Audio
❤2
. ──•◈•─────•◈•─
የዕለቱ ጥቅስ
──•◈•─────•◈•─
“ሁላችን እንሞታለን፥ በምድርም ላይ እንደ ፈሰሰና እንደማይመለስ ውኃ ነን፤ እግዚአብሔርም የነፍስን ጥፋት አይወድድም፥ ነገር ግን የተጣለ ሰው ፈጽሞ እንዳይጠፋ በምክሩ ያስባል።”
2ኛ ሳሙኤል 14፥14
ወደ ቻናሉ ለመ🀄️ላ🀄️ል፦ @Holy_scriptures

🥰6❤5👍2
#በዓለ_ኀምሳ
“ድንገት እንደሚነጥቅ ዓውሎ ነፋስ ከሰማይ ድምፅ መጣ፥ ተቀምጠው የነበሩበትንም ቤት ሁሉ ሞላው።”
ሐዋርያት 2፥2
ወደ ቻናሉ ለመ🀄️ላ🀄️ል፦ @Holy_scriptures
“ድንገት እንደሚነጥቅ ዓውሎ ነፋስ ከሰማይ ድምፅ መጣ፥ ተቀምጠው የነበሩበትንም ቤት ሁሉ ሞላው።”
ሐዋርያት 2፥2
ወደ ቻናሉ ለመ🀄️ላ🀄️ል፦ @Holy_scriptures
🔥7❤2
#እራሳችንን_እንመርምር
ከመንፈስ ቅዱስ ጋር ያለን ኅብረት እንዴት ነው? የሰላም? የማሳዘን? የማስመረር? እስቲ እራሳችንን እንመርምር
“እነርሱ ግን ዐመፁ ቅዱስ መንፈሱንም አስመረሩ፤ ስለዚህ ተመልሶ ጠላት ሆናቸው፥ እርሱም ተዋጋቸው።”
ኢሳይያስ 63፥10
“ለቤዛም ቀን የታተማችሁበትን ቅዱሱን የእግዚአብሔርን መንፈስ አታሳዝኑ።”
ኤፌሶን 4፥30

❤13🙏2👍1
. ──•◈•─────•◈•─
የዕለቱ ጥቅስ
──•◈•─────•◈•─
“መንፈስን አታጥፉ፤” (1ኛ ተሰሎንቄ 5፥19)
ወደ ቻናሉ ለመ🀄️ላ🀄️ል፦ @Holy_scriptures
የዕለቱ ጥቅስ
──•◈•─────•◈•─
“መንፈስን አታጥፉ፤” (1ኛ ተሰሎንቄ 5፥19)
ወደ ቻናሉ ለመ🀄️ላ🀄️ል፦ @Holy_scriptures
❤7
#
ምንጭ፦ lsj.gr/wiki/paracletus
ወደ ቻናሉ ለመ🀄️ላ🀄️ል፦ @Holy_scriptures
ጰራቅሊጦስ
ዛሬው ቀን መንፈስ ቅዱስ የወረደበት በዓለ ኀምሳ ነው። በቅዱሳት መጸሕፍት መንፈስ ቅዱስ ጰራቅሊጦስ ተብሎ ተገልጿል። ጰራቅሊጦስ (ግሪክ፡ παράκλητος፣ ላቲን፡ ጰራቅሊጦስ) ጠበቃ ወይም ረዳት ማለት ነው። በክርስትና ውስጥ፣ “ጰራቅሊጦስ” የሚለው ቃል በአብዛኛው የሚያመለክተው መንፈስ ቅዱስን ነው። ጰራቅሊጦስ የመጣው ከኮይኔ የግሪክ ቃል ነው παράκλητος (paráklētos)። ይህ ስያሜ የሁለት ጥምር ቃል ውህደት ነው። “ፓራ” (በጎን/ጎን) እና “ካሌይን” ("to call" ወይም ለመጥራት)። በመጀመሪያ በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ በዮሐንስ 14፥16 ይገኛል። በአጠቃላይ በአዲስ ኪዳን 5 ጊዜ የተጠቀሰ ሲሆን 4 ጊዜ በዮሐንስ ወንጌል(14፥16፤ 14፥26፤ 15፥26፤ 16፥7) አንድ ጊዜ ደግሞ በ1ኛ ዮሐንስ መልእክት (2፥1) ውስጥ ይገኛል። በ1ኛ ዮሐንስ ያለው ቃል የሚናገረው ስለጌታችን እና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ነው።ምንጭ፦ lsj.gr/wiki/paracletus
ወደ ቻናሉ ለመ🀄️ላ🀄️ል፦ @Holy_scriptures
❤11
. ──•◈•─────•◈•─
የዕለቱ ጥቅስ
──•◈•─────•◈•─
“ደግሞም ያተመን የመንፈሱንም መያዣ በልባችን የሰጠን እርሱ ነው።”
2ኛ ቆሮ 1፥22

❤9🔥2
የሉቃስ ወንጌል መክፈቻ.pdf
5.5 MB
❤4❤🔥3
. ──•◈•─────•◈•─
የዕለቱ ጥቅስ
──•◈•─────•◈•─
“ይህ ሕዝብ ወይም ነቢይ ወይም ካህን፦ የእግዚአብሔር ሸክም ምንድር ነው? ብሎ ቢጠይቅህ፥ አንተ፦ ሸክሙ እናንተ ናችሁ፥ እጥላችሁማለህ፥ ይላል እግዚአብሔር ትላቸዋለህ።”
ኤርምያስ 23፥33
ወደ ቻናሉ ለመ🀄️ላ🀄️ል፦ @Holy_scriptures
የዕለቱ ጥቅስ
──•◈•─────•◈•─
“ይህ ሕዝብ ወይም ነቢይ ወይም ካህን፦ የእግዚአብሔር ሸክም ምንድር ነው? ብሎ ቢጠይቅህ፥ አንተ፦ ሸክሙ እናንተ ናችሁ፥ እጥላችሁማለህ፥ ይላል እግዚአብሔር ትላቸዋለህ።”
ኤርምያስ 23፥33
ወደ ቻናሉ ለመ🀄️ላ🀄️ል፦ @Holy_scriptures
👍2👏1🙏1
ርኅሩኅ ሁን.pdf
5.4 MB
👉ርዕስ፦ ርኅሩኅ ሁን
ሉቃስ ምዕራፍ 1-13
አዳኙን ወደ መምሰል በበለጠ እንድናድግ የቀረበ ጥሪ
✍️ጸሐፊ፦ ዋረን ደብልዩ ዌርዝቢ
🗣ትርጉም፦ ግርማዊ
✏️እርማት፦ ዓለማየሁ ማሞ
ወደ ቻናሉ ለመ🀄️ላ🀄️ል፦ @Holy_scriptures
ሉቃስ ምዕራፍ 1-13
አዳኙን ወደ መምሰል በበለጠ እንድናድግ የቀረበ ጥሪ
✍️ጸሐፊ፦ ዋረን ደብልዩ ዌርዝቢ
🗣ትርጉም፦ ግርማዊ
✏️እርማት፦ ዓለማየሁ ማሞ
ወደ ቻናሉ ለመ🀄️ላ🀄️ል፦ @Holy_scriptures
❤5🔥1
የበረታህ ሁን.pdf
4.8 MB
👉ርዕስ፦ የበረታህ ሁን
ሉቃስ ምዕራፍ 14-24
የክርስቶስን ምሳሌነት ተከተል
✍️ጸሐፊ፦ ዋረን ደብልዩ ዌርዝቢ
🗣ትርጉም፦ ግርማዊ
✏️እርማት፦ ዓለማየሁ ማሞ
ወደ ቻናሉ ለመ🀄️ላ🀄️ል፦ @Holy_scriptures
ሉቃስ ምዕራፍ 14-24
የክርስቶስን ምሳሌነት ተከተል
✍️ጸሐፊ፦ ዋረን ደብልዩ ዌርዝቢ
🗣ትርጉም፦ ግርማዊ
✏️እርማት፦ ዓለማየሁ ማሞ
ወደ ቻናሉ ለመ🀄️ላ🀄️ል፦ @Holy_scriptures
👍7❤4🔥1
. ──•◈•─────•◈•─
የዕለቱ ጥቅስ
──•◈•─────•◈•─
“አባቶችህን ወድዶአልና ከእነርሱ በኋላ ዘራቸውን መረጠ፥ ዛሬ እንደ ሆነው ሁሉ ከአንተ የጸኑትን ታላላቆችን አሕዛብ በፊትህ እንዲያወጣ፥ አንተንም እንዲያገባህ፥ ምድራቸውንም ርስት አድርጎ እንዲሰጥህ፥ ከአንተ ጋር ሆኖ በታላቅ ኃይሉ ከግብፅ አወጣህ።”
ዘዳግም 4፥37-38

❤12
የመንፈሳዊ ራብ በረከት
መንፈሳዊ ራብ ጌታን መናፈቅን፣እሱን ለማግኘት መጓጓትን፣ወደ እሱ ለመጠጋት ማሰብን ወዘተ ያመለክታል፡፡
በግለሰብ ይሁን በወል ደረጃ መንፈሳዊ ራብና ጥማት ለእግዚአብሔር መለኮታዊ ጉብኝት እጅግ ወሳኝ ናቸው፡፡አውነተኛ የሆነ መንፈሳዊ ራብና ጥማት እግዚአብሔርን እንድንሻው፣ እንድንፈልገውና እንድንጠጋው ኃይል ይሆኑናል፡፡ ቃሉ “ጽድቅን የሚራቡና የሚጠሙ ብፁዓን ናቸው” (ማቴዎስ 5፡6) የሚለን ለዚህ ነው፡፡ “ብፁዓን” የሚለውን ቃል አምሊፋይድ መጽሐፍ ቅዱስ (Amplified Bible) ደስተኞች፣ በመንፈስ ባለጸጋ የሆኑ፣ የረኩ፣ የተባረኩ ወዘተ ብሎ ነው የሚገልጸው፡፡
ሐና መንፈሳዊ ራብ ያላቸው ሰዎች በጌታ ፊት ዋጋ ያላቸውና የማይረሱ እንደ ሆነ ስትናገር “ተርበው የነበሩ ከራብ አርፈዋል” (1 ሳሙኤል 2:5) ብላለች፤ አምላኳ የሚያረካ፣የሚያጠግብና የሚያሳርፍ መሆኑን በማወደስ፡፡
መንፈሳዊ ራብ በራሱ ትልቅ በረከት ነው፤ ወደ ፊት እንድንዘረጋ፣ እንድንቃትት፣ ፊቱን አንድንፈልግ ያደርገናል፡፡ የምር የሆነ መንፈሳዊ ራብ የሚመነጨው ደግሞ ያለንበትን ሁኔታ የእግዚአብሔር መንፈስ ሲያሳየንና ያለንበትን አዘቅት ስንጠላው ነው፡፡ መንፈሳዊ ራብ ይጐተጉተናል፣ አያስተኛንም፤ ቃሉ “የሠራተኛ ራብ ለርሱ ይሠራል አፉ ይጐተጉተዋል” (ምሳሌ 16፡26) ይላልና ፡፡ “ለርሱ ይሠራል” የሚለውን አስምሩልኝ፡፡ለማን? ለርሱ! አያስተኛውማ! ሳያገኝ አያሳርፈውማ! ለዚህ ነው መንፈሳዊ ራብ በራሱ የሚጓጓለት በረከት የሆነው፡፡
መንፈሳዊ ራብ ልክ እንደ ኤርምያስ ጌታን በትጋት እንድንፈልገው ያደርገናል፡፡ኤርምያስ ከብዙ ፍለጋ በኋላ ሕይወት የሚሰጠውን፣ መንፈስ የሆነውን፣ የጊዜውን ቃል ሲያገኝ እንዲህ ብሎ ተናገረ፦
“ቃልህ ተገኝቷል እኔም በልቼዋለሁ፤አቤቱ የሠራዊት ጌታ ሆይ በስምህ ተጠርቻለሁና ቃል ሐሤትና የልብ ደስታ ሆነኝ”
(ኤርምያስ 15፡16)
ከዚህ ምንባብ በጥቂቱ እንደምንረዳው፣ ኤርምያስ ቃሉን በትጋትና በተራበ መንፈስ ሲፈልግ የቆየ ይመስላል፡፡ ባገኘውም ጊዜ ከነበረው ናፍቆት የተነሣ ለመብላት ፋታ ያገኘም አይመስልም፡፡ እናም እስከሚረካና በሐሤት እስኪጥለቀለቅ ድረስ በላው፡፡
ንጉሥ ዳዊት እውነተኛ መንፈሳዊ ራብ ያላቸውን ሰዎች እግዚአብሔር እንዴት እንደሚባርክ ሲገልጽ፦ “የተራበችን ነፍስ አጥግቦአልና፤ የተራቈተችንም ነፍስ በበረከት ሞልቶአልና” (መዝ 107፡9) ብሎ ተናግሯል፡፡ አዎ መንፈሳዊ ራብ የገባበት ሰው ሲቆፍር፣ ሲፈልግ፣ ሲቃትት ወዘተ ያድራል፤ ዕረፍት አይኖረውም ያንን ራብ ሳያስታግስ፡፡ ራቡ ጐትጓች ነውና፣ አያስተኛውምና፡፡
ይህን መንፈሳዊ ራብ የሚያቀጣጥሉ ሦስት የታወቁ ነገሮች አሉ፡፡እነሱም፡-
1⃣የእግዚአብሔር ቃል አብዝቶ ማጥናትና ማሰላሰል
2⃣ደጋግሞ ለረጅም ጊዜ መጾም
3⃣በጌታ ፊት በውሳኔ መውደቅ
ጌታ እንደ ተስፋ ቃሉ መንፈሳዊን ነገር በሚራቡና በሚጠሙ ሰዎች ሕይወት፣ ከብዙ መሻት በኋላ ሲገለጥ አስደናቂ ነገር የሚሆነው፡፡ለዚህ ነው ሰፋ ካለ መንፈሳዊ መነቃቃት በፊት በቤተ ክርስትያን እርሱን የሚራቡና የሚጠሙ፣ እናም በጓዳ እሱን የሚሹና የሚፈልጉ ሰዎች አስቀድሞ የሚያስነሣው፡፡
አንድ ክርስትያን ይህ ራብ በውስጡ ለረጅም ጊዜ ከጠፋ፣ ለመውደቅ እየተንሸራተተ እንደ ሆነ ሊያስብ ይገባዋል፡፡
መንፈሳዊ ራቡ ልባችንን ባሰፋነው መጠን ያድጋል፡፡ አብዝተን እንድንቃትት ያደርገናል፡፡አብዝተን ስንጸልይ ደግሞ ጸሎቱ ሌላ ከፍ ያለ መንፈሳዊ ራብን ይወልዳል፡፡የሚመጣው መንፈሳዊ ራብ ደግሞ አብዝተን እንድንጸልይ ያደርገናል፡፡ወገኖቼ አንዱ አንዱን እየጨመረ ማብቂያ የሌለው አስደናቂ ነገር ውስጥ ነው የምንገባው፤ እኛ በሥጋዊ አካሄዶች መንፈስን እስካላጠፋን ድረስ፡፡
ጌታ ሆይ ከፍ ያለ አንተን የሚሻና የሚፈልግ ልብ ስጠን !
ምንጭ:-Divine Wisdom4

🔥11❤7👍1