል፡፡ወገኖቼ አንዱ አንዱን እየጨመረ ማብቂያ የሌለው አስደናቂ ነገር ውስጥ ነው የምንገባው፤ እኛ በሥጋዊ አካሄዶች መንፈስን እስካላጠፋን ድረስ፡፡


ጌታ ሆይ ከፍ ያለ አንተን የሚሻና የሚፈልግ ልብ ስጠን !  



ምንጭ:-Divine Wisdom4




ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
🔥117👍1
.       ──•◈•─────•◈•─
                          የዕለቱ ጥቅስ
        ──•◈•─────•◈•─
“ከእርሱ ዘንድ ካልሆነ ማን መብላትና መደሰት ይችላል?”
መክብብ 2፥25 (አዲሱ መ.ት)



ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
🥰91
Pilgrm's progress
Nigusse Denano
#መጻሕፍትን_በድምጽ

📔ርዕስ፦ የመናኝ ጉዞ
👤ጸሐፊ፦ ዮሐንስ ቡንያን
👉ክፍል-11

ይቀጥላል. . .


ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
ቅዱሳት መጻሕፍት
#በዓለ_ኀምሳ #ጰራቅሊጦስ የቀጠለ... የጉባኤ ኒቂያ ዘመን የኒቂያ ጉባኤ መነሻ ምክንያት የሆነው አርዮስ የተባለ የኑፋቄ መምህር ወልድ እና መንፈስ ቅዱስ ከእግዚአብሔር አብ ጋር በባሕርይ አንድ ያልሆኑ እና ፍጡራን ናቸው ብሎ በማስተማሩ ምክንያት ነው። በመጨረሻም ለአሪዮስ መንፈስ ቅዱስ በእግዚአብሔር ወልድ የተፈጠረ፣ በተፈጠረ አካል የተፈጠረ ፍጡር (የፍጡር ፍጡር) ነው። የአሪዮስ ኑፋቄያዊ አስተምህሮ…
#በዓለ_ኀምሳ
#ጰራቅሊጦስ

የቀጠለ...



የፕሮቴስታን ተሓድሶ ዘመን

የሮም ካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን በቅድመ ተሓድሶ ዘመን ከቅዱስ አውግስጢኖስ ሐሳብ ዞር በማለት የቶማስ አኳይናስን የሥነ መለኮት አስተምህሮ የቤተ ክርስቲያንቷ የእምነት አቋም ምሰሶ አድርጋ ይዛ ነበር። ይሁን እንጂ በፕሮቴስታንት ተሓድሶ ዘመን ቤተ ክርስቲያን በቅድመ ተሓድሶ ዘመን ተዘንግቶ ወደ ነበረው ወደ የቅዱስ አውግስጢኖስ ሐሳብ የተመለሰችበት ዘመን ነው። ሆኖም በፕሮቴስታንት የተሓድሶ ዘመን ቅዱሳት መጻሕፍትን አንብቦ መረዳት ላይ ከፍተኛ ትኩረት የተሰጠበት ዘመን ከመሆኑ የተነሣ፣ እንደ ማርቲን ሉተር ያሉት የፕሮቴስታንት የተሓድሶ አራማጆች፣ “አንድ ሰው በክርስቶስ የሚያምነው ቅዱሳት መጻሕፍትን አንብቦ መረዳት ሲችል ብቻ ነው” ብለው ያስተምሩና ለዚህ አስተምህሮ ከፍተኛ አጽንዖት ይሰጡ ስለ ነበር ሰዎችን በማዳን ሂደት ውስጥ መንፈስ ቅዱስ ያለው ሚና ምን እንደ ሆነ የተዘነጋ ይመስላል። ይሁን እንጂ ከተሓድሶ አራማጆች መካከል የሆነው ጆን ካልቪን በሮም ቤተ ክርስቲያን ውስጥ በቅድመ ተሓድሶ ዘመን ተዘንግቶ የነበረውን የቅዱስ አውግስጢኖስ አስተምህሮ፣ ማለትም መንፈስ ቅዱስ በሰዎች ድነት ውስጥ ያለውን ሚና እንደገና አነቃቅቷል።

የድኅረ ተሓድሶ ዘመን

በድኅረ ተሓድሶ ዘመን የመንፈስ ቅዱስ ኀይል ሰዎችን በማዳን ረገድ የሚያከናውናቸው ሁለት ነገሮች ጎልተው ወጥተዋል፤ እነዚህም የውሸት ብህትውና (False Mystcism) እና የውሸት አመክኑያዊነት (False Rationalism) ናቸው። ጆን ዊስሊ ከተሓድሶ ዘመን በኋላ በመንፈስ ቅዱስን አስተምህሮ ላይ ትልቅ ብርሃን የፈነጠቀው በዚህ ወቅት ነበር። ከዚያን ጊዜ ጀምሮ ቤተ ክርስቲያን ስለ መንፈስ ቅዱስ ይበልጥ መረዳት ጀመረች። ምንም እንኳ የጆን ዊስሊ ሥነ መለኮት ፍጹም ባይሆንም ቤተ ክርስቲያን ስለ መንፈስ ቅዱስ በደንብ መረዳት የጀመረችው ግን በእርሱ ዘመን መሆኑን መካድ አይቻልም።

መንፈስ ቅዱስ በዘመናችን

ከዚህ በላይ በተመለከትነው የቤተ ክርስቲያን ታሪክ ውስጥ ከመንፈስ ቅዱስ ጋር ተያያዥነት ያላቸው ኑፋቄዎች አብዛኞቹ በመንፈስ ቅዱስ ማንነት የሚያጠነጥኑ የአስተምህሮዊ ኑፋቄዎች ናቸው። ይሁን እንጂ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በኢትዮጵያ ውስጥ ከፍተኛ ትኩረት የሚሰጠው ለአስተምህሮ ሳይሆን ለክንዋኔ ሆኗል። በአተገባበርም ወቅት የሚፈጠሩ ስሕተቶች በብዛት በኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን ውስጥ ይስተዋላሉ። እነዚህን ስሕተቶች እንደ ኑፋቄ መመልከት አለብን ወይስ የለብንም? እነዚህ በአስተምህሮ ሊገሩ የሚችሉ ቀላል ስሕተቶች በመሆናቸው በኑፋቄ ጎራ ሊፈረጁ አይገባም የሚል
ሙግት ሊነሣ ይችላል። ይሁን እንጂ አንዳንድ ከመንፈስ ቅዱስ ጋር ከፍተኛ ቁርኝት ያላቸው የኢትዮጵያን ቤተ ክርስቲያን ልምምዶች ታሳቢ የሚያደርጉት ምንጫቸውን (አስተምህሯቸውን) በመሆኑ ልምምዶቹም የነፈቁ ናቸው ለማለት ያስደፍራል።



ምንጭ:- hintset.org



ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
9🔥1
.       ──•◈•─────•◈•─
                          የዕለቱ ጥቅስ
        ──•◈•─────•◈•─
“እነሆ፥ እግዚአብሔር የሚገሥጸው ሰው ምስጉን ነው፤ ስለዚህ ሁሉን የሚችለውን የአምላክን ተግሣጽ አትናቅ።”
ኢዮብ 5፥17



ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
10
Pilgrm's progress
Nigusse Denano
#መጻሕፍትን_በድምጽ

📔ርዕስ፦ የመናኝ ጉዞ
👤ጸሐፊ፦ ዮሐንስ ቡንያን
👉ክፍል-12

ይቀጥላል. . .


ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
የእግዚአብሔርን ፀጋ የምንጥልባቸው አራቱ መንገዶች


የእግዚአብሄርን ፀጋ የምናጣበት ሃይል አልባ የሚያደርጉን አራቱ መንገዶች

1. ትህትናን መጣል  

ሰው ትህትናን ከጣለ የጊዜ ጉዳይ ነው እንጂ እንደሚወድቅ ምንም ጥርጥር የለውም፡፡ ሰው እግዚአብሄር ከሰጠው ደረጃ በላይ ራሱን ከፍ አድርጎ ሲያይ ከእግዚአብሄር ጋር ይተላለፋል፡፡ እግዚአብሄር ፀጋን መስጠትና ማንሳት ከፍ ማድረግ እየፈለገ በራሱ ነገሮችን ማደርግ እንደሚችል የሚያስበውን ትእቢተኛን ሰው ግን ከመቃወም ውጭ ምንም ሊያደርገው አይችልም፡፡  

“ነገር ግን ጸጋን አብልጦ ይሰጣል፤ ስለዚህ፦ እግዚአብሔር ትዕቢተኞችን ይቃወማል፥ ለትሑታን ግን ጸጋን ይሰጣል ይላል።”
ያዕቆብ 4፥6

2. እውቀትን መጣል

ሰው ከመሬት ተነስቶ አውቆ የጨረሰ ከመሰለው በህይወቱ ማደግና መለወጥ አቁሟል ማለት ነው፡፡ ይህ ሰው ለአዲስ ተግዳሮት በእውቀት ራሱን ካላስታጠቀ መውደቁ አይቀሬ ነው፡፡ ይህ ሰው ያወቀና የጨረሰ ከመሰለው እጅግ አሰቃቂ ነው፡፡

"ለጣዖት ስለ ተሠዋ ሥጋም፥ ሁላችን እውቀት እንዳለን እናውቃለን። እውቀት ያስታብያል ፍቅር ግን ያንጻል። ማንም አንዳች የሚያውቅ ቢመስለው ሊያውቅ እንደሚገባው ገና አላወቀም፤" (1ኛ ቆሮ. 8፡1-2)

“ሕዝቤ እውቀት ከማጣቱ የተነሣ ጠፍቶአል፤ አንተም እውቀትን ጠልተሃልና እኔ ካህን እንዳትሆነኝ እጠላሃለሁ፤ የአምላክህንም ሕግ ረስተሃልና እኔ ደግሞ ልጆችህን እረሳለሁ።”
ሆሴዕ 4፥6

"በእግዚአብሔርና በጌታችን በኢየሱስ እውቀት ጸጋና ሰላም ይብዛላችሁ።"( 2ኛ ጴጥ. 1፥2)

3. እምነትን መጣል

ሰው በእግዚአብሄር ላይ መደገፍን ትቶ በራሱ ስራ ላይ ሲደገፍ ከእግዚአብሄር ፀጋ ይጎድላል፡፡ ሰው ለመዳንም ሆነ ከዳነ በኋላ ለመቀደስ ፣ ለእግዚአብሄር መንግስት ለመስራትና እግዚአብሄርን ለማስደሰት በራሱ ጉልበትና ቅልጥፍና ላይ ሲደገፍ ከእግዚአብሄር ፀጋ ይጎድላል፡፡

"በሕግ ልትጸድቁ የምትፈልጉ ከክርስቶስ ተለይታችሁ ከጸጋው ወድቃችኋል።" (ገላ. 5፥4)

4. ምስጋናን መጣል

ሰው ምንም ከማይወጣለት መልካም አምላክ ጋር እየኖረ ካጉረመረመና ማመስገን ካቃተው ከእግዚአብሄር ፀጋ ይጎድላል፡፡ ሰው በእግዚአብሄር አሰራር ላይ አቃቂር ማውጣት ከቻለ የሆነ የሳተው ነገር አለ ማለት ነው፡፡ ሰው ከእግዚአብሄር በላይ የሚያውቅ ከመሰለው የሆነ የተዛባ ነገር አለ ማለት ነው፡፡ ሰው በእግዚአብሄር አሰራር ካልታመነ ከእግዚአብሄር ጋር በየዋህነት መኖር ፣ ራሱን መስጠት ፣ ለእግዚአብሄር በየዋህነት መስራትና ፍሬያማ መሆን ያቅተዋል፡፡   

"አንድ መክሊትም የተቀበለው ደግሞ ቀርቦ፦ ጌታ ሆይ፥ካልዘራህባት የምታጭድ ካልበተንህባትም የምትሰበስብ ጨካኝ ሰው መሆንህን አውቃለሁ፤ ፈራሁም ሄጄም መክሊትህን በምድር ቀበርሁት፤ እነሆ፥ መክሊትህ አለህ አለ።"(ማቴ. 25፥24-25)

"ከእነርሱም አንዳንዶቹ እንዳንጎራጎሩ በሚያጠፋውም እንደጠፉ አታንጐርጕሩ።" (1ኛ ቆሮ. 10፥10)


ምንጭ:- አብይ ዋቁማ



ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
8🙏4👍2🔥2
ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
5