. ──•◈•─────•◈•─
የዕለቱ ጥቅስ
──•◈•─────•◈•─
“ለፍጥረቱ የበኵራት ዓይነት እንድንሆን በእውነት ቃል አስቦ ወለደን።”
ያዕቆብ 1፥18
ወደ ቻናሉ ለመ🀄️ላ🀄️ል፦ @Holy_scriptures

❤5👍4
#የእግዚአብሔር_ቃል_ምን_ይላል?
ሕዝቅኤል 36
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
²⁴ ከአሕዛብም መካከል አወጣችኋለሁ ከየአገሩም ሁሉ እሰበስባችኋለሁ ወደ ገዛ ምድራችሁም አመጣችኋለሁ።
²⁵ ጥሩ ውኃንም እረጭባችኋለሁ እናንተም ትጠራላችሁ፥ ከርኵሰታችሁም ሁሉ ከጣዖቶቻችሁም ሁሉ አጠራችኋለሁ።
²⁶ አዲስም ልብ እሰጣችኋለሁ አዲስም መንፈስ በውስጣችሁ አኖራለሁ፤ የድንጋዩንም ልብ ከሥጋችሁ አወጣለሁ የሥጋንም ልብ እሰጣችኋለሁ።
²⁷ መንፈሴንም በውስጣችሁ አኖራለሁ በትእዛዜም አስሄዳችኋለሁ፥ ፍርዴንም ትጠብቃላችሁ ታደርጉትማላችሁ።
²⁸ ለአባቶቻችሁም በሰጠኋት ምድር ትኖራላችሁ፤ ሕዝብም ትሆኑኛላችሁ እኔም አምላክ እሆናችኋለሁ።
²⁹ ከርኵሰታችሁም ሁሉ አድናችኋለሁ፤ እህልንም እጠራዋለሁ አበዛውማለሁ ራብንም አላመጣባችሁም።
³⁰ ደግሞም የራብን ስድብ ከአሕዛብ ዘንድ እንዳትሸከሙ የዛፍን ፍሬና የእርሻውን ቡቃያ አበዛለሁ።
³¹ ክፉውን መንገዳችሁንና መልካም ያይደለውን ሥራችሁንም ታስባላችሁ፥ ስለ በደላችሁና ስለ ርኵሰታችሁም ራሳችሁን ትጸየፋላችሁ።
³² ይህን የሠራሁ ስለ እናንተ እንዳይደለ በእናንተ ዘንድ የታወቀ ይሁን፥ ይላል ጌታ እግዚአብሔር፤ የእስራኤል ቤት ሆይ፥ ስለ መንገዳችሁ እፈሩና ተዋረዱ።

❤11🙏6
. ──•◈•─────•◈•─
የዕለቱ ጥቅስ
──•◈•─────•◈•─
“በተጠማ ላይ ውኃን በደረቅም መሬት ላይ ፈሳሾችን አፈስሳለሁና፤ መንፈሴን በዘርህ ላይ በረከቴንም በልጆችህ ላይ አፈስሳለሁ፥”
ኢሳይያስ 44፥3

❤8🔥1
ቅዱሳት መጻሕፍት
ወደ ቻናሉ ለመ🀄️ላ🀄️ል፦ @Holy_scriptures
#ከተማ_ወይም_ቦታ_በቅዱሳት_መጻሕፍት
#ኢየሩሳሌም
ኢየሩሳሌም በቅዱሳት መጻሕፍት ውስጥ ማእከላዊ እና የተቀደሰ ቦታን ይዛለች፣ እግዚአብሔር ከሕዝቡ ጋር ለገባው ቃል ኪዳን ታሪካዊ፣ መንፈሳዊ እና ትንቢታዊ ማዕከል ነች። ከተማዋ በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ከ800 ጊዜ በላይ የተጠቀሰች ሲሆን በመጽሐፍ ቅዱሳዊ ታሪክ ውስጥ በጣም ወሳኝ ለሆኑት ለብዙ ክንውኖች መነሻ ሆና ታገለግላለች።
ሀ. አብርሃም እና መልከ ጼዴቅ (ዘፍጥረት 14፥18-20)
ኢየሩሳሌም የሳሌም የሚባለው ቦታ እንደሆነች ይታመናል፣ የሳሌም ንጉሥ መልከ ጼዴቅ፣ የልዑል እግዚአብሔር ካህን፣ አብራምን (አብርሃምን) የባረከበት ቦታ ነው። ይህ ገጠመኝ ለክርስቶስ ክህነት ጥላ ነበር።
ለ. የይስሐቅ መሥዋዕት (ዘፍጥረት 22፥1-19)
አብርሃም ይስሐቅን እንዲሠዋ በመታዘዙ የተፈተነበት የሞሪያ ተራራ፣ በተለምዶ በኢየሩሳሌም ካለው የቤተመቅደስ ተራራ እንደሆነ ይታመናል። ይህ ክንውን ታዛዥነትን የሚያመለክት ሲሆን በኢየሱስ ክርስቶስ የተፈጸመውን ምትክ መሥዋዕት የሚያቀርብ ምሳሌ ነው።
ሐ. ንጉሥ ዳዊትና የቃል ኪዳኑ ታቦት
ዳዊት ኢየሩሳሌምን ከዚያም ኢያቡስን ድል አድርጎ የእስራኤል ዋና ከተማ አደረጋት (2ሳሙ 5፥6-10)። በኋላም የቃል ኪዳኑን ታቦት ወደ ከተማይቱ አምጥቶ የሕዝቡ መንፈሳዊ ማዕከል አድርጎ አቆመው (2ሳሙ 6)።
መ. የሰለሞን ቤተ መቅደስ
የዳዊት ልጅ ንጉሥ ሰሎሞን በሞሪያ ተራራ ላይ የመጀመሪያውን ቤተመቅደስ በኢየሩሳሌም ሠራ (1 ነገሥት 6)። ለእስራኤላውያን ማዕከላዊ የአምልኮ ቦታ እና የእግዚአብሔር መገኘት ማደሪያ ሆነ።
ሠ. የኢየሱስ ስቅለት እና ትንሳኤ
ኢየሩሳሌም የኢየሱስ ስቅለት፣ የተቀበረበት እና የትንሣኤ መቼት ነበረች (ማቴዎስ 27-28)። እነዚህ በክርስቲያናዊ ሥነ-መለኮት ውስጥ በጣም አስፈላጊ የሆኑ ክስተቶች በኢየሩሳሌም እና በዙሪያዋ እንደተከሰቱ ይታመናል።
ረ. የኢየሱስ ዕርገት
በሐዋርያት ሥራ 1፥9-12 እንደተመዘገበው ኢየሱስ በኢየሩሳሌም አቅራቢያ ካለው ከደብረ ዘይት ተራራ ወደ ሰማይ ዐረገ።
ሰ. በዓለ ኀምሳ
በሐዋርያት ሥራ 2 ላይ እንደተገለጸው በበዓለ ሃምሳ ቀን መንፈስ ቅዱስ በሐዋርያት ላይ የወረደበት ማዕከላዊ ስፍራ ሆናለች። ይህ ወቅት በኢየሩሳሌም የክርስቶስ ቤተክርስቲያን መወለድ እና የአለም አቀፍ የወንጌል ስርጭት መጀመሪያ ነበር።
ሸ. የኢየሩሳሌም ትንቢታዊ ሚና
ኢየሩሳሌም የመጽሐፍ ቅዱሳዊ ትንቢቶች ማዕከል ነች። ኢየሱስ በክብር የሚመለስበት፣ እና በመጨረሻም ሰላም የሚመሰረትበት ቦታ እንደሆነ ተገልጿል (ዘካርያስ 14፥1–4፤ ራእይ 21፥2)።
ምንጭ፦
Elwell, W. A., & Beitzel, B. J. (1988). Baker Encyclopedia of the Bible (Vols. 1–2). Baker Book House.
Ferguson, E. (2003). Church History: Volume One: From Christ to the Pre-Reformation. Zondervan Academic.
Tenney, M. C. (1976). The Zondervan Pictorial Encyclopedia of the Bible (Vols. 1–5). Zondervan.

❤7👍3
Didache.pdf
1.4 MB
ርዕስ፦ DIDACHE (The Teaching of The Twelve Apostles)
ዲዳኬ፣ እንዲሁም የአሥራ ሁለቱ ሐዋርያት ትምህርት በመባልም ይታወቃል፣ ከ50 -120 ዓ.ም ድረስ ባለው ጊዜ የተጻፈ ሰነድ ነው። እሱም እንደ ቤተ ክርስቲያን መመሪያ ሆኖ ያገለግላል፣ በክርስቲያናዊ ሥነ ምግባር፣ ሥርዓቶች (እንደ ጥምቀት፣ ጾም፣ እና ቁርባን ያሉ) እና የቤተ ክርስቲያን አደረጃጀት ላይ መመሪያ ይሰጣል። መጽሐፉ “ሁለት መንገዶች” የሚለውን ትምህርት የሕይወት መንገድ እና የሞት መንገድ የአማኞችን የሥነ ምግባር ጠባይ ያስቀምጣል። እንዲሁም በክርስቲያን ማህበረሰብ ውስጥ ሐዋርያትን፣ ነቢያትን፣ እና መሪዎችን እንዴት መያዝ እንዳለባቸው መመሪያዎችን ይሰጣል። ዲዳኬ ከመጀመሪያዎቹ መጽሐፍ ቅዱሳዊ ያልሆኑ ክርስቲያናዊ ጽሑፎች አንዱ እና ስለ ቀደመችው ቤተክርስቲያን ልምምዶች ጠቃሚ ግንዛቤን የሚሰጥ አጠር ያለ መጽሐፍ ነው።

👍6❤4
. ──•◈•─────•◈•─
የዕለቱ ጥቅስ
──•◈•─────•◈•─
“እንደዚህ የጌታችንን የኢየሱስ ክርስቶስን መገለጥ ስትጠባበቁ አንድ የጸጋ ስጦታ እንኳ አይጎድልባችሁም፤”
1ኛ ቆሮንቶስ 1፥7

❤7
ቅዱሳት መጻሕፍት
#በዓለ_ኀምሳ #ጰራቅሊጦስ የቀጠለ... መንፈስ ቅዱስ በታሪክ ውስጥ በዘመናችን የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን ምስባኮች ላይ መንፈስ ቅዱስ የሚለው ስም መጥራት የተለመደ ቢሆንም፣ ሕዝበ ክርስትያኑ ስለ መንፈስ ቅዱስ ማንነት ጠንቅቆ ያውቃል ለማለት አስቸጋሪ ይመስላል። መንፈስ ቅዱስን አስመልክቶ ግልጽ አስተምህሮ ያለም አይመስልም። ለአንዳንዶች መንፈስ ቅዱስ ተአምራት ማድረጊያ ኀይል፣ እንዲሁም በጨርቅ…
#በዓለ_ኀምሳ
#ጰራቅሊጦስ
የቀጠለ...
የጉባኤ ኒቂያ ዘመን
የኒቂያ ጉባኤ መነሻ ምክንያት የሆነው አርዮስ የተባለ የኑፋቄ መምህር ወልድ እና መንፈስ ቅዱስ ከእግዚአብሔር አብ ጋር በባሕርይ አንድ ያልሆኑ እና ፍጡራን ናቸው ብሎ በማስተማሩ ምክንያት ነው። በመጨረሻም ለአሪዮስ መንፈስ ቅዱስ በእግዚአብሔር ወልድ የተፈጠረ፣ በተፈጠረ አካል የተፈጠረ ፍጡር (የፍጡር ፍጡር) ነው። የአሪዮስ ኑፋቄያዊ አስተምህሮ በጥንቷ ቤተ ክርስቲያን ተወግዟል።
ድኅረ ጉባኤ ኒቂያ ዘመን
ከኒቂያ ጉባኤ በኋላም መቅዶንዮስ (Macedonius) “መንፈስ ቅዱስ ፍጡር ብቻ ነው” የሚለውን የአርዮስን አስተምህሮ እርሱም ማስተማሩን ቀጥሏል። ለዚህም ድርጊቱ ምክንያት ተደርጎ ብዙ ጊዜ የሚነሣው በኒቂያ ጉባኤ ላይ ስለ መንፈስ ቅዱስ አካልነት በግልጽ ባለመቀመጡ ምክንያት ነው። ስለዚህም በ385 ዓ.ም. በቁስጥንጥንያ በተደረገው ጉባኤ ውሳኔ እስኪያገኝ ድረስ ስለ መንፈስ ቅዱስ ማንነት ከፍተኛ ክርክር ነበር። በዚህኛው ጉባኤ ሦስቱም የሥላሴ አካላት በባሕርይ አንድ መሆናቸው በግልጽ ተቀምጧል።
የመካከለኛው ዘመን
በመካከለኛው ዘመን በመንፈስ ቅዱስ አስተምህሮ ላይ የነበረው ውዝግብ፣ ʻመንፈስ ቅዱስ ከአብ ብቻ ወይስ ከአብ እና ከወልድ የሚሰርጽ ነው?ʼ የሚል ነበር። ይህም ቤተ ክርስቲያንን በሁለት ጎራ ከፍሏት ነበር። የምሥራቋ ቤተ ክርስቲያን መንፈስ ቅዱስ ከአብ ብቻ ይሰርጻል የሚለውን የጉባኤ ኒቅያ አቋም ስታጸና፣ መንፈስ ቅዱስ ከአብ እና ከወልድ ይሰርጻል የሚለውን የምዕራብ ቤተ ክርስቲያን አስተምህሮ በኑፋቄነት ስትፈርጀው ኖራለች። የምዕራቧ ቤተ ክርስቲያንም የምሥራቋን በዚህ አስተምህሮ ትኮንናለች። ይህ በምሥራቅ እና በምዕራብ አብያተ ክርስቲያናት መካከል የልዩነት ጅማሬ ተደርጎ ሊወሰድ ይችላል።
ቅድመ ተሓድሶ ዘመን
በቅድመ ተሓድሶ ዘመን መንፈስ ቅዱስ የሚሰርጸው ከማን ነው? የሚለው ውዝግብ ሰፍቶ እና ጎልብቶ፣ የምሥራቋን እና የምዕራቧን ቤተ ክርስቲያን በ1054 ለሁለት ወደ መክፈል አመራ። ይህ በቤተ ክርስቲያን ታሪክ ውስጥ መከሰቱ በክርስቶስ ቤተ ክርስቲያን ላይ ያደረሰው ጉዳት እስከ አሁን ድረስ ይሰማል።
ይቀጥላል...
ምንጭ:- hintset.org

❤7👍2
. ──•◈•─────•◈•─
የዕለቱ ጥቅስ
──•◈•─────•◈•─
“የሰው ልጅ ከመላእክቱ ጋር በአባቱ ክብር ይመጣ ዘንድ አለውና፤ ያን ጊዜም ለሁሉ እንደ ሥራው ያስረክበዋል።”
ማቴዎስ 16፥27

❤5👏1
Audio
❤2
. ──•◈•─────•◈•─
የዕለቱ ጥቅስ
──•◈•─────•◈•─
“ሁላችን እንሞታለን፥ በምድርም ላይ እንደ ፈሰሰና እንደማይመለስ ውኃ ነን፤ እግዚአብሔርም የነፍስን ጥፋት አይወድድም፥ ነገር ግን የተጣለ ሰው ፈጽሞ እንዳይጠፋ በምክሩ ያስባል።”
2ኛ ሳሙኤል 14፥14

🥰6❤5👍2
#በዓለ_ኀምሳ
“ድንገት እንደሚነጥቅ ዓውሎ ነፋስ ከሰማይ ድምፅ መጣ፥ ተቀምጠው የነበሩበትንም ቤት ሁሉ ሞላው።”
ሐዋርያት 2፥2
ወደ ቻናሉ ለመ🀄️ላ🀄️ል፦ @Holy_scriptures
“ድንገት እንደሚነጥቅ ዓውሎ ነፋስ ከሰማይ ድምፅ መጣ፥ ተቀምጠው የነበሩበትንም ቤት ሁሉ ሞላው።”
ሐዋርያት 2፥2
ወደ ቻናሉ ለመ🀄️ላ🀄️ል፦ @Holy_scriptures
🔥7❤2
#እራሳችንን_እንመርምር
ከመንፈስ ቅዱስ ጋር ያለን ኅብረት እንዴት ነው? የሰላም? የማሳዘን? የማስመረር? እስቲ እራሳችንን እንመርምር
“እነርሱ ግን ዐመፁ ቅዱስ መንፈሱንም አስመረሩ፤ ስለዚህ ተመልሶ ጠላት ሆናቸው፥ እርሱም ተዋጋቸው።”
ኢሳይያስ 63፥10
“ለቤዛም ቀን የታተማችሁበትን ቅዱሱን የእግዚአብሔርን መንፈስ አታሳዝኑ።”
ኤፌሶን 4፥30

❤13🙏2👍1
. ──•◈•─────•◈•─
የዕለቱ ጥቅስ
──•◈•─────•◈•─
“መንፈስን አታጥፉ፤” (1ኛ ተሰሎንቄ 5፥19)
ወደ ቻናሉ ለመ🀄️ላ🀄️ል፦ @Holy_scriptures
የዕለቱ ጥቅስ
──•◈•─────•◈•─
“መንፈስን አታጥፉ፤” (1ኛ ተሰሎንቄ 5፥19)
ወደ ቻናሉ ለመ🀄️ላ🀄️ል፦ @Holy_scriptures
❤7