ቅዱሳት መጻሕፍት
7.45K subscribers
1.36K photos
61 videos
332 files
802 links
በዚህ ቻናል

👉ቅዱሳት መጻሕፍት ይጠናሉ::
👉መጽሐፍ ቅዱሳዊ ትምህርቶች ይቀርባሉ::
👉 ለቅዱሳት መጽሐፍት ጥናት የሚያግዙ መጻሕፍት ይለቀቃሉ።

⭐️⭐️⭐️⭐️⭐️

@Holy_scriptures
Download Telegram
ቅዱሳት መጻሕፍት
ክርስቲያናዊ ዓቅብተ እምነት – CHRISTIAN APOLOGETICS ክፍል-1 መግቢያ “ዳሩ ግን ጌታን እርሱም ክርስቶስ በልባችሁ ቀድሱት። በእናንተ ስላለ ተስፋ ምክንያትን ለሚጠይቁዋችሁ ሁሉ መልስ ለመስጠት ዘወትር የተዘጋጃችሁ ሁኑ፥ ነገር ግን በየዋህነትና በፍርሃት ይሁን።” 1ጴጥ. 3፥15 የክርስቶስ ቤተ ክርስቲያን ያለ ተግዳሮት የኖረችበት ዘመን የለም፡፡ በየዘመናቱ የነበሩት…
ክርስቲያናዊ ዓቅብተ እምነት – CHRISTIAN APOLOGETICS



          ክፍል-2

1.2. የክርስቲያን ዓቅብተ እምነት ታሪክ

የክርስቲያን ዓቅብተ እምነት ታሪክ ከመጀመርያው ክፍለ ዘመን የሚጀምር ቢሆንም እንደ አንድ የጥናት ዘርፍ የጎለበተውና ወጥ የሆነ መልክ የያዘው ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ነው፡፡ ክርስቲያናዊው ዓቅብተ እምነት በተለያዩ የዕድገት ደረጃዎች ውስጥ አልፏል፡፡

ክርስትና በተጀመረበት ዘመንና ተከትለው በነበሩት ጥቂት ክፍለ ዘመናት መካከል ክርስቲያኖች በሮማ መንግሥት ከፍተኛ ስደት ይደርስባቸው ነበር፡፡ ይህንን ስደት ለመቀስቀስና ለማጽደቅ ተቃዋሚዎች የተለያዩ የሐሰት ክሶችን ይጠቀሙ ነበር፡፡ ኔሮ የተባለው የሮም ንጉሥ ክርስቲያኖች ላይ ስደት ለማስነሳት በ64 ዓ.ም. ለስድስት ተከታታይ ቀናት በመንደድ የሮምን ከተማ አብዛኛውን ክፍል ያወደመውን የእሳት አደጋ ያቀጣጠሉት ክርስቲያኖች እንደሆኑ በሐሰት እንደወነጀላቸው ታሲተስ የተባለ ሮማዊ ጸሐፌ ታሪክ ዘግቧል፡፡ የጌታን እራት በቀጥታ በመተርጎም ክርስቲያኖች የሰው ሥጋ እንደሚበሉም ተከሰው ነበር፡፡ እንዲሁም ክርስቲያኖች “ወንድምና እህት” በማለት እርስ በርሳቸው የመጠራራት ልማድ ስለነበራቸው ይህንንም በቀጥታ በመተርጎም የዝምድና ጋብቻ (incest) እንደሚፈጽሙ ተወርቶባቸዋል፡፡ የይሁዲ ኃይማኖት፣ ኖስቲዝምና የግሪክ ፍልስፍና የክርስትናን አስተምህሮ የሚገዳደሩ አስተሳሰቦችም ነበሩ፡፡ እነዚህን የመሳሰሉ ውንጀላዎችንና ስም ማጥፋቶችን እንዲሁም አስተምሕሯዊ ተግዳሮቶችን ለመከላከል የጥንት የቤተ ክርስቲያን አበው የተለያዩ ጽሑፎችን መጻፍ አስፈልጓቸው ነበር፡፡

በጥቅሉ ሲታይ የአበው ጽሑፎች ሦስት ዓላማዎችን ያነገቡ ነበሩ። እነርሱም፦

1⃣ክርስትናን ከሐሰት ክሶችና ውንጀላዎች መከላከል

2⃣የብሉይ ኪዳን ትንቢቶች ፍጻሜ ላይ በመመሥረት የክርስትና አስተምህሮ እውነት መሆኑን ማስረዳት

3⃣ክርስትና የግሪክ ፍልስፍና ላዕላይና ምልዓት መሆኑን ማስረዳት ናቸው፡፡

የኋለኞቹ ክርስቲያን ዓቃቤ እምነታውያን ሥራዎች የተለያዩ የክርስትና አስተምሕሮዎችን ከተቃዋሚዎች በመከላከልና ስለ እግዚአብሔር መኖር አመክንዮአዊ ማስረጃዎችን በማቅረብ ላይ ያተኮሩ ናቸው፡፡

1.2.1. የጥንት ቤተ ክርስቲያን አቃቤ እምነታውያን


በዓቃቤ እምነታዊ ሥራቸው ከሚታወቁ የጥንት ቤተ ክርስቲያን አበው መካከል ዮስጦስ ሰማዕት (100-165 ዓ.ም.) ይጠቀሳል፡፡ ይህ አባት ከፕሌቶ የፍልስፍና አስተምሕሮ ወደ ክርስትና የተለወጠ ነበር፡፡ “ከአይሁዳዊው ትሪፎ ጋር የተደረገ ውይይት” በሚለው ጽሑፉ ውስጥ ኢየሱስ አይሁድ ሲጠብቁት የነበሩት መሲህ መሆኑን ለማሳየት የብሉይ ኪዳንን ትንቢቶች እንደ ማስረጃ ተጠቅሟል፡፡ “አፖሎጂስ” በሚል ርዕስ በተጻፉት ሁለት ጽሑፎቹ ውስጥ ደግሞ ክርስትና ነጻነትን ማግኘት ይችል ዘንድ የተለያዩ የሐሰት ክሶችን ውድቅ በማድረግና ከግብረ ገብነት አንጻር ክርስትና የበላይነት ያለው እውነተኛ ፍልስፍና መሆኑን በማመልከት ተከራክሯል፡፡ ዮስጦስ ሰማዕት የክርስቶስን ማንነት በተመለከተ ይከተል የነበረው አስተምሕሮ መጠነኛ ችግር የነበረበት ቢሆንም የአዲስ ኪዳን ጽሑፎች ከተጻፉ በኋላ ከተነሱት አበው መካከል ለክርስቲያናዊው ዓቅብተ እምነት መሠረት የጣለ ሰው እንደነበር መናገር ይቻላል፡፡


ይቀጥላል...



ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
10👏1
ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
3
አዲሱ_መደበኛ_ትርጉም_ከማጥኛ_ጹሑፍ_ጋር.pdf
198.9 MB
📜ርዕስ፦ አዲሱ መደበኛ ትርጉም
ከማጥኛ ጽሑፍ ጋር
💾መጠን፦ 198.9MB



ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
👏76👍3
.       ──•◈•─────•◈•─
                          የዕለቱ ጥቅስ
        ──•◈•─────•◈•─
“ትክክለኛና ቀና የሆነውን በማድረግ የእግዚአብሔርን (ያህዌ) መንገድ ይጠብቁ ዘንድ ልጆቹንና ከእርሱ በኋላ ቤተ ሰቦቹን እንዲያዝ መርጬዋለሁ፤ ይኸውም እግዚአብሔር (ያህዌ) ለአብርሃም የሰጠው ተስፋ ሁሉ እንዲፈጸም ነው።”
ዘፍጥረት 18፥19 (አዲሱ መ.ት)



ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
7
Audio
#መጻሕፍትን_በድምጽ

📔ርዕስ፦ የመጽሐፍ ቅዱስ አስተምህሮ
👤ጸሐፊ፦ ዶ/ር ቻርልስ ሲ.ራይሪ
🗣ተርጓሚ፦ ሲሳይ ደሳለኝ
👉ክፍል-9 (የመጨረሻ ክፍል)


ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
የአማኝ ሕይወት በእድገት መቀጠል ሲገባው ለምን ወደ ኋላ ይላል?

በመንፈሳዊ ሕይወት ውስጥ ከማደግ ይልቅ ወደ ኋላ ማፈግፈግ ብዙ ጊዜ ይስተዋላል። ከእነዚህ ምክንያቶች ውስጥ ዛሬ አንዱን እንመለከታለን።

1. "ተንኰልን የሙጥኝ " ብሎ ሲይዝ

2. "ሊመለስም እንቢ" ሲል

“እንግዲህ ይህ የኢየሩሳሌም ሕዝብ ዘወትር ስለ ምን ወደ ኋላው ይመለሳል? ተንኰልን ይዞአል ሊመለስም እንቢ ብሎአል።”
(ኤርምያስ 8፥5)

“ታዲያ፣ ይህ ሕዝብ ለምን ፊቱን አዙሮ ወደ ኋላ ይሄዳል? ለምንስ ኢየሩሳሌም ዘወትር ወደ ኋላ ትመለሳለች? ተንኰልን የሙጥኝ ብለው ይዘዋል፤ ሊመለሱም ፈቃደኛ አይደሉም።”
ኤርምያስ 8፥5 (አዲሱ መ.ት)


"እንግዲህ ክፋትን ሁሉ ተንኰልንም ሁሉ ግብዝነትንም ቅንዓትንም ሐሜትንም ሁሉ አስወግዳችሁ፥ ጌታ ቸር መሆኑን ቀምሳችሁ እንደ ሆነ፥ ለመዳን በእርሱ እንድታድጉ አሁን እንደ ተወለዱ ሕፃናት ተንኰል የሌለበትን የቃልን ወተት ተመኙ።"
(1ኛ ጴጥሮስ 2፥1-3)

ለመሆኑ "ተንኮል" ማለት ምን ማለት ነው? እስቲ በዚህ ነገር በአሳብ መስጫው ላይ አሳብ ስጡበት፤ ተወያዩበትም።



ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
13👍3
.       ──•◈•─────•◈•─
                          የዕለቱ ጥቅስ
        ──•◈•─────•◈•─
“ጌታ ኢየሱስም ከእነርሱ ጋር ከተናገረ በኋላ ወደ ሰማይ ዐረገ በእግዚአብሔርም ቀኝ ተቀመጠ።”
ማርቆስ 16፥19



ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
9👍3
ዛሬ የጌታችን እና የመድኃኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስ ዕርገት የሚከበርበት ቀን ነው። ከትንሣኤ በኋላ 40 ቀን መሆኑ ነው። ምድራዊ ተልእኮውን ጨርሶ ወደ አብ ያረገበት የክብር ጊዜ ነው። ዕርገቱ የስንብት አይደለም፣ ነገር ግን የተስፋው ቃል ማለትም ስፍራ ሊያዘጋጅልን እንደሚሄድ (ዮሐ. 14፥2-3) እና መንፈስ ቅዱስ ኃይል እንዲሰጠንና እንዲመራን እንደሚልክ የተናገረበትም ነው። ዕርገቱ ክርስቶስ በክብር እንደሚነግሥ፣ ስለ እኛ እንደሚማልድ ያሳስበናል፣ እናም ዜግነታችን በሰማይ መሆኑን ያረጋግጥልናል። ደቀ መዛሙርቱ ቆመው ሰማዩን እየተመለከቱ ሳለ የመላእክት መልእክት አሁንም ያስተጋባል። “... ወደ ሰማይ እየተመለከታችሁ ስለ ምን ቆማችኋል?” (ሐዋርያት 1፥11) አዎ፣ በፍርሃት ቀና ብለን ብቻ ሳይሆን በተልእኮ ወደ ፊት እንሂድ እስከ ምድር ዳርቻ ድረስ ምስክሮቹ እንሁን!



ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
🔥104
ቅዱሳት መጻሕፍት
#በዓለ_ኀምሳ #ጰራቅሊጦስ የቀጠለ... ለ. መንፈስ ቅዱስ የእግዚአብሔርን መልእክት ለሕዝቡ ለመንገር ይሠራ ነበር፡፡ ለምሳሌ በምድረ በዳ እስራኤላውያንን ይመራ የነበረው መንፈስ ቅዱስ ነው (ነህ 9፥20)፡፡ የእስራኤል መዘምራን መዝሙራቸውን በዘመሩ ጊዜ፣ የዘመሩት በጌታ መንፈስ ነው (2ሳሙ 23፥2፤ ከሐሥ1፥16፣20)፡፡ እንደዚሁም ነቢያት ቃሉን ለሕዝቡ ለመንገር በእግዚአብሔር መንፈስ ይመሩ…
#በዓለ_ኀምሳ
#ጰራቅሊጦስ

የቀጠለ...


ሠ. መንፈስ ቅዱስ አንድን ሰው ቀጥተኛ በሆነው የጽድቅ አኗኗር ለመምራት ፍላጎት እንዳለው በብሉይ ኪዳን ላይ ተስተውሎአል፤

ከዚህ ሐሳብ ጋር በተያያዘ መልኩም ዳዊት በአንዳንድ መዝሙሮቹ ላይ መስክሮአል (መዝ 51፥10-13፣ 143፥10)። የእግዚአብሔር ሕዝብ እግዚአብሔርን በመስማት ፈንታ የግላቸውን መንገድ የሚከተሉ ከሆነ፣ በትክክል ሲታይ የመንፈስ ቅዱስን መንገድ አንከተልም እያሉ ነው (ዘፍ 16፥2)፡፡ በእግዚአብሔር መንፈስ እየተመሩ ያልኖሩት፣ የእግዚአብሔርን ፍርድ በተለያየ መልኩ ሳይቀበሉ አልቀረም (ዘኊ 14፥29፤ ዘዳ1፥26)፡፡

ረ. በብሉይ ኪዳን ዘመን፣ መንፈስ ቅዱስ ለአገልግሎት ለማብቃት ወይም ትንቢት እንዲናገሩ ለማድረግ የመጣው በጣት በሚቈጠሩ ሰዎች ላይ መሆኑን ማስተዋል ተገቢ ነው

ለእስራኤል ሕዝብ ሁሉ የሆነ የመንፈስ ቅዱስ መውረድ አልነበረም (ከኢዮኤል 2፥28-29፤ ከሐሥ 2፥4፡16-18)፤ እስከ ታላቁ የጰንጠቆስጤ ዕለት ድረስ፣ ሰፋ ባለ መልኩ የመንፈስ ቅዱስ መውረድ አልተከሠተም ነበር (ሐሥ 2)።

2. በአዲስ ኪዳን መንፈስ ቅዱስ ራሱን የገለጠበት ሥራ፡፡

ሀ. መንፈስ ቅዱስ ስለ በደል የሚወቅስ (ዮሐ 16፥7-8)፣

ስለ ኢየሱስ ያለውን እውነት የሚገልጥ (ዮሐ 14፥16፡26)፣ አዲስ ልደትን የሚሰጥ (ዮሐ 3፥3-6)፣ ወደ ክርስቶስ አካል ውስጥ እንድንገባ የሚያደርግ የድነት ኀይል ነው። በክርስቶስ አምነን ስንለወጥ መንፈስ ቅዱስን እንቀበላለን (ዮሐ 3፥3-6፤ 20፥22)፤ የመለኮታዊ ባሕርይ ተካፋይም እንሆናለን (2ጴጥ 1፥4)።

ለ. መንፈስ ቅዱስ መቀደስን የሚያመጣ ኀይል ነው፡፡

በክርስቶስ አምነው በሚለወጡበት ጊዜ አማኞች የመንፈስ ቅዱስ ማደሪያ ይሆናሉ፤ ከዚያም በእርሱ የመቀደስ ተግባር ሥር ይሆናሉ (ሮሜ 8፥9፤ 1ቆሮ 6፡19)፡፡ መንፈስ ቅዱስ በውስጣችን ሲኖር፣ የሚሠራውን ሥራ ልብ በሉ፡፡ እርሱ ይቀድሰናል፣ ይኸውም ያነጻናል፤ ከኀጢአት ባርነት ነጻ በማውጣትም (ሮሜ 8፥24፣ ገላ 5፥16-17፤ 2ተሰ 2፥13) በቅዱስ ኑሮ እንድንመራ ያደፋፍረናል ማለት ነው፡፡ የእግዚአብሔር ልጆች እንደ ሆንን ይነግረናል (ሮሜ 8፥6)፣ እግዚአብሔርን በምናመልክበት ጊዜ (ሐሥ 10፥46) እና በጸሎት ሕይወታችን ያግዘናል፤ ወደ እግዚአብሔርም በምንጮኸበት ጊዜ ይማልድልናል (ሮሜ 8፥26-27)። ክርስቶስን እናከብር ዘንድ የክርስቶስ የሆኑትን የጸጋ ባሕርያት በውስጣችን ይፈጥርልናል (ገላ 5፥22-23፤ 1ጴጥ 1፥2)። እርሱ ኢየሱስን ለእኛ በመግለጥ፣ ከኢየሱስ ጋር የቀረበ ኅብረትና አንድነት እንዲኖረን በማድረግ (ዮሐ 14፥16-18፤ 16፥14)፡፡ ወደ እውነት ሁሉ የሚመራን መለኮታዊ አስተማሪያችን ነው (ዮሐ 16፥13፤ 14፥26፤ 1ቆሮ 2፥9-16)፡፡ ባለማቋረጥ የእግዚአብሔርን ፍቅር ወደ እኛ ያስተላልፋል (ሮሜ 5፥5)፡ ደስታን መጽናናትንና ርዳታን ይሰጠናል (ዮሐ 14፥16፤ 1ተሰ 1፥6)፡፡


ይቀጥላል...



ምንጭ፦ ምሉእ ሕይወት፤ ገጽ 1314-1315፣ 1679-80




ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
6👍4
.       ──•◈•─────•◈•─
                          የዕለቱ ጥቅስ
        ──•◈•─────•◈•─
“የእግዚአብሔር ፈቃድ እርሱም በጎና ደስ የሚያሰኝ ፍጹምም የሆነው ነገር ምን እንደ ሆነ ፈትናችሁ ታውቁ ዘንድ በልባችሁ መታደስ ተለወጡ እንጂ ይህን ዓለም አትምሰሉ።”
ሮሜ 12፥2



ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
12
ቅዱሳት መጻሕፍት
#በዓለ_ኀምሳ #ጰራቅሊጦስ የቀጠለ... ሠ. መንፈስ ቅዱስ አንድን ሰው ቀጥተኛ በሆነው የጽድቅ አኗኗር ለመምራት ፍላጎት እንዳለው በብሉይ ኪዳን ላይ ተስተውሎአል፤ ከዚህ ሐሳብ ጋር በተያያዘ መልኩም ዳዊት በአንዳንድ መዝሙሮቹ ላይ መስክሮአል (መዝ 51፥10-13፣ 143፥10)። የእግዚአብሔር ሕዝብ እግዚአብሔርን በመስማት ፈንታ የግላቸውን መንገድ የሚከተሉ ከሆነ፣ በትክክል ሲታይ የመንፈስ ቅዱስን…
#በዓለ_ኀምሳ
#ጰራቅሊጦስ

የቀጠለ...



ሐ. መንፈስ ቅዱስ አማኞችን ለአገልግሎትና ለምስክርነት የሚያስታጥቅ የአገልግሎት ብርትት ነው፡፡

ይህ የመንፈስ ቅዱስ ሥራ በመንፈስ ቅዱስ ከመጠመቅ ወይም በመንፈስ ቅዱስ ከመሞላት ጋር የተያያዘ ነው፡፡ በመንፈስ ቅዱስ ስንጠመቅ፣ ለክርስቶስ ለመመስከር እንዲሁም በቤተ ክርስቲያንና በዓለም ፊት ውጤታማ ሥራ ለመሥራት የሚያስችለንን ኀይል እንቀበላለን (ሐሥ 1፥8)። የእግዚአብሔርን ቃል እንድንናገርና (ሐሥ 1፥8፡4፥31) ታምራትን እንድናደርግ (ሐሥ 2፥43፣ 3፥2-8፤ 5፥15፤ 6፥8፡ 10፥38) የሚያስችለንን በደቀ መዛሙርትና (ሐ 2፥4፤ 1፥5 ይመ) በክርስቶስ (ዮሐ 1፥32-33) ላይ የወረደውን ዐይነት መለኮታዊ ቅባት እንቀበላለን፡፡ በዚህ ዘመን ያሉ ክርስቲያኖች በሙሉ በመንፈስ ቅዱስ እንዲጠመቁ ማድረግ እግዚአብሔር አስቀድሞ ያሰበው ዐላማ ነው (ሐሥ 2፥39):: በአገልግሎት ረገድ መንፈስ ቅዱስ በቤተ ክርስቲያን ያሉ ግለሰብ አባላት ቤተ ክርስቲያንን ለማነጽ ወይም ለማጠንከር የሚያስችሉአቸውን የመንፈስ ቅዱስ ስጦታዎችን ይሰጣቸዋል (1ቆሮ 12-14)፡፡ እነዚህ ስጦታዎች መንፈስ ቅዱስ በግለሰብ አማኞች ሕይወት ውስጥ የሚገለጥባቸው ምልክቶች ሲሆኑ፣ የክርስቶስ ሀልዎት፣ ፍቅር፣ እውነትና ጻድቅ መለኪያዎች ለጋራ ጥቅም (1ቆሮ 12፥7-10) በአማኞች ኅብረት ውስጥ እውን እንዲሆኑ የሚያደርጉ ናቸው::

መ. መንፈስ ቅዱስ አማኞች በአንዱ በክርስቶስ አካል ውስጥ እንዲተባበሩ የሚያደርግ ኀይል ነው (1ቆሮ 12፥13)፤

እርሱ በቤተ ክርስቲያን ውስጥ ይኖራል (1ቆሮ 3፥16)፤ ቤተ ክርስቲያንን ይገነባል (ኤፌ 2፥22)፣ የቤተ ክርስቲያንን አምልኮ ያንቀሳቅሳል (ፊል 3፥3 ) ፤ ተልእኮዋን ይመራል (ሐሥ 13፥2፡4)፡ ሠራተኞቿን ይሾማል (ሐሥ 20፥28)፣ ለቤተ ክርስቲያን ስጦታን ይሰጣል (ቆሮ 12፥1-11)፤ ሰባኪዎቿን ይቀባል (ሐሥ 2፥4፤ 1ቆሮ 2፥4)፡ ወንጌልን ይጠብቃል (2ጢሞ 1፥14)፤ የጽድቅንም ሕይወት እንዲስፋፋ ያደርጋል (ዮሐ 16፥8፡ዘ፥1ቆሮ 3፥16፤ 6፥18-20)፡፡

ሠ. የመንፈስ ቅዱስ ልዩ ልዩ አገልግሎቶች እርስ በርስ የሚደጋገፉ እንጂ የሚቃረኑ አይደሉም፡፡

እንደዚሁም የመንፈስ ቅዱስ ሥራ ልዩ ልዩ ገጽታዎች እርስ በርስ የተያያዙ ናቸው፤ ፈጽሞም ሊለያዩ አይችሉም፡፡ ስለዚህ

ሀ. በክርስቶስ ያለውን የአዲስ ሕይወት ሙላትን፣

ለ. ጽድቅን የኑሮ መርሕ ማድረግን፣

ሐ) ለጌታችን የመመስከር ኀይል መቀበልን ወይም

መ. በአካሉ ውስጥ ያለንን አንድነት በተናጥል መለማመድ አንችልም፡፡

ለምሳሌ የመንፈስ ቅዱስ ጥምቀት፣ መንፈስ ቅዱስ ጽድቅን በውስጣችን ለማፍራት ከሚሠራው ሥራ እንዲሁም ወደ መጽሐፍ ቅዱሳዊ እውነት በመምራትና ራሳችንን እንድንሰጥ በማድረግ ከሚፈጽመው ሥራ ተለይቶ በዘላቂነት ሊጠበቅ አይችልም።


ይቀጥላል ...


ምንጭ፦ ምሉእ ሕይወት፤ ገጽ 1679-1680




ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
6👏1
በቅዱሳት መጻሕፍት ውስጥ በሐዋርያው ጳውሎስ የመጀመሪያው የወንጌል ጉዞ (ሐዋ. 13፥1-14፥28) ወንጌል የሰሙ ከተሞች የትኞቹ ናቸው?
Anonymous Quiz
26%
ሀ. ቆጵሮስ
12%
ለ. ተሰሎንቄ
19%
ሐ. ኤፌሶን
15%
መ. መቄዶንያ
27%
ሠ. ሁሉም
👍61
.       ──•◈•─────•◈•─
                          የዕለቱ ጥቅስ
        ──•◈•─────•◈•─
“አሁን ግን እናንተ በፊት ርቃችሁ የነበራችሁ በክርስቶስ ኢየሱስ ሆናችሁ በክርስቶስ ደም ቀርባችኋል።”
ኤፌሶን 2፥13



ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
14
#መጻሕፍትን_በድምጽ

በቀጣይ

📔ርዕስ፦ የመናኝ ጉዞ
👤ጸሐፊ፦ ዮሐንስ ቡንያን


ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
8🔥1
ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
👏42
ምሉእ ሕይወት.pdf
108.8 MB
ምሉእ ሕይወት መጽሐፍ ቅዱስ
አዲሱ መደበኛ ትርጉም
ዋና አርታኢ፦ DONALD C. STAMPS
ተባባሪ አርታኢ፦ J. WESLEY ADAMS

LIFE PUBLISHERS INTERNATIONAL


ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
23🥰3
#እራሳችንን_እንመርምር


አማኝ ክርስቲያን ስንሆን በተለይ በእግዚአብሔር ቤት ውስጥ በቤተክርስቲያን ስንኖር እና ስናገለግል ከሰው የምናገኘውን ጥቅም የምናሰላና ከሰው እጅ ያለውን ለመንጠቅ የምንቋምጥ ከሆነ ምንኛ ምስኪን ነን? እንዴትስ መልእክታችን የተዛባ ነው?


“ሙሴም እጅግ ተቈጣ፥ እግዚአብሔርንም፦ ወደ ቍርባናቸው አትመልከት፤ እኔ ከእነርሱ አንድ አህያ ስንኳ አልወሰድሁም፥ ከእነርሱም አንድ ሰው አልበደልሁም አለው።”
ዘኍልቁ 16፥15

“እነሆኝ በእግዚአብሔርና እርሱ በቀባው ፊት መስክሩብኝ የማንን በሬ ወሰድሁ? የማንንስ አህያ ወሰድሁ? ማንንስ ሸነገልሁ? በማንስ ላይ ግፍ አደረግሁ? ዓይኖቼንስ ለማሳወር ከማን ጋር እጅ ጉቦ ተቀበልሁ? እኔም እመልስላችኋለሁ።”
1ኛ ሳሙኤል 12፥3

“ከማንም ብር ወይም ወርቅ ወይም ልብስ አልተመኘሁም፤”
ሐዋርያት 20፥33


ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
👍41
.       ──•◈•─────•◈•─
                          የዕለቱ ጥቅስ
        ──•◈•─────•◈•─
“ያን መንፈስም፥ በጸጋው ጸድቀን በዘላለም ሕይወት ተስፋ ወራሾች እንድንሆን፥ በመድኃኒታችን በኢየሱስ ክርስቶስ በእኛ ላይ አትርፎ አፈሰሰው።”
ቲቶ 3፥6-7



ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
8
ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
ጰራቅሊጦስ.pdf
2.1 MB
👉ርዕስ፦ ጰርቅሊጦስ
መንፈስ ቅዱስና ሥራው
✍️ጸሐፊ፦ ሰይፉ ከበደ
📑የገጽ ብዛት፦ 181


ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
7👍2👏1
.       ──•◈•─────•◈•─
                          የዕለቱ ጥቅስ
        ──•◈•─────•◈•─
“አምላክህን መፍራትህ መጽናናትህ፥ የቅንነትህም መንገድ ተስፋህ አይደለምን?”
ኢዮብ 4፥6



ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
🔥53